cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Ethio con Tender

የግንባታ ጨረታዎችን የምታገኙበት ቻናል ነው። የቻናሉ ቤተሰብ ይሁኑ!

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
3 370
Suscriptores
+1424 horas
+1187 días
+44330 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

የሰኔ_ወር_2016_ዓ_ም_የሀራጅ_ሽያጭ_ማስታወቂያ_1.PDF3.53 MB
የሰኔ_10_ቀን_2016_ዓ_ም_የተዘለለ_የሀራጅ_ሽያጭ_ማስታወቂያ.PDF0.55 KB
👍 1
➡️ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከካም ሴራሚክ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ጋር  በመሆን ከ2 ቢሊዮን  በላይ በሆነ ኢንቨስትመንት  የሴራሚክ አምራች ፋብሪካ አቋቋሙ። ⏺ የፋብሪካው ግንባታ የተጠናቀቀ ሲሆን በቅርቡ ወደ ምርት እንደሚገባ በስካይ ላይት ሆቴል  በተደረገው ይፋዊ የአክሲዮን  የመመስረቻ ስነ ስርአት ላይ ተገልጿል። ⏺ በስምምነት የፊርማ ስነ-ስርአቱ የተከበሩ አቶ ታረቀኝ ቡልልታ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የሥራ መመሪያ እና የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። ⏺ በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ  ወ/ሮ  መልእክት ሳህሉ ተገኝተዋል።
Mostrar todo...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
በ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ወጪ ለሚገነባ ኩባንያ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ፈሰስ ተደርጎበት ለሚገነባ ኩባንያ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የመሰረት ድንጋይ አስቀመጠ። የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሚል ኢብራሂም፣ የኮርፖሬት ሀብት አስተዳደር ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አለማየሁ ሰይፉ እና የፔሪ ሜትር ኮንሰልቲንግ ማኔጅንግ ዳይሬክተር ቤተልሄም ጥላሁን የመሰረተ ድንጋዩን አስቀምጠዋል። የሚገነባው ማምረቻ ከጤፍ የተለያዩ ስናኮችንና ደረቅ የምግብ ዓይነቶችን የሚያመርት ሲሆን በፔሪ ሜትር ኮንሰልቲንግ እና ትሬዲንግ ኩባንያ አማካኝነት ነው የሚገነባው። በዚሁ ወቅት የኮርፖሬሽኑ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሚል ኢብራሂም÷ ወደ ኮርፖሬሽኑ ለሚመጡ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል። በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ማምረቻውን በ11 ሄክታር የለማ መሬት ላይ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠለት የፔሪ ሜትር ኮንሰልቲንግ ኩባንያ ከ1 ኘጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ እንደሚደረግበትም የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡ የግንባታ ስራው ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር ምርቶቹን ወደ አውሮፓ፣ አሜሪካ እና የሩቅ ምስራቅ ሀገራት እንደሚልክ ተገልጿል። (FBC)
Mostrar todo...
👍 2 1
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግዥና ንብረት ባለስልጣን ረቂቅ አዋጅን አጸደቀ ምክር ቤቱ ዛሬ ሰኔ 4/2016ዓ/ም ባካሄደዉ መደበኛ ስብሰባ የባለስልጣኑን አዋጅ ማጽደቁ ተሰምቷል፡፡ የጸደቀዉ አዋጅ በአፈጻጸም ትግበራ ሂደት ያጋጠሙ ችግሮችን ለማረምና ከዘመነ አሰራር ጋር ለመራመድ የሚያሥችል፣ ብሎም የሃገር ዉስጥ ተወዳዳሪዎች ያላቸዉን ተሳትፎ ለማበረታታት የሚያስችል ድንጋጌ ያካተተ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የጸደቀዉ አዋጅ በመንግስት ልማት ድርጅቶች  ጭምር ተፈጻሚ መሆኑንና የሚከሰቱ የሕግ ጥሰቶች የሚያስከትሉትን አስተዳደራዊ ተጠያቂነት ያካተተ አዋጅ መሆኑም ተነግሯል፡፡ የባለስልጣኑ ረቂቅ በአዋጅ ቁጥር 1333/2016 ሆኖ በሙሉ ድምጽ መጽደቁን የተገኘዉ መረጃ ያመላክታል፡፡ (መግንባ)
Mostrar todo...
👍 2
የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር ECWCT/NCB/SG-113/2016 የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተለያዩ ያገለገሉ መሳሪያዎችና ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ስለሚፈልግ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ብቁ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡ 1.  በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል የዘመኑ ግብር የከፈሉበት ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት ማስረጃ በማቅረብ የማይመለስ ብር 400.00/አራት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት የሀገር ውስጥ ጥቅል ግዥ ቡድን ቢሮ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡ 2.  የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የሚመጣ ተዛማጅ የሆነ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ወይም መታወቂያ እና  የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ 3.  የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው፡፡ የጨረታው ሰነድ የተዘጋጀው በአማርኛ ቋንቋ ነው ፡፡ 4.  ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ ብር አስር በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ጋራንቲ (የባንክ ዋስትና) ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጪ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡ 5.  ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ግዥ መምሪያ-1 ገቢ የሚያደርጉበት የመጨረሻ ቀን ሰኔ 18 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው፡፡ 6.  ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ሰኔ 18 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ከጠዋቱ 05፡00 የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ቅጥር ግቢ በሚገኘው ግዥ መምሪያ-1 የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ 7.  መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 8.  ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡             የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በግዥ መምሪያ ቢሮ           አድራሻ፡-ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ህንፃ 200 ሜትር ገባ ብሎ     አንድነት ኢንተርናሽናል ት/ቤት ፊት-ለፊት    ስልክ ቁጥር 0118 72 29 91/ 0118-72 29 58
Mostrar todo...
👍 4🥰 2
Photo unavailableShow in Telegram
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ አዲስ ዘመን ሰኔ 1ቀን 2016 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ
Mostrar todo...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ አዲስ ዘመን ሰኔ 1ቀን 2016 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ
Mostrar todo...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ አዲስ ዘመን ግንቦት 30 ቀን 2016 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ
Mostrar todo...
👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ አዲስ ዘመን ግንቦት 30 ቀን 2016 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ
Mostrar todo...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
👉 የዛሬ የሰኔ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ኢትዮ ኮን ምሽት የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራማችን 🚧 ይህ የሬድዮ ፕሮግራም የሀገራችን የኮንስትራክሽን ዘርፍ የተለያዩ የግንባታ ተግዳሮቶች ውስጥ ያለ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከነዚህ ተግዳሮቶች ውስጥ የግንባታ ግብዓት ችግር፣ የቴክኖሎጂ ዕጥረት፣ ብቁ የሆነ ባለሙያ አለመገኘትና የግንባታ ደህንነት ወይንም ሴፍቲ እና ሌሎችም ጉዳዮች የሚነሱበት ሳምንታዊ ፕሮግራም ነው፡፡ ⏺ ወቅታዊ በዛሬው ወቅታዊ ፕሮግራማችን ላይ የምንመለከተው የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ሰሞኑን በአዳማ ከተማ ያካሄደውን መድረክ በተመለከተ ወደ እናንተ የምናደርሰው መረጃ ይኖረናል፡፡ 👷የእንግዳ ሰዓት -  ኢ/ር ጀበል ጀማል የጀጀኮን ኮንስትራክሽን ባለቤትና ዋና ስራ አስኪያጅ እና ኢ/ር ሀብታሙ ታደሰ የቲዌይ ኮንስትራክሽን ባለቤትና ስራ አስኪያጅ ጋር በእንግዳ ሰዓት ፕሮግራማችን ላይ በቀጥታ ስርጭት የምናደርገው ቆይታ እንደተጠበቀ ነው፡፡ ዛሬም እንደተለመደው ስራ ተቋራጮች በተመለከተ የምናነሳቸው ጉዳዮች ይኖራሉ፡፡ በዚህ በቴሌግራም ቻናላችን ላይ ያላችሁን ሀሳብ አስተያየት እንዲሁም ደግሞ ማንሳት የምትፈልጉት ጥያቄም ካለ እንደተለመደው አድርሱን፡፡ እንቀበላለን፡፡ 🥍📻 ምርጫችሁ አድርጋችሁ ምሽት ከ2፡30 — 3፡30 ሰዓት በአሀዱ ሬድዮ 94.3 ላይ በቀጥታ ስርጭት ፕሮግራሞቻችንን ትከታተሉ ዘንድ ከወዲሁ በአክብሮት እጋብዛለሁ፡፡
Mostrar todo...
👍 1