cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

ስለቤተሰብ ሕግ ፣ስለንግድ ሕግ፣ስለወንጀል ሕግ፣ስለውርስ ሕግ፣ስለውል ሕግ ፣የሰበር አስገዳጅ የሕግ ትርጉሞች የሚያገኙበት ቻናል ነው። ለጥያቄ እና አስተያየት @lawyerhenoktaye 📞 0953758395 ☎️LL.B)LL.M) 🔔 👇ሌሎች አማራጮችን ለማግኘት 🛑 https://linktr.ee/lawyerhenok? Youtube 🔥 https://youtu.be/5cnK4gX2Mrg

Mostrar más
Etiopía1 921Amárico1 510Ley856
Publicaciones publicitarias
11 165
Suscriptores
+324 horas
+287 días
+3330 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

በገጠር የመሬት ሽያጭ እና ግዢ የሚያከናውኑ ሰዎችን እስከ አምስት አመት በእስር የሚያስቀጣ አዋጅ በፓርላማ ጸደቀ የገጠር መሬትን በሸጠ ወይም በገዛ ማንኛውም ሰው ላይ እስከ አምስት ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ቅጣት የሚጥል አዋጅ በተወካዮች ምክር ቤት ጸደቀ። አዲሱ አዋጅ የግል፣ የወል ወይም የመንግስት ይዞታን በህገ ወጥ መንገድ ወርሮ ለተገኘ ሰውም ተመሳሳይ የእስራት ቅጣት ደንግጓል። የተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 6፤ 2016 በነበረው መደበኛ ስብሰባው በሙሉ ድምጽ ያጸደቀው ይህ አዋጅ፤ ከ18 ዓመት በፊት የወጣውን የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም አዋጅን ያሻሻለ ነው። አዲሱ አዋጅ አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮች እና ከፊል አርብቶ አደሮች በመሬት ላይ ያላቸውን መብቶች ያሻሻለ ሲሆን፤ የሴቶች እና ድጋፍ የሚሹ ሰዎችን የመሬት ተጠቃሚነት መብት ያረጋገጡ ድንጋጌዎችንም አካትቷል። አዋጁ በረቂቅ ደረጃ ለፓርላማ ከቀረበ በኋላ ከተደረጉ ማሻሻያዎች መካከል፤ “የወንጀል ተጠያቂነት” በሚመለከተው የተጨመረው አንቀጽ ይገኝበታል። “ከመሬት ጋር ተያይዘው የሚፈጸሙ ወንጀሎች ላይ አስተማሪ እና ተመጣጣኝ ቅጣት ማስቀመጥ አስፈላጊ በመሆኑ” ምክንያት እንደተካተተ የተነገረለት ይህ ድንጋጌ፤ ከመሬት ወረራ እስከ መሬት ሽያጭ ድረስ ያሉ የህግ ጥሰቶች የሚያስከትሏቸውን ቅጣቶች ዘርዝሯል። ማንኛውም ሰው መሬት የሸጠ ወይም የገዛ እንደሆነ፤ ከ100 ሺህ እስከ 200 ሺህ ብር ወይም ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ወይም በሁለቱም ሊቀጣ እንደሚችል በአዲሱ ድንጋጌ ላይ ሰፍሯል። በኢፌዲሪ ሕገ መንግስት መሰረት “መሬት የማይሸጥ፣ የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ንብረት ነው”። ሕገ መንግስቱ የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት የባለቤትነት መብትን የሰጠው “ለመንግስት እና ለህዝብ” ነው። ዛሬ በጸደቀው አዋጅ የግል፣ የወል ወይም የመንግስት ይዞታን በህገ ወጥ መንገድ የወረረ ማንኛውም ሰው፤ ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት አሊያም ከ30 ሺህ እስከ 100 ሺህ ብር ቅጣት ሊጣልበት እንደሚችል ተደንግጓል። በእነዚህ ይዞታዎች ላይ ጉዳት አድርሶ የተገኘ ማንኛውም ሰው፤ ከ3 ዓመት እስከ 7 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ወይም ከ50 ሺህ እስከ 150 ሺህ ብር እንደሚቀጣም በአዋጁ ላይ ተቀምጧል። ባልተፈቀደ ቦታ ላይ ማንኛውንም ግንባታ የሰራ ወይም እንዲሰራ የፈቀደ ሰው ደግሞ በአዲሱ አዋጅ መሰረት ከ1 ዓመት እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እስራት አሊያም ከ25 ሺህ እስከ 50 ሺህ ብር ይቀጣል። እነዚህ ቅጣቶች፤ ከመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ውጪ ይዞታውን ጥቅም ላይ አውሎ የተገኘ ሰው ላይ በተመሳሳይ መልኩ ተግባራዊ የሚደረጉ ይሆናል። ሀሰተኛ የመሬት ይዞታ ማስረጃ ያቀረበ ባለይዞታ እንዲሁም ማስረጃ የሰወረ ወይም የተሳሳተ ማስረጃ የሰጠ ባለሙያ ላይ የሚጣለው እስራት ከላይ እንዳሉት የህግ ጥሰቶች ተመሳሳይ ቢሆንም የገንዘብ ቅጣቱ መነሻ ግን ወደ 20 ሺህ ብር ዝቅ ብሏል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
Mostrar todo...
👍 16👏 1
★[በ0 አመት እና በልምድ] አንበሳ ኢንሹራንስ አዲስ የስራ ማስታወቂያ ♦Deadline: May 17, 2024 Lion Insurance Company invites fresh and qualified candidates for the following positions. ✔ Position 1: Junior Legal Officer ❇️ Educational  Background: LLB in Law ✔ Position 2: Legal Officer II ❇️ Educational  Background: LLB in Law ✔ Position 3: Legal Officer III 🔻 Educational  Background: LLB in Law ✔ Position 4: Senior Legal Officer ❇️ Educational  Background: LLB in Law 🔻Salary & Benefits: as per the salary Scale & Benefit Packages of the Company 🌀 How to Apply Online?? 👇👇👇👇👇 https://dailyjobsethiopia.com/2024/05/12/lion-insurance-vacancy-2/
Mostrar todo...
👍 9
Photo unavailableShow in Telegram
ክፍት ይስራ ማስታወቂያ!! የስራ ልምድ 0 ዓመት https://t.me/ethiolawtips
Mostrar todo...
3👏 1
የእርማት አቤቱታ =============== ፍ/ቤት በሰጠው ውሳኔና ትዕዛዝ ላይ የአጻጻፍ ስህተት፣ የቁጥር አጻጻፍ ጉድለት ወይም ያልታሰበና ባለማስተዋል የተዘለለ ድንገተኛ የቃል ስህተት እንዲታረም በተከራካሪዎች የሚቀርብ አቤቱታ አንድ ፍርድ ቤት በክርክሩ ዋነኛ ጭብጥ ላይ አከራክሮ የሰጠውን ውሳኔ ወይም ትዕዛዝ ስህተትን ማረም በሚል ሊያሻሽል ወይም ሊለውጥ አይችልም፡፡ ሰ/መ/ቁ. 37303 ቅጽ 8፣  ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 208 በማንኛውም ፍ/ቤት በሚካሄድ ክርክር ሥነሥርዓቱን ያልተከተለ ክስ የቀረበ እንደሆነ ወይም በክሱ ሂደት ሕጉ ያስቀመጣቸው የሥነሥርዓት ደንቦች በአግባቡ ያልተፈፀሙ እንደሆነ ፍርድ ቤት ሥርዓቱ ከሚያዘው ውጪ የተሠራውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ሊሰርዝ ይችላል፡፡ ይህም የሚከናወነው በተከራካሪዎች አመልካችነት ብቻ ሳይሆን በፍርድ ቤቱ በራሱ አነሳሽነትም ጭምር ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ መርህና ደንብ መሠረት በየትኛውም ደረጃ የሚገኙ ዳኞች በሚያካሂዱት የዳኝነት ሥራ የሥነሥርዓቱን ደንብ ያልተከተለ ክንውን በራሳቸውም ሆነ በአስተዳደር ክፍሉ መፈፀሙን ሲያውቁ ወይም ሲደርሱበት ስህተቱን እንዲያርሙ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በፍርድ ቤቶች አካባቢ የሚታየው የተለመደው አሠራር ዳኛ የሰጠውን ትዕዛዝ መቀየር አይችልም፣ መቀየር የሚችለው የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ብቻ ነው የሚል ቢሆንም ይህ በተለምዶ የዳበረው አሠራር የሥነሥርዓቱ ሕጉ ያሰፈረውን መሠረታዊ መርህ የሚጻረር ነው፡፡ ሥነ ሥርዓት ነክ የሆነን ጉዳይ የሚመለከት እስከሆነ ድረስ ባለጉዳዮች ወደ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት መሄድ ሳያስፈልጋቸው ስህተቱን ለፈፀመው ፍርድ ቤት ማመልከት ይፈቀድላቸዋል፣ ዳኞችም እርግጥም ሰህተት መሠራቱን ካመኑበት ስህተቱን የማረም ሥልጣንም አላቸው፡፡ ሰ/መ/ቁ. 17352 ቅጽ 1 ለሌሎች እንዲደርስ #share 🖐 Telegram 👇 @ethiolawtips @ethiolawtips
Mostrar todo...
👍 17
የአባላት የክፍያ መመሪያን Membership Fee Directive በተመለከተ የቀረበ ማብራሪያ ፤ ***       የአባላት የክፍያ መመሪያን Membership Fee Directive በተመለከተ በድጋፍና ክፍያው በዝቷል በሚል  የተለያዩ አስተያየቶች ለማህበሩ ደርሰዋል:: በዚህም መመሪያው ሲዘጋጅ ታሳቢ ያደርጋቸው መሰረታዊ ጉዳዮች የነበሩ ሲሆን እነዚህም ማህበሩ የተቋቋመበት አላማ እና ሊያሳካ የሚፈልጋቸው ግቦች አንፃር በቂ አቅም መፍጠር፤ ማህበሩ በህግ የወሰዳቸው ሀላፊነቶች መሰረታዊነት እና መጠን አንፃር ፤ የብር የመግዛት አቅም እና የማህበሩ አስፈላጊ ወጪዎች፤ እንዲሁም እያንዳንዱ ጠበቃ በግልም ሆነ በተደራጀ መንገድ በህግ ስርአት ውስጥ ሊኖረው የሚገባውን ግዙፍ ሚና የሚወክል ግዙፍ ተቋም የመፍጠር ራእይ እና መሰል አመንክዮዎች ከግምት ያስገባ ሲሆን በርካታ ውይይት እና ክርክር በአመራር ደረጃ ተደርጎበታል::      በተጨማሪም አቅም ለማይኖራቸው ጠበቆችና ለጀማሪ ባለሙያዎች በመመሪያው ታሳቢ የተደረጉ ልዪ አሰራሮችም አሉ::           በሌላ በኩል የማህበራችን አባላት በዚህ ደረጃ በማህበሩ እንቅስቃሴ ላይ የጎላ ተሳትፎ ማድረጋቸው እንደ ትልቅ ስኬት የሚታይ እና በእጅጉ የሚያበረታታ ነው:: ሆኖም ደንቡን ጨምሮ የሚቀርቡ ረቂቅ መመሪያዎች በሙሉ ግን የመነሻ መሆናቸውን ለማሳሰብ ይወዳል:: በዚህም አባላት ገንቢ ትችቶች ላይ በማተኮር ምክንያታዊ ሃሳቦችን እንዲያቀርቡ በድጋሚ ለማስታወስ እንወዳለን::           በመሆኑም መላው የማህበሩ አባላት በጠቅላላ ጉባኤ ላይ በመገኘት በሁሉም ረቂቆች ላይ የማሻሻያ ሃሳቦችን ከማቅረብ ጀምሮ እስከመለወጥ የሚደርስ ሃላፊነት/ሚና ያላቸው መሆኑን ተገንዝበው በንቃት በጉባኤው እንዲሳተፉ ማህበሩ በድጋሚ ጥሪውን ያቀርባል:: የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር ሚያዝያ 29 ቀን 2016ዓ.ም አዲስ አበባ፤
Mostrar todo...
👍 12
የአባላት የክፍያ መመሪያን Membership Fee Directive በተመለከተ የቀረበ ማብራሪያ ፤ *******       የአባላት የክፍያ መመሪያን Membership Fee Directive በተመለከተ በድጋፍና ክፍያው በዝቷል በሚል  የተለያዩ አስተያየቶች ለማህበሩ ደርሰዋል:: በዚህም መመሪያው ሲዘጋጅ ታሳቢ ያደርጋቸው መሰረታዊ ጉዳዮች የነበሩ ሲሆን እነዚህም ማህበሩ የተቋቋመበት አላማ እና ሊያሳካ የሚፈልጋቸው ግቦች አንፃር በቂ አቅም መፍጠር፤ ማህበሩ በህግ የወሰዳቸው ሀላፊነቶች መሰረታዊነት እና መጠን አንፃር ፤ የብር የመግዛት አቅም እና የማህበሩ አስፈላጊ ወጪዎች፤ እንዲሁም እያንዳንዱ ጠበቃ በግልም ሆነ በተደራጀ መንገድ በህግ ስርአት ውስጥ ሊኖረው የሚገባውን ግዙፍ ሚና የሚወክል ግዙፍ ተቋም የመፍጠር ራእይ እና መሰል አመንክዮዎች ከግምት ያስገባ ሲሆን በርካታ ውይይት እና ክርክር በአመራር ደረጃ ተደርጎበታል::      በተጨማሪም አቅም ለማይኖራቸው ጠበቆችና ለጀማሪ ባለሙያዎች በመመሪያው ታሳቢ የተደረጉ ልዪ አሰራሮችም አሉ::           በሌላ በኩል የማህበራችን አባላት በዚህ ደረጃ በማህበሩ እንቅስቃሴ ላይ የጎላ ተሳትፎ ማድረጋቸው እንደ ትልቅ ስኬት የሚታይ እና በእጅጉ የሚያበረታታ ነው:: ሆኖም ደንቡን ጨምሮ የሚቀርቡ ረቂቅ መመሪያዎች በሙሉ ግን የመነሻ መሆናቸውን ለማሳሰብ ይወዳል:: በዚህም አባላት ገንቢ ትችቶች ላይ በማተኮር ምክንያታዊ ሃሳቦችን እንዲያቀርቡ በድጋሚ ለማስታወስ እንወዳለን::           በመሆኑም መላው የማህበሩ አባላት በጠቅላላ ጉባኤ ላይ በመገኘት በሁሉም ረቂቆች ላይ የማሻሻያ ሃሳቦችን ከማቅረብ ጀምሮ እስከመለወጥ የሚደርስ ሃላፊነት/ሚና ያላቸው መሆኑን ተገንዝበው በንቃት በጉባኤው እንዲሳተፉ ማህበሩ በድጋሚ ጥሪውን ያቀርባል:: የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር ሚያዝያ 29 ቀን 2016ዓ.ም አዲስ አበባ፤
Mostrar todo...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

የኢትዮጵያ የፌደራል ጠበቆች ማህበር አባላት መዋጮ መመሪያ ቁጥር ………/2016 ለፌደራል ጠበቆች ----- በአጭሩ ረቂቅ መመሪያው አንድ ጠበቃ በዓመት 8400 ብር እንዲከፍል ይገደዳል! ይህን ያልከፈለ ፍቀድ እንዳያሳድስ እና የማህበሩን ጥቅም እንዳያገኝ ይሆናል ይላል!
Mostrar todo...
👍 6
Repost from Ethio Legal Hub
Mostrar todo...
Ethio Legal Hub on TikTok

@et_legalhub 19 Followers, 9 Following, 14 Likes - Watch awesome short videos created by Ethio Legal Hub