ሰዋስው ☘☘☘☘
Ir al canal en Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
Mostrar más1 161
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días
Archivo de publicaciones
1 161
ከዐሥራ ሁለት እልፍ የሚበዙ ሰዎች እንዲሁም ብዙ እንስሶች ላሉባት ታላቅ አገር ለሆነች ነነዌ እኔ አላዝንላትምን ከበደሉ ተመልሶ ንስሐ ለሚገባ እኔ መሐሪና ይቅር ባይ ነኝና" አለው።
❤ ከዚህም በኋላ ዮናስ ተነሥቶ ወደ አገሩ ተመልሶ በሰላም ዐረፈ መላው ዕድሜውም መቶ ሰባ ነው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በነቢዩ ቅዱስ ዮናስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 25 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለዮናስ በከርሠ አንበሪ ዘኖመ። አምሳለ ክርስቶስ ይኩን በውስተ መቃብር ተኀትሙ። እግዚአብሔር ይቤሎ ጊዜ በሑሩር ሐመ። ኢይሣሃላኑ ለነነዌ ወኢይምሕካኑ ፍጹመ። እንዘ አንተ ትምሕክ ዘኢተከልከ ሐምሐመ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ አርኬ የመስከረም 25።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ብፁዕ ብእሲ ዘአንተ ገሠፅኮ እግዚኦ። ወዘመሀርኮ ሕገከ። ከመ ይትገኃሥ እመዋዕለ እኩያት።" መዝ 93፥12-13። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 16፥21-24።
+ + +
❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ወአይቴ እጐይይ እምቅድመ ገጽከ። እመኒ ዐረጉ ውስተ ሰማይ ህየኒ አንተ። ወእመኒ ወረድኩ ውስተ ቀላያት ህየኒ ሀሎከ"። መዝ138፥7-8። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 2፥1-12፣ 2ኛ ጴጥ 3፥1-8 እና የሐዋ ሥራ 20፥9-28 የሚነበበው ወንጌል ማቴ 12፥38-43። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ። መልካም የነቢዩ ዮሐንስ የዕረፍት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ መስከረም ፳፭ (25) ቀን።
❤ እንኳን ከዐሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ ለሆነው ለየዋሁ ለቅዱስ ዮናስ ለዕረፍት በዓል፣ ለክረምት መውጫ ቀን በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱሳን ከፎቃ፣ ከዮሐንስ፣ ከእንድራዎስ፣ ከጴጥሮስ፣ ከጳውሎስ፣ ከእንጦንዮስ፣ ከበርባራ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ ነቢዩ ዮናስ ቅዱስ ዮናስ፦ ይህም እውነተኛ ነቢይ ዮናስ የሲዶና ክፍል በምትሆን ስራጵታ በምትባል አገር ለምትኖር መበለት ልጅዋ የሆነ ነቢይ ኤልያስም ከሙታን ለይቶ ያሥነሣው ኤልያስንም ያገለገለውና የትንቢት ጸጋ የተሰጠው ነው።
❤ ከዚህም በኋላ ስሙ ከፍ ከፍ ያለና የተመሰገነ እግዚአብሔር "ወደ ነነዌ አገር ሒደህ ሀገራቸሁ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ትጠፋለች" ብለህ አስተምር ብሎ አዘዘው። እግዚአብሔርም ይህን በአለው ጊዜ ዮናስ በልቡ እንዲህ ብሎ አሰበ "እግዚአብሔር ሊአጠፋቸው ቢወድ ኖሮ ሒደህ አስተምር ብሎ ባላዘዘኝ ነበር እግዚአብሔር መሐሪ ነውና ሲምራቸው እኔ በእነርሱ ዘንድ ሐሰተኛ ነቢይ እንዳልባል እፈራለሁ ከቶ ትምህርቴን አይቀበሉኝም ወይም ይገድሉኛል ወደዚያች አገርም ሒጄ እንዳላስተምር ከእግዚአብሔር ፊት ብኰበልልና ብታጣ ይሻለኛል"።
❤ ወንድሞች ሆይ ከፈጣሪው ከእግዚአብሔር ፊት ለፍጡር ማምለጥ ይቻለዋልን። ይህስ ዮናስ የእስራኤልን ልጆች ከሚያስተምሩ ነቢያት ውስጥ ሲሆን ይህን አያውቅምን ነገር ግን አግዚአብሔር በረቀቀ ጥበቡ ይህን አደረገ እንጂ የዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት አድሮ መውጣት መድኃኒታችን በመቃብር ሆድ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት አድሮ ከዚህ በኋላ ከሙታን ተለይቶ ለመነሣቱ ምልክት ይሆን ዘንድ ነው።
ዮናስም ከዓሣ አንበሪ ሆድ ያለ ምንም ጥፋት እንደመጣ እንዲሁ መደኃኒታችን ያለመለወጥ ተነሥቷልና።
❤ እንዲህም ሆነ ከእግዚአብሔር ፊት ዮናስ ሸሽቶ ወደ ተርሴስ አገር ሊሔድ ተነሣ ወደ ኢዮጴ አገርም ወርዶ ወደ ተርሴስ አገር የሚሔድ መርከብን አግኝቶ በገንዘቡ መርከቡን ተከራየ። ከእግዚአብሔር ፊት ኰብልሏልና ከእነርሱ ጋር ወደ ተርሴስ ይሔድ ዘንድ ወደ መርከቡ ወጣ እግዚአብሔርም ታላቁን ነፋስ ወደ ባሕር አመጣ የባሕሩም ማዕበል ከፍ ከፍ አለ መርከባቸውም ሊሰበር ቀረበ። ቀዛፊዎችም ፈርተው ወደ ጣዖቶቻቸው ጮኹ መርከባቸውም ይቀልላቸው ዘንድ ገንዘባቸውን፣ ዕቃቸውን አውጥተው ወደ ባሕር ጣሉ። ዮናስ ግን በዚያን ጊዜ ወደ ከርሠ ሐመሩ ወርዶ ተኝቶ ያንኰራፋ ነበር።
❤ መርከቡንም የሚቀዝፍ ቀዛፊ ወደ ርሱ ወርዶ "ምን ያስተኛሃል እንዳንሞት እግዚአብሔር ያድነን ዘንድ ተነሥተህ የፈጣሪህን ስም ጥራ" አለው። "ይህች መከራ ያገኘችን ስለማናችን ኃጢአት እንደ ሆነ እናውቅ ዘንድ እርስ በርሳቸው ኑ ዕጣ እንጣጣል" ተባባሉ በተጣጣሉም ጊዜ ዕጣ በዮናስ ወጣበት። እነርሱም "ይህች መከራ ያገኘችን በማናችን ኃጢአት እንደሆነ ንገረን አንተስ የምታመልከው ምንድንነው ከወዴትስ መጣህ አገርህስ የት ነው ወዴትስ ትሔዳለህ ወገንህስ ማንነው" አሉት።
❤ ዮናስም እኔስ "የእግዚአብሔር ባርያው ዕብራዊ ነኝ ፈጣሪዬም ምድርንና ሰማይን ባሕሩንና የብሱን የፈጠረ እግዚአብሔር ነው" አላቸው። እነዚያም ሰዎች ታላቅ ፍርሀትን ፈርተው "ምን አድርገሀል" አሉት እሱ ነግሮአቸዋልና ከእግዚአብሔር ፊት ኰብልሎ እንደሔደ እነርሱም አወቁት። ባሕሩ ይታወክ ነበርና ታላቅ ማዕበልም ተነሥቶ ነበርና "ባሕሩ ይተወን ዘንድ እንግዲህ ምን እናድርግህ" አሉት። ዮናስም "አንሥታችሁ ወደ ባሕር ጣሉኝ ባሕሩም ይተዋችኋል ይህ ታላቅ የማዕበል ሞገድ የመጣባችሁ በእኔ ምክንያት እንደ ሆነ አውቃለሁ" አላችው።
❤ ባሕሪቱ ትታወካለችና ማዕበሊቱም በእነሣቸው ትነሣለችና እነዚያ ሰዎች ወደ ምድር ሊመለሱ ወደዱ ነገር ግን ተሳናቸው። ሁሉም አንድ ሁነው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ "አቤቱ ስለዚህ ሰው በእውነት ልታጠፋን አይገባህም አቤቱ እንደ ወደድክ አድርገሃልና የጻድቅ ሰው ደም አታድርግብን" አሉ። ከዚህም በኋላ ዮናስን አንሥተው ወደ ባሕር ጣሉት ባሕርም ድርጎዋን ተቀብላ ጸጥ አለች። እነዚያም ሰዎች እግዚአብሔርን ፈሩት ለእርሱም መሥዋዕትን ሠዉ ስእለትንም ተሳሉ።
❤ እግዚአብሔርም ታላቅ ዓሣ አንባሪን ዮናስን ይውጠው ዘንድ አዘዘው ዮናስም በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት ኖረ። ዮናስም በአንበሪ ሆድ ውስጥ ሳለ ጸሎትን ጸለየ ከዚህም በኋላ በነነዌ አገር በኩል ያ ዓሣ አንበሪ ዮናስን ወደ የብስ ምድር ተፋው። የእግዚአብሔርም ቃሉ ዳግመኛ ወደ ዮናስ መጣ "ቀድሞ አስተምር ብዬ እንደ ነገርኩህ ወደ ታላቂቱ የነነዌ አገር ተነሥተህ ሒደህ አስተምራቸው" አለው።
❤ ዮናስም እግዚአብሔር አስተምር ብሎ እንደ ነገረው ተነሥቶ ወደ ነነዌ ሔደ። ነነዌ ግን ለእግዚአብሔር ታላቅ አገር ናት በዙሪያዋ ያለ ቅጽርዋም ከበር እስከ በር ድረስ በእግር የሦስት ቀን ጐዳና ነው። ወደ ከተማም ሊገባ ደርሶ ያንድ ቀን መንገድ ሲቀረው "ነነዌ እስከ ሦስት ቀን ትጠፋለች" ብሎ አስተማረ። የነነዌም ሰዎች በእግዚአብሔር ቃል አመኑ "ጾምን እንጹም" ብለው አዋጅ ነገሩ የክት ልብሳቸውንም ትተው ማቅ ምንጣፍ ትልቁም ትንሹም ለበሱ። የነነዌ ንጉሥም ይህን ሰምቶ ከዙፋኑ ተነሣ ልብሰ መንግሥቱንም ትቶ ማቅ ለበሰ በአመድ በትቢያ ላይም ተቀመጠ።
❤ "ሰዎችም ቢሆኑ ከብቶችም ምንም ምን አይብሉ ትልልቆችም ትንንሾችም አይጠጡ እንስሶችም ወደ ሣር አይሠማሩ ውኃም አይጠጡ" ብሎ አዋጅ ነገረ። እግዚአብሔርም ከክፉ ሥራቸው እንደ ተመለሱ አይቶ በእነርሱ ላይ ያደርገው ዘንድ ከተናገረው ክፉ ነገር ተመለሰ በእነርሱ ላይም ክፉ ጥፋትን አላደረገም።
❤ ዮናስም ጽኑ ኀዘንን አዘነ ወደ ፈጣሪው እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ለመነ "ጥንቱን በአገሬ ሳለሁ እንዲህ ብዬ የተናገርሁ አይደለሁምን አንተ ይቅር ባይ ርኅሩኅም ከመዓት የራቅህ ቸርነትህ የበዛ እውነተኛ የሆንክ ክፉ ነገርን ከማምጣት እንደምትመለስ አውቃለሁ ስለዚህ ከአንተ ኮብልዬ ወደ ተርሴስ ሔድሁ። ነቢየ ሐሰት እየተባልኩ ከመኖር ሞት ይሻለኛልና አቤቱ አሁን ነፍሴን ከሥጋዬ ለያት" አለ። እግዚአብሔርም ዮናስን "በዚህ ነገር አንተ እጅግ ታዝናለህን?" አለው እርሱም "አዎን አዝናለሁ" አለ። ከዚህም በኋላ ዮናስ ከከተማ ወጥቶ ከከተማው ውጭ ተቀመጠ ጎጆም ለራሱ ሠራ በአገር ላይ የሚደረገውን ነገር እስኪያይ ድረስ ከጥላዋ ሥር ተቀመጠ።
ይበቅል ዘንድ በዮናስ ራስ ላይ ይሸፍነው ዘንድ እግዚአብሔር ቅልን አዘዘ ቅሉም በዚያን ጊዜ በቅሎ የዮናስን ራስ የፀሐይ ትኩሳት እንዳያሳምመው በዮናስ ራስ ላይ ሸፈነው ዮናስም በቅሊቱ መብቀል ታላቅ ደስታ አደረገ።
❤ እግዚአብሔርም በማግሥቱ "ትሉን ይምጣ ቅሉንም ይምታ" ብሎ አዘዘ ቅሊቱንም ቆረጣት እርሷም ደረቀች እግዚአብሔርም ፀሐይ በወጣ ጊዜ "የሚያቃጥል ሐሩር ያለበት ነፋስ ይምጣ" ብሎ ዳግመኛ አዘዘ። ነፋሱም መጥቶ የዮናስን ራስ አሳመመው እርሱም አእምሮውን እስከማጣት ደርሶ በልቡናውም ተበሳጭቶ "ከመኖር ሞት ይሻለኛል" አለ።
❤ እግዚአብሔርም ዮናስን "በቅሊቱ መድረቅ እጅግ አዘንክን" አለው እርሱም "አዎን ልሙት እስከ ማለት ደርሼ አዘንኩ" አለ። እግዚአብሔርም "አንተስ በአንድ ሌሊት በቅላ በአንድ ሌሊት ለደረቀች ውኃ ላላጠጣሃት ላልደከምክባት ቅል ታዝናለህ። ቀኝና ግራቸውን ላልለዩ
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ መስከረም ፳፬ (24) ቀን።
❤ እንኳን ከሰባ ሁሉቱ አርድእት ለአንዱ ለሐዋርያው ለቅዱስ አድሊጦስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል፣ ከላይኛው ግብጽ ለሆኑ ለቅዱስ አባት ለመነኰስ ለአቡነ ጎርጎርዮስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ የሆነው ሐዋርያ ቅዱስ አድሊጦስ፦ ይህም ሐዋርያ ትውልዱ ከአቴና አገር ከታላላቆቿና ከምሁራኖቿ ነው እርሱም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመነ አገለገለውም።
+ + +
❤ አጽናኝ የሆነ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ በሃምሳኛው ቀን ከተቀበለ በኋላ ወደ ብዙዎች አገሮች ሒዶ ሕይወት የሆነ ወንጌልን ሰበከ መግኒን ወደሚባልም አገር ደርሶ በውስጧ የከበረ ወንጌልን ሰበከ የብዙዎችንም ልቦና ብሩህ አድርጎላቸው ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ። የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው ሕይወት የሆኑ የወንጌልንም ትእዛዞች አስተምሮ ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ሾመላቸው ።
❤ ከዚህም በኋላ ከእሳቸው ዘንድ ወጥቶ ወደ አቴና አገር ተመለሰ በውስጧም የከበረ ወንጌልን አስተማረ በዚያን ጊዜም በደንጊያ ወገሩት ጽኑዕ የሆነ ሥቃይንም አሠቃዩት። ከዚህም በኋላ ከእሳት ውስጥ ወረወሩትና በዚያ ተጋድሎውንና ምስክርነቱን ፈጽሞ የሕይወት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዱስ አድሊጦስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ አቡነ ጎርጎርዮስ ዘላዕላይ ግብጽ፦ የዚህም የቅዱስና የተመሰገነ ጎርጎርዮስ ወላጆቹ ደጎች ናቸው በዚህ ዓለም ገንዘብም እጅግ ባለጸጎች ነበሩ ይህን ልጃቸውን ጎርጎርዮስንም በበጎ አስተዳደግ አሳደጉት። መንፈሳዊ የሆነ የቤተ ክርስቲያን ትምህርትን ሁሉ ሥጋዊም የሆነ ጥበብንና ቋንቋን አስተማሩት።
❤ ከዚህም በኋላ የሀገራቸው ኤጲስቆጶስ ወደ ሆነ ወደ አባ ይስሐቅ ወሰዱት እርሱም እጁን በላዩ ጭኖ አናጒንስጢስነት ሾመው።
❤ ከዚህም በኋላ ወላጆቹ ሊአጋቡት አሰቡ እርሱ ግን ይህን ሥራ አልወደደም ሁለተኛም ወደ ጳጳስ ወስደውት ፍጹም ዲቁናን ተሾመ ወደ አባ ጳኲሚስም አዘውትሮ በመሔድ ከእርሱ የእግዚአብሔርን ሕግ የሚማር ሆነ ከወላጆቹም ብዙ ገንዘብን ወስዶ ወደ አባ ጳኲሚስ አቅርቦ በገዳማቱ ለሚሠሩ ሕንፃዎች ሥራ ያደርግለት ዘንድ ብዙ ልመናን ለመነው እርሱም ተሳትፎ እንዲሆንለት ለሕንፃ ቤተ ክርስቲያንና ለመነኰሳት ቤት መሥሪያ አደረገለት ።
❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዓለምን ትቶ ጥሪቱንና ገንዘቡን ሁሉ ንቆ በመተው ወደ ቅዱስ አባ ጳኲሚስም ሒዶ የምንኲስና ልብስን ለብሶ በጾም በጸሎት በመትጋት በመስገድ ከትሕትና፣ ከቅንነት፣ ከፍቅር ጋር ይጋደል ጀመረ አርአያነቱንና ምሳሌነቱን በአዩ ጊዜ ከእርሱ ፈሪሀ እግዚአብሔርን ተምረው አመንዝራዎች የከፋ ሥራቸውን እስከ ተውና ንስሐም ገብተው ንጹሐንም እስከ ሆኑ ድረስ ተጋደሉ። ከአባ ጳኲሚስም ዘንድ ዐሥራ ሦስት ዓመት ኖረ።
❤ አባ መቃርስም ወደ አባ ጳኲሚስ በመጣ ጊዜ ሰውነቱን በማድከም ታላቅ ተጋድሎን እየተጋደለ ጥቂት ቀኖች ኖረ ከዚያም በኋላ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሊመለስ ወደደ አባ ጳኲሚስም ከአባ መቃርስ ጋር እንዲሔድ አባ ጎርጎርዮስን አዘዘው እርሱም አብሮ ሔደ በእርሱም ዘንድ ብዙ ዘመናት ኖረ ።
❤ ከዚህም በኋላ በዋሻ ብቻውን ይኖር ዘንድ እንዲአሰናብተው የከበረ አባ መቃርስን ለመነው እርሱም "እንደ ወደድክ አድርግ" አለው። ያን ጊዜ ወደ ተራራ ሒዶ ታናሽ ዋሻ ቆርቁሮ በውስጧ ሰባት ዓመት ኖረ አባ መቃርስም በየዓመቱ ሁለት ጊዜ መጥቶ ይጎበኘዋል አንደኛ ለከበረ የልደት በዓል ሁለተኛ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተነሣባት በትንሣኤ በዓል ቀን ከርሱ ጋርም ሥጋውንና ደሙን ተቀብሎ ወደ ቦታው ይመለሳል። አባ መቃርስም ስለ ሥራው ሁሉ ይጠይቀዋል እርሱም የሚያየውንና በእርሱ የሆነውን ሁሉ ይገልጽለታል አባ መቃርስም ሊሠራው የሚገባውን የምንኲስና ሥራን ይሠራ ዘንድ ያዘዋል ።
❤ በተጋድሎም ውስጥ ሃያ ሁለት ዓመታት ሲፈጽሙለት ከዚህ የድካም ዓለም ያሳርፈው ዘንድ እግዚአብሔር ፈቅዶ መልአኩን ላከለት እርሱም ከሦስት ቀን በኋላ ከዚህ ከኀላፊው ዓለም ወጥተህ ወደ ዘላለም ሕይወት ትገባለህ አለው።
❤ አባ ጎርጎርዮስም በአስቄጥስ ገዳም ያሉ አረጋውያንን አስጠራቸውና ተሳለማቸው በጸሎታቸውም እንዲአስቡት ለመናቸው እነርሱም ደግሞ በእግዚአብሔር ዘንድ እንዲአስባቸው ለመኑት ከሦስት ቀንም በኋላ አርፎ ወደ ዘላለም ሕይወት ገባ።
+ + +
❤ ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ የሆነው ሐዋርያ ቅዱስ አድሊጦስ፦ ይህም ሐዋርያ ትውልዱ ከአቴና አገር ከታላላቆቿና ከምሁራኖቿ ነው እርሱም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመነ አገለገለውም ።
❤ አጽናኝ የሆነ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ በሃምሳኛው ቀን ከተቀበለ በኋላ ወደ ብዙዎች አገሮች ሒዶ ሕይወት የሆነ ወንጌልን ሰበከ መግኒን ወደሚባልም አገር ደርሶ በውስጧ የከበረ ወንጌልን ሰበከ የብዙዎችንም ልቦና ብሩህ አድርጎላቸው ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ። የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው ሕይወት የሆኑ የወንጌልንም ትእዛዞች አስተምሮ ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ሾመላቸው ።
❤ ከዚህም በኋላ ከእሳቸው ዘንድ ወጥቶ ወደ አቴና አገር ተመለሰ በውስጧም የከበረ ወንጌልን አስተማረ በዚያን ጊዜም በደንጊያ ወገሩት ጽኑዕ የሆነ ሥቃይንም አሠቃዩት። ከዚህም በኋላ ከእሳት ውስጥ ወረወሩትና በዚያ ተጋድሎውንና ምስክርነቱን ፈጽሞ የሕይወት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአቡነ ጎርጎርዮስ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ "ሰላም ለጎርጎርዮስ ወለደብራጦስ አያዩ። ዘውኂዘ መንፈስ ሰትየ ከመ ሐዋርያት ሰትዩ። ሶበ ገደፈ ቅድሜሁ እስከ ዘዕለት ሲሳዩ። ዘሎቱ ለሊሁ ወዘአበዊሁ አጥረዩ። ሥርዓተ ማኅበር ሐነፀ ጳኵሚስ በንዋዩ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመስከረም 24።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ። ወየሐውር እምኀይል ውስተ ኃይል። ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን"። መዝ 83፥6-7። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 10፥16-ፍ.ም።
+ + +
❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ። ወእስከ አፅናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ። ወውስተ ፀሓይ ሤመ ጽላሎቶ"። መዝ18፥4-5። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 2፥12-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 2፥20-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 10፥39-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 10፥1-12። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቅዳሴ ነው መልካም የሐዋርያው ቅዱስ አድሊጦስ እና የአቡነ ጎርጎርዮስ የዕረፍታቸው በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
ሁሉ መፅውታ ጨረሰች። ከዚያም አስቀድማ ያዘጋጀችውን ልብስ ምንኵስና ማለት ቀሚስዋን አጥልቃ አጽፋን ተጐናጽፋ ቆቧን ደፍታ ደብረ ሊባኖስ ከሴቶች ገዳም ደረሰች። የገዳሙ መነኰሳትም በታላቅ ክብር ተቀብለው ወደበዓታቸው መሰሰከረም 24 ቀን አስገቧት ...። ምንጭ ገድለ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ መስከረም ፳፬ (24) ቀን።
❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊቷ ጻድቅ ለታላቋ ለሰላም እናት ለቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም መንና ለገባች ቀን መታሰቢያ በዓል።
+ + +
❤ ክርስቶስ ሠምራ የአምላክ አገልጋይ
ይበራል ስምሽ ዛሬም በምድር ላይ
መመረጥ በእግዚአብሔር እንደ በትረ ማርያም
ለሰው ልጅ ጸልዪ እስከ ዘለዓለም
አዝ............................................
በትረ ማርያም ብሎ ክርስቶስ ሠምራ
ስሟን ለወጠላት ክርስቶስ ሠምራ
ሚካኤል ቀኝ እጅ ረዳት ቢያደርግላት
ዐሥር ሺህ ነፍሳት ክርስቶስ ሠምራ
ማረከች ከሲኦል ክርስቶስ ሠምራ
ባዶ ሆነ ቤቱ አፈረ ሳጥናኤል
የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ መዝሙር።
ስንኙ ይቀጥላል
+ + +
❤ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ፦ በሸዋ ከፍለ አገር በቡልጋ አውራጃ ልዩ ስሟ ቅዱስ ጌዬ የተባለች አገር ነበረች ይህችም የእናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የትውልድ አገሯ ናት። በዚህም አገር በወርቅና በብር በሐር እና በልዩ ልዩ ልብስ በወንድና በሴት አገልጋዮች በፈረስና በበቅሎ የከበረ አንድ ስሙ የታወቀ ሰው ነበር። የዚህ ሰው ስሙ ቅዱስ ደረሳኒ ሲሆን የሚስቱም ስም ቅድስት ዕሌኒ ይባላል ሁለቱም ባልና ሚስቱ እግዚአብሔር የሚፈሩ ደጋግ ሰዎች ስለነበሩ በጎ ሥራቸው በዓለም ሁሉ የታወቀ ነበር። እሊህም ሰዎች በእግዚአብሔር ዘንድ የተመረጠችና የከበረችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን ግንቦት 12 ቀን ወልደው በደም ግባቷና በጠባይዋ እየተደሰቱ አሳደጓት ከዚያም የእግዚአብሔርን ሕግጋትና ሥርዓቶችንም ሁሉ አስተማሯት። ባደገችና ለአቅመ ሔዋን በደረሰች ጊዜ የንጉሥ ባለሟል የሆነ ትውልዱ፤ ነገዱ ከአባ ፃሠርጓ ወገን የሆነ ለኢየሱስ ሞዓ ልጅ ለሠምረ ጊዮርጊስ በሕግ አጋቧት። እሱም በዚህ ዓለም ገንዘብ በጣም የከበረ ከመሆኑም በላይ በይበልጥ መንፈስ ቅዱስ ያደረበት ሰው ነበረ። ከደም ግባቷ የተነሣ ሙሽራይቱ ማለት እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን እጅግ አድርጎ ወደዳት። አሟቷ ኢየሱስ ሞዐም ይህች ብላቴና "በታላቅ ቁም ነገር የተመረጠች ነች" በማለት ትንቢት ይናገርላታል ስለዚህ እንደ እመቤቱ አድርጐ ያከብራት ነበር። ከዚህም በኋላም ለሕጋዊ ባሏ ለሠምረ ጊዮርጊስ ዓሥራ አንድ ልጆች ወለደችለት ከነዚህም መካከል ዘጠኙ ወንዶች ሁለቱ ሴቶች ነበሩ። ልጆችዋንም ሕገ እግዚአብሔርን እያስተማረች በክብር በሥርዓት አሳደገቻቸው።
❤ በዚያን ዘመን የእግዚአብሔር ባለሟል የሚሆን ዓፄ ገብረ መስቀል የሚባል የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበር። እርሱም ዝናዋን ሰምቶ ሥነ ምግባሯን ተመልክቶ ይልቁንም በሷ ላይ ያደረውን ኃይለ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ስለገለጸለት እጅግ አድርጐ ይወዳትና ያከብራት ነበር። ከዕለታት ባንድ ቀን በጸሎትሽ አስቢኝ በማለት በራሱ በንጉሡ ቤተ መንግሥት ከሚያገለግሉ አገልጋዮች ወይም ሠራተኞች መካከል እንዲያገለግሏት 174 አገልጋዮች ላካላት። ዳግመኛም ፈረስና በቅሎ ከነሥራታቸው እንደዚሁም ለነሥታት ሚስቶች የሚገባ ከሐርና ከወርቅ የተሠራ ልብስና የወርቅ ጫማ ላከላት። ነገር ግን እሷ ይህን ሁሉ ክብር አልፈለገችም ይልቁንም ለዓላማዊ ዕንቅፋት ወይም ከንቱ ውዳሴ ይሆንብኛል በዚያውስ ወርቁ ጌጡ ልብሱ ተሸጦ ለነዳያን ይመጸወታል ለቤተ ክርስቲያን መባዕ ይሰጣል እኒህን አገልጋዮች ግን ምን አደርጋቸዋለሁ በማለት ወደ እግዚአብሔር እያመለከተች ቆየች።
❤ ከአገልጋዮችዋ መካከል ምግባሯ የከፋ የምታናድዳትና የምታበሳጫት አገልጋይ ነበረች። ከዕለታት በአንድኛው ቀን እናታችን ክርስቶስ ሠምራ በጣም ተበሳጨችና በዚያች አገልጋይ አፍ ውስጥ የእሳት ትንታግ ጨመረችባት። ያም እሳት ትንታግ በአገልጋይዋ ጉረሮ ድረስ ዘለቀና ገደላት። በዚህን ጊዜ ቤተሰቦችዋ መጥተው የአገልጋይቱን አስከሬን ወደሌላ ክፍል ወሰዱት። ብፅዕት ክርስቶስ ሠምራም ደንግጣ ካለችበት ቤት ውስጥ ወደ ሌላው ክፍል ገባችና ወደ ሰማይ አቅንታ "ወይኔ ወዮልኝ ወዮታ አለብኝ የካህን ሚስት ስሆን ነፍስ ገዳይ ሆኛለሁና። ሰውስ ምን ይለኛል ለነፍሴስ ምን እመልስላታለሁ ከእግዲህ ከክርስቲያን ወገን ልቆጠር አይገባኝም በደሌንስ እንደምን አድርጌ ልሸሸሽጋት እችላለሁ" እያለች አለቀሰች።
❤ ከዚህ በኋላ እንዲህ ስትል ለእግዚአብሔር ብፅዓት አደረገች "አቤቱ ይህችን በእኔ እጅ የሞተችውን አገልጋይ ነፍስዋን ከሥጋዋ አዋህደህ ብታሥነሣልኝ ልጆቼን ቤቴን ንብረቴን ትቼ ባለ ዘመኔ ሁሉ አንተን እከተላለሁ። አንተን ከመከተል ከቶ ወደኋላ አልልም። ለሰውነቴ ጌጥ ወይም ግርማ ሞገስ የሚሆናት ወይም የሚሞቃት ልብስ ከቶ አልለብስም ሥጋዬን የሚያረካ ምግብም አልመገብም። አቤቱ ጌታዬ ሆይ ጸሎቴን ስማኝ ልመናዬም በፊትህ ፈጥኖ ይድረስ አቤቱ ፊትህን ከኔ ከባሪያህ አትመልስ"። እንዲህ እንዲህ እያለች በልቅሶና በኀዘን ለብዙ ሰዓት ከጸለየች በኋላ ድካም ተሰማትና ዕረፍት አደረገች። ከዚህ በኋላ ቤተሰቦችዋ እስዋ ወዳለችበት ክፍል መጥተው "እመቤታችን ሆይ ሙታ የነበረችው አገልጋይሽ በእግዚአብሔር ኃይልና በአንቺ ጸሎት ተነሥታለችና ደስ ይበልሽ" አሏት። በዚህ ጊዜ ፈጥና ተነሥታ ደስ እያላት ሙታ የነበረችው አገልጋይ ካለችበት ቦታ ደረሰችና ሕይወት አገኘቻት ከዚያም ቃሏን ከፍ አድርጋ "ልመናዬን ቸል ያላለ ቸርነቱንም ከኔ ከባሪያው ያላራቀ ፈጣሪ ይክበር ይመስገን" ብላ በታላቅ ምስጋና እግዚአብሔር አመሰገነች።
❤ ከዚህ በኋላ አስቀድሞ ከአፏ የወጣውን ከአንደበቷ የተነገረውን ቃል አስባ ልብሰ ምንኵስናዋን ማለት ቆቧን ቀሚሷን አጽፏን መታጠቂያዋን አዘጋጀች። ቤተሰቦቿና አገልጋዮቿም "እመቤታችን ሆይ ይህ የምታዘጋጂው የምናኔ ልብስ ለምንሽ ነው ወይስ ለማን ነው የምታዘጋጂው" አሏት። እርሷም "ሃይማኖት ያስተማሩኝ አባቴ ልብስ አልቆባቸዋል ሲሉ ሰምቼ ለሳቸው ነው የማዘጋጀው" አለቻቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ከዕለታት ባንደኛው ቀን እናታችን ክርስቶስ ሠምራ አገልጋዮቿን ወደ ቤተ ክርስቲያን እንሄድ ዘንድ ተዘጋጁ አለቻቸውና እነሱም አሺ በጎ ብለው አጅበዋት ወደቤተ ክርስቲያን ሄዱ። ከዚያም እንደደረሱ "በሉ እንዲህ እኔ ከዚህ ጥቂት እቆያለሁና እናንተ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ ለኔ ይህች አንድዲት አገልጋይና ይህ ሕፃን ልጅ ብቻ ይበቁኛል አለቻቸው። በዚያኑ ጊዜ አገልጋዮቿ እጅ እየሱ ወይም እየተሰናበቱ ወደቤታቸው ተመለሱ። ከዚያም ከዳዊት መዝሙር "ልቤ ጽኑ ነው አቤቱ ልቤ ጽኑ ነው እግዚአብሔርን ፈጽሜ አመሰግነዋለሁ እግዚአብሔር የደህንነቴ መብራት ስለሆነ ምን ያስደነግጠኛል እግዚአብሔር የሕይወቴ መተማመኛ ነው ምንስ ያስፈራኛል የሚለውን እየጸለየች የሚያልፈን ዓለም በማያልፈው ዓለም ለመተካት ወይም ለመለወጥ አውጭኝ እግሬ ብላ ገሠገሠች። ያ በልስላሴና በእንክብካቤ የኖረ እግር ከመንገዱ ብዛት እንደዚሁም ከቅርቅፍቱና ከእንቅፋቱ የተነሣ ፈለግ ሲያወጣ ሥጋውን እየቆረጠች ስትጥለው ደሙ እንደጒርፍ ውሃ ይወርድ ነበር። ያች የተከተለቻት አገልጋይ ግን ከእመቤቷ እግር እየተቆረጠ የሚወድቀውን የአካል ቊራጭ እያነሳች በልብሷ ትቋጥረው ነበር። በዚህ ዓይነት ችግርና ፀሐይ ሐሩር የብዙ ጐዳና ጉዞ ተጉዛ ከአሰበችበት አገር ደረሰች። በደብረ ሊባኖስ አቅራቢያ ወይም አካባቢ ስትደርስ የራስ ፀጒራን ይዛው በነበረ ምላጭ ላጨች ልብሷንም አውልቃ ለነዳያን አከፋፈለች የያዘችውንም ገንዘብ በመንገድ ላይ ላገኘችው
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ መስከረም ፳፫ (23) ቀን።
❤ እንኳን ለቅዱሳን ጻድቃን መነኰሳት አውናብዮስና እንድርያኖስ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓልና ለሰማዕቱ ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከመርዓተ ክርስቶስ (ከክርስቶስ ሙሽራ) ከቅድስት ድንግል ቴክላ ለመታሰቢያ በዓል፣ ከአርባ አራት ሰማዕታት፣ ከመንክራዊ ጎርጎርዮስ ከእንጺናና፣ ከብሊናም ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ የዚህ ሳምንት መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ በ፫ "ዝንቱ መስቀል ቤዛነ መድኃኒትነ ለአይሁድ ስደተ ኮነ ዝንቱ መስቀል ቤዛነ መድኃኒትነ ወለነኒ ሕይወተ ኮነነ ዝንቱ መስቀል ቤዛነ መድኃኒትነ ዮም መስቀል ተሰብሐ ዮም መስቀል ለአኅው አብርሃ ዝንቱ መስቀል ቤዛነ መድኅኒትነ ዝንቱ መስቀል ቤዛነ መድኅኒትነ። ትርጉም፦ መስቀል ለእኛ መድኃኒታችንና ሕይወት ሆነን፣ ለአይሁድ ግን ስደታቸው ሆነ፤ ዛሬ መስቀል ተመሰገነ (ከበረ) ዛሬ መስቀል ለወንድሞች አበራ።
+ + +
❤ ቅዱሳን ጻድቃን መነኰሳት አውናብዮስ እና እንድርያስ፦ እሊህ ቅዱሳንም ከልዳ ሀገር ከታላላቆቹ ተወላጆች ናቸው ከታናሽነታቸውም በአምላካዊ ምክር ተስማምተው በሶርያ ውስጥ ከሚገኙ ገዳማት ወዳንዱ ገዳም ሒደው መነኰሳት ሆኑ።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ ከበረ ወደ ተመሰገነ አባ መቃርስ ሔዱ ደቀ መዛሙርቱም ሁነው ታዘዙለት ምክሩንም በመቀበል በጾም በጸሎት በገድል ሁሉ ተጠምደው የሚኖሩ ሆኑ በእንዲህ ያለ ሥራም በዚያ ሦስት ዓመት ኖሩ በጎ የሆነ ተጋድሎአቸውና የአገልግሎታቸው ዜና በተሰማ ጊዜ አውናብዮስን መርጠው ኤጲስቆጶስነት፣ እንድርያስን ቅስና ሾሙአቸው በበጎ አጠባበቅም የክርስቶስን መንጋዎች ጠበቋቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ሥጋቸውን ፈጽሞ እስከ አደከሙ ድረስ ተጋድሎአቸውንና አገልግሎታቸውን እጅግ አበዙ። ከሀዲ ንጉሥ ዮልዮስም ስለእርሳቸው በሰማ ጊዜ ወታደሮች ልኮ ወደርሱ አስቀርቦ የክብር ባለቤት ክርስቶስን ክደው ወደ ረከሰች አምልኮቱ እንዲገቡ አዘዛቸው ያን ጊዜ እርሱንና የረከሱ ጣዖታቱን ረገሙ እርሱም ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃያቸው ወደ ብዙ ክፍልም ቆራርጦ ከፋፈላቸውና ነፍሳቸውን በእግዚአብሔር እጅ ሰጡ።
❤ እያንዳንዳቸውም ሦስት ሦስት አክሊላትን ተቀበሉ አንዱ በገድል ስለ መጸመድና ስለ ምንኲስና ዋጋ፣ ሁለተኛው ስለ ክህነት አገልግሎት፣ ሦስተኛው ደማቸውን ስለ ማፍሰሳቸው ነው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ "ሰላም ለአውናብዮስ ወለእንድርያስ ውሉዳ። ለምድረ ጊዮርጊስ ልዳ። እለ ኮኑ ስምዐ ለምድረ ዮልያኖስ በዐውዳ። ወሰላም ለቴክላ መርዓተ ክርስቶስ እንግዳ። ከመ ስንክሳር ወደሳ ወንዕዳ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ የመስከረም 23።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ። ከመ ያምሥጡ እምገጸ ቅስት። ወይድኀኑ ፍቁራኒከ"። መዝ 59፥4-5። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 1፥10-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 4፥1-12 እና የሐዋ ሥራ 2፥22-37። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 9፥18-28። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ። መልካም በዓልና ዕለተ ሰንበት ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
መስከረም 22 በቅዳሴ ጊዜ ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ። ከመ ያምሥጡ እምገጸ ቅስት። ወይድኀኑ ፍቁራኒከ"። መዝ 59፥4-5። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 1፥10-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 4፥1-12 እና የሐዋ ሥራ 2፥22-37። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 9፥18-28። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ። መልካም በዓልና ዕለተ ሰንበት ለሁላችንም ይሁንልን።
https://t.me/Eotcw
1 161
ዮስም ጣዖታቱን ያጠፋቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ለመነ በዚያን ጊዜም ጌታችን መልአኩን ልኮ የጣዖታቱን ራሶቻቸውን ቆረጠ ፊቶቻቸውንም በፍም አጠቆረ ሽልማታቸውንና ዘንባባውን የጣዖቱን ቤት ሥርዓት ሁሉ አቃጥሎ አጠፋ።
❤ ማግሥትም በሆነ ጊዜ ለአማልክቶቻቸው እንደ ልማዳቸው በዓልን ሊአከብሩላቸው በከበሩ ልብሶች ተሸልመው ሲመጡ ተጐሳቁለው ጠፍተው አዩአቸው የጣዖቶቻቸውን ድካማቸውን አወቁ። እንዲህም አሉ "አማልክቶቻችን ራሳቸውን ማዳን ያልቻሉ እኛን ያድኑ ዘንድ እንዴት ይችላሉ" ይህንንም ተናግረው ከአትሪብ መኰንን ጋር በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት አመኑ።
❤ ከዚያም ደግሞ ቅዱስ ዮልዮስ ጡዋ ወደሚባል አገር ሔደ ከርሱም ጋር የገምኑዲ መኰንንና የአትሪብ መኰንን አሉ የጡዋ መኰንን ወደ ሁነ ወደ እስክንድሮስ ቀርቦ በፊቱ ክብር ይግባውና በጌታችን ስም ታመነና እንዲህ አለው "ገድሌን ፈጽምልኝ ራሴንም እንዲቆርጡ እዘዝና የምስክርነት አክሊልን ተቀብዬ ወደ ክብር ባለቤት ወደ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ እንድሔድ"። እስክንድሮስም "እኔ አላሠቃይህም በአንተ ላይም ምንም ክፉ ነገር አላደርግም" አለው።
❤ ቅዱስ ዮልዮስም አምስት መቶ የሚሆኑ አገልጋዮቹን ሰይፎቻቸውን መዝዘው እስክንድሮስን እንዲአስፈሩት አዘዛቸው በዚያንም ጊዜ በእስክንድሮስ ላይ ተነሥተው "ለክብር ባለቤት ክርስቶስ ምስክሮቹ እንሆን ዘንድ የሁላችንም ራሶቻችንን እንዲቆርጡ ካላዘዝክ እኛ እንገድልሃለን" አሉት። ዳግመኛም ርኵስ መንፈስ እንዲጫንበት ቅዱስ ዮልዮስ አዘዘው ወዲያውኑ በመኰንኑ በእስክንድሮስ ላይ ተጫነበት በዚያንም ጊዜ ራሶቻቸውን ይቆርጧቸው ዘንድ በጽሑፍ አዘዘ ሁሉንም ቅዱሳን ሰማዕታትን ቆረጧቸው።
❤ እሊህም ቅዱስ ዮልዮስ፣ ልጁም ቴዎድሮስ፣ የከበረ ወንድሙ ዮንያስ፣ አምስት መቶ አገልጋዮቹ የገምኑዲና የአትሪብ መኰንኖች ብዙዎች ሕዝቦችም የሁሉም ቁጥራቸው አንድ ሺህ አምስት መቶ ነው። በዚያች ቀን ከቅዱስ ዮልዮስ ጋር በሰማዕትነት የሞቱ ናቸው የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ።
❤ የቅዱስ ዮልዮስን የልጁንና የወንድሙን ሥጋ አንሥተው ወደ እስክንድርያ አገር አደረሱ እርሱ በውስጧ ነዋሪ ሁኖ ነበርና ትውልዱ ግን አቅፋሐስ ከሚባል አገር ነው በአማረ ቦታ ውስጥም አኖሩአቸው። ከዚያም በኋላ ያማረች ቤተ ክርስቲያንን ሠሩላቸው ከእርሳቸው ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራት ተደረጉ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሁሉ ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 22 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለኮቶሎስ አኅወ እክሱ ብፅዕት። ወፍቁረ ጣጦስ ሰማዕት። ሶበ አተበ በመስቀል ትእምርተ ሕይወት። መጠነ ዐሠርቱ ወክልኤቱ በእመት። እምዐውደ ምኵናን ሰሰለ እሳት"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመስከረም 22።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ። ከመ ያምሥጡ እምገጸ ቅስት። ወይድኀኑ ፍቁራኒከ"። መዝ 59፥4-5። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 1፥10-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 4፥1-12 እና የሐዋ ሥራ 2፥22-37። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 9፥18-28። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ። መልካም በዓልና ዕለተ ሰንበት ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
ንዒ ማርያም ዘምስለትጉሃን ሐራ
ወንዒ ገራህት ፈራኢተ ቁርባን ጵርስፎራ
ዓለምሰ ታማስኖ ለዘአፍቀራ
መኑ ጠቢብ ወለባዊ ዘየአምር ግብራ
ዘቀተለት ብዙሀነ በሕምዛ አስጊራ
ንዒ ማርያም ለዕውር ብርሃኑ
ወንዒ ድንግል ለጽሙዕ አንቅዕተ ወይኑ
ተኀድገኒኑ ኦ ወትመንነኒኑ ሐዘነ ልብየ እነግር ለመኑ
ንዒ ማርያም ለእግዚአብሔር አስከሬኑ
እንተኢያወዐየኪ እሳተ ርዕስኑ
መሐረኒ ድንግል ወተሠሃለኒ በበዘመኑ
ለእመ መሀክኒ እግዝዕትየ ዘይኴንነኒ መኑ
ኮናኔ ሥጋ ወነፍስ ወልድኪ አኮኑ
1 161
#የመጀመሪያዋ #ማህሌተ ጽጌ እና የመስከረም 29 ቅድስት #አርሴማ በዓል ስርአተ ማህሌት እየተዘጋጀ ነው
ቀደም ተብሎ ይላካል!
#ይጠብቁን
#ለኦርቶዶክሳውያን ቻናሉን ያጋሩ
https://t.me/Eotcw
1 161
መዝሙር ዝንቱ ውእቱ መስቀል ከመስከረም ፲፯ - መስከረም ፳፫
(በ፫/ደ) ዝንቱ ውእቱ መስቀል በአማን ዕፁበ ያቀልል በጽንዐ ኃይል ወበሠናይ ምግባር በዕፀ መስቀሉ ኃጢአተ ይሠሪ፤ ጸርሑ ጻድቃን እምደብር ልዑል ወኃጥአነ ምድር በማዕከለ ደይን፤ ለእምነ ጽዮን ቆመ ማዕበል በዕለተ ሰንበት ገሠፃ ለባሕር፤ በዕለተ ሰንበት ገሠፃ ለባሕር ደቂቀ እስራኤል ዐደዉ በእግር፤ ደቂቀ እስራኤል ዐደዉ በእግር ንሕነ ነአምን ረድኤተ ወኃይለ፤ ንሕነ ነአምን ረድኤተ ወኃይለ ጽንዕነ ቤዛነ በማዕከለ ፀር፤ ኃይልነ ወፀወንነ ወሞገስነ ዝንቱ ውእቱ መስቀል።
@EOTCWW
https://t.me/Eotcw
# Join & share #
