Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Ir al canal en Telegram
● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸
Mostrar más213
Suscriptores
Sin datos24 horas
-17 días
-430 días
Archivo de publicaciones
እውነታው ይህ ነው!
እንደ ሙጂብ አሚኖ ያላችሁ ሰዎች አላህን ፍሩ‼️
ህዝበ-ሙስሊሙ ምንም አይነት የተቃውሞ ድምፅ ሳያሰማ ወይም ምንም አይነት እንቅስቃሴ ሳያደርግ ነው #በsniper ተለይቶ የተመታው።
t.me/ReshadIbnuMuzemil
ለ1444 አመታት በፅናት የዘለቀ ዲናችን (እምነታችን) በአምባ ገነኖች ወከባ አይናወጥም
በወቅታዊ ጉዳይ ከበድር ኢትዮጲያ የተላለፈ መግለጫ
የሸገር ሲቲን ምስረታን አስመልክቶ ሰሞኑን ከ20 በላይ የሚሆኑ መስጊዶቻችን መፍረሳቸውን አስመልክቶ በተነሳው ሰላማዊ ተቃውሞ ባለፈው ሳምንት ግንቦት 18 ቀን ለሁለት ንፁሀን ዜጎች ሞት ለበርካቶች መጎዳት እንዲሁም ብዙ መዕመናን ለእስርና እንገልት መዳረጋቸው የሚታወቅ ነው::
በዛሬው ዕለት ግንቦት 25 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በታላቁ አንዋር መስጅድ በሰላማዊ መንገድ የጁሙዓን ሰላት ለመስገድ በተሰባሰቡ ምዕመናን ላይ በተወሰደው ኢ-ሰብዓዊ ተግባር የደረሰውን ግድያ፣ የአካል መጉደልና እስራት በፅኑ እናወግዛለን::
ይህ ድርጊት ደግሞ የተደገመው ይጠብቀናል ባሉት የፀጥታ ሃይልና መንግስት ይሁንታ መሆኑና፣ባለፈው ሳምንት ሸሂድ(መስዋእት) የሆኑ የቆሰሉና እስካሁን በእስር የሚንገላቱ ወገኖቻችን ብሶት ሳይወጣልን፣ መሆኑ ክፋኛ ያማል።
በማን አለብኝነት ይህን ድርጊት እየፈፀሙ ያሉ ባለሥልጣናት የያዙት ሥልጣን ከህዝብ የተሰጣቸው መሆኑን ዛሬ ላይ ቢዘነጉትም ይህን የሚረዱበት ጊዜ በአላህ ፈቃድ ጊዜው ሩቅ አይሆንም።
አሁን በፊታውራሪነት ይህን ሙስሊም ጠል አድራጎት የሚመሩ ባለሥልጣናት እቅድ ምን እንደሆነ ብናውቅም መዳረሻቸውን እንኳን ህብረተሰቡ የድርጊቱ ተዋናዮች ራሳቸው የሚያውቁት አይመስለንም። ሁሉንም ዜጋ በተለያየ መልኩ የዳሰሰ ነውና። ሁላችንንም የሚያስማማን ነገር ቢኖር ሙስሊም ጠል መሆናቸው ነው።
ስልጣንን መከታ አድርገው ህዝባቸውን የሚበድሉ መንግስታት ሲመጡም ሲሄዱም አይተናል ነገር ግን አንድነታችንን፣ ፅናታችንንና አገራችንን ይዘው ሲሄዱ አላየንም።
በመጨረሻም እንደ በድር ኢትዮጵያ አደራ ለማለት የምንፈልገው፣ ይህ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት እስኪቆም፣ መስጊዶቻችን ዳግም እስኪገነቡ ለተጎዱ ወገኖች ተገቢው ካሳ እስኪሰጥ፣ ህገወጦች ለፍርድ እስኪቀርቡና መንግስትም ህብረተሰቡን በይፋ ይቅርታ እስኪጠይቅ ድረስ እንደ ሁልጊዜው ተናበን ሰላማዊ ትግላችንን መቀጠል ይኖርብናል::
ሀገሪቱን የሚመራው መንግስት የምንጠይቀው ያለምንም ቅድመሁኔታ በየ መስጅዱ የሚደረጉ ማዋከቦችን አፈሳን ጨምሮ በንፁሀን ላይ በጠራራ ፀሀይ እያደረሰው ያለውን ግድያ እንዲያቆም:: ለተጎጅዎች ተገቢውን የህክምና አገልግሎት እንዲያቀርብ:: እንዲሁም በየደረጃው ካሉ የመጅሊስ አመራሮች ጋር በመሆን የሙስሊሙን ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ነው::
መሪ ተቋማችን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ የአዲስ አበባና፣ የክልል መጅሊስ አመራሮቹ በዚህ ዙሪያ ላሳዩት በሳልና ብልህ አመራር እያመስገን ኃላፊነታቸውን በሚወጡበት ዘርፍ ሁሉ ዛሬም ነገም ከጎናቸው መሆችንን በድጋሚ ልናረጋግጥላቸው እንወዳለን።
አላሁ አክበር
በድር ኢትዮጵያ
t.me/ReshadIbnuMuzemil
በርካታ ወንድሞቻችን ላይ ሞትና ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱት እነዚህ በህንፃው ላይ ሆነው በስናይፐር የሚተኩሱት መሆናቸውን የዓይን እማኞች በውስጥ ጠቁመውኛል። አላህ ይፍረድ‼
#Murad_Tadessa
In the name of ALLAH, the most Merciful and the most Compassionate
May Allah's peace and blessings be unto you, especially to our families in Ethiopia during these trying days.
The First Hijrah Foundation (FHF) community is greatly harrowed by the deliberate, shot-to-kill, broad-day light massacre of peaceful Muslim worshippers in their own mosque compounds in Addis Ababa during today's and last week's Jumaa (Friday) prayer by the Ethiopian government forces.
These Jumaa massacres, beatings, mass detaining of peaceful Ethiopian Muslims were preceded by unjustly destroying 19 mosques located in the newly instituted city called Shaggar, around Addis Ababa.
We want the international community to know that the Ethiopian government is responsible for these tormenting and gross human right violations.
We demand, in most strongest terms, the government of Ethiopia to immediately cease and desist the killings with live bullets and terrorising of our Ethiopian Muslim families in Addis Ababa and elsewhere in the country.
FHF will release more detail public statements very soon, insha Allah.
We pray for our Ethiopian brothers and sons, who've lost their lives (martyrs) to accept them in the abode of Jenatul Firdewos.
We pray for our Ethiopian families who are physically hurt and admitted in hospitals to have speedy recovery.
We pray for entire Ethiopia Muslims to be blessed with Allah's peace at this very difficult time.
Ameen.
We remind the Ethiopain Muslims to peacefully stand-up in unity and defend its ALLAH given rights from being abused by government cadres and military, and security forces.
Allahu Akiber! "
ፌዴራል መጅሊሱም፣ የአዲስ አበባ መጅሊስም፣ በርካታ ታዋቂ ኡስታዞችና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ የማኅበረሰብ አንቂዎችና የሚታወቁ ሰዎች ሁሉ ዛሬ በአዲስ አበባ ምንም አይነት ተቃውሞ የለም በማለት ትናንት ጠንካራ መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወቃል።
እኔ በራሴ በተደጋጋሚ ስናገር ነበር። በዚህም የተነሳ የመርካቶ የዛሬ ድባብ ከወትሮው በጣም የተቀዛቀዘ ነበር። በአንዋር መስጅድም የተገኘው ሙስሊም ብዛት ከወትሮው ያነሰ ነበር።
ነገር ግን የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በመስጅዱ በር ድረስ በመሄድና ህንፃ ላይ ሆነው ስናይፐር በማጥመድ ወንድሞቻችንን በሚያሳዝን ሁኔታ ነጥቀውናል።
መጀመሪያውኑ አንዋር መስጅድ መስገድ አይቻልም ቢሉን የተሻለ ነበር። እነርሱ ግን ቢቃወሙም ባይቃወሙም ሳናጠቃቸው አንመለስም የሚል አላማ ያነገቡ በሚመስል መልኩ ሴት ወንድ ሳይሉ ንጹሐንን ክፉኛ አጠቁ።
አሁንም እንላለን! ጥያቄያችን አንድና አንድ ነው። እኛ ረብሻና ሁከት አንሻም። መስጅዶቻችንን አትንኩብን ነው‼
አላህ ይፍረደን‼
|| Murad Tadesse
t.me/ReshadIbnuMuzemil
ደብተርና ብዕር የያዘ ተማሪ መስጅድ ሰግዶ ሲወጣ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ተገድሏል። «ላ ኢላሃ ኢለ-ል'ሏህ» ሲል ይታያል። የሎሚ ሜዳ መድረሳ ልጅ ሲሆን በህይዎት አለ። በአቤት ሆስፒታል ሕክምናውን እየተከታተለ እንደሆነ ነግረውኛል። ለርሱም ለሆነ ለሌሎች ለቆሰሉ ወንድሞች አላህ ዓፊያውን ይመልስላቸው፤ ለሞቱት የሸሂድነትን ደረጃ ይስጣቸው።
ይህን ቪድዮ እስከ መጨረሻው ተመልከቱት‼
የጸቡ ጀማሪ ማን እንደሆነ ያስታውቃል።
||
t.me/ReshadIbnuMuzemil
መልዕክት ለመንግስት‼
=================
✍ መንግስት በሰላማዊ መንገድ መፍታት የሚችለውን ጥያቄ ወደአላስፈላጊ አቅጣጫ እንዲገባ አድርጎ በየሳንምንቱ ንጹሐን ወንድሞቻችንን እየነጠቀን ይገኛል።
አሁንም ቢሆን ወንድሞቻችንን የነጠቁንን የጸጥታ ኃይሎቹን ተጠያቂ ያድርግ፣ ያፈረሳቸውን መስጅዶች ይገንባ፣ የመፍረስ አደጋ ለተጋረጠባቸው ህጋዊ ዕውቅና ይስጥ፣ እስካሁን ለደረሰው የህይዎት መጥፋትና የንብረት መውደም በይፋ ይቅርታ ከመጠየቅ ጀምሮ ተገቢውን ካሳ ይክፈል።
አለበለዚያ ግን ቀጣይ የሚሆነው ዛሬና ባለፈ ሳምንት የተከሰተው አይነት ሳይሆን፤ ሁሉም ሙስሊም ተናቦ በጋራ ተቃውሞውን ማሰማቱ አይቀርም። ያኔ ስንቶቻችንን ገድ'ሎና አፍኖ እንደሚጨርስ እናየዋለን።
ሙስሊም ሲገ'ደልም፣ ሲታሰርም፣ ሲደበደብም… ለዲኔ ነው ብሎ ስለሚያስብ በኃይል የሚንበረከክ አይደለም።
መንግስት ጥያቄዎቻችንን በሰላማዊ መንገድ ይመልስ። ደጋፊው የነበረን ህዝብ ጠላቱ አያድርግ። የኛ ቤተ መንግስታችን መስጅዳችን ነው። ያነገብነው አንዳችም ፖለቲካዊ ጥያቄ የለም። የጠየቅነው መስጅዶቻችንን አትንኩብን እንጂ 4 ኪሎን አይደለም።
ይልቁንም ያለ አግባብ እኛን ሲበድል 4 ኪሎን ለሚመኙ መንገድ እየጠረጉ መሆናቸውን ይወቁት።
Cc:
===
Office of the Prime Minister-Ethiopia FDRE Government Communication Service-በኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
Abiy Ahmed Ali
Ethiopian Federal Police
Addis Ababa Police
||
t.me/ReshadIbnuMuzemil
#Update
የአዲስ አበባ መጅሊስ ፕሬዝዳንትና ከፍተኛ የመጅሊስ አመራሮች አንዋር መስጅድ ተገኝተው የታፈኑ ወንድሞቻችን በሰላም እንዲለቀቁና የተጎዱት ሕክምና እንዲያገኙ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተነጋገሩ ነው።
በኦሮሚያ ክልል ሸገር ሲቲ እየተካሄደ ያለውን የመስጅድ ማፍረስ ዘመቻ አስመልክቶ በስልጤ ዞን የዳሎቻ ከተማ ሙስሊሞች ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።
ሰጋጆችን ገደ'ሏቸው‼
===============
✍ የኢትዮጵያ መንግስት የጸጥታ ኃይሎች ወደ አንዋር መስጅድ ካኪና ሙሶላ ይዘው ሃገር ሰላም ብለው ባዶ እጃቸውን የገቡ ሰላማዊ ሰጋጆችን፤ ሶላታቸውን ከጨረሱ በኋላ ሱንና እንኳ እንዲሰግዱ ሳይፈቅዱላቸው ነበር ቀድመው በተዘጋጁበት ቀላልና ከባድ የጦር መሳሪያ ታግዘው የጥይት እሩምታ የከፈቱባቸው።
ሰላታቸውን ሰግደው በሰላም እየተመለሱ በነበሩ ሙስሊሞች ላይ የተፈፀመውን ጭፍጨፋ አጥብቀን እናወግዛለን!
#ሰጋጁን_ገደሉት
#የአንዋርመስጂድጭፍጨፋ
#ሙስሊምጠልነት
#ኢስላምጠልነት
#AnwarMsjidMassacre
#Islamophobia
#EthiopianMuslimsUnderAttack
|| CC
t.me/ReshadIbnuMuzemil
አሁንም ይታሰብበት‼
===============
✍ በአንዋር መስጅድ ውስጥ የሚገኙ ወንድምና እህቶች በር ተቆልፎባቸው ውስጥ ላይ ይገኛሉ።
በሌላ በኩል ገዳ'ዩና ደብዳቢው ኃይል በርካታ አውቶቢሶችን አዘጋጅቷል። ትንሽ መሸት ሲል ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን በጅምላ አፍሶ ወደ በርሃ በመውሰድ የእስር ሰቀቀን በማቅመስ ሞራላቸውንና አካላቸውን ለመጉዳት ተሰናድቷል።
በተጫማሪም መስጂዱ የሚገኙ አባቶች በጭሱ ምክንያት እየደከሙ ነው። ደም የፈሰሳቸውም ራሳቸውን እየሳቱ ነው። የግል አምቡላንስ እንዳይገባ ተከልክሏል። በመርካቶ ዙሪያ ያሉ መስጂዶች ከበባ ላይ ናቸው። መርካቶና አካባቢው ላይ ያሉ ወጣቶች እየተያዙ ነው። መስጂድ ውስጥ ያሉትን አፍሰው ለመጫን ከታች እንደምትመለከቱት ባዶ ባሶች ተደርድረዋል።
ሰዓቱ ሳይሄድ የሚመለከተው አካል በተለይ የመጅሊስ ሰዎች በአስቸኳይ ለታገቱት ሙስሊሞች መፍትሄ ሊያፈላልጉ ይገባል።
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት
|| CC
t.me/ReshadIbnuMuzemil
ትኩረት‼
=======
✍ በአንዋር መስጅድ ውስጥ የግቢው በር ተቆልፎባቸው ታፍነው የሚገኙ ከ2000 በላይ ሙስሊሞች አሉ። ከተለያዩ አካባቢዎች የጸጥታ አካላት ተሰባስበው እየከበቧቸው ነው። በውስጣቸው ጠቋሚዎችን አስገብተው በርካታ ወጣቶችን እያፈሱ ይገኛሉ።
ወቅቱ ከመሸ ደግሞ በጅምላ አፍሰው ለመውሰድ በዝግጅት ላይ እንዳሉ ከውስጥ የሚወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ።
አምቡላንሶች ወደ አካባቢው ቢደርሱም ቁስለኞችን ገብተው ማውጣት አልቻሉም። ወደ አንዋር መስጅድ የሚወስዱ መንገዶች ዙሪያውን ስለተከበቡ፤ ቁስለኞችን ማሳከም አልተቻለም።
የፌዴራልና የአዲስ አበባ መጅሊሶች በህብረት ተገቢውን ንግግር በማድረግ የታገኑ ወንድሞቻችን ታፍሰው ሳያልቁ ሊደርሱላቸው ይገባል። ቁስለኞችም የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ሊደረግ ይገባል። የሟቾች ሬሳም ያልተነሳው ሊነሳ ይገባል።
ሰዓት ሳይመሽ የሚመለከታችሁ አካላት አስቸኳይ መፍትሄ እንዲገኝ ልታደርጉ ይገባል።
♠
Cc:
===
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት
||
t.me/ReshadIbnuMuzemil
በኦሮሚያ ክልል ሸገር ሲቲ እየተካሄደ ያለውን የመስጅድ ማፍረስ ዘመቻ አስመልክቶ የሐረር ከተማ ሙስሊሞች ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።
