cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

መንፈሳዊ ጉባኤ

ወዳጄ ሆይ፥ ሁለንተናሽ ውብ ነው፥ነውርም የለብሽም። መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 4 : 7 @Menfesawi_Gubae ጥያቄ ካላችሁ ከታች ባለው አድራሻ መጠየቅ ትችላላችሁ። @HenokAsrat3

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
3 047
Suscriptores
-124 horas
-27 días
-1630 días
Distribuciones de tiempo de publicación

Carga de datos en curso...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Análisis de publicación
MensajesVistas
Acciones
Ver dinámicas
01
#ከሐልዮ_ኃጢአት_መጠበቅ ሰይጣን ነቅዓ ሐልዮን መጠበቅ ላልቻለ ወጣት በቀጣይ እርሱን የሚወጋበት ኹለተኛው ጦር ሐልዮ ኃጢአት ነው። “የሐልዮ ኃጢኣት ምን ትጎዳለች?” እያለ እንዲያስብ ያደርገዋል። በሐልዮ ኃጢአት ያዝለዋል። ይኸውም ደቂቀ ሴት ደቂቀ ቃኤልን ከመስማት አልፈው እንዲመለከቷቸው በማድረግ በዝሙት ፍላጻ እንደነደፋቸው ነው። ስለዚህ የተለያዩ ነገሮችን እንዲመለከት ያደርገዋል። ለምሳሌ ራስን በራስ ስለ ማጎሳቆል፣ ወይም ስለ ምስለ ሩካቤ፣ ወይም ስለሚያውቃት ሴት በዝሙት ሕሊና እንዲያስብ ያደርገዋል። ጓደኞቹ የተናገሩትን ነገር ወይም በመጽሔት ያነበበውን ወይም በተለያየ መንገድ ሲወራ የሰማውን “ይህ ምን ያረክሳል?” እያለ በሕሊናው እንዲያመላልሰው ያደርገዋል። እንደዚህ በሚኾንበት ጊዜ በየትኛውም ቀን ቢሰግድ ፆሩ ይመለስለታል። አንድ ወንድሜ እንደ ነገረኝ፡ እንደዚህ ያለ ፆር ሲመጣበት በሩካቤ አካሉ አከባቢ ካለው ፀጕር የተወሰነውን ይነጫል። በጣም ያማል። በዚያ ሰዓትም ከፆሩ ይልቅ ሕመሙ ስለሚበልጥ ፆሩን ከማሰብ ይመለሳል። ሕሊናው አድርገኝ አድርገኝ ብሎ እንዳይገፋፋው፣ ነጉዶ የመጣውን ፆሩን በተግባር ለመፈጸም ሰይጣንን እንዳይታዘዘው ያደርገዋል። እንደ ነደ እሳት የሚያቃጥለውን የፍትወትን ፆር እንዳያስነሣበት ይከልለዋል። የሐልዮ ኃጢኣት በተነሣ ጊዜ "ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ግን ሽሽ” እንደ ተባለው፥ ለዚህ ከሚዳርጉን ነገሮች (ቦታ፣ ኹኔታ) መራቅ የመጀመሪያው እርምጃ ነው። “ይህ አሳብ የእኔ አይደለም” ብሎ ለመሸሽም የሐልዮ ኃጢአት የምታመጣውን መከራ የሚነግረን መምህር ወይም አበ ነፍስ ማግኘት እጅግ አስፈላጊ ነው (2ኛ ጢሞ.2፥22)። መካሪ መምህር ሳናገኝ ቀርተን ካዋልናትና ካሳደርናት ለሰይጣነ ፍትወት እጅ እንደ መስጠትና ወድቀን ወደ ቀጣዩ ደረጃ ወደ ገቢር ልናልፍ እንችላለንና። ከክፉ አሳብ መራቁ ብቻውን በቂ አይደለም። ክቡር ዳዊት “ከክፉ ሽሽ” ካለ በኋላ በዚያ ሳያቆም ጨምሮ “መልካምንም አድርግ" ይላልና (መዝ.33፥14)። እርስ በእርሳቸው የተያያዙ ናቸው። ስለዚህ አንዲት ሴት ጥሩ ልብሷን ተሸላልማ ተጊያጊጣ እየተኩነሰነሰች ስትሔድ አይቶ ፈላስፋው ዲዮጋንስ ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች "ከዚች ክፉ ወጥመድ ሽሹ" እንዳላቸው ሸሽቶ ወደ በጎ ሥራ ፊትን ማዞር ይገባል። ከወደቁ በኋላ ከመጠበብ ሳይወድቁ መጠንቀቅ ይሻላልና። በሌላ መልኩ ደግሞ ተፈጥሮ ስለኾነ እነዚያ ስሜቶች ለምን መጡ ማለት አይቻልም። ስሜቶቹን ግን መቀደስ ስለሚቻል ከክፉ ሸሽቶ መልካም በማድረግ መቀደስ ይቻላል። አንድ ፈረስን የሚጋልብ ሰው፥ ፈረሱ ወደ ገደል ቢያመራ ጋላቢው የሚያደርገው ልጓሙን ማጥበቅ ብቻ አይደለም፤ ፈረሱ በትክክለኛው መንገድ እንዲሔድም ይመራዋል እንጂ። ስለዚህ እንደዚህ ዓይነት ስሜቶች ሲመጡብን ከመራቅ ባሻገር ወዲያው መንፈሳዊ ተግባር ማከናወንም አስፈላጊ ነው። ጸሎት ሊኾን ይችላል፤ ስግደት ሊኾን ይችላል፤ መጽሐፍ ማንበብ ሊኾን ይችላል፣ መንፈሳዊ አባት ጋር መደወል ሊኾን ይችላል። ከበረኻ አባቶች ከተሰጡት ምክሮች አንዱ እንዲህ የሚል ነው፦“ሌላ እኁም ከሰይጣነ ዝሙት ጋር ይጋደል ነበር። በሌሊት ተነሥቶም ከአረጋውያኑ ወደ አንዱ መጥቶ ስለ ሕሊናው ነገረው። አረጋዊውም ይታገሥ ዘንድ መከረው። በዚህ መንገድ እገዛ አግኝቶም ወደ በዓቱ ተመለሰ። ለኹለተኛ ጊዜም ወደ አረጋዊው መጥቶም እርዳታ አግኝቶ ወደ በዓቱ ተመለሰ። ውጊያው ለሦስተኛ ጊዜ ሲመጣበትም እንደገና  በሌሊት ወደዚያ አረጋዊ ሔደ። አረጋዊውም ወጣቱን አላሳዘነውም፤ እንደሚጠቅመው መክሮ ዘክሮ ነገረው እንጂ፤ እንዲህ ሲል፡- ምንም ዕድል እንዳትሰጠው። ሰይጣነ ዝሙት በፈተነህ በማናቸውም ሰዓት ወደ እኔ ና። ከዚያም ታጋልጠዋለህ። ስታጋልጠው ሸሽቶ ይሔዳል። ሰይጣነ ዝሙት እነዚህን አሳቦች የሚደብቃቸውንና የማይገልጣቸውን ሰው ያህል የሚፈትነው የለምና።" ያ እኁም በዚያች ሌሊት እርዳታ ፈልጎ ዓሥራ አንድ ጊዜ ወደ አረጋዊው እየተመላለሰ አሳቦቹን ተቃወማቸው። አረጋዊውም ሰይጣነ ዝሙቱ ከእርሱ እንደ ራቀ ነገረው። ነገር ግን ወደ በዓቱ በተመለሰ ጊዜ ውጊያው እንደ ገና መጣበት። ከብዙ ጊዜ ምልልስ በኋላም ያ እኁ አረጋዊውን:- አባ! ቸርነትህ ይደረግልኝ፡ እንዴት አድርጌ መኖር እንዳለብኝ ምከረኝ አለው። አረጋዊውም፡- ልጄ ፥ በርታ! እግዚአብሔር ፈቃዱ ከኾነ የእኔ ሕሊና ወደ አንተ ይመጣል። ከዚያም በኋላ ንጹሕ ሕሊና ይዘህ ትሔዳለህ እንጂ ከእንግዲህ ወዲህ በዚህ አትፈተንም' አለው። ይህን ብሎ ሲጨርስም እግዚአብሔር ሰይጣነ ዝሙቱን እስከ ወዲያኛው ከዚያ እኁ አራቀለት።” ስለዚህ ሰይጣነ ዝሙት መጥቶ ሲያሳስበን ወይም በሌላ መንገድ ያየነውንና የሰማነውን በሕሊናችን እንድናመላልሰው በሚፈልግበት ጊዜ ምንም ሳንሰለችና ዕድል ሳንሰጥ ወደ አበ ነፍሳችን መሮጥ እንዳለብን ያስረዳል። አበ ነፍሶችም በትዕግሥት ልጆቻቸውን የመርዳት መንፈሳዊ ግዴታ አለባቸው። ወላጆቻችንም ሊያግዙን ይችላሉ። የሐልዮ ኃጢአት በእኛ ላይ እንዲነግሥ ከሚያደርጉ ነገሮች ኣንዱ ለብቻና ሥራ ፈት መኾን ነው። ሥራ ፈትተን ለብቻችን ስንኾን ሰይጣን መጥቶ ያንን ኃጢአት በደንብ እንድናስብበት፣ ተግብረው ተግበረው ይለናል። ልክ ለሔዋን በለስን የምታስጎመጅ አድርጎ እንዳሳያት፥ በእኛም የማስተዋል ሕሊናችንን አጣምሞ ከዚያ ኃጢአት ስለምናገኘው ደስታ ያሳስበናል። “ሥራ ያጣ መነኩሴ ቆቡን ቀድዶ ይሰፋል” የተባለው መነኰሴ ሥራ ላለመፍታትና ከሓልዮ ኃጢኣት ለመራቅ ሲል ይህን ስለሚያደርግ ነው። ስለዚህ ዝም ብለን መቀመጥ አይገባንም። ይልቅስ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በመሳተፍ፣ ሌሎች በጎ ሥራዎችንም በመሥራት እንጠመድ። በዚህ ከተጎዱት ሰዎች መካከል አንዱ ነቢዩ ዳዊት ነው። ነቢዩ ዳዊት ወጣት ኾኖ በጎችን በሚጠብቅበት፣ ለሳኦል ጋሻ ጃግሬው ኾኖ በገና እየደረደረ በሚያገለግልበት፣ ሳኦል በምቀኝነት ተነሥቶበት በሚያሳድደው፣ ወደ ንግሥናው መጥቶ መንግሥቱ እስከ ተደላደለ ጊዜ ድረስ በዝሙት አልወደቀም ነበር። መንግሥቱ ተደላድሎ ከተመሠረተ፣ ክብሩ ከጨመረ በኋላ ግን ሥራ ፈትቶ በሰገነት ላይ ሲመላለስ የኦሪዮን ሚስት ቤርሳቤህን ስትታጠብ ተመለከታት። ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ፡- “ሰውነት ሥራ ሲፈታ፥ ሕሊናም ሥራ ይፈታል” እንዳለው፥ ንጉሥ ዳዊት ሥራ ፈትቶ ስለ ነበረም በቀላሉ በነቅዓ ሐልዮ ሳያበቃ ስለ እርሷ በማሰብ ወደ ሐልዮ ኃጢኣት ገባ። ስለዚህም “መልእክተኞች ልኮ አስመጣት፣ ወደ እርሱም ገባች፥ ከርኩሰትዋም ነጽታ ነበርና ከእርስዋ ጋር ተኛ" (2ኛ ሳሙ.11፥4)። በመኾኑም ራሳችንን ሰይጣን ወደ ሕሊናችን የሚያስገባውን የሐልዮ ኃጢአትን ከላይ በጠቀስናቸው መንገዶች በማራቅ፥ ንጽሕናችንን ጠብቀን ከሴት ከወንድ ርቀን እስከ ጋብቻ ድረስ መጽናት ይኖርብናል። አንዳንድ ጊዜ በሕልማችን ሩካቤ ስንፈጽም ልናይ እንችላለን። በዚህ ጊዜ እኛ ራሳችን ቀን ላይ ያሰብነው አሳብ አለመኾኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። በቀን ያሰብነው ሌሊት ቀጥሎ ከኾነ ከአበ ነፍስ ጋር ተነጋግሮ አሳቡን ማራቅ፣ ከዚያ ውጭ ግን ወጣቶች በመኾናችንና “ፒቱታሪ” የተባለው ዕጢ የዘር ፈሳሽ ማመንጨቱና አንዳንድ ጊዜ በራሱ ተስፈንጥሮ ስለሚወጣ በዚህ መነሻነት ወደ ሌላ ኣሳብ እንዳንሔድ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። (ገብረ እግዚአብሔር ኪደ  ከተጻፈው #ትንሿ_ቤተክርስቲያን መጽሐፍ - ገጽ 161-163)
1 30712Loading...
02
Media files
6932Loading...
03
ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡- ዓርብ :-ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል። በዚህ እለት ቤተ ክርሰቲያን በክርስቶስ ደም መመስረቷ ይነገራል።ክርስቶስ ስለ እርሷ እራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አጽንቶ በትንሳኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል የቤተክርስቲያን እራሷ መሰረቷ ክርስቶስ መሆኑን በስፋት እና በምልዐት ይሰበካል።
5881Loading...
04
Media files
6600Loading...
05
ሐሙስ -  [ አዳም ሐሙስ ] አዳም ማለት ትርጉሙ ፩ኛ.  የሰው ሁሉ አባት ፣ የሥጋው ተፈጥሮ ከአፈር ከመሬት ስለሆነ አዳም መባልን ከአዳም ወስዷል፡፡ [ ዘፍ ፪፥፲፤ ፲፱፥፳፯ ] ፪ኛ.  አዳም ማለት እንሰሳዊና መልአካዊ ሁለት ባሕርያት ስላሉት በሥጋው መዋቲ፣ ድኩም፣ ፈራሽ፣ በስባሽ፤ በነፍሱ ነባቢ፣ ልባዊ፣ ሕያው፣ ባለ አእምሮ ይባላል፡፡ [ዘፍ ፪፥፯] ፫ኛ. አዳም በ፮ኛ ቀን መጀመሪያ ከምድር የፈለቀ የሰው ሁሉ ምንጭ ስለሆነ፤ በዘር በሩካቤ ከእርሱ እየተቀዳ ሞትና መቃብር የሚጠጡት ምድራዊ ሰው ሁሉ በእርሱ ስም በምንጩ ስም አዳም አዳሜ ይባላል፡፡ [ዘፍ ፫፥፲፱] ስለዚህም አዳም የመጀመሪያ ሰውና የሰው ሁሉ አባት ነው፤ በ፮ኛው ቀን የተፈጠረ የሰው ሁሉ ምንጭ ስለሆነ የሰው ዘር ሁሉ ከእርሱ ተገኝቷል፡፡ በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው የተስፋ ቃል ስለመፈጸሙ፤ [ዘፍ. ፫÷፲፭]  አዳም ከነልጆቹ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻ ስለመውጣቱ ይታሰብበታል፡፡ ክርስቶስ በተነሳበት በአምስተኛው ቀን ሐሙስ  አዳም ይባላል፤ ጌታችን አዳምን ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ  አድንሃለሁ ብሎ  ቃል ገብቶለት  እንደነበር በቀሌምንጦስ ተጽፏል፡፡ አዳምና ሔዋን በገነት ፯ ዓመት ከቆዩ በኋላ ትእዛዙን በመተላለፋቸው ከኤደን ገነት አስወጣቸው [ ኩፋ.፬፥፲፮፤ዘፍ.፫፥፳፫ ]«ብዙ ተባዙ» ያለው ቃል እንዳይቀር በምድር ላይ ወርደው ልጆችን ወለዱ ይላል፡፡ የተወለዱትም ልጆችም በቁጥር ፷ እንደሆኑ [ ፩መቃ. ፳፰፥፮] የተወለዱት ልጆች ደጎችና ክፉዎች እንደ ነበሩ በአቤልና በቃየል ታውቋል። [ ዘፍ. ፬፥፰]። አዳም በዚህ ዓለም ፱፻፴ ዓመት ኑሮ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በ፵፻፭፻፸ ሚያዚያ ፮ ዐርፏል፡፡
4931Loading...
06
Media files
5070Loading...
07
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን   ክርስቶሰ ተንሥአ እሙታን በዐቢይ ኅይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዐዞ ለአዳም ሰላም  ****   እም ይእዜሰ ኮነ  ****   ፍሥሐ ወሰላም   ✍ "የትንሣኤው ምሥጢር"✍ ⚜️ረቡዕ  ⚜️⚜️⚜️ አልአዛር ⚜️⚜️⚜️ "ጌታዬ አምላኬ" (ዮሐ፳:፳፰) መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚል አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመቅደላዊት ቀጥሎ በዝግ ቤት ሳሉ ከሐዋርያው ከቶማስ ውጭ አንድ ጊዜ ተገልጦላቸው ነበር ፡፡ የሐዋርያውን የቶማስን ጥያቄ ሊመልስ ፤ እምነት ያሳድግ እና አምላክነቱን ይገልጥ ዘንድ ለሁለተኛ ጊዜ ከስምንት ቀን በኋላ ተገልጦላቸኋል፡፡ "ከስምነት ቀን በኋላም ደቀ መዛሙርቱ ደግመው በውስጥ ነበሩ ፤ ቶማስም ከእነርሱ ጋር ነበረ፡፡ ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ ፤ በመካከላቸውም ቆሞ ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው፡፡ ከዚያም በኋላ ቶማስን ፡- ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ እጅህንም አምጣና በጎኔ አግባው ፤ ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን አለው፡፡ ቶማስም ፡- ጌታዬ አምላኬም ብሎ መለሰለት፡፡ ኢየሱስም ፡- ስለ አየኸኝ አምነሃል ፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው አለው፡፡" እንዲል፡፡ (ዮሐ፳፡፳፮-፳፱) ሐዋርያው ቶማስ አምላኬ ጌታዬ ያለበት ምክንያት በዋናነት ጣቱን ወደ ጎኑ ባስገባት ጊዜ ከእሳት እንደገባ ጅማት ሆናለችና መዳሰሱን ሲያይ ጌታዬ አለ ፤ ማቃጠሉን ሲያይ ደግሞ አምላኬ አለ፡፡ ገቦ መለኮትን የዳሰሰች እጅ በሕያውነት ትኖራለች፡፡ በሕንድ ሀገር ከታቦት ጋር ከመንበር ላይ ነው የምትኖር በዓመት በዓመት በእመቤታችን በዓል በአስተርእዮ ሊያጥኑ ሲገቡ የሚሾመውን ወጥታ ቀኝ እጁን ትይዘዋለች ዓመት አገልግሎ ያርፋል ፤ በዓመቱ ሊያጥኑ ሲገቡ ትይዛቸዋለች እንዲህ እንዲህ እያለች ትኖራለች፡፡(ወንጌል ቅዱስ ገጽ፮፻፬) ሳናይ ልናምን እንደሚገባ እና ማመናችን ብፁአንም አንደሚያሰኘን ከገለጠለት በኋላ ቁጥር ፴ ላይ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፉ(በሌሎች ወንጌላት እና በተአምረ ኢየሱስ የተጻፉ) ብዙ ታምራትን እንዳደረገ ይህ ግን እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ (የባሕርይ አምላክ ነው) ብሎ ለማመን እንደተጻፈ ገልጦልናል፡፡ (ዮሐ፳፡፴፩) የሃያኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሊቅ የነበሩት መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ ስለ አምላካችን ስለ ኢየሱስ ክርሰቶስ ባሕርይ በጥልቀት ለካቶሊኩ መነኩሴ ዶክተር አባ አየለ በመለሱበት መጽሐፍ ስለ አምላክነቱ በግልጽ በአንድ ኃርፍተ ነገር ጽፈውልናል፡- "ክርስቶስ ፍጹም ሰው የሆነ ፍጹም አምላክ ነው"(መድሎተ አሚን ገጽ ፻፴፬)  "የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት " የሰው ልጆች በተለይ ቅዱሳን አማልክት ዘበጸጋ ይባላሉ ፤ ሙሴ በፈርዖን ላይ አምላክነትን ቢሾም በጸጋ ነው ፤ እናንተን አማልክት ናችሁ አልኋችሁ ግን ትሞታላችሁ የተባሉት እግዚአብሔር የመረጣቸው ቅዱሳኑን መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት ግን የባሕርይው ነው፡፡ እኛ ሁላችን የእግዚአብሔር ልጆች ብንባል በጸጋ ነው ፤ እርሱ ግን እግዚአብሔር ልጅ ሲባል በባሕርይ ልጅነት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት የገለጠ የእውነት ምሥክር ነው፡፡ ፩. አምላክነቱ በፈጣሪነቱ ተገልጧል፡፡ (ዘፍ፩፡፩ እና ዮሐ፩፡፫) ፪. አምላክነቱ በሥራው ተገልጧል፡፡ (ዮሐ፭፡፴፮) ፫. አምላክነቱ በትምህርቱ ተገልጧል፡፡ (ማቴ፯፡፳፱)  ፬. አምላክነቱ በፈዋሽነቱ ተገልጧል፡፡ (ሉቃ፬፡፴፮) ፭. አምላክነቱ ኃጢአትን በማስተስረይ ተገልጧል፡፡ (ሉቃ፭፡፳)  ፮. አምላክነቱ ሙታንን በማስነሳቱ ተገልጧል፡፡ (ሉቃ፯፡፲፯)  ፯. አምላክነቱ በመድኃኒትነቱ ተገልጧል፡፡ (ማቴ፰፡፩)  ፰. አምላክነቱ ዲያብሎስን በመሻሩ ተገልጧል፡፡ (ማቴ፰፡፲፮)  ፱. አምላክነቱ ሁሉን በማሸነፉ ተገልጧል፡፡ (ዮሐ፲፯፡፪)  ፲. አምላክነቱ ሁሉን በመግዛቱ ተገልጧል፡፡ (ማቴ፰፡፳፮)  ፲፩. አምላክነቱ ሞትን ድል በመንሳቱ ተገልጧል፡፡ (ሉቃ፯፡፲፬)  ፲፪. አምላክነቱ በሁሉ አዋቂነቱ ተገልጧል፡፡ (ዮሐ፩፡፵፰)  ፲፫. አምላክነቱ በሁሉ ቦታ በመኖር ተገልጧል፡፡ (ማቴ፲፰፡፳)  ፲፬. አምላክነቱ ሁሉን በማዳኑ ተገልጧል፡፡ (ማቴ፲፰፡፲፩)  ፲፫. አምላክነቱ በሁሉ ቦታ በመኖር ተገልጧል፡፡ (ማቴ፲፰፡፳)  ፲፮. አምላክነቱ በእግዚአብሔርነቱ ተገልጧል፡፡ (ሐዋ፳፡፳፰)  በአጠቃላይ ይህቺ ዕለት ቶማስ በመባሏ ለእነዚህ ሁሉ የትንሣኤው ምሥጢር ሕያው ምስክር ትሆን ዘንድ አባቶቻችን እንድናስባት አደረጉን፡፡ ወዳጆቼ በዋናነት ይህች ቅድስት ዕለት ወይም ሠሉስ የሐዋርያው ቶማስ በአምላካችን ፍቅር መማረክ ፤ ትንሣኤውን ማመኑ ፤ ሳያዩ የሚያምኑ ክርስቲያኖች የሚያገኙትን ብፅዕና ፤ የአምላካችን ተአምራቶችም ሆኑ ትምህርቶች በዚህ መጽሐፍ ብቻ የተጻፉት ብቻ እንዳልሆኑ ፤ ከሁሉ በላይ ኢየሱስ ክርስቶስን የባህርይ አምላክ ብሎ ማመን የተገባ እና መጽሐፍትም የተጻፉበት ዓላማ መሆኑን እንማራለን፡፡ ⚜️⚜️⚜️፫. ረቡዕ አልዓዛር ይባላል ⚜️⚜️⚜️ በዚህች ዕለት አምላካችን ትንሣኤ እና ሕይወት መሆኑን በተግባር በታላቅ ተአምራቱ ማሳየቱን የምናስብበት በመሆኑ ስያሜው አልዓዛር ተብሏል፡፡ የአራት ቀን ሬሳን ሕይወት ይዘራበት ዘንድ የፍቅር አምላካችን በሞት በሚፈልጉት በጠላቶቹ ሰፈር ተመላለሰ ፤ የደቀ መዛሙርቱን ክልከላ አልሰማም ፤ የመንገዱ ርቀት አላዘለውም ግን በፍቅር ስለ ፍቅር ሰው ሁሉ ተስፋ የቆረጠበትን ወዳጁ አለዓዛርን ከሞት ሊያስነሳ ወደ ቢታኒያ በፍቅር ተጓዘ ፤ እውነት ነው ሞት ለታወጀብን ለእኛ ለመመላለሱ ምሳሌ ነው ፤ ሞት ድል ያላደረገው የትንሣኤውን ጌታ አምላካችንን በእውነት እንደተነሳ እንድናስብ ቤተክርስቲያን በዚህ ዕለት በአልዓዛር አንጻር ትንሣኤ እና ሕይወት እርሱ እንደሆነ ታስተምረናለች፡፡ ይቆየን ... ወስብሐት ለእግዚአብሔር
5591Loading...
08
💦💦     💦ማክሰኞ ፪ኛ ቶማስ ይባላል 💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦 እንደ ኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ን በዓላት ቀኖና መሰረት ከትንሣኤ በኋላ ያለችው ዕለተ ማክሰኞ "ቶማስ" በመባል ይጠራል። ቶማስ ሐዋርያ ሲሆን፣ ቶማስ ማለት ‹‹ፀሐይ›› ማለት ነው።ከክስቶስ ትንሣኤ በኋላ ቅዱስ ቶማስ በጦር የተወጋ ጎኑን፤ በቀኖት የተቸነከረው እጁንና እግሩን ካላየሁ አላምንም በማለቱ ክርስቶስም «ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤እጅህንም አምጣና ወደ ጎኔ አግባ፤ እመን እንጂ ተጠራጣሪ አትሁን» ብሎታል። ቶማስም «ጌታዬ አምላኬም»፤ ብሎ በመለሰ ጊዜ ጌታችን ኢየሱስም «ስለ አየኸኝ አመንህን? ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓንስ ናቸው» አለው (ዮሐ ፳፥፳፯-፳፱)፤ ቶማስ የጌታን ፍቅር ተገንዝቦ ትንሣኤውን ስላመነ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዕለቱን ቶማስ ብላ ታስበዋለች። ዲዲሞስ የተባለ ከአሥራ አንዱ ደቀ መዛሙር አንዱ ቶማስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዝግ ቤት ገብቶ «ሰላም ለሁላችሁ ይሁን» ባላቸው ጊዜ ከእርሳቸው ጋራ አልነበረም»። ከ፲፪ቱ ሐዋርያት አንዱ (ማቴ. ፲፥፪-፫) ቶማስ በአራማይክ ዲዲሞስ በግሪክ መንታ ማለት ነው፤ (ዮሐ. ፳፥፳፬)፡፡ ቶማስ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በፋርስና በሕንድ ወንጌልን እንዳስተማረ ይነገራል። ለቶማስ ጎኑን እንዲዳስስ የፈቀደው ለሌሎችም ቅዱሳን ሐዋርያት የተቸነከረውን እጅና እግሩን ያሳየው ካህናት ሥጋውና ደሙን እንዲፈትቱ ነው፤ ዮሐንስም በእጃችን ዳሰስነው ብሏል፤ (ሉቃ. ፳፬፥፴፱)፡፡ ለማርያም መግደላዊት ግን የተነሣ ዕለት አትንኪኝ ማለቱ ለሴቶች ሥጋውን ደሙን መፈተት አልተፈቀደም ሲል ነው ብለው ሊቃውንት ያትታሉ፤ «አትንኪኝ፤ ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሂጅና፡- ወደ አባቴ÷ ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬ÷ ወደ አምላካችሁም አርጋለሁ አለ ብለሽ ንገሪአቸው» አላት፤ (ዮሐ. ፳፥፲፯)። መለኮቱን የዳሰሰች እጁ በሕይወት ትኖራለች፤ በሕንድ ሀገር ከታቦት ጋር በመንበር ላይ ትኖራለች። የሐዋርያ ቶማስ መታሰቢያ በዳግመ ትንሣኤ ላይ የሚነሳ ቢሆንም አባቶች በዓል ላይ በዓል እንዳይደራረብ ብሎ ከትንሣኤ በኋላ ባለው በዕለተ ማግሰኞ ቶማስ ተብሎ እንዲጠራ ስርዓት ሰርቶልናሉ። የአባቶቻችን በረከት ይደርብን በእውነት። በዓሉንም በዓለ ደስታና በዓለ ፍስሐ ያድርግልን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር
3101Loading...
09
🧚🧚🧚🧚 በዓሉ ከቤት ዉጭ ንፍሮ እየተበላለምን ይከበራል🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚 🌿👉 በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ትዉፊት መሰረት ሐና እና ኢያቄም ከአይሁድ ለማምለጥ ተሰደዉ በአድባረ ሊባኖስ ስር እመቤታችንን ወለዱ፡፡ በወቅቱ ከቤት የወጡት ለሽሽት ነበርና ስንቅ ስላልያዙ ምግባቸዉ ‹‹ንፍሮና ጥራጥሬ›› ነበር፡፡ይህንን ትዉፊት በመያዝ በዓሉ ከቤት ዉጭ ንፍሮ እየተበላ ይከበራል፡፡ነገር ግን በበጎ ነገሮች ሰበብ ክፉ ዓላማዉን ማስፈጸም የሚፈልገዉ ዲያቢሎስ በማር መካከል መርዝን ከሚጨምርባቸዉ መንፈሳዊ በዓላት አንዱ የግንቦት ልደታ (የእመቤታችን የልደት በዓል) ነዉ፡፡ በዚህ ዕለት አንዳንዶች ባለማወቅ ሌሎች ደግሞ በድፍረት ‹‹ለአድባር አዉጋር ነዉ፤ ቆሌዉን ለመለመን ነዉ›› እያሉ ለማያውቁት አምልኮ ንፍሮ የሚበትኑ፣ ቡና የሚረጩ፣ ቅቤ የሚቀቡ፣ የከብት ደም የሚያፈሱ አሉ፡፡ እውነታው እነዚህ በእርግጥም ጣዖት አምላኪዎች ናቸው፡፡ እኛ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ግን እነዚህን የሃይማኖት ለዋጮች ሥራቸውን እንጸየፋለን፡፡ ስለሆነም ከእንደዚህ ዓይነቱ ባዕድ አምልኮ በመለየት ይህንን ታላቅ በዓል በተገባና በተረዳ ነገር ልናከብረው ይገባል፡፡ . 🌿👉 ቤተክርስቲያናችን በሠራችልን ሥርዓት መሰረት በቀናች በተዋሕዶ እምነት ሆነን ፤ በምህረቱ የጎበኘንን አምላካችንን ብቻ እያመለክን ፤ የድኅነታችን ምክንያት የሆነችውን ድንግል ማርያምንም እያመሰገንን ልናከብረው ይገባል፡፡ . ✞❤️✞❤️✞አምላካችን እግዚአብሔር ከእመቤታችን ረድኤት በረከት ይክፈለን ፤ አ ሜ ን !!! ✞❤️✞❤️✞ . ✞❤️✞❤️✞ የእግዚአብሔር ቸርነት ፣ የንጽሕተ ንጹሐን ፣ የቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን ፤ አ ሜ ን !!! ✞❤️✞❤️✞ . ☘️🌼🌹💚💛❤️❤️💛💚🌹🌼☘️
3212Loading...
10
Media files
3042Loading...
11
Media files
3282Loading...
12
🍂  ሰኞ  ✨ #ማዕዶት ✨   ዐደወ = ተሻገረ     ማዕዶት = መሻገር                                 ✨ዛሬ ሰኞ የፋሲካ ማግስት ማዕዶት የሚል ስያሜ በቤተ-ክርስቲያን ተሰጥቶታል ትርጓሜውም መሻገር ማለት ነው። እስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት ነጻ የወጡበትን ቀን ነው ፋሲካ ብለው  የሚያከብሩት እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ባሕረ ኤርትራን ከፍለው እስራኤላውያን ተሻግረው ፈርኦንን ከነሰራዊቱ አስጥመው ወደ ዘለአለማዊ እረፍት ምድር ከነዓን ገብተዋል ይኽ ምሳሌ ነው ሙሴ የክርስቶስ በትር የመስቀል ባሕረ ኤርትራ የሲኦል ፈርኦን እና ሰራዊቱ የዲያብሎስ እስራኤላውያን የምዕመናን ምሳሌ ናቸው ክርስቶስ በመስቀል ተሰቅሎ ሲኦልን ከፍቶ አዳምን እና ልጆቹን አሻግሮ ዲያቢሎስን በሲኦል አስጥሞ ምዕመናንንበተድላ ገነት በምስጋናና በእልልታ አኑሯቸዋል።  በዚያምጊዜ የእስራኤል ልጆች ይህንን መዝሙር ለእግዚአብሔር  ዘምረዋል እንዲህም ብለው ተናግረዋል ። #በክብር_ከፍ_ከፍ_ብሎአልና_ለእግዚአብሔር_እዘምራለው ፤ #ፈረሱንና_ፈረሰኛውን_በባሕር_ጣለ ።     .     .     . ✨የፈርዖንን ሰረገሎች ሠራዊቱንም በባሕር ጣላቸው።                  ( ዘጸ 15 ፥ 1 , 4 )    👉 በመንገድም ይጠብቃቸውም ዘንድ መጋቤ ብሉይ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ይራዳቸው ነበር። ( ዘጸ 23 ፥ 19 ) 🍀 ይህንንም በዓል የፋሲካ ( የመሻገር ) በዓል ብለው በየአመቱ ያከብሩ ነበር እሥራኤላውያን። ✨ ከግብጽ ነጻ ቢወጡ ፤ ፈርኦን ከሠራዊቱ በባሕር በሲጥም ፣ የኤርትራን ባሕር ተሻግረው ከነዓን ቢገቡም፤   #ዘላለማዊ_ዕረፍትን_ግን_አላገኙም ። የሲኦልን ባሕር አልተሻገሩም ፤ ከዲያብሎስም አገዛዝ ነጻ አልወጡም።    🍂    +    +     +     +   +   🍂 ዘመኑ ሲደርስ በመጀመሪያው ፋሲካ በምሳሌ የተገለጸው        #አማናዊው_ፋሲካችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ +          እውነተኛውን መሻገር አሻገረን።  +         ከሞት ወደ ሕይወት ፣ +          ከኃጢአት ወደ ጽድቅ ፣    +     ከጨለማ ወደ ብርሃን መለሰን ።   ✨   ከግብጽ ከመሻገራቸው አስቀድሞ ስለ ታረደው ስለ ፋሲካው በግ አማናዊው ፋሲካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ ታርዶ ከሲኦል አንደ ተሻገርን ቅዱስ ጳውሎስ እንዲል አለ። " #ፋሲካችን_ክርስቶስ_ታርዷልና"         ( 1ኛ ቆሮ  5 ፥ 7 ) 🙏 ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል                  ድል መንሣትን       ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን 🙏             ( 1ኛ  ቆሮ 15 ፥ 55 - 57 )
5432Loading...
13
እንኳን አደረሳችሁ የመንፈሳዊ ጉባኤ አባላት እና ከልቤ ለምወዳችሁ የሰንበት ትምርትቤት አባላት አብረን በጸሎት በስግደት በምጽዋት በአንድ ልብ ሆነን ይህንን ጻም ተሻግረናል ልዩ ጊዜ ነበር የመንፈሳዊ አንድነታችንን እያጠነከርን ልንቀጥል ይገባል ። ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ እንደተነሳ እኛም ኃጢያታችንን ንስሀ ገብተን ድል ልናደርገው ይገባል በዚህ ጻም ንስሀ ገብታችሁ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ለተቀበላችሁ ለእናንተ ትንሳኤ በዓል ልዩ ነው። በረከታችሁ ይደርብን ።ለዚህ ክብር ለማግኘት መንገድ ላይ ያላችሁ አምላክ መገዳችሁ ይባርክ ይቀድስ ለዚህ ክብር ያብቃችሁ ልዩጊዜ ነበር አያችሁት ጸሎት ነገሮችን ሁሉ ይለውጣል አዲስ ሰውም ያደርጋል ከሌላ እምነት ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለተመለሳችሁ እህት ወንድሞች እንኳን ደስ አላችሁ ። ከእናንተ ጋር በዚህ መንፈሳዊ ጉባኤ አብረን በመማማራችን እጅግ ብዙ ለውጥ አግኝተንበታል አሁን ተግተን ህይወታችንን ለሱ ለፈጣሪያችን ልናስገዛ ይገባል እንኳን አደረሳችሁ ከልብ ነው የምወዳችሁ ሰላም ሁሉ እመኛለው መልካም የትንሳኤ በዓል
4290Loading...
14
💥💥💥💥💥💦💦💦💦💦💥💥💥💥💥💦💦💦💦💦💦💥💥💥💥💥💥 #እንኳን_ለጌታችን_መድኅኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_በዓለ_ትንሳኤ_በሰላም_አደረሳችሁ ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ አሰሮ ለሰይጣን፤ አግዐዞ ለአዳም፤ ሠላም፤ እምይዕዜሰ፤ ኮነ፤ ፍስሐ ወሰላም፡፡ "ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነስቷል እንጂ በዚህ የለም:: 'የሰው ልጅ በኃጢአተኞች እጅ አልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል: በሦስተኛውም ቀን ሊነሣ ግድ ነው' እያለ ገና በገሊላ ሳለ ለእናንተ እንደተናገረ አስቡ::" (ሉቃ. ፳፬፥፭-፰) #_ትንሣኤ_ዘክርስቶስ_የክርስቶስ_ትንሳኤ ☞ ሦስት መዓልት እና ሦስት ሌሊት በመቃብር? ☞ ሦስት መዓልት እና ሦስት ሌሊት የሞላው እንዴት ነው? ☞ እንዴት ተነሣ? ☞ ለምን በአዲስ መቃብር ተቀበረ? ☞ እንዴት በዝግ መቃብር ተነሣ? ☞ መቃብሩን ማን ከፈተው? ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድኅነተ ዓለምን በመስቀል ላይ ከፈጸመ በኋላ በአካለ ሥጋ ወደ መቃብር ወረደ ÷ ይኸውም በመቃብር ፈርሶ በስብሶ መቅረትን ሊያስቀርልን ነው፡፡ በአካለ ነፍስ ደግሞ ወደ ሲኦል ወረደ÷ ይኸውም በሲኦል ለነበሩ ነፍሳት ነፃነትን ይሰብክላቸው ዘንድ ነው፡፡ መለኮት፥ በተዋሕዶ፥ ከሥጋም ከነፍስም ጋር ነበረ፡፡ ለዚህ ነው፥ መቃብር ሥጋን ሊያስቀረው ያልቻለው፤ ሲኦልም ነፍስን ማስቀረት አልተቻለውም፡፡ ቅዱስ ዳዊት፡- « ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተዋትም» ያለው ይኽንን ታላቅ ምሥጢር በትንቢት ቃል ሲናገር ነው፡፡ መዝ ፲፭÷፲፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስም፡- «ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር (ወደ አብ÷ ወደ ራሱና ወደ መንፈስ ቅዱስ) እንዲያቀርበን፥ እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት (ስለ ሰው ልጆች ኃጢአት ተላልፎ በመሰጠት) ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ (በፈቃዱ ነፍሱን ከሥጋው ለየ)÷ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ÷ (ያን ሥጋ ነፍስ እንድተለየችው መለኰት አልተለየውም)÷ በእርሱም ደግሞ (መለኰት በተዋሐዳት ነፍስ) ሄዶ በወኅኒ ለነበሩት ነፍሳት ሰበከላቸው፤» ብሏል። ✞ #ሦስት_መዓልት_እና_ሦስት_ሌሊት_በመቃብር✞ ጌታችን በከርሰ መቃብር የቆየው ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት ነው፡፡ «ሥጋዬ ደግሞ በተስፋ ታድራለች፤» የሚለው ቃለ ትንቢት የሚያረጋግጥልን ይኽንኑ ነው፡፡ መዝ ፲፭፥፱፡፡ ምሥጢራዊ ትርጉሙም «ወደ መቃብር የወረደ ሥጋዬ በተስፋ ትንሣኤ ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት በመቃብር አደረ፤» ማለት ነው፡፡ ተስፋ ትንሣኤውም በተዋሕዶ ከሥጋ ጋር ወደ መቃብር የወረደ መለኰት ነው፡፡ ነቢዩ ሆሴዕም፡- «ኑ÷ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፤ እርሱ ሰብሮናልና÷ (በሞተ ሥጋ ላይ ሞተ ነፍስን ጨምሮ የፈረደብን እርሱ ነው)÷ እርሱም ይፈውሰናል፤ (መርገመ ሥጋን መርገመ ነፍስን አስወግዶ ከሞት ወደ ሕይወት ያሸጋግረናል)፤ እርሱ መትቶናል÷ እርሱም ይጠግነናል፡፡ ከሁለት ቀን በኋላ ያድነናል፤ በሦስተኛውም ቀን ያስነሣናል፡፡» በማለት ትንሣኤ ክርስቶስ በሦስተኛው ቀን መሆኑን አረጋግጧል፡፡ ሆሴ ፮÷፲፪፡፡ ይልቁንም ጌታችን ራሱ በመዋዕለ ሥጋዌው፡- ከሽማግሌዎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ፥ በሦስተኛውም ቀን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀመዛሙርቱ በግልጥ ነግሯቸዋል፡፡ ማቴ ፲፮÷፳፩፡፡ በገሊላም ሲመላለሱ፡- «ወልደ ዕጓለ እመሕያው ክርስቶስ በሰዎች እጅ አልፎ ይሰጥ ዘንድ አለው÷ ይገድሉትማል÷ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል፤» ብሏቸዋል፡፡ ማቴ ፲፯÷፳፡፡ ጻፎችና ፈሪሳውያንም ምልክት በጠየቁት ጊዜ፡- «ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል÷ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም፡፡ ዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ፥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደነበረ÷ እንዲሁ የሰው ልጅ (ወልደ ዕጓለ እመሕያው ክርስቶስ) በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል፡፡» ብሏቸዋል፡፡ ማቴ ፲፪፥፴፰-፵። ✞ #ሦስት_መዓልት_እና_ሦስት_ሌሊት_የሞላው እንዴት_ነው? ✞ ጌታ በከርሰ መቃብር የቆየው ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት ነው፡፡ ይኽንንም ለመረዳት ዕብራውያን ዕለታትን እንዴት እንደሚቆጥሩ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ እኛ በሀገራችን የሌሊቱን ሰዓት መቁጠር የምንጀምረው ከዋዜማው ከምሽቱ አንድ ሰዓት ነው÷ የቀኑን ሰዓት መቁጠር የምንጀምረው ደግሞ ከማለዳው አንድ ሰዓት ጀምሮ ነው፡፡ የሌሊቱ ሰዓት የሚያ ልቀው ከማለዳው አሥራ ሁለት ሰዓት ሲሆን፥ የቀኑ ደግሞ ከምሽቱ አሥራ ሁለት ሰዓት ሲሆን ነው፡፡ የቀኑም የሌሊቱም ሰ ዓት ተደምሮ ሃያ አራት ሰዓት ይሆናል፡፡ ሁሉም ሰዓት ዕለቱን ይወክላል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው እሑድ ዕለት ከሃያ አራቱ ሰዓ ት በአንዱ ቢወለድ እሑድ ተወለደ ይባላል÷ ቢሞትም እሑድ ሞተ ይባላል፡፡ ዕለቱ በሚጀምርበትም ሰዓት ሆነ፥ በሚያልቅ በት ሰዓት፥ ድርጊቱ ቢፈጸም ያ ሰዓት እንደ አንድ መዓልትና እንደ አንድ ሌሊት ይቆጠራል፡፡ አውሮፓውያን አንድ ብለው ሰዓት መቁጠር የሚጀምሩት በእኛ አቆጣጠር ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ነው፡፡ እስከ ሃያ አራት ይቆጥሩና በእኛ አቆጣጠር ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ሲሆን ይጨርሳሉ፡፡ ሃያ አራት ሰዓት ሲሆን ዜሮ ይሉና እንደገና አንድ ብለው መቁጠር ይጀምራሉ፡፡ በሌላ አነጋገር ከሌሊት እስከ ሌሊት ይቆጥራሉ፡፡ አሜሪካውያን ደግሞ በእኛ ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ሲሆን አንድ ብለው ይጀምሩና በእኛ ከቀኑ ስድስት ሰዓት ሲሆን አሥራ ሁለት ብለው ይጨርሳሉ፡፡ ከዚያም በእኛ አቆጣጠር ከቀኑ ሰባት ሰዓት እንደገና አንድ ብለው ይጀምሩና በእኛ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ሲሆን አሥራ ሁለት ብለው ይጨርሳሉ፡፡ ዕብራውያን ግን ዕለትን መቁጠር የሚጀምሩት ከዋዜማው ማለትም በአውሮፓውያን ከአሥራ ሰባት ሰዓት÷ በአሜሪካውያን ከአምስት ሰዓት (P.M.) ÷ በእኛ ደግሞ ከምሽቱ አሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ ነው፡፡ ከዚህ ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ አሥራ አንድ ሰዓት ድረስ ሃያ አራት ሰዓት ቆጥረው አንድ ቀን ይላሉ፡፡ ከላይ እንደተገለጠው እያንዳንዱ ሰዓት የዕለቱን መዓልትና ሌሊት ይወክላል፡፡ በዚህ መሠረት ጌታችን ከመስቀል ወርዶ የተቀበረው ዓርብ ቅዳሜ ከመግባቱ በፊት ነው፡፡ ዓርብ ዕለቱ የሚጀምረው ከዋዜማው ሐሙስ በእኛ አቆጣጠር ከቀኑ አሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ ነው፡፡ ስለዚህ ጌታ የተቀበረው በዓርብ ሃያ አራት ሰዓት ክልል ውስጥ በመሆኑ እንደ አንድ መዓልትና ሌሊት ይቆጠራል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ዓርብ ከቀኑ አሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ እስከ ቅዳሜ ቀን አሥራ አንድ ሰዓት ያለው ነው፡፡ ሦስተኛው ደግሞ ቅዳሜ ከቀኑ አሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ እስከ እሑድ ቀን አሥራ አንድ ሰዓት ያለው ነው፡፡ ከዚህ በኋላ የሰኞ ምሽት ይገባል፡፡ ጌታ የተነሣው በሦስተኛው ቀን እሑድ መንፈቀ ሌሊት ነው።
4741Loading...
15
Media files
7793Loading...
16
Media files
6502Loading...
17
ይኽ የጌታችን ትሕትና ብዙዎችን አስደንቋል፤ ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንትም በቅዳሴያቸው ላይ “በይእቲ ሌሊት አኀዝዎ ወጸቢሖ ረበናተ አይሁድ ወሊቃነ ካህናት ምስለ ጲላጦስ መስፍን ወነበሩ ዐውደ ለኰ ንኖቱ…” (በዚያች ሌ ሊት ያዙት. በነጋም ጊዜ የአይሁድ መምህሮችና የካህናት አለቆች ከገዢው ከጲላጦስ ጋራ ሊፈርዱበት በዐደባባይ ተቀመጡ፤ እንደ ሌባ የኋሊት አሰሩት እንደ የዋህ በግ በፍቅር ተከተላቸው፤ ሊፈርዱበት በዐደባባይ ተቀመጡ፤ የመላእክት ሰራዊት በመፍራት የሚቆሙለትን በፊታቸው አቆሙት፤ ክፉ ባሪያ ርሱን ያልበደለውን ፊቱን በጥፊ ይመታው ዘንድ እጁን አጸና፤ የመላእክት አለቆች በፍጹም ድንጋፄ ለሚሰግዱለት ለርሱ በትዕቢት ይሰግዱ ዘንድ አጐነበሱለት) በማለት ዐርብ ጠዋት አይሁድ ጌታን ወደ ፍርድ ዐደባባይ እንዴት እንዳቀረቡት በስፋት አስተምረዋል፡፡ ጌታ ከመወለዱ አንድ ሺሕ ዓመት አስቀድሞ ጌታችን በንጉሥ ዳዊት ዐድሮ በመዝ ፳፩፥፲፰ ላይ “ልብሶቼን ለራሳቸው ተከፋፈሉ፥ በቀሚሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ” በማለት ያናገረው ትንቢት ሊደርስ ሊፈጸም ጭፍሮች ጌታን ከሰቀሉት በኋላ ልብሶቹን ወስደው ለእያንዳንዱ ጭፍራ አንድ ክፍል ኾኖ በአራት ሲከፋፍሉት ከላይ ዠምሮ ወጥ ኾኖ የተሠራ ነበረ እንጂ የተሰፋ ያልነበረው እጀ ጠባቡን ደግሞ በመውሰድ ርስ በርሳቸው ለማን እንዲኾን በርሱ ዕጣ እንጣጣልበት እንጂ አንቅደደው ተባባለዋል፤ ይኽቺውም ቀሚሱ ሰብአ ሰገል ያመጡለት ሲያድግ የምታድግ ዐሥራ ኹለት ዓመት ደም ሲፈስሳት የነበረችው ሴት የተፈወሰችበት ገባሪተ ተአምራት ነበረች (ማቴ ፪፥፲፩፤ ፱፥፳)፡፡ አይሁድ ይኽነን ማድረጋቸው ለጊዜው “ኹለት ልብስ ያለው ለሌለው ያካፍል” (ማቴ ፭፥፵) በማለት ኹለት ልብስ አታኑሩ በማለት የሚያስተምረው የርሱ ልብስ ለአራት ቤት ጭፍራ በቃ ለማለት ለመዘበት ሲኾን ፍጻሜው ግን ልብስ የወንጌል ምሳሌ አራት ዕጣ መጣጣላቸው ወንጌል አራት ወገን ኹና ለመጻፏ፤ አለመቅደዳቸው በምስጢር አንድ የመኾኗ፤ አንድም አራቱ ኹሉ ባንዲቱ ዕጣ መጣጣላቸው ወንጌል አራት ክፍል ስትኾን አንድ ሕግ ለመኾኗ ምሳሌ፤ አንድም “አንቅደድ” ማለታቸው ትስብእቱን ከመለኮቱ ሳንለይ እንመን ሲያሰኛቸው ነው በማለት መተርጒማነ ሐዲስ ያመሰጥራሉ (ማቴ ፳፯፥፴፭፤ ማር ፲፭፥፳፬፤ ሉቃ ፳፫፥፴፬፤ ዮሐ ፲፱፥፳፫)፡፡ ቊጥራቸው ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት የሚኾን ኤልሳቤጥ፣ መልቴዳ፣ በርዜዳ የሚባሉት በጻፉት የጌታን ሕማማቱን በሚናገረው መጽሐፍ ላይ ይኽነን ሲገልጹ “ወእምዝ አዕተቱ አልባሲሁ ወአልበስዎ ሜላተ ልብስ…” (ከዚያም ልብሶቹን ገፍፈው የመንግሥት ልብስ የሚኾን ነጭ ሐር የካህናት ልብስ የሚኾን ቀይ ሐር ሕብራቸው ቀይና ጥቁር የሚኾን ልብስ አለበሱት፤ የአጣቢ ሳሙና ማንጻት የማይቻለው እንደ መብረቅ የሚያንጸባርቅ እንደ በረድ የኾነ ነጭ ልብስ የሚለብስ ሲኾን፤ ለኪሩቤል የመብረቅ ልብስን ለሱራፌል ግርማ ያለው ልብስን የሚያለብሳቸው ርሱን እንደዚኽ በምድር በመዘባበት ቀይ ሐርና ነጭ ልብስ አለበሱት) በማለት አስተምረዋል፡፡ ልዑል አምላክ ዘመኑ ሲፈጸም ስለሚቀበላቸው ሕማማተ መስቀል አስቀድሞ በነቢዩ ዳዊት ዐድሮ በመዝ ፳፩፥፲፮ ላይ “ብዙ ውሾች ከብበውኛልና የክፋተኞች ጉባኤም ያዙኝ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ፤ ዐጥንቶቼ ኹሉ ተቈጠሩ እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም” በማለት ውሻ ከአፉ ያወጣውን መልሶ ለምግብነት እንዲፈልገው፤ አይሁድም ኦሪትን እለፊ ካላት በኋላ ሲሠሯት በመገኘታቸው በውሻ መስሎ ትንቢት ያናገረባቸው ሲኾን፤ ዳግመኛም ከ፯፻ ዓመት አስቀድሞ በነቢዩ በኢሳይያስም ዐድሮ በምዕ ፶፥፮ ላይ “ዠርባዬን ለግርፋት ጕንጬንም ለጥፊ ፊቴንም ከውርደትና ከትፋት አልመለስኹም” በማለት ያናገረው ትንቢት ሊደርስ ሊፈጸም ጌታችንን አይሁድ ገርፈውታል፡፡ አንድም ንጹሐ ባሕርይ ጌታችን መገረፉ ዲያብሎስ የአዳምን ዘባነ ልቡና እየገረፈ ወደ ሲኦል አውርዶት ነበርና ለርሱ ሊክስለት ሲኾን ዳግመኛም በጌታ ላይ አይሁድ የግፍ ድርብ አድርገውበታል በሀገራቸው የሚሰቀል አይገረፍም ነበር በተጨማሪም በኦሪት ልምድ ከአርባ አትርፎ መግረፍ የተከለከለ ሲኾን እነርሱ ግን ፴፱ ጊዜ ከገረፉ በኋላ ቊጥር ተሳሳትን እያሉ ሥጋው ዐልቆ ዐጥንቱ እንደ በረድ ነጭ እስከሚኾን ድረስ ፮ሺሕ ከ፮፻፷፮ ግርፋትን ገርፈው እንደ ብራና ወደዚያና ወደዚኽ ወጥረው ሲሰቅሉት ዐጥንቱ ታይቶ የሚቈጠር ኹኗል፡፡ ቊጥራቸው ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት የሚኾን ኤልሳቤጥ፣ መልቴዳ፣ በርዜዳ የሚባሉት በጻፉት የጌታን ሕማማቱን በሚናገረው መጽሐፍ ላይ ይኽነኑ ሲያብራሩ “ወእምድኅረ አሠርዎ ቀሠፍዎ ለእግዚእ ኢየሱስ ጲላጦስ ወአርባዕቱ ሐራ በሐብል ወበአስዋጥ መጠነ ፷፻ ወ፮፻፷፮ … ” (ጌታችን ኢየሱስንም ካሠሩት በኋላ አራት ቤት ጭፍሮችና ጲላጦስ በገመድና ባለንጋ ፮ሺሕ ከ፮፻፷፮ ጊዜ ገረፉት፤ ዐምስት እልፍ ነው የሚሉም አሉ፤ የግርፋቱን ቊጥር እያሳሳቱ ገርፈውታልና፤ የሚሞት እንዳይገረፍ የማይሞት እንዲገረፍ እያወቁ፤ በግፍ ገርፈው በግፍ ገደሉት የተገረፈባቸውም አለንጋና ገመድ በደም ታለሉ፤ ከግርፋቱም ጽናት የተነሣ ሥጋው ኹሉ ዐለቀ፤ ሺሕ ከ፮፻ ከሚኾኑ ቊስሎቹም ወገን ዐጥንቶች ታዩ፤ ጥቁርና ሰማይ የሚመስሉ ቊስሎቹ ግን ሺሕ አንድ መቶ ከዘጠና ናቸው፤ የማይገረፍ አምላክ በዚኽ ሥጋ ተገረፈ፤ ጲላጦስ እጁን ከታጠበ በኋላ ጌታችንን የገረፈው በዦሮ ለሚሰማው በዐይን ለሚያየው ሰው ዕጹብ ድንቅ ነው፤ በመገረፉም አይሁድን ደስ አሰኛቸው፤ ጌታችን ኢየሱስ ግን በመገረፉ ሰው ኹሉ ከተገረፈባት ኀጢአት ፍዳ አዳነን፤ ስለ ልጆቹና ስለ አዳም መገረፍን መታሠርን ከፍሏልና) በማለት ለኹላችን ካሳ ስለተገረፈው ግርፋት አስተምረዋል፡፡ በነቢዩ ኢሳይያስ ላይ ጌታ ዐድሮ በምዕ ፶፥፮ ላይ “ዠርባዬን ለግርፋት ጕንጬንም ለጥፊ ፊቴንም ከውርደትና ከትፋት አልመለስኹም” ብሎ ያናገረው ሊደርስ ሊፈጸም ክብር ይግባውና በአምላካችን ፊት ላይ አይሁድ ምራቃቸውን ተፍተውበታል፤ ዳግመኛም ዲያብሎስ ምራቀ ምክሩን እየተፋ ወደ ሲኦል ላወረደው ለአዳም ሊክስለት የማኅበረ አይሁድን ምራቅ ክብር ይግባውና አምላካችን በትዕግሥት ተቀብሎታል፡፡ ይኽ ለካሳ አምላካችን ስለፈጸመው የድኅነት ምስጢር ቅዱሳት ደናግል ሲያብራሩ “አስተቀጸልዎ ከመዝ ለርእሰ ሕይወት አክሊለ ሦክ…” (የሕይወት መገኛ ርሱን የእሾኽ አክሊልን አቀዳጁት፤ መላእክትን የብርሃን ራስ ቁር የሚያቀዳጃቸው የነገሥታት ገዢ የሚኾን ርሱን የሾኽ አክሊል አቀዳጁት፤ በሾኽ አክሊልም ከራሱ ክፍል ያቆሰሉት ሺሕ ናቸው፤ ከራሱም ቊስሎች ደም እንደ ውሃ በዝቶ ፈሰሰ፤ ፊቱም ደምን ለበሰ ሰውነቱም በደም ተጠመቀ፤ የጽዮን ልጆች እናቱ ያቀዳጀችውን አክሊል ተቀዳጅቶ አዩት፤ ተድላ ደስታ የሚያደርግበትና የሙሽርነቱ ቀን ነውና፤ በቀኝ እጁ ዘንግ አስያዙት፤ ሲያሽሟጥጡ በፊቱ እየወደቁ እጅ ነሡለት፤ የመላእክት ሰራዊት እየደነገፁ የሚሰግዱለትን የአይሁድ ንጉሥ ቸር ውለኻል አሉት፤ ሥልጣናትና ሊቃናት እየፈሩ ለሚሰግዱለት ለርሱ በትዕቢት እጅ ነሡት፤ ዐምስት የሚኾኑ መዘባበቻቸውን ከጨረሱ በኋላ በምራቁ ኹለተኛ ዐይኖችን በሚፈጥር በርሱ ፊት ላይ ምራቃቸውን ተፉበት፤ ዳግመኛም ፊቱን በጥፊ መቱት፤ ኪሩቤል ፊቱን ከማየት የተነሣ በእሳት አክናፍ የሚሰወሩት ያልበደላቸውን ርሱን አይሁድ በጥፊ መቱት፤ ፊቱ እንደ መንፈስ ቅዱስና እንደ አባቱ ሲኾን በተዋሐደው ሥጋ ፊቱን ጸፉት ከፊቱ ግርማ የተነሣ ፍጥረቱ ኹሉ የሚርዱለት የሚንቀጠቀጡለት የፈጣሪያቸውን ፊቱን ጸፉት፤ መዠመሪያ በመመታቱና የሾኽ አክሊል በመቀዳጀቱ ራሱ የቈሰለ ከመኾኑም በላይ
4643Loading...
18
መንፈሳዊ ጉባኤ: Henok: 💦💦የሚገርም ፍቅር💦💦💦 ♥የጌታችን ሕማማት በሊቃውንት♥ : ☞በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ክብር ይግባውና ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕሙማነ ሥጋን በተአምራት ሕሙማነ ነፍስን በትምህርት በማዳኑ፣ ዕዉራነ ሥጋን በተአምራት ዕዉራነ ነፍስን በትምህርት በማብራቱ፣ ልሙጻነ ሥጋን በተአምራት ልሙጻነ ነፍስን በትምህርት በማንጻቱ፣ አጋንንትን በማውጣቱ፣ ሙታንን በማንሣቱና ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው የአብ የባሕርይ ልጅ መኾኑን በማስተማሩ አይሁድ ከፍተኛ ቅንአት ዐድሮባቸው ጌታን ይዘው የካህናት አለቃ ቀያፋ ወዳለበት ይዘውት በመኼድ የካህናት አለቆችና ሽማግሎች ሸንጎውም ኹሉ እንዲገድሉት በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የሐሰት ምስክር ቢፈልጉም ምንም ዐይነት በደል ሊያገኙበት አልቻሉም ነበር፤ በኋላም ሊቀ ካህናቱ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ የኾንኽ እንደ ኾነ እንድትነግረን በሕያው እግዚአብሔር አምልኻለኊ” ብሎ ሲጠይቀው፤ ጌታም “አንተ አልኽ፤ ነገር ግን እላችኋለኊ፤ ከእንግዲኽ ወዲኽ የሰው ልጅ በኀይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችኊ” በማለት ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው በአብ ቀኝ ያለው የአብ የባሕርይ ልጅ የኾነው ርሱን በኀይል ቀኝ በሰማይ ደመና ማለት፡- ዓለምን በማሳለፍ ኀይል ባለው ዕሪና በባሕርይ ክብሩ መጥቶ ታዩታላችኊ በማለት ተናገረው (ማቴ 26፡63-64)፡፡ ያን ጊዜ ሊቀ ካህናቱ በንዴት ልብሱን ቀደደ፤ በዘሌ 21፡10 ላይ “በራሱም ላይ የቅባት ዘይት የፈሰሰበት የክህነትም ልብስ ይለብስ ዘንድ የተቀደሰ ከወንድሞቹ የበለጠው ካህን ራሱን አይግለጥ ልብሱንም አይቅደድ” በማለት እንዳዘዘው በኦሪት ሥርዐት ካህን በሐዘን ምክንያት ልብሱን ከቀደደና ፊቱን ከነጨ ከሹመቱ የሚሻር ነውና በዚኽም የሊቀ ካህናቱ ኦሪታዊ ክህነት ማለፉን አጠይቋል፡፡ ከዚያ በኋላ ጌታን “ሞት ይገባዋል” በማለት በደረቅ ግንባር ላይ ዐይንን በፈጠረ በርሱ ፊት ላይ ምራቃቸውን ተፉበት፡- ጌታ በኢሳይያስ ዐድሮ በምዕ ፶፥፮ ላይ “ወኢይትሀከዩ ወሪቀ ውስተ ገጽየ ወኢሜጥኩ ገጽየ እምኀፍረተ ምራቅ” (ዠርባዬን ለገራፊዎች ጕንጬንም ለጠጕር ነጪዎች ሰጠኊ ፊቴንም ከውርደትና ከትፋት አልመለስኹም) ያለው ትንቢት ሊደርስ ሊፈጸም ምራቃቸውን ተፍተውበታል፡፡ አንድም አዳምን ዲያብሎስ በገጸ ልቡናው ምራቀ ምክሩን እየተፋ ሲኦል አውርዶት ነበርና ለርሱ ካሳ ሊኾን ንጹሐ ባሕርይ አምላክ ተተፍቶበታል፡፡ ከዚያም ራሱን በዘንግ መቱት “ወኲሉ ርእስ ለሕማም” (ራስ ኹሉ ለሕመም ኾኗል) ብሎ ኢሳይያስ የተናገረው ትንቢት ይደርስ ይፈጸም ዘንድ የሕይወት ራስ ርሱን በዘንግ መቱት (ኢሳ ፩፥፭)፤ አንድም ዲያብሎስ የአዳምን ርእሰ ልቡናውን በበትረ ምክሩ እየመታ ሲኦል አውርዶት ነበርና ካሳ ሊኾን ነበር፤ ከዚያም ፊቱን በሻሽ ሸፍነው “መኑ ውእቱ ክርስቶስ ዘጸፍዐከ” (ክርስቶስ በጥፊ የመታኽ ማነው? ንገረን እስቲ ዕወቀን) እያሉ ዘብተውበታል፤ ይኸውም መተርጒማን እንዳመሰጠሩት አዳምና ሔዋን የአምላክነትን ዕውቀት ዕንወቅ ብለው ሲኦል ወርደው ነበርና ልቡና ያሰበውን ኩላሊት ያመላለሰውን ኹሉን የሚያውቅ ርሱ ላይ በዚኽ ቃል መዘበታቸው ለአዳምና ለሔዋን ሊክስላቸው ነው፡፡ ከዋለበት እየዋሉ ካደረበት የሚያድሩ ቊጥራቸው ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት የኾኑት ኤልሳቤጥ፣ ቤርዜሊ፣ መልቴዳ በዕለተ ዐርብ በዐይናቸው ያዩትን የጌታን ሕማማት በተናገሩበት ድርሳን ላይ ይኽነን ሲገልጹ፡- “ወሶበ ዘበጥዎ አፉሁ ለእግዚእ ኢየሱስ ሐሙ ከናፍሪሁ ወአስናኒሁ፤ ወውሒዘ ደም ብዙኅ እምአፉሁ…” (ጌታችን ኢየሱስን አፉን በመቱት ጊዜ ከንፈሮቹ ጥርሶቹም ታመሙ፤ ከጌታችንም ከኢየሱስ አፍ ብዙ ደም ፈሰሰ፤ አሕዛብን በሚያጠፋበት ስለቱ (ሥልጣኑ) በኹለት ፊት የኾነ የተሳለ ሰይፍ ከአንደበቱ የሚወጣ ሲኾን (ወደ እኔ ኑ፣ ከእኔ ኺዱ የሚልበት ሥልጣን ገንዘቡ ሲኾን) (ማቴ ፳፭፥፴፩-፵፮)፤ ዳግመኛ አይሁድ ጌታችን ኢየሱስን ፊቱን ፳ ጊዜ በጡጫ መቱት ይኸውም እግዚአብሔር አብን መንፈስ ቅዱስንም በመልክ የሚመስል በባሕርይ የሚተካከል ነው (ዮሐ 10፡30)፤ በጌትነት ክብር በደብረ ታቦር በተገለጸ ጊዜ ተለውጦ እንደ ፀሓይ ያበራ መልኩ ፊቱ ነው (ማቴ ፲፯፥፪)፤ ርሱ የማይጠልቅ ፀሓይ የማይጠፋ ፋና ነውና፤ በወዳጆቹም ላይ ዘወትር የሚያበራ ፀሓይ ነውና (ራእ ፳፪፥፭)፤ ሰነፎች አይሁድም ከምድር ነገሥታት ይልቅ የሚያስፈራ ፊቱን ሲመቱት የጌታችን የኢየሱስ የፊቱ ግርማ ሦስት ጊዜ ወደ ምድር የኋሊት የጣላቸው መኾኑን አላሰቡትም) በማለት በቅንአት የሰከሩ የዝንጉኣን የአይሁድን ነገር አስምረዋል፡፡ ዓለምን ለማዳን ሲል አካላዊ ቃል ክርስቶስ የተቀበላቸውን ጸዋትወ መከራዎች ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅም በቅዳሴው ላይ ሲተነትናቸው፡- “በይእቲ ሌሊት እንተ ባቲ ረፈቀ ምስለ አርዳኢሁ መጠወ ነፍሶ ለሞት በፈቃደ አቡሁ ወበሥምረተ ርእሱ…” (ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ በተመጠባት በዚያች ሌሊት በአባቱ ፈቃድ በራሱም ፈቃድ ሰውነቱን ለሞት ሰጠ፤ ኹሉን የያዘውን ያዙት ኹሉን የሚገዛውን አሰሩት የሕያው የአምላክን ልጅ አሰሩት፤ በቊጣ ጐተቱት በፍቅር ተከተላቸው፤ በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተላቸው ወሰዱት፤ ሊቃነ መላእክት በመፍራትና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በዐደባባይ አቆሙት ኀጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፤ በመኳንንት በሚፈርደው በርሱ ፈረዱበት፤ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የእሾኽ ዘውድ አቀዳጁት፤ ለኪሩቤል የግርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሸፍነው በፊቱ የሚሰወሩለትን ርሱን (ኢሳ ፮፥፪፤ ራእ ፭፥፭-፲፬)፤ ክፉ ባሪያ እጁን አጽንቶ ፊቱን ጸፋው (ዮሐ ፲፰፥፳፪) የመላእክት ሰራዊት በፍጹም መደንገጥ ለሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ (ፊልጵ ፪፥፲) ይኽን ያኽል ትሕትና እንደ ምን ያለ ትሕትና ነው?፤ ይኽን ያኽል ዝምታ እንደ ምን ያለ ዝምታ ነው?፤ ይኽን ያኽል ቸርነት እንደ ምን ያለ ቸርነት ነው?፤ ይኽን ያኽል ሰውን ማፍቀር እንደ ምን ያለ ፍቅር ነው?፤ ኀያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው፤ በደል የሌለበትን እንደ በደለኛ ሰቀሉት፤ ሕይወት የሠራውን ከበደለኞች ጋራ ቈጠሩት፤ አዳምን የፈጠሩ እጆች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ወዮ፤ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ወዮ፤ በአዳም ላይ የሕይወት መንፈስን እፍ ያለ አፍ ከሐሞት ጋራ የተቀላቀለ የኾመጠጠ መጻጻን ጠጣ ወዮ፤ የወልድ መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው? ምን ከንፈር ነው? ምን አንደበት ነው? የፍቁር የጌታ ሕማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል ኅሊናም ይመታል ነፍስም ትንቀጠቀጣለች ሥጋም ይደክማል፤ የማይሞተው ሞተ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ) በማለት ሕማማቱን በስፋት አስተምሮታል፡፡ ወንጌላውያንም እንደጻፉት ጌታችንን አይሁድ ኀሙስ ማታ ከያዙት በኋላ “ወወሰድዎ ለእግዚእ ኢየሱስ እምኀበ ቀያፋ ኀበ ዐውድ ወጎሕ ውእቱ” ይላል በማለዳ ከቀያፋ ወደ ገዢው ግቢ ወደ ፍርድ ዐደባባይ አስረው በማለዳ ወደ ጲላጦስ ዘንድ ወስደውታል (ማቴ ፳፯፥፲፩፤ ማር ፲፭፥፩፤ ሉቃ ፳፫፥፩፤ዮሐ ፲፰፥፳፰) ይኸውም አዳምን ከመልአከ ገሀነም ፊት አስረው ወስደው አቁመውት ነበርና ለካሣ ሊኾን ነበር፡፡ .
3543Loading...
19
የያዘውን በትር ከእጁ ተቀብለው ራሱን መቱት፤ ነገር ግን የሾኽ አክሊልን በመቀዳጀቱ በምድራችን ላይ የበቀሉትን አሜከላና እሾኽ ርግማንን አጠፋልን፤ ራሱንም በዘንግ በመመታቱ የታላቁን እ ባብ ሰባቱን ራሶቹን ዐሥሩን ቀንዶቹን አጠፋልን) በማለት አስተምረዋል፡፡ ክብር ይግባውና ንጹሐ ባሕርይ ጌታችንን አይሁድ መስቀሉን አሸክመው ቀራንዮ ወደሚባል ቦታ ከወሰዱት በኋላ ኹለት ወንበዴዎችን በቀኝና በግራ ጌታችንን በመኻከል አድርገው ሰቅለውታል (ማቴ ፳፯፥፴፰፤ ማር ፲፭፥፳፯፤ ሉቃ ፳፪፥፴፫፤ ዮሐ ፲፱፥፲፰)፡፡ ክፉዎች አይሁድ ይኽነን ያደረጉበት ምክንያት በክፋት ነው ይኸውም በቀኝ የሚመጡ ሰዎች በቀኝ የተሰቀለውን ወንበዴ አይተው ይኽ ምንድነው? ብለው ሲጠይቁ ወንበዴ ነው ይሏቸዋል፤ ከዚያም ጌታን ይኽስ ምንድነው? ብለው ሲጠይቁ ይኽስ ከርሱ ልዩ ነውን አንድ ነው እንጂ ብለው ሰዎችን ለማሳሳት፤ በግራ የሚመጡ ሰዎች በግራ የተሰቀለውን ወንበዴ አይተው ይኽ ምንድነው? ብለው ሲጠይቁ ወንበዴ ነው ይሏቸዋል፤ ከዚያም ጌታን ይኽስ ምንድነው? ብለው ሲጠይቁ ይኽስ ከርሱ ልዩ ነውን አንድ ነው እንጂ ብለው ሰዎችን ለማሳሳት፤ ዳግመኛም አነገሥንኽ ብለውታልና ቀኛዝማች ግራዝማች ሾምንልኽ ለማለት ለመዘበት ነው በተጨማሪም ነቢዩ ኢሳይያስ በምዕ ፶፫፥፲፪ ላይ “ከዐመፀኞችም ጋር ተቈጥሯልና” የሚለው ትንቢቱን ሊፈጽም ሲኾን ምስጢሩ ግን በዕለተ ምጽአት እኛን ኃጥኣንን በግራ ጻድቃንን በቀኝ ታቆማለኽ ሲያሰኛቸው ነበር (ማቴ ፳፭፥፴፫፤ ራእ ፩፥፯)፡፡ ቊጥራቸው ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት ውስጥ የኸኑት ኤልሳቤጥ፣ መልቴዳና በርዜዳ ስለዚኽ ነገር ሲገልጹ “ወሰቀልዎ ለእግዚእ ኢየሱስ ዲበ ዕፀ መስቀል እንዘ ገጹ መንገለ ምሥራቅ ወእዴሁ ዘየማን መንገለ ደቡብ ወእዴሁ ዘፀጋም መንገለ ሰሜን…” (ጌታችን ኢየሱስንም በዕንጨት መስቀል ላይ ሰቀሉት፤ ፊቱን ወደ ምሥራቅ ቀኝ እጁን ወደ ደቡብ፤ ግራ እጁን ወደ ሰሜን አድርገው ሰቀሉት…ከርሱም ጋር ኹለቱን ወንበዴዎች አንዱን በቀኝ አንዱን በግራው በመኻከላቸው ጌታችን ኢየሱስን አድርገው ሰቀሉ፤ ሕዝቡም ርሱም እንደነርሱ ወንበዴ ነው ይሉት ዘንድ ሰቀሉት፤ ርሱ ግን ወድዶ ከወንበዴዎች ጋር በዕንጨት መስቀል ተሰቀለ፤ ልዑላን መላእክት ፈርተው በፊቱ ራሳቸውን ዝቅ ዝቅ የሚያደርጉለት ርሱ በሚሰቅሉት ፊት ራሱን ዝቅ አደረገ (ፊልጵ ፪፥፲፤ ራእ ፬፥፲-፲፩)፤ በከሃሊነቱ ሰማይና ምድርን ያጸና ከግርማውም የተነሣ ሰማያትና ምድር የሚንቀጠቀጡለትን ርሱን ደካማ ዕንጨት ተሸከመው (ምሳ ፴፥፬፤ ኢሳ ፵፪፥፭)፤ ርሱ ግን ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ከራሱ ያስታርቀን ዘንድ ከሰማይ ዝቅ ብሎ ከምድር ከፍ ብሎ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቀለ፤ ርሱም ስለእኛ በሥጋው በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቀለ፤ ከኀጢአታችን ይለየን ዘንድ በቸርነቱ ያድነን ዘንድ ተሰቀለ (፩ጴጥ ፪፥፳፬)፤ ርሱ ግን ሰማያትን ይቀድስ ዘንድ በአየር ያሉ አጋንንትን ያወርዳቸው ዘንድ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቀለ፤ ሙሴ አርዌ ብርትን በገዳም እንደ ሰቀለው ርሱም በዕንጨት ላይ ተሰቀለ ፤ በርሱ ያመነ ኹሉ ይድናል እንጂ እንዳይጐዳ የክብር ባለቤት ርሱ ግን ስለ እኛ በዕንጨት ላይ ተሰቀለ (ዮሐ ፫፥፲፬-፲፭)፤ አውቀውስ ቢኾን የክብር ባለቤት ጌታን ባልሰቀሉት ነበር (፩ቆሮ ፪፥፰)፤ ሰማይ ዙፋኑ ሲኾን ምድርም በእግሮቹ የተረገጠች ስትኾን ስለኛ በዕንጨት ተሰቀለ (ኢሳ ፷፮፥፩)፤ ርሱ ግን ተጠብቆለት ስላለ ስለ ደስታው የመስቀልን መከራ ንቆ አቃልሎ ተቀበለ ኀፍረትንም ናቃት፤ ለተሰቀለው ለርሱ የማይሰግድ ቢኖር የተለየ የተወገዘ ይኹን (ፊልጵ ፪፥፰-፲፩)፤ ርሱ ግን ስለ ዓለሙ ደኅንነት በማእዝነ ምድር ወደ ላይ ወደ ታች ወደ ግራ ወደ ቀኝ ኾኖ እንደ መጋረጃ በዕንጨት ላይ ተሰቀለ፤ እኛን ከጻድቃን ጋራ አንድ ያደርገን ዘንድ ርሱ ከበደለኞች ጋር ተቈጠረ) በማለት በስፋት የነገረ ስቅለቱን ምስጢር አስተምረዋል፡፡ በመስቀል ሲሰቀልም በቀኙ የተሰቀለው ጥጦስ በግራ የተሰቀለው ዳክርስ ይባላል፤ በቀኝ የተሰቀለው ጥጦስ ፀሓይ ስትጨልም፣ ጨረቃ ደም ስትኾን፣ ከዋክብት ከብርሃናቸው ሲራቈቱ፣ ድንጋዮች ሲሠነጠቁ፣ መቃብራት ሲከፈቱ፣ ሙታን ሲነሡ፣ የምኩራቡ መጋረጃ ወደ ኹለት ወደ ሦስት ሲቀደድ ሰባቱ ተአምራት ሲደረጉ አይቶ አምላክነቱን ተረድቶ ወደ ርሱ ሲለምን በግራ የተሰቀለው ወንበዴ ሰምቶ “አንተስ ክርስቶስ አይደለኽምን? ራስኽንም እኛንም አድን” ይል ዠመር (ሉቃ ፳፫፥፴፱)፡፡ ያን ጊዜ በቀኝ የተሰቀለው ወንበዴ ጌታችን ለቤዛ ዓለም የተሰቀለ እውነተኛ የባሕርይ አምላክነቱን ስለተረዳ በግራ የተሰቀለውን “አንተ እንደዚኽ ባለ ፍርድ ሳለኽ እግዚአብሔርን ከቶ አትፈራውምን? ስለ አደረግነውም የሚገባንን እንቀበላለንና በእኛስ እውነተኛ ፍርድ ነው፤ ይኽ ግን ምንም ክፋት አላደረገም” ብሎ ከገሠጸው በኋላ ኀጢአት ሳይኖርበት የተሰቀለውን ንጹሐ ባሕርይ አምላኩን “ተዘከረኒ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ” (ጌታ ሆይ በመንግሥትኽ በመጣኽ ጊዜ አስበኝ) እያለ ሲለምነው ጌታችንም “እውነት እልኻለኊ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትኾናለኽ” ብሎት ደመ ማኅተሙን ሰጥቶታልና ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በዚኽ መጽሐፉ ላይ፡- “ምስጋና ለአንተ ይገባል፤ የሞትን ፃዕረኝነት (ችንካር) ትሽር ዘንድ ክፋትን የሠራኽ ሳትኾን (ሳትሠራ) በኹለት ሽፍቶች (ወንበዶች) መኻከል የተቸነከርኽ እውነተኛ ኢየሱስ ምስጋና ለአንተ ይገባል” በማለት ንጹሐ ባሕርይ አምላኩን አመስግኗል (ሉቃ ፳፫፥፴፱-፵፫)፡፡ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ . . . .
5032Loading...
20
Media files
5710Loading...
21
መንፈሳዊ ጉባኤ: Henok: ❖ ❖ ❖ ጸሎተ ሐሙስ ❖ ❖ ❖ ጸሎተ ሐሙስ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ብዙ ስያሜ ያለው ነው፡፡ ይህም ምክንያቱ በዕለቱ የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ የተገለጠበት ስለሆነ ነው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ይህን በሚዘክር ሁኔታ ታስበዋለች፡፡        ❖ በዚህ ዕለት ምን ተፈጸመ? ❖ √ በዚች ዕለት በአልአዛር ቤት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በማዕድ ተቀመጡ፡፡ ከኅብስቱ ከፍሎ አማናዊ ሥጋ፤ ከወይኑ ከፍሎ አማናዊ ደም አድርጎ ባርኮ ቀድሶ አክብሮ እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡፡ ጽዋውንም አንሥቶ አመስግኖ ሰጣቸው እንዲህም አለ /ማቴ 26፥26/ በዚህ እለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕብስቱን ቆርሶ ይህ አማናዊ ሥጋዬ ነው ወይኑን ባርኮ ይህ ለሐዲስ ኪዳን ሥርየት የሚፈሰው ደሜ ነው ብሎ ለደቀመዛሙርቱ ሥርዓተ ቁርባንን በተግባር ያስተማረበት ነው፡፡ ይህ ዕለት በቃል ያስተማረውን ትምህርት በተግባር እንዴት መፈጸም እንዳለበት ያስተማረበት ዕለት ነው፡፡ ሌላው በዚህ ዕለት የተፈጸመው ተገባር ሕጽበተ እግር ነው፡፡ወንጌሉ እንዲህ ይላል “እራትም ሲበሉ ዲያብሎስ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ በይሁዳ ልብ አሳልፎ እንዲሰጠው ሐሳብ ካገባ በኋላ ኢየሱስ ከራት ተነሣ፤ ልብሱንም አኖረ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ የደቀመዛሙርቱን እግር አጠበ፡፡” � /ዮሐ.13፥1-10/ ቅዱስ ጴጥሮስ ግን ሊከላከል ሞከረ፤ ጌታችን እንዲህ አለው “እኔ የማደርገውን አሁን አንተ አታውቅም በኋላ ግን ታስተውለዋለህ አለው” /ዮሐ.13፥10/፡፡ ጴጥሮስ የእኔን እግር ለዘላለም አታጥብም ባለው ጊዜ የጌታችን መልስ ይህ ነበር “ካላጠብሁህ ከእኔ ጋር ዕድል የለህም” በዚህም ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ደቀ መዛሙርቱን ሥርዓተ ጥምቀት ፈጸመ ሁለተኛ በቃል ያስተማረውን ትኅትና በተግባር ለደቀ መዛሙርቱ አስተምሮል፡፡ “ከእኔ ተማሩ እኔ የዋሕ በልቤም ትሁት ነኝና” እንዲል /ማቴ. 11፥29/፡፡ ይህንም ሲፈጽም አሳልፎ ሊሰጠው ያለውን የአስቆሮቱን ይሁዳ አላየውም፡፡    √ ሌላው በዚህ ዕለት ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጠው ተናገረ በዚህም ማንነቱን ጭምር ለይቶ ነገራቸው፡፡ እንዲህም ብሎ “እጁን በወጭቱ ያጠለቀው እኔን አሳልፎ የሚሰጥ ነው” በዚህ ዕለትም የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ መከራ የተቀበለልን የእኛን ሥጋ የተዋሐደ ፍጹም አምላክ፤ ፍጹም ሰው መሆኑን ለማጠየቅ ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እኪይዙት ድረስ ሲጸልይ በማደሩ ምክንያት ነው፤ /ማቴ.26፥36-46፣ ዮሐ.17/     ❖ የዚህ ዕለት ስያሜዎች፦ ❖       ☞  ጸሎተ ሐሙስ ፦ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ይለምን የነበረን ሥጋን የተዋሐደ ፍጹም አምላክ፤ ፍጹም ሰው መሆኑን ለማጠየቅ ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እኪይዙት ድረስ ሲጸልይ በማደሩ ምክንያት ነው፤ /ማቴ.26፤36-46፣ ዮሐ.17/ በዚህም ምክንያት ጸሎተ ሐሙስ እየተባለ ይጠራል፡፡        ☞  ሕጽበተ እግር ፦ ይህ ስያሜ የተሰጠው ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀመዛሙርቱን እግር በማጠቡ ምክንያት ነው፡፡ ወንጌሉ እንደሚል “እራትም ሲበሉ ዲያብሎስ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ በይሁዳ ልብ አሳልፎ እንዲሰጠው ዐሳብ ካገባ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ከራት ተነሣ፤ ልብሱንም አኖረ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ የደቀመዛሙርቱን እግር አጠበ፡፡”/ማቴ.26፥27/            ☞  የምሥጢር ቀን ፦ በዚች ዕለት በአልአዛር ቤት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በማዕድ ተቀመጡ፡፡ ከኅብስቱ ከፍሎ አማናዊ ሥጋ፤ ከወይኑ ከፍሎ አማናዊ ደም አድርጎ ባርኮ ቀድሶ አክብሮ እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡፡ ጽዋውንም አንሥቶ አመስግኖ ሰጣቸው እንዲህም አለ /ማቴ 26፥26/ በዚህ ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕብስቱን ቆርሶ ይህ አማናዊ ሥጋዬ ነው ወይኑን ባርኮ ይህ ለሐዲስ ኪዳን ሥርየት የሚፈሰው ደሜ ነው ብሎ ለደቀመዛሙርቱ ሥርዓተ ቁርባንን በተግባር ያስተማረበት ነው፡፡ ይህ ዕለት በቃል ያስተማረውን ትምህርት በተግባር እንዴት መፈጸም እንዳለበት ያስተማረበት ዕለት በመሆኑ የምሥጢር ቀን ይባላል፡፡       ☞  የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ፦ በዚህ ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዲስ የሆነውን የሐዲስ ኪዳን መስዋዕት የመሠረተበት ነው፡፡ ቀድሞ የነበረውን መስዋዕተ ኦሪት ሽሮ የሐዲስ ኪዳን ደምና ሥጋውን ፈትቶ ስላቀበላቸው የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡፡ /ሉቃ.22፥20/      ☞  የነጻነት ሐሙስ ፦ በመብል ያጣነውን ክብር በመብል የመለሰበት ዕለት በመሆኑ ጌታችን በሰጠን ሥልጣን ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባርያ ሆኖ መኖር በማብቃቱ የነጻነት ሐሙስ ይባላል፡፡         ❖ሥርዓተ ጸሎተ ሐሙስ ❖ ☞ በዚህ ዕለት ስግደቱ፣ ጸሎቱ፣ ምንባባቱ እንደተለመደው ይከናወናሉ ለየት ያለው ሥርዓት መንበሩ /ታቦት/ ጥቁር ልብስ ይለብሳል ጸሎተ ዕጣን ይጸለያል ቤተ ክርስቲያኑ በማዕጠንት ይታጠናል፡፡ በዘጠኝ ሰዓት ዲያቆኑ ሁለት ኰስኰስቶችን ውኃ ሞልቶ ያቀርባል አንዱ ለእግር፣ አንዱ ለእጅ መታጠቢያ፡፡ ጸሎተ አኮቴት የተባለ የጸሎት ዐይነት ተጸልዮ ወንጌል ተነቦ ውኃው በካህኑ /በሊቀ ጳጳሱ/ እጅ ተባርኮ የሕጽበተ እግር ሥርዓት ከካህናት እስከ ምእመናን ከወንዶች እስከ ሴቶች በካህኑ አስተናጋጅነት ይከናወናል፡፡ ሥርዓተ ኅጽበቱ የሚከናወነውም በውኃ ብቻ ሳይሆን የወይራና የወይን ቅጠልንም ለሥርዓቱ ማስፈጸሚያነት እንጠቀምባቸዋለን፡፡ ምስጢሩም ወይራ ጸኑዕ ነው ክርስቶስ ጽኑ መከራ መቀበሉን ከማስረዳቱ በተጨማሪ እኛም /የሚያጥበውና የሚታጠበው ክርስቲያን/ መከራ ለመቀበል ዝግጁ ነን ለማለት ነው፡፡ የወይኑ ቅጠል በወይን የተመሰለ ደሙን አፍስሶ ለምእመናን የሕይወት መጠጥ ይሆናቸው ዘንድ መስጠቱን ለማዘከር ነው፡፡ ማቴ 26.26 ይህም ሥርዓት ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠብ ያሳየውን የተግባር ትምህርት ለምእመናን ለማሳየት ነው ዮሐ. 13፤14፡፡ በቀኝና በግራ የቆሙ ሊቃውንትም ሐዋርያቲሁ ከበበ እግረ አርዳኢሁ ሐፀበ እያሉ ይዘምራሉ፡፡ ይህ ሥርዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ሥርዓተ ቅዳሴው ተከናውኖ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ምእመናን ይቀበላሉ፡፡ የጸሎተ ሐሙስ ቅዳሴው የሚከናወነው በተመጠነ ድምፅ ነው፡፡ ደወሉ የጸናጽል ድምጽ ሲሆን በቀስታ ስለሚጮህ ነው፡፡ የድምጽ ማጉያ አይጠቀሙም፡፡ ምክንያቱም ዲያቆኑና ካህኑ ዜማውን በቀስታ የሚሉት ይሁዳ በምስጢር ጌታችንን ማስያዙን ለመጠቆም ሲሆን በሌላ በኩል የዘመነ ብሉይ ጸሎት ዋጋው ምድራዊ እንደነበር ለማስታወስ ነው፡፡ በመቀጠል ክቡር ይእቲ፣ ዕጣነ ሞገር ዝማሬ የተባሉ የድጓ ክፍሎች ተዘምረው አገልግሎቱ ይጠናቀቃል፡፡ ሕዝቡም ያለ ኑዛዜና ቡራኬ ይሰናበታሉ፡፡             ❖  ጉልባን  ❖ ጉልባን ከባቄላ ክክ፣ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጅና የጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ነው፡፡ በጸሎተ ሐሙስ በቤት ውስጥ ከሚፈጸሙ ተግባራት አንዱ ጉልባን ማዘጋጀት ነው፡፡ ጉልባን እስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት ሲወጡ በችኮላ መጓዛቸውን የምናስታውስበት ከእስራኤላውያን የመጣ ትውፊታዊ ሥርዓት ነው፡፡ በአገራችን ኢትዮጵያ አብዛኞቹ የትውፊት ክንዋኔዎች የብሉይ ኪዳን መነሻ ስላላቸው ይህ ሥርዓት ዛሬም በኢትዮጵያውያን ምእመናን ዘንድ ይከበራል፡፡ ጉልባን እስራኤላውያን ከባርነት በወጡ ጊዜ አቡክተው፣ ጋግረው መብላት አለመቻላቸውን ያስታውሰናል፡፡ በወቅቱ ያልቦካውን ሊጥ
5005Loading...
22
እየጋገሩ ቂጣ መመገብ፤ ንፍሮ ቀቅለው ስንቅ መያዝ የመንገድ ተግባራቸው ነበርና፡፡ ይህን ታሪክ ለማሰብም በሰሙነ ሕማማት በተለይም በጸሎተ ሐሙስ ቂጣና ጉልባን ይዘጋጃል፡፡ በጸሎተ ሐሙስ የሚዘጋጀው ጉልባንና ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ ይጨመርበታል፡፡ ይኸውም ጨው ውኃ እንደሚያስጠማ ዅሉ፣ ጌታችንም በመከራው ወቅት ውኃ መጠማቱን ለማስታወስ ነው፡፡ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም ዓመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሓ ወበሰላም አሜን !!! ያለ ደዌና ያለ ሕማም ያለጥምና ያለ ድካም እግዚአብሔር ለትንሣኤው ብርሃን እንደ ዛሬ ቀን በደስታና በፍቅር በአንድነት ያድርሰን ያድርሳችሁ አሜን !!! የዘመኑን ወረርሽኝ በቸርነቱ ያስታግስልን አሜን!!! ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖
4333Loading...
#ከሐልዮ_ኃጢአት_መጠበቅ ሰይጣን ነቅዓ ሐልዮን መጠበቅ ላልቻለ ወጣት በቀጣይ እርሱን የሚወጋበት ኹለተኛው ጦር ሐልዮ ኃጢአት ነው። “የሐልዮ ኃጢኣት ምን ትጎዳለች?” እያለ እንዲያስብ ያደርገዋል። በሐልዮ ኃጢአት ያዝለዋል። ይኸውም ደቂቀ ሴት ደቂቀ ቃኤልን ከመስማት አልፈው እንዲመለከቷቸው በማድረግ በዝሙት ፍላጻ እንደነደፋቸው ነው። ስለዚህ የተለያዩ ነገሮችን እንዲመለከት ያደርገዋል። ለምሳሌ ራስን በራስ ስለ ማጎሳቆል፣ ወይም ስለ ምስለ ሩካቤ፣ ወይም ስለሚያውቃት ሴት በዝሙት ሕሊና እንዲያስብ ያደርገዋል። ጓደኞቹ የተናገሩትን ነገር ወይም በመጽሔት ያነበበውን ወይም በተለያየ መንገድ ሲወራ የሰማውን “ይህ ምን ያረክሳል?” እያለ በሕሊናው እንዲያመላልሰው ያደርገዋል። እንደዚህ በሚኾንበት ጊዜ በየትኛውም ቀን ቢሰግድ ፆሩ ይመለስለታል። አንድ ወንድሜ እንደ ነገረኝ፡ እንደዚህ ያለ ፆር ሲመጣበት በሩካቤ አካሉ አከባቢ ካለው ፀጕር የተወሰነውን ይነጫል። በጣም ያማል። በዚያ ሰዓትም ከፆሩ ይልቅ ሕመሙ ስለሚበልጥ ፆሩን ከማሰብ ይመለሳል። ሕሊናው አድርገኝ አድርገኝ ብሎ እንዳይገፋፋው፣ ነጉዶ የመጣውን ፆሩን በተግባር ለመፈጸም ሰይጣንን እንዳይታዘዘው ያደርገዋል። እንደ ነደ እሳት የሚያቃጥለውን የፍትወትን ፆር እንዳያስነሣበት ይከልለዋል። የሐልዮ ኃጢኣት በተነሣ ጊዜ "ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ግን ሽሽ” እንደ ተባለው፥ ለዚህ ከሚዳርጉን ነገሮች (ቦታ፣ ኹኔታ) መራቅ የመጀመሪያው እርምጃ ነው። “ይህ አሳብ የእኔ አይደለም” ብሎ ለመሸሽም የሐልዮ ኃጢአት የምታመጣውን መከራ የሚነግረን መምህር ወይም አበ ነፍስ ማግኘት እጅግ አስፈላጊ ነው (2ኛ ጢሞ.2፥22)። መካሪ መምህር ሳናገኝ ቀርተን ካዋልናትና ካሳደርናት ለሰይጣነ ፍትወት እጅ እንደ መስጠትና ወድቀን ወደ ቀጣዩ ደረጃ ወደ ገቢር ልናልፍ እንችላለንና። ከክፉ አሳብ መራቁ ብቻውን በቂ አይደለም። ክቡር ዳዊት “ከክፉ ሽሽ” ካለ በኋላ በዚያ ሳያቆም ጨምሮ “መልካምንም አድርግ" ይላልና (መዝ.33፥14)። እርስ በእርሳቸው የተያያዙ ናቸው። ስለዚህ አንዲት ሴት ጥሩ ልብሷን ተሸላልማ ተጊያጊጣ እየተኩነሰነሰች ስትሔድ አይቶ ፈላስፋው ዲዮጋንስ ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች "ከዚች ክፉ ወጥመድ ሽሹ" እንዳላቸው ሸሽቶ ወደ በጎ ሥራ ፊትን ማዞር ይገባል። ከወደቁ በኋላ ከመጠበብ ሳይወድቁ መጠንቀቅ ይሻላልና። በሌላ መልኩ ደግሞ ተፈጥሮ ስለኾነ እነዚያ ስሜቶች ለምን መጡ ማለት አይቻልም። ስሜቶቹን ግን መቀደስ ስለሚቻል ከክፉ ሸሽቶ መልካም በማድረግ መቀደስ ይቻላል። አንድ ፈረስን የሚጋልብ ሰው፥ ፈረሱ ወደ ገደል ቢያመራ ጋላቢው የሚያደርገው ልጓሙን ማጥበቅ ብቻ አይደለም፤ ፈረሱ በትክክለኛው መንገድ እንዲሔድም ይመራዋል እንጂ። ስለዚህ እንደዚህ ዓይነት ስሜቶች ሲመጡብን ከመራቅ ባሻገር ወዲያው መንፈሳዊ ተግባር ማከናወንም አስፈላጊ ነው። ጸሎት ሊኾን ይችላል፤ ስግደት ሊኾን ይችላል፤ መጽሐፍ ማንበብ ሊኾን ይችላል፣ መንፈሳዊ አባት ጋር መደወል ሊኾን ይችላል። ከበረኻ አባቶች ከተሰጡት ምክሮች አንዱ እንዲህ የሚል ነው፦“ሌላ እኁም ከሰይጣነ ዝሙት ጋር ይጋደል ነበር። በሌሊት ተነሥቶም ከአረጋውያኑ ወደ አንዱ መጥቶ ስለ ሕሊናው ነገረው። አረጋዊውም ይታገሥ ዘንድ መከረው። በዚህ መንገድ እገዛ አግኝቶም ወደ በዓቱ ተመለሰ። ለኹለተኛ ጊዜም ወደ አረጋዊው መጥቶም እርዳታ አግኝቶ ወደ በዓቱ ተመለሰ። ውጊያው ለሦስተኛ ጊዜ ሲመጣበትም እንደገና  በሌሊት ወደዚያ አረጋዊ ሔደ። አረጋዊውም ወጣቱን አላሳዘነውም፤ እንደሚጠቅመው መክሮ ዘክሮ ነገረው እንጂ፤ እንዲህ ሲል፡- ምንም ዕድል እንዳትሰጠው። ሰይጣነ ዝሙት በፈተነህ በማናቸውም ሰዓት ወደ እኔ ና። ከዚያም ታጋልጠዋለህ። ስታጋልጠው ሸሽቶ ይሔዳል። ሰይጣነ ዝሙት እነዚህን አሳቦች የሚደብቃቸውንና የማይገልጣቸውን ሰው ያህል የሚፈትነው የለምና።" ያ እኁም በዚያች ሌሊት እርዳታ ፈልጎ ዓሥራ አንድ ጊዜ ወደ አረጋዊው እየተመላለሰ አሳቦቹን ተቃወማቸው። አረጋዊውም ሰይጣነ ዝሙቱ ከእርሱ እንደ ራቀ ነገረው። ነገር ግን ወደ በዓቱ በተመለሰ ጊዜ ውጊያው እንደ ገና መጣበት። ከብዙ ጊዜ ምልልስ በኋላም ያ እኁ አረጋዊውን:- አባ! ቸርነትህ ይደረግልኝ፡ እንዴት አድርጌ መኖር እንዳለብኝ ምከረኝ አለው። አረጋዊውም፡- ልጄ ፥ በርታ! እግዚአብሔር ፈቃዱ ከኾነ የእኔ ሕሊና ወደ አንተ ይመጣል። ከዚያም በኋላ ንጹሕ ሕሊና ይዘህ ትሔዳለህ እንጂ ከእንግዲህ ወዲህ በዚህ አትፈተንም' አለው። ይህን ብሎ ሲጨርስም እግዚአብሔር ሰይጣነ ዝሙቱን እስከ ወዲያኛው ከዚያ እኁ አራቀለት።” ስለዚህ ሰይጣነ ዝሙት መጥቶ ሲያሳስበን ወይም በሌላ መንገድ ያየነውንና የሰማነውን በሕሊናችን እንድናመላልሰው በሚፈልግበት ጊዜ ምንም ሳንሰለችና ዕድል ሳንሰጥ ወደ አበ ነፍሳችን መሮጥ እንዳለብን ያስረዳል። አበ ነፍሶችም በትዕግሥት ልጆቻቸውን የመርዳት መንፈሳዊ ግዴታ አለባቸው። ወላጆቻችንም ሊያግዙን ይችላሉ። የሐልዮ ኃጢአት በእኛ ላይ እንዲነግሥ ከሚያደርጉ ነገሮች ኣንዱ ለብቻና ሥራ ፈት መኾን ነው። ሥራ ፈትተን ለብቻችን ስንኾን ሰይጣን መጥቶ ያንን ኃጢአት በደንብ እንድናስብበት፣ ተግብረው ተግበረው ይለናል። ልክ ለሔዋን በለስን የምታስጎመጅ አድርጎ እንዳሳያት፥ በእኛም የማስተዋል ሕሊናችንን አጣምሞ ከዚያ ኃጢአት ስለምናገኘው ደስታ ያሳስበናል። “ሥራ ያጣ መነኩሴ ቆቡን ቀድዶ ይሰፋል” የተባለው መነኰሴ ሥራ ላለመፍታትና ከሓልዮ ኃጢኣት ለመራቅ ሲል ይህን ስለሚያደርግ ነው። ስለዚህ ዝም ብለን መቀመጥ አይገባንም። ይልቅስ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በመሳተፍ፣ ሌሎች በጎ ሥራዎችንም በመሥራት እንጠመድ። በዚህ ከተጎዱት ሰዎች መካከል አንዱ ነቢዩ ዳዊት ነው። ነቢዩ ዳዊት ወጣት ኾኖ በጎችን በሚጠብቅበት፣ ለሳኦል ጋሻ ጃግሬው ኾኖ በገና እየደረደረ በሚያገለግልበት፣ ሳኦል በምቀኝነት ተነሥቶበት በሚያሳድደው፣ ወደ ንግሥናው መጥቶ መንግሥቱ እስከ ተደላደለ ጊዜ ድረስ በዝሙት አልወደቀም ነበር። መንግሥቱ ተደላድሎ ከተመሠረተ፣ ክብሩ ከጨመረ በኋላ ግን ሥራ ፈትቶ በሰገነት ላይ ሲመላለስ የኦሪዮን ሚስት ቤርሳቤህን ስትታጠብ ተመለከታት። ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ፡- “ሰውነት ሥራ ሲፈታ፥ ሕሊናም ሥራ ይፈታል” እንዳለው፥ ንጉሥ ዳዊት ሥራ ፈትቶ ስለ ነበረም በቀላሉ በነቅዓ ሐልዮ ሳያበቃ ስለ እርሷ በማሰብ ወደ ሐልዮ ኃጢኣት ገባ። ስለዚህም “መልእክተኞች ልኮ አስመጣት፣ ወደ እርሱም ገባች፥ ከርኩሰትዋም ነጽታ ነበርና ከእርስዋ ጋር ተኛ" (2ኛ ሳሙ.11፥4)። በመኾኑም ራሳችንን ሰይጣን ወደ ሕሊናችን የሚያስገባውን የሐልዮ ኃጢአትን ከላይ በጠቀስናቸው መንገዶች በማራቅ፥ ንጽሕናችንን ጠብቀን ከሴት ከወንድ ርቀን እስከ ጋብቻ ድረስ መጽናት ይኖርብናል። አንዳንድ ጊዜ በሕልማችን ሩካቤ ስንፈጽም ልናይ እንችላለን። በዚህ ጊዜ እኛ ራሳችን ቀን ላይ ያሰብነው አሳብ አለመኾኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። በቀን ያሰብነው ሌሊት ቀጥሎ ከኾነ ከአበ ነፍስ ጋር ተነጋግሮ አሳቡን ማራቅ፣ ከዚያ ውጭ ግን ወጣቶች በመኾናችንና “ፒቱታሪ” የተባለው ዕጢ የዘር ፈሳሽ ማመንጨቱና አንዳንድ ጊዜ በራሱ ተስፈንጥሮ ስለሚወጣ በዚህ መነሻነት ወደ ሌላ ኣሳብ እንዳንሔድ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። (ገብረ እግዚአብሔር ኪደ  ከተጻፈው #ትንሿ_ቤተክርስቲያን መጽሐፍ - ገጽ 161-163)
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram