cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ASD AJ LAH

ካነበብኩት…

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
744
Suscriptores
+1224 horas
+757 días
+8630 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Photo unavailableShow in Telegram
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ ⏰ #አሱለሳዒ 2⃣6⃣#ዙልሒጃ 1⃣4⃣4⃣5⃣ ሂ
Mostrar todo...
ጥቆማ ለ12 ክፍል ተማሪዎች! በመጀመሪያ መልካም ዝግጅት መልካም ፈተና ተመኘሁ:: አላህ የተሻለ ውጤትን ይግጠማችሁ:: 📌 ሰዓቱ ከፈተና በፊት ያለ ነውና ጤናችሁን በማይነካ መልኩ (አብዝቶ ባለመተኛት) ንባብ ላይ በርቱ:: ንባቡን ያለፈውን በመከለስና ጥያቄዎችን በመስራት ላይ አድርጉት:: 📌 ከዚያ በተጨማሪ በዋናነት ራሳችሁን ከጭንቀት አፅዱ:: ስላለፈው ጊዜ ፈፅሞ እንዳታስቡ:: ትኩረታችሁ አሁንና አሁን ብቻ ይሁን:: ትኩረታችሁ ነገና ነገ ብቻ ይሁን:: ሙሉ ለሙሉ አላህን ተጠግታችሁ በመተማመን ውስጥ ከጭንቀት የፀዳ ከባቢን ፍጠሩ:: ይህንን ማድረግ ካልቻላችሁ ምን ያህል እውቀት ምን ያህል ንባብ ቢኖር ምንም አትሰሩም:: ማድረግ ከቻላችሁ ደግሞ ተዓምር መስራት ትችላላችሁ:: ለዚህ እኔ ምስክር ነኝ:: Entranceን ለአመት ያክል ከንባብ ከተለያየሁ ቡሃላ ሳምንት ባልሞላ ንባብ ነው የተፈተንኩት:: ግን ጭንቀት አልነበረብኝም:: አላህን አምነው ነበር:: እሱም አላሳፈረኝም:: ከAAU አስገብቶኛል:: 📌 በፈተና ወቅት ትኩረታችሁ ፈተናው ብቻ ይሁን:: ለማስኮረጅ እንዳትጋጋጡ:: ሐራም ከመሆኑም ባሻገር ትኩረታችሁን በታትኖ ከጉድጓድ ይከታችሗል:: 🔺 ከዚያ ውጭ ለፈተና ወደ ካምፓስ ስትገቡ ሙሰላና ጥቂት ኩኪሳኩኪስ ያዙ:: ጥቂት ብርም ያዝ አድርጉ:: ሲርባችሁ ላውንጅ ለመብላት:: ሶላትና ዱዓ ላይ ተበራቱ:: ሳምንት ላልሞላ ቆይታ የካምፓስ ተማሪ ልሆን ብላችሁ ሰው የሚበዛበት ቦታ አብዝታችሁ አትገኙ:: ተስፋ የቆረጡ ተማሪዎች ወደ ብዙ ፈሳዶች ውስጥ ገብተው እንደነበር ከባለፉ ተማሪዎች ሰምተናል:: በድጋሜ መልካም ዝግጅት! መልካም ፈተና!! Mohammadammin
Mostrar todo...
👍 7
Repost from Mohammedamin Kassaw
ጥቆማ ለ12 ክፍል ተማሪዎች! በመጀመሪያ መልካም ዝግጅት መልካም ፈተና ተመኘሁ:: አላህ የተሻለ ውጤትን ይግጠማችሁ:: 📌 ሰዓቱ ከፈተና በፊት ያለ ነውና ጤናችሁን በማይነካ መልኩ (አብዝቶ ባለመተኛት) ንባብ ላይ በርቱ:: ንባቡን ያለፈውን በመከለስና ጥያቄዎችን በመስራት ላይ አድርጉት:: 📌 ከዚያ በተጨማሪ በዋናነት ራሳችሁን ከጭንቀት አፅዱ:: ስላለፈው ጊዜ ፈፅሞ እንዳታስቡ:: ትኩረታችሁ አሁንና አሁን ብቻ ይሁን:: ትኩረታችሁ ነገና ነገ ብቻ ይሁን:: ሙሉ ለሙሉ አላህን ተጠግታችሁ በመተማመን ውስጥ ከጭንቀት የፀዳ ከባቢን ፍጠሩ:: ይህንን ማድረግ ካልቻላችሁ ምን ያህል እውቀት ምን ያህል ንባብ ቢኖር ምንም አትሰሩም:: ማድረግ ከቻላችሁ ደግሞ ተዓምር መስራት ትችላላችሁ:: ለዚህ እኔ ምስክር ነኝ:: Entranceን ለአመት ያክል ከንባብ ከተለያየሁ ቡሃላ ሳምንት ባልሞላ ንባብ ነው የተፈተንኩት:: ግን ጭንቀት አልነበረብኝም:: አላህን አምነው ነበር:: እሱም አላሳፈረኝም:: ከAAU አስገብቶኛል:: 📌 በፈተና ወቅት ትኩረታችሁ ፈተናው ብቻ ይሁን:: ለማስኮረጅ እንዳትጋጋጡ:: ሐራም ከመሆኑም ባሻገር ትኩረታችሁን በታትኖ ከጉድጓድ ይከታችሗል:: 🔺 ከዚያ ውጭ ለፈተና ወደ ካምፓስ ስትገቡ ሙሰላና ጥቂት ኩኪሳኩኪስ ያዙ:: ጥቂት ብርም ያዝ አድርጉ:: ሲርባችሁ ላውንጅ ለመብላት:: ሶላትና ዱዓ ላይ ተበራቱ:: ሳምንት ላልሞላ ቆይታ የካምፓስ ተማሪ ልሆን ብላችሁ ሰው የሚበዛበት ቦታ አብዝታችሁ አትገኙ:: ተስፋ የቆረጡ ተማሪዎች ወደ ብዙ ፈሳዶች ውስጥ ገብተው እንደነበር ከባለፉ ተማሪዎች ሰምተናል:: በድጋሜ መልካም ዝግጅት! መልካም ፈተና!! @MohammadamminKassaw
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
እግርህ ጀነትን እስክትረግጥ ትፈተናለህ። አሁንም አሁንም ትሰቃያለህ። በላይ በላዩ ይደራረብብሀል ስቃዩ። ከዚያም ጀነት አዝልቀው አንዴ ነክረው ያወጡሀል። በጌታዬ ይሁንብኝ ብለህ ትምላለህ። "ስቃይ መች አጊኝቶኝ ያውቅና" እስክትል ህመምህን ትረሳለህ። ይህን ደረጃ ከታጋሾች በቀር ማንም አያገኘውም። ጌታዬ ሆይ! ታግሰው ከሚመነዱ፣ ሰብረው ከሚሸለሙ ዕንባቸውን በፈገግታ ከቀየርክላቸው ባለሟሎችህ ዘንድ መድበን። እኛንም እነርሱንም። @yesheh_kalidrashid_daewawoch @yesheh_kalidrashid_daewawoch
Mostrar todo...
👍 11😢 1
إعطاء الزكاة لمن يريد أن يتزوج‼ أحد أصدقائي يريد أن يتزوج وليس معه من الأموال ما يكفي نفقات الزواج، فهل يجوز لي أن أساعده وأحسب هذه الأموال من الزكاة ؟. الجواب الحمد لله. نعم ، يجوز إعطاء الزكاة لمن يريد أن يتزوج ، إذا كان لا يجد ما يكفيه للزواج ، وهذا لا يخرج عن أصناف الزكاة الثمانية التي ذكرها الله تعالى في قوله : ( إِنَّمَا الصَّدَقَاتُ لِلْفُقَرَاءِ وَالْمَسَاكِينِ وَالْعَامِلِينَ عَلَيْهَا وَالْمُؤَلَّفَةِ قُلُوبُهُمْ وَفِي الرِّقَابِ وَالْغَارِمِينَ وَفِي سَبِيلِ اللَّهِ وَابْنِ السَّبِيلِ فَرِيضَةً مِنَ اللَّهِ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ ) التوبة / 60 ، لأن من لا يجد ما يكفيه فهو فقير أو مسكين فيجوز دفع الزكاة إليه . قال الشيخ ابن عثيمين : " لو وجدنا شخصاً يستطيع أن يكتسب للأكل والشرب ، والسكنى لكنه يحتاج إلى الزواج وليس عنده ما يتزوج به فهل يجوز أن نزوجه من الزكاة ؟ الجواب : نعم يجوز أن نزوجه من الزكاة ويعطى المهر كاملاً ، فإن قيل : ما وجه كون تزويج الفقير من الزكاة جائزاً ولو كان الذي يعطى إياه كثيراً ؟ قلنا : لأن حاجة الإنسان إلى الزواج ملحة قد تكون في بعض الأحيان كحاجته إلى الأكل والشرب ، ولذلك قال أهل العلم : إنه يجب على من تلزمه نفقة شخص أن يزوجه إن كان ماله يتسع لذلك فيجب على الأب أن يزوج ابنه إذا احتاج الابن للزواج ولم يكن عنده ما يتزوج به ، لكن سمعت أن بعض الآباء الذي نسوا حالهم حال الشباب إذا طلب ابنه منه الزواج قال له : تزوج من عرق جبينك . وهذا غير جائز وحرام عليه إذا كان قادراً على تزويجه ، وسوف يخاصمه ابنه يوم القيامة إذا لم يزوجه مع قدرته على تزويجه " . اهـ ( فتاوى أركان الإسلام ص440-441 ) وسئل الشيخ ابن باز رحمه الله عن دفع الزكاة للشاب العاجز عن الزواج فقال : يجوز دفع الزكاة لهذا الشاب ، مساعدة له في الزواج إذا كان عاجزاً عن مؤونته . فتاوى الشيخ ابن باز(14/275) وسئلت اللجنة الدائمة : هل يجوز صرف الزكاة لشاب يريد الزواج من أجل إعفاف فرجه فأجابت : يجوز ذلك إذا كان لا يجد نفقات الزواج العرفية التي لا إسراف بها . فتاوى اللجنة الدائمة (10/17) والله تعالى أعلم .
Mostrar todo...
ደሊል አምጣ ካሉህ እንካ፦ حكم صرف الزكاة لمن عجز عن الزواج⁉️ السؤال: هذا سائل يقول: سماحة الشيخ! رجل يرغب في الزواج وهو غير مستطيع، هل تجوز له الزكاة ليتمكن من الزواج؟ الجواب: نعم، العاجزون عن الزواج يعطون من الزكاة ما يعينهم على الزواج، إذا كانوا عاجزين يشرع أن يعطوا من الزكاة ما يعينهم على الزواج. نعم. አል-ኢማም ኢብኑ ባዝ (ይህቺን ይዘህ saved message ላይ አስቀምጣት። አንድ ቀን ትጠቅምህ ይሆናል።)
Mostrar todo...
በነገራችን ላይ ዘካህ ሊሰጣቸው ከሚገቡ ሰዎች ውስጥ፤ የሰርግን ወጪ መሸፈን ከብዷቸው ከትዳር የራቁ ወንድሞች ተጠቃሽ ናቸው። ዘካህ ከሚገባቸው ስምንቱ ውስጥ «ሚስኪን/ፈቂር» በሚለው ይካተታሉ። (እንዲህ አይነት መረጃዎችን እየያዝክ ላጤው!)
Mostrar todo...
Repost from Mohammedamin Kassaw
Photo unavailableShow in Telegram
አሳማሚ እውነት! ፍቅር ሲሳይ ነው:: ሲሳይህ በየትኛው ልብ ውስጥ ተቀምጦ እየጠበቀህ እንደሆነ አታውቅም:: ዩሱፍን ከቅርቡ ያሉት ወንድሞች "ዩሱፍን ግደሉ!" አሉ:: ከሩቅ ያለው የማይውቀው ባዳው ደግሞ "መኖሪያውንም አክብሪ!" አለ:: @MohammadamminKassaw
Mostrar todo...
አሰላሙ ዐለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ t.me/asdajlahh በሚቀጥለው ወር የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል የመሰናዶ ትምህርት ማጠናቀቂያ ወይም ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና አስመልክቶ ሙስሊም ተማሪዎች ምን አይነት ዝግጅት እና ምን አይነት ግዜ ሊኖራቸው ይገባል የሚለውን አምና ተፈታኝ ሆኘ ካሳለፍኩትኝ ሁኔታ አንጻር የተወሰኑ ጥቆማዎችን ለተፈታኞ አደርስ ዘነድ የሞነጫጨርኳት… ፈጅር እንደተሰገደ እንድትሰባሰቡ ወደታዘዛችሁበት ትምህርትቤት በመሄድ በተዘጋጀው የየትምህርትቤታችሁ ባስ ላይ ከመጀመርያ ዙር ቀለል ያለ ፍተሻ በኋላ ገብታችሁ ወደ መፈተኛ ዩኒቨርሲቲ ጉዞ ትጀምራላችሁ፡፡ መፈተኛ ግቢ እንደደረሳችሁ የያዛችሁት እቃ እንደ እቃችሁ ብዛት ጠንከር ላለ ፍተሻ ይበተናል፡፡(በዚህ ፍተሻ ሰዐት ቤታችሁ ጥንቅቅ አድርጋ እናታችሁ ያስተካከላችው ልብስ ከፍተሻ በኋላ እንዳልነበረ ሆኖ ሻንጣችሁ ሊጠባችሁ ስለሚችል እቃ አለማብዛቱ ይመከራል)፡፡ ግቢ ከገባችሁ በኋላ በመጀመርያ ወደተመደባችሁበት ብሎክ በመሄድ ከብሎካችሁ ስር ከሚገኛው ዶርሚተሪ ዶርም ውስጥ በሚገኘው አልጋ ልክ እየመደበ ለአንዳችሁ የዶርም ቁልፍ ይሰጣል፡፡(በአንዳንድ ግቢዎች ላይ እንደተፈታኙ ፍላጎት የዶርም ምደባ ስለሚደረግ ለማንኛውም ግዜያችሁን በአግባቡ ሊያስጠቅም የሚችል ጓደኛ ጋር ቀድማችሁ በመነጋገር ቀደም ብላችሁ በመገኘት ከዶርሚተሪ ቁልፍ በመቀበል የራሳችሁን ዶርም ለመያዝ ብትሞክሩ የተሻለ ነው፡፡) ከፈተናው አንድ ቀን ቀደም ብሎ በምትፈተኑበት አዳራሽ በሱፐር ቫይዘሮች ቀለል ያለ ኦረንቴሽን ይሰጣል፡፡ ፈተና እስኪያልቅ ድረስ በየእለቱ ሁለት ፈተና (ጠዋት አንደ ከከሰዐት አንድ) ይሰጣል፡፡ ከፈተና በፊት በሚደረገው ሁሉም ፍተሻ የሴት እና የወንድ ፍተሻ የተለየ ስለሆነ ኒቃብ የምታደርጉ ተማሪዎች ሳትደናገጡ ዩኒፎርማችሁን እንደለበሳችሁ ከነኒቃባችሁ በመቅረብ ፈተና መፈተን የምትችሉ ሲሆን ( ሆነ ብለው ከፈተና እንዳርቋችሁ በመጀመርያ ግቢ ላይ በሚኖራችሁ ፍተሸ ስትማሩ እንደነበራችሁት በማስክ እና በሂጃባችሁ ብትሸፈኑ እላለሁ) የግል ተፈታኝ ተማሪዎች ደግሞ እስከነጅልባባችሁ ያስፈትኗችኋል፡፡ ከፈተና 30 ደቂቃ በፊት መገኘት እና ፈተና ከተጀመረ ኋላ እስከ 45 ደቂቃ ድረስ መቀመጥ ግዴታ ስለሆነ በግዜ መገኘት ትእግስት አድርጋችሁ መቆያታችሁን አትዘንጉ፡፡ ወደ መፈተኛ ክፍል ስትገቡ ADMISSION CARD ፣ ማንነጽን የሚገልጽ መታወቂያ ፣ እስራስ ፣ ላጲስ እና መቅረጫ ውጭ (የእጅ ሰዐትም ቢሆን) ይዛችሁ አለመግባታችሁን አረጋግጡ፡፡ * ምግብ ከዩኒቨርሲቲው የምትመገቡ ምሳ ከ5፡30 እስከ 7፡00 ፣ እራት ከምሽቱ 12፡30 እስከ 2፡00 እንዲሁም ቁርስ ከጠዋቱ 12፡30 እስከ 2፡00 ድረስ ብቻ መሆኑን አውቃችሁ በሰዐታችሁ ተገኝታችሁ መመገባችሁን መዘንጋት የለባችሁም፡፡ ምግቡ በአብዛኛው ተመሳሳይ ሊሆን ቢችልም የሚታማ አይነት ምግብ ስላልሆነ ብትመገቡት አትጎዱም ይልቅ ወስፋታችሁ ይከፈት ዘንድ ከታች የዘረዘርኩላችሁን ደረቅ ምግቦች ብትጠቀሙ አሪፍ ነው፡፡ ካፌ ከፍላችሁ ተጠቃሚ የምትሆኑ ከሆነ ደግሞ ምግብ ሊያልቅ ስለሚችል ከሁሉም በፊት ቀደም ብላችሁ በመገኘት ምግብ ማዘዝ ይኖርባችኋል፡፡ * ከሁሉም በላይ መረሳት የሌለበት ነገር ቢኖር የሰላት ወቅት ሲሆን በዩኒቨርሲቲዎች አከባቢ መሳጂዶች ላይኖሩ ስለሚችል ዲስኮ(ደቂቃ ብቻ የሚቆጥር መዘነጫ ያልሆነ የእጅ ሰዐት) መያዝ እና የሰላት አውቃቶችን እና የቂብላ አቅጣጫን ግቢ ከመግባታችሁ በፊት ማረጋገጥ ተመራጭ ነው፡፡ ለፈጅር ሰላት ለመነሳት ብቸኛው መፍትሄ በግዜ መተኛት ስለሆነ ከአልባሌ መዝናኛ ቦታዎች ራስን ማራቁ ይመረጣል፡፡ የተፈታኙ ብዛት ከፍተኛ በሆነበት ዩኒቨርሲቲ ብዛት ያለው ጀማዐ ሊከለከል ስለሚችል ለደህንነታችሁ ሲባል እናንተ ብሎክ ጋር ካሉ ተማሪዎች ጋር ብቻ ባዶ በሆኑ ዶርሞች ወይም ከዶርም አጠገብ በሚኖረው ግሪን ኤሪያ ላይ ብትሰግዱ የተሻለ ነው፡፡ * ዶርም ውስጥ ሁሉም ተማሪ የየግሉ ሎከር ስለሚኖረው ተመሳሳይ መክፈቻ በመይገኝለት የጋን ቁልፍ መቆለፍ የሌለበት ጉዳይ ነው፡፡ * ተማሪዎች ሰብሰብ ብለው ከሚያመሹባቸው ቦታዎች ራስን ማራቁ ከደህንነት በተጨማሪ በአቻ ግፊት ምክንያት ከሚመጡ ፈሳዶች ይከላከላል፡፡ በተረፈ በሚኖራችሁ ትርፍ ግዜ መጽሀፍ ማንበብ ከድብርት ሙድ ውስጥ ያወጣችኋል፡፡ * በፈተና የመጭሻ ቀን በየቦታው የቡድን ጸቦች ስለሚኖሩ ከዶርም አካባቢ ራቅ በማለት ራሳችሁን የምትጠብቁበት ቦታ ብትሆኑ እና በየትኛውም አይነት ጸብ እጃችሁን ከማስገባት መቆጠብ ይኖርባችኋል፡፡ * ካልተመደባችሁበት ብሎክ እና ወንዶች ወደሴቶች ዶርም ሴቶች ወደወንዶች ዶርም መሄድ ካለማወቅ ከሚፈጠሩ ምናልባትም ቅጣታቸው ከፍ ያለ ሊሆን ከሚችሉ ስህተቶች ውስጥ ነው፡፡ * ለማንኛውም ፈታኝ ፣ ጥበቃ ፣ የስራ ሀላፊ በተለይ ለማንኛውም ከጸጥታ አካላት ለሚመጣ ትእዛዝ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ይኖርባችኋል፡፡ * ዳቦ ፣ ነጠላ ጫማ እና ፈሳሽ ምግቦች ሱቅ ላይ ስለሚገኙ ባትሸከሙ… * ልትይዟቸው የሚገቡ … 1 ታጣፊ የኪስ መስገጃ እና በመጠኑ አነስ ያለ ቁርዐን(ብዙ ተፈታኝ የሚዘነጋቸው) 2 በትርፍ ግዜ ሊነበቡ የሚችሉ አጠር አጠር ያሉ አዝና እና አስተማሪ መጽሀፍት(ሁለት መጽሀፍ በቂ ነው) 3 የ ATM ማሽን ያሉባቸው ቦታዎች በጸጥታ እና በንብረት ጥበቃ ጉዳይ ዝግ ሊሆኑ ስለሚችሉ ለዝርፊያ የሜጋልጣችሁን ቢበዛ እስከ 1000 ብር ካሽ 4 የምትመገቡት ምግብ መላመዱ ሊከብዳችሁ እና እንደ ቤት ላይሆን ስለሚችል ከቤት የተዘጋጁ ደረቅ ምግቦችን እና የታሸጉ ምግቦችን(ለውዝ ቅቤ ፣ ማርቤላ) መያዝ 5 ፍተሸ ሰአት እንዳትቸገሩ ከዪኒፎርም ውጭ ሁለት ተቀያሪ ልብስ ብቻ መያዝ 6 ማንነትን ሊገልጽ የሚችል መታወቂያ (የትምህርት ቤት ፣ የቀበሌ ፣ ብሄራዊ መታወቂያ) 7 የሻንጣ ጋን ቁልፍ(ትንሿን ብቻ) 8 ለፍተሸ ምቹ የሆነ ንብረታችሁን በሙሉ በትክክል ሊይዝ የሚገባ ሻንጣ ወይም ቦርሳ 9 የሰላት እና ሌሎች ግዜያችሁን አብቃቅታችሁ ለመጠቀም ዲስኮ ሰዐት መያዝ 10 ለሴቶች የወር አበባ መቆጣጠሪያ(ሞዴስ) 11 የታዘዘላችሁ መድሀኒት ካለ እስከነማዘዣ ወረቀቱ ይዛችሁ መገኘት ባትይዟቸው የሚመረጡ እና እንዳትይዟቸው የሚከለከሉ 1 በጠንካራ ማይካ ወይም ፕላስቲክ ፣ በጠርሙስ እና በብረት የታሸጉ ማንኛውም አይነት ነገሮች 2 እንደ በሶያሉ ዱቄት ይዘት ያላቸው ምግብ ነክ ነገሮች ጋር አደገኛ እጾች ስለሚገቡ የጸጥታአካላት ሊያስጥሏችሁ ይችላሉ 3 ጥቅል ሶፍት(ግቢ ውስጥ ባሉ ሱቆች ውስጥ ስለሚገኝ ባትይዙ) 4 ከስክስ ሰፍቲ የወንድም የሴትም ጫማ አላህ ከናንተ ጋር ይሁን፡፡ ጽሁፉን በከፊልም ሙሉውንም ሀሳባችሁንም አድርጋችሁ ለተማሪዎች ማጋራት ትችላላችሁ፡፡ https://t.me/asdajlahh
Mostrar todo...
ASD AJ LAH

ካነበብኩት…

👍 5
Photo unavailableShow in Telegram
😁 3🤣 1
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.