cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ኡመተ ረሱል

የአላህ ሰላም እና እዝነት በናንተ ላይ ይውረድ ውድ የአላህ ባሮች በዚህ #channel ላይ የተለያዩ ♥ ኢስላማዊ አስተምህሮቶች ♥ አስተማሪ ታሪኮች ♥ ቀልዶች እና ♥ ወቅታዊ አሳሳቢ ነገሮችን ወደናንተ እናደርሳለን ፨ ፨ ፨ ለማንኛውም አስተያየት @Ummate_resul_bot ይጠቀሙ

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
1 977
Suscriptores
Sin datos24 horas
-157 días
-6230 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Photo unavailableShow in Telegram
በሀገረ ሞሮኮ በሐውዝ ከተማ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ሰውነቷ ቆስሎ ከፍርስራሽ መሐል ተጋግጣ ወደ ሆስፒታል አቀናች። ራሷን አውቃ ስትነቃ ጋዘጠኞች ጥያቄ ሊያቀርቡላት ከሆስፒታሉ ቅጥር ከተሙ። ስለሰለባው ሊጠይቋት ማይካቸውን አስጠጉ። ንፁኋ ሴት ግን ባሏ እስካልፈቀደላት ካሜራ ፊት ቀርባ ክስተቱን ለማውጋት ፈቃደኛ አለመሆኗን ተናገረች። @yesheh_kalidrashid_daewawoch @yesheh_kalidrashid_daewawoch
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
መነሻውን በሞሮኮ ያደረገው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር 6.7 ስኬል አልፎ በአልጄሪያና በሞሪታኒያ ድንበር ከተሞች እየተዛመተ ይገኛል። እስካሁን የሟቾች ቁጥር ከ 1000 ማለፉን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ዘግቧል። ጌታዬ ሆይ! ኃያልነትህን እንዳሳየካቸው እዝነትህን ቸራቸው @yesheh_kalidrashid_daewawoch @yesheh_kalidrashid_daewawoch
Mostrar todo...
ካነበብኳቸው ልብ አስለቃሽ ታሪኮች 1- በስኳር በሽታ ለደከመችው እንስት "ህመሙ ሰውነትሽ ውስጥ እየተሰራጨ ነውና እጅሽ መቆረጥ አለበት" ተባለች። ደንገጥ ብላ እየተመለከተች "ልጄ ወደ ሌላ ሀገር ሊጓዝ ትንሽ ቀናት ስለቀረው አይሮፕላን ውስጥ ሲገባ እጄን አወዛውዤ እንድሰናበተው አንድ ሳምንት መጠበቅ እችላለሁን?" በማለት ጠየቀች። 2- ከምሽቱ 2 ሰአት ፈጣሪ አለመኖሩን የሚያትት ጽሁፍ በማስታወሻ ደብተሬ ላይ አስፍሬ ጎኔን ላሳርፍ አልጋዬ ላይ ተጋደምኩኝ። አላህ የሆነ ነገር እንዳያደርገኝ በመስጋት ማብራቱን ለማጥፋት ፈራሁ። 3- የእናቴን ጀናዛ በሲድር አጥቤ እንዳበቃሁ ከፈኗን ሚስክ እየቀባሁ የአፍንጫዋን ቀዳዳ ለመክደን ጥጥ ፈልጌ ተጣራሁ ጮክ ብዬ "እማ! ያንን ጥጥ ስጪኝ" አልኳት። 4- ባለቤቴ ከሚቀርበው ምግብ ውስጥ የረገፈ ፀጉሬን ሁሌ ስለሚያገኝ ንፅህናሽን የማትጠብቂ ቸልተኛ ሴት ይለኛል ካንሰር እንዳለብኝ ግን አያውቅም። #ሼር #share #join Https://t.me/smithhk
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
እንደ አውሮጳውያን የዘመን ቀመር 2016 በፍቅር የቀለሱት ጎጆ በእርሱ ህመም ደበዘዘ። በሽታ እያንፈራፈረ አልጋ ላይ አኖረው። ህመሙ በጠናበት አንድ ዕለት እንዲህ ተከሰተ። ፍራሹ ላይ ተንጋሎ ዓይኖቹን እንደምንም እየገለጠ ያ ኡሙል-ሙቅረአይን ሲል ተጣራ። ሲወዳት አምሳያ የሌላት ሚስቱ ናትና እንዲህ ነው የሚጠራት። ሰባቱን ልጆቹን ቁርአንን እንድትሐሳፍዛቸው አደራ እያለ እስትንፋሱ ተቋረጠ። ወሲያ መሆኑ ነው። እርሷም አደራውን ተቀብላ ከዱንያ ውጣ ውረድ ጋር ታግላ እናትም አባትም ሆና ልጆቿን እያሳደገች ተራ በተራ ቁርአንን አስሐፈዘች። ከቀናት በፊት የመጨረሻው ሰባተኛው ልጇ ቁርአንን ሐፍዞ በመጨረሱ የምስክር ወረቀት ተበረከተላት። እንዲህ ያሉ እናቶች ሲኖሩ የኢስላም ክብር ዳግም ያብባል ኢንሻ አላህ። @yesheh_kalidrashid_daewawoch @yesheh_kalidrashid_daewawoch
Mostrar todo...
ሰለዋት እናብዛ‼️ 🌴☘🌴☘🌴☘ ምን ያህሎቻችን ነን ጁምዓ ተጠባብቀን በረሱል [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] ላይ ሰለዋት የምናወርደው❓❓ ለምንድን ነው ከዚህ ትልቅ ስራ የምንዘናጋው❓❓ 📚እስኪ አላህና መልዕክተኛውን ምን እንደ ሚሉን እንመልከት 👇👇👇 🌴💥🕋🌴💥🕋 قال الله تعالى ﴿إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلّونَ عَلَى النَّبِيِّ يا أَيُّهَا الَّذينَ آمَنوا صَلّوا عَلَيهِ وَسَلِّموا تَسليمًا﴾ [الأحزاب: ٥٦] አላህ እንዲህ ይላል፦ {አላህና መላዒካዎቹ በነብዩ ላይ ሰለዋት ያወርዳሉ; እናንተ ያመናችሁ ሆይ በእሱ (በነብዩ) ላይ ሰለዋትና ሰላምን አውርዱ} 📖የአላህ መልዕክተኛም እንዲህ ይሉናል👇👇 "أكثروا الصلاة علي يوم الجمعة وليلة الجمعة فمن صلى علي صلاة صلى الله عليه عشرا " و حـسـنه الألباني في السلسلة الصحيحة 1407 {ጁምዓ ቀንና ጁምዓ ሌሊት በእኔ ላይ ሰለዋት አብዙ። በእኔ ላይ አንድ ጊዜ ሰለዋት ያወረደ ሰው በእሱ ላይ አላህ አስር ጊዜ ሰለዋት ያወርድበታል} "من صلى علي مرة كتب الله له بها عشر حسنات" وصـحــحه العلامة الألباني رحمه الله في السلسلة الصحيحة (٣٣٥٩) {በእኔ ላይ አንድ ጊዜ ሰለዋት ያወረደ ሰው አላህ ለእሱ በዚህ ምክንያት አስር ምንዳ ይፅፍለታል} " من صلى علي من أمتي صلاة مخلصا من قلبه صلى الله عليه بها عشر صلوات ورفعه بها عشر درجات وكتب له بها عشر حسنات ومحا عنه عشر سيئات " وصـحــحه العلامة الألباني رحمه الله في السلسلة الصحيحة ( ٣٣٦٠) {ከኡመቶቼ ውስጥ ከቀልቡ ጥርት አድርጎ በእኔ ላይ ሰለዋት ያወረደ የሆነ ሰው; አላህ በእሷ ምክንያት አስር ሰለዋት ያወርድበታል፣ አስር ደረጃም ከፍ ያደርግለታል፣ አስር ምንዳም ይፅፍለታል፣ አስር ወንጀልም ይሰርዝለታል} " من صلى علي واحدة صلى الله عليه عشرا " رواه أبو داود في سننه (١٥٣٠) وصححه الألباني رحمه الله {በእኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ በእሱ ላይ አላህ አስር ያወርድበታል} 🌴🌱🌴🌱🌴🌱 "اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد" ✍"ወደ መልካም ያመላከተ እንደ ሰሪው ነው"‼ #share #Join @smithhk
Mostrar todo...
"ያስተነትኑም ዘንድ ታሪኮችን ተርክላቸው" ፒ ዲኤ ፍ @yesheh_kalidrashid_daewawoch @yesheh_kalidrashid_daewawoch
Mostrar todo...
tarikochen terekelachew.pdf15.65 MB
Photo unavailableShow in Telegram
ይህ መፅሐፍ ....... በሚያናውዝ የስቃይና የግፍ ትውስታ ጀምሮ ልብን በሐዘን አየናጠ በቁጭት ቀልብን አተራምሶ ወደ ጀግንነት መንደር ይዘልቃል። ገድላቸውን አያተተ በሀሴት ውስጥን ያረሰርሳል። የማር ወለላን የተላበሱ የአርአያዎቻችንን የፍትሕ ብርሐን ይተርካል። በምናብ ሰመመን ውስጥ አስጥሞ ያለንበትን የኑረት ሹረት አስወግዶ ከግሳንግስ ትርክምርኪ አርቲፊሻል ገጽታ አውጥቶ ውብ ከሆነው ዘመን ወደ ተምሳሌቶቻችን የሕይወት ገጽ ያዘልቀናል። አንዲያ ያለ ዓለም፣ አንዲያ ያለ መጣፈጥ፣ አንደዚያ ያለ ፍትሕ በተዋበ ልዕልነት ልስልስ ባለ ሙቀት ውስጥ ጥዶ አጀብ የሚያሰኝ ፍትሕን ይዳስሳል። ታሪክ መስራት ላቃተን ለአኔው ዘመን እርቃነ ገላዎች በከፊሉም ቢሆን ዓውራችንን በመሸፈን ከቦታው ያለን እስክንመስል ዱር ሸንተረሩን አልፈን አብረን አንዘልቃለን። በንዴት በደስታ በፈገግታ አየታጀብን እንነጉዳለን። እየዋለሉ የሚተራመሱ ነፍሶች ላይ ሕይወትን የዘሩ ተምሳሌቶችን በአስገራሚ የኑረት ኃይል ንዝረትን እየቃኘ ድንቃድንቅ ክስተቶችን አያወሳ ይጠናቀቃል። ትንፋሽ አያቆራረጠ በጥልቁ ወደ ኃያልነት ይመጥቃል። በጥልቅ ማንቀላፋት ውስጥ ያሉትን ወደራስጌያችው ጠጋ ብሎ የተጠቀለሉበትን አንሶላ ገፎ ንቁ እያለ ይጣራል። አንደጠዋት ፀሓይ በመስኮት ዘልቆ ያበራል አንሻአላህ። በ410 ገፅ ተሰናድቶ የተዘጋጀውን ይህን የፅሑፎቼን ስብስብ ኢንሻ አላህ ፒ ዲ ኤፉን ነገ በዚህ የቴሌግራም ቻናል እለቀዋለሁ አላህ የምንጠቀምበት ያድርገን። @yesheh_kalidrashid_daewawoch @yesheh_kalidrashid_daewawoch
Mostrar todo...
አልጄሪያዊቷ ጋዜጠኛ ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካን እየጎበኘሁ ነበር በማለት ገጠመኟን ማውጋት ጀመረች። "ዕቃ ለመግዛት ወደ አንድ ሱፐር ማርኬት አቀናሁ። ሒሳብ ለመክፈል ወረፋዬን እየጠበቅኩ ሳለ ሂጃቧን ጠንቅቃ የለበሰች አንዲት ሴት ወደ ሱፐር ማርኬቱ ገባች። የድካም ምልክቶች ይታይባታል። የሳር ማጨጃ ማሽን በእጇ ይዛለች። ክፍያ ለመቀበል ወደተቀመጠችው ሰራተኛ ዘንድ አቀናች። "ይህንን ማሽን በ500 ዶላር ከሌሎች ዕቃዎች ጋር ገዝቼ ነበር... በማለት ንግግሯን ጀመረች ደንበኛ በማስተናገድ የተጠመደችው ሰራተኛ ከአፏ ቀበል አድርጋ "መመለስ ፈልገሽ ነው ታዲያ?" በማለት ጠየቀቻት። ሙተሐጂባዋ ቀጠለች "ዋጋውን መክፈል ፈልጌ ነው....." ካሽ ሪጅስተር ማሽኑ ላይ የተጣደችው የሒሳብ ሰራተኛ "አልገባኝም ትናንት ገዛሁት አላልሽኝም? ሌላ ሱቅ ርካሽ አጊኝተሽ ከሆነ የዋጋው ማረጋገጫ እስካለሽ ድረስ ልዩነቱን አስልተን የምንመልስበት ፖሊሲ አለን" አለች። "ይሄም ያም አይደለም" በማለት ለማስረዳት መናገር ጀመረች "ትላንት በክሬዲት ካርዴ ይህንን ማሽን ከሌሎች ዕቃዎች ጋር ገዛሁ። መኖርያ ቤቴ ከሱፐር ማርኬቱ ሁለት ሰአታት ያህል ይርቃል። ቤት ገብቼ ሂሳቡን ማየት ስጀምር የዚህን ማሽን ዋጋ ከክፍያ ሪሲቱ ላይ አጣሁት። በዚህ ምክንያት በስራሽ ክፍተት እንዳይፈጠር ደረሰኙ ላይ ባገኘሁት ቁጥር ደግሜ ደጋግሜ ደወልኩኝ። የስራ ሰዓቱ አልፎ ነበርና ሊነሳልኝ ግን አልቻለም። ዛሬ ስራ አስፈቅጄ ማሽኑን ይዤ መጣሁ። መዝግበሽ ከሂሳብ እንድትከችውና ክፍያውን እንደ አዲስ እንድፈፅም አንቺ በእኔ ምክንያት ስራሽን እንዳታጪ እኔም ባልከፈልኩት ነገር እንዳላገለግል" ይህን የሰማችው ሰራተኛ ከመቀመጫዋ ተነሳች። ሙተሐጂባዋን እያየች አይኖቿ እንባ እንዳቀረሩ አቅፋ ትስማት ጀመር። "የእኔ ጥፋት ሆኖ ሳለ ገንዘቡን ለመክፈል እንዴት ተመልሰሽ ለመምጣት ወሰንሽ?" በማለት ጠየቀቻት። በአግራሞት ተጭራ "ይህን ከባድ ሳጥን ተሸክመሽ ከስራ ገበታሽ አስፈቅደሽ ደርሶ መልስ አራት ሰአታት የሚያስኬድ መንገድ አቋርጠሽ እኮ እንዴት?!" ሰራተኛዋ ተገረመች። ሙስሊሟ ሴት ምላሽ ሰጠች፡- "ምክንያቱም ይህ አማና ነው" አለቻት። በእስልምና የታማኝነትን ትርጉም አስረዳቻት የአማናን ክብደት አስተማረቻት። ቢሮ ውስጥ ወዳለው ስራ አስኪያጇ ወሰደቻት። ተያይዘው ገቡ። ከቢሮው መስታወት ጀርባ ብንመለከታቸውም የሚያወሩት ግን አልተሰማንም። የሱፐር ማርኬቱ ሰራተኛ ሙስሊሟ ሴት ያደረገችውን ​​ለማናጀሯ ስትነግራት ስሜታዊ ትመስላለች። ከደቂቃዎች በኋላ... ሥራ አስኪያጁ ሰራተኞቹን በመደብሩ ውስጥ ሰብስቦ ስለ ሙስሊሟ ሴት ማውራት ጀመረ። እሷ ሃይማኖቷ ያዘዛትን ግዴታዋን እንጂ ሌላ ምንም እንዳላደረገች በዓይን አፋርነት ስሜት አንገቷን ሰበር አድርጋ መግለፅ ጀመረች። ስለ እስልምናና አስተምህሮቱ ይጠይቋት ጀመር። እሷም በሚገርም የራስ መተማመን ቅንነትን በተላበሰ ትህትና መለሰች። ሥራ አስኪያጁ ማሽኑ እንደ ስጦታ ድርጅቱ ሊሰጣት ማሰቡን ነገራት። ነገር ግን ሽልማቷን ከአላህ ዘንድ እንጂ ማሽኑን ከፍላ መግዛት እንደምትችል ተናገረች። ይህ መልካም ስራዋ እንዲያበላሽላት እንደማትፈልግም ይቅርታ ጠይቃ አልቀበልም አለች። እነሱ እየተገረሙ እርሷም በዝግታ እየተራመደች የማሽኑን ዋጋ ከፍላ ከሱፐር ማርኬቱ ወጣች። ውስጤ በሐሴት ተናጠ። አንዳች ኩራት ተሰማኝ። ከሄደች በኋላ ስለ እሷ በሠራተኞቹ ብቻ ሳይሆን ዕቃ ሊገዙ በተሰበሰቡት ደንበኞች መካከልም ቀጠለ። ስለ ኢስላም መወራት ጀመረ። ይህ ኢስላም ነው ትክክለኛው የአላህ ዲን ተባለ። ድሮ ድሮ ሙስሊሞች ከአማና ጋር የጠበቀ ግንኙነት ነበራቸው አማናው የተቀመጠበትን የፌስታል ቋጠሮ እንኳ ሳይፈታ ዘመናትን ተሻግሮ ባለቤቶቹ ሲመጡ ዕቃቸውን እንዳስቀመጡት ያገኙት ነበር አሁን አሁን ግን የአማናችን ነገር ...... #ሼር #share #join Https://t.me/smithhk
Mostrar todo...
ከአላህ ጋር ነግዶ ማን ከሰረ በሰባዎቹ መጀመሪያ በሀገረ ግብፅ ግዛት ተፈህና አል-አሽረፍ በምትሰኝ ትንሽዬ መንደር ውስጥ ምንም የሌለው ደሀ የግብርና መሃንዲስ ጣራዋ በተቀደደ፣ ግርግዳዋ በተፈረፈረ ደሳሳ የጭቃ ቤት ውስጥ ከወላጆቹ ጋር ጎጆውን ቀልሶ ይኖር ይዟል። ግርግዳው በጋዜጣ የተሸፈነ ቤት!! በወላጆቹ ልፋት ተምሮ ለወግ ማዕረግ በቅቶ ቢመረቅም ስራ ማግኘት ግን አልተቻለውም። ሰላህ አጢያ ይሰኛል። ያረጀ እንጂ አዲስ ልብስ ለብሶ አያውቅም። ትክክለኛው የጫማ ቁጥር 42 ቢሆንም ከቆሻሻ ገንዳ ያገኛትን 44 ቁጥር ጫማ እንዳታልቅበት በቀስታ እየረገጠ ይጓዝባታል። በግብርና ፋኩሊቲ ተመርቀው በከፋ ድህነት የሚሰቃዩ፣ ስራ ለመጀመር የሚፈልጉ ዘጠኝ የመንደራቸውን ሰዎች ሰብስቦ አነስተኛ ፕሮጀክት ለመጀመር ወሰነ። አማከራቸው ተስማሙ። አስረኛ አጋር እየፈለጉ እያንዳንዳቸው 200 የግብፅ ፓውንድ አዘጋጅተው ጠበቁ። ተሰብስበው ሻይ እየጠጡ ወደነበሩት አጋሮቹ ዘንድ አቀናና "አስረኛውን አጋር አግኝቻለሁ" አላቸው። "ማን እነደሆነ ንገረን" ሲሉ ጠየቁ "አላህ ነው" በማለት መለሰላቸው። "ገንዘባችንን ከአደጋ ለመጠበቅ፣ ኃብታችንን ለማፋፋት እርሱ አንደኛው አጋራችን ይሆናል" በማለት ንግግሩን አከለ። ሁሉም ተስማሙ። በጋራ የተቋቋመው የህብረት ኩባኒያ ውሉ ፀድቆ "አስረኛው ባለድርሻ አላህ የትርፉን አንድ አስረኛ ይወስዳል" የሚለው ቃል ከውሉ ወረቀት ላይ ሰፍሮ ሁላቸውም ፊርማቸውን አኖሩ። እውነተኛ የህብረት ስራ፣ ግልፅ ስምምነት ተደረገ። የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ዙር ውጤት ጥሩ ትርፍና የተለየ ምርት ማስተናገዱን ሲመለከቱ ለተገኘው ትርፍ ለአላህ ምስጋና ይሆን ዘንድ የምርት ዑደት ውጤቱን "የታላቁ አጋር ድርሻ" በሚል መጠኑን ለመጨመር የአላህን ድርሻ ወደ 20% ለማሳደግ ወሰኑ። በየአመቱ ከፍ እያለ የአላህ ድርሻ 50% ደረሰ። አርሰው ቡቃያውን ወቅተው ምርቱን ይሸጣሉ። ነግደው ካተረፉት የአላህን ድርሻ ሳያጓድሉ ሀቁን ጠብቀው ትክክለኛ ቦታ ላይ ያውላሉ። መስጂዶች፣ የሴቶች ሒፍዝ ማዕከል የአይታሞች ማደርያ የአቅመ ደካሞች መመገብያ ተቋማትን በአላህ ድርሻ ገነቡ። ትርፉ እያደገ ሲመጣ ለመሳኪኖች የዕርዳታ ድርጅትን አቋቋሙ.. በግብፅ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ትንሽዬ መንደር ውስጥ ደረጃቸውን የጠበቁ አራት ኮሌጆችን ገነቡ። እያንዳዳቸው ለ600 ተማሪዎች የሚሆን ማደርያ 1000 ተማሪዎችን የሚያስተናግዱ ኮሌጆች! ማንኛውም የኮሌጁ ተማሪ ወደ ቀዬው ለመሄድ ሲፈልግ ነፃ ትኬት ማግኘት እንዲችል በይተል ማል የሚል ቢሮን አቋቋሙ። በመንደሩ ደሃ እስኪጠፋ ተቋሙ ፋፋ። ኸይራቱ ወደ ጎረቤት መንደሮች ጭምር ዘለቀ። ስራ አጥ ወጣቶች ከድህነታቸው ተላቀው እንዲሰሩ ተመቻቸላቸው። ለጎረቤት ሀገራት አትክልቶችን ኤክስፖርት ማድረግ ጀመሩ። ምርት በሚሰበሰብበት ወቅት ለከተማዋ ነዋሪ ከትልቅ እስከ ትንሹ የአትክልት ከረጢት በስጦታ ይበረከትላቸው ገባ። በረመዳን የመጀመሪያዎቹ ቀናት ኢፍጣር ተዘጋጅቶ ወንዶች በአደባባይ ሴቶች በየቤታቸው በፍቅር በአብሮነት ተሰብስበው ያፈጥራሉ። ወላጅ አልባ ሴቶች ለትዳር ሲደርሱ ወጪያቸው ተሸፍኖ ይዳራሉ። ይህ ሁሉ በአላህ ድርሻ የሚሰራ መልካም ተግባር መሆኑ ያስገረማቸው መስራቾቹ የፕሮጀክቱ ባለቤትነት ወደ አላህ እንዲዞር ወሰኑ። እነርሱም የአላህ ሰራተኛ የረቢ አገልጋይ ሆኑ። ባለቤትነቱን ወደአላህ ሲያዞሩ "ትርፉ ሳይቋረጥ ድሆች ይጠቀሙ ዘንድ ጌታችን ሆይ አደራ!" የሚለውን ቃል ከውሉ ወረቀት ላይ አሰፈሩ። አትራፊ ንግድ!! መልካም ግብይይት!! "አላህ ከምእምናን ነፍሶቻቸውንና ገንዘቦቻቸውን ጀነት ለእነሱ ብቻ ያላቸው በመኾን ገዛቸው" ይሉሀል ይህ ነው። ኢንጂነር ሰላህ አጢያ በ70 አመታቸው በጉበት በሽታ ሲሰቃዩ ቆይተው እንደ አውሮጳውያን የዘመን ቀመር ጥር 11 ቀን 2016 ሩሐቸው ከጀሰዳቸው ተላቀቀች። ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ጀናዛቸውን ሸኘ። እየተላቀሱ ጀሰዳቸውን ከለህዱ አሳረፉ። ልጅ አልነበራቸውም። አላህ ከምህረቱ አጎናፅፎ ጀነተል ፊርደውሱን ይወፍቃቸው። ╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍ ምንጮቼ:- - الشيخ خالد الجندي ينعي صلاح عطية نسخة محفوظة 25 فبراير 2020 - تفهنا الأشراف قرية بلا عاطل أو فقير نسخة محفوظة 17 مايو 2017 - صلاح عطية رجل أعمال تاجر مع الله نسخة محفوظة 12 مايو 2017 على موقع واي باك مشين #ሼር #share #join Https://t.me/smithhk
Mostrar todo...
"ሡልጣን ሆይ! ሰላትህን በጀመዓ አትሰግድምና ምስክርነትህ ተቀባይነት የለውም..." ╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍ አሁን የምንገኝው በሙስሊሞች ዋና ከተማ ቡርሳ ነው። በታላቁ መሪ በሱልጣን ባየዚድ ቢን ሙራድ ዘመነ መንግስት! ቡልጋሪያን፣ ቡርሳንና አልባኒያን ድል አድርጎ የከፈተው የክፍለ ዘመኑ ኃያል መሪ ቃዲ ሸምሰ ድ-ዲን ዘንድ በአንድ ጉዳይ ላይ የምስክርነት ቃሉን ሊሰጥ ከፊታቸው ተጥዷል። እንደማንኛውም ምስክር እጆቹን አጣምሮ ከችሎቱ ፊት ቆሟል። ዳኛው ዓይኑን አማትሮ ሡልጣኑን እየተመለከተ ከእግር እስከ ራሱ በትኩረት ቃኘ "ሡልጣን ሆይ!" አለ ዓይን ዓይኑን እያየ። ታዳሚው በዝምታ ተውጦ የዳኛውን ንግግር ለመስማት ጆሮውን ቀሰረ "ሡልጣን ሆይ! ሰላትህን በጀመዓ አትሰግድምና ምስክርነትህ ተቀባይነት የለውም። ሰላቱን በጀመዓ የማይሰግድ በምስክርነት ቃሉ ሊዋሽ ይችላልና አይታመንም ተብሎ ስለሚገመት ያንተን ምስክር አንቀበልህም ሂድ" አሉት። በፍርድ ቤቱ የተገኙ የዳኛውን ንግግር የሰሙ ታዳሚያን በድንጋጤ አይናቸውን ለጠጡ። ሡልጣን ባይዚድን በሰዎች ፊት ዝቅ ያደረገውን ዳኛ መጨረሻ ለማየት፣ ለዳኛው እየፈሩ ባሉበት ቦታ ተቀመጡ። ችሎቱ ፀጥ ረጭ አለ። ሡልጣን ባየዚድ አንዲትም ቃል ከአፉ ሳያወጣ አንገቱን ከመሬቱ እንደደፋ በእርጋታ እየተራመደ ፍርድ ቤቱን ለቆ ወጣ። በዚያው ቀን ከቤተ መንግስቱ አጠገብ መስጂድ እንዲሰራ አዘዘ። ተገንብቶ እንዳለቀ ሰላቱን ሳያዛንፍ አምስቱንም አውቃት በጀመዓ የሚሰግድ የአላህ ባርያ ሆነ። ይህ ፍትህ የንግስና መሰረት፣ የኢስላም ዳኞችና ዑለማኦች ከአላህ በቀር ማንንም በማይፈሩበት ወቅት የተገኘ አስገራሚ ታሪክ ነው ╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍ ምንጮቼ:- إنباء الغمر بأنباء العمر الشقائق النعمانية في علماء الدولة العثمانية حديقة السلاطين روائع من التاريخ العثماني، سيرة السلاطين الأوائل #ሼር #share #join Https://t.me/smithhk
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.