es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Ir al canal en Telegram
1 318
Suscriptores
Sin datos24 horas
+207 días
+14930 días
Archivo de publicaciones
ጥቃቅንነና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ለአጠቃላይ ኢኮኖሚው እድገት የሚያበረክቱት ሚና የጎላ መሆኑ ተገለፀ። በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሞዴል ኢንተርፕራይዞች የምርቃትና ሽግግር በዓል ተካሂዷል በመድረኩ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ በአገራችን እንዲሁም እንደ አስተዳደር የጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ ያለውን የስራ አጥነት ችግር በመቀነስ እንዲሁም ዜጎች የራሳቸውን ስራ በመፍጠር ውጤታማ ከመሆን ባለፈ ለሌሎች የስራ እድል እንዲፈጥሩ እያስቻለ እንደሚገኝ ገልፀዋል። ዘርፉ በአንድ ተቋም ጥረት ብቻ አመርቂ ውጤት ለማምጣት እንደማይቻል አውስተው ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት አንደየ አግባቡ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ አቶ ሀርቢ መልክት አሰወተላልፈዋል። አስተዳደሩ በዘርፉ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን ከመቅረፍ አኳያ እንደ መፍትሄ የሚቀርቡ እቅዶችን በቀጣይ ተግባራዊ እንዲሆኑ ተገቢውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ምክትል ከንቲባው አመላክተዋል። የድረደዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በበኩላቸው በየዓመቱ የሞዴል ኢንተርፕራይዞች ምርቃትና ሽግግር እንደሚካሄድ ገልፀዋል። በዛሬው መድረክም በከተማም በገጠርም የተለያዩ ድጋፍ ሲደረግላቸው የቆዩ ኢንተርፕራይዞች የእድገት ደረጃ እውቅና ሰርተፍኬት፣በቅድመ ሞዴልነት ተመልምለው የተደረላቸውን ድጋፍ በአግባቡ ተጠቅመው ወደ ሞዴልነት የተሸጋገሩ ኢንተርፕራይዞች እውቅና ሰርተፍኬት እንዲሁም የተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን ድጋፎችን ተጠቅመው የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ አንቀሳቃሾች እውቅና እንደተሰጠ ገልፀዋል። በዘርፉ ከከተማው ክፍል በተጨማሪ በገጠር፣ ከስደት ተመላሾች እንዲሁም አካል ጉዳተኞች ተሰማርተው ውጤት እንዲያመጡ ብሎም ሌሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ አቅሞችን እንዲፈጥሩ የሚያስችሉ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቢሮ ኃላፊው ጠቁመዋል። ©️ DGC | ሰኔ 21/2018

በድሬዳዋ ለ7ኛ ጊዜ የተካሄደው የ“ብሩህ” የንግድ ፈጠራ ውድድር ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል እየፈጠረ መሆኑ ተገለጸ። የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ያዘጋጀው የ2018 ዓ.ም “ብሩህ” የንግድ ፈጠራ ስራ ውድድር፤ ተወዳዳሪዎች የፈጠራ እቅዳቸውን ወደ ተግባር በመቀየር ራሳቸውን እንዲችሉና ለሌሎች ዜጎችም ሰፊ የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩ መንገድ እያመቻቸ መሆኑ ተገለጸ። በአስተዳደር ደረጃ ለ7ኛ ጊዜ በተካሄደው በዚህ ውድድር ላይ ከተረፈ ምርት የሚወጣ ነዳጅ እና የዲጂታል መተግበሪያዎችን ጨምሮ በርካታ አዳዲስና ዘመናዊ የፈጠራ ስራዎች ቀርበዋል። ​ ​የውድድሩ ዋና ዓላማ የንግድ ፈጠራ ሥልጠናና ዕውቀት ያላቸው ወጣቶች የፈጠራ ሀሳባቸውን ከወረቀት ወደ ተግባር እንዲያሸጋግሩ ማገዝ ሲሆን፤ ይህም ከውድድር ባለፈ በተጨባጭ የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። ​የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በውድድሩ ላይ እንደገለጹት፤ በየዓመቱ በዚህ መድረክ ላይ የሚሳተፉ ወጣቶች የራሳቸውን የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ፣ ለሌሎች በርካታ ዜጎችም የሥራ ዕድል ማበርከት ችለዋል። ​በቢሮው የሥራ ዕድል ፈጠራና የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማስተባበሪያ ዳይሬክተር አቶ ሰኢድ አሊ በበኩላቸው፤ ከተረጂነት አስተሳሰብ ለመላቀቅ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የፈጠራ ሀሳብ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰዋል። ይህ ውድድር ዜጎች ሀሳባቸውን ወደ ተግባር እንዲቀይሩ ጉልህ ሚና እንደሚጫወትና በውድድሩ ካለው ተስፋ ሰጪ አቅም መነሻነት በሀገር አቀፍ ደረጃ ተሸላሚ የሚሆኑ ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ከድሬዳዋ እንደሚወጡ ይጠበቃል ብለዋል። ​በዘንድሮው የ2018 ዓ.ም የ“ብሩህ” የፈጠራ ውድድር ላይ በርካታ ጠቃሚና አዳዲስ የፈጠራ ሀሳቦች ለውድድር የቀረቡ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል መልሶ ጥቅም ላይ የሚውል የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ (ፓድ) ሁሉንም አገልግሎቶች በአንድ ላይ የያዘ የዲጂታል መተግበሪያ ፣ ከቆሻሻና ከተረፈ ምርቶች የቤንዚንና ናፍጣ ነዳጅ ማውጫ ቴክኖሎጂ፣ ዘመናዊ የእህል መውቂያ ማሽን እና በአንድ ጊዜ ብዙ እንጀራ መጋገር የሚችል ምጣድ፣ የፕላስቲክ ውጤቶችን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋያ ቴክኖሎጂ፣ የዲጂታል ገበያ ትስስር ሥርዓት እና የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያዎች ይገኙበታል። ​ይህ በአስተዳደሩ ለሰባተኛ ጊዜ የተካሄደው ውድድር አሸናፊዎች በቀጣይ በሚዘጋጅ ትልቅ መድረክ ላይ ይፋ የሚደረጉ ሲሆን፤ በውድድሩ የላቀ ውጤት የሚያስመዘግቡት ተወዳዳሪዎች ድሬዳዋን ወክለው በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው የ“ብሩህ” የንግድ ፈጠራ ሀሳብ ውድድር ላይ የመሳተፍ ዕድል እንደሚመቻችላቸው ከመድረኩ ተመልክቷል። ​ ©️ DireTvአማርኛ | ሰኔ 20 ፥ 2018 ዓ.ም | ድሬዳዋ

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ EASE ፕሮጀክት የአምራች ኢንዱስትሪው ፍላጎትን መነሻ አድርጎ በኮሌጁ የተዘጋጀው የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ማጠቃለያ መድረክ ተካሄደ:: #EIPC ሰኔ 19/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ በEASE ፕሮጀክት ድጋፍ በኮሌጁ በተዘጋጀው ጥናት በቴክኒክና ሙያ ስልጠና፣ በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ እንዱስትሪውን ከመደገፍ አኳያ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ታልሞ በጥናት ቡድኑ የተዘጋጀ ሲሆን የኮሌጁ ኢንዱስትሪ እድቫይዘሪንግ ቦርድ አባላት በተገኙበት የማጠቃለያ ሪፓርት ቀርቧል:: ኮሌጁ ከኢንዱስሪዎች ጋር ያለውን ትስስር ውጤታማነት ለማረጋገጥ የጥናት ቡድኑ በአጭር ፣በመካከለኛና በረጅም ጊዜ የሚተገበሩ ዝርዝር ጉዳዮችን በዳሰሳ ጥናቱ ማስቀመጡን የገለፁት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ሲሆኑ አክለውም በኮሌጁ የተካሄዱ ጥናቶችን ወደ ተግባር ለመቀየር ጊዜ ሳይወስድ ትግበራ ማስጀመር እንደሚገባም አሳስበው በትግበራው የተመዘገቡ ውጤቶችን በየጊዜው መገምገም እንደሚገባም ተናግረዋል:: የፍላጎት ዳሰሳ ጥናቱ በአስተዳደሩ በሚገኙና የትኩረት ዘርፍ በሆኑ ሶስት አምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ መካሄዱን የገለፁት በኮሌጁ የEASE ፕሮጀክት አስተባባሪ ኢ/ር ፋሲል ማዘንጊያ ሲሆኑ በቀጣይ ተሞክሮችን በመቀመርና አቅምን በማጎልብት ወደ ሌሎች ኢንዱስትሪዎችም የማስፋት ተግባር እንደሚከናወን ገልፀዋል:: በዳሰሳ ጥናቱ ማጠቃለያ ላይ በቀረበው ሪፖርት ከኢንዱስትሪ ተወካዮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን በቀጣይ የሚኖረው ትግበራ ውጤታማነትን ለማረጋገጥ አምራች ኢንዱስትሪዎች ሊያከናውኗቸው የሚገቡ ዝርዝር ጉዳዮችም በመድረኩ ተመላክተዋል:: ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡- በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001 በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/@ethioitaly2001?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1 በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/

የምስራቅ አፍሪካ የቴክኒክና ሙያ ልህቀት ማእከል የሆነው የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዘንድሮ አመት የ12ኛ ክፍል ፈተና ለሚፈተኑ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት አጠናቃቂዎች ተግባር ተኮር የኮምፒተር አጠ
+4
የምስራቅ አፍሪካ የቴክኒክና ሙያ ልህቀት ማእከል የሆነው የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዘንድሮ አመት የ12ኛ ክፍል ፈተና ለሚፈተኑ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት አጠናቃቂዎች ተግባር ተኮር የኮምፒተር አጠቃቀም ስልጠና እየሰጠ ይገኛል ኮሌጁ ከትንሿ ኢትዮጵያ የፍቅር ከተማ በሆነችወ ድሬዳዋ አስተዳደር ከተለያዩ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የመልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች መሰረታዊ የኮምፒተር አጠቃቀም ስልጠና በመሰጠት የሞዴል ፈተና እንዲወስዱ እያደረገ ይገኛል፡፡ በዚህም በ 2018 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚሰጠው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና በበይነ መረብ (ኦንላይን) ለመፈተን የሚያስችላቸውን ክህሎት እንዲያገኙ እና ከመፈተኛ ሲስተሙ ጋር እንዲግባቡ የሚያስችል ክህሎት መስጠት ተችሏል፡፡ በኮሌጁ የተተገበረው ይህ ስራ ተማሪዎችን ለፈተና ከማዘጋጀትም ባሻገር መሰረታዊ የኮምፒተር አጠቃቀም ክህሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን ላለፉት 5 ተከታታይ ቀናት ያለምንም ችግር ሞዴል ፈተናቸውን እንዲወስዱም አስችሏል፡፡ ኮሌጁ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ዙሮች ከ13 በላይ የመፈተኛ ክፍሎችን በማዘጋጀት ተፈታኞች ያለምንም ችግር ፈተናቸውን እንዲወስዱ የሚያስችል ተግባሮችን በስኬት ማጠናቀቁ የሚታወስ ሲሆን በዘንድሮ አመትም ይህ ተግባር በተሸለ መልኩ እንዲተገበር የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በመስራት ፈተናው ያለ ምንም ችግር እንዲሰጥ ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ሰኔ 19/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ በተቋማት አቅም ግንባታ ዙሪያ ከአሰልጣኝ መምህራን ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ።

“የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ስኬት የሚለካው በተመራቂዎች ብዛት ብቻ አይደለም፣ በፈጠሩት ሥራ፤ በመሰረቱት ኢንተርፕራይዞች እና በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ባሳደሩት ተጽዕኖ ጭምር ነው” ክቡር አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት ተጠሪ እና የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ስር የሚገኙ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆች አሰልጣኝ መምህራንና ባለሙያዎች እንዲሁም የዲፓርትመንት ተጠሪዎችን አቅም ለማሳደግ የሚያስችል "የ21ኛው ክፍለ ዘመን የTVET ራዕይ: ከክህሎት ወደ ሀገራዊ ኢኮኖሚያዊ ትራንስፎርሜሽን" በሚል መሪ ሀሳብ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት ተጠሪ እና የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል፡፡ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት እውቀትን ከክህሎት ጋር አሰናስለው እጀ- ወርቅ ባለሙያ እንዲሆኑ በማገዝ እረገድ የቴክኒክ ሙያ እና ትምህርት ስልጠና ጥራትን በማሻሻል ከዘመናዊ የዲጂታል የስራ ገበያ ጋር የተጣጣሙ የስራ ፈጠራ ክህሎቶችን በማዳበር  ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸው ይህም በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በዓለም የሥራ ገበያ ላይ ስኬታማ ለመሆን በራስ መተማመንን ያጎናፅፋል ብለዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በበኩላቸው ነባሩን ትምህርትና ስልጠና ጥራት ባለው መልኩ በአዲስ መልክ ፖሊሲን በማሻሻል ጠንካራ ተቋማትን በመፍጠር ሂደት ወስጥ ውጤታማ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አንስተው ትውልድን በመቅረጽ እና ሀገርን በማሻገር በተቋም ግንባታ ቢሮው በሰው ሀይል በቴክኖሎጂ፣ በግብዓት አቅርቦት እንዲሁም ክህሎትን በብቃት የተላበሰ የሰው ሀይልን በመፍጠር ረገድ አመርቂ ስራዎች መሰራታቸውን የተናገሩ ሲሆን በቀረበውም ገለጻ ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሰኔ 18/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

#አሁን #Happeningnow በአስተዳደሩ ለሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራንና አጠቃላይ ማህበረሰብ "የ21ኛው ክፍለ ዘመን የTVET ራዕይ: ከክህሎት ወደ ሀገራዊ ኢ
+4
#አሁን #Happeningnow በአስተዳደሩ ለሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራንና አጠቃላይ ማህበረሰብ "የ21ኛው ክፍለ ዘመን የTVET ራዕይ: ከክህሎት ወደ ሀገራዊ ኢኮኖሚያዊ ትራንስፎርሜሽን" በሚል መሪ ሀሳብ ሰነድ እየቀረበ ይገኛል። ሰኔ  18/2018 ዓ.ም፤ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የEASE (Education and Skills for Employability) ፕሮጀክት ትግበራ አጠቃላይ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ:: EIPC ሰኔ 17/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ የEASE ፕሮጀክት በኮሌጁ ትግበራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ባለፋት ሁለት አመታት የነበረውን አጠቃላይ የፕሮጀክቱ አፈፃፀም ከአለም ባንክ እንዲሁም ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር የተወጣጡ የፕሮጀክቱ ሀላፊዎችን ያካተተ ልኡካን ቡድን የኮሌጁ አድቫይዘሪንግ ቦርድ በተገኘበት የፕሮጀክቱን አፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል:: የፕሮጀክቱ ትግበራ አፈፃፀም ሪፖርት በኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አማካኝነት ለልዑካን ቡድኑ የቀረበ ሲሆን በዚህም የEASE(Education and Skills for Employability ፕሮጀክት ትግበራ ትኩረት ከሚያደርግባቸው ስምንቱ Sub-Components አኳያ የተሰሩ ስራዎችን በዝርዝር አቅርበዋል:: በቀረበው ሪፖርት መሰረት በፕሮጀክቱ የሁለት አመት ቆይታ ከተከናወኑ ቁልፍ ተግባራት መካከል …. - የአሰልጣኝ መምህራን እና ሰራተኞች አቅም ግንባታ... - የወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ... - የኢንዱስትሪዎች ትስስርን የማጎልበት... - በኮሌጁ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ ስራዎች... - የICT መሰረተ ልማት ዝርጋታ... - ኮሌጁን ኢንተርፕሩነር ለማድረግ የተሰሩ ስራዎች... - ሴት ሰልጣኞች እና ሴት ሰራተኞችን በልዩ ሁኔታ የማብቃት የመደግፍ ስራ... - እንዲሁም አካታችነት ላይ ሴቶችና አካል ጉዳተኞችን የመደገፍና የማቋቋም ስራዎች በኮሌጁ በEASE ፕሮጀክት ባለፉት ሁለት አመታት ከተከናወኑ ቁልፍ ተግባራት መካከል እንደሚጠቀሱ በሪፖርቱ ተመላክቷል:: የልኡካን ቡድኑ ከቀረበው የአፈፃፀም ሪፖርት ባሻገር በEASE ፕሮጀክት በኮሌጁ የተከናወኑ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን በተጨማሪም በኢንዱስትሪ ትስስር ላይ የተከናወኑ ውጤታማ ስራዎችንም እንዱስትሪዎች ላይ በአካል በመገኘት ምልከታም አድርገዋል:: ኮሌጁ በEASE ፕሮጀክት ባሳየው የላቀ አፈፃፀም መደነቃቸውን የገለፁት በዓለም ባንክ የEASE ፕሮጀክት የሥራ ቡድን መሪ የሆኑት አና ኦሌፊር (Anna Olefir) ሲሆኑ አክለውም ኮሌጁ አሁን ያለበት የአፈፃፀም ደረጃ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው በመግለፅ በቀጣይ ትኩረት ይሻሉ ያሏቸውንም ጉዳዮች አመላክተዋል:: በኢፌዲሪ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት የሥልጠና እና አቅም ግንባታ ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና በሀገር አቀፍ የEASE ፕሮጀክት ዋና አስተባባሪ ሀፍቶም ገ/እግዚአብሔር (ዶ/ር) በበኩላቸው የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የEASE (Education and Skills for Employability) ፕሮጀክት በኮሌጁ ትግበራውን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በሁሉም መመዘኛ የተሻለ አፈፃፀም እያሳየ የመጣ ተቋም መሆኑን አስታውሰው ለዚህ ውጤት መገኘት የኮሌጁ አመራሮች እንዲሁም በኮሌጁ የሚገኙ የፕሮጀክቱ አስተባባሪና ባለሙያዎች ያሳዩት ቁርጠኝነትና በቅንጅት የመስራት አቅም መሆኑንም ገልፀዋል:: የEASE ፕሮጀክት ከአለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በሀገሪቱ በሚገኙ 24 ኮሌጆች በመተግበር ላይ የሚገኝ ፕሮጀክት ነው:: ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡- በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001 በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/@ethioitaly2001?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1 በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/

ኮሌጁ በ2018 ዓ.ም ያስመዘገባቸውን ስኬቶች በቀጣይነት በማስቀጠል የአካባቢው ማህበረሰብ እውቀትና ክህሎት የሚያገኙበት ምርጥ ተቋም እንዲሆን በጋራ መስራት ይኖርብናል ተባለ፡፡ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ 2018 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም እና የ 2019 በጀት አመት እቅድ የኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራን እንዲሁም የአስተዳደር ሰራተኞች በተገኙበት የውይይት እና የግምገማ መድረክ በዛሬው እለት አካሄደ ።  በ2018 ዓ.ም በጀት አመት ከትምህርትና ስልጠና፣በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት፣ ለኮሌጁ በገቢ እራሱን ለመቻል አንጻር አንዲሁም በአጫጭር ስልጠና እና ከኢንዱስትሪዎች ጋር መልካም ትስስርን በመፍጠር አንጻር በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን እና ስራዎቹም ፍሬ ያፈሩበት አመት ነበር ያሉት የኮሌጁ ውጤት ተኮር ት/ስልጠና ም/ዲን የሆኑት አቶ ቢቂላ ታደሰ ሲሆኑ ኮሌጁ የማህበረሰቡን ችግር ለመፍታት እንዲሁም የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች የሚፈልቁበት ተቋም እንዲሆን የተለያዩ ስራዎች በቀጣይ የሚሰሩ ይሆናል ብለዋል፡፡አያይዘውም በመጠናቀቅ ላይ ባለው በጀት አመት ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች በማስቀጠል የአካባቢው ማህበረሰብ አስፈላጊውን አገልግሎት የሚያገኙበት ተቋም እንዲሆን በጋራ  መስራት ይኖርብናል ብለዋል፡፡ በእለቱ በቀረበው የ2018 ዓ.ም በጀት አመት አፈጻጸም ሪፖርት ኮሌጁ ያስመዘገባቸው ስኬቶች በተለይ በትምህርትና ስልጠና፣በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት፣ለኮሌጁ ተጨማሪ ገቢን ከማስገኘት አንጻር አንዲሁም በአጫጭር ስልጠና እና ከኢንዱስትሪዎች ጋር መልካም ትስስርን በመፍጠርና ተተኪ መለዋወጫ ምርቶችን ከማምረት እና ገጽታ ግንባታ ስራዎች እንዲሁም ስራዎችን ለማቀላጠፍ የሚረዳውን የዲጂታላይዜሽን ስራ እና የስልጠና ጥራትንና የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት  ላይ  በትኩረት የተሰራባቸው ዋና ዋና ዘርፎች ሲሆኑ በቀጣይም እነዚህ ስራዎች በስፋትና በጥራት ትኩረት ሰጥቶባቸው  በመስራት የአካባቢውን ማህበረሰብ በቴክኖሎጂ እንዲሁም በተለያዩ አገልግሎቶች ተጠቃሚ እንዱሆኑ የሚሰራ መሆኑን በእለቱ ከቀረበው ሪፖርት ማወቅ ተችሏል፡፡ በእለቱም በበጀት አመቱ የተሰሩ እንዲሁም ደግሞ በ 2019 በጀት አመት ለመስራት የታቀዱ ስራዎች በኮሌጁ የእቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ኃላፊ በሆኑት በአቶ ዘየደ ተክሌ የቀረበ ሲሆን በአፈጻጸሙ ላይና በእቅዱ ላይ ሰፊ ውይይትም ተደርጓል ።በተጨማሪም የኮሌጁን አንድነትና ህብረት በሚያጠናክሩ ስራዎች ላይ በስፋት ውይይት ተደርጓል፡፡   የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ሰኔ 17/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

#ዜና | በድሬዳዋ ከ150 በላይ ወጣቶች በአጭር ጊዜ የሙያ ስልጠና ተመረቁ:: የኤስ ኦ ኤስ ሐረር ህፃናት መንደር ድሬዳዋ ፕሮጀክት እና የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በመተባበር፣ ላለፉት ሶስት ወራት በአጭር ጊዜ የሙያ ክህሎት ስልጠና ሲከታተሉ የነበሩ 151 ወጣቶችን አስመረቁ። ​በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ እንደተገለጸው፣ ስልጠናው በዋናነት ያተኮረው የወጣቶችን የስራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ እና በገበያው ላይ ተፈላጊ የሆኑ የክህሎት ክፍተቶችን ለመሙላት ነው። ​ሰልጣኞቹ በሆቴልና ቱሪዝም፣ በኤሌክትሪካል፣ በግንባታ እንዲሁም በኮምፒውተርና መረጃ ቴክኖሎጂ (ICT) ስር በሚገኙ 7 የሙያ መስኮች የንድፈ-ሀሳብና የተግባር ትምህርታቸውን አጠናቀዋል። ከእነዚህ ተመራቂዎች መካከል 91 ያህሉ ሴቶች መሆናቸው፣ ፕሮጀክቱ ሴቶችን በኢኮኖሚው ዘርፍ ተጠቃሚ ለማድረግ ለሰጠው ትኩረት ማሳያ መሆኑ ተጠቅሷል። ​ ​የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በምረቃው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ተቋማቸው ከኤስ ኦ ኤስ ጋር በመሆን የወጣቶችን ስራ አጥነት ለመቅረፍ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በሁለቱ ወገኖች መካከል የተደረገውን የ5 ዓመት ስምምነት አስመልክተው ሲያብራሩም "በዚህ ስትራቴጂካዊ ስምምነት መሰረት፣ በቀጣይ ዓመታት ከ2 ሺህ በላይ ወጣቶችን በአጭርና በረጅም ጊዜ ስልጠናዎች የሙያ ባለቤት ለማድረግ አቅደን እየሰራን እንገኛለን።" ብለዋል። ​ዲኑ አክለውም ምሩቃን በቆይታቸው የቀሰሙትን ዘመናዊ ቴክኒካዊ እውቀትና ክህሎት ወደ ተግባር በመቀየር፣ ራሳቸውን ችለው ሀገራቸውን እንዲጠቅሙ አሳስበዋል። ​የኤስ ኦ ኤስ ህፃናት መንደር ድሬዳዋ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ አቶ ሚካኤል ስንታየሁ በበኩላቸው፣ ድርጅቱ በ170 ሀገራት እንዲሁም በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች በችግር ውስጥ ያሉ ህጻናትን መልሶ ማቋቋምና የአካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚ ማድረግ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል። ወጣቶችን በሙያ አሰልጥኖና አቅማቸውን ገንብቶ ለሥራ ገበታ ማብቃትም የድርጅቱ ሌላኛውና ዋነኛ ዓላማ መሆኑን አብራርተዋል። ​የእለቱ ተመራቂዎች በሰጡት አስተያየት፣ ከኮሌጁ ያገኙት ተግባራዊና ጥራት ያለው ክህሎት በስራ ገበያው ላይ ተወዳዳሪና በራሳቸው የሚተማመኑ እንደሚያደርጋቸው ጠቅሰዋል። በተማሩበት የሙያ ዘርፍ ተሰማርተው የራሳቸውን ስራ ለመፍጠርም ሆነ በተቀጣሪነት ለሀገራቸው ውጤታማ ስራዎችን ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውን በኩራት ገልጸዋል። #DireTvአማርኛ | ሰኔ 12 ፥ 2018 ዓ.ም | ድሬዳዋ ​