cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Comfort Home Care Service

Enables patients to stay in their homes by monitoring and recording patient condition, providing support and administering medications. Phone: +251912969713 Email: [email protected] Website: https://comforthealthservice.com

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
214
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
-230 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Repost from Hakim
የስኳር ህመም ህክምና የስኳር ህመም እንድት እናክማለን !? ሀ/ የስኳር ህመም ያለበት ሰው ማድረግ ያለብት ጥንቃቄዎች እና ጉዳዮች:- 1) ጤናማ አመጋገብ - በየእለቱ በተመሳሳይና መደበኛ በሆነ ሰዓት መመገብ፣ - አትክልት ቅጠላቅጠልና ፍራፍሬ ማዘውተር፣ - ጣፋጭ፣ ቅባትና ስብ የበዛብት ምግብ መቀነስ፣ ማሳሰቢያ:- ለእርስዎ የሚስማማዎትን አመጋገብ የበለጠ ለመረዳት ሐኪምዎን ያማክሩ። በተለይም ደግሞ ከስኳር ህመም ውጭ ሌላ ተጓዳኝ ችግር ካለብዎ፣ ለምሳሌ:- ደም ግፊት፣ የልብ ህመም፣ የሪህ በሽታና የጉበት ችግር ካለብዎ በአመጋገብ ላይ መውሰድ ስላለብዎት ተጨማሪ ጥንቃቄ ሐኪምዎን ያማክሩ። 2) የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ - በየእለቱ ቢያንስ ለ 30 ደቂቃ ፈጠን ያለ እርምጃ የእግር ጉዞ ማድረግ 3) ለእግር ተገቢዉን ጥንቃቄና እንክብካቤ ማድረግ - በየእለቱ የእግርን ዙሪያ ገባውን ማየት፣ የማይታየን የእግር ክፍል ካለ መስታወት መጠቀም፣ - ፈፅሞ በባዶ እግር አለመሄድ፣ -ከታጠቡ በኋላ የጣቶችን መሃል ጨምሮ እግርን በፎጣ ማድረግ፣ - የእግር ጉዳት ወይም ችግር ካጋጠምው ወዳውኑ ወደ ህክምና መሄድ፣ 4)/ሲጋራ ፈፅሞ አለማጨስ 5) ክብደትን መከታተል - የሰውነት ክብደትዎ ያለ ማቋረት የሚቀንስ ወይም በጣም የሚጨምር ከሆነ ሐኪምዎን ማናገር 6) የአፍንና የጥርስን ጤንነት መጠበቅ - ከምግብ በኋላ አፍን መጉመጥመጥ፣ - ጥርስን ቢያንስ በቀን ሁለት ጊዜ ማፅዳት 7/ በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን መረዳት - በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን በየግዜው መከታተል፣ - አማካኝ የሶስት ወራት የስኳር ዉጤት ምርመራ ማድረግ - ቢያንስ በአመት አንድ ጊዜ:- - የአይን፣ የኩላሊት፣ የነርቭ፣ የልብ፣ የደም ቅባት (ኮሌስትሮል) ምርመራ እንዳስፈላጊነቱ ሐኪምዎት በሚያዘው መሰረት ማድረግ ለ/ የስኳር ህመም እንክብሎችን መውሰድ - ሁለተኛው እይነት የስኳር ህመም ታካሚ ከሆኑ በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ለመቆጣጠር በሐኪም የታዘዘልዎትን እንክብል መድሃኒት ይዉሰዱ። - ብዙ የስኳር ህመም እንክብል አማራጮች ሲኖሩ ሐኪምዎት ለእርስዎ የሚስማማዎትን መድሃኒት ለመምረጥ ተጓዳኝ ችግሮችን ውይም ህመሞችን መሰረት ሊያደርግ ይችላል። ሐ/ ኢንሱሊን በተገቢው ሰዓትና ሁኔታ መውሰድ - በዋናነት አንደኛው የስኳር ህመም አይነት ካለብዎ ሐኪምዎ ኢንሱሊን ሊያዝልወት ግድ ይላል። ምክንያቱም በዚህኛው የስኳር ህመም እይነት ቆሽት ምንም አይነት ኢንሱሊን ስለማያመነጭ የሰውነታችኝ ህዋሳት በር ተከፍቶ ስኳር (Glucose) እንዲቀበሉና ከዚያም ስኳርን አቃጥለው ሃይል (ጉልበት) እንዲፈጠር የሚያደርግ ንጥረ- ቅመም (ኢንሱሊን) ግደታ ከውጭ በመርፌ መውሰድ ያስፈልጋል። ይህም ሲሆን ደማችን ውስጥ ያለው የስኳር መጠን እንዲቀንስ፣ እንዲስተካከልና ህዋሳቶቻችን በቂ ስኳር እንዲያገኙ ያደርጋል። - ኢንሱሊን አንድ አንድ ጊዜም ለሁለተኛው አይነት የስኳር ህመም ሊታዘዝ ይችላል። የስኳርን ህመም መረዳትና መገንዘብ የስኳርን ህመም ምንነት፣ የአጭርና የረዥም ጊዜ የስኳር ህመም ጉዳቶች፣ የደም ውስጥ የስኳር መጠን መጨመርና መቀነስ ምልክቶች፣ መድሃኒትን ሐኪም ባዘዘው መሰረት በአግባቡ መውሰድ የሚያመጣው ጥቅም፣ እንድሁም የስኳር መድሃኒቶችን ባህሪ ማወቅ ከሐኪምዎት ጋር ያለወትን መግባባት በእጅጉ በመጨመር ውጤታማ የሆነ የስኳር ቁጥጥር እንዲኖር ከማስቻሉም በተጨማሪ፣ የስኳር ህመም የሚያመጣውን ጉዳት መከላከልና መቆጣጠር ያስችላል። Source : eda/ ዶ/ር ሙሃመድ ዩሱፍ ( MD, Internist ) @HakimEthio
Mostrar todo...
👍 1
Repost from Hakim
ዛሬ ስለ እውቁ የሙዚቃ ባለሙያ ቦብ ማርሌ (Bob Marley) ለህልፈት የዳረገውን በሽታ ስለ ሜላኖማ ላጋራቹ አብዛኞቻችን የምናደንቀው ታዋቂው የሬጌ ሙዚቀኛ ገና በአፍላነት እድሜ በ1981 አመተምህረት በ36 አመቱ ሜላኖማ በሚባል በቆዳ ካነሰር በሽታ ምክንያት ነው። ይህ ችግር ጥቁር ቀለም ያለው ከእግሩ ጥፍር ስር ኳስ ሲጫወት በጉዳት ምክንያት ነበር የተከሰተበት። ቦብ ይህ ችግር ለከፋ ነገር ይጥለኛል ብሎም አላሰበም ነበር። በስተመጨረሻም ከጊዚያቶች በዃላ የጤናው ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ከደረሰ በዃላ ሲመረመር Acral lentiginious melanoma የሚባል የቆዳ ካንሰር ሆኖ ወደ ተለያየ የሰውነቱ ክፍል ተሰራጭቶ ነገኘ። ህይወቱም በአጭሩ ተቀጨ። የቆዳ ካንሰር ምንድን ነው? -አንድ የተለመደ አባባል አለ። ጠይም ወይም ጥቁር ሰው ጥቁር ቆዳ ቀለም ያለው ሰው የቆዳ ካንሰር ሊይዘው አይችልም ወይም ከፀሀይ ብርሀን ራስን መጠበቅ አያስፈልግም የሚል አመለካከት አለ። ይህ ፍፁም ስህተት ነው። ይህ አስተሳሰብ የመጣው ጥቁር ቆዳ ያላቸው ሰዎች ብዙ ሜላኒን አለን ስለዚህ ተጋላጭ አደለንም ተብሎ ስለሚታሰብ ነው። ሜላኒን ከፀሀይ ብርሀን ቢጠብቅም 100% ይከላከላል ማለት አይደለም። - የቆዳ ካንሰር ማለት ቆዳችን ላይ የሚገኙት ፣የሴሎቻችን ደህንነት በሚቆጣጠሩ የዘረመል (genetics) ለውጥ የሚመጣ በሽታ ነው። በዚህ ጊዜ እነዚህ ህዋሳት ባልተለመደ ሁኔታ ይከፋፈሉና ያድጋሉ። ከዚያም ቁጥጥር በሌለዉ መንገድ ይራባሉ ከጊዜ በዃላም በአንድ ላይ የተሰበሰቡ የተናጉ ሴሎች እብጠትን ፣ አጢን (tumor) ይፈጥራሉ። -ዋና ዋና የምንላቸው የቆዳ ካንሰር basal cell carcinoma, squamous cell carcinoma እና melanoma ናቸው። -የቆዳ ካንሰር በተለያየ ቀለም እና ቅረፆች ሊከሰቱ ይችላሉ። በአብዛኛው የቆዳ ካንሰር ምልክቶች ሳይስተዋሉ ይቀራሉ። ለቆዳ ካንሰር አጋላጭ ምክንያቶች ምንድን ናቸው? -ነጭ ወይም ቀላ ያለ የቆዳ ቀለም ያላቸው ሰዎች -ጥቁር ነጥብ (በተለምዶ የማርያም ስሞሽ) -ከፍ ያለ እብጠቶች ወይም ሞል -የተከፈተ ቁስል -እድሜ እየገፋ ሲሄድ -ለረጅም ጊዜ ለፀሀይ ብርሀን ተጋላጭ መሆን -በቤተሰብ ወይ የግል የቆዳ ካንሰር ታሪክ ያላቸው -ለረጅም ጊዜ ለx-ray ተጋላጭ መሆን -ደካማ የበሽታ የመከላከል አቅም ሲኖር። ሜላኖማ (melanoma) ምንድን ነው? -ከቆዳ ካንሰር አይነቶች ውስጥ በጣም አደገኛ እና በፍጥነት ከሚዛመቱት ውስጥ ስለ ሜላኖማ ስናስብ ፣ ምንም እንኳን ከሌሎቹ የቆዳ ካንሰር የመከሰት እድሉ አነስ ቢልም ከሌሎቹ በበለጠ ለሞት የሚያደርስ፣ እና አደገኛው የሚባለው የቆዳ ካንሰር አይነት ሲሆን ወደ ሌላው የሰውነታችን ክፍል የመሰራጨት እድሉ ከፍተኛ ነው። -መጀመሪያ በቆዳችን ላይ ሜላኖሳይት የሚባሉ ህዋሳት ሜላኒን የምንለውን በሰውነት ውስጥ የቆዳ፣ የፀጉር እና የቆዳ ቀለም የሚያመርት ንጥረነገር ያመርታሉ። ይህ ንጥረ ነገር በተፈጥሮ የሚገኝ ፀሀይ ብርሀን መከላከያ ነው። በተለይም በአልትራቫዮሌት ጉዳት ምክንያት የሚመጡ ጉዳቶችን ይከላከላል። ይህ ማለት ግን ሙሉ ለሙሉ ይከላከላል ማለት አይደለም። ስለዚህ ማላኖማ የሚከሰተው ሜላኖሳይቶች በተለያዩ ምክንያቶን ያለ አግባብ ሲያድጉ እና ሲጎዱ ነው። -ይህ ችግር በብዛት ደረት፣ ጀርባ፣ አንገት፣ እና ፊት ላይ ይስተዋላል። ከዚህ በተጨማሪ የእጅ መዳፍ፣አይን ሊይ፣ የውስጥ እግር ፣እና ጥፍር ስር ይታያል። -አጠቃላይ ስናየው ሜላኖማ በብዛት ወንዶች ላይ ይስተዋላል ነገር ግን ከ50 አመት እድሜ በታች ላይ ደግሞ በብዛት ሴቶች ላይ ይስተዋላል። ***Acral lentiginious melanoma የምንለው የሜላኖማ አይነት ደግሞ የውሰጥ እግር ወይም መርገጫችንን እና መዳፋችን ላይ የሚከሰት ችግር ነው። "Acral" የተባለበትም ምክንያት እጅ እና እግር ላይ ስለሚከሰት ነው። ከሌሎች ሜላኖማ አይነት የሚለየው በፀሀይ ብርሀን ብዛት ሳይሆን የዘረመል ለውጥ(genetic mutation) ነው ተብሎ ይታሰባል። ሜላኖማ ማን ላይ ይከሰታል? -ሜላኖማ በሁለቱም ፆታ እና በማንኛውም የእድሜ ክልል ሊከሰት ይችላል። ወደ ሌላው የሰውነታችን ክፍል ውስጥ ይሰራጭ ይሆን? - ሜላኖማ በቶሎ ካልታከመ ወደ ሌላው የሰውነት ክፍል ለምሳሌ ወደ አቅራቢያ የሚገኝ ፍርንትት (lymph node) ፣ ወደ ሳንባ ፣ጉበት፣ አጥንት፣ አእምሮ የመሰራጨት እድሉ ከፍተኛ ነው። ምልክቶቹስ ምንድን ናቸው? -በቀላሉ ምልክቶቹን ለመረዳት ቆዳ ላይ የወጣው ሞል ቅርፁ የተለያየ ወይም ወጥ ካልሆነ (irregular) ከሆነ፣ ጠርዛቸው ወይም (ጫፋቸው) የተለያየ ከሆነ ፣ቀለሙ የተለያየ አይነት ከሆነ፣ ከአተር ፍሬ ከፍ ያሉ ከሆኑ፣እና በሳምንታት ወይም በወራት ውስጥ ተቀያያሪ ፀባይ ካላቸው። -በቆዳ ላይ ጠቆር ጠቆር ያሉ ብዛት ያላቸው ሞሎች፣ ጠቃጠቆዎች፣ እንደ ቡናማ እና ጠቆር ጠቆር ያሉ እና እድገት ያለው ነው። ተጋላጭነታችንን እንዴት መቀነስ እንችላለን? -ብዙዎቻችን ፀሀይ መመቆን ልምድ አርገናል። የፀሀይ ብርሀን በመጠኑ ሲሆን ቫይታሚን D በሰውነታችን እንዲመረት ይረዳል ነገር ግን መዘንጋት የሌለብን ነገር የፀሀይ ጨረር ከፍተኛ በሚሆንበት ሰአት ራሳችንን መጠበቅ፣ ቆዳችንን መሸፈን ፣ባረኔጣዎችን እና ጥላ መመጠቀም፣ የፀሐይ መከላከያ (ሰን ስክሪን) በሀኪም ትእዛዝ መጠቀም ፣በየጊዜው ቆዳችን ላይ ለውጥ እያሳየ ያለ ጥቁር ነጥብ ሲኖር በቆዳ ስፔሻሊስት መታየት ተገቢ ነው። -ቆዳችንን ስናይ ሙሉ በሙሉ የሰውነታችን ክፍል መሆን ይጠበቅበታል። በተለይ ጠየም ያለ ወይም ጠቆር ያለ የቆዳ ቀለም ያላቸው ሰዎች የውስጥ እግራቸውን፣ መዳፍን እና ጥፍራቸውን መመልከትን መርሳት የለባቸውም። -በጣም ወሳኙ ነገር ማህበረሰቡን ማስተማር በተለይ ወላጆችን ስለ ምልከቶቹ ፣ አጋላጭ ምክንያቶቹ እንዲሁም ምልክቶቹ ማስተማር ይጠበቅብናል። የህክምና አማራጮቹስ? -እንደየደረጃቸው የህክምና አማራጮቹም ይለያያሉ። -ዋነኛው የህክምና አማራጭ ቀዶ ጥገና ሲሆን ይህም በተለይ በመጀመሪያዎቹ ደረጃዎች ላይ ካንሰሩን እና የተወሰነ በዙሪያው ያለውን የቆዳ ክፍል ማስወገድን ያካትታል።ሌሎች የህክምና አማራጮች ለምሳሌ ሊምፍአዲኔክቶሚ (lymphadenectomy)፣ ሜታስታቴክቶሚ (metastasectomy)፣ የጨረር ህክምና (radiation theraphy)፣ ኢሚዩንቴራፒ (immunetherapy) እና ኬሞቴራፒ (Chemotherapy) ያካትታል። ከህክምናው በዃላም የሀኪም ክትትል ማድረግ አስፈላጊ ነው። ጤና ይብዛላቹ ዶ/ር ኤርሚያስ ማሞ @HakimEthio
Mostrar todo...
Repost from Hakim
የደም ስር መዘጋት እና “ጋንግሪን” o በሰውነታችን ውስጥ የተጣራ ደም ከልብ ወደ ልዩ ልዩ የሰውነት ክፍሎች የሚያሰራጩ "ደም ቀጂ /አከፋፋይ " ደም ስሮች(arteries) እና ጥቅም ላይ የዋለ ደምን ይጣራ ዘንድ ወደ ሳንባ እና ልብ የሚመልሱ "ደም-መልስ" ደም ስሮች(veins) ይገኛሉ። o ዋና ዋና ደም አከፋፋይ የደም ስሮች (arteries) ሲዘጉ ፤ በደም ስሩ ምግብና ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች ያገኝ የነበረው የሰውነት ክፍል (እጅ፣እግር፣አንጀት ወዘተ...) ሊሞት ይችላል፤ ይሄኔ "ጋንግሪን/gangrene" ሆነ ይባላል። o በእርግጥ እንደተዘጋው የደም ስር አይነት እና ቦታ ታካሚዎች በ“ስትሮክ”፣ ልብ ድካም፣ በአንጀት መዘጋት ወይም በሌሎች ምልክቶች ወደ ህክምና ተቋም ሊመጡ ይችላሉ። o የዚህ ፅሁፍ ዓላማ በተለይ በእጅና፡ እግር ላይ የሚከሰት አጣዳፊ የደም ስር መዘጋት በሽታ ምልክቶች እና ህክምናን በተመለከተ በወፍ በረር ለማስተዋወቅ ነው። o የደም ስሮች በልዩ ልዩ ምክንያት ፤በአጣዳፊነት ወይም ቀስ በቀስ ሊዘጉ ይችላሉ። ከአጣዳፊ ምክንያቶች መካከል : በድንገተኛ አደጋ(በመኪና፣ በጥይት ፣በጩቤ፣በማሽን አደጋ ወዘተ...) ፣በደም መርጋት ፣ከልብ በሚበተን የረጋ ደም(embolus)፤ ተጠቃሽ ናቸው። ይህንን በመሰለው ችግር ምክንያት የሚመጣ የደም ስር መዘጋት ፣ በአብዛኛው ፋታ የማይሰጥ ነው ። በመሆኑም በአስቸኳይ የደም ስር ህክምና/ቀዶ ህክምና ካልተደረገ በሰዓታት ውስጥ ደም ያጠረው የሰውነት አካል(እጅ፣እግር፣አንጀት ወዘተ...) ወደ መሞት("ጋንግሪን") ሊያመራ ይችላል ። o ቀስ በቀስ የሚከሰት የደም ስር መጥበብ ቀድሞ የነበራቸው ታካሚዎች ሲሆኑ ከአጣዳፊው ክስተት በፊት ሌሎች ምልክቶች ይኖራቸዋል።ለምሳሌ በሚራመዱበት ጊዜ እግር ህመም (በአብዛኛው ባት እና ታፋ ላይ ) ይሰማል፣ ቆዳ ይደርቃል፣ ጥፍሮች ይጠነክራሉ፣ ወዘተ …። ችግሩ እየተባባሰ ሄዶ አስከፊ ደረጃ ላይ ሲደርስ ያለምንም እንቅስቃሴ በተለይም በመኝታ ግዜ የእግር መርገጫ ና ጣቶችን ማቃጠል፣መቁሰልና መሰል ችግሮች ይኖራሉ። አጣዳፊ የደም ስር መዘጋት ምልክቶች የእጅ/እግር ደም ስሮች መዘጋት ልዩ ልዩ ምልክቶች ሊያሳይ ይችላል፡ ከነዚህም መካከል : o የጣቶች ህመም/ማቃጠል፣ መደንዘዝ ፣ ውሃ መቋጠር o ጣቶች፣እግርን/ እጅን ማዘዝ (ማንቀሳቀስ) አለመቻል o የእጅ እና እግር መጥቆር እና ፈሳሽ ማምጣት ሊሆን ይችላል o የእግር የደም ስሮች ሆድ ውስጥ ካለው ትልቀ የደም ስር(aorta)ጀምሮ ድንገት ሲዘጉ የሁለቱም እግሮች አለመታዘዝ ሊያጋጥም ይችላል :: ህክምናው እንዴት ነው? · የደም ስር በአጣዳፊነት ተዘግቶ ባለበት ሁኔታ የምትጠፋ እያንዳንዷ ሰዓት የእጅና የእግርን የመትረፍ ዕድል እያመነመነው ይሄዳል(ህክምና ቢሰጥ እንኳ)። አልፎ ተርፎም በህይወትም ላይ ጭምር አደጋ ሊያመጣ ይችላል። · ታካሚዎች በጊዜ ወደ ህክምና ተቋም ከመጡ - እንደበሽታው መንስኤ የተለያዩ አካል ማዳንን ታሳቢ ያደርጉ ህክምናዎች ሊሠጡ ይችላል: · መድሃኒት በመስጠት (ደም ማቅጠኛዎችን ጨምሮ እንደ ስኳርና የደም ብዛት ላሉ ሌሎች ተጓዳኝ በሽታዎች)፣ እንዲሁም · በቀዶ ህክምና o የረጋ ደምን መጥረግ(thromoboembolectomy)፣ o ከአጣዳፊው የደም ስር መዘጋት/ደም መርጋት በፊት የነበረ(የከረመ)ለአጭር ርቀት የተዘጋ/የጠበበ ደም ስርን መጠገን/መለጠፍ(endarterectomy) ሊደርግ ይችላል። o ከአጣዳፊው የደም ስር መዘጋት/ደም መርጋት በፊት የነበረ(የከረመ)ረጅም የሆነ የደምስር መጥበብ ወይም መዘጋት) በሚኖርበት ጊዜ አማራጭ ደም ስር በመንቀል ቅያሪ የደም ስር (bypass) ሊሰራ ይችላል። o በአደጋ ምክንያት የተከሰተ የደምስር ጉዳት ሲሆን ደግሞ እንደ ጉዳቱ መጠን ቀጥታ በመስፈት(primary repair)፣ በሌላ ደም ስር መለወጥ(interposition graft) ጨምሮ ሌሎች ቀዶ ህክምናዎች መስጠት ይቻላል። · በአደጉ አገራት ቀዶ ህክምና ሳያስፈልግ በቆዳ በኩል ወደ ተዘጋው ደም ስር ቱቦዎችን በማስገባት ደም ስር የመክፈት ህክምና (endovascular therapy ) በስፋት ይሰጣል። ከነዚህም መካከል የረጋ ደምን ማቅለጥ(thrombolysis) እና መጥረግ (Mechanical / Aspiration thrombectomy) እና ሌሎች መንገዶች ይገኙበታል። ነገር ግን እነዚህ ህክምናዎች ዋጋቸው እጅግ ከፍተኛ ስለሆነ ለብዙዎቹ የሀገራችን ታካሚዎች የሚቀርቡ አይደሉም ። የእጅ/ እግር መቆረጥ(“Amputation”) ህሙማን እጃቸው/ እግራችው ከሞተ በኋላ ከመጡ፣ ወይንም አካልን የማዳን ህክምና በልዩ ልዩ ምክንያት ሳይሳካ ቢቀር የሰውነት አካልን(የእጅ፣ እግር፣ጣቶች) በቀዶ ህክምና ማስወገድ ህይወት ለማዳን አስፈላጊ ይሆናል። አንዳንድ ጊዜ ምንም እንኳን ጣቶችን ወይም ከዛ በላይ አካልን ማስወገድ ግዴታ ቢሆንም የቀረውን የእጅ/እግር ለማዳን ተጨማሪ የደም ስር ህክምና ሊያስፈልግ ይችላል። በመሆኑም የደም ስር ሐኪም በሚገኝበት ተቋም ሌሎች ባለሙያዎች እጅ እና እግር ከመቁረጥ ውሳኔ በፊት የደም ስር ቀዶ ሐኪም እንዲያማክሩ እናበረታታለን። በተለይ በሽታው በተጠረጠረ ሰዓት:(ጊዜ ሳያጠፉ) ህሙማንን ህክምናው ወደሚሰጥባቸው ሆስፒታሎች በፍጥነት ማስተላለፍ ያስፈልጋል ። Time is Limb; Time is Life! ዶ/ር ፈርዖን እባላለሁ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጠቅላላ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ና የደም ስር ቀዶ ህክምና ሰብ ስፔሻሊስስት ሐኪም ነኝ። የደም ስር ቀዶ ህክምና መወያያ ግሩፕ https://t.me/vascularsurgery_Ethiopia ከፍቻለው የዚህ መድረክ አላማ:- 1. ከፍተኛ የደም ስር ህክምና ለሚፈልጉ ታካሚዎች ና ማማከር ለሚፈልጉ የጤና ባለሙያዎች ተደራሽ መሆን እንዲሁም፣ 2.ከደም ስር ጋር በተያያዘ ስለሚነሱ በሽታዎች ለጤና ባለሙያዎች፣ ለታካሚዎች ና ለማህበረሰቡ መሠረታዊ መረጃዎችን መስጠት ነዉ። መድረኩን ይጎብኙ ፤ እባክዎ ሌሎችም እንዲቀላቀሉ add በማድረግ ና invitation በመላክ ይተባበሩ። @HakimEthio
Mostrar todo...
Repost from Hakim
Photo unavailableShow in Telegram
የወጣቶችን ጤና እያመሳቀለ ያለው መድሐኒት : ትራማዶል ትራማዶል የሚባለው የህመም ማጥፊያ መድሐኒት ያለ አግባብ በወጣቶች ኪስ ተዘውትሯል። ከስምንተኛ እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች በዚህ መድሐኒት ሱስ ተለክፈዋል። መድሐኒቱ ያለ በቂ ምክንያት እና ተዘውትሮ ሲወሰድ ወደ ሱስነት ይሸጋገራል። አንድ የገጠመኝ ተማሪ በቀን 26 ትራማዶል ክኒን መውሰድ ደረጃ የደረሰ ነበር። በቀን 26 ማለት ለመውሰድ ቀርቶ ለመቁጠር የሚታክት ነው። ሱስ የማያደርገው የለምና እያደረገ ቆይቷል። ከዚህ ደረጃ የደረሰው በአንድ ቀን አልነበረም። በቀን አንድ ተጀምሮ ቀስ በቀስ መላመድ ስላለው የሚፈለገው የሱስ ቃና ስለማያስገኝ መጠኑን እንዲጨምር በሱስ ትዕዛዝ ሁለት፣ አራት፣ ስድስት፣.....እያለ ሀያ ስድስት ክኒን ላይ ደርሷል። የትራማዶል ሱስ በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ የሚገኝ አደገኛ የስነ አእምሮ ችግር ነው። ከመድሐኒት ጋር ተያይዞ የሚመጣ የስነ አእምሮ ችግር የማይነካው ማዕዘን የለም። የግለሰብ ፣የቤተሰብና የማህበረሰብ ጤና፤ ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ መስተጋብሮችን አደጋ ላይ ይጥላል። ትራማዶል ከድንገተኛ መሞት እስከ ቀጣይነት ያላቸው የጤና እክሎች ያስከትላል። በአንድ ግዜ በብዛት ከተወሰደ ለሞት ይዳርጋል። የአንጎል ንዝረት፣የኩላሊት መድከም/መባባስ፣ ለጡንቻ መቅለጥ እና ለከፋ የስነ ልቦና ችግር የሚዳርግ ነው። ችግሩ ትኩረት የተሰጠው አይደለም። ምንም እንኳ በጤና ጥበቃ በኩል መድሐኒቱን ያለ ልዩ ማዘዧ እንዳይታዘዝ የሚል መመሪያ ቢነገርም ተፈፃሚነቱ ላይ ግን አጠያያቂ ነው። ከዚያ ባሻገር ሰፊ የግንዛቤ መድረክ ፈጥሮ የችግሩን አሳሳቢነትና አስከፊነት ማሳወቅ ተገቢ ነው። ትኩረት ይሰጠው። ኪኒኑን በመውሰድ ሱሳቸውን ማብረድ ሲሳናቸው በመርፌ መውሰድ ይጀምራሉ። ከዚህ ደረጃ ተደረሰ ማለት በችግር ላይ ሰፊ ችግር ተባዝቶ ለልብና አንጎል የጤና እክል ለሚዳርግ መጥፎ ሁኔታ ይዳርጋል። የልብ በር ኢንፌክሺን በመፍጠር ለእስትሮክ ይዳርጋል። እስትሮክ ወጣቶች ላይ ከሚከሰትባቸው መንስኤዎች አንዱ በደም ስር የሱስ መድሐኒት መውሰድ ጋር የተያያዘ ነው። ትራማዶልና መሰል የሱስ አምጪ መድሐኒቶችን በመርፌ መውሰድ ለእስትሮክ ያጋልጣሉ። ሱስ ሁሉን አቀፍ የጋራ ትብብርና ቅንጅት የሚፈልግ የአእምሮ ጤና እክል ነው። ዶ/ር መስፍን በኃይሉ @HakimEthio
Mostrar todo...
Repost from Hakim
Photo unavailableShow in Telegram
በአጠቃላይ የጥርስ ብሩሽዎን በየሶስት እስከ አራት ወር እንዲቀይሩ ይመከራል። ከጊዜ በኋላ በብሩሹ ላይ ያለው ጥርስ ሊዳከም ስለሚችል በጥርስ እና በድድ ላይ ያለን ቆሻሻ ለማስወገድ ውጤታማነታቸውን ይቀንሳል። ብሩሽን አዘውትሮ መተካት ጥርስዎን በብቃት ለማጽዳት እና የአፍ ንፅህናን ለመጠበቅ ይረዳል። በተጨማሪም ፣ ያረጀ የጥርስ ብሩሽ ባክቴሪያን ይይዛል ፣ እና አዘውትሮ መተካት የባክቴሪያዎችን አደጋ ለመቀነስ ይረዳል ። FaceBook - https://www.facebook.com/smilesdentalcenter Instagram - https://www.instagram.com/smile_designer__ethiopian/ Telegram - https://t.me/+POOhvXmULsQ4ODQ0 Tiktok - https://www.tiktok.com/@smilespecialtydental
Mostrar todo...
Repost from Hakim
የዓለም የውፍረት ቀን (March 4-2024) የዘንድሮው የዓለም የውፍረት ቀን ''ስለውፍረት እናውራ.....'' በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ነው። የዓለም ውፍረት ቀን በየአመቱ March 4 እ.ኤ.አ ይካሄዳል። ከመጠን ያለፈ ውፍረት እውነታዎች 👉እ.ኤ.አ. በ 2022 በዓለም ላይ ከ8 ሰዎች አንዱ ከመጠን በላይ ውፍረት (obesity) ይኖሩ ነበር። 👉ከ1990 ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአዋቂዎች ከመጣን በላይ ውፍረት ከእጥፍ በላይ ጨምሯል፣ እና የጉርምስና ጊዜ ከመጠን በላይ ውፍረት በአራት እጥፍ ጨምሯል። 👉በ 2022 2.5 ቢሊዮን ጎልማሶች (18 ዓመት እና ከዚያ በላይ) ከመጠን በላይ ወፍራም ነበሩ። ከእነዚህ ውስጥ 890 ሚሊዮን የሚሆኑት በጣም ከመጠን ያለፈ ውፍረት ይኖሩ ነበር። 👉እ.ኤ.አ. በ 2022 ዕድሜያቸው 18 እና ከዚያ በላይ ከሆናቸው ጎልማሶች 43% ውፍረት አለባቸው 16% የሚሆኑት ደግሞ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ይኖሩ ነበር። 👉እ.ኤ.አ. በ 2035 በዓለም ዙሪያ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ጋር የሚኖሩ ሰዎች ቁጥር 1.9 ቢሊዮን እንደሚሆን ይጠበቃል ። 👉እ.ኤ.አ. በ2035 ከ4 ሰው አንዱ ከ መጠን ያለፈ ውፍረት ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል። የአለም ጤና ድርጅት ውፍረትን (overweight) እና ከመጠን ያለፈ ውፍረት (obesity) እንደሚከተለው ይገልፃል። 👉 ውፍረት የሚባለው BMI ከ 25 እና ከዚያ በላይ ሲሆን 👉 ከመጠን በላይ ውፍረት ደግሞ BMI ከ 30 እና ከዚያ በላይ ሲሆን ነው። # ውፍረትን እንዴት መከላከል እና ማከም ይቻላል? በግለሰብ ደረጃ 👉በእርግዝና ወቅት ተገቢውን የክብደት መጨመር ማረጋገጥ። 👉ከወለዱ በኋላ ባሉት 6 ወራት ውስጥ ጡት ብቻ ማጥባትን ይለማመዱ እና እስከ 24 ወር ወይም ከዚያ በላይ ጡት ማጥባትዎን ይቀጥሉ። 👉የወቅቱ የክብደት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን በጤናማ አመጋገብ፣ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ እና በጥሩ እንቅልፍ ዙሪያ ያሉ ባህሪያትን መደገፍ። 👉የስክሪን (ስልክ እና ሌሎች) ጊዜን ይገድቡ። 👉 ስኳር ፣ ጣፋጭ መጠጦችን እና ስብ የበዛበት ምግብ መገደብ እና ሌሎች ጤናማ የአመጋገብ ባህሪያትን መከተል። 👉ተገቢ የሆነ የእንቅልፍ ቆይታ እና ጥራት ያስፈልጋል። ትንባሆን እና አልኮልን ያስወግዱ። 👉ፍራፍሬ እና አትክልት ፍጆታ እንዲሁም ጥራጥሬዎች፣ እህሎች እና ከእፅዋት የሚገኝ ስብ ፍጆታ መጨመር። 👉መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ። 👉ውፍረት የተለያዩ የህክምና አማራጮች እንዳሉት አውቆ የህክምና ባለሙያን ማማከር በህክምና ቦታ የሚሰጡ አገልግሎቶች 👉 ወደ ጤና ተቋማት የሚመጡ ሰዎችን ክብደት እና ቁመት (BMI) መለካት 👉ስለ ጤናማ አመጋገብ እና የአኗኗር ዘይቤዎች ምክር መስጠት; 👉 ከመጠን ያለፈ ውፍረት ምርመራ በሚታወቅበት ጊዜ ደግሞ የተቀናጀ ውፍረት መከላከል እና ህክምና መስጠት። ጤናማ አመጋገብን ማጠናከር ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣በመድሀኒት እንዲሁም የቀዶ ጥገና ህክምናን ጨምሮ ሊሰጥ ይችላል። 👉ሌሎች ተጓዳኝ ህመሞችን(የስኳር፣ የኮሌስትሮል እና የደም ግፊት እና የአእምሮ ጤና መታወክን ጨምሮ መከታተል። ዶ/ር ክብረት እንየው (Endocrinology and metabolism fellow) @HakimEthio
Mostrar todo...
Repost from Hakim
ፎሮፎር | Seborrheic dermatitis ✔️ፎሮፎር ምንድነው? ፎሮፎር እየተመላለሰ ለረዥም ጊዜ የሚቆይ ከሰው ወደ ሰው የማይተላለፍ የቆዳ ህመም አይነት ነው። ፎሮፎር በባህሪው ጠንካራ ያልሆነ ብዙም ምልክት የሌለው እና ትንንሽ ብናኞች ያሉት ሊሆን ይችላል፤ይህ የተለመደው አይነት ፎሮፎር ሲሆን ዳንድረፍ (dandruff) በመባል ይታወቃል። በተቃራኒው ደግሞ ጠንካራ የሚባለው የፎረፎር አይነት አብዛኛውን የራስ ቆዳችንን እንዲሁም ሌሎች የአካል ክፍሎቻችን ላይ ጭምር ሊከሰት ይችላል፤ ቅርፊቶቹም ወፍራም እና ከራስ ቆዳችን ጋር የተጣበቁ ሊሆኑ ይችላሉ ✔️ ፎሮፎር ምን አይነት ሰዎች ላይ ይከሰታል? - ከሁለት ሳምንት እስከ አንድ አመት ባሉ ህጻናት እና ከጉርምስና እድሜ በላይ በሆኑ ግለሰቦች ላይ ይከሰታል - አብዛኞቹ ፎሮፎር የሚኖርባቸው ግለሰቦች ሌላ ተጓዳኝ ህመም አይኖራቸውም አንዳንድ ጊዜ ግን ከHIV ፣ Parkinson ፣ የሚጥል ህመም (Epilepsy) ፣ ጭንቀት ገር ተያይዞ ሊከሰት ይችላል ✔️ ፎሮፎር መንስኤው ምንድነው? -የፎሮፎር መንስኤ በትክክል ይሄ ነው ተብሎ መናገር ባይቻልም ከቆዳችን ጋር ተስማምተው በሚኖሩ (normal flora) የፈንገስ አይነት (Malassezia) ምክንያት ይከሰታል ተብሎ ይታሰባል -ፎሮፎር ወዝ አመንጪ እጢዎች (Sebaceous glands) ተከማችተው በሚገኙበት የአካል ክፍሎቻችን (የራስ ቆዳ ፣ ፊት፣ ደረት አካባቢ፣ የላይኛው የጀርባችን ክፍል ፣ የውጭኛው የጆሮ ክፍል ፣ ብብት ፣ ጡት ስር ፣ በላይኛው የጭን ክፍል እና ብልት መሀከል በሚገኘው ቦታ) ላይ ይከሰታል ✔️ ፎሮፎር እንዴት ይታከማል ? - መድሀኒትነት ያላቸው መታጠቢያ ሻምፖዎችን (ketoconazole 2%, Selenium sulfied, Ciclopirox , Zinc pyrithione) በመጠቀም ፎሮፎርን መቆጣጠር ይቻላል። - ሻምፖውን ተቀብተን ከ5-10 ደቂቃ አቆይተን መታጠብ ይህንንም በሳምንት ከ 2-3 ጊዜ መደጋገም ያስፈልጋል - ከዚህ በተጨማሪ የማሳከክ ስሜት ካለው፣ጠንካራ የሚባለው የፎሮፎር አይነት ከሆነ፣ከራስ ቆዳችን ውጪ ከተከሰተ፣ተጓዳኝ ህመሞች ካሉ እንዲሁም ህጻናት ላይ ከተከሰተ የቆዳ ሐኪም በሚያዘው መሰረት ተጨማሪ መድሀኒቶች ያስፈልጋሉ። ✔️ ፎሮፎር ለምን ይመላለሳል? መንስኤው በትክክል ስለማይታወቅ እና ምክንያት ነው ተብሎ የሚታሰበው የፈንገስ አይነት ከቆዳችን ጋር ተስማምቶ የሚኖር በመሆኑ ፎሮፎርን በህክምና ማዳን አይቻልም(not curable) ለዚህም ነው የሚመላለሰው ፤ ነገር ግን ምልክቶቹን መቆጣጠር እና የሚመላለስበትን የጊዜ ፍጥነት መቀነስ ይቻላል ✔️ ፎሮፎር እንዳይመላለስብን ምን እናድርግ? ከላይ በተጠቀሰው መሠረት ምልክቶቹ እስኪጠፉ በሻምፖ መታጠብ ያስፈልጋል(የቆዳ ሐኪሙ ተጨማሪ መድሀኒቶችን ሊያዝ ይችላል)፤ ምልክቶቹ ከጠፉ በኋላ ሻምፖውን በሳምንት አንድ ጊዜ ወይም በሁለት ሳምንት አንድ ጊዜ መጠቀም ፎሮፎር እንዳይመላለስ ይረዳል ✔️ ፎሮፎር ፀጉር እንዲነቃቀል ያደርጋል? በፎሮፎር ምክንያት የፀጉር መነቃቀል የተለመደ አይደለም ነገር ግን ከፍተኛ የሆነ የማሳከክ ስሜት ካለ ጊዜያዊ የሆነና ተመልሶ የሚተካ የፀጉር መነቃቀል ሊያስከትል ይችላል በመጨረሻም የቆዳ ሐኪም ሳያማክሩ መድሀኒቶችን ባለመጠቀም ቆዳዎን ከተጨማሪ ጉዳት ይጠብቁ!! ዶ/ር ዮሐንስ ታደሰ ፤ የቆዳና አባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት @HakimEthio
Mostrar todo...
👍 2
Repost from Hakim
የአፍንጫ ደም መፍሰስ (epistaxis) መንስኤው ምንድን ነው? የተለመዱ የአፍንጫ ደም መንስኤዎች የሚከተሉትን ያካትታል: • አፍንጫ መጎርጎር • ፈጣን የአየር ሙቀት ለውጦች • አለርጂዎች • ሥር የሰደደ ጉንፋን ወይም የ sinus ችግሮች • ኮኬይን መጠቀም • ሄሞፊሊያ ወይም በዘር የሚተላለፍ ሄመሬጂክ telangiectasia • በአፍንጫ ላይ የሚደርስ ጉዳት • እቃዎችን ወደ አፍንጫ ማስገባት • እንደ አስፕሪን፣ ዋርፋሪን (ኮማዲን) ወይም ክሎፒዶግሬል (ፕላቪክስ) ያሉ ደሙን ለማቅጠን ሚረዱ መድሃኒቶችን መውሰድ 👨🏾‍⚕️የአፍንጫ ደም መፍሰስ (epistaxis) ለማስቆም የሚከተሉትን ደረጃዎች ይከተሉ • መረጋጋት እና ከተቻለ መቀመጥ አስፈላጊ የመጀመሪያ እርምጃ ነው። ምክንያቱም የጭንቀት ሆርሞኖች የደም ግፊትን ይጨምራሉ። ይህም የደም መፍሰስን ሊያባብስ ይችላል ። • ወደ ፊት ማዘንበል፡ ትንሽ ወደ ፊት መደገፍ ደሙ ከአፍንጫው እንዲወጣ እና ወደ ታች እንዲንጠባጠብ ያስችለዋል። ጭንቅላትን ከልብ በላይ ያድርጉት። • አፍንጫውን ያጽዱ፣ አፍንጫው ከማንኛውም የውጭ ነገሮች የጸዳ መሆኑን ያረጋግጡ። • አፍንጫውን መቆንጠጥ፡ የአፍንጫውን ለስላሳ ክፍል፣ ከጠንካራው cartilage በታች፣ በአውራ ጣት እና በመረጃ ጠቋሚ ያዙ። ግፊቱን ለ 10-15 ደቂቃዎች ይያዙ በዚህ ጊዜ ውስጥ በአፍ ውስጥ ይተንፍሱ። • መልቀቅ፡ ከ5 ደቂቃ በኋላ አፍንጫውን ይልቀቁ። ደሙ ካልቆመ ለተጨማሪ 5 ደቂቃዎች ቆዩ እና እንደገና ያረጋግጡ። ይህን ሂደት እስከ 20 ደቂቃዎች ድረስ ይቀጥሉ። • እንቅስቃሴን ያስወግዱ፡ አካላዊ ጥረት የደም ግፊትን ሊጨምር እና የደም መፍሰስን ሊያባብስ ይችላል። ይህንን ማስወገድ የአፍንጫ ደም እንዲፈወስ ይረዳል። ዶ/ር አማኑኤል ወ/ገብርኤል: የውስጥ ደዌ ሀኪም @HakimEthio
Mostrar todo...
Repost from Hakim
የሚጥል በሽታ ያለባቸው ሰዎች በሚያንዘፈዝፋቸው ወይም ራሳቸውን በሚስቱ ወቅት ምን ማድረግ እንችላለን? 🔴 #የሚጥል_በሽታ ("#Epilepsy") የሚጥል በሽታ ምንድን ነው? 👉 እንፍርፍሪት ("Seizure") ማለት አዕምሮ ወስጥ የሚከሰት ከመጠን ያለፈ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ሲሆን የባህርይ ለውጥ ወይም ከቁጥጥር ውጭ የሆነ የሰውነት መንዘፍዘፍ ዋና መገለጫው ነው። 👉 የሚጥል በሽታ ("Epilepsy") ማለት ደግሞ ተደጋጋሚ እንፍርፍሪት ሲከሰት የሚመጣ የበሽታ ዓይነት ነው። ነገር ግን በስኳር መውረድ እና በሌሎች ጊዜያዊ ችግሮች የሚመጣ እንፍርፍሪት የሚጥል በሽታ ውስጥ አይካተትም። የሚጥል በሽታ አይነቶች ☑️ አንደኛው ዓይነት መላው ሰውነትን የሚያንዘፈዝፍና ራስን የሚያስት ሲሆን ☑️ ሁለተኛው ዓይነት ደግሞ የተወሰነ የሰውነት ክፍልን የሚያንዘፈዝፍ ሆኖ ራስ መሳት ያለው ወይም የሌለው ነው። የሚጥል በሽታ መንስኤዎች ምን ምን ናቸው? 🔶 በዘር የሚመጣ 🔶 ጭንቅላት ላይ የሚደርስ አደጋ 🔶 ስትሮክ 🔶 የጭንቅላት ኢንፌክሽን 🔶 የአንጎል ዕጢ የሚጥል በሽታ ቀስቃሽ ምክንያቶች 👉 ከፍተኛ የሆነ ስሜታዊነት 👉 ከባድ ስፓርት 👉 ከፍተኛ ድምፅ ወይም ብርሃን 👉 ትኩሳት 👉 የወር አበባ 👉 ዕንቅልፍ ማጣት 👉 ጭንቀት የሚጥል በሽታ ምልክቶች ምንድን ናቸው? 🔘 የሰውነት ማንቀጥቀጥ ወይም መንዘፍዘፍ 🔘 ተከታታይ የእጅና የእግር መወራጨት 🔘 ሲቃ ያለው ድምፅ ማሰማት 🔘 የሰውነት ድርቅ ማለት 🔘 ዓይንን ወደላይ መገልበጥ 🔘 ራስን መሳት 🔘 አረፋ መድፈቅ 🔘 ሽንት ማምለጥ 🔘 ከነቁ በኋላ ግራ መጋባት 🔘 ምላስ መንከስ የሚታዘዙ ምርመራዎች 👉 የተለያዩ የደም ምርመራዎች 👉 አዕምሮ ውስጥ ያለውን የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ መለኪያ ("EEG") 👉 የጭንቅላት "CT Scan" ወይም "MRI" 👉 የአንጎል ወይም የሰረሰር ፈሳሽ ምርመራ የሚጥል በሽታ ህክምና 👉 ምክንያቱን መለየትና ማከም 👉 ፀረ-ኢፕለፕሲ መድሃኒቶች 👉 ከላይ የተዘረዘሩትን ቀስቃሽ ነገሮች ማስወገድ ወይም መታከም 👉 የአዕምሮ ቀዶ ጥገና (በሚከታተል ሃኪም የሚወሰን እና ለጥቂት ህሙማን ብቻ የሚሰጥ) የሚጥል በሽታን እንዴት መቆጣጠር ይቻላል? ✔️በሀኪም የታዘዘን መድሃኒት ሳያቋርጡና በትክክለኛው ሰዓት በመውሰድ። ✔️ በቂ እንቅልፍ በመተኛት ❌ የአልኮል መጠጥ ባለመጠጣት የሚጥል በሽታ ያለባቸው ሰዎች በሚያንዘፈዝፋቸው ወይም ራሳቸውን በሚስቱ ወቅት ምን ማድረግ እንችላለን? ✔️ በጎን በኩል እንዲተኙ ማድረግ። ይህም ጉሮሮ አካባቢ ያለ ፈሳሽ ነገር ወደ አየር ቧንቧ እንዳይገባ ይረዳል። ✔️ በጭንቅላት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ምቾት ያለው ትራስ ማድረግ ✔️ አንገት አካባቢ የታሰረ ማንኛውም ጌጣጌጥ እና ጥብቅ ያለን ልብስ ማላላት። ✔️ ታማሚውን አስጨንቆ አለመያዝ ✔️ አፉን እንዲከፍት አለመታገል ✔️ ያልተለመደ ሁኔታ ሲያጋጥም ወደ ሃኪም ቤት መውሰድ። ❌ ክብሪት ወይም ማንኛውንም አይነት ጭስ አለማሸተት ማስታወሻ፦ 🚫 የሚጥል በሽታ ያለበት ሰው መኪና ባያሽከረክር ይመከራል ወይም የሚከታተልን ሀኪም ማማከር ያስፈልጋል። 🚫 ከእርግዝና በፊት ወይም በእርግዝና ወቅት ከፍተኛ ክትትል ማድረግና መድሃኒት ማስቀየር ያስፈልጋል። 🚫 በሃኪም እስካልተወሰነ ድረስ መድሃኒት ማቋረጥ ፈፅሞ አይመከርም። References 1. The Epilepsy Foundation 2. National Library of Medicine 3. International League Against Epilepsy and the International Bureau for Epilepsy ዶ/ር ጋሻው ሶለላ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት @HakimEthio
Mostrar todo...
Repost from Hakim
በተለምዶ በሀገራችን ሰይጣን ፣ እርኩስ መንፈስ የሰው አይን እየተባለ ስለሚጠራው ፣ በአለም ላይ ከ50 ሚልየን ህዝብ በላይ የሚያጠቃውን በተለምዶ "የሚጥል በሽታ" (Epilepsy ) ተንሽ ነገር ልበላቹ። የሚጥል በሽታ (Epilepsy) የምንለው አንጎልን ከሚያጠቃ የአእምሮ በሽታዎች ፣ተላላፊ ያልሆነ በአለም ላይ ተንሰራፍተው ከሚገኙ በሽታዎች አንዱ እና ዋነኛው ነው። አእምሯችን የነርቭ ሴል ውህድ ሲሆን ከ 100 ቢሊየን በላይ የነርቭ ሴሎች አሉት። እነዚህ የነርቭ ሴሎች አንዱ ከሌላው ጋር እየተናበበ የሚሰራበት የራሱ የሆነ መንገድ (neural network) አለው። እነዚህ የነርቭ ክፍሎች በተለያየ ምክንያት እክል ይገጥማቸዋል። ይህ ሲሆነ የነርቭ ስርአቱ ይዛባል። በዚህ ሰአት በአንጎል ውስጥ በሚገኙ ሴሎች ውስጥ ከመጠን በላይ በሆነ ኤሌክትሪካዊ ንዝረት (electrical discharge) ጊዚያዊ መረበሽ ምክንያት የአእምሮ ትግበራ በድንገት መታወክ ሲኖር ምልክት ለተወሰኑ ደቂቃዎች በሚያሳይ ጊዜ አንድ ሰው ሲዝ አደረገ ፣ (seizure) ተከሰተ እንላለን። - Epliepsy ምክንያቱ ባልታወቀ ቢያንስ በ24 ሰአት ልዩነት ሁለት ወይ ከዚያ በላይ ጊዜ ሲዝ ሲያደርግ እና በአብዛኛው ጊዜ ለአጭር ደቂቃዎች የሚቆይ ነው። አንድ ሰው ሲዝ ሲያደረግ የሚያሳየው ምልክቶችሰ? -አንድ ሰው ሲዝ አደረገ የምንለው ከላይ የተጠቀሱት ሁኔታዎች እንዳሉ ሆነው ፣ የእጅ እና እግር መንዘርዘር ፣ መነቀጥቀጥ ለምሳሌ የፊት ብቻ መነቀጥቀጥ ፣ ወይም የእጅ ብቻ በአንድ በኩል ስሜት ማጣት ፣ የእይታ በአንድ በኩል ብልጭለጭታ ወይም ሽፍን ማለት ፣ አንዳንድ ጊዜ እራስን መሳት፣ የአይነ መገለባበጥ ፣ ምራቅ በአፍ መፍሰስ ሊኖር ይችላል ማንን ያጠቃል? -Epilepsy ማንኛውንም የእድሜ ክልል የሚያጠቃ በሽታ ነው። አጋላጭ ምክንያቶችስ? -ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ሰዎች ምክንያታቸው አይታወቅም -አንጎል ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች ፣ ቁስለቶች ፣ ኢንፌክሽን ፣ የጭንቅላት ወባ ፣ በዘር ሀረግ ፣ ወደ አንጎል የሚሄደው ደም ሰር ሲዘጋ ወይም ደም ሲፈስ ፣ ጭንቀት ፣ አልኮል መጠጥ ከመጠን በላይ የሚጠጡ ሰዎች ፣ የጭንቅላት እጢ ፣ መድሀኒቶችን በድንገት ማቆም ፣ አደንዛዥ እፅ ተጠቃሚዎች ፣ በእርግዝና ግዜ የሚፈጠር የየፅንስ አፈጣጠር ችግር እና በውልደት ጊዜ የፀንስ መታፈን ፣ የምጥ መርዘም ፣ በተለያየ ምክንያት ህፃናት ላይ ከመጠን በላይ ሙቀት መጨመር ለምሳሌ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ፣ የሳንባ ምች ሲኖር ፣ እንቅልፍ ማጣት ፣ እንዴት መከላከል እንችላለን? -የጭንቅላት ጉዳት እንዳይከሰት መከላከል በተለይ ሞተር አሽከርካሪዎች ሄልሜት እንዲያደርጉ ይመከራል -በእርግዝና ጊዜ በቂ የሆነ ፅንስ ክትትል ማድረግ -ህፃናት ላይ የሰውነት ሙቀት መጨመር ሲኖር ወዲያውኑ ህክምና ማድረግ -የደም ግፊት እና የደም ስኳር መጠን እንዳይጨምር መቆጣጠር -ከመጠን በላይ አልኮል መጠጥ እና አደንዛዥ እፆችን አለመጠቀም -የወባ በሽታ ምልክቶች ካሉ በቶሎ መታከም የሚያመጣውሰ ችግር? - መሬት ላይ በመውደቅ ግዜ መሰበር ፣ ድባቴ (depression) ፣ መገለል ፣ የማህበራዊ ሂወት መስተጓጎል ፣ የኢኮኖሚ ጥገኝነት ፣ ከትምህርት ቤት እና ከስራ መሰተጓጎል ፣ የአንጎል ስራ ማቆም ፣ እስከሞት ሊዳርግ ይችላል። አንድን ሰው ሲዝ ሲያደርግ ብናገኝ ምን ማድረግ እንችላለን? -የሚጥል በሽታ በአብዛኛው መቆጣጠር ስለሚቻል በተቻለ መጠን አለመደናገጥ -በተለምዶ ክብሪት በተለምዶ መለኮስ ምንም ጥቅም የለውም -አንድ ሰው ሲወድቅ ቦታ ስለማይመርጥ ሊመታው የሚችለውን ነገር ማራቅ -ከወደቁ በዃላ አንገታቸው ጋር ትራስ ወይም ጨረቅ አድርጎ መደገፍ -በጎናቸው በኩል ጉልበታቸውን አጠፍ አድርገው አንገታቸውን ቀና ፣ አፋቸውን ዝቅ አድርገው ምላሳቸው ታጥፎ ወደ አየር ቧንቧ እንዳይገባ እና መታፈን እንዳይኖር መከታተል ከዛም መንቀጥቀጡ ሲያበቃ ወደ ህክምና ተቋም መውሰድ ህክምና ተቋም ከደረሱስ በዃላስ? -የህክምና ባለሙያው አተነፋፈሱ ፣ የደም ግፊቱ ፣ የደም ስኳር መጠን እና አካላዊ ምርመራ አድርጎ ደህና መሆኑን አረጋግጦ ተጨማሪ እና አስፈላጊውን ምርመራ ሊያዝ ይችላል። - ምክንያቱ የታወቀ ከሆነ ማከም - ከዛም እንደ አስፈላጊነቱ ረዘም ለወራት እና ለአመታት ረዘም ላለ ጊዜ መድሀኒቶች ሊታዘዙ ይችላሉ። -መድሀኒቶች ከታዘዙ በዃላ የሀኪም ክትትል ማድረግ እጅግ በጣም ወሳኙ የህክምናው አካል ነው። አንድ የሚጥል ቀሽታ (Epliepsy) ያለበት ሰው ወደ እሳት አካባቢ እና የውሀ ዋና ስፓርት የሚያዘወትር ከሆነ በሚጥለው ጊዜ ለከፋ አደጋ ስለሚያጋልጥ በተቻለ መጠን መራቅ ያሰፈለጋል። መድሀኒቶችን እና የህክምና ክትትል ማቋረጥ ላልተፈለገ እና ለባሰ አደጋ ያጋልጣል። ዶ/ር ኤርሚያስ ማሞ ጤና ይብዛሎ! @HakimEthio
Mostrar todo...