es
Feedback
Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

Ir al canal en Telegram

● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸

Mostrar más
213
Suscriptores
Sin datos24 horas
-17 días
-430 días
Archivo de publicaciones
በኦሮሚያ ክልል ሸገር ሲቲ እየተካሄደ ያለውን የመስጅድ ማፍረስ ዘመቻ አስመልክቶ የዶዶላ ከተማ ሙስሊሞች ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።
በኦሮሚያ ክልል ሸገር ሲቲ እየተካሄደ ያለውን የመስጅድ ማፍረስ ዘመቻ አስመልክቶ የዶዶላ ከተማ ሙስሊሞች ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

«አስቸኳይ መልዕክት ለመንግስት የጸጥታ ኃይሎች‼️ በታላቁ አንዋር መስጂድ የጁምዓ ሰላቱን ለመስገድ ከቤቱ የወጣን እና በመስጂድ ያለን ንፁሃን ህዝበ ሙስሊም ላይ ያለምንም ርህራሄ በጥይት የሀይል እርምጃ መውሰድ ኢ ሰብዓዊ ተግባር ነው:: ባዶ እጁን ለሰላት በወጡ ንፁሀን ላይ እየተወሰደ ያለውን የኃይል እርምጃ የፀጥታ ኃይሎች ያቆሙ ዘንድ አሳስባለሁ። በመስጂዱ ተጠልለው የሚገኙ እና ያለህራሄ በጥይት ተመትተው በመስጂዱ ውስጥ እና ዙሪያውን ወድቀው የሚገኙት ወንድሞቻችን በአስቸኳይ ወደ ህክምና ቦታ ይወሰዱ ዘንድ አምቡላንስ ወደ ቦታው እንዲገባ መንገዱን ክፍት ልታደርጉ ይገባል።» ©: ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ

ትናንት መጅሊስ ለዛሬ ተቃውሞ የለም ሲለን ያቋቋማቸው ዘጠኝ ኮሚቴዎች ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር እያደረጉት ያለው ውይይት ጥሩ ውጤት ያመጣል ብለን ተስፋን ሰንቀን፣ ረብሻን ፈርተን፣ ሁከት
ትናንት መጅሊስ ለዛሬ ተቃውሞ የለም ሲለን ያቋቋማቸው ዘጠኝ ኮሚቴዎች ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር እያደረጉት ያለው ውይይት ጥሩ ውጤት ያመጣል ብለን ተስፋን ሰንቀን፣ ረብሻን ፈርተን፣ ሁከት ላለመቀስቀስ ነበር ዛሬ ተቃውሞ የለም ብለን በተደጋጋሚ እየተሰደብን ስንወተውት የነበረው። የመንግስት ኃይሎች ግን ተቃውሞ ቢኖርም ባይኖርም ለመግደል አቅደው፣ ለሳምንት ያክል ተዘጋጅተው ነበርና የወጡት፤ እንኳን ሊቃወሙ  ሰግደው ባልጨረሱ ወንድሞችና እህቶች ላይ የጥይት እሩምታ በአንዋር መስጅድ ከፍተው የቻሉትን ገ'ደሉ፣ ደበደቡ፣ አፈኑ። ትናንት ተቃውሞ ያለን መጅሊስ ቢያንስ አሁን በአንዋር መስጅድ የታፈኑትን ሙስሊሞች ያስለቅቅልን።

🚨 URGENT ALERT 🚨 🕌 Muslims Under Attack at Anwar Masjid 🕌 We are receiving distressing reports that the Ethiopian government forces are currently launching a violent assault on Anwar Masjid, targeting innocent Muslims. The situation is critical and demands immediate attention. Eyewitnesses report that without any justification or legal basis, security forces have unleashed a barrage of gunfire upon defenseless Muslims, including women and children. The number of casualties remains unconfirmed, but there are reports of numerous fatalities and a large number of innocent Muslims left severely injured. The sanctity of a place of worship is being violated as we speak. It is an unimaginable act of aggression against a peaceful community seeking solace and spiritual refuge. We urgently call upon the international community, human rights organizations, and all people of conscience to take immediate action. The world must be made aware of this appalling atrocity, and pressure must be applied to ensure the safety and protection of innocent lives. It is our moral duty to share this message far and wide across social media platforms. Let us unite in solidarity, raising our collective voice against these senseless acts of violence and oppression. No one should ever have to fear for their lives simply because of their faith. We urge governments, diplomats, and humanitarian agencies to intervene swiftly and put an end to this horrifying assault. Lives are hanging in the balance, and time is of the essence. Please share this urgent message with your networks, friends, and family. Together, we can make a difference and bring attention to this dire situation. Let us stand together for justice, peace, and the protection of fundamental human rights. #AnwarMasjidAttack #Ethiopia #UrgentHelpNeeded #HumanRights #StandForJustice

ያሳዝናል‼ ======== ✍ በአንዋር መስጅድ በዛሬው ዕለት የተካሄደ ምንም አይነት ተቃውሞ ባይኖርም፤ ደም የጠማቸው የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ወደ ህዝቡ ቀጥታ የጦር መሳሪያ እየተኮሱ እንደሆነ በአ
+1
ያሳዝናል‼ ======== ✍ በአንዋር መስጅድ በዛሬው ዕለት የተካሄደ ምንም አይነት ተቃውሞ ባይኖርም፤ ደም የጠማቸው የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ወደ ህዝቡ ቀጥታ የጦር መሳሪያ እየተኮሱ እንደሆነ በአካባቢው ያሉ ሰዎች ገልጸዋል። እስካሁን ቁጥራቸው በቅጡ ያልታወቁ ሙስሊሞች መሞታቸውንና በርካታ ሰዎችም መጎዳታቸውን አብረው ገልጸዋል። የጸጥታ ኃይሎቹ ዙሪያውን ከበው እየተኮሱ ስለሆነ ተጎጂዎች ሕክምና እንዲያገኙ እንኳ ማድረግ አልተቻለም። ጥቃቱ ወደ ሴቶች መስጅድም የዘለቀ ሲሆን ሴት እህቶች ላይም የጸጥታ አካሉ የጥይት እሩምታ ከፍቷል። ዝርዝሩን እየተከታተልን ሲሆን መረጃዎችን ወደናንተ የምናድርስ ይሆናል። Murad Tadesse t.me/ReshadIbnuMuzemil

ከድር መርቱ አሁንም ብቅ ብሏል!! ሙስሊም ዘፋኝ ሊሆን፣ ወንጀል ሊሰራ ወዘተ ይችላል! ጉዳዩም ከሰውየው እና ከጌታው ጋር ነው። እስልምና ሲጠቃ፣ ሙስሊሞች ሲነኩ፣ መስጂዶች ሲፈርሱ ግን የፈለገ ቢሆን የትኛውም ሙስሊም ዝም አይልም!!! የሀይማኖት ተቆርቋሪነትን ሊገድበው የሚችል ምንም ነገር የለም!!! ወንድማችን ከድር መርቱ ይህን በተደጋጋሚ በተግባር አሳይቶናል!!! ኦሮሞነት ከእስልምና በላይ አይደለም!! ኦሮሞም ሆነ ጉራጌ፣ አማራም ሆነ ትግሬ ስልጤም ሆነ ወላይታ፣ አፋርም ሆነ ሶማሌ ... ሙስሊም መሆኑ ብቻ ወንድምህ ያደርገዋል!!! ከኢስላም ወንድማማችነት በመቀጠል ደግሞ ዘሩ ማንም ይሁን ምን ሰው ሰው በመሆኑ ብቻ የሰብአዊነት ክብሩ የተጠበቀ ሊሆን የተገባ ነው። "ያፈረስነው የስልጤና ጉራጌ መስጂድ እንጂ የኦሮሞ አይደለም" የሚል እውር ጴንጤ ፖለቲከኛ የፈለገበት ኢስላምን መዋጋት እንጂ ፈፅሞ ከ"ኦሮሞ ህዝብ ነፃነት" ጋር ግንኙነት የለውም። ከድር መርቱ ትክክለኛ ኦሮመነትን በተግባር ያሳየክ ወንድማችን ደግመን እናመሰግንካለን!!! #በኔ_ዘመን_መስጂድ_የፈረሰበት_ትውልድ_ሆኜ_ጥቁር_ታሪክ_ለትውልድ_አላስተላልፍም

Thank you AbdeenTube‼

Injustice Prevails in Addis Ababa's Merkato Market‼ ======================================== ✍ Today, we bring your attention to a distressing development in Ethiopia. The Ethiopian government has taken the extreme measure of prohibiting commercial activities in Merkato, a renowned market center in Addis Ababa. This action is a direct result of the government's fear of Muslim protesters following today's Friday prayer at Anwar Mosque and other mosques in the area. This decision to forcefully close down businesses demonstrates a clear infringement on the rights of the people and the principles of economic freedom. By imposing these restrictions, the government is attempting to suppress the voices of Muslim protesters who have been peacefully advocating against the demolition of over 20 mosques in Sheger City, located in the Oromia regional state surrounding the capital, Addis Ababa. Last week, during the Friday prayer at Anwar Mosque, our fellow Muslims gathered to express their concerns and opposition to the wanton destruction of our sacred places of worship. Tragically, government security forces responded with excessive violence, fatally shooting two young Muslims and causing injuries to numerous innocent individuals. It is with deep sorrow and concern that we witness the repetition of this brutal action against our community during today's Friday prayer. We firmly condemn the abuse of power and the use of excessive force against peaceful protesters. Such actions not only violate our fundamental rights to freedom of expression and assembly but also perpetuate a cycle of injustice and oppression. It is a stark reminder that true justice lies in halting the demolitions and respecting the religious and cultural rights of all citizens. We call upon the international community to take note of these grave violations and to stand with the Ethiopian Muslim community. Share this message, raise awareness, and use your platform to demand an end to the destruction of our mosques and the mistreatment of innocent civilians. Let our voices unite in solidarity, transcending boundaries and differences, as we advocate for justice, peace, and religious freedom. Together, we can work towards a society that upholds the rights and dignity of all individuals. #JusticeForEthiopianMuslims #StopMosqueDemolitions #StandAgainstInjustice Cc: === CNN CNN International Al Jazeera Channel - قناة الجزيرة FRANCE 24 Reuters BBC News عربي CGTN RT BBC News Africa The Washington Times The New York Times The Telegraph ABC || Murad_Tadessa t.me/ReshadIbnuMuzemil

ነጃሺ ኢትዮጵያን ካናዳውያን በቶሮንቶ ያወጣው መግለጫ t.me/ReshadIbnuMuzemil
ነጃሺ ኢትዮጵያን ካናዳውያን በቶሮንቶ ያወጣው መግለጫ t.me/ReshadIbnuMuzemil

ነገ በአዲስ አበባ ከተማ ተቃውሞ አይኖርም‼ ============================== (ይህ ብልህነትና ሌላ የተቃውሞ ስልት እንጂ ፍርሃት ስላልሆነ አምናችሁበት ተግብሩት። መልዕክቱንም ላልሰሙ አሰሙ። ያልተጠናና የተናጠል ትግል ላልተገባ ዋጋ መክፈል ይዳርጋል፤ የጠላት መጠቀሚያ ያደርጋል፣ ረጅም ጉዞን ይቀጫል። በስሜትና በእልህ ሳይሆን በስሌትና ጥቅምን ከጉዳት በማመዛዘን እንጓዝ።) || ✍ በሸገር ሲቲ እየተካሄደ ያለው መስጂዶችን የማፍረስ ዘመቻም ሆነ ባለፈው ጁምዓ ይህን ግፍ በሰላማዊ መንገድ በተቃወሙ ዜጎች ላይ በአንዋር መስጂድና አከባቢው የተፈፀመውን ግድያ እና የመብት ጥሰት ተከትሎ ከፍተኛ የህዝብ ቁጣ እየተቀጣጠለ ይገኛል። በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎችም ሰላማዊ ተቃውሞዎች ተደርገዋል። ሆኖም ይህ የህዝብ ቁጣ በአግባቡ ካልተስተናገደና ወደተናበበ ትግል ካልተቀየረ መልሶ ህዝበ ሙስሊሙን ሊጎዳ ወደሚችል አቅጣጫ እንዳይሄድ ያሰጋል። ሌላ አላማ ባላቸው አካላት የሚጠለፍበትንም ሆነ ተቃውሞውን ለማፈን ለሚፈልገው የጸጥታ ኃይል ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል። ለምሳሌ፦ በመዲናችን አዲስ አበባ እንደ ባለፈው ሳምንት ያልተቀናጀ ተቃውሞ የሚካሄድ ከሆነ የመንግስት ፀጥታ ኃይሎች ትግሉን ከመነሻው ለማፈን ላቀዱት ከፍተኛ የጥቃት ወጥመድ ውስጥ እንዳንገባ ያሰጋል። ከዚህም በተጨማሪ ሀገራችንም ሆነ ቀጠናው ላይ ያለው ውስብስብ የፀጥታ ተጨባጭ እንዲሁም ሙስሊሙን ከፊት በማድረግ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎቻችንን መጠቀሚያ ለማድረግ ያለሙ ተጨባጭ እንቅስቃሴዎችን ታሳቢ በማድረግ አላስፈላጊ መስዕዋትነቶችን መከላከል ያስፈልጋል። ይህን ስንል ምንም አይነት የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች አይኖሩም ማለት አልያም ግፉ ሳይቆም ትግላችንን እናቆማለን ማለት ሳይሆን ህዝባችን ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት መቀነስ ያማከለ፣ የተጠና እና አዋጭ ትግል እናደርጋለን ማለት ነው። በዚህም መሰረት በነገው ጁሙዓህ አዲስ አበባ ላይ ምንም አይነት ተቃውሞ የለም። በምትኩ በየሆስፒታሉ እና እስር ቤት ያሉ ወገኖቻችንን በመዘየር እና በመደገፍ የትግላችንን ቀጣይነት እናሳያለን። በተጨማሪ በተመረጡ የክፍለ ሀገር ከተሞች ከጁሙዓህ ሰላት በኋላ በተክቢራ ተቃውሟችንን እንገልፃለን። መሰጂዶቻችንን በግፍ ማፍረስ ቁሞ፣ የፈረሱትም ዳግም የሚሰሩበት ሁኔታ ካልተመቻቸ፤ በመሪዎቻችን ለሚጠራው ሀገር- አቀፍ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍና ሁሉን አቀፍ ትግል እየተዘጋጀን እንቆያለን። በአዲስ አበባ መቼ ተቃውሞ እንደሚኖር በቅርቡ የምናሳውቅ ይሆናል። #ሸገርሲቲ #ሙስሊም_ጠልነት #IslamophobiaInEthiopia #ShegerCity #StopMosqueDemolition #ReligiousFreedomInEthiopia || t.me/ReshadIbnuMuzemil

4/በአንዋር መስጂድ የተደረገውን ተቃውሞ ተከትሎ የተፈፀመውን የንፁሃን ዜጎች ግድያ ሁኔታና፣ ከቤት ማፍረስ ጋር ተያይዞ በተለያዩ የሸገር ከተማ ቦታዎች በመንግስት አካላት የተፈፀሙ ግድያዎች በገለልተኛ አካል እንዲጣራና የኃይል እርምጃውን የፈፀሙ የፀጥታ አካላት ላይ መንግስት ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ፣ ስለሁኔታውም ለህዝቡ ግልፅ ማብራሪያ እንዲሰጥ እንጠይቃለን። 5/ህዝባችንም ያለ አግባብ በሚነዛበት የከፋፋዮች ፕሮፓጋንዳ ሳይደናገር፣ እንደተለመደው አንድነቱንና ከሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ጋር ያለውን የወንድማማችነት መልካም እሴቱን ጠብቆ እንዲቆይ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ግንቦት 23 ቀን 2015 ዓም ፊንፊኔ፣ ኦሮሚያ t.me/ReshadIbnuMuzemil

የኦሮሞ ፌደራል ኮንግረስ ድርጂት(ኦፌኮ) በሸገር ሲቲ ስለ ፈረሱ ቤተዕምነቶች መግለጫ አወጣ!! በሸገር ከተማ እየተካሄደ ባለው የግል ቤትና የእምነት ተቋማት ቤቶች ማፍረስ ተግባር፣ እንዲሁም የንፁሃን ዜጎች ግድያ አስመልክቶ ከኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) የተሰጠ መግለጫ ======== "ህገ-ወጥ አሰራርን ተከትሎ ህግን ማስከበር አይቻልም" * ከጥቂት ወራት ወዲህ በኦሮሚያ ክልል የሸገር ከተማ መቋቋምን ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ የግለሰቦች የመኖሪያ ቤትና የእምነት ተቋማት ቤቶች የማፍረስ ተግባር በስፋት እየተካሄደ ይገኛል።  በዚህም ምክንያት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ቤቶችና መንደሮች ሙሉ በሙሉ የፈረሱ ሲሆን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችም እንዲፈናቀሉና ቤት አልባ ሆነው ጎዳና ላይ እንዲወድቁ ተደርጓል። ቁጥራቸው የተለያየ ቢሆንም ብዛት ያላቸው መስጂዶች፣ ቤተ ክርስቲያኖችና፣ የፕሮቴስታንት ቤተ እምነቶች  የሃይማኖት መብቶችን በሚዳፈርና የአማኞችን ክብር በሚነካ መንገድ በአፍራሽ ግብረ ኃይል በግዳጅ እንዲፈርሱ ተደርገዋል። ይህ የቤትና የእምነት ተቋማት ማፍረስ ተግባር በመሬት ወረራ እና ህጋዊ ባልሆነ መንገድ የተገነቡ ቤቶችን እና የእምነት ተቋማት ቤቶች ላይ ብቻ  ያተኮረ፣ የከተማዋን ማስተር ፕላንና የህግ ማስከበር ተግባር እንደሆነ የከተማው እስተዳደር ይገልፃል። ነገር ግን ከነዋሪዎች ቅሬታ፣ ጉዳዩን በቅርበት ከተከታተሉና ምርመራ ካከናወኑ የኢትዮጲያ ሰብዓዊ መብት ተቋማት ሪፖርት እንዲሁም ፓርቲያችን በራሱ ካደረገው ግምገማ በመነሳት በሸገር ከተማ እየተካሄደ ያለው የቤትና የእምነት ተቋማት ቤቶች የማፍረስ ተግባር ህጋዊነትን ያልተከተለ፣ በተሳሳተ ፖሊሲ ላይ የተመሰረተ፣ ወቅታዊነትን ያላገናዘበ፣ አማራጭ መፍትሄዎችን ያላካተተ፣ በአድሏዊ መንገድ እየተፈፀመ ያለና ብዙ ሺህ ዜጎችን ለማህራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ያጋለጠ ህገወጥ ተግባር መሆኑን ተገንዝበናል። ይህ የግል ቤቶችና የእምነት ተቋማት ቤቶች ማፍረስ ተግባር  ሲጀመር በቂ ጥናትና ልየታ ያልተካሄደበት እና በህጋዊም ሆነ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ የተገነቡትን የግልና የእምነት ተቋማትን ቤቶች ሳይለይ በጅምላ እንዲፈርሱ ያደረገ ነው። ከዚህም ባለፈ የግል ቤትና የእምነት ተቋማት ቤቶችን ወደ ማፍረሱ ተገግባር ሳይካሄድ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የህብረተሰብ ክፍሎችና የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች ጋር ህጉ በሚያዘው መሰረት አስፈላጊውንና በቂ ውይይት ሳይደረግ፣ አስፈላጊው ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥበት በማን አለብኝነት እየተፈፀመ  ያለ ተግባር ነው። የግል ቤትና የእምነት ተቋማት ቤቶች የማፍረስ ተግባሩ አድሏዊነት፣ ሙስናና ብልሹ አሰራር የተስተዋለበት መሆኑን ከነዋሪዎች ቅሬታና ከሰብዓዊ መብት ተቋማት እየወጡ ካሉ መረጃዎች መገንዘብ ተችሏል። ኦፌኮ እንደ ፓርቲ ህገወጥ የመሬት ወረራ መስፋፋትን የሚቃወም ሲሆን፣ የከተማ መሪ እቅድን ያልተከተሉ ህገወጥ ቤቶች መገንባታቸውንም አይደግፍም። ጉዳዩን አሳሳቢ የሚያደርገው ግን መንግስት በህገመንግስቱና በአለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች የተረጋገጡትን ዜጎች በቂ የመኖሪያ ቤትና የቤት መስሪያ ቦታ ከሙስናና ከተንዛዛ ቢሮክራሲያዊ አሰራር በፀዳ መልኩ የማግኘት መብትን ሳያከብርና መንግስታዊ ግዴታውን ሳይወጣና ህጋዊ መስመሮችን በአግባቡ ሳይዘረጋ የተወሰደ  ግብታዊ እርምጃ መሆኑ ነው። የመሬት አስተዳደር ፖሊሲው ግልፅነት የጎደለውና ለሙስናና ብልሹ አሰራር የተጋለጠ ነው። መሬት በህገመንግስቱ መሠረት የህዝብና የመንግሰት ነው ቢባልም በተግባር ግን መሬት የገዢው ፓርቲና የባለሟሎቹ የግል መጠቀሚያ ሆኗል። መንግስት ፍትሃዊ የመሬት አስተዳደርና ምቹ አሰራር ያለመዘርጋቱ ዜጎች ኢመደበኛ መንገድ እንዲከተሉ አስገድዷል የሚል እምነት አለን። በህጋዊ መንገድ የቤት መስሪያ ቦታ ማግኘት ያልቻሉትና የአንገት ማስገቢያ በማጣት ወደ ኢመደበኛ ተግባራት የገቡት ላይ ህጋዊነት በጎደለው መንገድ እርምጃ መውሰድ ከሞራልም ከህግም አንፃር ተቀባይነት ያሌለው ነው። ከዚህም በላይ ዛሬ ህገወጥ ተብለው እንዲፈርሱ እየተደረጉ ያሉ የግልና የእምነት ተቋማት ቤቶች ግንባታ ላይ የመንግሰት አስተዳደር አካላት ቀጥተኛና ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ የተባበሩና ተሳታፊ ሆነው ሳለ፤ በነዚህ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ ሳይወስዱ ቤቶቹን ወደ ማፍረስ መገባቱ የራስን ስህተት በህጋዊነት ሽፋን ለመደበቅ የሚደረግ እንቅስቃሴ እንደሆነ እንገነዘባለን። በዚህም ምክንያት ህዝቡ ላይ ከፍተኛ የሆነ ቅሬታ የፈጠረና በሂደቱ ላይ ተቃውሞ እንዲያነሳ እያደረገው ይገኛል። ከቤት ማፍረስ ተግባር ጋር ተያይዞ በሚፈጠሩ አንባጓሮዎች በሸገር ከተማ የተለያዩ ቦታዎች ብዙ ሰዎች በመንግሰት ኃይሎች እንደተገደሉ በቂ መረጃዎች ተገኝተዋል። የሸገር ከተማ እያካሄደ ባለው የሃይማኖት ተቋማት ቤቶች ማፍረስ ምክንያት የሙስሊሙ ህዝብ ያለውን ተቃውሞ የፊንፊኔን ከተማን ጨምሮ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች በሰላማዊ መንገድ አሰምቷል። ይሁን እንጂ ባለፈው አርብ ግንቦት 18 ቀን 2015 ዓም ሙስሊሙ ህዝብ ያለውን ተቃውሞ በአንዋር መስጂድ ውስጥ በመሆን በሰላማዊ መንገድ በማሰማት ላይ እያለ የታጠቁ የመንግሰት የፀጥታ ኃይሎች መስጂድ ቅፅር ግቢ ጥሰው በመግባት ከፈፀሙት ትንኮሳና ጥቃት ጋር ተያይዞ የሁለት ንፁሃን ሰዎች ህይወት አልፏል። ይህ የመንግስት ፀጥታ ኃይሎች ተግባር አላስፈላጊና የሃይማኖት ተቋማትንና የእምነቱን ተከታዮችን ክብር ያዋረደ፣ ኃላፈነት የጎደለው የኃይል ተግባር ነው። ኦፌኮ በአንዋር መስጂድ ከተካሄደው ተቃውሞ ጋር በተያያዘ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈፀመውን ግድያ፣ አካላዊ ጉዳትና እስራት በፅኑ ያወግዛል። በዚህም ህይወታቸውን ላጡና የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን የተሰማውን ጥልቅ ኃዘን እየገለፀ ለሟቾች ቤተሰብና ለመላው ሙስሊሙ ህዝብ መፅናናትን ይመኛል። ከዚህ ጋር ተያይዞ በብልፅግና ፓርቲ መንግስት የአስተዳደር ግድፈትና በተቋማቱ የተወሰዱ ህገወጥ ተግባራትን አስታኮ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ያልተገባ የስም የማጥፋት ዘመቻ እየተካሄደ ያለ ሲሆን የጉዳዩንም ቅርፅ በመለወጥ ለራሳቸው የፖለቲካ አላማ ለማዋል ያሰፈሰፉ ኃይሎች ተስተውለዋል። ይህን አጋጣሚ በመጠቀምም የኦሮሞን ህዝብ በሃይማኖትና በጎሳ ለመከፋፈል ከፍተኛና የተቀናጀ ጥረት እያደረጉ ያሉ ኃይሎችም አሉ። የነዚህ ኃይሎች ዓላማ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ግጭቶችና አለመግባባቶች እንዲስፋፉ በማድረግ የህዝብን አንድነትና ወንድማማችነት ማፍረስ ስለሆነ ህዝባችን በንቃት እንዲከታተላቸው እናሳስባለን። በመጨረሻም  በህዝቡ ዘንድ የተፈጠረውን ቅሬታ ለመፍታትና ለችግሩም ዘላቂ መፍትሄ ለማበጀት፣ እዲሁም ከግድያው ጋር የታይዞ የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ:- 1/የሸገር ከተማ አስተዳደርና የኦሮሚያ ክልል መንግስት የግልቤቶችንና የእምነት ተቋማት ቤቶች ማፍረሱን ተግባር በአፋጣኝ አቁሞ በህጋዊነቱና አተገባበሩ  ዙሪያ እየተስተዋሉ ያሉ ክፍተቶችን እንደገና እንዲፈትሽ፣ 2/ሁኔታዎች ከአሁኑ በላይ ሳይወሳሰቡና የባሰ አደጋ ሳያስከትሉ ከህዝቡና የሃይማኖት ተቋማት ኃላፊዎች ጋርም በመሆን በውይይት መፍትሄ እንዲያበጅ ጥሪ እናቀርባለን። 3/የሸገር ከተማን ጨምሮ የከተሞች ልማትና መሪ እቅዶች የህዝቡን የመኖሪያ ቤት የማግኘት  ሰብዓዊ መብትና የሃይማኖት ተቋማትን የማደራጀት መብት ባገናዘበ መልኩ ብዝሃነትን ባከበረና ፍትሃዊነትን በተላበሰ መንገድ እንዲቀረፅ እንጠይቃለን።

🚨 Unjust Demolition of Mosques: Speak Out Against Injustice! 🕌💔 🔴 Injustice Unveiled: Condemning the Demolition of Mosques in Sheger City 🔴 Today, we are confronted with an appalling revelation from the Oromia Communication Bureau . The intentional demolishing of numerous mosques in Sheger City has been officially confirmed. This act of cultural and religious oppression cannot be overlooked or justified. Government official Hailu Adugna's statements, labeling those who criticize the demolitions as "fundamentalists" and "terrorists," are deeply alarming. Such rhetoric seeks to silence dissent and undermines the right to express legitimate concerns. It is a grave injustice to tarnish the reputation of peaceful individuals who dare to question these demolitions. The demolition of mosques, sacred places of worship, is an assault on religious freedom and an attack on the cultural fabric of our society. The announcement that this destructive campaign will extend to over 600 cities is a chilling indication of the disregard for the rights and values of the Ethiopian people. Such actions not only breed resentment and discord but also perpetuate an environment of inequality and injustice. We must stand together to condemn this blatant violation of human rights. Silence is not an option when our brothers and sisters are subjected to such discrimination and persecution. We call upon the international community to raise their voices and demand an immediate halt to the demolitions, ensuring that religious freedom and cultural heritage are protected. Let us unite in solidarity, regardless of our differences, to denounce these injustices. We must shine a light on the truth, challenge the narrative of division, and demand accountability from those responsible. Only by working together can we strive for a just and inclusive society, where the rights of all individuals are respected and upheld. Share this message, raise awareness, and use the power of social media to demand justice for our fellow Ethiopians. Together, we can make a difference. #StopMosqueDemolitions #StandForReligiousFreedom #EthiopianUnity #ShegerCity ♠ Cc: === CNN International CNN FRANCE 24 Al Jazeera Channel - قناة الجزيرة BBC News عربي CGTN Reuters RT BBC News Africa The New York Times The Washington Times The Telegraph ABC || t.me/ReshadIbnuMuzemil

🔰 መንግስት የለምና! ጥሪ ለህዝቤ ነው - መንግስት የለምና፤ ሙስሊምን የሚጠላ - በጣም በዝቷልና፤ በኛው ተምሮ - በኛው ፈረጠመና፤ በሙስሊም ግድያ - በሙስሊም ጭቆና መስጂድ አፈረሱ - ጠጥተው መ
🔰 መንግስት የለምና! ጥሪ ለህዝቤ ነው - መንግስት የለምና፤ ሙስሊምን የሚጠላ - በጣም በዝቷልና፤ በኛው ተምሮ - በኛው ፈረጠመና፤ በሙስሊም ግድያ - በሙስሊም ጭቆና መስጂድ አፈረሱ - ጠጥተው መጡና። እኛው አሳድገን - ለመአረግ ባበቃን፤ ከተማ ባሸበረቅን - አኛው አልምተን በወንበር እንዲደላደል - እኛው በመረጥን፤ ብዙዎች ተቀጠፉ - እኛኑ እየገደሉን። መስጂዶች ፈረሱ - የሙስሊም ደም ፈሰሰ፤ ውስጣችን ቆሰለ - እንባችን ፈሰሰ፣ አዲስ የነበረው አሮጌ - በደም ተለወሰ፣ ግድያው *ፈረሳው - ይሀው ተባባሰ። በሁሉም ሁኔታ - ይጧጧፍ ትግሉ፤ እንግዲህ ይብቃችው - ሙስሊም አይግደሉ፤ ሰክረው በመጡ ጊዜ - መስጂድ አያፍርሱ፤ እኛን ይተውን - ብልግናቸውን ይንተራሱ። በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል t.me/ReshadMuzemil t.me/InspiresWorld fb.com/InspiresWorldWide Instagram.com/inspiresworldwide twitter.com/InspireWorldW

በእስልምና ዕምነት ተቋማት ላይ የሚፈጸም የመስጊድ ፈረሳና በዕምነቱ ተከታዮች ላይ የሚፈጸም የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ይቁም! የኢሰመጉ አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ-ግንቦት 23/2015 ዓ.ም ቻናላችንን
+1
በእስልምና ዕምነት ተቋማት ላይ የሚፈጸም የመስጊድ ፈረሳና በዕምነቱ ተከታዮች ላይ የሚፈጸም የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ይቁም! የኢሰመጉ አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ-ግንቦት 23/2015 ዓ.ም ቻናላችንን ለመቀላቀል ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይንኩ። 1. Telegram t.me/InspiresWorld 2. Facebook fb.com/InspiresWorldWide 3. Instagram Instagram.com/inspiresworldwide 4. Twitter twitter.com/InspireWorldW 5. YouTube www.youtube.com/@InspireWorldwide