ሰዋስው ☘☘☘☘
Ir al canal en Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
Mostrar más1 161
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días
Archivo de publicaciones
1 161
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ሉቃ. 1፥1-23 "እስመ ብዙኃን እለ ወጠኑ" - "የከበርህ፡ቴዎፍሎስ፡ሆይ፥ከመጀመሪያው፡በዐይን፡ያዩትና፡የቃሉ፡አገልጋዮች፡የሆኑት፡እንዳስተላለፉልን፥ በኛ፡ዘንድ፡ስለተፈጸመው፡ነገር፡ብዙዎች፡ታሪክን፡በየተራው፡ለማዘጋጀት፡ስለ፡
ሞከሩ፥እኔ፡ደግሞ፡ስለተማርኸው፡ቃል፡እርግጡን፡እንድታውቅ፡በጥንቃቄ፡ሁሉን፡ከመጀመሪያው፡ተከትዬ፡በየተራው፡ልጽፍልህ፡መልካም፡ሆኖ፡ታየኝ። በይሁዳ፡ንጉሥ፡በሄሮድስ፡ዘመን፡ከአብያ፡ክፍል፡የሆነ፡ዘካርያስ፡የሚባል፡አንድ፡ካህን፡ነበረ፤ሚስቱም፡ከአሮን፡ልጆች፡ነበረች፥ስሟም፡ኤልሳቤጥ፡ነበረ። ሁለቱም፡በጌታ፡ትእዛዝና፡ሕግጋት፡ሄሉ፡ያለነቀፋ፡እየሄዱ፥በእግዚአብሔር፡ፊት፡ጻድቃን፡ነበሩ። ኤልሳቤጥም፡መካን፡ነበረችና፡ልጅ፡አልነበራቸውም፤ሁለቱም፡በዕድሜያቸው፡አርጅተው፡ነበር። እርሱም፡በክፍሉ፡ተራ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ሲያገለግል፥ እንደ፡ካህናት፡ሥርዐት፡ወደጌታ፡ቤተ፡መቅደስ፡ገብቶ፡ለማጠን፡ዕጣ፡ደረሰበት። በዕጣንም፡ጊዜ፡ሕዝቡ፡ዅሉ፡በውጭ፡ቆመው፡ይጸልዩ፡ነበር። የጌታም፡መልአክ፡በዕጣኑ፡መሠዊያ፡ቀኝ፡ቆሞ፡ታየው። ዘካርያስም፡ባየው፡ጊዜ፡ደነገጠ፥ፍርሀትም፡ወደቀበት። መልአኩም፡እንዲህ፡አለው፦ዘካርያስ፡ሆይ፥ጸሎትኽ፡ተሰምቶልኻልና፥አትፍራ፤ሚስትኽ፡ኤልሳቤጥም፡ወንድ፡ልጅ፡ትወልድልኻለች፥.ስሙንም፡ዮሐንስ፡ትለዋለህ። ደስታና፡ተድላም፡ይኾንልኻል፥በመወለዱም፡ብዙዎች፡ደስ፡ይላቸዋል። በጌታ፡ፊት፡ታላቅ፡ይኾናልና፥የወይን፡ጠጅና፡የሚያሰክር፡መጠጥ፡አይጠጣም፤ገናም፡በእናቱ፡ማሕፀን፡ሳለ፡መንፈስ፡ቅዱስ፡ይሞላበታል፤ ከእስራኤልም፡ልጆች፡ብዙዎችን፡ወደ፡ጌታ፡ወደ፡አምላካቸው፡ይመልሳል።
እርሱም፡የተዘጋጁትን፡ሕዝብ፡ለጌታ፡እንዲያሰናዳ፥የአባቶችን፡ልብ፡ወደ፡ልጆች፡የማይታዘዙትንም፡ወደጻድቃን፡ጥበብ፡ይመልስ፡ዘንድ፡በኤልያስ፡መንፈስና፡ኀይል፡በፊቱ፡ይሄዳል። ዘካርያስም፡መልአኩን፦እኔ፡ሽማግሌ፡ነኝ፥ሚስቴም፡በዕድሜዋ፡አርጅታለችና፥ይህን፡በምን፡ዐውቃለሁ? አለው። መልአኩም፡መልሶ፦እኔ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡የምቆመው፡ገብርኤል፡ነኝ፥እንድናገርህም፡ይህችንም፡የምሥራች፡እንድሰብክልህ፡ተልኬ፡ነበር፤ እንሆም፥በጊዜው፡የሚፈጸመውን፡ቃሌን፡ስላላመንህ፥ ይህ፡ነገር፡እስከሚሆን፡ቀን፡ድረስ፡ዲዳ፡ትሆናለህ፡መናገርም፡አትችልም፡አለው። ሕዝቡም፡ዘካርያስን፡ይጠብቁት፡ነበር፤በቤተ፡መቅደስም፡ውስጥ፡ስለ፡ዘገየ፡ይደነቁ፡ነበር። በወጣም፡ጊዜ፡ሊነግራቸው፡አልቻለም፥በቤተ፡መቅደስም፡ራእይ፡እንዳየ፡አስተዋሉ፤ርሱም፡
ይጠቅሳቸው፡ነበር፤ድዳም፡ኾኖ፡ኖረ።
23፤የማገልገሉም፡ወራት፡ሲፈጸም፡ወደ፡ቤቱ፡ሄደ።"
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
1 161
26/1/2015 ዓ.ም (፳፮/፩/፳፻፲፭ ዓ.ም)
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
በቅድመ መላእክቲከ እዜምር ለከ።
ወእሰግድ ውስተ ጽርሐ መቅደስከ።
ወእገኒ ለስምከ፡፡ መዝ 137:1
🕯 ትርጉም
በመላዕክት ፊት እዘምርልሃለሁ።
ወደ ቅድስናህ መቅደስ እሰግዳለሁ።
በስምህ ሁሉ ላይ ቅዱስነትህን ከፍ ከፍ አድርገሃልና፡፡
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
1 161
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ማቴ. 6:22-25፡ "ማኅቶቱ ለሥጋከ ዐይንከ ውእቱ" - "የሰውነት፡መብራት፡ዐይን፡ናት።ዐይንህ፡እንግዲህ፡ጤናማ፡ብትሆን፥ሰውነትህ፡ሁሉ፡ብሩህ፡ይሆናል፤ ዐይንህ፡ግን፡ታማሚ፡ብትሆን፥ሰውነትህ፡ሁሉ፡የጨለመ፡ይሆናል።እንግዲህ፡ባንተ፡ያለው፡ብርሃን፡ጨለማ፡ከሆነ፥ጨለማውስ፡እንዴት፡ይበረታ! ለሁለት፡ጌታዎች፡መገዛት፡የሚቻለው፡ማንም፡የለም፤ ወይም፡አንዱን፡ይጠላል፡ሁለተኛውንም፡ይወዳል፤ ወይም፡ወደ፡አንዱ፡ይጠጋል፡ሁለተኛውንም፡ይንቃል፤ለእግዚአብሔርና፡ለገንዘብ፡መገዛት፡አትችሉም። ስለዚህ፥እላችኋለሁ፥ስለ፡ነፍሳችሁ፡በምትበሉትና፡በምትጠጡት፥ወይም፡ስለ፡ሰውነታችሁ፡በምትለብሱት፡አትጨነቁ፤ነፍስ፡ከመብል፣ሰውነትም፡ከልብስ፡አይበልጥምን?"
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
1 161
26/1/2015 ዓ.ም (፳፮/፩/፳፻፲፭ ዓ.ም)
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
ትእዛዙ ለእግዚአብሔር ብሩህ ወያበርህ አዕይንተ።
ፈሪሀ እግዚአብሔር ንጹሕ ወየሐዩ ለዓለም።
ፍትሑ ለእግዚአብሔር ጽድቅ ወርትዕ ኅቡረ። መዝ 18፥8
🕯 ትርጉም
የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፥ዐይንንም፡ያበራል።
የእግዚአብሔር ፍርሀት ንጹሕ ነው፤ ለዘለዓለም ይኖራል።
የእግዚአብሔር ፍርድ እውነትና ቅንነት
በአንድነት ነው።
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ መስከረም ፳፮ (26) ቀን።
❤ እንኳን ለእናታችን ለእመቤታች ለቅድስት ድንግል ማርያም ለልጇ ለወዳጇ ለክብር ባለቤት ለጌታችን ለመድኃኒታች ለኢየሱስ ክርስቶስ ለስደታቸው መታሰቢያ ለፈቃድ ጾም (ለጽጌ ጾም) በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ "አዘክሪ ድንግል ንግደቶ ዘምስሌኪ እንዘ ትጐይዪ ምስለ እምሀገር ለሀገር በመዋዕለ ሄሮድስ ርጉም። አዘክሪ ድንግል አንብዐ መሪረ ዘውኅዘ እምአዕንትኪ ወወረደ ዲበ ገጸ ፍቁር ወልድኪ። አዘክሪ ድንግል ረኃበ ወጽምዐ ምንዳቤ ወኀዘን ወኵሎ ዐፀባ ዘበጽሐኪ ምስሌሁ"። ትርጉም፦ ድንግል ሆይ ርጉም በሆነ በሄሮድስ ዘመን ከእርሱ (ልጅሽ) ጋር ከሀገር ወደ ሀገር ስትሸሺ ከአንቺ ጋር መሰደዱን አሳስቢ። ድንግል ሆይ ከዓይኖችሽ የፈሰሰውንና በተወደደ ልጅሽ ፊት የወረደውን መሪር ዕንባ አሳስቢ፡፡ ድንግል ሆይ ርኃቡንና ጥሙን ችግሩንና ኀዘኑን ከእርሱ ጋር በመሆን የደረሰብሽን ጭንቅ (መከራ) ሁሉ አሳስቢ"። ሊቁ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም በቁጥር 167-169 ላይ።
❤ ጾሙ ከአገራችን ኢትዮጵያ ጦርነትን የሚያጠፋ እና ሰላም፣ ፍቅርንና አንድነትን የሚያመጣ ያድርግልን። መልካም ጾም ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ መስከረም ፳፮ (26) ቀን።
❤ ለእንኳን ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ገብርኤል ወደ በራክዩ ልጅ ቅዱስ ዘካርያስ ለተላከበት መጥምቀ መለኮትን ከእርሱ ስለ መወለዱ ለአበሰረበት ( ለመጥምቀ መለኮት ለቅዱስ ዮሐንስ ለጽንሰት በዓል)ና ለሰማዕቱ ለቅዱስ ዮስጦስ ልጅ ለቅዱስ አቦሊ ለሥጋው ፍልሰት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከዐሥር ሽህ ሰማዕታት፣ ከቅድስት አጋታ፣ ከበርባራ፣ ከዮልያና፣ ከአባት ጊዮርጊስም ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ የየመላእት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ለቅዱስ ዘካርያስ የመጥምቀ መለኮትን የቅዱስ ዮሐንስ መጸነስ እዳበሰረው፦ ስሙ የተመሰገነ እግዚአብሔር ልጅን ይሰጠው ዘንድ አስቀድሞ ሁል ጊዜ በመጸለይ ወደ እግዚአብሔር ይማልድ ነበር። ልጅ ያልወለደውን እግዚአብሔር ብዙ ተባዙ ምድርን ምሉዋት ያለውን በረከት ያጣ ነው በማለት እስራኤል ይገዳደሩት ነበርና።
❤ ልመናውንም ሰማ በቤተ መቅደስም ቁሞ ዕጣንን ሲያሳርግ መልአኩን ላከለት በከበረ ወንጌልም እንደተባለ መንገዱን ይጠርግ ዘንድ በንጉሥ ክርስቶስ ፊት እንደሚሔድ የተነገረለት ታላቅ ነቢይ ዮሐንስ ከእርሱ መወለዱን አበሠረው።
❤ ዘካርያስም የሰውነቱን መድከም የመውለጃውም ዘመን እንዳለፈና ፈጽሞ እንዳረጅ የሚስቱም እንዲሁ ዘመኗ እንዳለፈና ፈጽማ እንዳረጀች መካንም እንደሆነች ያውቃልና ስለዚህ ይህ ነገር እንዴት ይሆንልኛል "እኔ ያረጀሁ ሽማግሌ ነኝ ሚስቴም እንዲሁ ዘመኗ አልፎ መካን ሁናለች" ብሎ የእግዚአብሔርን መልአክ ተከራከረው።
❤ መልአኩም "እኔ ይህን ልነግርህ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወዳንተ ተልኬ ነበር ልትጠራጠር ባልተገባህም ነበር አሁንም ይህ በጊዜው እስቲፈጸም ዲዳ ሁነህ መናገር ይሳንሃል" ብሎ ገሠጸው። ዘካርያስም የወልደ እግዚአብሔርን መንገድ የሚጠርግ ዮሐንስ እስከሚወለድበት ጊዜ ድረስ ዲዳ ሆነ።
❤ በሚገረዝበትም ቀን የሕፃኑን አባት ዘካርያስን የሕፃኑን ስም ምን ብለው እንደሚሰይሙት ጠየቁት እርሱም ብራና ለምኖ "ስሙ ዮሐንስ ነው" ብሎ ጻፈ በዚያም ጊዜ አንደበቱ ተፈትቶ እግዚአብሔርን አመሰገነው። ስለ ልጁ ዮሐንስም እርሱ የልዑል ነቢይ እንዲባል መንገዱንም ይጠርግ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት እንደሚሔድ ትንቢት ተናገረ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ዘካርያስና በቅድስት ኤልሳቤጥ በልጃቸው በቅዱስ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ "ሰላም ለፅንሰትከ በሠሌዳ ከርሣ ዘተገልፈ። ለኤልሳቤጥ እምከ እምድኅረ ወርኃ ኀለፈ። ዮሐንስ መልአክ እንተ ትኴንን አእላፈ። ከመ እፈጽም ዘወጠንኩ ስብሐቲከ ትሩፈ። በውስተ ዕዝንየ አልኆስስ መጽሐፈ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመስከረም 26።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "በቅድመ መላእክቲከ እዜምር ለከ። ወእሰግድ ውስተ ጽርሐ መቅደስከ። ወእገኒ ለስመከ"። መዝ137፥1-2። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 12፥1-11፣ 1ኛ 2፥20-ፍ.ም እና የሐዋ 10፥1-9። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥1-23። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ኤጲፋንዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ ገብርኤል በዓልና የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የጽንሰት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
የክረምት መውጫ
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
❖ ዳግመኛም ይኽች ዕለት የክረምት መውጫ ሆናለች፤ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር (የጊዜ ቀመር) መሠረት በዓመት ውስጥ አራቱ ወቅቶች አሉ፡፡ እነዚህም ክረምት፣ መፀው (መኸር ወይም መከር)፣ ሐጋይ (በጋ) እና ፀደይ (በልግ) ናቸው።
❖ አራቱ ሊቃነ ከዋክብት የሚባሉት ናርኤል፣ ብርክኤል፣ ምልኤል እና ኅልመልሜሌክ እነዚህ እያንዳንዳቸው አራቱን ወቅቶች በየተራ ይመግባሉ፡፡
❖ አንድ ዓመት በውስጡ 13 ወራትን የያዘ ሆኖ በአራት ወቅቶች የተከፈለ ነው፤ ቅዱስ ያሬድ በድርሰቱ አንዱን ዓመት በአራት ክፍለ ዘመን ከፍሎታል፡፡
📌 አራቱ ክፍላተ ዘመን የሚባሉትም
1. ክረምት ማለት ከሰኔ 26- መስከረም 25 ያለው ነው፡፡
2. መፀው (መከር) ማለት ከመስከረም 26- ታኅሣሥ 25 ያለው ነው፡፡
3. በጋ (ሐጋይ) ማለት ከታኅሣሥ 26-መጋቢት 25 ያለው ነው፡፡
❖ ከክረምት በስተቀር እያንዳንዱ ወቅት በውስጡ ዘጠና ዘጠና ቀናት ይዟል፤ ክረምት ግን ለብቻው 95 ቀናትን የያዘ ነው፡፡
📌 ዘመነ መፀው
❖ መፀው በሌላ አነጋገር ጥቢ ይባላል፤ እንደ ሌሊት ከብዶ የሚታየው ክረምት አልፎ መስከረም ከጠባ በኋላ በ4ኛው ሳምንት ስለሚጀምር ነው ጥቢ የሚባል ተጨማሪ ስያሜ የተሰጠው፡፡
❖ ዘመነ መፀው ከመስከረም 26 እስከ ታኅሣሥ 25 ድረስ ያለው ጊዜ ነው፤ የዕለቱ ቁጥርም 90 ይሆናል፡፡
❖ ከዘመነ ክረምት ቀጥሎ በመሆኑ ዘመነ ክረምትን በማስቀደም ፅጌንና መፀውን በማስተባበር ቅዱስ ያሬድ የሚከተለውን ብሏል፡፡
✍“ግሩም በሆነው ኃይልህ እንመካ ዘንድ አንተ ዘመናትን ሠራህ ክረምትን ለዝናባት መፀውን ለአበቦች ሰጠህ”
📚ድጓ ዘጽጌ
❖ መፀው መሬት በክረምት የተሰጣትን ዘር አበርክታ፣ አብዝታ ለፍሬ የምታደርስበት የምርት ወቅት ነው፤ መፀው በአብዛኛው የአዝመራ መሰብሰቢያ ጊዜው ነው፡፡
📌ዘመነ ሐጋይ
❖ ዘመነ ሐጋይ (በጋ) ይህ የበጋ ወቅት ነው፤ “ሐጋይ”….በጋ ሆነ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ነው፤ ይህም ከታኅሣሥ 26 እስከ መጋቢት 25 ቀን ያለውን ጊዜ ያጠቃልላል፤ ሐጋይ የጥርን፣ የየካቲትንና የመጋቢትን ወር ይይዛል፡፡
❖ ዘመነ ሐጋይ የቃሉ ትርጓሜ ዘመነ ፀሐይ ማለት ሲሆን ሥርወ ቃሉም ኃገየ … ከሚለው ግእዝ የተገኘ ነው፤ ከአራቱ ክፍላተ ዘመን አንዱ እጅ ወይም አንድ አራተኛው ሐጋይ ይባላል፤ የሐጋይ ፍቺ በጋ እንደሆነ ሁሉ እንዲሁም መፀውም ጸደይም በእርሱ ስም በጋ ይባላሉ፡፡
✍“ዘጠኝ ወር በጋ” እንዲሉ፣ አንዳንድ ጊዜም መጽሐፍት በሁለት ከፍለው ይናገራሉ “ክረምትና በጋን አንተ ሠራህ” ፤ “በበጋም በክረምትም እንዲህ ይሆናል”
📖መዝ 75፥17፣
📖ዘካ 14፥10፣
📖ዘፍ 10፥22
❖ ኃጋይ ማለት መገኛ መክረሚያ በጋ፣ ፀደይ፣ ደረቅ ወቅት ነው፤ በዚህ ወቅት በመፀው ያሸተውና ያፈራው መኸር የሚታጨድበት፣ የሚሰበሰብበትና በየማሳው ከተከመረ በኋላ የሚበራይበት፣ በጎተራ የሚከተትበት በመሆኑ “የካቲት” የሚለውን ወር ይዞ እናገኘዋለን፡
❖ የግብርናው ኅብረተሰብ እህሉን በጎተራው ከትቶ ለተወሰነ ጊዜ የሚያርፍበት በመሆኑ የዓመት በዓላት እንደ ልደት፣ ጥምቀት ያሉት፣ ዘመነ መርዓዊ የሚባለው የጋብቻ ዘመን በዚህ ወቅት የተካተቱ ናቸው፡፡
📌ዘመነ ጸደይ
❖ በአብዛኛው ግን ዘመነ በልግ ነው፤ ቅዱስ ያሬድ በድጓው “ይሁብ ዝናመ ተወን” የበልግ ዝናምን ይሰጣል እንዳለው የበልግ ወቅት ነው፡፡
✍“አንድ ሰኔ የነቀለውን ሁለት ሰኔ አይተካውም” እንደሚባለው የግብርናው ኅብረተሰብ ቀጣይ የግብርና ሥራውን በትጋት የሚሠራበት ወቅት ነው፡፡
📌 ዘመነ ክረምት
❖ ዘመነ ክረምት ማለት ዘመነ ውሃ ማለት ነውና በዚህ ዘመን ውኃ ይሰለጥናል፤ ውሃ አፈርን ያጥባል፣ እሳትን ያጠፋል፣ ቢሆንም በብሩህነቱ ከእሳት፣ በቀዝቃዛነቱ ከነፋስ፣ በእርጥብነቱ ከመሬት ጋር ተስማምቶ ይኖራል፡፡
❖ ክረምት በውስጡ አራት ወራትን (ሐምሌ፣ ነሐሴ፣ ጳጉሜንና መስከረም) የያዘ ነው፤ ቅዱስ ያሬድ “ያረሁ ክረምተ በበዓመት፣ ይሰምዑ ቃሎ ደመናት፣ በየዓመቱ ክረምትን ያገባል፤ ደመናትም ቃሉን ይሰሙታል” ሲል በድጓው እንደነገረን የዘመናት ጌታ ልዑል እግዚአብሔር በየዓመቱ አዙሮ የሚያመጣልን ወቅት ነው፡፡
❖ ደመናትም ለቃሉ ትእዛዝ ተገዢዎች በመሆን ዝናመ ምሕረቱን ጠለ በረከቱን የሚያወርዱበት ጊዜ ነው፤ ከሰኔ 26 እስከ መስከረም 25 ድረስ ያለውን ጊዜ ይይዛል፡፡
በዲ/ን የአብስራ ጌታሁን
https://t.me/Eotcw
1 161
እንኳን ለጽጌ ፆም በሠላም አደረሳቹ?
መልካም ጾም እያልኩኝ እነኆ የተወደደች እና የምትወደድ ጽጌ እነኆ መጣች ልባችንን በወረብ ወደ ሰማይ ወደ መንበረ ጸባዖት ልትወስድ በእመቤታችን እጅ ልታስባርከን እነኆ የተወደደች ጽጌ መጣች!!!
እንደተለመደው ማህበረ ሰዋስው ግሩፕ ና ቻናል የእናንተን ፍላጎት ለማሟላት ከወዲሁ ዝግጅቱን አጠናቋል!!!
የየሳምንቱ
🌹ወረብ በዜማ
🌹 የዕለቱ ምስባክ በዜማ
እዲሁም ሙሉ ማኅሌቱ ማኅሌተ ጽጌው ዚቁ ወረቡን በጽሑፍ አዘጋጅተናል።
ስለዚህ የዘንድሮን ጽጌ ከማህበረ ሰዋስው ግሩፕ ና ቻናል ጋር እናሣልፍ !!!
https://t.me/Eotcw
1 161
ለዘንድሮ ተፈታኞች
+ ተማሪዎች ፈተና ከመፈተናቸው በፊት ይህን ይጸልዩ +
ቅዱስ ቄርሎስ ሣድሳዊ ዘእስክንድርያ የደረሱት
+++ ጸሎት +++
‹‹ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ
‹‹በችግርህ ቀን ጥራኝ ፤ አድንሃለሁ አንተም ታከብረኛለህ›› ብለህ የአንተን መጠጊያነት መፈለግን ስላስተማርከኝ አመሰግንሃለሁ!
አሁንም ጌታ ሆይ! በዚህ የፈተና ሰዓት ጥበብና ማስተዋልን ትሰጠኝ ዘንድ እማጸንሃለሁ፡፡
ይህን ፈተና በሰላም አልፍ ዘንድ ጸጋን (ሞገስን) ስጠኝ፡፡ ፈተናውን በምሠራ ጊዜ ጥልቅ የሆነ ሰላምህንና በረከትህን ስጠኝ፡፡
ጌታዬ ኢየሱስ ውጤት በሚሰጡኝ ጊዜ በመምህራኖቼ ዓይን መወደድን ትሰጠኝና ልባቸውን ታለሰልስልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡ የከበርከው ጌታእኔ ኃጢአተኛ ነኝ ፤ ዓመቱን ሙሉ አንተን ደስ አላሰኘሁህም ፤ ውስጤንም ጭምር ፤ ነገር ግን ከልቤ ደንዳናነትና ከኃጢአቶቼ የተነሣ ሳይሆን ከምሕረትህ እና ከርኅርኄህ የተነሣ እንደትረዳኝ እለምንሃለሁ፡
ጌታ ሆይ ‹‹ለምኑ ይሰጣችኋል፣ እሹ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ ይከፈትላችኋል›› ብለሃል፡፡ እናም እነሆኝ እየለመንኩ ነው፤ የምሕረትህንም ደጅ እያንኳኳሁ ነው፡፡ ‹‹ወደ እኔ የሚመጣውን ከቶ ከእኔ አላወጣውም›› ብለሃልና ጸሎቴን አትናቅ፡፡በቅድስት ድንግልና በመላእክትህ ሁሉ አማላጅነት መልስልኝ!! አሜን!"
ለዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን!
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
1 161
#ጾመ #ጽጌ #እንኳን #አደረሳችሁ !
ከመስከረም 26- ህዳር 5
የእመቤታችን ስደት በጾም በጸሎት የምታስቡ ወይም የምታሳልፉ የእመቤታችን የድንግል ማርያም የቃልኪዳን ልጆች ከወዲሁ እንኳን አደረሳችሁ
ጾመ ጽጌ ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ያለው አንድ ወር ከዐሥር ቀን ወይም 40 ቀን ወርኃ ጽጌ፣ ዘመነ ጸጌ፣ ተብሎ ይጠራል፡፡
በነዚህም ቀናት በየቤተክርስቲያኑ የሚነበቡ ምንባቦች፣ የሚዘመሩት መዝሙሮች፣ የሚሰበከው ስብከት፣ የሚቆመው ማኅሌት በጠቅላላው የሚነገረው ስብሐት እግዚአብሔር ሁሉ ሰማይ በከዋክብት ምድር በጽጌያት አሸብርቀው የሚታዩ መሆናቸውን የሚገልጽ ነው፡፡
ወርኃ ጽጌ ለሚከናወነው መንፈሰዊ አገልግሎት መነሻው “መልአኩ ሕፃኑንና እናቱን ወደ ግብፅ ይዘሃቸው ሽሽ፣ የሕፃኑን ነፍስ ሊገድሉት ይፈልጋሉና” ሲል ለዮሴፍ በሕልሙ በነገረው መሠረተ ዮሴፍም ሕፃኑንና እናቱን ድንግል ማርያምን ይዞ ወደ ግብፅ መሰደዱና እመቤታችንና ሕፃኑ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ በስደት ከኖሩ በኋላ /ራእይ.12፣6/ ወደ አገራቸው ወደ ናዝሬት የመመለሳቸው መታሰቢያ ነው፡፡ /ማቴ. 2፣13-23፣ ት.ኢሳ.19፣1፣ እንባቆም 3፣6-7፣ መዝ.83፣3/፡፡
ይህንንም በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሡ አባ ጽጌ ብርሃን ፍሬ ከአበባ አበባም ከፍሬ እንደሚገኝ ሁሉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስን በአበባና በፍሬ እየመለሰ በሚያስረዳው ድርሰታቸው እንዲህ በማለት ገልጸውለታል፡፡ “ አፈወ ሮማን ማርያም ጽጌ ቀናንሞ ወአበሜ፣ እስከ ተጸምሐየየ በጾም ዘመልክዕኪ ጊዜ ድክታሜ፣ እምተመነይኩ ተሳትፎ ከመ አኅትኪ ሰሎሜ፣ ወፍሥሓኪ ዘአልቦ ፍጻሜ”፡፡ ሲተረጎምም የሮማን ሽቱ የቀናንሞ አበባ የምትሆኚ ማርያም ሆይ፣ በርሃብ በጾም አበባ የመሰለ የመልክሽ ደም ግባት እስኪጠወልግ ድረስ በስደትና በልቅሶ የደረሰብሽን ችግርና ድካም መከራሽንም ሁሉ እንደ እኅትሽ እንደ ሰሎሜ አብሬሽ ብቀበል ምኞቴ ነበር፤ በዚህ ፍጻሜ የሌለውን ደስታሽን እሳተፍ ነበር፡፡ እንዲሁም አባ አርክ ሥሉስ በስደቷ የደረሰባትን ኀዘን ፣ ልቅሶና ሰቆቃ አስመልክተው በደረሱት ‘ሰቆቃወ ድንግል” በሚለው ድርሰታቸው እንዲህ አሉ፣ ፀሐይን የምትለብሽ የብርሃን ልጅ ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ከሄሮድስ ዘንድ ልጅሽን ባሸሸሽ ጊዜ የደረሰብሽን ችግሮች ጨረቃን የሚጫሙ እግሮችሽ በመንገድ ብዛትና በአሸዋ ግለት እንደ ጎበጎቡ ሲሰማ ሰው ይቅርና ድንጋዩም ባለቀሰ ነበር”፡
የእመቤታችን የስደቷ መታሰቢያ ወር በቤተ ክርስቲያናችን የሚከበረው በማኅሌት፣ በቅዳሴና በዝክር ነው፡፡ በወርኃ ጽጌ ባሉት ሳምንታት ከቅዳሜ ማታ እስከ እሑድ ጠዋት አበው ካህናት የሚያቀርቡት ዝማሬ ከቅዱስ ያሬድ ድጓ፣ ከማኅሌት ጽጌና ከሰቆቃው ድንግል የተውጣጣና ሦስት ወገን ያለው ነው፡፡ ዝክሩም፣ በአሁኑ ወቅት በከተሞች አካባቢ እየተረሳ ቢመጣም፣ ዘወትር እሑድ የአንድ አካባቢ ሰዎች ማዕከላዊ በሆነ ቦታ ተሰባስበው በእመቤታችን ስም የሚዘክሩት ነው፡፡ ዐቅመ ደካሞች፣ ድሆችና መንገደኞች ተጠርተው በእመቤታችን ስም እንዲበሉና እንዲጠጡ ይደረጋል፡፡
ይህም ትውፊት እመቤታችን ወደ ኢትዮጵያ በመጣች ጊዜ ኢትዮጵያውያን አባቶችና እናቶች ያደረጉላትን መስተንግዶ ለማሰብ ነው፡፡ ከእመቤታችን በረከት ያሳትፈን አሜን!!!
በዲ/ን የአብስራ ጌታሁን
https://t.me/Eotcw
