1 318
Suscriptores
+324 horas
+207 días
+15030 días
Archivo de publicaciones
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
በአስተዳደሩ ለሚገኙ ወጣቶች የክረምት ወቅት የሙያ ስልጠና በኮሌጁ መስጠት ተጀመረ::
#EIPC ሐምሌ 21. 2018 ድሬዳዋ
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2018 የክረምት ወቅት የክህሎት ስልጠና "አንድ ሙያ ለአንድ ዜጋ" በሚል በአስተዳደሩ ለሚገኙ ተማሪዎችና ወጣቶች በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ያዘጋጀውን የክህሎት ስልጠና ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር አካሂዷል::
በእለቱ ለወጣቶቹ በተዘጋጀው ኦረንቴሽን ላይ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ባስተላለፉት መልዕክት የዚህ የክረምት ወቅት ስልጠና የተዘጋጀበት ዋና አላማ ጊዜው የክህሎት በመሆኑ ወጣቶች የክረምት ጊዜያቸውን ቁምነገር ላይ በማዋል ቢያንስ የአንድ ሙያ ባለቤት እንዲሆኑ ለማስቻል መሆኑን ገልፀው በተለይም የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ክረምቱን በኮሌጃችን በሚኖራችሁ ቆይታ ስለ ቴክኒክና ሙያ ዘርፍ በጥልቀት የምትገነዘቡ በመሆኑ በቀጣይ ምዕራፋችሁ ለሙያ ተኮር ስልጠናዎች ቅድሚያ እንድሰጡ ይረዳችኃልም ብለዋል::
ወጣቶች በትምህርት ያገኙትንም ሆነ ያላቸውን ሀሳብ ወደ ተግባር ለመቀየር ከየትኛውም ቦታ በተሻለ ቴክኒክና ሙያ ላይ ምቹ ሁኔታ መኖሩን የገለፁት የኮሌጁ ም/ል ዲን እና የትምህርትና ስልጠና ዋና ሀላፊ አቶ ኤሊያስ አህመድ ሲሆኑ አክለውም ወጣቶች በተመቻቸላቸው ወርቃማ እድል ስልጠናውን በአግባቡ በመውሰድ በቆይታቸው ተፈላጊውን ክህሎት ይዘው እንዲወጡ አሳስበዋል::
ቴክኒክና ሙያ ከሌሎች የትምህርት ተቋማት ልዩ የሚያደርገው ወጣቶች የተማሩትን በእጃቸው ነካክተው በተግባር የሚሰለጥኑበትና ሰርተው የሚያሳዩበት ተቋም በመሆኑ ነው ያሉት ደግሞ የኮሌጁ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንዱስትሪ ኤክስቴሽን አገልግሎት ዋና ሀላፊ እና ም/ል ዲን የሆኑት አቶ ተሾመ ሸዋዬ ሲሆኑ አያይዘውም የክረምት ሰልጣኞች ከሚወስዷቸው ስልጠናዎች በተጨማሪ ወደ ቢዝነስ ሊቀይሩት የሚችሉት የቢዝነስ ሀሳብ ካላቸው ቢዝነስ ፕላናቸውን በኮሌጁ እንዲሰሩ ከማድረግ በተጨማሪ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትልም የሚደረግ መሆኑን በመድረኩ ገልፀዋል::
የ2018 የአንድ ሙያ ለአንድ ዜጋ የክረምት ስልጠና ላይ ለመሳተፍ ወደ ኮሌጁ የመጡ ወጣቶች በቅድሚያ የህይወት ክህሎት(Life Skill) ስልጠና የሚሰጣቸው ሲሆን የህይወት ክህሎት ስልጠናውም የቀጣይ ህይወታቸውን የመምራት ክህሎት፣ችግሮችን የመፍታት ክህሎት እንዲሁም የውሳኔ አሰጣጥ ክህሎቶችን የሚያዳብሩበት ስልጠና ሲሆን የህይወት ክህሎት ስልጠናውን እንዳጠናቀቁ በቀጣይ በመረጡት የሙያ ዘርፍ ላይ ስልጠናቸውን የሚወስዱ ይሆናል::
ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr
በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001
በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/@ethioitaly2001?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1
በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/
+8
ትልቅ ብሔራዊ የስራ ቅጥር ማስታወቂያ | በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የአገር መከላከያ ሚንስቴር!
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የአገር መከላከያ ሚንስቴር የመደበኛ ሠራዊት፣ ለዕጩ መኮንን እና ለልዩ ልዩ ሙያተኞች ስራ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሰራተኞችን ለመቅጠር ማስታወቂያ አውጥቷል።
📅 የማመልከቻ ጊዜ፡
⏲ የመደበኛ ሰራዊት እና የሙያተኛ ምዝገባ እስከ ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም ድረስ ይሆናል።
📍 ማመልከቻ ቦታ፡ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ዕድል ፈጠራና የአንድ ማዕከል ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መመዝገብ ይቻላል።
ኢትዮጵያ እንዴት ወደብ-አልባ ሆነች? ሴራ እና የሀገር ክህደት
*****
ኢትዮጵያ እንዴት ወደብ-አልባ ሆነች? የ1983 ዓ.ም የሥልጣን ሽግግር ኢትዮጵያን ከባሕር በር በማራቅ ሀገርን ለማያቋርጥ የደኅንነት ስጋት ያጋለጠበት ወቅት ነበር።
የኢትዮጵያ ወደብ-አልባ መሆን ድንገተኛ የታሪክ አጋጣሚ ሳይሆን፣ በወቅቱ ሥልጣን በያዙት የሕወሓት/ኢሕአዴግ መሪዎች ሆን ተብሎ የተፈጸመ፣ ሕጋዊ መሠረት የሌለው ውሳኔ ውጤት ነው።
የሥልጣን አልባነት እና የታሪክ ምጸት
የሴራው የመጀመሪያው ምዕራፍ የሚጀምረው በሽግግሩ ወቅት ነው። በወቅቱ የፖለቲካ ሥልጣኑን በኃይል የተቆጣጠሩት፣ በለንደን ጉባኤ እና በሌሎች መድረኮች ኤርትራ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንድትገነጠል ፈቃዳቸውን ሰጡ።
እዚህ ላይ መስተዋል ያለበት ትልቁ የታሪክ ምጸት እና የሕግ ስተት፣ የባሕር በር አሳልፎ የመስጠት ውሳኔ የወሰነው አካል (የሽግግር መንግሥቱ) እንዲህ ዓይነት ዘላቂ እና ብሔራዊ ውሳኔ ለማሳረፍ የሚያስችል ሕጋዊም ሆነ ሞራላዊ ውክልና (ሥልጣን) ያልነበረው መሆኑ ነው።
ያለ ሕዝበ ውሳኔ፣ ያለ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ተሳትፎ እና ያለ ጥልቅ ብሔራዊ ውይይት፣ በአንድ የታጠቀ ቡድን ፍላጎት ብቻ ኢትዮጵያ ለዘመናት ስትጠቀምባቸው የነበሩትን፣ በተለይም እንደ አሰብ ያሉ ስትራቴጂክ ወደቦችን አጣች። ይህንን ውሳኔ ያሳለፈ ተጠያቂ የሚሆን ተቋም አለመኖሩ ደግሞ ጉዳዩን እስካሁን ድረስ አስገራሚ አድርጎታል።
በዚህ ውሳኔ ኢትዮጵያ ለዘመናት የነበራትን ቀጥተኛ የባሕር ንግድ መስመር እና ዓለም አቀፍ ተደራሽነት አቋረጠች።
የታሪክ ጥያቄ እና የአክሱም ሥልጣኔ ላይ የተፈጸመው ክህደት
ይህ ውሳኔ ያለ ተቃውሞ አልቀጠለም። በርካታ ኢትዮጵያውያን ምሁራን፣ አንጋፋ ዐርበኞች እና የፖለቲካ ተንታኞች እና ዕድሉ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ሁሉ ይህንን በጽኑ በመቃወም፣ ሥርዓቱን ተጋፍጠውታል።
በተለይም ሻለቃ አድማሴ፣ ፕሮፌሰር ያዕቆብ ኃይለማርያም የመሳሰሉ ምሁራን ያሰሙት የነበረውን አቤቱታ እና ድምፅ ትውልድ የሚዘነጋው አይሆንም። በርካታ የዩኒቨርሲቲ ምሁራንም በይፋ አውግዘዋል።
የኢትዮጵያን ሕጋዊ እና ታሪካዊ የባሕር በር መብት መከበር እንዳለበት አጥብቀው ተከራክረዋል። የኤርትራ መገንጠል የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ፣ የጂኦ-ፖለቲካ እና የደኅንነት ጥቅም በጽኑ የሚጎዳ መሆኑን አስጠንቅቀዋል።
ይሁን እንጂ፣ የወቅቱ መሪዎች እነዚህን ተቺዎች ‘የፊውዳል ሥርዓት ርዝራዦች’፣ ‘የሰውን ሀገር ለመቀማት የሚቋምጡ ተስፋፊዎች’ በማለት በሶሻሊስታዊ ቀኖና አጣጥለውታል።
ይባስ ብሎም፣ የጥንታዊቷ ኢትዮጵያ እና የአክሱም መንግሥት የነበራትን የቀይ ባሕር ተጋሪነት መብት የሚገልጹትን ጥንታዊ የታሪክ ማስረጃዎች ‘ተረት ተረት’ በማለት አዲሱ ትውልድ ስለ ታሪኩ እንዳያውቅ አደረጉ።
የአክሱም ሥልጣኔ የባሕር ንግድ መስመሮችን በመቆጣጠር የደረሰበትን ከፍታ የሚዘክሩትን የታሪክ ሰነዶች ችላ በማለት፣ “አክሱም እስከ ባሕር ደርሳ አታውቅም” የሚል ታሪካዊ ክህደት እንደ መርሕ ይዘው ቀጠሉ።
ከ1983 በኋላ ያመለጡ ዕድሎች እና የሠላሳ ዓመቱ ቸልተኝነት
ኢትዮጵያ ወደብ-አልባ እንድትሆን የተደረገው በ1983ቱ ውሳኔ ብቻ አይደለም፤ ከዚያ በኋላም መብቷን ለማስከበር የሚያስችሉ በርካታ ዕድሎች ሆን ተብሎ እንዲባክኑ ተደርገዋል።
የአሰብ ራስ-ገዝ መዋቅር ችላ መባል፦ ደርግ ከመውደቁ በፊት ለአሰብ ልዩ የራስ-ገዝ አስተዳደር መዋቅር ዘርግቶ ነበር። ይህ መዋቅር ኢትዮጵያ ከኤርትራ መገንጠል በኋላም ቢሆን የአሰብን ወደብ ሕጋዊ ባለቤትነት ለመጠየቅ እንደ አንድ ጠንካራ መሠረት ሊያገለግል ይችል ነበር። ይሁን እንጂ፣ የኢሕአዴግ መንግሥት ይህንን ዕድል ሙሉ በሙሉ ችላ በማለት ወደቡን አሳልፎ ሰጠ።
የ1990-1992ቱ ጦርነት እና ታላቁ ክህደት
በሁለቱ ሀገራት መካከል የተነሣው የድንበር ጦርነት፣ ኢትዮጵያ በኃይልም ሆነ በዲፕሎማሲ የወደብ መብቷን የምታስከብርበት ታላቅ ዕድል ተፈጥሮ ነበር። የኢትዮጵያ ሠራዊት በውጊያ መስክ የበላይነት ይዞ በነበረበት ወቅት፣ የአሰብን መግቢያ በሮች መቆጣጠር ይቻል ነበር።
የዓለም አቀፍ ሕግ ዕድል እና የአሜሪካ ፍንጭ
በወቅቱ እንደ ዶክተር ያዕቆብ ኃይለ ማርያም ያሉ ታዋቂ ዓለም አቀፍ የሕግ ባለሙያዎች በዝርዝር እንደተነተኑት እና መጽሐፋቸው ላይ እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት የባሕር በር የማግኘት መብት ነበራት።
እንዲያውም፣ በወቅቱ የአሜሪካ መንግሥት ዲፕሎማቶች ሳይቀሩ ኢትዮጵያ ይህንን ሕጋዊ መብቷን በዓለም አቀፍ መድረክ እንድትጠይቅ ፍንጭ እና ዕድል ሰጥተው ነበር። ይሁን እንጂ፣ የኢሕአዴግ መሪዎች ይህንን ዕድል ለመጠቀም ፈቃደኛ አልሆኑም።
የባድመ ማደናገሪያ እና የአልጀርስ ስምምነት
የኢትዮጵያ ሠራዊት በውጊያ መስክ የበላይነት ይዞ የአሰብን በር ባንኳኳበት ወቅት፣ የወቅቱ መንግሥት የሕዝቡን ቀልብ ወደ ባድመ (የድንበር) ጉዳይ ብቻ በማዞር፣ የወደቡን ወሳኝ ጥያቄ አጠፋው።
በመጨረሻም በአልጀርስ የተፈረመው ስምምነት የኢትዮጵያን የወደብ መብት ሙሉ በሙሉ ችላ ያለ፣ የወደብ ጉዳይ ሐሳቡም እንዳይነሣ በግልጽ የተከለከለበት ባድመንም ሆነ የወደብ ዕድልን ያጣችበት “የዲፕሎማሲ ክሥረት” ሆነ።
ውጤቱ እና ዋጋው
በዚህ ተከታታይ ክህደት እና ያመለጡ ዕድሎች ምክንያት ኢትዮጵያ ለ30 ዓመታት በባሕር ንግድ ለመሳተፍ ለጎረቤት ሀገሮች (በዋናነት ለጅቡቲ) በየዓመቱ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ክፍያ ለመክፈል ተገድዳለች።
ይህ የኢኮኖሚ ደም-ፍሰት የሀገራችንን ዕድገት ገድቧል። ከዚህም በላይ፣ የባሕር በሯን ማጣቷ የጂኦ-ፖለቲካ ተፅዕኖዋን እና የብሔራዊ ደኅንነቷን አዳክሟል።
ይህ ብቻ ሳይሆን በኢሕአዴግ አገዛዝ ዘመን ስለ ወደብ መናገርም ሆነ መጠየቅ እንደ ወንጀል ተቆጥሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን ለብዙ ችግር ተዳርገዋል። ወደብ ከማሳጣት በላይ ሐሳቡንም ማንሣት ወንጀለኛ የሚያስብልበት ሥርዓት መፈጠሩ የዘመን ውድቀት ያደርገዋል።
የትውልዱ መነሳት እና የማይቀረው ጥያቄ
የባሕር በር ጉዳይ ለኢትዮጵያ የሕልውና፣ የኢኮኖሚ ነጻነት እና የብሔራዊ ክብር ጉዳይ ነው። ያለፈው ትውልድ በሴራ ያሳጣውን መብት፣ የዛሬው እና የቀጣዩ ትውልድ በሰላማዊ፣ በሕጋዊ እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ማስመለሱ የማይቀር ነው።
ኢትዮጵያውያን መብታቸውን ለማስከበር ቁርጠኝነታቸውን እያሳዩ ነው። ስለሆነም፣ የኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ መፍትሔ እስካላገኘ ድረስ፣ ትውልዱ እንቅልፉን ሊተኛ አይችልም። ይህ የትውልድ አደራ እና የሀገር ጥሪ ነው።
©️ EBC
በቀጣዮቹ አስር ቀናት የተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 15/2018 (ኢዜአ)፦በቀጣዮቹ አስር ቀናት የተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ገለጸ።
ኢንስቲትዩቱ ለኢዜአ በላከው መረጃ መሰረት፣ ከሐምሌ 14 እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት አስር ቀናት ውስጥ የዝናብ ሁኔታን የሚፈጥሩ ሁኔታዎች የበለጠ እየተጠናከሩ እንደሚሄዱ አሰታወቋል።
በዚህም መሰረት በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን፣ መካከለኛው፣ ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቷ ክፍሎች የተሻለ የዝናብ ሥርጭት መጠን ይኖራቸዋል።
በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብና ሰሜን የሀገራችን አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ገልጿል።
በተጨማሪም በመካከለኛው፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ እና ደቡብ የሀገሪቷ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመለክታሉ ብሏል።
በሚቀጥሉት አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑ የሀገሪቱ አብዛኛዎቹ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙም ነው ኢንስቲትዩቱ የጠቆመው።
በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን እና በመካከለኛው የሀገሪቷ አካባቢዎች ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ገልጿል።
በተጨማሪም በኤሊ ዳር፣ ዱብቲ፣ ሰመራ፣ ቡሬ፣ አሳይታ፣ ሁንዱፎ፣ ገዋኔ፣ ሚሌ፣ ዳሊፋጊ፣ አይሻ፣ ጉሊና፣ አዋሽ አርባ፣ ባቲ፣ ዶሎ አዶ፣ ዳዋ፣ አሶሶ፣ ጎዴ፣ ቋራ፣ አዋሽ ፈንታሌ፣ ጭፍራ፣ ላሬ፣ መተሀራ እና፣ ላሬ፣ ፉኙዶ አካባቢዎች ከሚኖረው የቀን ከፍተኛ የፀሀይ ሀይል ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ሙቀት ይኖራቸዋል።
ኢንስቲትዩቱ በቀጣይ ቀናት የሚኖረውን መልካም አጋጣሚዎችን ለመጠቀም እና የሚጠበቁ አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ለመከላከል የግብርና ሚቲዎሮሎጂ ምክር ሀሳብን ከወዲሁ መተግበር እንደሚያስፈልግ አሳስቧል።
©️ ኢዜአ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
በድሬዳዋ አስተዳደር ከሁለተኛ እስከ አምስተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች እና ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሲሰጥ የነበረው አገር አቀፍ ፈተና በስኬት መጠናቀቁን ኮሌጁ አስታወቀ፡፡
የ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገርአቀፍ ፈተና በድሬዳዋ ከተማ በበይነመረብ (online) ፈተና ለመስጠት ከተመረጡ ሁለት ተቋማት መካከል የድዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አንዱ መሆኑ የሚታወስ ነው።
በሀገር አቀፍ ደረጃ የተሰጠውን ይህ ሀላፊነትን በተገቢው መንገድ ለመወጣት የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ሲሰራ ቆይቶ ከሰኔ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 4 ዙሮች በበይነመረብ (online) ሲሰጥ የነበረውን ፈተና በብቃት በመወጣት የፈተና መርሃ ግብሩን በተሳካ ሁኔታ ለማጠናቀቅ ችሏል፡፡
የፈተናውን ሂደት በሰላም መጠናቀቁን በማስመልከት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ እንዳሉት የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገርአቀፍ ፈተና በስኬት እንዲጠናቀቅ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅቶችን በማድረግ ከባለፈው አመት በተሸለ መልኩ ተፈታኞች ፈተናቸውን ያለምንም ችግር መውሰድ እንዲችሉ የተለያዩ ስራዎችን ሰርተናል እንዚህን ስራዎችን በተገቢው መንገድ መስራታችን ደግሞ ተፈታኞች ፈተናቸውን ያለምንም ችግር መፈተን እንዲችሉ ያደረገ ነው ያሉ ሲሆን አያይዘውም እንዲህ አይነት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጡ የተለያዩ ሃላፊነቶችን በተገቢው መንገድ የመወጣት አቅም እንዳለን ይህ የሃገር አቀፍ ፈተና አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ለዚህ ፈተና መሳካ አስተዋጽኦ ላበረከታችሁ የኮሌጁ ICT ትምህርት ክፍልና አሰልጣኝ መምህራን፣ከተለያዩ ክልሎች የመጣችሁ ፈታኞች፣የፌደራል ፖሊስ አባላት፣የኮሌጁ የጥበቃ ሰራተኞች፣የኢትዮ ቴሌኮም፣ለመብራት ኃይል ሰራተኞችና ለኮሌጁ ካፊቴርያ ባለሙያዎች እንዲሁም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ የተለያዩ ድጋፎችን ላደረጋችሁ አጋር አካላት በሙሉ በኮሌጁና በራሴ ስም ለማመስገን እወዳለሁ ብለዋል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ሐምሌ 14/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
በድሬዳዋ አስተዳደር ከሁለተኛ እስከ አምስተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች እና ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሲሰጥ የነበረው አገር አቀፍ ፈተና በስኬት መጠናቀቁን ኮሌጁ አስታወቀ፡፡
የ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገርአቀፍ ፈተና በድሬዳዋ ከተማ በበይነመረብ (online) ፈተና ለመስጠት ከተመረጡ ሁለት ተቋማት መካከል የድዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አንዱ መሆኑ የሚታወስ ነው።
በሀገር አቀፍ ደረጃ የተሰጠውን ይህ ሀላፊነትን በተገቢው መንገድ ለመወጣት የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ሲሰራ ቆይቶ ከሰኔ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 4 ዙሮች በበይነመረብ (online) ሲሰጥ የነበረውን ፈተና በብቃት በመወጣት የፈተና መርሃ ግብሩን በተሳካ ሁኔታ ለማጠናቀቅ ችሏል፡፡
የፈተናውን ሂደት በሰላም መጠናቀቁን በማስመልከት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ እንዳሉት የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገርአቀፍ ፈተና በስኬት እንዲጠናቀቅ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅቶችን በማድረግ ከባለፈው አመት በተሸለ መልኩ ተፈታኞች ፈተናቸውን ያለምንም ችግር መውሰድ እንዲችሉ የተለያዩ ስራዎችን ሰርተናል እንዚህን ስራዎችን በተገቢው መንገድ መስራታችን ደግሞ ተፈታኞች ፈተናቸውን ያለምንም ችግር መፈተን እንዲችሉ ያደረገ ነው ያሉ ሲሆን አያይዘውም እንዲህ አይነት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጡ የተለያዩ ሃላፊነቶችን በተገቢው መንገድ የመወጣት አቅም እንዳለን ይህ የሃገር አቀፍ ፈተና አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ለዚህ ፈተና መሳካ አስተዋጽኦ ላበረከታችሁ የኮሌጁ ICT ትምህርት ክፍልና አሰልጣኝ መምህራን፣ከተለያዩ ክልሎች የመጣችሁ ፈታኞች፣የፌደራል ፖሊስ አባላት፣የኮሌጁ የጥበቃ ሰራተኞች፣የኢትዮ ቴሌኮም፣ለመብራት ኃይል ሰራተኞችና ለኮሌጁ ካፊቴርያ ባለሙያዎች እንዲሁም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ የተለያዩ ድጋፎችን ላደረጋችሁ አጋር አካላት በሙሉ በኮሌጁና በራሴ ስም ለማመስገን እወዳለሁ ብለዋል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ሐምሌ 14/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የኮንስትራክሽ ዘርፍ ላይ ያተኮረ የሙያ ክህሎት ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል::
#EIPC ሐምሌ 13 2018 ዓ.ም ድሬዳዋ
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የኮስትራክሽን ኮንትራክተሮች ማህበር ከኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመቀናጀት የሚሰጠው ይህ የክህሎት ስልጠና ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ስልጠና ሲሆን በሁለት የሙያ ዘርፎችም በኮሌጁ እየተካሄደ ይገኛል::
በኮሌጁ እየተሰጠ የሚገኘው የክህሎት ስልጠና ለኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራን፣ ለኮሌጅ ሰልጣኝ ተማሪዎች እንዲሁም ሳይት ላይ ለሚሰሩ ባለሙያዎች ባጠቃላይ ለ50 ተሳታፊዎች ሙሉ ማሰልጠኛ ማቴሪያሎች ተሟልተው የተግባር ስልጠናው በሁለት የሙያ ዘርፎች ማለትም በRefrigeration, Heat Pump Technology and Air Conditioning System እንዲሁም በSolar grid system ሙያዎች እየተሰጠ እንደሚገኝም ተገልፇል::
ይህ ስልጠና በጀርመኑ BAUVERBÄNDE NRW e.V. እና በኢትዮጵያ የግንባታ ዘርፍ ማህበራት እንዲሁም የሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት መካከል በሚደረግ የሙያ ትምህርትና ስልጠና አጋርነት አማካኝነት የተገኘ እንደሆነም ማወቅ ተችሏል::
ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr
በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001
በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/@ethioitaly2001?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1
በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
#ልዩየክረምት ስልጠና ያለምንም ክፍያ በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
#ክህሎትዎን ያሳድጉ የነገ የህይወት አቅጣጫዎን ዛሬ በሚያገኙት ክህሎት ያስተካክሉ
ለመላው ኢትዮጵያውያን የተላለፈ መልዕክት
+++++++
በሀገራችን ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተከናወነ ያለውና ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው እጅግ መሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ የሚመካከሩበት ታሪካዊ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ እንዲሳካ ዜጎች ራሳቸውን ከሀሰተኛ መረጃ በመጠበቅ እና በኮሚሽኑ ላይ ሙሉ እምነት በማሳደር ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጥሪ ያቀርባል፡፡
ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም የተጀመረውን ታሪካዊው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ በተመለከተ አንዳንድ ግለሰቦችና ቡድኖች በማህበራዊ ሚዲያ አውታሮች አማካኝነት ከእውነታ የራቁ መረጃዎችን እያሰራጩ መሆኑን ኮሚሽኑ ደርሶበታል፡፡
ኮሚሽኑ የመናገር ነጻነትን ሙሉ በሙሉ የሚያከብር ገለልተኛ ተቋም እንደመሆኑ ገንቢ የሆኑ ሃሳቦችንና ውይይቶችን የሚቀበል ቢሆንም ሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሀሰተኛ መረጃዎች እንዳይታለል አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ ለህዝብ ይፋ ለማድረግ ይገደዳል፡፡
ሀገራዊ ምክክሩ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ነው። የዚህ ሂደት ስኬት የሚወሰነው ዜጎች በትዕግስት፣ በጥበብ እና በጋራ የኃላፊነት ስሜት ለመሳተፍ በሚያሳዩት የጋራ ቁርጠኝነት ላይ ነው። ይህም እየተከናወነ ይገኛል፡፡ ሂደቱ ተጀመረ እንጂ ውጤቱ ገና ነው፡፡ ይህንን ውጤት በትዕግስት መጠበቅ ደግሞ ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚጠበቅ ይሆናል፡፡
ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም የተጀመረው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ኮሚሽኑ ባወጣቸው የአሰራር ሂደቶች መሰረት እየተከናወነ ይገኛል፡፡ በዚህ መሰረት ባለፉት አራት ቀናት ኮሚሽኑ የጉባኤው ተሳታፊዎች የተጣለባቸውን ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ እርስ በእርስ እንዲተዋወቁ ማድረግን ጨምሮ ለሂደቱ ጠቃሚ በሆኑ የእውቀት እና የስነ-ልቦና ዝግጅቶች እንዲያደርጉ መደላድሉን ፈጥሯል፤ ይህም የሀገራዊ ምክክር ጉባኤው አንድ አካል መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡
ይህ እየሆነ ባለበት አንዳንድ ግለሰቦችና ቡድኖች በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ኮሚሽኑ ምክክሩን ለመጀመር እክል እንደገጠመው የተሳሳተ መረጃ ሲያሰራጩ ተመልክተናል፡፡
በመሆኑም መሰል የተሳሳቱ መረጃዎች የራሳቸው ዓላማ ባላቸው ግለሰቦችና ቡድኖች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ስለሚችሉ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በየእለቱ የሚኖሩ የምክክር ሂደቶችን ኮሚሽኑ ከሚሰጣቸው መግለጫዎችና የምክክሩን ሂደት ለመዘገብ በስፍራው ከተገኙ መገናኛ ብዙኃን ብቻ በመከታተል ራሱን ከተሳሳቱ መረጃዎች በመጠበቅ የምክክሩን ሂደት እንዲደግፍ ኮሚሽኑ ጥሪ ያቀርባል፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን
ሐምሌ 12 ቀን 2018 ዓ.ም
