1 327
Suscriptores
-124 horas
+67 días
+8830 días
Archivo de publicaciones
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ ሰልጣኝ ልማትና ተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ያዘጋጀው የገበያ ተኮር አጫጭር ስልጠናን ፍትሃዊነት ለማረጋገጥ እና የስልጠና ጥራት ለማሻሻል ብሎም ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል ከከተማና ከገጠር ወረዳዎች ምክትል ስራ አስፈፃሚዎችና የአንድ ማእከል አስተባባሪች እንዲሁም ከሁለቱ የመንግስት ፖሊ ቴክኒክ የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ምክትል ዲኖችና የስልጠና አስተባባሪዎች የተሳተፉበት የግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት መድረክ አካሄደ፡፡
በግንዛቤ ማስጨበጫና በውይይት መድረኩ ላይ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ያተኮረ ሲሆን በዋነኛነት የ2017 ዓ.ም የገበያ ተኮር አጫጭር ስልጠና በእስካሁኑ ዕቅድ አፈፃፀም የተገኙ ውጤቶችና የታዩ ክፍተቶች የተለዩበት ሲሆን በቀጣይ የገበያ ተኮር አጫጭር ስልጠናን በገጠር ወረዳዎች ተደራሽ ለማድረግ የMobile TVET ስርአትን ለመተግበር የሚያስችል ምቹ ሁኔታዎች ዙሪያ ከገጠር ወረዳ ምክትል ስራ አስፈፃሚዎችና አስተባባሪዎች ጋር መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ የሰልጣኝ ልማትና ተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጀማል አደን እንደገለፁት የገበያ ተኮር አጫጭር ስልጠናን ፍትሃዊነት ለማረጋገጥ እና የስልጠና ጥራት ለማሻሻል ብሎም ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተጀመረውን ቅንጅታዊ አሰራር አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ታህሳስ16/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
የTVT ሴክተሩ ከአመለካከት ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የሆነ ችግር የሚታይበት ዘርፍ በመሆኑ ከሚድያ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ ተግለፀ::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ EASE ፕሮጀክት በአስተዳደሩ ለሚገኙ የሚዲያ ባለሙያዎች ዘርፉን አስመልክቶ የግንዛቤ መስጫ መድረክ አካሄደ::
የግንዛቤ መስጫ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የስራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ሀላፊና የኤጀንሲው ሀላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በንግግራቸው በአስተዳደሩ የሚገኙ የሚዲያ ተቋማት በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ያሉ እንቅስቃሴዎች ላይ የሚሰሯቸው ስራንዎችና ለዘርፉ የሚሰጡትን የአየር ሰዓት በማሻሻል ተገቢውን ትኩረት መስጠት እንደሚገባቸው ገልፀው በተጨማሪም የሚዲያ ባለሙያዎች ስለዘርፉ በጥልቀት ለመገንዘብ እንዲረዳ በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ውስጥ አንድ የሙያ ክህሎት እንዲሰለጥኑ ምክረ ሀሳብ አቅርበዋል::
ማህበረሰቡ ስለ ቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ያለው አመለካከት በጣም ዝቅተኛ መሆኑን የገለፁት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ሲሆኑ በዘርፉ ተገቢውን ግንዛቤ ለመፍጠር የሚዲያ አካላት በተለያየ አጋጣሚ በሚያደርጏቸው እንቅስቃሴዎች ውስጥ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ በህብረተሰቡ ውስጥ ሰርፇ ዋና ኢላማውን እንዲመታ እንዲሁም የተሻለ የስራ እድል ተፈጥሮ የወጣቱን ብሎም የማህበረሰቡን ህይወት መቀየር እንዲቻል የሚታየውን የተዛባ አመለካከትን መቀያር አስፈላጊ በመሆኑ ለዚህም የሚዲያ አካላት የአንበሳውን ድርሻ እንደሚወስዱ አፅዕኖት ሰጥተው ተናግረዋል::
የኮሌጁ ዲን አክለውም ተቋሙ በቀጣይ በአስተዳደሩ ከሚገኙ የሚዲያ ተቋማት ጋር በርካታና ዘላቂነት ያላቸው ስራዎችን በቅንጅት ለመስራት በእቅድ መያዙን ገልፀው ለዚህም እንዲረዳ የሚዲያ አካላት ከተቋሙ ጋር በጋራ ሊሰሩባቸው የሚችሉ ሀሳቦችንም ይዘው ቢመጡ ኮሌጁ በየትኛውም መንገድ በቅንጅት ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል::
በእዲሱ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ፓሊሲ ዙሪያ ለተሳታፊዎች ግንዛቤ የሰጡት በስራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ት/ት ስልጠና የሰልጣኞች ልማት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ምንልክያለው ወርቅነህ ሲሆን በዚህም ነባሩ ፖሊሲ ላይ የነበሩ ክፍተቶችን ጨምሮ በአዲሱ ፖሊሲ የተካተቱ የለውጥ ሀሳቦችን በዝርዝር ለተሳተፊዎች አቅርበዋል::
በመድረኩ ኮሌጁ በEASE ፕሮጀክት በቀጣይ 5አመት ትግበራ ምን ሊሰራ እንዳቀደ ለሚዲያ አካላት በዝርዝር የቀርበ ሲሆን ከመድረኩ በቀረቡ ሃሳቦች ላይ እንዲሁም በቀጣይ ስለሚኖረው የጋራ እንቅስቃሴ ዙሪያ ሰፊ ውይይትም ተካሂዷል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
ታህሳስ 16/2017 ዓ.ም
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የEASE ፕሮጀክት በተቋሙ አገልግሎት ዘርፍ ላይ ለሚሰሩ ሰራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ::
ኮሌጁ በEASE(Education and Skills for Employ Ability) ፕሮጀክት አማካኝነት ያዘጋጀው ይህን የአቅም ግንባታ ስልጠና Work Ethics & Service Delivery ላይ መሰረት ያደረገ ስልጠና ሲሆን በአስተዳደር ከሚገኘው የስራ አመራር ኢኒስቲትዩት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ መሆኑም ተገልፇል::
ስልጠናውን በንግግር ያስጀመሩት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ባስተላለፋት መልዕክት "ይህ ስልጠና ሲዘጋጅ በተቋሙ ጥናት ተደርጎበትና አስፈላጊነቱም በማኔጅመንቱ ታምኖበት የተዘጋጀ ስልጠና በመሆኑ ሰልጣኞች እዚህ በሚኖራችሁ የ5ቀን ቆይታ የሚሰጠውን ስልጠና በአግባቡና በሀላፊነት ሰልጥናችሁ ወደ ኮሌጁ ስትመለሱ በየምትሰሩበት የስራ ክፍል ላይ በተግባር የሚታይ ለውጥ ማሳየት ይጠበቅባችኃል ያሉ ሲሆን ይህም ስልጠና እንደ ማስጀመርያ መሆኑን እና ተቋሙ በቀጣይ ያቀዳቸውና በየክፍሉ በተለዩ የስልጠና ፍላጎቶች ላይ ተመርኩዞ ክፍተቶችን በስልጠናዎች የሚሞላ መሆኑንም ገልፀዋል::
የኮሌጁ ዲን አክለውም ተቋሙ በዚህ አመት በርካታ አሳይመንቶች እንዳሉበትና አንደኛውም የISO ጉዳይ መሆኑን አስታውሰው IOS በዋናነት ሚያተኩረው Costomer Focus ላይ ነው ያሉ ሲሆን አሁን ያለንበት የCostomer satisfaction survey ከኛ ብዙ እንደሚጠበቅ አመላካች በመሆኑና ይህንንም ለመፈፀም የስራ ስነ-ምግባር ወሳኝነት ያለው በመሆኑ ምክንያት ይህንን ስልጠና ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ አጊኝተነዋልም ብለዋል::
የአቅም ግንባታው ስልጠናው በኢንቲትዩቱ አሰልጣኞች የሚሰጥ ሲሆን ስልጠናው በሁለት ዙር ተከፍሎ ሲሰጥ ይህ የመጀመርያ ዙር ስልጠና ለቀጣዮቹ 5ቀናትም የሚቆይ ይሆናል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
ታህሳስ 15/2017 ዓ.ም
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
የአፋር ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊዎችና የአፋር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የማኔጅምንት አባላት በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የመስክ የስራ ጉብኝት እና የልምድ ልውውጥ አደረጉ፡፡
በመስክ ጉብኝቱ እና በልምድ ልውውጡ ላይ በመገኘት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆኑ በንግግራቸውም እንኳን ወደ ምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማእከል እና ሁለተኛ ቤታችሁ ወደ ሆነው የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በደህና መጣችሁ ፡፡ ኮሌጁ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ ብዙ ሺህ ወጣቶች የሙያና የክህሎት ባለቤት ያደረገ ኮሌጅ ነው ኮሌጁ አሁን ለደረሰበት ስኬትም የከተማ አስተዳደሩ እንዲሁም የኮሌጁ ማህበረሰቦችና ባለድርሻ አካላቶች የማይተካ ሚና አላቸው ያሉ ሲሆን ኮሌጁ በቀጣይ የባቡር ምህንድስና የልህቀት ማእከል እንደመሆኑ መጠን ለድሬዳዋ መመስረት ምክንያት የሆነውን የባቡር ቴክኖሎጂ ለማዘመንና አሁን ያሉትን ባለሞያዎች የሚረከቡ ባለሞያዎችን እያፈራ የሚገኝ ተቋም ነው ፡፡ እንዲሁም በአስራ አንዱ የቴክኒክና ሙያ ዘረመሎች አንጻር ኮሌጁ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
የመስክ ምልከታውን እና የልምድ ልውውጡን መሰረት በማድረግም የልኡካን ቡድኑ የመሩት የአፋር ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አብዱ ሀሰን እንዳሉት አጠቃላይ የኮሌጁ እንቅስቃሴ እጅግ በጣም ጥሩ የሚባልና በኮሌጁ ውስጥ እየተገነባ የሚገኘውም የምስራቅ አፍሪካ የልህቀት መአከል ግንባታ በከፍተኛ ፍጥነት ተከናውኖ ለሚፈለገው አላማ መዋል እንዲችል የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እየወሰደ ያለው ቁርጠኝነት ለሌሎች ከተሞች አርአያ መሆን የሚችል ነው ብለዋል፡፡ በኮሌጁ የሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ክፍሎች ያላቸው አቅም ከሌሎች ኮሌጆች አንጻር ከድሬዳዋ አልፎ ለምስራቁ የሀገራችን ክፍሎች የሚበቃ ነው ያሉ ሲሆን ይህንን አቅም በተገቢው መንገድ በመጠቀም ከተማችሁን ብሎም የምስራቁ የሀገራችንን ክፍል ማልማት የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡
በመስክ ጉብኝቱ ወቅት የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የኮሌጁ እና በኮሌጁ የሚገኙ ፕሮጀክቶ አፈጸጸም እንዲሁም አጠቃላይ የኮሌጁን እንቅስቃሴ በአቶ መሳይ ጥላሁንና በአቶ ዘየደ ተክሌ የቀረበ ሲሆን በመቀጠልም ከአፋር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለኮሌጁ ዲን የአፋር ባህላዊ አልባሳት ስጦታ ተበርክቷል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ታህሳስ 14/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ
በአስተዳደሩ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዝ ልማትን የሚደግፉ ፕሮጀክቶች ከቢሮውና ብድር ከሚያቀርቡ ባንኮች ጋር ያላቸው ቅንጅታዊ አጠቃላይ የስራ አፈጻጸም ግምገማ እና የመስክ ምልከታ ተደረገ፡፡
በዚህም አቶ ተፈሪ ታደሰ የኢኔብሊንግ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ፣ አቶ ንጉሱ ጥላሁን የኢኔብሊነግ ኢትዮጵያ ሲንየር አማካሪ፣ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊ እንዲሁም የቢሮው ባለሙያዎች በተገኙበት የፕሮጀክቶቹ አፈጻጸም ቀርቦ በመስክ ምልከታ የታዩ ጉዳዮችን ጨምሮ ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡
በመስክ ምልከታ አፈጻጸማቸው ከታየ ፕሮጀክቶች ጥላ ፕሮጀክት አንዱ ሲሆን ገቢያቸው አነስተኛ ለሆኑ የገጠር ወጣት ሴቶች ቀጣይነት ያለው የኑሮ መሻሻል እንዲፈጠር መነሻ ካፒታል የሚሆን የሶስት አመት ከዋስትና ነጻ የብድር አቅርቦት በማመቻቸት ስልጠናዎችን እንዲያገኙ እና ቢዝነሶቹን በቅርበት ውጤታማነታቸውን በመከታተል መደገፍ ላይ ያለበት ደረጃ ታይቷል።
ሌላኛው አፈጻጸሙ የታየው ሳፊ ፕሮግራም ሲሆን ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ላይ የሚሰራና መደበኛ እና ኢ-መደበኛ ብድሮችን በማቅረብ በተለይ ለኢ-መደበኛ ተበዳሪዎች በመታወቂያ ብቻ ብድሮችን ከእጅ ንክኪ ነጻ የሆነ በAI ታግዘው ብድሮችን ያመቻቻሉ፤ በዚህም በዋናነት 80% ሴቶች፣ 10% ለአካል ጉዳተኞች እና 10% ለተፈናቃዮች ትኩረት አድርጎ የሰራቸው ስራዎች በተጨባጭ ምን ላይ እንደሚገኙ ምልከታ ተደርጎባቸዋል፡፡
በተጨማሪም መስመር ፕሮግራም የብድር አገልገሎት ሴቶችና ወጣት ሥራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታትና ሥራቸውን ለማስፋፋት የሚሰጠውን የብድር አገልገሎት በአስተዳደሩ የሚገኙ በተለይም በወጣት ሴቶች የሚመሩ የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን በመጠነኛ ዋስትናና በአነስተኛ የወለድ መጠን እንዲሁም የሸሪአ መርህን የተከተለ ከወለድ ነጻ የብድር አገልገሎት ተጠቃሚ የማድረግ ስራ ተጠቃሚዎችን በአካል በማነጋገር ያሉበትን ሁኔታ መመልከት ተችሏል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ታህሳስ 14/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በአስተዳደሩ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ስራዎችን የሚደግፉ ፕሮጀክቶች ያላቸው አጠቃላይ የስራ አፈጻጸም ተገመገመ፡፡
በዚህም አቶ ተፈሪ ተደሰ የኢኔብሊንግ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ፣ አቶ ንጉሱ ጥላሁን የኢኔብሊነግ ኢትዮጵያ ሲንየር አማካሪ፣ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊ እንዲሁም የቢሮው ባለሙያዎች በተገኙበት የፕሮጀክቶቹ አፈጻጸም ቀርቦ በመስክ ምልከታ የታዩ ጉዳዮችን ጨምሮ ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡
በመስክ ምልከታ አፈጻጸማቸው ከታየ ፕሮጀክቶች ጥላ ፕሮጀክት አንዱ ሲሆን (unpaid rural women) ገቢያቸው አነስተኛ ለሆኑ የገጠር ወጣት ሴቶች ቀጣይነት ያለው የኑሮ መሻሻል እንዲኖራቸው መነሻ ካፒታል የሚሆን የሶስት አመት ከዋስትና ነጻ የብድር አቅርቦት በማመቻቸት ስልጠናዎችን እንዲያገኙ እና ቢዝነሶቹን በቅርበት ውጤታማነታቸውን በመከታተል የሚደግፍ መሆኑ ታይቷል።
ሌላኛው አፈጻጸሙ የታየው ሳፊ ፕሮግራም ሲሆን ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ላይ የሚሰራና መደበኛ እና ኢ-መደበኛ ብድሮችን በማቅረብ በተለይ ለኢ-መደበኛ ተበዳሪዎች በመታወቂያ ብቻ ብድሮችን ከእጅ ንክኪ ነጻ የሆነ በAI ታግዘው ብድሮችን ያመቻቻሉ፤ በዚህም በዋናነት 80% ሴቶች፣ 10% ለአካል ጉዳተኞች እና 10% ለተፈናቃዮች ትኩረት አድርጎ የሰራቸው ስራዎች በተጨባጭ ምን ላይ እንደሚገኙ ምልከታ ተደርጎባቸዋል፡፡
በተጨማሪም መስመር ፕሮግራም የብድር አገልገሎት ሴቶችና ወጣት ሥራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታትና ሥራቸውን ለማስፋፋት የሚሰጠውን የብድር አገልገሎት በአስተዳደሩ የሚገኙ በተለይም በወጣት ሴቶች የሚመሩ የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን በመጠነኛ ዋስትናና በአነስተኛ የወለድ መጠን እንዲሁም የሸሪአ መርህን የተከተለ ከወለድ ነጻ የብድር አገልገሎት ተጠቃሚ የማድረግ ስራ ተጠቃሚዎችን በአካል በማነጋገር ያሉበትን ሁኔታ መመልከት ተችሏል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ታህሳስ 14/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ወደ ሥራ ያስገባውን የሀሳብና ክህሎት ባንክ / Idea and Skill Bank/ የፈጠራ ሀሳብ እና ክህሎት ያላቸው ዜጎች ሀሳብና ክህሎታቸውን የሚያካፍሉበት፣ ለገበያ የሚያቀርቡበት እንዲሁም ሀሳብና ክህሎታቸውን አቅናጅተው ሥራ የሚፈጥሩበትን ትስስር ከተለያዩ አካላት ጋር መፍጠር የሚያስችላቸው ነው፡፡ የሚከተለውን የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ማስፈንጠሪያን በመጠቀም አሁኑኑ ይቀላቀሉ https://www.lmis.gov.et
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
‹‹ወጣቶችን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክህሎቶችን በማስገንዘብ የፈጠራ ሃሳባቸውን በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ውስጥ እንዲያዳብሩ በማድረግ ለሃገር የሚጠቅሙ ዜጎችን መፍጠር ያስፈልጋል››
የኮሌጁ ዲን
አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ
********************************************************
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከተለያዩ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ የሳይንስ ትምህርቶች ላይ ዝንባሌ ላላቸውና የፈጠራ ሃሳብ ላላቸው ወጣቶች በSTEM Power ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በዛሬው እለት አከናወነ፡፡
በመድረኩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ እንደተናገሩት በቅድሚያ ወደ ምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማእከል እና ሁለተኛ ቤታችሁ ወደሆነው ድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በደህና መጣችሁ ያሉ ሲሆን አያይዘውም ኮሌጁ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ በርካታ ወጣቶችን በእውቀት በክህሎት በአመለካከት ከማሰልጠን ውጪ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ወጣቶች በመቀበል እንዲሁም ሊሰሩት ያሰቡትን ቴክኖሎጂ ወደ መሬት አውርደው ለራሳቸው ብሎም ለሃገራቸው የሚተርፍ ቴክኖሎጂዎችን እንዲፈጥሩና ሃሳባቸውን ወደ ቢዝነስ እንዲቀይሩ የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ ቆይቷል ያሉ ሲሆን
የፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ወጣቶች የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክህሎቶችን በማስገንዘብ የፈጠራ ሃሳባቸውን በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ውስጥ እንዲያዳብሩ በማድረግ ለሃገር የሚጠቅሙ ዜጎችን መፍጠር ያስፈልጋል ለዚህ ደግሞ ኮሌጁ ቀን ከሌት እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
በመቀጠል ንግግር ያደረጉት ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ዲን የሆኑት ወ/ሮ ትግስት በዙ ሲሆኑ በንግግራቸውም አሁንም በዚህ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ የተሳተፋችሁ እንዲሁም በትምህርት ቤት ውስጥ ያሉ የፈጠራ ሃሳብ ላላቸው የከተማችን ወጣቶች የፈጠራ ሃሳባቸውን ይዘው መጥተው ከፈጠራ ስራቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ በራካታ ስራዎችን በጋራ በመስራት ለራሳቸው ብሎም ለሃገር እንዲጠቅሙ የምንሰራ ይሆናል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ም/ዲኗ እንደገለጹት ኮሌጃችን በአሁኑ ሰአት በባቡር ቴክነሎጂ እንዲሁም በICT የትምህርት ዘርፎች የምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማእከል ነው ስለዚህ የከተማችን ወጣቶች ይህንን እድል በአግባቡ ተጠቅመው እራሳቸውንም ሃገራቸውንም እንዲጠቅሙ በዚሁ አጋጣሚ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ ብለዋል፡፡
በመድረኩ ላይ በኮሌጁ ውስጥ ተማሪዎች ቢመጡ በምን አይነት መንገድ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክህሎቶቻቸውን ማደበር እንደሚችሉ ግንዛቤ የተፈጠረ ሲሆን በመቀጠልም በተለያዩ ትምህርት ክፍሎች ጉብኝት በማድረግ የመድረኩ ፍጻሜ ሆኗል፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ከኔዘርላንድ የልማት ድርጅት (SNV) ጋር በመተባበር 35 በወጣት ሴቶች ለሚመሩ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በበግና ፍየል ማድለብ ለተሰማሩ በአጠቃላይ 156 አባላትን (149 ሴት እና 7 ወንድ) ለእያንዳንዱ ኢንተርፕራይዝ 60,000 ብር የሚገመት ስራ ማስጀመሪያ ድጋፍ ተደረገ፤
የድጋፍ ርክክብ ስነ ስርዓቱ የቢሮው ተወካይ እና የልማት ድርጅቱ ተወካይ እንዲሁም የእንስሳት ጤና እና ሀብት ልማት ተወካይ በተገኙበት የተደረገ ሲሆን የተደራጁት ሴት ወጣቶች የሥራ እድል ለራሳቸውና ለሌሎች እንደሚፈጥሩ እንዲሁም ለሌሎች ምሳሌ በመሆን በበግና ፍየል ማድለብ ላይ በአነስተኛ አቅምና እውቀት አሁን በመጀመር በቀጣይ አስፍተውና አጠናክረው እንዲቀጥሉ ከባለሙያዎች ጋር ገለጻ ተደርጎላቸዋል፤
የልማት ድርጅቱ ከቢሮው ጋር በመተባበር ሥራ የሌላቸው ሴቶችና ወጣቶችን በገጠርና በከተማ በማደራጀት በተለያዩ ርዕስ ጉዳዮዎች በተለይ በኢንተርፕሩነርሺፕና በህይወት ክህሎት ስልጠናዎችን በመስጠት እና ተደራጅተው በሚሰማሩበት ሥራ ዘርፍ ላይ አሰፈላጊው ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱንና የዛሬውን ድጋፍ ጨምሮ በአጠቃላይ በከተማና በገጠር ለተደራጁ ወጣቶች በተመሳሳይ ኢንተርፕራይዞቹን በቅርበት በመከታተል ድጋፍ የተደረገ መሆኑንም ታውቋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ታህሳስ 11/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
