cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

መንፈሳዊ ጉባኤ

ወዳጄ ሆይ፥ ሁለንተናሽ ውብ ነው፥ነውርም የለብሽም። መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 4 : 7 @Menfesawi_Gubae ጥያቄ ካላችሁ ከታች ባለው አድራሻ መጠየቅ ትችላላችሁ። @HenokAsrat3

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
3 056
Suscriptores
-224 horas
-57 días
-1430 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡- ዓርብ :-ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል። በዚህ እለት ቤተ ክርሰቲያን በክርስቶስ ደም መመስረቷ ይነገራል።ክርስቶስ ስለ እርሷ እራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አጽንቶ በትንሳኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል የቤተክርስቲያን እራሷ መሰረቷ ክርስቶስ መሆኑን በስፋት እና በምልዐት ይሰበካል።
Mostrar todo...
ሐሙስ -  [ አዳም ሐሙስ ] አዳም ማለት ትርጉሙ ፩ኛ.  የሰው ሁሉ አባት ፣ የሥጋው ተፈጥሮ ከአፈር ከመሬት ስለሆነ አዳም መባልን ከአዳም ወስዷል፡፡ [ ዘፍ ፪፥፲፤ ፲፱፥፳፯ ] ፪ኛ.  አዳም ማለት እንሰሳዊና መልአካዊ ሁለት ባሕርያት ስላሉት በሥጋው መዋቲ፣ ድኩም፣ ፈራሽ፣ በስባሽ፤ በነፍሱ ነባቢ፣ ልባዊ፣ ሕያው፣ ባለ አእምሮ ይባላል፡፡ [ዘፍ ፪፥፯] ፫ኛ. አዳም በ፮ኛ ቀን መጀመሪያ ከምድር የፈለቀ የሰው ሁሉ ምንጭ ስለሆነ፤ በዘር በሩካቤ ከእርሱ እየተቀዳ ሞትና መቃብር የሚጠጡት ምድራዊ ሰው ሁሉ በእርሱ ስም በምንጩ ስም አዳም አዳሜ ይባላል፡፡ [ዘፍ ፫፥፲፱] ስለዚህም አዳም የመጀመሪያ ሰውና የሰው ሁሉ አባት ነው፤ በ፮ኛው ቀን የተፈጠረ የሰው ሁሉ ምንጭ ስለሆነ የሰው ዘር ሁሉ ከእርሱ ተገኝቷል፡፡ በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው የተስፋ ቃል ስለመፈጸሙ፤ [ዘፍ. ፫÷፲፭]  አዳም ከነልጆቹ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻ ስለመውጣቱ ይታሰብበታል፡፡ ክርስቶስ በተነሳበት በአምስተኛው ቀን ሐሙስ  አዳም ይባላል፤ ጌታችን አዳምን ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ  አድንሃለሁ ብሎ  ቃል ገብቶለት  እንደነበር በቀሌምንጦስ ተጽፏል፡፡ አዳምና ሔዋን በገነት ፯ ዓመት ከቆዩ በኋላ ትእዛዙን በመተላለፋቸው ከኤደን ገነት አስወጣቸው [ ኩፋ.፬፥፲፮፤ዘፍ.፫፥፳፫ ]«ብዙ ተባዙ» ያለው ቃል እንዳይቀር በምድር ላይ ወርደው ልጆችን ወለዱ ይላል፡፡ የተወለዱትም ልጆችም በቁጥር ፷ እንደሆኑ [ ፩መቃ. ፳፰፥፮] የተወለዱት ልጆች ደጎችና ክፉዎች እንደ ነበሩ በአቤልና በቃየል ታውቋል። [ ዘፍ. ፬፥፰]። አዳም በዚህ ዓለም ፱፻፴ ዓመት ኑሮ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በ፵፻፭፻፸ ሚያዚያ ፮ ዐርፏል፡፡
Mostrar todo...
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን   ክርስቶሰ ተንሥአ እሙታን በዐቢይ ኅይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዐዞ ለአዳም ሰላም  ****   እም ይእዜሰ ኮነ  ****   ፍሥሐ ወሰላም   ✍ "የትንሣኤው ምሥጢር"✍ ⚜️ረቡዕ  ⚜️⚜️⚜️ አልአዛር ⚜️⚜️⚜️ "ጌታዬ አምላኬ" (ዮሐ፳:፳፰) መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚል አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመቅደላዊት ቀጥሎ በዝግ ቤት ሳሉ ከሐዋርያው ከቶማስ ውጭ አንድ ጊዜ ተገልጦላቸው ነበር ፡፡ የሐዋርያውን የቶማስን ጥያቄ ሊመልስ ፤ እምነት ያሳድግ እና አምላክነቱን ይገልጥ ዘንድ ለሁለተኛ ጊዜ ከስምንት ቀን በኋላ ተገልጦላቸኋል፡፡ "ከስምነት ቀን በኋላም ደቀ መዛሙርቱ ደግመው በውስጥ ነበሩ ፤ ቶማስም ከእነርሱ ጋር ነበረ፡፡ ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ ፤ በመካከላቸውም ቆሞ ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው፡፡ ከዚያም በኋላ ቶማስን ፡- ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ እጅህንም አምጣና በጎኔ አግባው ፤ ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን አለው፡፡ ቶማስም ፡- ጌታዬ አምላኬም ብሎ መለሰለት፡፡ ኢየሱስም ፡- ስለ አየኸኝ አምነሃል ፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው አለው፡፡" እንዲል፡፡ (ዮሐ፳፡፳፮-፳፱) ሐዋርያው ቶማስ አምላኬ ጌታዬ ያለበት ምክንያት በዋናነት ጣቱን ወደ ጎኑ ባስገባት ጊዜ ከእሳት እንደገባ ጅማት ሆናለችና መዳሰሱን ሲያይ ጌታዬ አለ ፤ ማቃጠሉን ሲያይ ደግሞ አምላኬ አለ፡፡ ገቦ መለኮትን የዳሰሰች እጅ በሕያውነት ትኖራለች፡፡ በሕንድ ሀገር ከታቦት ጋር ከመንበር ላይ ነው የምትኖር በዓመት በዓመት በእመቤታችን በዓል በአስተርእዮ ሊያጥኑ ሲገቡ የሚሾመውን ወጥታ ቀኝ እጁን ትይዘዋለች ዓመት አገልግሎ ያርፋል ፤ በዓመቱ ሊያጥኑ ሲገቡ ትይዛቸዋለች እንዲህ እንዲህ እያለች ትኖራለች፡፡(ወንጌል ቅዱስ ገጽ፮፻፬) ሳናይ ልናምን እንደሚገባ እና ማመናችን ብፁአንም አንደሚያሰኘን ከገለጠለት በኋላ ቁጥር ፴ ላይ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፉ(በሌሎች ወንጌላት እና በተአምረ ኢየሱስ የተጻፉ) ብዙ ታምራትን እንዳደረገ ይህ ግን እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ (የባሕርይ አምላክ ነው) ብሎ ለማመን እንደተጻፈ ገልጦልናል፡፡ (ዮሐ፳፡፴፩) የሃያኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሊቅ የነበሩት መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ ስለ አምላካችን ስለ ኢየሱስ ክርሰቶስ ባሕርይ በጥልቀት ለካቶሊኩ መነኩሴ ዶክተር አባ አየለ በመለሱበት መጽሐፍ ስለ አምላክነቱ በግልጽ በአንድ ኃርፍተ ነገር ጽፈውልናል፡- "ክርስቶስ ፍጹም ሰው የሆነ ፍጹም አምላክ ነው"(መድሎተ አሚን ገጽ ፻፴፬)  "የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት " የሰው ልጆች በተለይ ቅዱሳን አማልክት ዘበጸጋ ይባላሉ ፤ ሙሴ በፈርዖን ላይ አምላክነትን ቢሾም በጸጋ ነው ፤ እናንተን አማልክት ናችሁ አልኋችሁ ግን ትሞታላችሁ የተባሉት እግዚአብሔር የመረጣቸው ቅዱሳኑን መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት ግን የባሕርይው ነው፡፡ እኛ ሁላችን የእግዚአብሔር ልጆች ብንባል በጸጋ ነው ፤ እርሱ ግን እግዚአብሔር ልጅ ሲባል በባሕርይ ልጅነት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት የገለጠ የእውነት ምሥክር ነው፡፡ ፩. አምላክነቱ በፈጣሪነቱ ተገልጧል፡፡ (ዘፍ፩፡፩ እና ዮሐ፩፡፫) ፪. አምላክነቱ በሥራው ተገልጧል፡፡ (ዮሐ፭፡፴፮) ፫. አምላክነቱ በትምህርቱ ተገልጧል፡፡ (ማቴ፯፡፳፱)  ፬. አምላክነቱ በፈዋሽነቱ ተገልጧል፡፡ (ሉቃ፬፡፴፮) ፭. አምላክነቱ ኃጢአትን በማስተስረይ ተገልጧል፡፡ (ሉቃ፭፡፳)  ፮. አምላክነቱ ሙታንን በማስነሳቱ ተገልጧል፡፡ (ሉቃ፯፡፲፯)  ፯. አምላክነቱ በመድኃኒትነቱ ተገልጧል፡፡ (ማቴ፰፡፩)  ፰. አምላክነቱ ዲያብሎስን በመሻሩ ተገልጧል፡፡ (ማቴ፰፡፲፮)  ፱. አምላክነቱ ሁሉን በማሸነፉ ተገልጧል፡፡ (ዮሐ፲፯፡፪)  ፲. አምላክነቱ ሁሉን በመግዛቱ ተገልጧል፡፡ (ማቴ፰፡፳፮)  ፲፩. አምላክነቱ ሞትን ድል በመንሳቱ ተገልጧል፡፡ (ሉቃ፯፡፲፬)  ፲፪. አምላክነቱ በሁሉ አዋቂነቱ ተገልጧል፡፡ (ዮሐ፩፡፵፰)  ፲፫. አምላክነቱ በሁሉ ቦታ በመኖር ተገልጧል፡፡ (ማቴ፲፰፡፳)  ፲፬. አምላክነቱ ሁሉን በማዳኑ ተገልጧል፡፡ (ማቴ፲፰፡፲፩)  ፲፫. አምላክነቱ በሁሉ ቦታ በመኖር ተገልጧል፡፡ (ማቴ፲፰፡፳)  ፲፮. አምላክነቱ በእግዚአብሔርነቱ ተገልጧል፡፡ (ሐዋ፳፡፳፰)  በአጠቃላይ ይህቺ ዕለት ቶማስ በመባሏ ለእነዚህ ሁሉ የትንሣኤው ምሥጢር ሕያው ምስክር ትሆን ዘንድ አባቶቻችን እንድናስባት አደረጉን፡፡ ወዳጆቼ በዋናነት ይህች ቅድስት ዕለት ወይም ሠሉስ የሐዋርያው ቶማስ በአምላካችን ፍቅር መማረክ ፤ ትንሣኤውን ማመኑ ፤ ሳያዩ የሚያምኑ ክርስቲያኖች የሚያገኙትን ብፅዕና ፤ የአምላካችን ተአምራቶችም ሆኑ ትምህርቶች በዚህ መጽሐፍ ብቻ የተጻፉት ብቻ እንዳልሆኑ ፤ ከሁሉ በላይ ኢየሱስ ክርስቶስን የባህርይ አምላክ ብሎ ማመን የተገባ እና መጽሐፍትም የተጻፉበት ዓላማ መሆኑን እንማራለን፡፡ ⚜️⚜️⚜️፫. ረቡዕ አልዓዛር ይባላል ⚜️⚜️⚜️ በዚህች ዕለት አምላካችን ትንሣኤ እና ሕይወት መሆኑን በተግባር በታላቅ ተአምራቱ ማሳየቱን የምናስብበት በመሆኑ ስያሜው አልዓዛር ተብሏል፡፡ የአራት ቀን ሬሳን ሕይወት ይዘራበት ዘንድ የፍቅር አምላካችን በሞት በሚፈልጉት በጠላቶቹ ሰፈር ተመላለሰ ፤ የደቀ መዛሙርቱን ክልከላ አልሰማም ፤ የመንገዱ ርቀት አላዘለውም ግን በፍቅር ስለ ፍቅር ሰው ሁሉ ተስፋ የቆረጠበትን ወዳጁ አለዓዛርን ከሞት ሊያስነሳ ወደ ቢታኒያ በፍቅር ተጓዘ ፤ እውነት ነው ሞት ለታወጀብን ለእኛ ለመመላለሱ ምሳሌ ነው ፤ ሞት ድል ያላደረገው የትንሣኤውን ጌታ አምላካችንን በእውነት እንደተነሳ እንድናስብ ቤተክርስቲያን በዚህ ዕለት በአልዓዛር አንጻር ትንሣኤ እና ሕይወት እርሱ እንደሆነ ታስተምረናለች፡፡ ይቆየን ... ወስብሐት ለእግዚአብሔር
Mostrar todo...
💦💦     💦ማክሰኞ ፪ኛ ቶማስ ይባላል 💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦 እንደ ኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ን በዓላት ቀኖና መሰረት ከትንሣኤ በኋላ ያለችው ዕለተ ማክሰኞ "ቶማስ" በመባል ይጠራል። ቶማስ ሐዋርያ ሲሆን፣ ቶማስ ማለት ‹‹ፀሐይ›› ማለት ነው።ከክስቶስ ትንሣኤ በኋላ ቅዱስ ቶማስ በጦር የተወጋ ጎኑን፤ በቀኖት የተቸነከረው እጁንና እግሩን ካላየሁ አላምንም በማለቱ ክርስቶስም «ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤እጅህንም አምጣና ወደ ጎኔ አግባ፤ እመን እንጂ ተጠራጣሪ አትሁን» ብሎታል። ቶማስም «ጌታዬ አምላኬም»፤ ብሎ በመለሰ ጊዜ ጌታችን ኢየሱስም «ስለ አየኸኝ አመንህን? ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓንስ ናቸው» አለው (ዮሐ ፳፥፳፯-፳፱)፤ ቶማስ የጌታን ፍቅር ተገንዝቦ ትንሣኤውን ስላመነ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዕለቱን ቶማስ ብላ ታስበዋለች። ዲዲሞስ የተባለ ከአሥራ አንዱ ደቀ መዛሙር አንዱ ቶማስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዝግ ቤት ገብቶ «ሰላም ለሁላችሁ ይሁን» ባላቸው ጊዜ ከእርሳቸው ጋራ አልነበረም»። ከ፲፪ቱ ሐዋርያት አንዱ (ማቴ. ፲፥፪-፫) ቶማስ በአራማይክ ዲዲሞስ በግሪክ መንታ ማለት ነው፤ (ዮሐ. ፳፥፳፬)፡፡ ቶማስ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በፋርስና በሕንድ ወንጌልን እንዳስተማረ ይነገራል። ለቶማስ ጎኑን እንዲዳስስ የፈቀደው ለሌሎችም ቅዱሳን ሐዋርያት የተቸነከረውን እጅና እግሩን ያሳየው ካህናት ሥጋውና ደሙን እንዲፈትቱ ነው፤ ዮሐንስም በእጃችን ዳሰስነው ብሏል፤ (ሉቃ. ፳፬፥፴፱)፡፡ ለማርያም መግደላዊት ግን የተነሣ ዕለት አትንኪኝ ማለቱ ለሴቶች ሥጋውን ደሙን መፈተት አልተፈቀደም ሲል ነው ብለው ሊቃውንት ያትታሉ፤ «አትንኪኝ፤ ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሂጅና፡- ወደ አባቴ÷ ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬ÷ ወደ አምላካችሁም አርጋለሁ አለ ብለሽ ንገሪአቸው» አላት፤ (ዮሐ. ፳፥፲፯)። መለኮቱን የዳሰሰች እጁ በሕይወት ትኖራለች፤ በሕንድ ሀገር ከታቦት ጋር በመንበር ላይ ትኖራለች። የሐዋርያ ቶማስ መታሰቢያ በዳግመ ትንሣኤ ላይ የሚነሳ ቢሆንም አባቶች በዓል ላይ በዓል እንዳይደራረብ ብሎ ከትንሣኤ በኋላ ባለው በዕለተ ማግሰኞ ቶማስ ተብሎ እንዲጠራ ስርዓት ሰርቶልናሉ። የአባቶቻችን በረከት ይደርብን በእውነት። በዓሉንም በዓለ ደስታና በዓለ ፍስሐ ያድርግልን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር
Mostrar todo...
🧚🧚🧚🧚 በዓሉ ከቤት ዉጭ ንፍሮ እየተበላለምን ይከበራል🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚 🌿👉 በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ትዉፊት መሰረት ሐና እና ኢያቄም ከአይሁድ ለማምለጥ ተሰደዉ በአድባረ ሊባኖስ ስር እመቤታችንን ወለዱ፡፡ በወቅቱ ከቤት የወጡት ለሽሽት ነበርና ስንቅ ስላልያዙ ምግባቸዉ ‹‹ንፍሮና ጥራጥሬ›› ነበር፡፡ይህንን ትዉፊት በመያዝ በዓሉ ከቤት ዉጭ ንፍሮ እየተበላ ይከበራል፡፡ነገር ግን በበጎ ነገሮች ሰበብ ክፉ ዓላማዉን ማስፈጸም የሚፈልገዉ ዲያቢሎስ በማር መካከል መርዝን ከሚጨምርባቸዉ መንፈሳዊ በዓላት አንዱ የግንቦት ልደታ (የእመቤታችን የልደት በዓል) ነዉ፡፡ በዚህ ዕለት አንዳንዶች ባለማወቅ ሌሎች ደግሞ በድፍረት ‹‹ለአድባር አዉጋር ነዉ፤ ቆሌዉን ለመለመን ነዉ›› እያሉ ለማያውቁት አምልኮ ንፍሮ የሚበትኑ፣ ቡና የሚረጩ፣ ቅቤ የሚቀቡ፣ የከብት ደም የሚያፈሱ አሉ፡፡ እውነታው እነዚህ በእርግጥም ጣዖት አምላኪዎች ናቸው፡፡ እኛ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ግን እነዚህን የሃይማኖት ለዋጮች ሥራቸውን እንጸየፋለን፡፡ ስለሆነም ከእንደዚህ ዓይነቱ ባዕድ አምልኮ በመለየት ይህንን ታላቅ በዓል በተገባና በተረዳ ነገር ልናከብረው ይገባል፡፡ . 🌿👉 ቤተክርስቲያናችን በሠራችልን ሥርዓት መሰረት በቀናች በተዋሕዶ እምነት ሆነን ፤ በምህረቱ የጎበኘንን አምላካችንን ብቻ እያመለክን ፤ የድኅነታችን ምክንያት የሆነችውን ድንግል ማርያምንም እያመሰገንን ልናከብረው ይገባል፡፡ . ✞❤️✞❤️✞አምላካችን እግዚአብሔር ከእመቤታችን ረድኤት በረከት ይክፈለን ፤ አ ሜ ን !!! ✞❤️✞❤️✞ . ✞❤️✞❤️✞ የእግዚአብሔር ቸርነት ፣ የንጽሕተ ንጹሐን ፣ የቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን ፤ አ ሜ ን !!! ✞❤️✞❤️✞ . ☘️🌼🌹💚💛❤️❤️💛💚🌹🌼☘️
Mostrar todo...