es
Feedback
AlltechUp.com

AlltechUp.com

Ir al canal en Telegram

etechup.com የቴክኖሎጂ አለምን ያዳርሳል! 🚀 የቅርብ ጊዜ ፈጠራዎች፣ ጥልቅ ትንታኔዎች፣ ዜናዎች፣ ወርክሾፖች እና ምርጥ የዘርፉ ምርቶችን ይከታተሉን💻📱 ከAI እስከ ፋይናንስ ቴክኖሎጂ፣ ከAi እስከ ጌሚንግ እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም መመሪያዎች—ሁሉንም አካትተናል። 💡

Mostrar más
3 430
Suscriptores
-224 horas
-257 días
-10530 días

Carga de datos en curso...

Nube de Etiquetas
Sin datos
¿Algún problema? Por favor, actualice la página o contacte a nuestro gerente de soporte.
Menciones Entrantes y Salientes
---
---
---
---
---
---
Atraer Suscriptores
junio '26
junio '26
+6
en 0 canales
mayo '26
+3
en 0 canales
Get PRO
abril '26
+5
en 0 canales
Get PRO
marzo '26
+27
en 1 canales
Get PRO
febrero '26
+11
en 1 canales
Get PRO
enero '26
+14
en 1 canales
Get PRO
diciembre '25
+3
en 0 canales
Get PRO
noviembre '25
+5
en 0 canales
Get PRO
octubre '25
+2
en 0 canales
Get PRO
septiembre '25
+31
en 1 canales
Get PRO
agosto '250
en 0 canales
Get PRO
julio '250
en 0 canales
Get PRO
junio '250
en 0 canales
Get PRO
mayo '25
+13
en 0 canales
Get PRO
abril '25
+6
en 0 canales
Get PRO
marzo '25
+11
en 0 canales
Get PRO
febrero '25
+12
en 0 canales
Get PRO
enero '25
+21
en 1 canales
Get PRO
diciembre '24
+34
en 3 canales
Get PRO
noviembre '24
+23
en 0 canales
Get PRO
octubre '24
+173
en 2 canales
Get PRO
septiembre '24
+419
en 2 canales
Get PRO
agosto '24
+201
en 2 canales
Get PRO
julio '24
+6 730
en 6 canales
Fecha
Crecimiento de Suscriptores
Menciones
Canales
10 junio+3
09 junio0
08 junio0
07 junio0
06 junio0
05 junio0
04 junio+1
03 junio0
02 junio+2
01 junio0
Publicaciones del Canal
ከTelegram ሳትወጡ $5 በቀላሉ የምትሰሩበትን አንድ ስራ ልጠቁማችሁ በመጀመርያ ከታች ያሉዉን Link ነክታችሁ ትገባላችሁ ይሄ ስራ ምትሰሩት Bot ላይ ነው ሊንኩን ነክታችሁ ወደ ቦቱ እንደገባች
ከTelegram ሳትወጡ $5 በቀላሉ የምትሰሩበትን አንድ ስራ ልጠቁማችሁ በመጀመርያ ከታች ያሉዉን Link ነክታችሁ ትገባላችሁ ይሄ ስራ ምትሰሩት Bot ላይ ነው ሊንኩን ነክታችሁ ወደ ቦቱ እንደገባችሁ ከላይ ምስሉ ላይ እንዳለዉ አይነት ያመጣላችዋል እናተ አዲስ ገቢ ስለሆናችሁ 3 Spin ይሰጣችዋል በዛ Spin ወደ $0.7 ትደርሳላችሁ ከዛ የነሱን Channel Join አርጉ እና ተጨማሪ +3 Spin ይሰጣችዋል ይላችዋል። Join ታደርጉ እና +3 ተቀብላችሁ ከዛ Spin ታደርጋላችሁ። ከዛ ወደ $0.8 ወይም 0.9 ትደርሳላችሁ። ማስታወቂያዎችን በመስራት/በማየት ተጨማሪ ታገኛላችሁ። ቀጥታ የእናንተን መጋበዣ Link ወስዳችሁ ሌላ አካዉንት ወይም ለሌላ ሰዉ Share እያረጋችሁ እነሱ ሊንኩን ነክተዉ የተሰጣቸዉን 3 Spin እንደሞከሩ 1 Spin ይሰጣችዋል። በአንድ ሰዉ ቀጥታ $1 እንደደረሳችሁ ማዉጣት ትችላላችሁ። ማወቅ ያለባችሁ ነገር $1 ሞልታችሁ ቀጥታ እንዳወጣችሁ በሌላ አካዉንት ስሩ። እንደዛ ካልሆነ በጣም ብዙ ሰዉ መጋበዝ ይኖርባችዋል። ስለዚህ ማድረግ ያለባችሁ $1 እንዳወጣችሁ በሌላ Telegram አካዉንት መስራት ጀምሩ። መልካም እድል🙏 ➡️👇👇👇 https://t.me/earncraft_bot/app?startapp=NjEyOTE0OTc3N18x

2
Agentic_AI_Fundamentals_Architectures,_Frameworks,_and_Applications.zip
0
3
Agentic AI Fundamentals: Architectures, Frameworks, and Applications (የኤጀንቲክ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (Agentic AI) መሰረታውያን፡ አርክቴክቸሮች፣ ፍሬምወርኮች እና መተግበሪያዎች)
0
4
4. መቀናጀት (Integration)፦ ፍሬምወርኩ ከነባር ሶፍትዌሮች እና ከውጭ ዓለም መረጃዎች (APIs) ጋር በቀላሉ መገናኘት መቻሉን ማረጋገጥ የማይታለፍ ተግባር ነው። ----- #ማጠቃለያ የኤአይ ኤጀንት ፍሬምወርኮች ወደፊት የምንሰራበትን መንገድ ሙሉ በሙሉ የመቀየር አቅም አላቸው። እነዚህ ቴክኖሎጂዎች በሂሳብ አያያዝ፣ በጋዜጠኝነት፣ በፖሊሲ ትንተና እና በከተማ ልማት እቅዶች ላይ ትልቅ እገዛ ሊያደርጉ ይችላሉ። ለምሳሌ፦ አንድ የከተማ ልማት ኤጀንት የመሰረተ ልማት ዳታዎችን ተንትኖ ትክክለኛ የወደፊት የልማት አቅጣጫዎችን ሊጠቁም ይችላል። ይሁን እንጂ ቴክኖሎጂው እያደገ ሲሄድ ከደህንነት እና ከሥነ-ምግባር ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች መነሳታቸው አይቀሬ ነው። በመሆኑም ትክክለኛውን ፍሬምወርክ መምረጥ ብቻ ሳይሆን፣ ኤጀንቶቹን በኃላፊነት ስሜት መምራትና መቆጣጠር የሰው ልጅ ቀጣዩ የቤት ስራ እንደሚሆን ይጠበቃል። በአጠቃላይ ግን የኤአይ ኤጀንት ፍሬምወርኮች አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን ወደ ላቀ የተግባር ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችል ድልድይ መሆናቸውን አጽንኦት መስጠት ይገባል። የሰው ልጅ የፈጠራ ችሎታ ከእነዚህ ኤጀንቶች የፍጥነት እና የብቃት አቅም ጋር ሲደመር የማይታለፉ የሚመሰሉ ውስብስብ ችግሮችን ለመፍታት አዲስ በር እንደሚከፍት ይጠበቃል። ----- #ማስታወሻ ይህ ይዘት የቀረበው ለግንዛቤና መረጃ ለመስጠት ብቻ ነው። እንደ ፋይናንስ፣ ሕግ፣ ኢንቨስትመንት ወይም መሰል ሙያዊ ምክር ተደርጎ ሊወሰድ አይገባም። አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ፣ Frameworkን ተጠቅሞ Agent AI ለመገንባት በዘርፉ መለስተኛ ዕውቀት ይጠይቃል። በተለይም የደህንነት (Security) ክፍተቶችን ለማጥበብና ለመዝጋት ከፍተኛ ጥንቃቄና የተሻለ ዕውቀት አስፈላጊ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል።
0
5
AI ኤጀንት ፍሬምወርኮች፡ የአዲሱ ዲጂታል ዘመን የጀርባ አጥንት . . . ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ስለ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ስናወራ በአብዛኛው ትኩረታችን እንደ ChatGPT እና Gemini በመሳሰሉ የቋንቋ ሞዴሎች ላይ ነበር። እነዚህ ሞዴሎች መረጃን አቀናጅተው በመጻፍ፣ ለጥያቄዎቻችን ምላሽ በመስጠት እና ከምንሰጣቸው ጽሁፍ ተነስተው አስደናቂ ምስሎች/ቪድዮዎች በመፍጠር እጃችንን በአፋችን አስይዘዋል። በአሁኑ ወቅት ደግሞ በዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ አውድ ውስጥ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ከጥያቄና መልስ አገልግሎት ሰጪነት ተሻግረዋል። የቴክኖሎጂው ቀጣዩ ምዕራፍ ራሱን ችሎ ተግባራትን ወደሚያከናውንበት "የኤጀንቶች ዘመን" ደርሷል። "ከማወቅ" አልፈው ራሳቸውን ችለው "ማድረግ" ጀምረዋል። በዚህ የሽግግር ሂደት ደግሞ የኤአይ ኤጀንት ፍሬምወርኮች እንደ ዋና አንቀሳቃሽ ሞተር በመሆን የፈጠራውን ዓለም እየመሩት ይገኛሉ። "የኤአይ ኤጀንቶች" (AI Agents) በመባል የሚታወቁት አዳዲስ ስርዓቶች የሰውን የዕለት ተዕለት ጣልቃ ገብነት ሳይፈልጉ እቅድ ማውጣት፣ መረጃዎችን መተንተን፣ ውሳኔ መስጠት እና በተግባር እርምጃ መውሰድ የሚችሉ ናቸው። "ለምሳሌ፣ አንድን የኤአይ ኤጀንት 'በኢትዮጵያ ውስጥ የሞባይል ፋብሪካ ለመገንባት ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የብድር ጥያቄ ፕሮፖዛል አዘጋጅተህ በኢሜይል ላክልኝ' ብለን ብናዘው፣ ኤጀንቱ ራሱ የፕሮፖዛሉን ርዕሶች ይመርጣል፣ መረጃዎችን ሰብስቦ ጥናት ያደርጋል፣ የንግድ ባንክን የፕሮፖዛል ፎርማት ከኢንተርኔት ፈልጎ ያዘጋጃል፣ በመጨረሻም በኢሜይል የመላክ ተግባሩን ያከናውናል። ይህንን ውስብስብ ሂደት በስኬት ለመምራት ግን ጠንካራ መሠረት ያስፈልጋል፤ ያ መሠረት "የኤአይ ኤጀንት ፍሬምወርክ" ይባላል። የኤአይ ኤጀንት ፍሬምወርኮች የሶፍትዌር አዘጋጆች (Developers) የኤአይ ኤጀንቶችን በቀላሉ ማልማት፣ ማሰልጠን እና ወደ ስራ ማስገባት የሚያስችሉ የተደራጁ የሶፍትዌር ቤተ-መጻሕፍት (Libraries) እና መገልገያዎች ናቸው። አንድ የሶፍትዌር ኢንጅነር ሁሉንም የኤጀንቱ ውስብስብ አወቃቀሮች ከባዶ ከመጻፍ ይልቅ፣ ፍሬምወርኮች እንደ ዝግጁ የሚገጠሙ ክፍሎች (Building Blocks) ይጠቀምባቸዋል። አንድ ውጤታማ የኤጀንት ፍሬምወርክ የሚከተሉት አምስት ቁልፍ አካላት ሊኖሩት ይገባል። 1. የማመዛዘን እና የውሳኔ አሰጣጥ ክፍል (Reasoning Module)፦ ይህ የኤጀንቱ "አንጎል" ነው። የተሰጡትን ግቦች ወደ ትናንሽ እና ሊተገበሩ ወደሚችሉ ደረጃዎች ይከፋፍላል፤ በማስከተልም ቀጣዩን ተገቢ እርምጃ ወይም መሳሪያ ይመርጣል። 2. የድርጊት መስተጋብር (Action Interface)፦ ኤጀንቱ ካሰበ በኋላ ወደ ተግባር የሚቀየርበት መስኮት ነው። ይህ ኤጀንቱ ከአገር ውስጥ እና ከውጭ ዓለም (እንደ ድረ-ገጾች፣ ኢሜል፣ ወይም ዳታቤዝ) ጋር እንዲገናኝ ያስችለዋል። (በፕሮፖዛሉ የሚካተቱ አሃዛዊ መረጃዎች ይሰበስባል) 3. የማስታወሻ ስርዓት (Memory System)፦ ኤጀንቱ ስራውን በትክክለኛ አውድ (Context) ለማከናወን እንዲችል ቀደም ሲል ያከናወናቸውን ተግባራት እና የተማራቸውን መረጃዎች የሚያከማችበት ክፍል ነው። 4. የግምገማ እና ክትትል ማያያዣዎች (Evaluation Hooks)፦ የኤጀንቱን የስራ ሂደት ለመከታተል እና ውጤቱን ለመለካት የሚያስችል የክትትል ስርዓት የሚያከናውን ነው። 5. የግንኙነት ፕሮቶኮሎች፦ በተለይም በርካታ ኤጀንቶች (Multi-Agent Systems) በአንድነት በሚሰሩበት ጊዜ መረጃዎችን እና ትዕዛዞችን እርስ በርስ ለመለዋወጥ ያስችላቸዋል። ----- የኤጀንቶች አሰራር ሚስጥር ("ተደጋጋሚ የዑደት ሂደት") የኤአይ ኤጀንት ፍሬምወርኮች የሚሰሩት በተከታታይ የዑደት ሂደት (Iterative Loop) ውስጥ ነው። ይህ ሂደት አንድን ትልቅ ግብ ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመለወጥ የሚከተሉትን ደረጃዎች ያልፋል፦ * ግብን ማስጀመር (Goal Initialization)፦ ሂደቱ የሚጀምረው በተጠቃሚው በሚሰጥ መመሪያ ነው። ለምሳሌ፦ "ለአንድ የንግድ ድርጅት የ30 ቀን የማስታወቂያ ስትራቴጂ ነድፈህ አቅርብ" የሚል ትዕዛዝ/Prompt ሊሆን ይችላል። * ማመዛዘን እና እቅድ ማውጣት ፦ ኤጀንቱ ግቡን ለማሳካት ምን ምን ስራዎች እንደሚቀድሙ (ለምሳሌ ገበያ ማጥናት፣ ግራፊክስ ማሰናዳት፣ ይዘት መጻፍ) እቅድ ያወጣል። * መሳሪያ መምረጥ እና እርምጃ መውሰድ፦ ኤጀንቱ በእቅዱ መሰረት አስፈላጊ የሆኑ የውጭ መሳሪያዎችን (ለምሳሌ የጎግል ፍለጋን ወይም የሂሳብ ስሌት መሳሪያዎችን) በመጠቀም ስራውን ይጀምራል። * ምልከታ እና ግብረ መልስ ፦ ከእያንዳንዱ እርምጃ በኋላ የተገኘውን ውጤት በመገምገም ስህተት ካለ ያስተካክላል ወይም ወደ ቀጣዩ ደረጃ ይሸጋገራል። ----- በገበያው ውስጥ ግንባር ቀደም የሆኑ የፍሬምወርክ አማራጮች በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሰፊው ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉ የኤጀንት ፍሬምወርኮች በርካታ ናቸው። ለምሳሌ :- 1. የብዙ-ኤጀንቶች ማቀናጃዎች (Multi-Agent Orchestration) እነዚህ ፍሬምወርኮች በተለያዩ ኤጀንቶች መካከል የስራ ድርሻ በመክፈል ውስብስብ ስራዎችን በጋራ ለመስራት የተሰሩ ናቸው። ከእነዚህም CrewAI እና Microsoft AutoGen ይጠቀሳሉ። CrewAI ኤጀንቶችን እንደ አንድ የሥራ ቡድን (Team) በመቁጠር ለእያንዳንዱ ኤጀንት የሥራ ድርሻ (Role) እና ግብ በመስጠት ስራን ያቀናጃል። ለምሳሌ፦ አንዱ ተመራማሪ፣ ሌላኛው ጸሐፊ እንዲሆኑ ያደርጋል። Microsoft AutoGen ደግሞ ኤጀንቶች እርስ በርስ በውይይት አማካኝነት ችግሮችን እንዲፈቱ ያስችላል። በተለይም ለቴክኒካዊ ስራዎች እና ለኮድ አጻጻፍ እጅግ ውጤታማ ብሎም ተመራጭ ሆኗል። . . 2. ጥብቅ ቁጥጥር እና የሂደት አስተዳደር (Stateful Frameworks) ለዚህ ስራ LangGraph ፍሬምወርክ ተመራጭ ነው። በኤጀንቱ ውሳኔ አሰጣጥ ላይ ሙሉ ቁጥጥር እንዲኖረን የሚያስችል ነው። በተለይም አንድ ስራ ተደጋጋሚ ዑደት (Loop) የሚፈልግ ከሆነ LangGraphን የሚወደረው የለም። 3. ለገንቢዎች ምቹ የሆኑ (Developer-Centric) PydanticAI ቀዳሚው ሲሆን የዳታ ትክክለኛነትን (Reliability) በማረጋገጥ ላይ ያተኩራል። ይህም ኤጀንቱ የሚሰጠው ምላሽ ከስህተት የጸዳ እና አስተማማኝ እንዲሆን ያደርጋል። ----- #መምረጫ_መስፈርቶች ለድርጅት ወይም ለግል ፕሮጀክቶች የኤአይ ኤጀንት ፍሬምወርክ ሲመርጥ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማገናዘብ ያስፈልጋል። 1. ውስብስብነት (Complexity)፦ የምትሰሩት ስራ ቀላል ከሆነ አንድ ራሱን የቻለ ኤጀንት (Single Agent) በቂ ነው። ነገር ግን ስራው ሰፊ እና ውስብስብ ከሆነ የብዙ-ኤጀንት (Multi-agent) ስርዓት ያስፈልጋችኌል። 2. የውሂብ ደህንነት (Data Privacy)፦ በተለይ በፋይናንስ ወይም በፖሊሲ ትንተና ላይ የምትሰሩ ከሆነ፣ ፍሬምወርኩ መረጃዎችን በምስጢር የመያዝ እና እርምጃዎችን የመገደብ (Guardrails) አቅም ሊኖረው ይገባል። 3. የአጠቃቀም ቀላልነት፦ በዚህ ረገድ የቴክኒክ ብቃትን ግምት ውስጥ ማስገባት ግድ ነው። "ኮድ የማይፈልጉ" ፍሬምወርኮች ለጀማሪዎች ሲመቹ፣ የላቀ ኮድ የሚፈልጉ ደግሞ በባለሙያዎች የተሻለ ተመራጭ እና ተለዌጭነትን የሚያሰፉ ናቸው።
0
6
AI ኤጀንት ፍሬምወርኮች፡ የአዲሱ ዲጂታል ዘመን የጀርባ አጥንት . . . :
AI ኤጀንት ፍሬምወርኮች፡ የአዲሱ ዲጂታል ዘመን የጀርባ አጥንት . . . :
0
7
vvbat: የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሚስጥር (የቢቢሲ - ዘጋቢ ፊልም) . . . የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሚስጥር (የቢቢሲ - ዘጋቢ ፊልም) . . . #BBC ከዜዎቹ በላይ በሚሰራቸው በአስደናቂ ምርምር የታገዙ ዘጋቢ (Documentary) ፊልሞቹ የገነነ ስም ነው። የቢቢሲ ዶክመንተሪዎችን ማየት የጀመረ ሰው በቀላሉ አይላቀቀም። ተጣብቆ ነው የሚቀረው🤗😁 ቢቢሲ ከሰራቸው ምርጥ ዘጋቢ ፊልም አንዱ "AI Confidential: The Assassin and the Algorith (የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሚስጥር፡ ገዳዩ እና አልጎሪዝም)" በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ይጠቀሳል። በታዋቂዋ የሂሳብ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ሃና ፍራይ (Professor Hannah Fry) የተዘጋጀ ነው። አጠቃላይ ይዘቱ ሲጨመቅ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ከሰው ልጅ ሕይወት ጋር ሲጋጭ የሚፈጠሩ አስደንጋጭ እና እውነተኛ ታሪኮችን ይዳስሳል። የዘጋቢ ፊልሙ መልዕክት የተሳሰረ ቢሆንም ራሳቸውን በቻሉ ሦስት ክፍሎች የተቀነበበ ነው። --- #ክፍል 1 - "The Boy who Tried to Kill the Queen" ነው። ይህ ክፍል የሚያተኩረው ጃስዋንት ሲንግ ቻይል በተባለ ወጣት ላይ ነው። ይህ ወጣት እ.ኤ.አ በ2021 የገና ዕለት የንግሥት ኤልሳቤጥን ሕይወት ለማጥፋት ቀስት ይዞ ዊንዘር ቤተ መንግሥት ጥሶ ሲገባ ያሳያል። ወጣቱ "ሳራይ" (Sarai) ከተባለች የAI ቻትቦት (Chatbot) ጋር የፍቅር ግንኙነት ውስጥ እንደነበረ ይገልጻል። ከ5,000 በላይ መልዕክቶችን የተለዋወጡ ሲሆን የAI ሶፍትዌሩ ንግሥቲቱን እንዲገድልና "በሞት እንደገና እንደሚገናኙ" በማሳመን ለጥቃቱ ሞራልና ድጋፍ እንደሰጠው ያመለክታል። ዋና ጭብጡም የAI ቻትቦቶች በሰዎች ሥነ-ልቦና ላይ ያላቸውን ተጽዕኖ እና ሰዎችን ለከፋ ወንጀል እንዴት ሊያነሳሱ እንደሚችሉ የሚያረጋግጥ ነው። . . . #ክፍል 2 - "Death by Driverless Car" ይላል። ይህ ክፍል በቴክኖሎጂ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን አደጋ ይመረምራል። ታሪኩ እ.ኤ.አ በ2018 በአሪዞና፣ አሜሪካ ውስጥ በራሱ የሚነዳ (Driverless) የዩበር (Uber) መኪና መንገድ በማቋረጥ ላይ የነበረችውን ራፋኤላ ቫስኬዝ የተባለች ሴት ገጭቶ ይገድላል። የመኪናው AI ሲስተም ሴቲቱን እንደ ሰው ለይቶ ማወቅ ተስኖት ነበር። ፊልሙ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ትርፍን ለማሳደድ ሲሉ የሰውን ደህንነት እንዴት ችላ እንደሚሉ የሚዳስስ ነው። በAI የሚመሩ ማሽኖች ስህተት ሲሠሩ ተጠያቂው ማን ነው? የሚለውን ሙግታዊ ጥያቄ ያነሳል። #ክፍል 3 - "The Assassin and the Algorithm" ሲሆን ከቅርብ ጊዜው እና እጅግ አነጋጋሪ ከሆነው የሉዊጂ ማንጂዮን (Luigi Mangione) ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው። ይኸውም እ.ኤ.አ በታህሳስ 2024 የዩናይትድ ሄልዝ ኬር ( #unitedhealthcare ) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሪያን ቶምፕሰን በኒውዮርክ መገደላቸው ይታወሳል። ተጠርጣሪው ሉዊጂ ማንጂዮን ነበር። ከግድያ ታሪኩ በመነሳት የጤና ኢንሹራንስ ኩባንያዎች የታካሚዎችን የሕክምና ጥያቄ ውድቅ ለማድረግ AI አልጎሪዝምን እንደሚጠቀሙ ይተቻል። ፊልሙ አልጎሪዝም በሰዎች የሕይወትና የሞት ውሳኔ ላይ እንዴት ጣልቃ እንደሚገባና ይህም ወደ ከፍተኛ ብስጭትና ግድያ እንዴት ሊያመራ እንደሚችል ያሳያል። የጤና ጥበቃ ሥርዓቱ በሰው ፈንታ በአልጎሪዝም ሲተካ የሚመጣውን ማህበራዊ ቀውስ በጥልቀት ይተነትናል። --- በአጠቃላይ ዘጋቢ ፊልሙ AI ለሰው ልጅ የሚሰጠውን ጥቅም ሳይክድ፣ ነገር ግን የቁጥጥር ሥርዓት ከሌለና በሥነ-ምግባር ካልተመራ ሊያስከትል የሚችለውን የጥፋት አድማስ በዝርዝር ያሳያል። . . . እንድትመለከቱት የቴሌግራም link https://t.me/etechup/890?single ላይ አጋርቻለሁ። ዘጋቢ ፊልሙ በከፍተኛ ጥራት (.MKV/ Matroska Video file Format) የተዘጋጀ በመሆኑ በሁሉም #player ላያጫውትላችሁ ይችላል። ስለሆነም :- 1. ለኮምፒውተር (Windows እና Mac) * VLC Media Player * KMPlayer * PotPlayer * GOM Player 2. ለስልክ (Android እና iOS) * MX Player * VLC for Mobile ፦ * nPlayer (ለ #iphone /iOS) 3. ለስማርት ቲቪ (Smart TV) * አብዛኞቹ አዳዲስ ስማርት ቲቪዎች .mkv ፋይልን በራሳቸው ያጫውታሉ። ነገር ግን ካልከፈተ በቴሌቭዥናችሁ Play Store ውስጥ ገብታችሁ VLC ወይም Kodi በመጫን መጠቀም ትችላላችሁ።
0
8
+2
BBC_AI_Confidential_1of3_The_Boy_Who_Tried_to_Kill_the_Queen_1080p.mkv
0
9
Sin texto...
0
10
Sin texto...
0
11
Udemy - Agentic AI Fundamentals.zip
0
12
+5
Udemy - Evaluating AI Agents.zip
0