ጫት እና አደጋው
ብዙ ሰዎች ጫትን ራሳቸውን ለማነቃቃት፣ ለማንበብና ጊዜያቸውን ለማሳለፍ …እንደመዝናኛም ይጠቀሙበታል። ጫት እንደ glycosides, tannins, more than 40 alkaloids, amino acids, vitamins, minerals & amphetamine, caffeine, Catharine, Cathinone, eduline and ephedrine ያሉ ንጥረነገሮችን በመያዙ ሰውነታችን በተለይ አእምሮአችን ከሚችለው በላይ የሆነ ስራን እንዲያከናውን ይረዱታል። ሆኖም አዕምሮአችን ለጥቂት ጊዜ ፈጣን ከሆነ በኋላ በጫት ሱስ እየተጠመደ ይሄድና በስተመጨረሻ ያለ ጫት የማይንቀሳቀስ ፉርጎ ይሆናል። ጫት ወጣቱን ፣ሽማግሌውን፣ ወንዱን፣ሴቱን ፣ማህበረሰቡን በጠቅላላ ና የሀገርንየሰው ሀይል እያቆረቆዘ የሚገኝ መጥፎ መሳሪያ ነው። መጥፎ ስራን መቃወም ከእምነት ጭምር ነውና በጫት ላይ ያሉ የተወሰኑ የጫት ጉዳቶችን በማቅረብ ምን ያህል ጎጂና በኢስላምም የተወገዘ መሆኑን ለማሳየት እወዳለሁ። የጫትን ጉዳቶች ለመረዳት እንዲያመቸን ዱኒያዊና አኸይራዊ በማለት ለሁለት ከፍለን እናየዋለን።
ዱንያዊ፦
በዚህ ርዕስ ስር ጫት በተጠቃሚውና በአካባቢው ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ለማሳየት እንደሚከተለው ከፋፍለን እናየዋለን።
1, በገንዘብ ላይ፦
ሰዎች ከልጆቻቸው ና ከቤተሰባቸው አፍ በመንጠቅ ገንዘባቸውን ለጫት ሲያውሉ ይስተዋላል። ይህ ደግሞ አባወራዎች አላህ የጣለባቸውን ቤተሰብን የማሰተዳደር ሀላፊነት ባለመወጣት ለተጠያቂነት ይዳርጋቸዋል።
ነቢዩ እንዲህ ብለዋል «ሁላችሁም እረኞች ናችሁ፤ ከረኝነታችሁም ትጠየቃላችሁ።»
በሌላ በኩል ችግረኞች እያሉ እነሱ ገንዘባቸውን በጫት ላይ ማዋላቸው ለተጠያቂነት ይዳርጋቸዋል። አላህ በቁርዓኑ አባካኞችን ከሸይጧን ጋር አቆራኝቷቸዋልና።
«አታባክን፣ አባካኝ የሸይጧን ጓደኛ ነውና»እቤት ውስጥ ወጭ ሲጠየቅ አሻፈረኝ ያለው ሰው እጫት ተራ ሲሄድ ምን ያክል እንደሚያወጣ ለእናንተ ልተወው.......
2, በጤና ላይ
ጤና በአብዘኞቻችን እጅ ያለ ያላወቅነው ትልቁ ሀብታችንና ፀጋችን ነው። ይህን ፀጋ የሚያው ነተነጠቀው ብቻ ነው። ለዚህም ነው ነቢዩ በተለያዩ ሀዲሶቻቸው የጤናን ደረጃ የገለፁት። ጫት በቅድሚያ ከፍተኛ ችግር የሚያስከትለው በጥርስ ላይ ነው። ጥርስ ራሱን መተካት የማይችል በመሆኑ በቀላሉ ከተጎዳ ዳግም ተፈጥሮአዊ በሆነ መልኩ መጠገኑ የማይቻል ነው። ነቢዩም ጥርሳቸውን ከመንከባከብ አልፈው ተከታዮቻቸውንም ያዙ ነበር።«ባላጠብቅባችሁ ኖሮ በየውዱዑ በመፋቂያ አዛችሁ ነበር» ነቢዩ
በሌላ በኩል ጫት ውስጣዊ አካላት ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ከመጀመሪያው የከፋ ነው። ጉበት፣ ኩላሊትና የሽንት ፊኛ በጫት ኬሞካሎች የሚጎዱ ሲሆን ከረጅም አመታት በኋላ ደግሞ እንደ ምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ እንቅልፍ ማጣት፣ የስነልቦና ችግርና ሽንተ ማጥ ላሉ ከፍተኛና ብሎም ለሞት ለሚያደርሱ በሽታዎች ያጋልጣል።
በጫት ዙሪያ በተደረጉ ጥናቶች መሰረት ጫት በመተንፈሻ አካለት ፣ በደም ዝውውር አካላት፣ Gastrointestinal sys.፣ Hepatobiliary sys.፣ Genitourinary sys.፣ Obstetric effects፣ Metabolic and endocrine effects፣ በነርቭ አካላት ላይ መጠነ ሰፊ ጉዳቶችን ያስከትላል።
ይህ ብቻ አይደለም ጫት አእምሮን ክፉኛ የሚያደነዝዝ፣ በሱስ ከተያዙ በቀላሉ እንዳይላቀቁ የሚያደርግና ድብርትን የሚያመጣ ነው።ይህ ደግሞ ጤነኛ የነበረውን የሰዎች አስተሳሰብ አዛብቶ ለተበላሸ ማህበራዊ ህይወትና ለተቃወሰ ጤና ይዳርጋል። እንዲሁም በጫት ሱስ ተጠምደው ብዙ ጊዜያትን ያሳለፉ ወንዶች ስሜታቸው ይቀንሳል ብሎም ያጡታል።
3, በጊዜ ላይ
አረቦች ጊዜ ከሂዎት በላይ ነው ይላሉ። እውነት ነው፣ ጊዜ እጅግ ውድ ሀብታችን ነው። ብዙ ነገሮች በጊዜ ይወጠናሉ በጊዜ ይፈፀማሉ። ጊዜን በትክክል ካልተጠቀምንበት ግን በወቅቱ ማግኘት የሚገባንን ነገር እነድናጣና ብሎም ለኪሳራ እንድንዳረግ ያደርግናል። አንዱ ተጠቃሽ ጫት ነው። ሰዎች ጧት የጀበና ሲሉ ቆይተው ስራው ሳያልቅ ከሰዐት ደግሞ ለጫት ሲቀመጡ ይስተዋላል። ሌሎች ደግሞ ከጧት እስከማታ ሲጠምዱት ይታያሉ። ይህ ስራቸውን በጊዜ ፈፅመው ኖሮአቸውን እንዳያሻሽሉ የሚያደርግ የድህነት ማነቆ ነው።
በሌላ በኩል ጫት፣ ሰው በጊዜው ለአኸይራ ቤቱ የሚሆን ስንቅ እንዳይሰንቅ ያደርገዋል። ይኸኛው ከቀደሙት የባሰ መጥፎ የጫት ገፅታ ነው። ጊዜያችንን በአግባቡ ካልተጠቀምንበት ደግሞ አላህ ዘንድ ከሚጠብቁን አራቱ ጥያቄዎች ሁለቱን መመለስ አልቻልንም ማለት ነው። አንዱ ሀብትህን በምን አዋልከው? የሚልና በጊዜህ ምን ሰራህበት? በጫት…..
4, በቤተሰብ ላይ
በቤተሰብ መዋቅር ውስጥ የቅድሚያውን ቦታ ሚይዙት ወላጆች ናቸው። ወላጆች ወልደው እንደማሳደጋቸው ሁሉ ምንም እንኳን ሀቃቸውን ባይመልስም እነርሱን ማገልገል መርዳት እና ለነርሱ ዝቅ ማለት በቁርዐን የተጣለብን ግዴታ ነው። «…ለወላጆቻችሁም መልካም ስሩ በአንተ ዘንድ ኾነው አንዳቸውንም ይሁን ሁለታቸውን ኡፍ አትበላቸው አትገላምጣቸውም መልካም ቃልም ተናገራቸው» ኢስራዕ 23
ሆኖም ጫት መንከባከብ የሚገባንን ቤተሰቦቻችንን እንድንረሳና ቁርዐንን እንድንጥስ ምክንያት ይሆነናል። ይህን እየተመለከቱ የሚያድጉት ታናናሾቻችንም ከዚህ በከፋ መልኩ ስርዓት አልባና ጋጠወጥ እንዲሆኑ በር ይከፍታል።
✅ሚስት ሌላዋ ተጠቂ ናት። ባሏ የጫት ሱሰኛ ከሆነ ለልጆቹም ሆነ ለርሷ ማድረግ የሚገባውን እንክብካቤ አይፈፅምም። ከዚህ በተጨማሪም የሚስቱን ሀቅ ሊያጓድልና ግዴታዎቹንም ሊዘነጋ ይችላል። ይህ ደግሞ በቤተሰብና በግለሰቡ ላይ የሚያሳድረው ስንልቦናዊ መቃወስ ይህ ነው ተብሎ የሚገለፅ አይደለም። ልጆችም በለጋነታቸው ሱሰኞች የሚሆኑበት አጋጣሚም ይከሰታል። ሲገፋ ደግሞ ቤተሰብ እስከ መበተንም ይደርሳል።
✅✅አኸይራዊ
በዚህ ርዕስ ስር ጫት ምን ያህል አኸይራችንን ሊጎዳ እንደሚችል እናያለን። በቅድሚያ በሶላት ዙሪያ የሚያስከትለውን ችግር እንመልከት።
1, ከሶላት ጋር በተያያዘ፦
በአብዘኛው የጫት ሱሰኛ የሆነ ሰው አንድ ጊዜ ከተቀመጠ በኋላ እስከሚረካ ለምንም ቢሆን ዳግም መነሳቱ ይከብደዋል። ይህ ባህሪ ደግሞ ቀርተዋል(ስለዲን ዕውቀት አላቸው) የሚባሉ ሰዎች ላይ ሳይቀር የሚስተዋል ነው። እንግዲህ ጫትን እየቃመ ያለ ሰው ሶላት ሲደርስ ተነስቶ መስገድ ከከበደው አደጋው እዚህ ጋር ነው። በብዛት ሰዎች ጫትን የሚቅሙት(የሚፈርሹት) ከዝሁር በኋላ ሲሆን በምርቃና ተውጠው የአሱር ሶላት ሲያልፋቸው ይስተዋላል። ትንሽ ጠንካራ የሚባሉት ጀመዓ ቢያመልጣቸውም ተነስተው በሰዓቱ የሚሰግዱ ሲሆን ሌሎቹ ግን ሶላታቸውን አዘግይተው ሲሰግዱ ጥቂቶች ደግሞ አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ ከመግሪብ ጋር ያዳብሉታል። ይህ ችግር የሰዎችን ዘልዐለማዊ ቤት ክፉኛ የሚጎዳ ነው። አላህ ግን የአሱር ሶላትን እድንጠባበቃት አዞን ነበር።
«በሶላታችሁ ተጠባበቁ በተለይ በመካከለኛይቱ ሶላት፤ ታዛዦች ሆናችሁ ለአላህ ቁሙ» ቁርዓን በቀራህ