cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Hijra Tube [Official]

ሒጅራ ቲዩብ ኢስላማዊ ድረገፅ ትኩስ ትኩስ የሙስሊሙን አለም የተመለከቱ መረጃዎች ጠቃሚ ፅሁፎችና ዳእዋዎች ይቀርቡበታል

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
10 065
Suscriptores
-424 horas
-367 días
-14030 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

የቤት ኪራይ ጨምሩ፣ ወይም "ቤቱን ልቀቁ፣ ወይም እንዲያ ላደርግ እንድህ ላደርገ ፈልጌ ነው" ሚል ግፊት ከደረሰባችሁ ከታች ባለው የስልከ ቁጥሮች ደውላችሁ ጠቁሙ!! +251118722917 +251118553820 አዲስ አበባ የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ
Mostrar todo...
👍 4
እጅግ ጠቃሚ የጁምኣ ኹጥባ " አማናን መወጣት" 8:44 አማርኛው ይጀምራል ሰኔ 14/2016 ዙልሂጃ 15/1445 ኡስታዝ _አብዱልዋሲዕ ሼኽ ነስሮ አዲስአበባ ተንኢም መስጂድ
Mostrar todo...
የጁምዓ ኹጥባ 8.mp324.69 MB
#የነፍስ_ዓይነቶች 📚ቁርኣን ነፍስን ከጠባዩዋና ከባሕሪዋ አንፃር ለሦስት ይከፍላታል... 1ኛ- "አን-ነፍሱል ዓማረቱ ቢሱእ"፤ በመጥፎ የምታዝ ነፍስ እንላታለን። የዚህች ዓይነት ነፍስ ባለቤት ሰውየውን ሙሉ ለሙሉ የምትቆጣጠረውና የምታዝዘው ሲሆን ሁሌም አላህን ወደ ማመጽ ትገፋዋለች። ይህች ነፍስ ሀጢያትና ወንጀልን ተቀብላ ያለምንም ትግል ታስተናግዳለች። ♦️ነቢዩላህ ዩሱፍን (عليه السلام) ለነፍሷ ፍላጎት ያባበለቻቸው ያቺ የንጉሱ ሚስት ምን ነበር ያለችው... وَمَاۤ أُبَرِّئُ نَفۡسِیۤۚ إِنَّ ٱلنَّفۡسَ لَأَمَّارَةُۢ بِٱلسُّوۤءِ إِلَّا مَا رَحِمَ رَبِّیۤۚ إِنَّ رَبِّی غَفُورࣱ رَّحِیمࣱ «ነፍሴንም (ከስሕተት) አላጠራም፡፡ ነፍስ ሁሉ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና፡፡ ጌታዬ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው» (አለች)፡፡ [12፥53] 2ኛ- "አን-ነፍሱ ላዋማህ"፤ ዋቃሽ ነፍስ እንላታለን። ይህች ነፍስ ባሕሪዋ ሆኖ አንድ ሁኔታ ላይ አትጸናም። መገለባበጥና መለዋወጥ ታበዛለች። ሲሆንላት አላህን ታወሳለች ደግሞ ትዘነጋለች። አንዴ ወደ አላህ ትገባለች ከዚያ ትመለሳለች። አንዴ በዒባዳ ትደሰታለች ደግሞ ስሜት ታጣበታለች። ትወዳለች ትጠላለች። ሲላት ቀጥ ብላ "አላህ አላህ" ትላለች ደግሞ ወንጀልም ትቀላቅላች። ♦️ይህች ነፍስ አንድ ወንጀል ስትሰራ ሰውየውን ለምን እያለች አንዲያስብ ታደርገዋለች። ወንጀል ላይ በወደቀች ቁጥር አላህን በማሰብ ጥበትና በወንጀሉ ማፈር የሚከተላት ናት። አላህ በዚህች ነፍስ ምሏል። لَاۤ أُقۡسِمُ بِیَوۡمِ ٱلۡقِیَـٰمَةِ ❝(ነገሩ ከሓዲዎች እንደሚሉት) አይደለም፡፡ በትንሣኤ ቀን እምላለሁ፡፡❞ [75፥1] وَلَاۤ أُقۡسِمُ بِٱلنَّفۡسِ ٱللَّوَّامَةِ ❝(ራሷን) ወቃሽ በኾነች ነፍስም እምላለሁ፡፡ (በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ)፡፡❞ [75፥2] ♦️ይህች ነፍስ ከመጀመሪያዋ ነፍስ የተሻለች ናት። በል እንደውም በጣም ከፍ ያለች ናት። ሁሌም ኣኺራንና ቂያማን ታስታውሳለች። ለተውበትም የቀረበችና የተገራች ናት። በመጥፎ የምታዝን ነፍስ ወደዚህች ራሷን ወቃሽ ወደሆነችው ነፍስ ለመለወጥ አኺራን ደጋግሞ ማስታወስ መድኃኒት መሆኑን ልብ እንበል። ♦️በመጥፎ የምታዘውን ነፍሱን "አላህ ጋር ትገናኛለሽ፣ አላህ ፊት ትቆሚያለሽ..." እያለ አኺራንና ቂያማን በማስታወስ መገሠጽ ፈውስ ይሆናል። ነገሩ ያላሰለሰ ጥረት የሚፈለግና መቋረጥ የሌለበት የመዳን መንገድ ነው። ማወቅ ያለብን ነፍስ መቀየርና መለወጥን የምትቀበል ፍጡር ናት። 3ኛ- "አን-ነፍሱ አል-ሙጥመኢናህ" የተረጋጋች ነፍስ እንላታለን። ይህች ነፍስ አላህን የምትፈራ፣ አላህን የምትናፍቅ፣ አላህን የምትወድ በዚህም የረጋችና የረካች ደግ ነፍስ ናት። ነፍስ በአላህ የረካች እንደሆነ፣ አላህን በማውሳት የጸዳች ከሆነ፣ ወደ አላህም ጠቅልላ የገባች ከሆነ፣ ወደ አላህ በመቅረብ ብቸኝነቷን ያስወገደች ከሆነ፣ አላህን መገናኘት የምትናፍቅ ከሆነ ይህች ነፍስ "ሙጥመኢናህ" የተረጋጋች ናት ማለት ነው። ♦️ይህች ነፍስ ሞት መጥቶ ከሰውነት ስትወጣ እንዲህ ትባላለች (አላህ ያድለንና)፦ یَـٰۤأَیَّتُهَا ٱلنَّفۡسُ ٱلۡمُطۡمَىِٕنَّةُ ❝(ለአመነች ነፍስም) "አንቺ የረካሺው ነፍስ ሆይ! [89፥27] ٱرۡجِعِیۤ إِلَىٰ رَبِّكِ رَاضِیَةࣰ مَّرۡضِیَّةࣰ ❝ወዳጅ ተወዳጅ ኾነሽ ወደ ጌታሽ ተመለሺ..[89፥28] فَٱدۡخُلِی فِی عِبَـٰدِی ❝በባሮቼም ውስጥ ግቢ..[89፥29] وَٱدۡخُلِی جَنَّتِی ❝ገነቴንም ግቢ፤» (ትባላለች)።❞ [89፥30] 💥አንዲት ነፍስ ሦስቱንም ባሕሪ ተላብሳ ልናገኛት እንችላለን። በመጥፎ የምታዝ ሆናም፤ ራሷን ወቃሽ ሆናም፤ የተረጋጋች ሆናም ይስተዋላል። ባሕሪዋ ከአንዱ ወደ አንዱ ሁኔታ ይለዋወጣል። አላህ ነፍሳችንን ይቅጣልን❤ አሚን💚
Mostrar todo...
9👍 5
አንድ ሰው አርባ አመት ሲሞላው፦ ”ወደ አኼራ ጎዞህ ተቃርቧልና ስንቅህን አዘጋጅ።˝ ብሎ ከሰማይ☝️ ተጣሪ ይጣራል። 📚ረውደቱ አል ዑቀላእ (52)
Mostrar todo...
👍 6
Photo unavailableShow in Telegram
3
📢📢📢 ታላቅ የምስራች ለወላጆች እና ለመምህራን 🌤በብዙዎች ጥያቄ መሰረት በተለያዩ ቦታዎች እንሰጥ የነበረውን  የተርቢያ(ልጆቻችንን በተርቢያ የማሳደግ) ስልጠና በአሏህ ፈቃድ በተቀናጀ እና ቀጣይነት ባለው መልኩ በማእከላችን ልንሰጥ ዝግጅታችንን አጠናቀን ምዝገባ መጀመራችንን  ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው:: ትውልድን በመልካም ማነፅ የሁሉም ሀላፊነት በመሆኑ እኛም የበኩላችንን ለማበርከት በማእከላችን የሚሰጠውን የመጀመሪያ ዙር የአንድ ወር ስልጠና አሰናድተን  የናንተን መምጣት በመጠባበቅ ላይ ነን:: ይምጡ አበቦቻችንን በጋራ እንኮትኩት:: 🌴 ስልጠና የሚሰጠው ቅዳሜ ጠዋት ከ3:30_6:00 ሰዐት            ወይም ቅዳሜ ከሰአት ከ7:30 _10:00 ሰዐት የሚጀመረው ከአረፋ በኋላ የመጀመሪያው ቅዳሜ(ሰኔ 15/2016) ለምዝገባ እና ለበለጠ መረጃ 👇ይደውሉ :: የምንቀበለው የሰልጣኝ ብዛት ውስን ስለሆነ ቀድመው ይመዝገቡ:: አድራሻ ከጀርመን አደባባይ ከፍ ብሎ ገቢዎች አካባቢ:: ☎️ 0982002437 አል ማሒር የተርቢያ ማእከል 👉ለሴቶች ብቻ
Mostrar todo...
👍 4 2
sticker.webp0.84 KB
√ወንጀሉ ላሳሰበው ሰው ትልቅ ብስራት ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ «የአረፋ ቀን ፆም የሁለት አመት ወንጀል ያብሳል።» ትንሽ ሰርቶ ብዙ ማትረፍ ማለት ይህ ነው። ከአቡቀታዳህ ተይዞ እንደተወራው የአላህ መልእክተኛ - ﷺ - ስለ አረፋ ቀን ፆም ተጠይቀው እንዲህ አሉ፦ {ያለፈውንም የወደፊቱንም (የሁለት) አመት ወንጀል ያብሳል}። ሙስሊም ዘግቦታል። ይህ ሀቂቃ ለተጠቀመበት ሰው ትልቅ እድል ነው። √√የአረፋ ቀን ማለት፦ ⸕ሰዎች ከጀሀነም ነፃ የሚወጡበት ⸕ወንጀሎቻቸው በብዛት የሚማርበት ⸕ዱአቸው ይበልጥ ተቀባይነት የሚያገኝበት ⸕አረፋ ተራራ ላይ በቆሙት ባሮቹ አላህ የሚፎክርበት ⸕የሀጅ ዋና ሩክን የሆነው አረፋ ተራራ ላይ የሚቆምበት ⸕አላህ እዝነቱ ለባሮቹ የሚቸርበት የአመቱ ምርጥ ቀን ነው። ⁌ይህንን ወሳኝ ቀን፦ ☞ቀኑን በመፃም ☞ዱአ በማብዛት ☞ቁርአን በመቅራት ☞ዚክር በመዘከር ☞ሶደቃ በመስጠት ☞ተክቢራ በማብዛትና 👉በሌሎችም መልካም ስራ ላይ ሆነን ልናሳልፈው ይገባል። « ይህንን ታላቅ እድል ቀጣይ አመት ላታገኘው ትችላለህና ዛሬ ላይ በአግባቡ ተጠቀምበት።»
Mostrar todo...
16👍 3
sticker.webp0.59 KB
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.