es
Feedback
Joseph Math Tutor

Joseph Math Tutor

Ir al canal en Telegram

Hello, welcome to Joseph Math Tutor channel! https://youtu.be/D8K0MVqynVA?si=y_uFeHG7awC1oX9Y Subscribe our youtube channel On tiktok : josephmathtutor Owner: Yosef Adefris @yosef_2580

Mostrar más
1 854
Suscriptores
Sin datos24 horas
+57 días
+2130 días
Archivo de publicaciones
Mathematics AASTU/ASTU Entrance Exam Answer with explanation

+4
#AASTU_and_ASTU These are demo exams from the last 3 years. Please try to prepare like your matric exams you did before. 👇 Join us 👇 @Joseph_maths_tutorial

የተሰሩት መልሶች ትክክል አይደሉም

የMathsun መልስ ልስራላችሁ?

Repost from Joseph Math Tutor
+2
👉 Maths ASTU/AASTU Online Entrance Exam. Le Adis Gebi temariwoch🧑‍💻 #Share @Joseph_maths_tutorial

📢 ASTU ( Adama Science and Technology University ) 📚 አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ ከአዲስአበባ በ 100km ርቀት የሚገኝ ሲሆን ኢትዮጵያ ካሏት ሁለት የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ አንዱ ነው። 📚 የScience እና Technology  ዩኒቨርሲቲ እንደመሆኑ የሚሰጣቸው Departmentoch ውስን ናቸው ማለትም Engineering እና Applied Science ፊልዶች ብቻ ናቸው ። 🔎 በ Engineering ስር 3 Collgeoችን  1-College of Electrical 2-College of Mechanical 3-College of Civil and Architecture 📚 በእነዚህ Collegoች ስርም ፦ 1. College of Electrical computing ስር 📌-Software engineering 📌-Computer science and engineering(CSE) 📌 -Power and Control 📌 -Communication and Electronics 2.በCollege of Mechanical chemical and material ስር 📌 - Mechanical engineering 📌 -Chemical engineering 📌 -Material Science and Engineering 3.በCollege of Civil and Architecture ስር 📌 -Civil engineering 📌 -Architectural engineering 📌 -Water engineering      📚 በApplied Science ውስጥ ፦ 📌 -Applied Mathematics 📌 -Applied Chemistry 📌 -Applied Physics 📌 -Applied Geology 📌 -Industrial chemistry 📌 - Pharmacy 📚 ወደ ዩኒቨርስቲው ለመቀላቀል ፈተና ያለው ሲሆን የሚቀበላቸው ተማሪዎች ውስን ናቸው ተማሪ የምንቀበለው በ Laboratoryኣችን ልክ ነው ብለው ስለሚያምኑ ! በጠቅላላ ግቢው ውስጥ ከ Fresh እስከ Masters 7000 ተማሪዎች 2000 ሰራተኞች ይገኛሉ ። 📚 ተማሪዎች ትንሽ ከመሆናቸው አንፃር ምግብ ከየትኛውም ግቢ የተሻለ ነው ።  📚 library 1-Central Library 2-Applied Library 3-Liberal arts library 4-Post graduate library 5-Females library 📚 እንዲሁም በየdepartmentቶች  የየራሳቸው library ያላቸው ሲሆን የሴቶቹ ለብቻቸው የሚጠቀሙበትም አላቸው ።ሌላው ነገር libraryዎቹ በውስጣቸው በጣም ፈጣን WiFi እና Computer አላቸው ። ግቢው ለሚጠቀምበት በጣም ብዙ laboratoryዎች አሉ ። 📚 ግቢው ውስጥ Anfi የሚባል ቦታ አለ እዛ ላይ በ cinema standard led screen አለ እንዲሁም ሶስት ቦታዎች ላይ አነስተኛ screenoch አሉ ። ለሴቶች ትንሽ ሻል ያለ አገልግሎት ይሰጣል በዶርሚተሪ በlibraryም በብዙ ነገር ይጠቀማሉ ! 📚የራሱ ውሀ ማጣሪያ ያለው ሲሆን ፤ ብዙም የውሀ ችግር የለም መብራት አይጠፋም ከጠፋም በ 5 ደቂቃ ውስጥ የሚነሳ automatic generator አለ ። Dormitory አሪፍ  የሚባል ነው ።  የግቢ መግቢያ ሰዓት 3:00 ከሌሎች የተሻለ ነው ። ሌላው በፍፁም ሰው የማይተናኮሉ ለማዳ ለመባል የሚቀርቡ ጅቦች አሉ ፤ 🔎 በጣም ጠቃሚ ነገር 🔎 📌 ከሌሎች ዩኒቨርስቲዎች በተለየ ነው ት/ት የሚሰጠው ለምሳሌ Comon course የሚባል ነገር የለም engineering የሚገባ ቀጥታ pre engineering ይማራል  Appliedም እንደዛው ነው ። Gpa ከ 3.5 በላይ ካለ እና ሌላ ፊልድ ደርቦ መመረቅ ለሚፈልግም dual degree ይሰጣል ሁለት degree ማለት ነው ። 

✅‎የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ: 2025 ➡️የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች በሚሰጡት የአገልግሎት ጥራት በየአመቱ ደረጀ የሚቀመጥላቸው ሲሆን ከዚህ በታች እንደሚከተለው ተቀምጦላችኋል ። ይህ መረጃ ቀጣይ University ለምትመርጡ ተማሪዎች ያግዛችኋል 🙏 1 Addis Ababa University 2 University of Gondar 3 Bahir Dar University 4 Jimma University 5 Mekelle University 6 Hawassa University 7 Haramaya University 8 Adama Science and Technology University 9 Arba Minch University 10 Jigjiga University 11 Addis Ababa Science and Technology University 12 Ambo University 13 Dilla University 14 Unity University 15 Debre Berhan University 16 Wollo University 17 Debre Markos University 18 Wolaita Sodo University 19 Madda Walabu University 20 Worabe University 21 Wachamo University 22 Debre Tabor University 23 Wolkite University 24 Ethiopian Civil Service University 25 Arsi University 26 Samara University 27 Assosa University 28 Dire Dawa University 29 Wollega University 30 Mattu University 31 Mizan-Tepi University 32 Kotebe Education University 33 Adigrat University 34 Woldia University 35 Oromia State University 36 Bule Hora University 37 Aksum University 38 Bonga University 39 Rift Valley University 40 Oda Bultum University 41 Raya University 42 Injibara University 43 Selale University 44 Debark University 45 Kebri Dehar University 46 Gambella University 47 Mekdela Amba University 48 Dembi Dolo University 49 Jinka University 50 Borena University 51 Ethiopian Police University ‎  🌏‎Source: UNIRANKS® — Top-Ranked Universities in Ethiopia (2025)

#JustForInfo (For new fresh students) This is a comment from one of the AAU students. Last year, the cutoff CGPA for Software
#JustForInfo (For new fresh students) This is a comment from one of the AAU students. Last year, the cutoff CGPA for Software Engineering was around 3.95 for male students. Just letting you know so you can make an informed decision. #Share

መመዝገቢያ Link http://admission.aau.edu.et/login

አዲስአበባ ዩኒቨርስቲ (AAU) አዲስ የቅድመ ምረቃ ፕሮግራም የማመልከቻ (Registration) ጊዜ ነገ ያበቃል።

#Update አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአዲስ ገቢ የቅድመ ምረቃ አመልካቾች የ2025/26 ትምህርት ዘመን የማመልከቻ እና የምዝገባ ጊዜ ማስተካከያ፦ ⏩ አዲስ የቅድመ ምረቃ ፕሮግራም የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦ መስከረም 09/2018 ዓ.ም ⏩ የ Presidential Scholarship Program የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦ መስከረም 09/2018 ዓ.ም ⏩ የመምህራን ትምህርት ነጻ የትምህርት ዕድል ፕሮግራም የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦ መስከረም 09/2018 ዓ.ም ⏩ የቅድመ ምረቃ ቅበላ መግቢያ ፈተና (UAT) የፈተና ማዕከላት የሚገለፁት፦ መስከረም 10/2018 ዓ.ም ⏩ የቅድመ ምረቃ ቅበላ መግቢያ ፈተና (UAT) የሚሰጥበት፦ መስከረም 12-14/2018 ዓ.ም ⏩ የቅድመ ምረቃ ቅበላ መግቢያ ፈተና (UAT) ውጤት የሚገለፅበት፦ መስከረም 16/2018 ዓ.ም ⏩ የቅድመ ምረቃ ፕሮግራም የመደበኛ እና የማታ ተማሪዎች የምደባ ውጤት የሚለቀቅበት፦ መስከረም 19/2018 ዓ.ም ⏩ የአዲስ ገቢ የቅድመ ምረቃ ፕሮግራም መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ፦ መስከረም 22-23/2018 ዓ.ም ⏩ የአዲስ ገቢ የቅድመ ምረቃ ፕሮግራም የማታ ተማሪዎች ምዝገባ፦ መስከረም 24/2018 ዓ.ም ⏩ የአዲስ ገቢ ተማሪዎች ትምህርት የሚጀምርበት፦ መስከረም 26/2018 ዓ.ም

#AASTU #ASTU የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ትምህርት ዘመን በመጀመሪያ ዲግሪ መርሐግብር ተማሪዎችን ተቀብለው ለማስተማር ዝግጅ
+1
#AASTU #ASTU የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ትምህርት ዘመን በመጀመሪያ ዲግሪ መርሐግብር ተማሪዎችን ተቀብለው ለማስተማር ዝግጅት አጠናቀዋል። ሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች በጋራ ባዘጋጁት የቅበላ ፈተና ተማሪዎችን አወዳድረው እንደሚቀበሉ ገልፀዋል፡፡ የመግቢያ ፈተናው ከሂሳብ፣ እንግሊዘኛ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ እና ባዮሎጂ የትምህርት ዓይነቶች በእኩል የተውጣጡ ጥያቄዎችን የያዘ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡ በኦንላይን የመመዝገቢያ አድራሻ፣ የምዝገባ ቀን፣ ፈተና የሚሰጥበት ቀን፣ የመፈተኛ ጣቢያዎች እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች በቀጣይ ቀናት ይገለጻል ተብሏል፡፡ (በሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጡ የመጀመሪያ ዲግሪ መርሐግብር የትምህርት መስኮች ዝርዝር ከላይ ተያይዟል፡፡)

For ASTU 1st and 2nd year students
For ASTU 1st and 2nd year students

#በEntrance Exam ዉጤት ከዚህ ልጅ በላይ ደስተኛ ይኖራል ብላችሁ ታስባላችሁ???
#በEntrance Exam ዉጤት ከዚህ ልጅ በላይ ደስተኛ ይኖራል ብላችሁ ታስባላችሁ???

" የሁለተኛው ዙር የፊዚክስ ፈተና ውጤት ችግር አለበት " - ተማሪዎች እና ወላጆቻቸው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዛሬ ይፋ ሆኖ ተማሪዎች ውጤታቸውን ሲያዩ ውለዋል። ነገር ግን ከተፈጥሮ ሳይን
" የሁለተኛው ዙር የፊዚክስ ፈተና ውጤት ችግር አለበት " - ተማሪዎች እና ወላጆቻቸው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዛሬ ይፋ ሆኖ ተማሪዎች ውጤታቸውን ሲያዩ ውለዋል። ነገር ግን ከተፈጥሮ ሳይንስ የሁለተኛው ዙር የፊዚክስ ፈተና ጋር በተያያዘ ችግር እንዳለ ተማሪዎቹ እና ወላጆቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። " ከ60 የታረመው ውጤት ወደ 100 ስኬል ተቀይሮ አልተሰራም። እንዳለ ነው የተቀመጠው። በዚህም የሁለተኛ ዙር ተፈታኞች የፊዚክስ ትምህርት ፈተና ውጤት ዝቅተኛ ሆኖ ተመዝግቧል። የበርካታ ተማሪዎች ውጤት ወርዷል። የሚመለከተው አካል ይይልን፣ ይስተካከል " ሲሉ ጠይቀዋል። ተማሪዎቹ ስላነሱት ጉዳይ የሚመለከታቸው የትምህርት ተቋማትን  የጠየቅን ሲሆን፤ ሁለት የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተማሪዎቹ ጥያቄ በነሱ ተፈታኞች ላይ ያጋጠመ እንደሆም አመልክተዋል። የፊዚክስ ፈተና ጉዳይን በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ጥያቄውን ያቀረበ ሲሆን ምላሽ ሲሰጥ እናቀርባለን።

አሁን በደንብ እየሰራ ነው Check it!