Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗
Ir al canal en Telegram
Addis Ababa, Ethiopia Con-Site is a Comprehensive Construction Filed Works and Materials Reference Catalogue for Architects, Engineers, Consultants and Customer service. t.me/ConsitesolutionBot ☜|]Chat us! Buy ads: https://telega.io/c/consite
Mostrar más3 586
Suscriptores
-324 horas
-227 días
-1130 días
Archivo de publicaciones
ስለ Field Hammer Test
🚧በአሁኑ ሰዓት ያለው የኮንክሬት ቅይጥ አተገባበር (Concrete Mixing Methodology) የተሻሻለ እየሆነ ቢመጣም አንዳድን ችግሮች ይስተዋላሉ።
🏷ለምሳሌ ያህል፦ ወጥ የሆነ የጠጠር እና የአሸዋ አይነት አለመጠቀም፣ በቤተሙከራ የቅይጥ ምጥጥን (Mix Design Ratio) ሳይወሰንላቸው የተለያዩ የሲሚንቶ ምርት አይነቶች መጠቀን፣ ሌላ ቦታ ተቀይጦ የሚመጣ እና የኮንክሬት grade ለባለቤቱ በውል ያልተገለጸ አርማታን ለሙሌት መጠቀም (ready mix concrete) የመሳሰሉት ይገኙበታል።
እነዚህ ሂደቶች ለሕንጻው ወይም ለአርማታ መዋቅሩ ስትራክቸራል ፍላጎት አለመሟላት ሊያስከትል ይችላል።
በመሆኑም በሳይት ላይ የምንጠቀማቸው ሙከራዎች ያሉ ሲሆን በዋናነት ሐመር ቴስት (Hammer
⭐️በተለምዶ የመዶሻ ሙከራ በመባል የሚታወቀው Hammer Test ኮንክሪት ከተሞላ በኋላ ባሉት በ7ኛ እና በ28ኛ ቀናት ውስጥ ሊከናወን ይችላል (በእርግጥ በመካከል ባሉ ቀናት እና ከ28ኛ ቀን በኋላም እስከ 3 ወር ድረስ የሚተገብሩ ሀገራት አሉ)።
ይህ Non-Destructive Test ምድብ የሆነ የሙከራ ዘዴ የኮንክሪት ጥንካሬን የሚለካ ሲሆን ይህም ከአርማታ ውቅሩ ጥንካሬ ጋር የተያያዘ ምዘና ነው። በመሆኑም፦
1ኛ) በ7ኛ ቀን፦ የ7ኛ ቀን የመዶሻ ሙከራው የአርማታው መዋቅር (Concrete Structure) ያጎለበተውን የጥንካሬ እድገት የምለካበት ሲሆን እስከ 7ኛ ቀን ድረስ ከሚጠበቀው ዝቅተኛ ጥንካሬ (Minimum Compressive strength) ውስጥ ከ60% - 70% ድረስ ማጎልበት ይኖርበታል።
2ኛ) በ28ኛ ቀን፦ በ28ኛ ቀን የሚደረግ ሙከራ የአርማታ ውቅሩ የሚጠበቅበትን 100% ጥንካሬ ማጎልበቱን የምናረጋግጥበት የሜዳ ሙከራ (Field Test) ነው።
⚡️ልብ ሊባል የሚገባው ይህ የሐመር ቴስት የኮንክሪት ጥንካሬን ለመወሰን ብቸኛው ዘዴ ሳይሆን እንደ ተጨማሪ ዘዴ መጠቀም የምንችለው መሆኑን ነው። ለበለጠ ውጤት ደግሞ Core Sampling፣ Cylinder test የመሳሰሉትን የጥንካሬ መፈተሻዎችን መጠቀም አለብን።
🔰የሐመር ቴስት ትግበራ ጥንቃቄ (Cautions during field Hammer test)፦
~ ቢያንስ 10 ቦታዎች ላይ መሞከርና ማንበብ
~ እያንዳንዱ ናሙና እርስ በእርሱ ቢያንስ 2.5ሴ.ሜ ተራራቁ መሆን አለባቸው
~ ከኮንክሬት መዋቅሩ ጠርዝ ቢያንስ 10ሴ.ሜ መራቅ
~ ሐመር ቴስት መሳሪያው የሚመታበትን አንግል ማወቅ (90° ቢሆም ይመረጣል)
~ የአሥሩን ናሙናዎች አማካኝ ማስላትና እና የመጣውን አማካኝ (Average) ውጤት ለውሳኔ መጠቀም ናቸው።
+2
ፌሮ የአርማታ ብረት መግዛት ስትፈልጉ ጥሩ ደንበኞች አቅራቢዎች ስላሉን አድራሻቸውን ልንሰጣችሁ እችላለን
📞+251-908280208 | +251- 707999001 | +251-89999001 ለመልዕክት ይጠቀሙ, ይደርሰናልቴሌግራም መልዕክት መስጫ ቦት
t.me/unitysupplydbot • ••☜|]ፈጣን ምልሽ ያገኛሉ! ሰናይ ጊዜ🤚
+5
ሴራሚክ ቴራዞ መግዛት ስትፈልጉ ጥሩ አቅም ያላቸው ደንበኞች አቅራቢዎች ስላሉን አድራሻቸውን ልንሰጣችሁ እችላለን
📞+251-908280208 | +251- 707999001 | +251-89999001 ቴሌግራም" ጥያቄም ሆነ ሀሳብ ካለችሁ በቀጥታ ከስር /ያለውን: t.me/UnitySupplydbot ☜|] ለመልዕክት ይጠቀሙ, ይደርሰናልፈጣን ምላሽ እንሰጣለን.. .)
የግንባታ መመሪያ ሴፍቲን በተመለከተ!
Via~ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ➡️https://t.me/con_site 🏗💠
👉ሙሉ ግንባታው ሊጠናቀቅ 2.4 በመቶ ብቻ የቀረው ታላቁ የ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ 80 ቢሊዮን ብር ያስፈልገዋል መባሉን ሸገር ሬድዮ ዘግቧል።
🚧ግንባታው 97.6 በመቶ እንደደረሰና ጥቂት የማጠናቀቂያ ስራዎች ብቻ እንደቀሩት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ የፕሮጀክት ፅህፈት ቤት ተናግሯል ተብሏል፡፡
🏷ከ 14 ዓመት አመታት በፊት የግንባታው መሰረት ድንጋይ ሲጣል 80 ቢሊዮን ብር ያስፈልገዋል ተብሎ የተጀመረው የታላቁ ህዳሴ ግድብ፤ የ2.4 በመቶ ስራም ቀርቶት ለምን 80 ቢሊዮን ብር እንዳስፈለገ በብዙዎች ጥያቄን ጭሯል።
⏺በጉዳዩ ዙሪያ የህዳሴ ግድብን የቦንድ ሽያጭ ሲከውን የቆየውን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የካፒታል ገበያ ዳይሬክቶርት ዳይሬክተር አቶ ዳዊት አማረ ከሸገር ሬድዮ ለቀረበላቸው ጥያቄ የግንባታ ስራው በተለያ ደረጃ ስለሚመራ ስለዚህ ጉዳይ ፕሮጀክቱን የሚመሩት የስራ ሃላፊዎች ናቸው የሚያውቁት ብለዋል፡፡
⏺ይሁንና ልማት ባንክ የቦንድ ሽያጭ ላይ እንደመሳተፉ እስካሁን ከህዝቡ ከ20.2 ቢሊየን ብር በላይ መዋጣቱን መናገር እንችላለን ብለዋል፡፡
⏺ለማጠናቀቂያ ስራው ከሚያስፈልገው ገንዘብ ልማት ባንክ 10 ሚሊዮን ብር መስጠቱንም አቶ ዳዊት ተናግረዋል፡፡
⏺ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤቱ በበኩሉ በዚህ ዓመት እስከ 1.6 ቢሊዮን ብር ከህዝቡ ለመሰብሰብ አቅዶ እየሰራ መሆኑን ተናግሯል፡፡
⏺በዚህም ባሳለፍነው ዓርብ 110 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታስቦ በተካሄደ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ከፋናንስ ተቋማት መሰብሰብ የተቻለው 25.9 ሚሊዮን ብር ብቻ መሆኑን ዘገባው አመላክቷል፡፡
@etconp
ክፍት ስራ
Amish construction
1 -site engineer
1 -office engineer ይፈልጋል
🏷የስራ ልምድ ቢኖራችሁ ይመረጣል
📍የስራ ቦታ 24 ነው ስራው የሚመለከታችሁ በ +251967082822 Telegram ላይ CV ላኩ!
Repost from Akla engineering plc
+9
ድርጅታችን አክላ እንጂነርንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ጥራታቸውን የጠበቁ ለመጋዘን ፡ ለመኖሪያ ቤት እንድሁም ለአጥሪ የምሆኑ
EGA SHEET METAL
EGA TILES
CIS O.4 ,0.3,0.25 & 0.2 mm
ለ ቆርቆሮ አምራች ድርጅት ኮይል(coil) በብዛት እናቀርባለን
በ 1እና 1.2 ሜትር ስፋት (width )
ክፍለሀገር በአጋርነት መስራት ለሚፈልጉ ነጋዴዎች ድርጅታችን ዝግጁ መሆኑን እናሳዉቃለን
ለበለጠ መረጃ
📲 0906852424
. 0986047070
email aklaengineerigplc@gmail.com
Telegram akla engineering plc
https://t.me/aklaengineeringplc
በጎረቤት መሬት ውስጥ ወሰን አልፎ ግንባታ ስለመፈጸም -- (የሕግ አግባብ)
🚧ከግንባታ ሥራ ጋር ተያይዞ በሀገራችን ፍርድ ቤቶች ከቀረቡ ሪፖርቶች መካከል ሰፊውን ቦታ የያዘው «ጎረቤት ወሰን አልፎ አጥር ማጠር፣ እጽዋት መትከል እና በመሬት ውስጥ ወይም በአየር ላይ ግንባታ መፈጸም» በሚሉ ጉዳዮች የቀረቡ አቤቱታዎች ናቸው።
⏺በመሆኑም አንድ ሰው የይዞታ ማረጋገጫ ከተሰጠበት የይዞታ ድንበር መስመሮች ውጪ በመሬት ውስጥም ይሁን ከመሬት በላይ (በአየር ላይ አንጠልጥሎ) ግንባታ መፈጸም አይችልም።
⏺ግንባታ ይቅርና ባለይዞታው ካልፈቀደ በቀር እና በህግ ትእዛዝ ካልተሰጠ በቀር ማንም ሰው በሌላ ይዞታ ላይ አልፎ መግባት (መራመድ፣ መቆም) አይችልም (ፍ/ብ ሕ/ቁ 1216)።
⏺አንድ ጎረቤት በራሱ ይዞታ ላይ ዛፍ ቢተክልና ዛፉ እያደገ ሲሄድ የዛፉ ሥሮች በመሬት ውስጥ ወደሌላኛው ባለይዞታ መሬት ውስጥ ቢገቡ አልፈው የገቡትን የዛፉን ሥሮች የመቁረጥ ግዴታ አለበት፣ የዛፉ ቅርንጫፎችም በአየር ላይ በሰው ይዞታ ላይ ከገቡ ወይም ቅርንጫፎቹ ወደሌላ ጎረቤት ይዞታ ውስጥ ከተስፋፉ እነዚያን ቅርንጫፎች የመቁረጥ ግዴታ አለበት (ፍ/ብ ሕ/ቁ 1212)
📜በመሆኑም በፍትሐብሔር ህግ ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው አንድ ሰው በጎረቤቱ ይዞታ ላይ ግንባታ የፈጸመ ከሆነ (በመሬት ውስጥ መሰረት ግንባታ Foundation፣ በመሬት ላይ ወለል ወይም በአየር ላይ ተንጠልጣይ ውቅር Cantliver Structure ሊሆን ይችላል) ይዞታ የተጣሰበት አካል የባለቤትነት አቤቱታ በፍትሐ ብሔር /ሕ/ቁ 1206 መሰረት በማዘጋጀት ስልጣን ላለው ፍ/ቤት የማመልከት መብት አለው፡፡
⏺አቤቱታው ይዞታው በሚገኝበት አካባቢ ባለ ፍርድ ቤት ቢሆን የተመረጠ ሲሆን በይዘት ደረጃ የይዞታው ባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ የተያያዘበት፣ ግንባታ የፈጸመው አካል ምን ያህል ካሬሜትር አልፎ እንደገባ፣ እና ያለአግባብ የተፈጸመውን የግንባታ አይነት በመጥቀስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
⏺የአቤቱታው ፍሬ ነገር (ፍላጎት ደግሞ) ግንባታ የፈጸመው አካል አልፎ የገነባውን የግንባታ አይነት በራሱ ወጪ አፍርሶ ይዞታውን ቀድሞ በነበረበት ይዘት እንዲያስረክብ ውሳኔ እንዲወሰን የሚጠይቅ መሆን አለበት።
ም
Century Addis Construction PLC
Contract Bole on Atlas Road Above 2000 Habesha Restaurant or Near Aya or Mado Hotel at Century Executive Tower 17th Floor office Human Resources Development and Management Department ,
Addis Ababa
January 13, 2025 - January 25, 2025
1. Civil Engineer
Job Requirement
Qualification: MSc/B.Sc. in Civil Engineering or Related Field
Experience: 4/6 years relevant experience
Qty: 2
Work Place: Addis Ababa
2. Site Engineer
Job Requirement
Qualification: MSc/B.Sc. in Civil Engineering or Related Field
Experience: 5/7 years relevant experience
Work Place: Debre brhan
How to ApplyNB: – Interested and qualified applicants who meet the above requirements are invited to summit their copies of testimonials with update CV and work Experience within 10 working days in persons.Address: – Bole on Atlas Road Above 2000 Habesha Restaurant or Near Aya or Mado Hotel at Century Executive Tower 17th Floor office Human Resources Development and Management Department For More information:– Any question please contact us at 09-60-99-99-97
📌 የፌደራል መንግስት የግዥ አፈፃፀም ረቂቅ መመሪያ ከላይ ተያይዟል።የፌደራል ግዥና ንብረት ባለስልጣን ባለድርሻ አካላትን በማወያየት ግብአት እያሰባሰበበት ይገኛል።
📌 ከረቂቅ መመሪያው መረዳት እንደሚቻለው የውለታ ጊዜያቸው 18 ወራትና ከዚያ በላይ ለሆኑ የግንባታ ሥራዎች ብቻ የዋጋ ማስተካከያ እንደሚደረግ የሚገልፀውና ማስተካከያው ተፈጻሚ የሚሆነው ከአስራ ሁለት ወራት በኋላ መሆኑን የሚያስቀምጠው የዋጋ ማስተካከያ አንቀፅ ማሻሻያ አልተደረገበትም።
በቦሌ ለሚ የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ይስተዋል የነበረውን የሃይል መቆራረጥ ችግር ለመቅረፍ የተከናወነ የማስፋፊያ ስራና በአካባቢው የሚገኙ ደንበኞች አስተያየት !
የ "Site Diary" ጥቅምና ይዘት
{The importance and Format of Site Diary}
🚧በግንባታ ሂደት ውስጥ የምናገኛቸው የተለያየ ዓላማና ይዘት ያላቸው ሰነዶች አሉ። ለምሳሌ ያህል፦ የውል ሰነድ (contract document)፣ የሥራ ፍቃድ (Work Permit/order)፣ የግንባታ ፍቃድ (Building Permit)፣ የሥራ ምዘና መዝገብ (Checklists)፣ የዕለት ሥራ ማስታወሻ (Site Diary)፣ ንድፎች (Drawings) ... የመሳሰሉት ይገኙበታል። በሀገራችን የውል ፈጻሚዎች (አሠሪ፣ ተቋራጭ እና አማካሪ) ግጭት ውስጥ ለመግባታቸው አንዱና ዋነኛው ምክንያት እነዚህ ሰነዶች በግንባታ ሥራ አለመሟላታቸው መሆኑን የተጠኑ ጥናቶችም ጠቁመዋል።
💫ከእነዚህ ውስጥ አንዱ የሆነውን የዕለት ሥራ ማስታወሻ (Site Diary) እንመለከታለን።
⏺ብዙ ጊዜ ስለዚህ ሰነድ ያለን ትኩረት ለዘብ ያለ ሆኖ የሚስተዋል ቢሆንም ብዙ የሥራ ተቋራጮች፣ አማካሪዎች እና አሠሪዎች ከስረውበታል።
ክፍል አንድ ዋና ዋና ጥቅሙ፦1ኛ). የዕለት ተግባራትን መመዝገቢያ፡ ይህ የማስታወሻ ጥራዝ ወይም ሰነድ በየቀኑ በግንባታ ቦታው ላይ የተከናወኑ ሥራዎችን እንመዘግብበታለን። የተሰሩ ሥራዎችን፣ ግንባታው ያለበትን ደረጃ፣ በዕለቱ ያለውን የአየር ሁኔታ፣ ለግንባታ ሥራው የተሳተፉ ባለሙያዎችንና የጉልበት ሰራተኞችን ብዛት፣ የገጠሙ ችግሮችን፣ የተወሰዱ መፍትሔዎችን፣ በባለድርሻ አካላት የታዘዙ ልዩ ትእዛዞች (ካሉ) እነዚህ መረጃዎች የምንመዘግብበት የሁሉም የግንባታ ስራዎች አጠቃላይ ዕለታዊ መዝገብ ሆኖ ያገለግላል። ይህ ሰነድ የፕሮጀክቱን እድገት ለመከታተል ወሳኝ ሲሆን በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴው ውስጥ ግልፅነትን ያረጋግጣል፣ የፕሮጀክት አስተዳዳሪዎች እና ባለድርሻ አካላት ስለቦታው ሁኔታ እንዲያውቁ ያግዛል። 2ኛ). ቅሬታ ወይም የክርክር የሚፈታበት ነው፦ በግንባታ ፕሮጀክቶች ውስጥ መጓተትን፣ የአቅም ለውጥን ወይም የሥራ ጥራትን በተመለከተ አለመግባባቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ። በመሆኑም የዕለት ክስተት ማስታወሻው ሰነድ በቦታው ላይ ስለ ሁነቶች እና ሁኔታዎች ማስረጃ የሚያቀርብ ህጋዊ የግንባታ ሰነድ ሆኖ የሚቆጠር ስለሆነ በየትኛውም የፍትህ መንገድ ቅቡልነት አለው። ለምሳሌ ያህል፦ የጊዜ መጓተት የሚፈጥሩ ክስተቶች ካሉ (ለአብነት) ቀኑን ሙሉ ዝናብ ቢውል ወይም አካባቢው ረብሻ ቢሆን እነዚህ ክስተቶች የወሰዱትን ጊዜ (ሰዓት፣ ቀን፣ ወር) በቁጥር የምናሰላው ከ'Site Diary ላይ ለቅመን ስለሆነ ክስተቶቹ ባስተጓጎሉት የጊዜ መጠን ልክ በውሉ ላይ የነበረውን ግንባታ የሚጠናቀቅበትን ጊዜ ለማራዘም ያግዛል። በሌላም በኩል (ለምሳሌ) የግንባታ ግብአት ማቅረብ የአሠሪው (Client/employer) ድርሻ ቢሆን እና የግንባታ ጊዜ በዚህ የተነሳ ቢጓተትበት ሥራ ተቋራጩ የጊዜ ማራዘሚያ እና የሠራተኞች ያለሥራ የቆዩበትን ክፍያ አሠሪው እንዲከፍል ሊጠይቅበት የሚችለው በ'Site Diary ላይ በአግባቡ የተቀመጠ መዝገብ ካለ ነው። 3ኛ) ጥራትን ለመቆጣጠር ማረጋገጫ ይሆናል፦ site diary መያዝ የጥራት ቁጥጥር እርምጃዎችን እና ፍተሻዎችን ለመመዝገብ ያስችላል። ለምሳሌ፦ በዕለቱ የተሠራው ሥራ የፌሮ ብረት እና የአርማታ ሙሌት ነው ብለን ብናስብ ለእያንዳንዱ ስትራክቸር የተጠቀምንው የፌሮ ብረት አይነትና ብዛት፣ የሲሚንቶ የአሸዋ እና የጠጠር ብዛት፣ የተከናወኑ የቤተሙከራ ሥራዎችና ውጤቶቻቸው እና የተስተዋሉ ያልተሟሉ ጉዳዮችን የምንመዘግብበት ስለሆነ የግንባታ ሥራ በዲዛይኑ መሰረት ዝቅተኛውን መስፈርት አሟልቶ እየተከናወነ ስለመሆኑና ስላለመሆኑ ጥራቱን እንድንቆጣጠር፣ የሚፈለገውን ደረጃና መስፈርት የሚያሟላ መሆኑን ለማረጋገጥ፣ ተጠያቂነትን ለማስፈን እና አጠቃላይ የፕሮጀክት ጥራትን ለማሻሻል ያግዛል።
ክፍል ሁለት፡ ይዘቱ ምን መምሰል አለበትይቀጥላል .....
🔺ታምራት ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ🏗
📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን
✂️ላሜራ መቁረጫ መብሻና ማጠፊያ ማሽኖች አሉን
🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ እናበጃለን እንዲሁም እናጥፋለን
📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን እንሰራለን
📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን!
➕➕➕➕➕➕➕➕➕
📍አድራሻችን፦ ቁ.1 አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)
ቁ.2 መርካቶ
ቁ.3 ተክለሀይማኖት
📞0904040477
📞0911016833
+3
ማስታወቂያ | AdvertisingMhretiab Construction Materials Trade/ምህረትአብ ገ/እግዚአብሔር አጠቃላይ የብረት ንግድ- አቅራቢ🏗 ጥራትና ታማኝነትን የተላበሰ አገልግሎት" ከደንበኞች አብዛኛሆቻችሁ ታውቁታላችሁ
መገኛ አድራሻው ቦታ:-📍- ተክለሃይማኖት በርበሬ በረንዳ ፔፕሲ
ስልክ ቁጥር:-🔺📞+251- 944454610 🔺📞+251- 952730999 #LTZ 28 #LTZ 38 #LTZ 48 #CHS ከ ባለ 12mm ጀምሮ .... #RHS #I BEAM #U CHANNEL #H BEAM #Mesh Wire #የ ኣጥር ሽቦ #Galvanized Pipe #Angle #Aluminium Sheet #D ብረት#8 ቁጥር #ፌርሞችን በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ! ስትፈልጉ በቀጥታ ይደውሉ📞..
