es
Feedback
Bashewam Primary & Junior School 1-8

Bashewam Primary & Junior School 1-8

Ir al canal en Telegram

Bashewam School Grade 1-8

Mostrar más
2 778
Suscriptores
+1524 horas
+287 días
+8230 días
Archivo de publicaciones
በባሸዋም ትምህርት ቤት የክረምት ተማሪዎች የሶሮባን ወይም የአባከስ ስልጠና ሲሰለጥኑ

በባሸዋም ትምህርት ቤት የክረምት ትምህርት እና ስልጠና የምትከታተሉ ተማሪዎች ትምህርት የሚጀምረው ከጠዋቱ 2:30 ሲሆን የመውጫ ሰዓት ደግሞ 7:00 ነው። ወላጆች 7:00 ሰዓት ሲሆን ትምህርት ቤት በመምጣት ልጆቻችሁ እንድትወስዱ እናሳስባለን።

ውድ የባሸዋም ትምህርት ቤት ወላጆች ከቀን 19/11/2015 ዓ.ም ጀምሮ ምዝገባ መመዝገብ የሚቻለው በቅጣት ስለሆነ፡ ቀድማችሁ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን። . ከሀምሌ 20/2015 ዓ.ም ጀምሮ በነባር ተማሪዎች ቦታ አዲስ ተማሪዎችን የምንቀበል መሆኑን በጥብቅ እያሳወቅን፡ በቦታ መሙላት ምክንያት ለሚፈጠር ችግር ሀላፊነት የማንወስድ መሆኑን ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን። ፡ ነባር ተማሪዎች ለምዝገባ ስትመጡ ሁለት ፎቶግራፍ ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን።

በተጨማሪም :ሁሉንም ከ5 ወደ6 እና ከ7 ወደ 8 የሚዘዋወሩ ተማሪዎች ለብሔራዊ ፈተና ይረዳቸው ዘንድ:ልዩ የክረምት ት|ት የሚሰጥ ሲሆን ከሰኞ 10|11|15 ጀምሮ ለ 45 ቀናት የሚሰጥ ይሆናል ።በዘንድሮ ዓመት የብሄራዊ ፈተና የወሰዳችሁ የ 6እና 8 ክፍል ተማሪዎች:ውጤት እስኪመጣ :በ መጠባበቂያ(waiting list)ተመዝግባችሁ የምትቆዩ ይሆናል።

ለባሸዋም ትምህርት ቤት ወላጆች እና ተማሪዎች በሙሉ ፡ ቅዳሜ እለት ከጠዋቱ 2:00 -- 6:30 ምዝገባ የምንመዘግብ ስለሆነ ፡ ያልተመዘገባችሁ ተማሪዎች በሰዓቱ መጥታችሁ እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን። ቅዳሜ ቀን እስከ 6:30 ምዝገባ አለ።