es
Feedback
The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus - EECMY

The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus - EECMY

Ir al canal en Telegram

The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus (EECMY) is a national Lutheran church with more than 10 million members.

Mostrar más
3 291
Suscriptores
+224 horas
+127 días
+10030 días
Archivo de publicaciones
የምዕራብ ጊቤ ሲኖዶስ 3ኛ መደበኛ ጉባኤ በእርቅ እና አዳዲስ መሪዎችን በመምረጥ በስኬት ተጠናቋል ሲኖዶሱ የጉባኤውን "የመንፈስ አንድነት ለመጠበቅ ትጉ" ኤፌ 4:3 በሚል መሪ ቃል በሀዲያ ዞን ጊምቢቹ ከተማ ከሐምሌ 10-12 ቀን 2017 ዓ.ም አካሂዷል። የጉባኤው ተሳታፊዎች ባለፉት 4 ዓመታት በሲኖዶሱ የተከናወኑ ተግባራቶችን ከሲኖዶሱ ፕሬዚዳንት መርኀ ንግግር፣ ከጠቅላይ ጸሐፊውና ከዲፖርትመንቶች በቀረቡ ሪፖርት አድምጧል። የጉባኤው ተሳታፊዎችም በቡድኖች ተከፋፍለው በመወያየት የውይይቶቻቸውን ውጤት እና የውሳኔ አቅጣጫዎች ለጉባኤው አቅርበዋል። በተለያዩ አለመግባባቶች ምክንያት ከሲኖዶሱ መዋቅር ተለይተው የነበሩ አራት ሰበኮችና በስራቸው የሚገኙ 56 ማኀበራነ ምዕመናን የነበሩ ችግሮችን በውይይትና በእርቅ በመፍታ ወደ አንድነት መምጣታ ጉባኤውን ልዩ አድጎታል። የቤተ ክርስቲያኒቱም ፕሬዚዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ ለጉባኤው ማጠቃለያ ባስተላለፉት መልዕክት ተሰናባቹ አመራር በአገልግሎቱ ዘመን ችግሮችን በእርቅ መፍታቱ ታላቅ ስኬት መሆኑን እና ወደ ኋላ በመመልከት የሚያመሰግንበት መሆኑን ገልፀዋል። ጉባኤውም ባካሄደው ምርጫ ለቀጣይ ዓራት ዓመታት ሲኖዶሱን የሚመሩ መሪዎችን የመረጠ ሲሆን፤ በዚህ መሠረት ፦ 1. ቄስ ታምራት ጨቆሬ የሲኖዶሱ ፕሬዚዳንት 2. ቄስ በየነ ኩብሩ የሲኖዶሱ ምክትል ፕሬዚዳንት 3. ገራድ ታደሰ አንሴቦ አቃቤ ንዋይ እንዲሆኑ ተመርጠዋል። የቤተ ክርስቲያኒቱ የወንጌልና ቲኦሎጂ መምሪያ ዳይሬክተር ቄስ ዶ/ር ለሊሳ ዳንኤል ጉባኤውን ተካፍለዋል። ለአዲሱ አመራር የአገልግሎት ስኬት ቤተ ክርስቲያን ትፀልያለች።

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የፋይናንስ እና አስተዳደር መምሪያ ዓመታዊ የሥልጠና እና የምክክር ስብሰባውን በቤተ ክርስቲያኒቱ ዋና ጽሕፈት ቤት አካሂዷል። በመርሃ ግብሩም ከሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቱ ሲኖዶሶች የመጡ የፋይናንስና አስተዳደር ሀላፊዎች፣ የሲኖዶሶቹ ፀሐፊዎች፣ የጋራ ፕሮግራሞች የፋይናንስ ሀላፊዎች ተካፍለዋል። የቤተ ክርስቲያን የፋይናንስ እና አስተዳደር መምሪያ ተጠባባቂ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰብለ አሰፋ እንደገለፁት የምክክሩ ዓላማ የቤተ ክርስቲያኒቱን የፋይናንስ ሥርዓትና የሀብት አስተዳደር ደረጃውን ጠብቆ እንዲቀጥል፣ ቤተ ከርስቲያ የምትጠቀማነው የፋይናንስ ሥርዓቶች መተግበራቸውን ማረጋገጥ እና ባሳለፍነው የበጀት ዓመት የተስተዋሉ ተግዳሮቶች ላይ ለመምከር መሆኑን ገልፀዋል። አንክሮት በመስጠትም ለውጤታማ የፋይናንስ ሥርዓት ክፍሎቹ የውስጥ ቁጥጥር ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ አሳስበዋል። በተያያዘ መልኩ አጠቃላይ የኦዲት ሪፖርት(Summurized Audit Report)፣ የ2026 በጀት ዝግችት(2026 Budget Proposal) ፣ የሂሳብ ሪፖርት(Financial Report) ፣ የውስጥ ቁጥጥር(Internal Come control) እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ሥልጠናዎች እና ምክክሮች ተካሂደዋል። በስብሰባውም ተጋባዥ ተናጋሪ የነበሩት የቤተ ክርስቲያኒቱ የጡረታ ቦርድ፣ የኢንቨስትመንት እና ኢንሹራንስ ኮምሽን ኮምሽነር የሆኑት አቶ ገመችስ ማቴዎስ "በሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ወቅታዊ የዋጋ ግሽበት(Inflation) እና መደረግ በሚገባቸው ጥንቃቄዎችና ግብረ መልሶች" ዙሪያ ሰፊ ጽሑፍ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የሚስዩን እና ቲኦሎጂ መምሪያ ከፒ-ኤል-አይ ኢንተርናሽናል(PLI International) ጋር በትብብር የሚሰጠው የመጋቢነት አመራር ሥልጠና የደቡብ ክላስተር፤ ዛሬ በደቡብ ሲኖዶስ አዘጋጅነት በዲላ ከተማ መሰጠት ተጀምሯል። ሥልጠናውም ላለፉት ሶስት ዓመታት የቤተ ክርስቲያኒቱን መሪዎችና አገልጋዮች ከትዳር አጋሮቻቸው ጋር በተለያዩ ዓርዕስት ሥልጠና በመስጠት ሲያበቃ የቆየ ሲሆን የማጠቃለያ ዓመት በሆነው የዓራተኛው ዓመት ሥልጠና "ደቀመዛሙርትን፣ ደቀመዛሙት አድራጊዎችን እና መሪዎችን ማባዛት" በሚል ዋና ዐርስት ላይ መሠረት በማድረግ በመላው ኢትዮጵያ በተለያዩ ክላስተሮች ሥልጠናው በመካሄድ ላይ ይገኛል። በዚህም ክላስተር ሥልጠና በደቡብ ኢትዮጵያ ከሚገኙ 14 ሲኖዶሶች የመጡ በሲኖዶስ፣ በሰበካ እና ማ/ም ጀረጃዎን የሚያገለግሉ መሪዎች እና አገልጋዮች ከትዳር አጋሮቻቸው ጋር በመካፈል ላይ ይገኛሉ። የቤተ ክርስቲያኒቱም የሚስዩንና ፒኦሎጂ መምሪያ ዳይሬክተር ቄስ ዶ/ር ለሊሳ ዳንኤልን፣ የአዲስ አበባ ሲኖዶስ ኘሬዚዳንት ቄስ ዶ/ር ጽጌ በረሃ እና የቤ/ክኒቱ የካምፓስ አገልግሎትና ከተማ ወንጌል ማዳረስ የሥራ ክፍል አስተባባሪ የሆኑት ቄስ ወርቁ ኤባ ሥልጠናውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ። ሐምሌ 7/ 2017 ዲላ ኢትዮጵያ

ሀገርአቀፍ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት መሪዎች የህብረት: የስልጠና: እና የምክክር ጊዜ ተካሄደ === የኢት./ወ/ቤ/ክ/መካነ ኢየሱስ አመታዊው ሀገር አቀፍ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት መሪዎች የህብረት: የስልጠና: እና የምክክር ጊዜ በጉዲና ቱምሳ ሁለንተናዊ የስልጠና ማዕከል ተካሂዷል፡፡ በምክክሩም ከቤተክርስቲያኒቱ ሲኖዶሶች የተወጣጡ የአገልግሎቱ መሪዎች የተሳተፉ ሲሆን፡ የቤተክርስቲያኒቱ ጠቅላይ ጸሐፊ ቄስ ዶ/ር ተሾመ አመኑ በምክክሩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸውም ልጆችና ወጣቶችን የእግዚአብሔርን ቃል እና የቤተ ክርስቲያኒቱን መሰረተ እምነት አስጠብቆ፣ ጊዜውንና ትውልዱን በሚመጥን መልኩ ማሳደግ እና ማብቃት አስፈላጊ መሆኑን በማንሳት ለዚህም ጠንክሮ መስራት አስፈላጊ መሆኑን በማንሳት መልዕክት አስተላልፈዋል። በፕሮግራሙም እየተሰራበት ባለው ሁለንተናዊ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት ፓኬጅ ዙርያ ሰፊ የምክክር እና ልምድ ልውውጥ ጊዜ የተካሄደ ሲሆን፡ ከምክክሩ በኃላ ተሳታፊዎች በሳይንስ ሙዝየም ጉብኝት አድርገዋል። የቤተክርስቲያኒቱ ፕረዚዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ በፕሮግራሙ ማጠቃለያ በመገኘት በልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ ተቀርጾ እየተሰራበት ያለው ፓኬጅ ልጆች እና ወጣቶችን በሁለንተናዊ መልኩ ቀርጾ ለማሳደግ በጣም አስፈላጊ መሆኑን በማንሳት : ለስኬቱ የአገልግሎቱ መሪዎች እና አስተባባሪዎች በትጋት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ምክር ለግሰዋል። በተጨማሪም በምክክሩ በተነሱ አንዳንድ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በፕሮግራሙም እየተሰራበት ባለው ሁለንተናዊ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት ፓኬጅ ዙርያ የምክክር እና ልምድ ልውውጥ ጊዜ የተካሄደ ሲሆን፡ ፓኬጁን በማስፈጸም ከፍተኛ: አበረታች እና መልካም ጅማሮ ላሳዩ ሲኖዶሶች የማበረታቻ የምስክር ወረቀት እና ስጦታ ተሰጥቷቸዋል፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱ የልጆችና ወጣቶች አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ወንድማገኝ ኡዴሳ አመታዊው የምክክር እና የስልጠና መርሃግብሩ የጋራ ህብረት ያደረጉበት: ውጤታማ ስልጠናዎች የተሰጡበት እና በልጆችና ወጣቶች አገልግሎት ላይ ልምድ ልውውጥ የተደረገበት : እንዲሁም በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር የተደረገበት ነበር:: በሳይንስ ሙዚየም በተደረገው ጉብኝትም በ Artificial Intelligence, Climate Effect, Modern Agriculture, Water & Energy & Aviation Technology ጥሩ ግንዛቤ ማግኘት ተችሏል። *** *** *** Yeroo Tokkummaa, Leenjii fi Marii Gaggeessitoota Tajaajajila Ijoollee fi Dargaggootaa Adeemsifame === W/K/W/W/Makaana Yesuus Itoophiyaatti, yeroo Tokkummaa, Leenjii fi Marii Gaggeessitoota Tajaajajila Ijoollee fi Dargaggootaa biyyoolessaa Dhaabbta Leenjii Hundagaleessa Guddinaa Tumsaatti adeemsifameera. Saganticha irrattis sinoodoosii waldattii hundumaarraa daayrektarootnii fi qindeessitootniiq gaggeessitootni tajaajilichaa kan hirmaatan yoo ta’u, Muummicha Barreessaa Waldattii kan ta’an Lubni Dr. Tashoomaa Ammaanuu baniinsa sagantichaa irratti argamuudhaan ergaa dabarsaniiru. Ergaa isaaniitiinis, ijoollee fi dargaggoota Sagalee Waaqayyoo bu’uura tolfachuudhaan, barsiisaa fi eenyummaa Waldaasaanii hubachiisanii; bifa yerichaa fi dhaloota madaaluun guddisuun barbaachisaa ta’uusaa kaasuudhaan, isa kanaafis ciminaan irratti hojjachuun barbaachisaa akka ta’e kaasuun ergaa dabarsaniiru. Saganticha irrattis Paakeejii Hundagaleessa Ijoollee fi Dargaggootaa irratti hojjatamaa jiru irratti yeroo marii fi muuxannoo wal jirjiiruu kan adeemsifame yoo ta’u, sagantaa marii booda immoo hirmaattotni Muuziyeemii Saayinsiittin daawwannaa taasisaniiru. Pirezidaantiin WKWWMYI xumura sagantichaa irratti argamuudhaan, paakeejiin hundagaleessi tajaajila ijoollee fi dargaggootaa ijoollee fi dargaggoota bifa hundagaleessaan guddisuudhaaf baay’ee barbaachisaa ta’uusaa kaasuudhaan, milkaa’ina tajaajila kanaaf gaggeessitootnii fi qindeessitootni tajaajila kanaa kan taatan hundumtuu ciminaan hojjachuun isinirraa eegama jechuun ergaa dabarsaniiru. Dabalataanis haala yeroo tokko tokko irratti ibsa bal’aa kennaniiru. Saganticha irratti, sinoodoosota paakeejicha hojiitti hiikuu irratti hojii adda duree hojjatan, kan sochii gaarii mul’isanii fi jalqabbii gaarii agarsiisaniif waraqaan ragaa fi kennaan kennameeraaf. Daarektarri Qajeelcha Tajaajila Ijoollee fi Dargaggoo Wondmagegn Udessa, sagantichi yeroo tokkummaa fi marii bal’aan kan irratti gaggeeffame, leenjiin bu’a qabeessa ta’es kan itti kenname, yeroon muuxannoo wal jirjiiruus kan itti gaggeeffame, haala yeroo irrattis mariin kan irratti godhame ta'uu ibsaniiru. Daawwannaa muuziyeemii saayinsiitti godhamettis,waa’ee Artificial Intelligence, Climate Effect, Modern Agriculture, Water & Energy, & Aviation Technology irratti hubannaa gaarii argachuun danda’ameera. ''Isa mootummaadhaa fi Waaqayyo abbaa isaatiif luboota akka taanu nu godhate sanaaf, ulfinnii fi aangoon baraa hamma bara baraatti haa ta'u! Ameen.'' Mul'ata 1:6 === EECMY- Annual Consultation of Children & Youth Ministry Directors, & Coordinators @GTWTC #EECMY #DepartmentOfChildrenAndYouthMinistry #MekaneYesus

MYS Announcement! We are thrilled to announce the new intake for the 2025-26 academic year at Mekane Yesus Seminary! Explore our diverse theological study programs, including: - Master of Arts in Theology (with various specializations) - Post-Graduate Diploma in Biblical and Theological Studies - Bachelor of Theology 🔍 Important Dates: - Entrance exams: July 1-4, 2025 - Regular classes start: August 25, 2025 For details on admission requirements and to prepare for your future in theology, check out the full announcement above! 📞 For inquiries, please contact us at: 0911485345 | 0911943347 | 0911089078 | 0917821573 Join us in this journey of faith and education! #MYS #Theology #Education #NewIntake2025