1 330
Suscriptores
Sin datos24 horas
+97 días
+8030 días
Archivo de publicaciones
የድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የISO 9001:2015 የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ባለቤት ሆነ።
በድሬዳዋ አስተዳደር ከሚገኙት የመንግስት ኮሌጆች አንዱ የሆነው የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የትምህርት ስርዓት የጥራት ማረጋገጫ እና የብቃት መመዘኛ ISO 9001:2015 QMS አለም አቀፍ ሰርተፊኬት አገኘ።
በሰርተፊኬት ርክክብ ስነ-ስርአቱ ላይ የተገኙት የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ እንዲሁም የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ሀርቢ ቡህ በድሬዳዋ 233 አነስተኛ ፣ 70 መካከለኛ እና 36 ከፍተኛ የኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች እንደተመዘገበ ጠቁመው የምስራቋ የኢንደስትሪ ኮሪደር እንደመሆኗ መጠን በኮሌጁ የሰለጠኑ ባለሙያዎችና ከፍተኛ የሰው ሃይል እንደሚያስፈልጋት አረጋግጠዋል።
ጥራት ያለው የሰው ሃይል ለማፍራት ፤ ጥራት ባለው የትምህርት ስርዓት እና ምዘና ማለፍ ይገባል ሲሉ በመክፈቻ ንግግራቸው ወቅት የገለፁት የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ሃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ሲሆኑ በብቃት የሰለጠነ የሰው ሃይልን በማፍራት ለኢንደስትሪው ማበርከት ይጠበቅብናል ሲሉ ተናግረዋል።
በመድረኩ ላይ በእንግድነት የተገኙት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ነቢሃ መሀመድ እንደገለፁት በሀገር አቀፍ ደረጃ እድሉን ካገኙ 20 ትቋማት መካከል 5ቱ እራሳቸውን በጥራት ደረጃ ማሳለፍ መቻላቸውንና ከእነዚህም መካከል የኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እንዱ መሆኑን አስታውቀዋል።
አክለውም ይህ የጥራት ማረጋገጫ ከምስራቅ ኢትዮጵያ የመጀመሪያው እንደሚያደርገው ገልፀው በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እና ተፈላጊ ባለሙያዎችን በማሰልጠን የስራ እድልን ከመፍጠር በዘለለ ትልልቅ ድርጅቶችንና ኩባንያዎችን የሚያንቀሳቅሱ ለማድረግ መታቀዱን ጠቁመዋል።
የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬቱን ለኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ያስረከቡት የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መዓዛ አበራ ተቋማቸው በሀገሪቱ 9 የተደራጁ የጥራት ላቦራቶሪዎችን በማደራጀት እየፈተሸ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።
በግብርና ፣ በምግብ ስርዓት ፣ በኢንደስትሪ ምርት እና በትምህርት ስልጠና የብቃት ደረጃዎችን የመለካት ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገልፀው በአጠቃላይም 50 ሚሊየን ዶላር በመመደብ የጥራት ደረጃዎችን ለማሻሻልና ለመፈተሽ እየሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
በመርሃግብሩ ማጠቃለያም ለኮሌጁ የትምህርት ስርዓትና የጥራት ደረጃ አስተዋፅኦ ላበረከቱ መምህራን የእውቅና እና ማበረታቻ ሽልማት ተበርክቷል።
©️ Diretv ህዳር 3/2017
በዛሬው ዕለት በተለምዶ ኮንጎ ሜዳ ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ በሚገኘው የወጣቶች ማዕከል አዳራሽ የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልን አስመልክቶ በአስተዳደሩ ባሉ የሴክተር ተቋማትና ወረዳዎች የተከናወኑ ስራዎችን የሚያስቃኝ የፎቶ አውደ-ርዕይ ተጀመረ።
በፎቶ አውደ ርዕዩ ላይ በእንግድነት ተገኝተው በይፋ ያስጀመሩት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር እንደተናገሩት ብልፅግና ፓርቲ ከህዝብና ባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን መስተጋብር ከፍ በማድረግ፤ ድጋፍ ለማሰባሰብና ቅቡልነቱን ለማሳደግ በህዝባዊ ተሳትፎ ቀጣይነት ያለው ስኬቶችን እያስመዘገበ ይገኛል ብለዋል
ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር አክለውም በሥራ እድል ፈጠራ ፣ በአምራች ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ልማት ከዚያም ባለፈ የአገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን ረገድ የተሻሉ ስኬቶችን ማስመዝገብ መቻሉን ገልፀዋል።
የፎቶ አውደ-ርዕዩ ከህዳር 2 እስከ ህዳር 6 የሚቆይ ሲሆን የብልፅግና ፓርቲ አምስተኛ አመት የምስረታን በማስመልከት ከህዳር 1 እስከ ህዳር 15 በተለያዩ ኹነቶች እና የበጎ አድራጎት ተግባራቶች እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል።
ህዳር 2/2017 ዓ.ም
ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት አምስት አመታት በፖለቲካ፣ በማህበራዊ እና በልማቱ ዘርፍ ተጨባጭ ለውጥ ያስመዘበበት ነው ሲሉ የድሬዳዋ አሰተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ገለጹ ።
ብልፅግና ፓርቲ "የህልም ጉልበት ለእምርታዊ ዕድገት"ለመንግስት ሠራተኛ አባላቶቹ የሠጠውን ስልጠና ሲያጠናቅቅ 5ኛ አመት ምስረታውንም አያይዞ አክብሯል።
በዚሁ ጊዜም የድሬዳዋ አሰተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በፖለቲካ፣ በማህበራዊና በኢኮኖሚ ዘርፍ ተጨባጭ ለውጦች ላለፉት አምስት አመታት መገኘታቸውን ጠቅሠው በቀጣይነትም በእነዚህ አምስት አመታት የፓርቲው ጉዞ ጎልተው የወጡ ጠንካራ ጎኖችን አጠናክሮ ማስቀጠል ክፍተቶችን ደግሞ እያረሙ መሄድ ያስፈልጋል ብለዋል።
አቶ ሮቤል አክለውም በሀገራችን በቀደመው የፖለቲካ ምህዳር አንዱ ተጠቃሚ ሌላው ከዳር ተመልካች እንደነበር አስታውሰው ባለፉት አምስት አመታት ግን እንደ ብልፅግና ፖርቲ ከተመዘገቡ ስኬቶች መካከል በተግባቦት ላይ የተመሠረተ፣ ሁሉን አሳታፊና አካታች የፖለቲካ መስመር መዘርጋት መቻሉ ዋነኛው መሆኑን ገልፀዋል።
ባለፉት የብልጽግና የአምስት አመታት ጉዞ ከተመዘገቡ አብይ ድሎች ሌላኛው አደጋ ላይ ከመውደቅ ባለፈ አፈጻጸሙ የተጓተተውን ታላቁን የህዳሴ ግድብ የነበሩበትን ግዙፍ ችግሮች ቀርፎ በትክክለኛ ቁመና ስራው እንዲከናወን ማድረግ መቻሉ ነው ያሉት ደግሞ በዛው የሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ናቸው።
"የህልም ጉልበት ለእምርታዊ ዕድገት" ለመንግስት ሠራተኞች ብልጽግና ፓርቲ ሲሠጥ የነበረው ስልጠና የተጠናቀቀ ሲሆን ይሄው ስልጠና ለከተማ ቀበሌ የፓርቲው አባል ሠራተኞች እየተሠጠ ይገኛል።
©️ Dire tv አማርኛ ጥቅምት 30/2017
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዘንድሮ አዲስ ለማሰልጠን የተቀበላቸውን ሰልጣኞች በአስተዳደሩ የሚገኙ የተለያዩ ኢንዱስትሪዎችን አስጎበኘ::
ኮሌጁ ያዘጋጀው የጉብኝት መርሃ-ግብር በእስተዳደሩ ከሚገኙ የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ጋር በመተባበር የተከናወነ ሲሆን በዚህም ሰልጣኝ ተማሪዎች ጉብኝታቸውን በኮካኮላ፣ናሽናል ሲሚንት፣ሬድዋ ሞተርስ እና ኒውዌቭ ፋብሪካዎች ላይ ተዘዋውረው እዲጎበኙ ማድረግ ተችሏል::
ሰልጣኝ ተማሪዎቹ በኢንዱስትሪ ጉብኝት ቆይታቸው በኮሌጁ ለመሰልጠን ከመረጡት የሙያ ዘርፍ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ፉብሪካዎች ላይ ተመድበው የጎበኙ ሲሆን ይህም በኮሌጁ ቆይታቸው ስለሚሰለጥኑት የሙያ ዘርፍ የተሻለ ግንዛቤ እንዲያገኙም አስችሏቸዋል::
ይህን መሰል መርሃ-ግብር ሰልጣኝ ተማሪዎች በኮሌጁ ስልጠናቸውን ካጠናቀቁ በኃላ ያሏቸውን የስራ እድሎች ምን እንደሚመስሉ ከውዲሁ እንዲረዱና በቴ.ሙ.ስ ዘርፍ በሚኖራቸው ቆይታ መነቃቃትን እንዲፈጥርላቸው ታስቦ የተዘጋጀ የጉብኝት መርሃ-ግብር ነው::
ኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም
«የህልም ጉልበት፣ ለእምርታዊ እድገት» በሚል መሪ ቃል ለሥራና ክህሎት ቢሮ የብልፅግና ፓርቲ መሰረታዊ ድርጅት አባላት 4ተኛ ዙር የአባላት የአቅም ግንባታ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ።
ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም
#ዜና | የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ በገጠር ሥራ እድል ፈጠራ ዙሪያ ከቢዮ አዋሌ ወረዳ እና ቀበሌ አመራሮች ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት አካሄደ።
የውይይት መድረኩ የቢዮ አዋሌ ገጠር ወረዳ አመራሮችን ጨምሮ ከ12ቱም ቀበሌ አመራሮች የተውጣጡ ተሳታፊዎችን ያካተተ ሲሆን በወረዳው ያሉትን ፀጋዎች በመጠቀም የኑሮ ሁኔታቸውን ለማሻሻል የታለመ ነው።
ቢሮው ከ2016 ጀምሮ በከተማ ወረዳዎች ላይ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን አከናውኖ ብዙ ውጤት ተገኝቷል፤ በ2017 የአስተዳደሩን ገጠር አካባቢ በተመሳሳይ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በክህሎት መር ሥራ እድል ፈጠራ አቅዶ ወደ ስራ ገብቷል።
የከተማ ሥራ እድል ፈጠራ ሲመራበት የነበረው ሂደት ከገጠሩ አሰራር ጋር ሲነፃፀር በተለይ የቴክኒክና ሙያን አጣምሮ የመሄድ ክፍተት የሚታይበት ሲሆን አሁን ላይ ወጣቶችን በማሰልጠን ባሉበት ወረዳዎች ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ ይገኛል።
የሥራ እድል ፈጠራ እና የብድር ምችችት በከተማ ወረዳዎች ላይ በሰፊው ብዙዎችን ተጠቃሚ ሲያደርግ መቆየቱን የገለፁት የሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ሲሆኑ በገጠሩም ክፍል ወጥነት ባለው ደንብና መመሪያ እንዲጓዝ መፅደቁን ጠቁመዋል።
አያይዘውም የመድረኩ አላማ ከብድር ምችችት ሂደት ስርዓት በፊት አመራሩ ሊይዝ የሚገባውን ግንዛቤዎች ለማጎልበት እንደሆነ ገልፀዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ የገጠር ሥራ ዕድል ፈጠራ እንቅስቃሴን ለማነቃቃት በሥራ ዕድል ፈጠራ ዙሪያ በቢዮ አዋሌ ወረዳ ያካሄደው የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት በተቀሩት ሶስቱ ወረዳዎች ላይ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል።
©️ #Diretv አማርኛ ጥቅምት 27/2017
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም የስልጠና ዘመን አዲስ ለተቀበላቸው ሰልጣኞች የህይወት ክህሎት ስልጠና መስጠ ጀመረ::
አዲስ ገቢ ሰልጣኞቹ በቀጣዮቹ 3ቀናት የህይወት ክህሎት(Life skill )ስልጠናውን እየወሰዱ እንደሚቆዩ የተገለፀ ሲሆን ይህ ስልጠናም ሰልጣኞች የቀጣይ ህይወታቸውን በእቅድ እዲመሩ እንዲሁም ራሳቸውን ፈልገው እንዲያገኙና ሚገጥማቸውን የተለያዩ ፈተናዎች በራስ መተማመን እንዲወጡ የሚያስችላቸውን ልምድ የሚያገኙበት ስልጠና ጭምር መሆኑም ተነግሯል::
ሰልጣኞቹ ይህን ስልጠና አጠናቀው ሲጨርሱ በእስተዳደሩ የሚገኙ የተለያዩ ፋብሪካዎችንና ድርጅቶችን ተዘዋውረው የሚጎበኙ ሲሆን ይህም በተሻለ ግንዛቤና መነቃቃት መደበኛ ስልጠናቸውን እንዲጀምሩ የሚያደርጋቸውም ይሆናል::
ኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
የምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማእከል የሆነው የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በዘንድሮ አመት 12ኛ ክፍልን አጠናቃችሁ የቴክኒክና ሙያ ስልጠናን ለምትፈልጉ በሙሉ አንጋፋው ኮሌጃችን በ12 የሙያ መስኮች ትምህርትና ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል በዘንድሮ አመትም ምዝገባ ላይ እንደሚገኝ በደስታ ያበስራል፡፡ ከነዚህ ሞያዎች መካከል electrical electronics technology departmentን በጥቂቱ እናስቃኛችሁ!!!!
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
የምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማእከል የሆነው የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በዘንድሮ አመት 12ኛ ክፍልን አጠናቃችሁ የቴክኒክና ሙያ ስልጠናን ለምትፈልጉ በሙሉ አንጋፋው ኮሌጃችን በ12 የሙያ መስኮች ትምህርትና ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል በዘንድሮ አመትም ምዝገባ ላይ እንደሚገኝ በደስታ ያበስራል፡፡ ከነዚህ ሞያዎች መካከል automotive technology departmentን በጥቂቱ እናስቃኛችሁ!!!!
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ2017ዓ.ም የስልጠና ዘመን አዲስ ለተቀበላቸው ሰልጣኝ ተማሪዎች ኦረንቴሽን በመስጠት የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል አደረገ::
ሰልጣኝ ተማሪዎቹን ለመቀበል በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ በመገኘት መድረኩን ያስጀመሩት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ሲሆኑ በቅድሚያ አዲስ ሰልጣኝ ተማሪዎችን በኮሌጁ ለመሰልጠን እዚህ በመገኘታቸው እንኳን ደህና መጣችሁ ያሉ ሲሆን ወቅቱ ሚጠይቀውን ምርጫ መርጣችሁ በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለመሰልጠን ዘርፉን በመቀላቀላችሁ እጅግ እድለኞች ናችሁና እንኳን ደስ አላችሁም ብለዋል::
የኮሌጁ ዲን ቀጥለውም እንዳሉት በኮሌጁ በተለያዩ ሙያዎች ለመሰልጠን እዚህ የተገኛችሁ ወጣቶች አሁን የምትገኙበት እድሜ በራሳችሁ ውሳኔ ምትወስኑበት እድሜ ነውና ትክክለኛውን መንገድ በመምረጥ የወጣትነት እድሚያችሁን በአግባቡ በመጠቀም ለቀጣይ ህይወታችሁ ፍሬ የምታፈሩበት ሊሆን እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል::
እሁን ላይ የቴክኒክና ሙያ ዘርፉ ራሱን ችሎ እስከ ከፍተኛው የትምህርት እርከን ድርስ ማሰልጠን እንደጀመረ የገለፁት የኮሌጁ ዲን አንድ ሰልጣኝ ከታች ከ ደረጃ 1(ሰርተፊኬት) ጀምሮ እራሱን እያሻሻለና እያበቃ እስከ ደረጃ 8(ዶክትሬት) ድረስ መድረስ እንደሚችልና መንገዱም የተመቻቸ መሆኑን ለሰልጣኞቹ ገልፀው ሰልጣኞችም ህንን ትልቅ አጋጣሚ በመጠቀም ለራሳቸውም ብሎም ለሀገራቸው የሚጠቅሙ ብቁ ዜጋ መሆን እንደሚጠበቅባቸው አፅዕኖት ሰተው ተናግረዋል::
የኮሌጁ ዲን በመጨረሻም በኮሌጁ የትኩረት ዘርፍ ተብለው የተያዙትና በዓለም ባንክ ፕሮጀክት ጭምር የሚደገፉ ሁለት ዘርፎች መኖራቸውን ገልፀው እነርሱም የማኑፋክቸሪንግ ዲፓርትመንት እና የኤክትሪካል/እሌክትሮኒክስ ዲፓርትመንት ናቸው ያሉ ሲሆን በእነዚህ ሁለት ዘርፎች ውስጥ ያሉ ሙያዎችን ለመሰልጠን የመረጡ ሰልጣኞችም ከምንም በላይ እድለኞች ያረጋቸዋል ብለዋል::
በመጨረሻም ሰልጣኝ ተማሪዎች በኮሌጁ የሚኖራቸው ቆይታንና የትምህርትና ስልጠናው ሂደት ምን እንደሚመስል በዝርዝር ገለፃ የተደረገላቸው ሲሆን በተጨማሪም ስልጠናቸውን አጠናቀው እስኪወጡ ድረስ በኮሌጁ ውስጥ በሚኖራቸው ቆይታ ወቅት የተቀመጠላቸውን መብትና ግዴታዎች ከወዲሁ እንዲያውቋቸው በትምህርትና ስልጠና አስተባባሪው በኩል ሰፊ ገለፃና ማብራሪያ ተደርጎላቸዋል::
ሰልጣኝ ተማሪዎቹ በቀጣዮቹ 3ቀናት በኮሌጁ በሚኖራቸው ቆይታ የህይወት ክህሎት(Life Skill) ስልጠና የሚወስዱ ሲሆን እሱን እንዳጠናቀቁ የትብብር ስልጠና የሚወጡባቸውን የተለያዩ እንዱስትሪዎችና ተቋማትን እንዲጎበኙ መርሃ-ግብር መያዙም ተገልፇል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም
