Mereb Media- መረብ ሚዲያ
Ir al canal en Telegram
341
Suscriptores
+424 horas
+47 días
+430 días
Carga de datos en curso...
Canales Similares
Nube de Etiquetas
Sin datos
¿Algún problema? Por favor, actualice la página o contacte a nuestro gerente de soporte.
Menciones Entrantes y Salientes
---
---
---
---
---
---
Atraer Suscriptores
diciembre '24dic '24
diciembre '24
+13
en 2 canales
noviembre '24
+49
en 1 canales
Get PRO
octubre '24
+32
en 0 canales
Get PRO
septiembre '24
+62
en 0 canales
Get PRO
agosto '240
en 0 canales
Get PRO
julio '240
en 0 canales
Get PRO
junio '240
en 0 canales
Get PRO
mayo '240
en 0 canales
Get PRO
abril '240
en 0 canales
Get PRO
marzo '240
en 0 canales
Get PRO
febrero '240
en 0 canales
Get PRO
enero '240
en 0 canales
Get PRO
diciembre '23
+1
en 0 canales
Get PRO
noviembre '23
+7
en 0 canales
Get PRO
octubre '23
+331
en 0 canales
| Fecha | Crecimiento de Suscriptores | Menciones | Canales | |
| 09 diciembre | +2 | |||
| 08 diciembre | +2 | |||
| 07 diciembre | +3 | |||
| 06 diciembre | +3 | |||
| 05 diciembre | 0 | |||
| 04 diciembre | 0 | |||
| 03 diciembre | 0 | |||
| 02 diciembre | 0 | |||
| 01 diciembre | +3 |
Publicaciones del Canal
| 2 | በደቡብ ጎንደር ዞን የመና ቀጣዋ ወረዳና የአከባቢው አርሶ አደሮች የፋኖ አመራሮች በውጊያ ወቅት ከፊት እንዳንሰለፍ እየከለከሉን ነው ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ።
ፋኖ ልጆቻችን ከፊት ለፊት ተሰልፈው ከጠላት ጋር ሲተናነቁ እኛ አርሶ አደሮች ከኋላ እንድንሰለፍ የተደረገበት ምክኒያት አግባብነት የለውም ሲሉ አርሶ አደሮቹ ተናግረዋል።
በደቡብ ጎንደር ዞን ከአንድ ዓመት በላይ በፋኖ እየተዳደረ ባለው የመና መቀጣዋ ወረዳና የአከባቢው አርሶ አደሮች በውጊያ ወቅት ከፊት እንዳንሰለፍ በፋኖ የጦር ዘመቻ አመራሮች እየተከለከልን ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ከመረብ ሚዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል።
በውጊያ ወቅት የፋኖ አባላት ብቻ ከፊት ተሰልፈው እየተዋደቁ ነው የሚሉት አርሶ አደሮቹ፡ እኛም ከፊት ለፊት ተሰልፈን መዋጋት አለብን፣ ምሽግ ሰበራ ላይም መሳተፍ አለብን በሚል ብንሰለፍም የፋኖ አባላቱ ይበቃሉ እናንተ ወደ ኋላ ሁኑ በሚል የፋኖ አዛዦች ከልክለውናል ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
ከመረብ ሚዲያ ጋር ቆይታ ያደረጉት አርሶ አደሮቹ፡ አገዛዙ አማራን ለማጥፋት የከፈተውን ጦርነት ለመመከት የፋኖ አባላቱ ከፊት ለፊት ተሰልፈው እየተዋጉ ባለበት እኛ አርሶ አደሮችም ከፊት እንዳንሰለፍ የተከለከልንበትና የኋላ ደጀን ብቻ እንድንሆን የተደረግንበት ምክኒያት አግባብነት የለውም ብለዋል።
አርሶ አደሮቹ አክለውም፡ "ይህ አገዛዝ ወጣት አይልም ሽማግሌ አይልም፣ አርሶ አደር ወይም ተማሪ በሚል አይመርጥም፣ አማራን እንደ ህዝብ ነው ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳው" ያሉ ሲሆን ይሄንን አደጋ ለመመከት የፋኖ አባላቱ ከፊት ለፊት ተሰልፈው ጠላትን ድባቅ በመምታት ሲያሸንፉ ድላቸውን እንደምንጋራው ሁሉ እኛም እኩል ተሰልፈን ሞታቸውንም መጋራት አለብን ብለዋል።
እንደ አማራ የተደቀነብንን አደጋ ለመመከት ሁላችንም በጋራ እኩል መሰለፍ አለብን እንጂ አንዱ ሲሞት አንዱ ዳር ቆሞ መመልከት የለብትም ሲሉ አርሶ አደሮቹ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
አርሶ አደሮቹ ባነሱት ቅሬታ ዙሪያ ለመረብ ሚዲያ ምላሽ የሰጠው በአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ የእቴጌ ጣይቱ ክ/ጦር ቃል አቀባይ የሆነው ፋኖ መምህር መልካሙ ጣሴ፡ አርሶ አደሮቹ ከፊት አሰልፉን በሚል በተደጋጋሚ ጥያቄ እንደሚያቀርቡ ጠቅሶ፡ ከጠላት ኃይል ደካማነትና ከወገን ኃይል ብዛትና ጥንካሬ አንፃር ለጊዜው አርሶ አደሩ ከፊት ለፊት ተሰልፎ ከሚዋጋ ይልቅ የኋላ ደጀን ሆኖ ይቆይ በሚል እንደ ክፍለጦር ውሳኔ ላይ ተደርሶበት ነው ብሏል።
"አሁን ላይ ግዙፍ የሆነ የሙሉ ጊዜ ተዋጊ ጦር ገንብተናል፣ የጠላትን ኃይል አስጊ የማይሆንበት ደረጃ ላይ አድርሰነዋል" ሲል የገለፀው ቃል አቀባዩ፡ በዚህ ሁኔታ አርሶ አደሩ ከፊት ለፊት ሆኖ ውጊያ ላይ ከሚገባ ይልቅ የኋላ ደጀን በመሆን ጎን ለጎን የግብርና ስራውን ቢያከናውን እንደ ህዝብ ይበልጥ ውጤታማ እንሆናለን በሚል ነው ከፊት ለፊት እንዳይገቡ የከለከልንበት ምክኒያት ሲል ምላሽ ሰቷል።
(ምስል የመናመቀጣዋ እና የደጋ መልዛ አርሶ አደሮች)
###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
የቴሌግራም 👉 https://t.me/MerebMedia24
ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803 | 189 |
| 3 | እማሆይ!
ሁለት ልጆቻቸው ጦር ግምባር ላይ ናቸው።
ልጆቻቸውን ለመጠየቅ የገብስ ቆሎአቸውን ቆልተው በነጠላቸው ጫፍ ቋጥረው ሁሌም በየወሩ አይቀሩም። ምሽግ ድረስ በመሄድ ልጆቻቸውን ስመው፣ ድል ከእናንተ ጋር ትሁን ብለው መርቀው ይመለሳሉ።
ጎንደር! ደጋ መልዛ
###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
የቴሌግራም 👉 https://t.me/MerebMedia24
ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803 | 196 |
| 4 | Sin texto... | 334 |
| 5 | እንደምን አረፈዳችሁ!
ጀግና እናስተዋውቃችሁ!
ፋኖ ረዴ አስቻለ ተካ ወይም በቅፅል ስሙ እምብብሽ ይባላል። መስማት የተሳነው ነው።
የደፈጣ ጥቃት ሊቀጠበብት ነው ይሉታል አብረውት ከምሽግ ውለው የሚያድሩት ጓዶቹ።
የትግል ጓዶቹ አክለውም፡ እልኸኛ ነው በአንድ ጥይት ሁለት ጠላት ካልጣለ ይበሳጫል፣ በአንድ ቦንብ አስር እና ከዛ በላይ የጠላት ኃይል ካልጣለ የተዋጋም አይመስለው ይላሉ።
ፋኖ ረዴ(እምብብሽ) የሰሜን ወሎ ዞን ዋና መቀመጫ በሆነችው ወልድያ ከተማ ጎንደር በር አከባቢ ትልቅ የሸቀጣሸቀጥ ማከፋፈያ ሱቅ ነበረው።ወልድያ ከተማ ላይ እሱን ያማያውቅ አልነበረም።በከተማዋ አሉ ከሚባሉ ትልልቅ ነጋዴዎች ተርታ የተሰለፈ የናጠጠ ነጋዴም ነበር።ባለትዳርና የሦስት ልጆች አባትም ነው።
የሕወሓት ቡድን በአማራ ሕዝብ ላይ ወረራ ሲከፍት ወረራውን ለመመከት የንግድ ሱቁን በመዝጋት ክላሹን ገዝቶ ምስራቅ አማራ ፋኖን ተቀላቀለ።
በወቅቱ በምስራቅ አማራ ፋኖና በአማራ ልዩ ኃይል መሪነት እንዲሁም በአገዛዙ ጥምር ጦር አጋዥነት ከደሴ እስከ ወልድያ፣ ከወልድያ እስከ ቆቦ፣ ከቆቦ እስከ በር ተክላይ ከባድ ትንቅንቅ ሲካሄድ ፋኖ እምብብሽ ከጓዶቹ ጋር በመሆን ታሪክ በወርቅ ቀለሙ የሚፅፈው አኩሪ ገድል ፈፅሟል።
ሁለተኛውን ዙር ወረራ ለመመከትም እንዲሁ ከምሽግ ምሽግ እየተወረወረ እጅን ባፍ የሚያስጭን ገድል፣ አጃኢብ የሚያስብል ጀብድ ሰርቷል።
ከተኩለሽ እስከ ገደባ፣ ከወንዳይ እስከ አቡሃይ ጋሪያ፣ከአዲስ ቅኝ እስከ ጎለሻ፣ ከአሳ መምቻ እስከ ጠበለት፣ ከበዋ ሚካኤል እስከ ንጉስ ጋሌ አቦ፣ ከዞብል እስከ ራማ፣ከዲኖ እስከ አማያ፣ ከቀዩ ጋሪያ እስከ ዲቢ፣ ከጎብየ እስከ ጉራ ወርቄ የነበሩ ምሽጎች የዚህን ጀግና ገድል መስክሩ ቢባሉ አፍ አውጥተው ይመሰክራል።
የሕወሓት ወራሪ ኃይል የከፈተው ወረራ ተቀለበሰ ከተባለ ወዲህ ገዢው ቡድን ሳይውል ሳያድር አፈሙዙን ወደ አማራ ሕዝብ በማዞሩ ፋኖ እምብብሽም ይሄንን መንግስት መር ዘር ማጥፋት ለመከላከል ዱር ቤቴ እንዳለ ቀረ።
ፋኖ እምብብሽ መውዜሩን ትዳር ካደረገ ቀናቶች ቀናቶችን እየፀነሱ፣ ወራቶች ወራትን እየወለዱ፣ በዓመታት ተተኩ። ፋኖ ብብሽ ጣቱን ከክላሹ ምላጭ ሳይለይ ዛሬም በምሽጉ እንደነገሰ ነው።
በዚህ አንድ አመት ውስጥ እንኳን የቃሊምና የደላንታ ተራሮች፣ የኮረታና የእዜት በር ጋሪያዎች፣ ሰንሰለታማዎቹ የግሽን ደብረ ከርቤ ተራሮችና የበሸሎ ሸለቆዎች፡የጊራና እና የውጫሌ ስፍራዎች የፋኖ እምብብሽን ጀግንነ፣ አልሞ አይስቴነት ጥንቅቅ አድርገው ያውቃሉ።
ፋኖ እምብብሽ በጨበጣ ውጊያ ከሚፈፅማቸው ጀብዱዎች በላይ በደፈጣ እና በምሽት ውጊያ የሚፈፅማቸው ገድሎች ትዕንግርት ናቸው ይላሉ የትግል ጓዶቹ።
ፋኖ እምብብሽ በሚሳተፍበት የደፈጣ ጥቃት ኦፕሬሽን፡ ለምስክርነት የሚተርፍ የጠላት ኃይል ይኖራል ብሎ ከማሰብ ከአምበሳ ጉሮሮ ሙዳ ስጋ መንጭቆ እንደማውጣት ነው ይላሉ።የማይታሰብ ነገር ነው።
እሱ በተሳተፈበት የደፈጣ ጥቃት በቅፅበት ልዩነት የጠላት ኃይል እንዳልነበረ ይሆናል፣ ሲንቀሳቀስበት የነበረው ተሽከርካሪም ዶግ አመድ ይሆናል።
ፋኖ እምብብሽ መስማት የተሳነው ቢሆንም ነገር ግን በውጊያ ወቅት ጥይት ከየት ወዴት እንደሚመጣ ጥንቅቅ አድርጎ የሚያውቅ ጀግና ነው። አብዛኻኛውን ጊዜ የምሽት ውጊያ ለሱ ሰርግና ምላሹ ነው ይባልለታል።
ፋኖ እምብብሽ ከሰሜኑ ጦርነት ጀምሮ አሁን እያደረገ እስካለበት ትግል ደርስ በተደጋጋሚ የቆሰለ ሲሆን፣ "የኔ መቁሰል አይደንቅም፣ ጓዶቼ ተሰውተዋል።እኔ የነሱን አላማ ከግብ ለማድረስ እስከመጨረሻዋ ህቅታ እታገላለሁ" የሚል ቃል ነው የምንጊዜም ምላሹ።
ፋኖ እምብብሽ በቅርብ የሚተኮስን የከባድ መሣሪያ ፍንዳታ በጥቂቱ ይሰማል።የፋኖ የሕክምና ባለሙያዎች እንደገለፁት በጆሮው ላይ የሚገጠም አጋዥ ማሽን ቢገኝለት በከፊል የመስማት እድል ይኖረዋል ብለዋል።
ቤቴን፣ ትዳሬን፣ ልጆቼን ሳይል ለአማራ ሕዝብ ነፃነት ሲል አንድያ ሕይወቱን አስይዞ ወጥቶ በዱር በገደሉ ለሚዋደቅ ጀግና፡ ለመስማት የሚያግዘው ጆሮ ላይ የሚገጠም ማሽን ለመግዛት ማን ወደ ኋላ ይላል?
ስለዚህ ከሃገር ውጭም ሆነ በሃገር ውስጥ የምትኖሩ የትግሉ ደጋፊ ወገኖች ይደር የማይባል የቤት ስራ ይሁናችሁ።
ለፋኖ ረዴ አስቻለ(እምብብሽ)ን ማስማት የሚያግዝ የጆሮ ማሽን ገዝቶ ለመስጠት የምታስቡ ልበቀና ሰዎች በአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ መቅደላ ፅናት ክ/ጦርን ማነጋገር ትችላላሁ።
###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
የቴሌግራም 👉 https://t.me/MerebMedia24
ዩቲዩብ👉
http://www.youtube.com/@Merebmedia%E1%88%98%E1%88%A8%E1%89%A5%E1%88%9A%E1%8B%B2%E1%8B%AB
ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803 | 300 |
| 6 | Sin texto... | 243 |
| 7 | በወልድያ ከተማ ሼክ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ ስቴዲየምና በማር ማቀነባበሪያ ካምፑ ሰፍሮ ከነበረው ሰሜን ምስራቅ ዕዝ ውስጥ በርካታ ወታደሮች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው በመውጣት ፋኖን መቀላቀላቸው ታወቀ።
ነሐሴ 14/2016 ዓ/ም በዋርካው ምሬ ወዳጆ በሚመራው አማራ ፋኖ በወሎ ሜካናይዝድ ክፍሉ የሞርተር ጥቃት በፈፀመበት በወልድያ ከተማ በሚገኘው በሼክ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ ስቴዲየምና በማር ማቀነባበሪያ ካምፑ ሰፍሮ ከነበረው ሰሜን ምስራቅ ዕዝ ውስጥ በርካታ ወታደሮች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን መቀላቀላቸውን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።
ወታደሮቹ ግፍን በመቃዎም ከነሙሉ ትጥቃቸው በመውጣት ፋኖን የተቀላቀሉት የትናንት በስቲያው ሞርተር ጥቃት ከመፈፀሙ ሁለትና ሦስት ቀናት ቀደም ብሎ መሆኑም ታውቋል።
ፋኖን የተቀላቀሉት ወታደሮች፡ አዛዦቻችን በሚሰጡት ትዕዛዝ በወልድያ ከተማና በዙሪያዋ የሚንገኙ ነዋሪዎች ላይ የሚፈፀመውን ግፍ መመልከት አልቻልንም፡ ህሊናችን ሰላም አጥቷል ያሉ ሲሆን ግፍን ተቃውመን ለወንድሞቻችን ይጠቅማል ያልነውን የጦር መሣሪያ መርጠን ይዘን ወጥተናል ሲሉ ከመረብ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልፀዋል።
በከተማዋ በተለይ በሼክ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ ስቴዲየምና ማር ማቀነባበሪያ ካምፕ ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው ንፁኋን በአሰቃቂ ሁኔታ ተረሽነው መቀበራቸውን የገለፁት ወታደሮቹ፡ ከሟቾቹ መካከል አብዛኻኞቹ እስካሁን ቤተሰቦቻቸው መርዶውን እንዳልሰሙ ገልፀዋል።
በስቴዲየሙ እና በማር ማቀነባበሪያ ካምፑ በአሰቃቂ ሁኔታ የሚገደሉት ንፁኋን ፋኖን ትደግፋላችሁ፣ ፋኖን የተቀላቀለ ወንድምና እህት እንዲሁም ልጅ አላችሁ በሚል በተለያየ ጊዜ በዞኑ ስር ከሚገኙ አከባቢዎች ታፍነው የሚመጡ ናቸው ብለዋል።
ከእስረኞቹ መካከል በግል ቂም የተነሳ በተሰጠባቸው የተሳሳተ ጥቆማ ለእስር ተዳርገው የሚገኙ መኖራቸውንም ወታደሮቹ ለመረብ ሚዲያ ገልፀዋል።
አሰቃቂ ግድያ የሚፈፀምባቸው ሰዎች በወታደራዊ አዛዦች የሚጠየቁትን የብር መጠን መክፈል ያልቻሉ እና ከዚህ ቀደም በተለያየ የውይይት መድረኮች ላይ ብልፅግና ፓርቲን ተችታችኋል የተባሉ ሰዎች መሆናቸውንም ወታደሮቹ ጨምረው ገልፀዋል።
ከመቶ ሺ ብር ጀምሮ እስከ ግማሽ ሚሊየን የሚጠየቁትን ክፍያ መክፈል የቻሉ ሰዎች ወድያው ከእስር ይለቀቃሉ፡ ነገር ግን ይሄንን የተጠየቁትን ገንዘብ መክፈል ያልቻሉ ሰዎች ግን ይረሸናሉ ነው የተባለው።
በተመሣሣይ ነሐሴ 14/2016 ዓ/ም የአማራ ፋኖ በወሎ ሜካናይዝድ ክፍሉ በሁለቱ ትላልቅ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ወታደር ካምፖች ላይ የሞርተር ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ በርካታ ወታደሮች ከነመሣሪያቸው የደረሱበት እንዳልታወቀ ተሰምቷል።
የትናንት በስቲያውን ግርግር ተጠቅመው ከነሙሉ ትጥቃቸው ከአሃዳቸው ከድተው የወጡት ወታደሮች ብዛታቸው ምን ያህል እንደሆነ በውል የታወቀ ነገር ባይኖርም የጠፉ ወታደሮችን ለማገኘት ቤት ለቤት አሰሳ ሲደረግ እንደነበር መረብ ሚዲያ በወልድያ ከተማ መኖሪያ ቤታቸው የተፈተሸ የጎንደር በር አከባቢ ነዋሪዎችን በማነጋገር ለማረጋገጥ ችሏል።
###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
የቴሌግራም 👉 https://t.me/MerebMedia24
ዩቲዩብ👉
http://www.youtube.com/@Merebmedia%E1%88%98%E1%88%A8%E1%89%A5%E1%88%9A%E1%8B%B2%E1%8B%AB
ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803 | 229 |
| 8 | Sin texto... | 210 |
| 9 | ሰበር ዜና!#
በራያ ቆቦ ወረዳ ከቆቦ ከተማ በቅርብ ርቀት አንታጉዶ በተባለ አከባቢ ሦስት ወጣቶች በመንግስት ፀጥታ ኃይሎች መገደላቸው ተሰምቷል።
ሦስቱም ወጣቶች የተገደሉት ዛሬ ነሐሴ 15/2016 ዓ/ም ረፋድ መሆኑንም የቆቦ ከተማ ነዋሪዎች ለመረብ ሚዲያ ገልፀዋል።
በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ ከሆርማት ወታደራዊ ካምፕ በቅርብ ርቀት ልዩ ስሙ አንታጉዶ በተባለ ስፍራ ዕድሜያቸው በሃያዎቹ መጀመሪያ የሚሆን ሦስት ወጣቶች በመንግስት ፀጥታ ኃይሎች መረሸናቸውን የአከባቢው ነዋሪዎች ለመረብ ሚዲያ ገልፀዋል።
ወጣቶቹ ከሁለት ቀናት በፊት ከዋጃ ከተማ ታፍነው በቆቦ ከተማ ዙሪያ በሚገኘው ሆርማት ወታደራዊ ካምፕ ላይ ታስረው የነበረ ሲሆን ዛሬ ማርፈጃውን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ነው ጣቢያችን ለማረጋገጥ የቻለው።
ከሳምንት በፊት ኤልሳ የተባለች ወጣት በራያ ቆቦ ከተማ ውስጥ በገዢው ቡድን ወታደሮች በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደለች ሲሆን በዕለቱ ታላቅ እህቷም ከነዚኸው የመንግስት ኃይሎች በተተኮሰባት ጥይት ቆስላ ወደ ሆስፒታል መወሰዷ ታውቋል።
በቆቦ ከተማና በዙሪያዋ ባሉ አከባቢዎች የሚኖሩ አርሶ አደሮች በአገዛዙ ኃይሎች እየታፈኑ ለማስፈቻ የሚሆን ከመቶ ሺ ብር ጀምሮ እየተጠየቀባቸው ሲሆን፡ ገንዘቡን መክፈል ያልቻሉ የፋኖ ደጋፊ ናቸው በሚል በአሰቃቂ ሁኔታ እንደሚገደሉ ነው መረብ ሚዲያ ካሰባሰበው መረጃ ለማረጋገጥ የቻለው።
የአገዛዙ ኃይል መንቀሳቀስ በማይችልባቸው ከቆቦ ከተማ ውጭ ያሉ የገጠር ቀበሌ ነዋሪዎችም ለገበያ እና ለሕክምና እንዲሁም ዘመድ ለመጠየቅ ወደ ቆቦ ከተማ ሲገቡ ኬላ ላይ እየተያዙ "ፋኖን ትቀልባላችሁ፣ መከላከያ ሰራዊት ከፋኖ ጋር ሲገጥም እገዛ አታደርጉም" እየተባሉ እንደሚታሰሩም ነው የተነገረው።
በዚህም ማህበረሰቡ ወጥቶ መግባት አለመቻሉ የተገለፀ ሲሆን፡ ይባስ ብሎ ቆቦ ከተማና ሆርማት ወታደራዊ ካምፕ በተጠመደ ከባድ መሣሪያ በከተማዋ ዙሪያ የሚገኙ አከባቢዎች ዘወትር እንደሚደበደቡም ነው ነዋሪዎቹ እየተፈፀመባቸው ያለውን ግፍ ለመረብ ሚዲያ የገለፁት።
(ምስል፦ከማህበራዊ ሚዲያ/ ቆቦ ከተማ/)
###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
የቴሌግራም 👉 https://t.me/MerebMedia24
ዩቲዩብ👉
http://www.youtube.com/@Merebmedia%E1%88%98%E1%88%A8%E1%89%A5%E1%88%9A%E1%8B%B2%E1%8B%AB
ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803 | 216 |
| 10 | Sin texto... | 155 |
| 11 | ሰበር ዜና!
በወልድያ ከተማ ውጥረት ነግሶ መዋሉ ተሰማ!
በዚህም የዞንና የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ከነ አጃቢዎቻቸው በ7 ፓትሮል ተሳፍረው ከተማዋን ለቀው መውጣታቸው ታውቋል።
የሰሜን ወሎ ዞን ዋና መቀመጫ በሆነችው ወልድያ ከተማ ዛሬ ነሐሴ 14/2016 ዓ/ም ከንጋት ጀምሮ እስከ አመሻሹ ከባድ የሆነ ውጥረት ነግሶ መዋሉን የከተማዋ ነዋሪዎች ለመረብ ሚዲያ ገልፀዋል።
በከተማዋ ማርፈጃውን ጎንደር በር እና መብራት ኃይል በተባሉ ሰፈሮች ላይ የቦንብ ፍንዳታ የተፈፀመ ሲሆን የቦንብ ፍንዳታው በሰዎች ላይ ያደረሰው ጉዳት ስለመኖሩ የታወቀ ነገር የለም።
የቦንብ ጥቃቱን የፈፀሙት የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ብርጌድ ፋኖዎች ሲሆኑ፡ ከቦንብ ጥቃቱ በተጨማሪ የተጣለውን የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እግድን ጥሰዋል የተባሉ የባለ ሦስት እግር ባጃጅ አሽከርካሪዎች ከባድ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጡም የብርጌዱ አመራሮች ለመረብ ሚዲያ ገልፀዋል።
በተመሣሣይ በከተማዋ ፋኖን ትደግፋላችሁ በሚል በርካታ ንፁኋኖች የሚታሰሩበት ጎንደር በር የሚገኘው ማር ማቀነባበሪያ ካምፕ እና የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና ወታደራዊ ቤዝ ከሆነው ከሼክ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ ስቴዲየም ላይ ተደጋጋሚ የሆነ የሞርተር ጥቃት መፈፀሙ ታውቋል።
በሁለቱ ትልልቅ ወታደራዊ ካምቦች ላይ የሞርተር ጥቃቱን የፈፀመው የአማራ ፋኖ በወሎ ሜካናይዝድ ክፍል ሲሆን፡ በጥቃቱ ምን ያህል ወታደር እንደተገደለና ምን ያህል ወታደራዊ ንብረት እንደወደመ እስካሁን በውል የታወቀ ነገር ባይኖርም ነገር ግን ቁስለኛ የያዙ አምቡላንሶች ከማር ማቀነባበሪያ ካምፑ ወደ ሆስፒታል በተደጋጋሚ ሲመላልሱ ማየታቸውን የአይን እማኞች ለመረብ ሚዲያ ገልፀዋል።
በዚህም ማርፈጃውን የዞንና የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ከነ አጃቢዎቻቸው በ7 ፓትሮል ተሳፍረው በሃራ በኩል አቆራርጠው ወደ አፋር መሸሻቸውን መረብ ሚዲያ ከታማኝ ምንጮቹ ለማረጋገጥ ችሏል።
አፋር የገቡት የዞንና የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች በባቲ አድርገው ወደ ደሴና ኮምቦልቻ ሊገቡ ይችላሉ ሲሉ ምንጮቻችን አክለው ገልፀዋል።
የከተማዋ አራቱም መግቢያ በሮች በዋርካው ምሬ ወዳጆ በሚመራው አማራ ፋኖ በወሎና በኮሎኔል ፈንታው ሙሃቤ በሚመራው አማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ እንዲሁም በፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ብርጌድ ፋኖዎች ቁጥጥር ስር የገቡ ሲሆን፡ የአገዛዙ ጦር ከሼክ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ ስቴዲየምና ገብርኤል ተራራ ላይ አስቀምጧቸው የነበሩ አንዳንድ ከባባድ መሳሪያዎቹን ወደ ጭፍራ እያሸሸ መሆኑም ታውቋል።
(ምስል፦ ወልድያ ከተማ ዛሬ ረፋድ የቦንብ ፍንዳታ የተፈፀመበት መብራት ኃይል አከባቢ)
###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
የቴሌግራም 👉 https://t.me/MerebMedia24
ዩቲዩብ👉
http://www.youtube.com/@Merebmedia%E1%88%98%E1%88%A8%E1%89%A5%E1%88%9A%E1%8B%B2%E1%8B%AB
ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803 | 169 |
| 12 | Sin texto... | 268 |
| 13 | እንደምን አደራችሁ!
ጀግና እናስተዋውቃችሁ!
"ይህ ትግል ግራ እጄን በድሽቃ የተቆረጥኩበት፡ ጓዶቼን የገበርኩበት ትግል ነው" ፋኖ ፍስሐ የማታው
ፋኖ ፍስሐ የማታው ይባላል። የሕልውና ትግሉን የተቀላቀለው ከሰሜኑ ጦርነት ጀምሮ ነው።
የሕወሓት ቡድን በአማራ ሕዝብ ላይ ወረራ በፈፀመበት ወቅት ወረራውን ለመመከት ከሚማርበት ትምህርት ቤት አቋርጦ ትግሉን በይፋ ተቀላቀለ።
ትግሉን ከተቀላቀለበት 2013 ዓ/ም ጀምሮ ላለፉት ሦስት ዓመታት በፅናትና በጀግንነት ያለ ስስትት ስለ አማራ ሕዝብ ነፃነት ሲል ተፋልሟል።አሁንም እንደቀጠለነው።
ከሕወሓት ታጣቂ ጋር በነበረው ጦርነት ስለዚህ ወጣት ጀግንነትና ስለፈፀመው ገድል እነዛ ሰንሰለታማ የዞብልና የራማ ተራሮች፣ የበላጎና የቃሊም ሰማይ ጠቀስ ጋሪያዎች ተናገሩ ቢባሉ አፍ አውጥተው ይመሰክሩለታል።
እንሆ ከአንድ ዓመት በፊት ጀምሮ ደግሞ ገዢው ቡድን በአማራ ልዝብ ላይ በይፋ የከፈተውን ጦርነት ለመመከት ውሎና አዳሩ ምሽግ ውስጥ ነው።
እነዛን ሰንሰለታማ የግሸን ተራሮችን ልክ እንደ ቤቱ ያውቃቸዋል። ከአምባሰል እስከ ወልድያ ምላሽ፣ ከዋድላ ደላንታ እስከ መቄት፣ ከተንታ እስከ ወረባቦ፣ ከጊራና እስከ ሃብሩ ከምሽግ ምሽግ እየተራመደ ታሪክ በወርቅ ቀለሙ የሚፅፈው፣ ትውልድ የሚዘክረው ገድል እየፈፀመ ይገኛል።
በአንድ ወቅት በአንድ ግምባር ላይ ከባድ ውጊያ እያደረጉ ባለበት ከበባ ውስጥ ገብተው የተቆረጡ ጓዶቹን ለማውጣት ሳንጃ ነቅሎ በደረቱ ተስቦ ከበባውን ሰብሮ ጓዶቹን አውጥቶ ወደ ኋላ እየተመለሰ እያለ ከጠላት በተተኮሰ ተደጋጋሚ የሆነ የዲሽቃ ጥይት ግራ እጁ ክንዱ ላይ ክፉኛ ቆሰለ። በወቅቱ በቂ የሆነ ሕክምና ባለማገኘቱ እጁ ሊቆረጥ ግድ ሆነ።
አሁን ላይ ልክ እንደ ተርብ ከምሽግ ምሽግ እየተወረወረ ታጣፊ ክላሹን በአንድ እጁ የተኮሰ ጊዜ ጠላት የሚይዘው የሚጨብጡው ያጣል ይባላል።
ፋኖ ፍስሐ ስለ እጁ መቆጥ ምን እንደተሰማው ከመረብ ሚዲያ የግምባር ዘጋቢዎች ለተነሳለት ጥያቄ ሲመልስ እንዲህ ይላል "እጄ በመቆረጡ ብዙም አልቆጭም።ምክኒያቱም እኔ እጄን በቆሰልኩበት አውደ ውጊያ ጓዶቼ ተሰውተዋል።እኔ ግን አለሁ።የነሱን አደራ፣ የነሱን ቃል በቀረው በአንድ እጄ እፈፅመዋለሁ። ስለ አማራ ሕዝብ ነፃነት አይደለም ግራ እጄን ገና አንገቴን እሰጣለሁ" ይሄው ነበር ምላሹ።
ፋኖ ፍስሐ አክሎም "አሁን አሁን በምሰማቸው የበላይ አመራሮቻችን አለመግባባት ውስጤ ይረበሻል። "ወንዝ ከላይ ሲደፈርስ ከታችም ይደፈርሳል" እንዲሉ፡ የነሱ አለመግባባት ከታች ላለነው ለኛም እንዳይተርፈን እፈራለሁ።
ይህ ትግል ግራ እጄን በድሽቃ የተቆረጥኩበት፡ ጓዶቼን የገበርኩበት ትግል ነው፡ ዋጋ ከፍየበታለሁ።ከጫፍ ላደርስ የጓዶቼ አደራ አለብኝ። ስለዚህ የበላይ አመራሮቻችን ቁጭ ብለው ተነጋግረው ለአማራ ሕዝብ የሚጠቅም የጋራ የሆነ መስመር እንዲከተሉ ወንድማዊ ምክሬ ነው" ሲል ከመረብ ሚዲያ ጋር በነበረው ቆይታ መልዕክት አስተላልፏል።
ፋኖ ፍስሐ እጁ የተቆረጠበት ቦታ ቅዝቃዜ ሲነካው ሕመሙ ያገረሽበታል። ሕመሙን ዋጥ አድርጎ፣ ዛሬም የምሽጉ ንጉስ ነው።በአማራ ፋኖ በወሎ ልጅ የእያሱ ክ/ጦር አባል ነው።
ጀግናው ፋኖ ፍስሐ አርቴፊሻል እጅ ቢገጠምለት ከዚህ የተሻለ ስራ መስራትና አሁን እየፈፀመ ካለው ገድል ይበልጥ የሚያስደምም ገድል እንደሚፈፅም እሙን ነው። ስለዚህ ከሃገር ውጭም ከሃገር ውስጥም የምትኖሩ የትግሉ ደጋፊ ወገኖች ይደር የማይባል የቤት ስራ ይሁናችሁ።
ሙሉ የቪድዮ ቆይታውን በቅርቡ ይጠብቁን
###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
የቴሌግራም 👉 https://t.me/MerebMedia24
ዩቲዩብ👉
http://www.youtube.com/@Merebmedia%E1%88%98%E1%88%A8%E1%89%A5%E1%88%9A%E1%8B%B2%E1%8B%AB
ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803 | 164 |
| 14 | Sin texto... | 141 |
| 15 | ዘመቻ እነዋሪን ወፍ ሳይጮህ ገና በማለዳ የተገበረችው የአፄ ዘረያቆብ ከተማ ደብረብርሃን ፀጥ እረጭ ብላ ውላለች!
ለወትሮው ያቺ ከአዲስ አበባ ወሎ የሚጓዙትን ጨምሮ በርካታ ተሽከርካሪዎች የሚተራመሱባት፣ ቀዝቃዛማዋ ደብረብርሃን ሰው በሃገሩ የለለ እስኪመስል ድረስ የንግድ ተቋማቶቿን ጥርቅም፣ አውራ ጎዳናዎቿን ክርችም አድርጋ ውላለች።
ምክኒያቱ ያዘዟት የምትወዳቸው የምትሳሳላቸው ልጆቿ ናቸውና።
ከደብረብርሃን በተጨማሪ የከባድ ጭነትና የባለሦስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎች ትርምስ ተለይቷት የማያውቀው ሸዋሮቢት ከተማን ጨምሮ በቆሎ ምርቶቿ የምትታወቀው ደብረሲና እንዲሁም አርመኒያ እና ሌሎች የሸዋ ከተሞች መንገዶቻቸውን ክርችም አድርገው ዘግተው ዘመቻ እነዋሪን መቀላቀላቸውን ሲገልፁ ገና ንጋት አልቀደማቸውም ነበር።
የአገዛዙ ጦር እነዋሪ ላይ በርካታ ፋኖ ደመሰስኩ በሚል የራሱን ሟች ወታደሮች አስክሬንን ጨምሮ የፎቶ ፕሮፓጋንዳ እያሰራ ቢሆንም ነገር ግን እውነታው ሲገለጥ ይህ አይደለም።
የሞረት እና ጅሩ ወረዳ መቀመጫ በሆነችው እነዋሪ ከተማና በዙሪያ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአገዛዙ ኮማንዶዎች አስከሬን እንደ ደረቀ ዛፍ ቅጠል መርገፉን የአከባቢው ነዋሪዎች ለመረብ ሚዲያ ገልፀዋል።
ይህን መረጃ ለመረብ ሚዲያ ያደረሱት የእነዋሪ ከተማና የአከባቢው ነዋሪዎች እንደገለፁት፡ በጣት የሚቆጠሩ ልጆቻችን በክብር የተሰው ቢሆንም ነገር ግን ሺ ጥለው ነው የወደቁት፣ አይቆጨንም ብለዋል።
ነዋሪዎቹ አክለውም "እነዋሪ ላይ በክብር የተሰውት እነዛ ጀግና ልጆቻችን ከመውደቃቸው በፊት በያዙት አረር የቆሉት በርካታ ቁጥር ያለው የኮማንዶ አስከሬን በየማሳችን ወድቋል፣ የሰማይ አሞራ እየተራኮተበት ነው፣ የዱር አራዊት እየተሻማበት ነው" ሲሉ ቃል በቃል ተናግረዋል።
በተመሣሣይ ትናንት ነሐሴ 12/2016 ዓ/ም ከመዘዞ በቅርብ ርቀት ልዩ ስሙ አሞራው ገብርኤል በተባለ ቦታ ለግማሽ ሰዓታት በተደረገ ውጊያ ከባድ የሆነ ኪሳራ በገዢው ኃይል ላይ መድረሱ ነው የተሰማው።
በደብረሲና፣ በጣርማበርና በጎች ጋጥ ተብሎ በሚጠራ አከባቢ አድርጎ በሦስት አቅጣጫ በመግባት አሞራው ገብርኤል ላይ ተኩስ የከፈተው የ103ኛ እና 105ኛ አጋኣዚ ኮማንዶ ያሰበው ሳይሳካ ሙትና ቁስለኛውን ይዞ መውጣት በማይችልበት ደረጃ ተቀጥቅጦ የተረፈው ወደ ደብረብርሃን ከተማ አቅጣጫ መፈርጠጡን ነው መረብ ሚዲያ የአማራ ፋኖ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ምክትል ቃል አቀባይ የሆነው ፋኖ ስንታየሁ ደመቀን በማነጋገር ለማረጋገጥ የቻለው።
በዚህ ውጊያ አንድ ዲሽቃ፣ አራት ብሬን እና ሦስት ራሺያ ሰራሽ ስናይፐርን ጨምሮ በርካታ ነፍስ ወከፍ ክላሽንኮቭ መሣሪያ በፋኖ እጅ መግባቱም ታውቋል።
በውጊያው በርካታ ቁጥር ያለው የኮማንዶ አባል አሞራው ገብርኤል ተራራ ላይ የረገፈ ሲሆን በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል፣ እድል የቀናቸው ጥቂቶች ደግሞ እጃቸውን ለፋኖ መስጠታቸውን ነው ምክትል ቃል አቀባዩ ከመረብ ሚዲያ ጋር በነበረው ቆይታ የገለፀው።
ይህን ያህል ኪሳራን ከግር እስከ እራሱ የተከናነበው የአገዛዙ ጦር በጣት የሚቆጠሩ የፋኖ አባላትን ጣልኩ ብሎ በሚዲያ በማጮህ እራሱን በራሱ ሲያስደስት ተመልክተናል።
(ከወሎ ደብረብርሃን ዋናው መስመር)
###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
የቴሌግራም 👉 https://t.me/MerebMedia24
ዩቲዩብ👉
http://www.youtube.com/@Merebmedia%E1%88%98%E1%88%A8%E1%89%A5%E1%88%9A%E1%8B%B2%E1%8B%AB
ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803 | 170 |
| 16 | Sin texto... | 211 |
| 17 | ሰበር ዜና!
በደቡብ ወሎ ዞን አንዲት የ10 ዓመት ታዳጊ በመንግስት ፀጥታ ኃይል መደፈሯ ተሰማ!
በደቡብ ወሎ ዞን ከደሴ ከተማ በ152 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው መቅደላ ወረዳ ልዩ ስሙ የደንጣ በተባለ ቀበሌ ዛሬ ነሐሴ 12/2016 ዓ/ም አንዲት የ10 ዓመት ታዳጊ በመንግስት ፀጥታ ኃይል አባል መደፈሯን የታዳጊዋ ቤተሰቦች ለመረብ ሚዲያ ተናግረዋል።
ታዳጊዋ የአስገድዶ መድፈር ድርጊቱ የተፈፀመባት ዛሬ እኩለቀን ገደማ ሲሆን ወዲያውኑ ወደ ማሻ ሆስፒታል የተወሰደች ቢሆንም ነገር ግን የሕክምና ባለሙያዎቹ ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ ወደ ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል እንደላኳት የታዳጊዋ ቤተሰቦችና የአከባቢው ነዋሪዎች ለመረብ ሚዲያ ጨምረው ገልፀዋል።
ታዳጊዋ በተፈፀመባት አሰቃቂ ድርጊት ከፍተኛ ደም ስለፈሰሳት እራሷን መሳቷ የተነገረ ሲሆን የሕክምና ባለሙያዎች ሕይወቷን ለማትረፍ ርብርብ እያደረጉ ነው ተብሏል።
የታዳጊዋ ወላጅ አባት አርሶ አደር አስናቀ ድርጊቱን የፈፀመው የፀጥታ ኃይል አባል በሕግ ይጠየቅልኝ የሚል ጥያቄ በማንሳቱ ለእስር መዳረጉም ነው የተነገረው።
የአስገድዶ መድፈር ድርጊቱ የተፈፀመባት የ10 ዓመት ታዳጊ ወላጅ አባት ብቻ ሳይሆን በታዳጊዋ ላይ በደረሰው አሰቃቂ ድርጊት የተቆጡና ፍትሕ እንዲሰጥ ለመጠየቅ የተሰባሰቡ የደንጣ ቀበሌና የአከባቢው ነዋሪዎችም በጅምላ ታፍሰው መታሰራቸውንም መረብ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመላክታል።
ከዚህ ጋር ተያይዞም በአከባቢው ውጥረት የነገሰ ሲሆን ገዢው ቡድንም በየደንጣ ቀበሌ አመፅ እንዳይቀሰቀስ በሚል ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፀጥታ ኃይል ማሰማራቱ ታውቋል።
ድርጊቱን የፈፀመው የመቅደላ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ አባል የሆነ የአድማ ብተና አባል ሲሆን፣ እስካሁን ወደ ህግ እንዳልቀረበ ነው የታዳጊዋ ቤተሰቦች እንባ ታጅበው ለጣቢያችን የገለፁት።
የደንጣ ቀበሌ በደቡብ ወሎ ዞን ከሚገኙ 24 ገደማ ወረዳዎች መካከል አንዱ በሆነው መቅደላ ወረዳ ስር፡ ከወረዳው መቀመጫ ማሻ ከተማ በቅርብ ርቀት የምትገኝ ቀጠራማ ቀበሌ ናት።
###
መረበኞች ነን...መረጃ አጥማጆች!
የቴሌግራም 👉 https://t.me/MerebMedia24
ዩቲዩብ👉
http://www.youtube.com/@Merebmedia%E1%88%98%E1%88%A8%E1%89%A5%E1%88%9A%E1%8B%B2%E1%8B%AB
ድየፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803 | 167 |
| 18 | Sin texto... | 217 |
| 19 | ሰበር ዜና!
በአርሲ ካህኑ ስጋ ወደሙን አቀብለው ምእመናንን እያሳለሙ ሳለ በታጣቂዎች መገደላቸው ተገለጸ ፡፡
በአርሲ ሀገረ ስብከት አሰኮ ወረዳ ጢዮ ቀበሌ ጠለታ ጨፋ ከተማ የጠለታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህንን ጨምሮ 6 ኦርቶዶክሳውያን ኦነግ ሸኔ ተብለው በሚጠሩ ታጣቂዎች መገደላቸውን የአካባቢው ምእመናን ተናግረዋል፡፡
ግድያው የተፈጸመው ነሐሴ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ሲሆን ከሞቱት በተጨማሪም 3 ኦርቶዶክሳውያን ከባድ ጥቃት ደርሶባቸው በህክምና ላይ እንደሚገኙ ጣቢያችን ሰምቷል፡፡
ካህኑን ጨምሮ የተገደሉት ምእመናንን አስከሬናቸውን ለማንሳትና ለመቅበር አስቸጋሪ እንደነበር ገልጸው በዚህም ሁኔታ ከአጥቢያው ራቅ ወዳለ ቦታ በመውሰድ የቀብር ሥርዓቱን መፈጸም መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡
አስተያየት ሰጭዎች አክለውም በተለያየ መንገድ ቤተ ክርስቲያንን ሲረዱ የነበሩ ኦርቶዶክሳውያን ተለይተው ሀብት ንብረታቸው መቃጠሉንና የአካባቢው ምእመናንም ቤታቸውን ትተው በዱር በስጋት ውስጥ ናቸው ብለዋል፡፡
ጥቃቱ ከዚህ ቀደምም ተፈጥሮ እንደነበር ያነሱት አስተያየት ሰጭ ምእመናን ለበላይ አካል ብናሳውቅም ጩኸታችንን የሚሰማ አጥተናል በማለት ጥሪ አቅርበዋል።
ምንጭ፦ ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን | 216 |
| 20 | የአማራ ፋኖ በጎጃም! | 242 |
