cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

መንግስቱ ዘገየ አባተ፤ በማናቸውም ፍርድ ቤት ጠበቃና የህግ አማካሪ Mengistu Zegeye Law Office

@መንግስቱ ዘገየ አባተ ፣ በማናቸውም የፌዴራልና የክልል ፍርድ ቤቶች ጠበቃና የህግ አማካሪ ፣ @ዋና ቢሮ፣ ደሴ ከተማ ፤ መናፈሻ ሰፈር፤ ከደቡብ ወሎ መስተዳድር ዞን ህንጻ አጠገብ ከሚገኘው የደቡብ ወሎ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዲሱ ህንጻ፤ፊት ለፊት። @ጠበቃ መንግስቱ ዘገየን ማግኘት የምትፈልጉ የስልክ ቁጥሩ፣ 09-20-18-49-27 ወይም 09-14-71-34-31 @ ቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ።

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
3 728
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
-1430 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ሰ/መ/ቁጥር 206083 ግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ/ም የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 1809 ተፈጻሚ ሊሆን የሚችለው እንደውሉ ከመፈጸሙ በፊት ነው፡፡ በከፊል ወይም በሙሉ በውሉ መሰረት ከተፈጸመ በኋላ ውሉ የማይረጋበትን ምክንያት በመጥቀስ መቃወሚያ አድረጎ ማቅረብ ተቀባይነት ሊያገኝ አይገባም፡፡ በፍ/ሕ/ቁጥር 1808(1) ከተዋዋዮቹ አንዱ ፍቃዱን በመሳሳት፣ በተፈፀመበት የተንኮል ወይም የማስገደድ ተግባር ወይም ችሎታ ሳይኖረው የሰጠ እንደሆነ ይህን ምክንያት በመጥቀስ እና በማስረጃ በማረጋገጥ ውሉ ፈራሽ እንዲደረግለት ዳኝነት የሚጠይቅበትን አግባብ የሚያመላክት ነው፡፡ በአንፃሩ በንዑስ አንቀፅ 2 ስር የተገለፀው የውል ጉዳዩ ህገ ወጥ ወይም ኢሞራላዊ የሆነ ወይም በሕጉ የተገለፀውን የአቀራረፅ ስርዓት ባለመከተሉ ከመጀመረያውም ሕግ እውቅና የማይሰጠው እንዳልነበረ የሚቆጠር ቢሆንም ይመለከተኛል ባይ 3ኛ ወገን ወይም ተዋዋዮች ውሉ ዋጋ አልባ እንዲባል ዳኝነት የሚጠይቁበትን ሁኔታ የሚያመላክት ነው፡፡ ነገር ግን በዚህ አግባብ ውሉ ፈራሽ ወይም ዋጋ አልባ ነው በማለት እንዲወሰን ቀድሞ ዳኝነት ያልጠየቀበት ተዋዋይ በሌላኛው ተዋዋይ እንደ ውሉ እንዲፈፀምለት የጠየቀው እንደሆነ በፍ/ሕ/ቁጥር 1809 መሰረት ውሉ የማይረጋበትን ምክንያት በመጥቀስ በማንኛውም ጊዜ መቃወሚያ ሊያደረገው ይችላል፡፡ ይህ ድንጋጌ ዋጋ አልባ ወይም ፈራሽ ውሎችን በማለት ለይቶ መመዘኛ የማያስቀምጥ በመሆኑ ለሁለቱም ሁኔታዎች ተግባራዊ የሚሆን ድንጋጌ ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ውሉ የማይረጋበትን ምክንያት በመጥቀስ መቃወሚያ አድረጎ ማንሳት የሚችለው በውሉ መሰረት መፈጸም ያልተጀመረ ከሆነ ብቻ ነው? ወይስ በሙሉ ወይም በከፊል ውሉ ከተፈጸመ ውሉ የማይረጋበትን ምክንያት መቃወሚያ አድረጎ ማንሳት ይችላል ወይስ አይችልም? የሚሉት ነጥቦች በትኩረት ሊመረመሩ ይገባል፡፡ በፍ/ህ/ቁጥር 1809 አገላለጽ ውሉ የማይረጋበት ምክንያት እያለ በውሉ መሰረት በሙሉ ወይም በከፊል ከተፈጸመ በተግባር ውሉ ተቀባይነት እንዳገኘ አመላካች ነው፡፡ አንድ ተዋዋይ በተግባር ተቀብሎ በውሉ መሰረት ተፈጽሞ እያለ ክስ ስለቀረበበት ብቻ ውሉ የማይረጋበትን ምክንያት በመጥቀስ የሚያቀርበው መቃወሚያ በተግባር የተቀበለውን የውል ውጤት የሚቃረን በመሆኑ መቃወሚያው ተቀባይነት ሊያገኝ አይገባም፡፡ ይህ ማለት ግን ውሉ አይረጋም የሚል ወገን ክስ አቅርቦ ውሉን ማስፈረስ አይችልም ማለት ባለመሆኑ በውሉ መሰረት በከፊል ወይም በሙሉ እንደውሉ ከተፈጸመ በህጉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ክስ አቅርቦ ውሉን እስካላስፈረሰ ድረስ በውሉ መሰረት ሊፈጸም አይገባም በማለት የሚያነሳው መቃወሚያ ተቀባይነት የለውም፡፡ በመሆኑም የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 1809 ተፈጻሚ ሊሆን የሚችለው እንደውሉ ከመፈጸሙ በፊት ነው፡፡ በከፊል ወይም በሙሉ በውሉ መሰረት ከተፈጸመ በኋላ ውሉ የማይረጋበትን ምክንያት በመጥቀስ መቃወሚያ አድረጎ ማቅረብ ተቀባይነት ሊያገኝ አይገባም፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ቀደም ሲል በሰበር መዝገብ ቁጥር2 12820 እና ሌሎች መዝገቦች የህግ ትርጉም የተሰጠበት ጉዳይ ነው፡፡ Khalid kebede
Mostrar todo...
Mostrar todo...
Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

ሰ/መ/ቁ 226490 ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ/ም የወራሽነት ማስረጃ ከፍርድ ቤት የተሰጠው ሰው የመብት ጥያቄ ሲያቀርብ ሌላኛው ወራሽ የመውረስ መብት እንደሌለው ክርክር ለማቅረብ በቅድሚያ የወራሽነት ማስረጃውን ማሰረዝ አስፈላጊ አይደለም። ስለሆነም የወራሽነት ማስረጃ የተሰጠው ሰው የውርስ ድርሻውን ለማግኘት ባቀረበው ክስ ላይ የሟች ልጅ አይደለም ብሎ ለመቃወም በቅድሚያ የወራሽነት ማስረጃው እንዲሰረዝ አቤቱታ አቅርቦ ማሰረዝ አይጠበቅበትም። ወራሽነትን በማረጋግጥ የሚሰጥ የወራሽነት ማስረጃ በአመልካች ብቻ የቀረበውን የአንድ ወገን ማስረጃ በመቀበል የሚሰጥ ማስረጃ (Declaratory judgment) ለመክሰስ መብትና ጥቅም ያለው መሆኑን አሳይቶ የድርሻ ክፍፍል ጥያቄ ለማቅረብ በማስረጃነት የሚቀርብ፤ በማንኛውም ተዓማኒነት እና ክብደት ባለው ማስረጃ ሊስተባበል የሚችል ማስረጃ በመሆኑ ማስረጃው በተሰጠበት መዝገብ ላይ መብት ወይንም ጥቅሜን ይነካል በማለት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሠረት የፍርድ መቃወሚያ የሚቀርብበት አይደለም። @habeshaadvocatesllp t.me/ethiolawtips

Mostrar todo...
ጀግናው ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ | ጀግና በመከራ ቀን ይወለዳል #shorts

በዚህ ክፉ ወቅት በአላማው ፀንቶ ልጆቹን ያፀና አባት ። #shorts ------------ website ---------------

https://gollemtimes.com/

------------- App ---------------------

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.gollemtimes.riddle&hl=en&gl=US

----------------- social --------------- Twitter :

https://twitter.com/GollemTube

facebook :

https://www.facebook.com/gollem.tube.3

Tiktok :

https://www.tiktok.com/@gollemtimes

Mostrar todo...
አሥራት ሚዲያ Asrat Media ®

በኦርቶዶክሳዊ የጠበቆች ቡድን አማካኝነት የፌደራል ፖሊስ ዛሬ ችሎት ባቀረባቸው 12 ኦርቶዶክሳውያን ተጠርጣሪዎች ላይ ሰባቱ በዋስ እንዲለቀቁ ተደረገ። የፌደራል ፖሊስ 'በሽብር ተግባር እና ሕገ መንግሥቱን በኃይል ለመናድ ኢ-መደበኛ አደረጃጀት ፈጥረው ሲንቀሳቀሱ ይዣቸዋለሁ በሚል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናንን ዛሬ የካቲት 6 ቀን 2015 ዓ.ም ለችሎት ማቅረቡ ይታወሳል። በወቅታዊው የቤተ ክርስቲያን ችግር ምክንያት በተቋቋመው  የጠበቆች ቡድን ዛሬ በተሰየመው አንድ ችሎት ብቻ 10 ጠበቆች መሟገታቸው ተገልጿል። በእነዚህ የጠበቆች ቡድን ክርክር በመደረጉም ሰባት ተጠርጣሪዎች በዋስ እንዲለቀቁ ተደርጎል። እንዲሁም መ/ር ምሕረተአብ አሰፋና ኪሩቤል አሰፋ ላይ የ8 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ሊሰጥ መቻሉን ተገልጿል። በተመሳሳይ ክስ (የጊዜ ቀጠሮ መጠየቂያ)  በሌላ መዝገብ  ፌቨን ዘሪሁን እና ብሩክታዊት ነብዩ እንዲሁም ፋሲል አግደው ላይ በአጠቃላይ  5 ሰዎች ላይ የ8 ቀን ጊዜ ቀጠሮ  መፈቀዱን ተነግሯል። እንዲህ ዓይነት ትንኮሳዎች እየጨመሩ ሊመጡ ስለሚችል የሕግ ባለሙያዎች ሙያዊ አሥራታችሁን ለቤተ ክርስቲያን  ታበረክቱ ዘንድ ጥሪ ቀርቧል ሲል የዘገበው አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ነው። የካቲት 7 ቀን 2015 ዓ.ም Telegram:-

https://t.me/asrat_news

Facebook:-

https://www.facebook.com/AsratNews

♠የሰበር መዝ/ቁ 212950 ``````````ያልታተመ`````````` ♦በወንጀል የማስረጃ ምዘና መርህ የተከሳሽ ሀላፊነት♦ ~~~ በወንጀል የማስረጃ ምዘና መርህ መሰረት ከተከሳሽ የሚጠበቀው የማስረዳት ደረጃ እንደ ዐቃቢ ህግ ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በፀዳ መልኩ ማስተባበል ወይም በቂ እና አሳማኝ በሆነ መልኩ ማስረዳት ሳይሆን በቀረቡት የዐቃቢ ህግ ማስረጃዎች ቃል እና በወንጀሉ መፈፀም ላይ "ጥርጣሬ መፍጠር" ብቻ ነው። share 👇👇 t.me/ethiolawtips
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ከኹለት ቀናት በፊት በቀድሞ ስማቸው አባ ንዋየ ሥላሴ ይባሉ የነበሩት ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ በመሄድ የይቅርታ ደብዳቤያቸውንና በሕገ ወጥ መንገድ የተሰጣቸውን አስኬማና አልባሳት መመለሳቸው ይታወቃል። ይህን በተመለከተ ሾሟቸው የነበረው አካል የሚከተለውን መግለጫ አውጥቶ ነበር። በመግለጫውም ፦ « ጥር 14፣ 2015 በመንፈስ ቅዱስ ጥሪ ኤጵስ ቆጶስ ሆኖ ከተሾሙት ሁለት ይሁዳዎች ተገኝቷል። ከሰላሳ ድናር ድርድር ማለፍ ያልቻሉ፣ የመንፈስ ቅዱስን ፀጋ መሸከም ያልቻሉ፣ እንድሁም ለስለላ የተላኩ የዘመናችን ይሁዳዎች ተፈጥረዋል። ለቅዱስ ሲኖዶሳችን እየደረሰን ያለው መረጃ መሰረት አባ ንዋየ ሥላሴ በንዋይ ፍቅር እና እኛን ለመሰለል ከሀገረ እስራዔል ድረስ መጥቶ ምድራዊ ስራ እየሰሩ፣ ከመንፈስ ቅዱስ የተሰጣቸውን ስልጣን ክዶ ወደ በህገወጥ ሰዎች በተሞላው የድሮው ሲኖዶስ ሲሄዱ አይተናል። አዎ ከሀዲ ይሁዳዎችን አይተናል። ይሁዳ የክርስቶን ልደት በደስታ ብያይም የትንሳዔውን ብርሀን ለማየት አልታደለምና እጁን ወደ ወጭቱ ሰዶ መስረቁም ግደታ ነበር። ተፈጥሮው ክህደትና ስርቆት ነበርና» ይላል። ይኸው አካል ዛሬ ደግሞ በሰበር ዜናው የግለሰቡን መመለስ በተመለከተ ባወጣው መግለጫ « እጁግ የተከበሩ እና ሊቁ አባ ሀብተማሪያም የመንፈስ ቅዱስ ተልእኮዓቸውን ጨርሶ በሰላም ወደ ቅዱስ ሲኖዶሱ ተመልሷል።»  ብሏል። ትናንት "እኛን ለመሰለል ከእስራኤል ድረስ መጡ“ ዛሬ ተልዕኳቸውን ጨርሰው ወደ እኛ ተመለሱ" የሚል የልጅ ጨዋታ ከመጫዎት ይልቅ ማን አፍኖ፣ አስፈራርቶና አስገድዶ እንደመለሳቸው ነገ ታሪክ ያወጣዋል። እስከዚያው በጊዜያዊ መግለጫዎች ተዝናኑ። ይልቅስ ሌሎቹንም የታፈኑት ይለቀቁና ወደመረጡት ይሂዱ ‼ አዳዲስ መረጃ ይከታተሉ! https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw
Mostrar todo...
፨ሰ.መ.ቁ. 161448 [ቅፅ 25] ፨ ደረቅ ቼክ እንደ ወንጀል እና ደረቅ ቼክ እንደ መተማመኛ ሰነድ ቼክ በሚወጣበት ወይም ለክፍያ በሚቀርብበት ጊዜ አውጭው የሚያዝበት ገንዘብ ሳይኖረው ቼክ ያወጣ ከሆነ ወንጀል ስለመሆኑ የወ/ህ/ቁ. 693 ይደነግጋል። ይሁን እንጅ የፌ/ጠ/ፍ/ ቤት በቅፅ 25 የመ/ቁ. 161448 ከዚህ ቀደም በመ/ቁ. 67947 የሰጠውን የህግ ትርጉም በማሻሻል በወንጀል የማያስጠይቅበትን አንድ ልዩ ሁኔታ ከነመስፈርቱ በግልፅ አስቀምጧል። ፨ ደረቅ ቼክ በወንጀል የመያስጠይቅበት ልዩ ሁኔታ: ቼኩ በተከሳሽ እና የግል ተበዳይ መካከል ባለ የንግድ ግንኙነት ለመተማመኛ (በመያዥያነት)የተሰጠ ከሆነ። ፨መሟላት የሚገባው መስፈርት: የዋስትና/መያዥያ/ ዉሉ በንግድ ህጉ (አንቀፅ 952)  እና በፍ/ህግ (አንቀፅ 2864-2866) በተቀመጠው መስፈርት ይዘት ያካተተ በፅሁፍ ውል የተፈፀመ ስለመሆኑ በራሱ በዉሉ ሰነድ ሲረጋገጥ ነው። ይህም ማለት የውል ሰነዱ ባልቀረበበት ሁኔታ በሰው ምስክር ማረጋገጥ አይቻልም።
Mostrar todo...
የሰበር ችሎት በሠበር አጣሪ ችሎት የተያዘውን ጭብጥ ቀይሮ ውሳኔ መስጠት ይችላል?                                                                                                                                                                   ዳኞች ገንዘብ ተቀብለዋል በሚል ከችሎት ሊነሱ የሚችሉበት አግባብ #danielfikadu የሰ/መ/ቁጥር 223024 /ያልታተመ/ ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ/ም በአዋጅ ቁጥር1234/2013 የሠበር ችሎቱ የግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተጠናቆ መዝገቡን ሲመረምር በሠበር አጣሪ ችሎት የተያዘውን ጭብጥ ቀይሮ ውሳኔ መስጠት የሚችል ስለመሆን አለመሆኑ የተመለከተ ነገር የለም፡፡ በቀጥታ ክስ የክርክር ሂደት ፍርድ ቤቱ የያዛቸውን ጭብጦች ለውጦ ውሳኔ መስጠት እንደሚችል በፍ/ሥ/ሥ/ሕጉ በአንቀጽ 251እና342 ላይ ተመልክቷል፡፡ ይህ ድንጋጌ በተመሳሳይ መልኩ(analogy) በሠበር ክርክር ወቅትም ተፈጻሚ ሊሆን ይገባል፡፡ እንደዚሁም የፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 328(2)(3) አቀራረጽ የይግባኝ አቤቱታ አቅራቢው ባቀረበው የቅሬታ ዝርዝር ፍርድ ቤቱ በዋናነት መወሰን እንዳለበት የሚያዝ ሲሆን በይግባኝ አቤቱታው ከተመለከተው ዝርዝር ክርክር ወጥቶ ሊወስን የሚችለው በንዑስ ቁጥር ሦስት እንደተመለከተው ፍርድ ቤቱ ጭብጥ አድርጎ በያዘው እና ግራቀኙ እንዲከራከሩበት እድል በተሠጠበት ጉዳይ ላይ ብቻ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ በዚህም መሰረት ተጠሪዎች አመልካች ባቀረቡት የሠበር አቤቱታ ክርክር እና ፍርድ ቤቱ የያዘው ጭብጥ ከመጥሪያ ጋር የተላከላቸውም ፍርድ ቤቱ መሠረት አድርጎ ሊወስንበት የሚችለው በሠበር አቤቱታው በተመለከተው ወይም/እና የሠበር አጣሪ ችሎት በያዘው ጭብጥ ላይ ሊሆን ስለሚችል ተጠሪዎች የመደመጥ መብታቸው በተሟላ ሁኔታ የሚከበረው ሁሉቱም ሲደርሳቸው መለስ ሲሰጡ መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ነው፡፡ በተጨማሪም የሠበር ችሎት አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በሠበር አጣሪ ችሎት የተያዘውን ጭብጥ መቀየር እንደሚችል፤ ተጠሪም መልስ ማቅረብ ያለበት ያስቀርባል በተባለው ጭብጥ ላይ ብቻ ሳይሆን የሠበር ቅሬታውን መሰረት በማድረግ መሆን እንዳለበት እና ተጠሪ በጭብጥነት በተያዘው ነጥብ ላይ ብቻ መልስ የሚሰጥ ከሆነ በሌሎች በሠበር ቅሬታ ላይ በተመለከቱ ነገሮች መልስ ማቅረብ እንዳልፈለገ ተቆጥሮ በተቀየረው ጭብጥ መሰረት ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሠበር መዝገብ ቁጥር 169554 እና በሌሎች መዝገቦች የህግ ትርጉም የተሰጠበት ጉዳይ ነው፡፡ ሌላው ተጠሪዎች በችሎቱ የተሰየሙት ዳኞች ከችሎቱ ሊነሱ ይገባል የሚሉበት ምክንያት ማስረጃ የመመዘን ስልጣን ሳይኖራችሁ የአመልካቾችን ማስረጃ ብቻ በመመዘን የፍሬ ነገር ድምዳሜ ቀይራችኋል የሚል ነው፡፡ እንደሚታወቀው ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 80/3/ሀ እና በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 10 የተሰጠው የዳኝነት ስልጣን መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመባቸውን የመጨረሻ ውሳኔዎች ማረም ነው፡፡ በዚህ ሥልጣኑ ተከራካሪ ወገኖች ማስረጃ ለመቀበል፣ ለመስማትና ለመመዘን ሥልጣን ለተሰጣቸዉ የስር ፍርድ ቤቶች ያቀረቡትን ማስረጃዎች የመመዘን ጉዳይ ዉስጥ በመግባት ማስረጃዎችን በመመርመርና በመመዘን አከራካሪ የሆነዉ የፍሬ ነገር ጭብጥ መኖር አለመኖሩን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥልጣን ሰበር ችሎቱ አልተሰጠዉም ማለት ነው፡፡ ሆኖም የማስረጃ አቀራረብን፣ አግባብነትን፣ ተቀባይነትን እና ማስረጃ አቅርቦ አንድን ፍሬ ነገር የማስረዳት ሸክም መርህ (Production, relevancy, admissibility and burden of proof of evidence)እንዲሁም የማስረጃ ምዘናን ወይም የማስረዳት ደረጃን (standard of proof or weight of evidence) የሚመለከቱ መሰረታዊ መርሆዎች ተጥሶ የተሰጠ የመጨረሻ ዉሳኔ ሲኖር መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለሚሆን በሰበር ሰሚ ችሎት የሚታረም ይሆናል፡፡ ተጠሪዎች ውሳኔው የተሰጠው አመልካቾች በጉዳይ አስፈጻሚ በኩል ለዳኞች ገንዘብ በመሰጠቱ ነው የሚል እምነት አለን በሚል ያቀረቡትን ምክንያት ስንመለከት እንደሚታወቀው በአንድ ክርክር ላይ ተሳታፊ የሚሆኑት ሁለት ተከራካሪ ወገኖች ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት አንደኛው ተከራካሪ ወገን ይፈረድለታል ሌላኛው ተከራካሪ ወገን ደግሞ ይፈረድበታል፡፡ ይህ የፍርድ ቤት የስራ ባህሪ ነው፡፡ ፍርድ ቤትም አንዱን ወገን የክርክሩ ረቺ በማድረግ ለመወሰን የግራ ቀኝ ተከራካሪ ወገኖችን ክርክር ከሕግ እናከማስረጃ አንጻር ብቻ መርምሮ ውሳኔ የመስጠት ኃላፊነት ያለበት መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ነገር ግን አንድ ዳኛ አንድን ወገን ተጠቃሚ የሚያደርግ ውሳኔ የሰጠው ከባለጉዳዩ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ገንዘብ በመቀበል ከሆነ ዳኛው ይህንን ማድረጉን የሚያሳይ ማስረጃ ሊቀርብበት ይገባል፡፡ ዳኛው ድርጊቱን መፈጸሙ ከተረጋገጠም በሕግ ተጠያቂ ሊሆን ይገባል፡፡ በተያዘው ጉዳይ ተጠሪዎች በችሎቱ የተሰየሙት ዳኞች ውሳኔ የሰጡት በገንዘብ መሆኑን በወሬ ደረጃ ሰምተናል ከማለት ባለፈ ከአቤቱታቸው ጋር አያይዘው ያቀረቡት ማስረጃ የለም፡፡ አመልካቾች ፍርዱ ከመሰጠቱ በፊት እንዲህ አይነት ወሬ ከሰሙ ለምን ለችሎቱ ወይም ለሌላ ለሚመለከተው አካ በማሳወቅ ፍትህን የማገዝ ኃላፊነታቸውን አልተወጡም? የችሎቱ ዳኞች ውሳኔውን የሰጠነው ተጠሪዎች በወሬ ሰማን እንደሚሉት ከአመልካቾች ወይም ከጉዳይ አስፈጻሚ ገንዘብ ተቀብለን ሳይሆን ሕግን እና ማስረጃን መሰረት አድርገን ተገቢ ነው ብለን ያመንበትን በመሆኑ ተጠሪዎች በዚህ ረገድ ያቀረቡት ምክንያትም ከችሎት የሚያስነሳ ሆኖ አላገኘነውም፡፡ በአጠቃላይ ተጠሪዎች የዳግም ዳኝነት አቤቱታ እንዳንመለከት የችሎቱ ዳኞች ከችሎት እንድንነሳ ያቀረቡት አቤቱታ በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 33 ስር የተዘረዘሩትን ምክንያቶች መሰረት በማድረግ የቀረበ ባለመሆኑ ተጠሪዎች ያቀረቡትን ዳኞች ከችሎት ይነሱልን አቤቱታ በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 34/3 መሰረት አልተቀበልነውም፡፡
Mostrar todo...
Mostrar todo...
ስለ-ሕግ ⚖️ ABOUT-LAW

የኩባንያ መፍረስ *** ኩባንያዎች ጠቅለል ባለ መልኩ በ3 ምክንያቶች ሊፈርሱ እንደሚችሉ ከንግድ ህጉ አዋጅ ቁ. 1243/2013 ድንጋጌዎች በተለይም ከቁጥር 181፣463-491/ አክስዮን ማህበራት/ ፣ 531ና 532/ኃ/የት/የግ/ማህበር/ ተደንግጓል ፤ እነሱም 1.በአባላት ስምምነት 2.በህግ ወይም/እና በመመስረቻ ፅሁፍ በተቀመጠ ድንጋጌ 3. በፍርድ ቤት ውሳኔ ናቸው። ከስር የተቀመጠው የፌ/የመ/ደ/ፍ/ቤት የንግድ ችሎት ውሳኔ ሶስተኛውን የማፍረሻ ምክንያት ያብራራል ። ( ውሳኔው የተሰጠው የቀድሞው የንግድ ህግ በስራ ላይ እያለ ቢሆንም ትንታኔው በአሁኑም የንግድ ህግ አስተማሪ ነው) ” በፍርድ ቤት አንድ ኩባንያ ይፍረስ ተብሎ ስለተጠየቅ ብቻ ምክንያቶቹ ሳይመረመሩ የማፍረስ ውሳኔ አይሰጥም። ማህበሩን ሊያፈርስ የሚችል በቂና ትክክለኛ ምክንያት / sufficient and good cause/ መኖሩ ሊመዘን ይገባል” ዳንኤል ፍቃዱ / ጠበቃና የህግ አማካሪ/

Mostrar todo...
Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

ማስታወሻ:— በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ 50% እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ ተማሪዎች ዛሬ ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ የተመደባችሁበት ዩኒቨርስቲ በሚከተሉት አማራጮች ማየት ትችላላችሁ። Website:

https://result.ethernet.edu.et

SMS: 9444 Telegram bot: @moestudentbot ከምደባ ጋር ተያይዞ ላላችሁ ማንኛውም ጥያቄ result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት Complaint    ትምህርት ሚኒስቴር ፈጣን ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት ይህንን የቴሌግራም ቻናል Join በማለት ይከታተሉ👇 http://t.me/wasulife  http://t.me/wasulife