Joseph Math Tutor
Ir al canal en Telegram
Hello, welcome to Joseph Math Tutor channel! https://youtu.be/D8K0MVqynVA?si=y_uFeHG7awC1oX9Y Subscribe our youtube channel On tiktok : josephmathtutor Owner: Yosef Adefris @yosef_2580
Mostrar más1 771
Suscriptores
+524 horas
+297 días
+9330 días
Archivo de publicaciones
1 775
There is last model exam next week Friday.
From Grade 9-12
Grade 9-10 old curriculum
Grade 11-12 new curriculum
70 Questions
Time Allowed= 3:30
1 775
For Joseph Math Tutorial students:
We will finished Grade 12 Next monday. there is no tutorial class tomorrow due to the holiday.
1 775
#RemedialExam
የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና ከግንቦት 25-30/2017 ዓ.ም ይሰጣል፡፡
መርሐግብሩ እንደሚያሳየው ከማዕከል የሚሰጠው ፈተና ለአምስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን፤ ግንቦት 25/2017 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሚሰጠው የባዮሎጂ ትምህርት ፈተና ይጀመራል፡፡
በኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል ምክንያት ፈተናው አርብ ግንቦት 29/2017 ዓ.ም የማይሰጥ መሆኑን መርሐግብር ያሳያል፡፡
ፈተናው ግንቦት 30/2017 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ለማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በሚሰጠው የእንግሊዝኛ ትምህርት ፈተና እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡
የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ግምገማ ከ100% ከማዕከል ብቻ እንደሚሆን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወሳል፡፡
1 775
የእናት ነገር ለመናገር ከቃላት በላይ ነው
➕➕➕➕➕➕➕➕➕➕➕➕
እናት ማለት ትርጉሙ ከባድ ነው የእናትን ትርጉም ለመተርጎም ቃላት አይገኙለትም። ከሁሉም ፍጥረታት እናት ትለያለች ከማህፀኗ ጀምሮ ሁሌም በልቧ አዝላን ትኖራለች ።
የራሷን ህይወት ሳትሰስት ለልጇ ትሰጣለች በቃ እናት እናት ......ናት ሁሌም በልብ ውስጥ ትኖራለች ::
ክብር፤ ረጅም ዕድሜ፤ ጤና ፤ደስታ፤ ሰላም ለውድ እናቶቻችን🙏🙏🙏
ያኔ በለጋው ልጅነት
ሳላውቅ ያን ክፋት ደግነት
እቅፍ አርገሽኝ በአንቀልባ
ጠዋት ማታ ሆድሽ ሲባባ
ልጄ ስትይ ተጨንቀሻል
የእናት ፍቅር ዋጋ ከፍለሻል
ማን ለእኔ ይተካሻል።😍
1 775
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ተደረገ።
የ2017 ትምህርት ዘመን ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ / የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚሰጥበት መርሃ ግብር ይፋ ተደርጓል።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ይፋ ባደረገው መርሃ ግብር ፈተናው ከሰኔ 23/2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 8/2017 ዓ/ም የሚሰጥ ይሆናል።
በወረቀት የሚፈተኑ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 21 እና 22/2017 ዓ/ም እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 29 እና 30/2017 ዓ/ም ወደሚፈተኑበት ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ይሆናል፡፡
በበይነ መረብ የሚፈተኑ ተፈታኞች ከመኖሪያ ቤታቸው በየቀኑ እየተመላለሱ በተመደቡበት መፈተኛ ማዕከል የሚፈተኑ ሲሆን ዝርዝር መርሃ ግብሩ ከላይ ተያይዟል።
የፈተናው ይዘት በተማሪው መጽሐፍ ላይ ያተኮረ በመሆኑ እያንዳንዱ ተፈታኝ በትምህርት ቤቱ የተማረበትን የተማሪ መጽሐፍ መሠረት አድርጎ ተገቢ የሆኑ አጋዥ መጽሐፍትን ለበለጠ እውቀትና መረዳት በመጠቀም እንዲዘጋጅ አገልግሎቱ ጥሪውን አስተላልፏል።
በፈተና ወቅት ለፈተና ስርቆትና ኩረጃ የሚውሉ ማንኛውንም ቁሳቁሶች መጠቀም የተከለከለ ነው ተብሏል።
መረጃው ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የተላከ ነው።
1 775
+2
ዛሬ በዱር በገደሉ ሮጠው፤ ያንን ነጫጭባ ጠላት አፈራርሰው አባረው፤ ይህቺን ሉዓላዊት አገር ለእኛ ያስረከቡ አባቶቻችን እና እናቶቻችን መታሰቢያ ታላቅ ቀን ነው።
እነዚህ የመሰሉ ጀግኖች የነበሩባት ናት ኢትዮጵያ !!!
እነርሱ ለእኛ ይህን ጀግንነት አስረከቡ እኛስ ለቀጣዩ ትውልድ ምን እናስረክብ ይሆን?!?!
ሀ. ዘረኝነትን
ለ. ዲቪ እየሞሉ አገር ጥሎ መጥፋትን
ሐ. ምን ሳናደርግላት ኢትዮጵያ ደሃ ናት ብሎ ማውራትን
መ. በሃይማኖት እየተከራከሩ ስንት አመት ተከብረው የቆዩ እምነቶችን ማሰደብ እና መስደብ
ሠ. አለመተሳሰብ፤ አለመዋደድ፤አለመከባበርን
መልሳችን ከእነዚህ አያልፍም ምክንያቱም ሌላ ምንም በጎ ነገር ስለሌለን!!!!!!
ወደ ራሳችን እንመለስ።።።።።።
ክብር ለጀግኖች አባቶች እና እናቶቻችን ሁሌም እንዘክራችኋለን፤ እናከብራችኋለን🙏🙏🙏🙏
1 775
ዛሬ በተሰማሩበት ሞያ ፤ በተሰማሩበት ሁሉ በቅንነት ፣ በታማኝነት ህዝባቸውን እና ማህረሰባቸውን ለማገዝ ሌት ተቀን ፀሀዩ ፣ ብርዱ ፣ ዝናቡ ሳይበግራቸው ለሚተጉ ቀናቸው ነው።
መልካም የላብአደሮች ቀን!
1 775
There is a Quiz #6 from grade 9 unit 5 (Statistics and probability) old curriculum for grade 12 students (revision) at 2:00 LT (night)
1 775
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳዔ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
" ትንሳዔከ ለእለ አመነ ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ"
(ትንሳዔህን ለምናምን ለእኛ ብርሃንን ላክልን ወደ እኛ)
መልካም በዓል
#JOSEPH_MATH_TUTORIAL
1 775
+1
#MoE
" ከ2019 ጀምሮ 3ኛ ዓመት የጨረሱ ተማሪዎች 4ኛ አመት ከመግባታቸው በፊት የ1 ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል " - ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)
በዩኒቨርሲቲ የሚማሩ 3ኛ ዓመት የጨረሱ ተማሪዎች 4ኛ ዓመት ሳይገቡ በፊት የአንድ ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የተጀመረው እንቅስቃሴ ከ2019 ዓ/ም ጀምሮ ተግባር ላይ እንደሚውል የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ጠቁመዋል።
ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ፤ " በሚቀጥለው ዓመት ላይደርስልን ይችላል ግን ህጋዊ ስርዓቱን በሙሉ ጨርሰን በ2019 ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚማሩ 3ኛ ዓመት የጨረሱ ተማሪዎች ከ2019 ጀምሮ 4ኛ አመት ከመግባታቸው በፊት የ1 ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ይድረጋል " ብለዋል።
" ከዚህ በፊት የነበረ ነው አዲስ አይደለም በጃንሆይ ጊዜ (በአጼ ኃይለስላሴ ጊዜ ማለታቸው ነው) የነበረ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
" ሁለት ጥቅም አለው ብለን ነው ይሄን የምናደርገው አንደኛ ልጆቹ ዝም ብሎ የቀለም ትምህርት ብቻ ተምረው ሳይሆን ተግባራዊ የሆነ ትምህርትም ለአንድ ዓመት ሄደው የሚሰሩበት ከማህበረሰቡ ጋር የሚተዋወቁበት ነው። ሁለተኛ የአስተማሪዎች እጥረትም ስላለ ልጆችን ወደ አስተማሪነት ለአንድ አመት ቢሆንም ለማስገባት ነው " ብለዋል።
¡Ya disponible! Investigación de Telegram 2025 — los principales insights del año 
