1 321
Suscriptores
+224 horas
+87 días
+15130 días
Archivo de publicaciones
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
ኮሌጁ የምስራቅ አፍሪካ የቴክኒክና ሙያ የልህቀት ማእከል እንደ መሆኑ መጠን የአካባቢው ወጣቶች በኮሌጁ ያለውን እምቅ አቅም በመጠቀም የፈጠራና የቴክኖሎጂ ባለቤት እንዲሆኑ ጥሪ ቀረበ፡፡
ከድሬዳዋ አጠቃላይ እና ከአዲሱ ሁለተኛ ትምህርት ቤት የተውጣጡ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ትምህርታዊ ጉብኝት አደረጉ፡፡
አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መጋቢዎች እንደመሆናቸው መጠን በትምህርት ቤት ቆይታቸው ሊማሯቸው የሚችሉ የተለያዩ የቴክኒክና ሙያ ስልጠናዎች በምን አይነት መንገድ እንደሚሰጡና ሰልጣኞች በኮሌጁ የሚገኙ እምቅ እውቀቶችን መጠቀም የሚችሉበትን መልካም አጋጣሚ ለመፍጠር ታልሞ በተዘጋጀው ትምህርታዊ ጉብኝት ላይ መልእክት ያስተላለፉት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሀሚድ እንዳሉት ኮሌጁ የምስራቅ አፍሪካ የቴክኒክና ሙያ የልህቀት ማእከል እንደ መሆኑ መጠን የአካባቢው ወጣቶች በኮሌጁ ያለውን እምቅ አቅም በመጠቀም የፈጠራና የቴክኖሎጂ ባለቤት መሆን የሚያስችላቸውን ክህሎት ማግኘት ትችላላችሁ ብለዋል፡፡
የኮሌጁ ዲን አያይዘውም የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በአእምሯቸው እያሰቡ በእጃቸው እየሰሩ ሃገርና የሚገነቡ ስልጡን ዜጎች የሚፈሩበት ተቋም እንደመሆናቸው መጠን በዚህ ጉብኝት የተሳተፋችሁ እንዲሁም በአካባቢው የሚገኙ ወጣቶች ይህንን ዘርፍ በመቀላቀል ስኬታማ ህይወት እንዲመሩ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
በጉብኝቱ ወቅት ለተማሪዎቹ ገለጻ ያደረጉት ደግሞ የኮሌጁ ኢ/ኤ/ቴ/ሽ ም/ዲን የሆኑት ወ/ሮ ትግስት በዙ ሲሆኑ በንግግራቸውም ኮሌጁ በርካታ ስልጠናዎችን እንደመስጠቱ መጠን ለሰልጣኞች የሚሰጣቸው ስልጠናዎች በሙሉ የ21ኛውን ክፍለዘም የስልጠና ሂደት የተከተሉ ናቸው፡፡በተለይ ደግሞ ለ1ኛን 2ተኛ ደረጃ ተማሪዎች ደግሞ የSTEM እና የቴክኖሎጂ ፈጠራን ማጎልበት በሚያስችሉ ወርክሾፖችን በማዘጋጀት ስልጠናዎችን እንዲወስዱ በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
ዛሬ በተደረገው ትምህርታዊ ጉብኝት ላይ የተሳተፉ የድሬዳዋ አጠቃላይ እና የአዲሱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ባዩት ነገር እጅግ እንደተደሰቱና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ምርጥ ባለሙያዎችን የሚያፈሩ ተቋማ እንደሆኑ ተረድተናል ያሉ ሲሆን በቀጣይም ከሚማሩት ትምህርት ጎን ለጎን በኮሌጁ በሚሰጡ የተለያዩ ስልጠናዎች በመሳተፍ እራሳቸውን የሙያና ክህሎት ባለቤት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
መልካም ስብዕና ያለው ትውልድን በመገንባት ሙስናን በዘላቂነት መከላከል እንደሚገባ ተገለፀ::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮችና ሰራተኞች በአለም አቀፍ ደረጃ ለ21ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ20ኛ ጊዜ "ትውልድን በስነ-ምግባር ተቋምን በአሰራር " በሚል መሪ ቃል የዓለም የፀረ-ሙስና ቀንን በፖናል ውይይት አክብረዋል::
በክብረ በዓሉን ላይ ለሰራተኛው መልዕክት ያስተላለፉት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በንግግራቸው ሙስና በባህሪው በግልፅ የማይታይና ውስብስብ የሆነ መገልጫ ያለው በመሆኑ በመንግስት አቅም ብቻ ተቆጣጥሮ ችግሩን መቅረፍ አይቻልም ያሉ ሲሆን አስተሳሰቡ የዳበረና ሙስናን የሚጠየፍ ትውልድ በመቅረፁ ረገድ እንደ ተቋም የድርሻችንን ማበርከት ይጠበቅብናልም ብለዋል::
የኮሌጁ ዲን አክለውም ሙስና ያልተገባ ጥቅም ማግኘት ብቻ ሳይሆን እንደ ተቋም የአገልግሎት አሰጣጥን በእስታንዳርዱ መሰረት ለዜጎች አለመስጠትንም ይጨምራል ያሉ ሲሆን በዚህም የምንሰጣቸውን አገልግሎቶ ከማዘመን ጀምሮ ሁላችንም ባለንበት የስራ ዘርፍ የድርሻችንን መወጣት ስንችል ሀገር በማሻገር ሂደት ውስጥ አሻይራችንን ማሳረፍ እንችላለንም ብለዋል::
በመድረኩ ክብረ-በዓሉን አስመልክቶ የተዘጋጀው ሰነድ በኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አማካኝነት ለሰራተኛው ቀርቦ ግንዛቤ መፍጠር የተቻለ ሲሆን በቀረበው ሰነድ ላይም በተሳፊዎች ውይይት ተደርጎበታል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
ታህሳስ 15/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ የሥራና ክህሎት ቢሮ ብልጽግና ህብረት የወጣቶች ክንፍ የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሄደ።
የጥያቄና መልሱ መርሃግብር አላማም የብልፅግና ፓርቲ ወጣት አባላትን ለማብቃት ሲሆን በዚህም በፖለቲካዊ፣ በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎች የፓርቲውን ዕሳቤ የተከተለ ተሳታፊነትን ማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶታል።
የጥያቄና መልስ ውድድሩ ጥያቄዎች በዋነኝነት በብልፅግና ፓርቲ መተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም በድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ወጣቶች ክንፍ መተዳደሪያ ደንብ ዙሪያ ላይ ሲሆን ሰፊ ሀገራዊ ጉዳዮችንም የዳሰሰ ሆኗል።
ለጥያቄና መልስ ውድድሩ አሸናፊዎች ማበረታቻ ሽልማት ተበርክቷል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ታህሳስ 15/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የድሬዳዋ አስተዳደተር ስራና ክህሎት ቢሮ ከጤግሮስ ትሬዲንግ ጋር በመተባበር ለአስተዳደራችን ስራ ፈላጊዎች ምርጥ አማራጭ የስራ እድል ይዞ ቀርቧል፡፡
በተመረጡ 4 የንግድ ዘርፎች ባለ ሱቅ ሊያደርጋችሁ ነው
#እንዴት?
በሸቀጣ ሸቀጥ በአልበሳት በኮስሞቲክስ እና በስቴሽነሪ ለተደራጁ ሦስት ሦስት ወጣቶች ሙሉ የሱቅ እቃ በነጻ ያቀርባል በመጀመሪያ የተረከቡትን ሸጠው ሲጨርሱ እና ዋናውን ሲመልሱ ሌላ ዙር ሙሉ የሱቅ እቃ ያቀርባል አሁን ሲጨርሱ ዋናውን መልሰው ሌላ ዙር ይመጣሎታል
#ይህንን አስገራሚ እድል ተጠቃሚ ለመሆን ምን ማድረግ አለብን?
3 ሆኖ መደራጀት ለስልጠና እያንዳንዱ የማህበር አባል 4500 ብር መክፈል (የአሰልጣኞች ወጪና የመመዝገቢያ ) በመጨረሻም ንግድ ፍቃድ አውጥቶ ሱቁን ብቻ ማዘጋጀት፡፡
#ከዛስ?
ከዛማ ምን ጥያቄ አለው የሱቅ ባለቤት በመሆን አስተማማኝ የስራ እድል ይፈጠርላችኋል በአምስት አመት ውስጥ ትልቅ ሱፐር ማርኬት እንዲከፍቱ ድጋፍ ይደረግላችኋል፡፡
ተጨማሪ መረጃ በሁሉም ወረዳዎች (ቀበሌ) የስራ እና ክህሎት ማስተባባሪያ ጎራ እያላችሁ መረጃውን መውሰድ ትችላላችሁ
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
የሳቢያን አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጉብኝት አካሄዱ::
ኮሌጁ ከ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ጋር ባለው ቅንጅትና ተማሪዎች ላይ እየፈጠረ የሚገኘውን ግንዛቤ መነሻ በማድረግ ተማሪዎች ስለዘርፉ ይበልጥ እውቀት እንዲኖራቸው እንዲሁም ኮሌጁ ስልጠናዎችን የሚሰጥበት አጠቃላይ እንቅስቃሴ እንዲመለከቱ ለማድረግ በአካል ተገኝተው እንዲጎበኙ ማድረግ ተችሏል::
ከጉብኝቱ አስቀድሞ ለተማሪዎቹ ኦረንቴሽን የሰጡት የኮሌጁ ም/ል ዲን እና የቴ/ሽ/ኢ/ኤ/አ ዋና ስራ ሂደት ሀላፊ የሆኑት አቶ ተሾመ ሸዋዬ ሲሆኑ በንግግራቸውም በቅድሚያ በቀጣይ የክህሎት ባለቤት ወደሚያደርጋችሁ ኮሌጃችሁ እንኳን በደህና መጣችሁ ያሉ ሲሆን አክለውም እዚህ በኮሌጃችን ላይ የሚሰጡ ስልጠናዎች ከመደበኛው ትምህርት የሚለይባቸው ዋነኛ ምክንያት ሰልጣኞች አምስቱንም የስሜት ህዋሶችን ተጠቅመው የሚሰለጥኑበት በመሆኑ 100% ውጤታማና ብቁ የክህሎት ባለቤት የሆነ ዜጋ የሚፈራበት ዘርፍ በመሆኑ ነውም ብለዋል::
ም/ል ዲኑ አክለውም ኮሌጁ በቀጣይ ተማሪዎቹ ከመደበኛ ትምህርታቸው ጎን ለጎን በአጫጭር ስልጠናዎች በመረጡት የሙያ መስክ በማሰልጠን የሙያ ባለቤት ለማድረግ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልፀው ተማሪዎች በቀጣይ በኮሌጁ የሚኖራቸውን ቆይታ ራሳቸውን ለማብቃት ሊጠቀሙበት እንደሚገባም አሳስበዋል::
የሳቢያን አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በጉብኝቱ ኮሌጁ ያለውን የማሰልጠን አቅምና STEMን መሰረት ያረጉ የማሰልጠኛ ወክሾፖችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን በቀጣይም በአጫጭር ስልጠና ማዕቀፍ በFinishing እንዲሁም በFurniture Making ሙያ ስልጠናዎችን በተከታታይ የሚሰለጥኑ መሆኑም ተገልፇል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
የሆቴልና ሆስፒታሊቲ ኢንዱስትሪ ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች እንዲመራ ኮሌጁ አስፈላጊውን ስራ እንደሚሰራ ገለጸ፡፡
#ዜና|የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሳምራት ሆቴል ባለሙያዎችን በአጫጭር ስልጠና በሆቴልና ሆስፒታሊቲ ዘርፍ አስመረቀ፡፡
የሆቴልና ሆስፒታሊቲ ዘርፍ ክህሎትና እውቀት ያለው በቂ ባለሙያ የሚፈልግ ነው፡፡ ይህን ኢንዱስትሪ ለማሳደግ ደግሞ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአጫጭርና በረጃጅም ስልጠናዎች ባለሙያዎችን እያፈራ ይገኛል ያሉት የኮሌጁ ዲን ተወካይ አቶ ዘየደ ተክሌ ሲሆኑ አያይዘውም ድሬዳዋ ከተማ የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመት እንደመሆኗ መጠን ከተማችን ባላት የቱሪዝም መዳረሻዎች ከተማዋን ለመጎብኘት የሚመጡ እንግዶችን ተቀብሎ ለማስተናገድ ብቃት ያላቸው ባለሙያዎች ያስፈልጋሉ ስለዚህ እነዚህን ባለሙያዎች ለማፍራት ደግሞ ኮሌጁ በትጋት እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
በመቀጠልም በምርቃት መርሃ-ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የሳምራት ሆቴል ተወካይ አቶ መልካሙ እንዳሉት ሆቴሉ በፍጥነት እያደገችና ብዙ ታሪኮች ባላት ትልቅ ከተማ ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች እንዲሁም ከውጪ ሀገራት የሚመጡ እንግዶችን እየተቀበለና ተገቢውን መስተንግዶ እየሰጠ የሚገኝ ትልቅ ሆቴል ነው ያሉ ሲሆን አያይዘውም በዚህ ሆቴል ውስጥ እየሰሩ የሚገኙ ሰራተኞች ያላቸውን ሙያዊ ክፍተቶች ከኮሌጁ ጋር በመሆን ለመሙላት የተሰሩ ስራዎች እጅግ በጣም የሚያረካና በቀጣይም በተለያዩ ሙያዎች ከኮሌጁ ጋር አብረን እንድንሰራ የሚያነሳሳ ነው ብለዋል፡፡በመጨረሻም ይህን ስልጠና በአግባቡ ሲያሰለጥኑ ለነበሩ የኮሌጁ መምህራኖችና የኮሌጁ ኃላፊዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በመጨረሻም በምረቃት መርሃ ግብሩላይ መልእክት ያስተላለፉት በስራና ክህሎት ቢሮ የCOC ማእከል ተወካይ አቶ መኳንንት እንዳሉት የሆቴልና ሆስፒታሊቲ ዘርፉን ለማሳደግ ከሚሰጠው ትምህርት ስልጠና ጎን ለጎን ባለሙያዎች ብቁ መሆናቸውን የማረጋገጥ ስራ መስራት ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን አያይዘውም የCOC ማእከሉ በተለያዩ ተቋማት የሚገኙ ባለሙያዎችን በአጫጭርም ሆነ በረጃጅም ሙያዎች የሰለጠኑ እንዲሁም በልምድ የተገኘ እውቀቶችን የመመዘን ስራዎችን የሚሰራ ይሆናል ብለዋል፡፡ይህም የስራ ዘርፎቹ ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች እንዲመሩ ያስችላል ብለዋል፡፡
ኮሌጁ ያስመረቃቸው የሳምራት ባለሙያዎች በአጠቃላይ 80 የሚሆኑ ሰልጣኞች ሲሆኑ Front office, Food and Beverage service, Housekeeping እና Food Preparation ሙያዎች በስራ ቦታቸው ላይ በመሆን(in company Training ) ስልጠናውን መስጠት እንደተቻለ ለማወቅ ተችሏል፡፡በመጨረሻም በሆቴሉ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ሰራተኞች የእውቅና መርሃ ግብር ተከናውኗል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ
Repost from Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ትልሞች በሦስት ዋና ጉዳዮች ያተኩራሉ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ትልሞች በዋናነት በሦስት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ማጠቃለያ እና በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 በይፋ የማስመጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በዚሁ ወቅትም የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ዋና ራዕዩን ሰብሰብ አድርገን ስንገልጸው ሦስት ነገሮችን ለማሟላት ያለመ ነው ብለዋል።
በዚህም መሠረት የመጀመሪያው አቅርቦት(አክሰስ) መሆኑን ገልጸው፤ ይህ ማለት ሁሉም ዜጎች ካሉበት ሆነው የሚፈልጉትን አገልግሎት ማግኘት የሚችሉበትን ዕድል መፍጠር መሆኑን አስረድተዋል።
በመሆኑም ዜጎች እኩል እድል እና እኩል አገልግሎት እንዲያገኙ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የመጀመሪያ ትልሙ አቅርቦት ነው ብለዋል።
ሁለተኛው ዕድል(ኦፖርቹኒቲ) መሆኑን አመላክተው፤ እኩል እድል ባልሰጠንበት መስክና ሁኔታ እኩል ተጠቃሚ መሆን አይቻልም ነው ያሉት በማብራሪያቸው።
በጾታ፣ በአካል ጉዳት ወይም በርቀት ምክንያት ዜጎች ሊያገኙ የሚገባውን እድል እኩል የሚያመቻች ሥርዓት መፍጠር እንደሚያስፈልግም ነው ያስገነዘቡት።
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 እንዲያሳካ ከሚፈለጉት ጉዳዮች አንዱ ለዜጎች እኩል እድል መስጠት መሆኑንም አመላክተዋል።
ሦስተኛው ዲጂታል ኢትይጵያ 2030 እንዲያሳከው የሚፈለገው ትልም መተማመን(ትረስት) መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም መሠረት በዜጎችና በተቋማት መካከል መተማመን ካልተፈጠረ፤ የገንዘብ ዝውውር፣ መማር ማስተማር፣ ለጤና ዳታ መስጠት፣ ደፍሮ ለሥራ ማመልከት፣ የግል መረጃን በክላውድ ላይ ማስቀመጥ የሚታሰብ አይደለም ሲሉ አብራርተዋል።
ቴክኖሎጂ አሳላጭ መሆን ተስኖት በጥርጣሬ የሚታይና የሚፈራ ብሎም ዜጎች የማያምኑበት ከሆነ የምናስበውን ነገር አያሳካም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በገለጻቸው።
ሦስቱ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ትልሞች አቅርቦት፣ ዕድል እና መተማመን ተደምረው ለዜጎች በርከት ያለ የሥራ ዕድል መፍጠር ብሎም ለሀገር ዕድገት ማረጋገጥ አለባቸው ብለዋል።
ሥራ እና ዕድገት ብቻውን በቂ እንዳልሆነ የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፤ ሉዓላዊነትንም የሚያረጋግጥ መሆን እንዳለበት አስረድተዋል።
ስለዚህ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ከላይ በተገለጹት ጉዳዮች ላይ አተኩሮ የኢትዮጵያን ብልጽግና ከሚያረጋግጡ ዋና ዋና ሴክተሮች(ምሠሦዎች) አንዱ ሆኖ ያገለግላል ተብሎ በመንግሥት መታሰቡን አውስተዋል።
በመሆኑም በትብብር ከሠራን ይህን ራዕይ እንደምናሳካ ሙሉ እምነት አለኝ ሲሉም ተናግረዋል። ዘገባው የኢዜአ ነው።
ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም
🔗ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
Repost from Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ዋና ዋና አምዶች; ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም
🔗ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
Repost from Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
𝟮.𝟱 𝘆𝗲𝗮𝗿𝘀, 𝟭.𝟭 𝗠𝗶𝗹𝗹𝗶𝗼𝗻+ 𝘆𝗼𝘂𝘁𝗵 𝗥𝗲𝗮𝗰𝗵𝗲𝗱, 𝟯𝟮𝟱,𝟬𝟬𝟬+ 𝘆𝗼𝘂𝘁𝗵 𝗶𝗻 𝘄𝗼𝗿𝗸 𝗿𝗲𝗴𝗶𝘀𝘁𝗲𝗿𝗲𝗱, 𝗘𝗧𝗕 𝟯.𝟳𝟭+ 𝗕𝗶𝗹𝗹𝗶𝗼𝗻 𝗗𝗶𝘀𝗯𝘂𝗿𝘀𝗲𝗱.
-----------------------------------------
The SEED Program, led by EDI in partnership with MastercardFoundation, is delivering measurable results for youth employment in Ethiopia. In just two and a half years the program has:
✅ Reached 1,167,804 youth.
✅ Connected 325,204 young people to sustainable work opportunities.
✅Supported 52,300 enterprises in scaling their operations.
✅Facilitated ETB 3.71 Billion in financing for 16,320 SMEs and startups through CBE.
We have reached our 5-year goal early by reaching targeted youth ~(1.1 million) and training 1,022 TVT leaders (102.2% of target).
Our commitment to equity remains firm: 78% of our outreach participants are women, and we have successfully integrated 3,270 vulnerable youth into the workforce.
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
+7
የአሰልጣኝ መምህሩን አቅም መገንባት የስልጠና ጥራቱን ከማሻሻል አንጻር የላቀ ሚና እንደሚጫወት ተገለፀ::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ሂደት በምሽት ስልጠና በተለያዩ ሙያዎች ስልጠና ለሚሰጡ አዲስ አሰልጣኝ መምህራን የማሰልጠን ስነ-ዘዴ (Training Methodology) ስልጠና ሰጠ::
ስልጠናው ለአሰልጣኝ መምህራኑ ከስልጠና ጥራት ጋር ተያይዞ የዘርፉን እሳቤ ተረድተው ስልጠናውን በሚፈለገው ደረጃ መስጠት እንዲያስችላቸው እንዲሁም ከምዘና ሂደት እና የምዘና ውጤት አገባብ ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ከወዲሁ ለማስቀረት ታሳቢ ያደረገ ስልጠና እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን የሚነሱ ተያያዥ ቅሬታዎችንም ለመፍታት ያግዛልም ተብሏል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
ታህሳስ 11/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
