Yeneta Courses
Ir al canal en Telegram
2 787
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días
Archivo de publicaciones
2 787
12ኛ ክፍል ‼️
ዛሬ የ 12ኛ ክፍል ውጤትን በተመለከተ መረጃ ለመጠየቅ ወደ ትምህርት ሚኒስቴር ቢሮ ሄደን ነበር። ነገር ግን ከፍተኛ አመራሮች ከ አብይ ጋር ለነበረው ስብሰባ ለመታደም ሄደዋል ተባልን።
እዛው ያሉ ሰራተኞችን 👉 የ 12ኛ ክፍል ፈተና መች ይፋ ይሆናል ብለን ጠይቀን ያገኘነው መረጃ .....
👉 ሁሉ ነገር ተጠናቋል። ነገር ግን መቼ ይፋ እንደሚሆን ማንም አያቅም። እስካሁን የተቆረጠ ቀን የለም ግን በዚህ ሳምንት ውስጥ የሚል ወሬ ሰምተናል። ( እነሱም አያቁም)
👉 ሌላኛው ሰረተኛ በ 22 የሚባል ነገር ጭምጭምታ አለ ግን እርግጠኛ አይደለሁም። ብቻ በዚህ ሳምንት እንደሚሆን ተስፋ አለ።
👉 3ኛው ደግሞ ከነገ ጀምራችሁ መጠበቅ ነው እንግዲህ እኔም እንዲሁ ነበር ኢንትራንስን ያለፍኩት😁 ስል መልሶልናል።
🔦 ለማንኛውም ትምህርት ሚኒስቴር በዚህች 3ት ቀን ውስጥ ይፋ የማያደርግ ከሆነ ትላልቅ ሚዲያዎች ጋር በመሄድ እንድጠይቁና ቁርጥ ቀኑን እንድነግሩን እናደርጋለን።
© hulumedia
🎖📖🎖
@aplusacademyy
@aplusacademyy
▬▬▬▬▬▬▬▬
2 787
የ 12ኛ ክፍል ውጤትን አስመለክቶ በርካታ ጥያቄዎች እየደረሱን ስለነበር ከሚመለከተው አካል ለማጣራት ሞክረን ነበር።
ከ ትምህርት ሚኒስቴር አካላት የተሰጠን መልስ የ 1ኛ ዙር ፈተና እርማት ተጠናቋል። አሁን የ 2ኛው ዙር እርማት እየተደረገ ነው። ስለዚህ የተማሪዎች ውጤት ወደ ሲስተሙ ከገባ ቡሃላ ለተማሪዎች ይፋ ይሆናል።
ትክክለኛው ይፋ የሚሆንበት ቀን መቼ ነው? እስካሁን ይህ ነው የሚል ቀን አልተወሰነም። ነገር ግን በቅርቡ ይፋ ይሆናል። ተማሪዎች መታገስ አለባቸው ። ውጤቶች ላይ ምንም ስህተት እንዳይኖር ጥንቃቄዎች ከተሰወዱ ቡሃላ ይለቀቃል ።
- Hulumedia
2 787
LOVE
በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና። የዮሐንስ መልእክት 1 4:9
✝️🙏✝️ እንኳን አደረሳችሁ ✝️🙏✝️
2 787
💫💫💫የነገው ፈተና መልስ ✨✨✨✨✨
1 መ
2 ል
3 ካ
4 ም
5 የ
6 ገ
7 ና
8 በ
9 ዓ
10 ል
11ይ
12 ሁ
13 ን
14 ላ
15 ች
16 ሁ
2 787
የዩኒቨርሲቲ ምደባ እንዴት ይሰራል⁉️
የዩኒቨርሲቲ ምደባ የሚሰራው እንደድሮው ጊዜ በቀጥታ በሰዎች ሳይሆን ዘመናዊ እና አለምአቀፋዊ ተቀባይነት ባለው ማሽን ነው።
ታድያምደባው ሲካሄድ በዋነኝነት የተማሪዎችን ውጤት መሰረት በማድረግ ነው፡፡ ይኸውም:-
ምደባው በቅድሚያ ምደባውን ለሚያከናውነው ማሽን እነዚህ የመረጃ ግብዓቶች inpute ይሰጡታል። እነሱም
👉 ከመቁረጫ ነጥብ በላይ ያመጡ ተማሪዎች ስም ዝርዝር
👉 የዩኒቨርሲቲዎች የመቀበል አቅም
👉 የመቁረጫ ነጥብ
👉 የተማሪዎች ውጤት
👉 PHASE (ምድብ)
PHASE ማለት ለምሳሌ እነሱ inpute ሲያስገቡ
PHASE 1 ከ አንደኛ ምርጫ እስከ አምስተኛ ምርጫ
PHASE 2 ከ አምስተኛ ምርጫ እስከ አስረኛ ምርጫ ወ.ዘ.ተ እያለ እንዲሰጥ አድርገው program ያደርጉታል ማለት ነው።
ከላይ ያሉት የመረጃ ግብዓቶች ከገቡለት በኋላ ማሽኑ
1⃣ የተማሪውን ውጤት (ነጥብ)
2⃣ የተማሪውን የምደባ ምርጫ አሞላል
3⃣ የዩኒቨርሲቲዎች የመቀበል አቅምን
መሰረት በማድረግ ተማሪዎችን ይመድባል፡፡ በዚህ መልኩ ምደባ ሲሰራ እነሱ ብቻ በሚያውቁት scale መሰረት:
➖ በጣም ጥሩ ውጤት ያመጣ ተማሪ
PHASE = ONE , CHOICE = ONE
ይደርሰዋል ማለት ነው። ማለትም የመጀመሪያ ምድብ የመጀመሪያ ምርጫ ማለት ነው፡፡
➖ ከዚያ scale ቀጥሎ ያመጣ ተማሪ ደግሞ:
PHASE = 1 , CHOICE = 2
ይደርሰዋል ማለት ነው። ማለትም የመጀመሪያ ምድብ ሁለተኛ ምርጫ ማለት ነው።
የምደባ ውጤት በቅርብ ቀናት ውስጥ ይፋ ይደረጋል።
🎖📖🎖
@aplusacademyy
@aplusacademyy
▬▬▬▬▬▬▬▬
2 787
" የፈተናውን ውጤት በአጭር ጊዜ እናሳውቃለን " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አሳውቋል።
አገልግሎቱ ፤ ይህ የፈተና ሥራ በውጤታማነት እንዲጠናቀቅ አወንታዊ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ምስጋና ያቀረበ ሲሆን ለተፈታኞች ደግሞ መልካም ውጤት ተመኝቷል።
" በአጭር ጊዜ ውስጥ የፈተናውን ውጤት የምናሳውቅ ይሆናል " ያለው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ ተፈታኞች በትዕግስት እንዲጠባበቁ መልዕክት አስተላልፏል።
🎖📖🎖
@aplusacademyy
@aplusacademyy
▬▬▬▬▬▬▬▬
2 787
Addis Ababa City Administration Education Bureau 2015 E. C Grade 12 First Semester Model Exam Time Table
2 787
All Grade 12 Students' Textbooks and Teachers' Guide Books
🇪🇹1.Mathematics textbooks & Guide Book
🇪🇹2.Physics textbooks & Guide Book
🇪🇹3.Chemistry textbooks & Guide Book
🇪🇹4.Biology textbooks & Guide Book
🇪🇹5.Geography textbooks & Guide Book
🇪🇹6.Civics textbooks & Guide Book
🇪🇹7. TD textbooks & Guide Book
🇪🇹8.ICT textbooks & Guide Book
🇪🇹9.Economics textbooks & Guide Book
🇪🇹10.English textbooks & Guide Book
🇪🇹11.አማርኛ textbooks & Guide Book
🇪🇹12.Afam-Oromo textbooks & Guide Book
🇪🇹13.Soomaali textbooks & Guide Book
ከላይ የተጠቀሱትን ሁሉንም የ 12ኛ ክፍል የተማሪዎች እና የመምህራን መምሪያ የያዘ App ስለሆነ ለአጠቃቀም ምቹ ነው.
🎖📖🎖
@aplusacademyy
@aplusacademyy
▬▬▬▬▬▬▬▬
2 787
ወደ ግቢ ጉዞ ለምታደርጉ የ 2ተኛ ዙር የ 12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ተማሪዎች በሙሉ መልካም ፈተና ‼️🙏
ያነበባችሁትን ተረጋግታችሁ የምትሰሩበት ግዜ እንዲኖራችሁ ተመኘሁ 🙏
በሰላም አስጀምሮ እና አስጨርሶ በሰላም ከ ቤተሰቦቻችሁ ጋር ለመገናኘት ያብቃችሁ 🙏
🎖📖🎖
@aplusacademyy
@aplusacademyy
▬▬▬▬▬▬▬▬
2 787
የ12ተኛ ክፍል ውጤት መቼ ይወጣል
በተለያዩ ምክንያቶች በመጀመሪያው ዙር ፈተና መውሰድ ያልቻሉ ተማሪዎች ከታህሳስ 18 እስከ 21 ድረስ ባሉት ቀናት ፈተናቸውን ይወስዳሉ።
የመጀመሪያ ዙር ተማሪዎች ፈተና ውጤት እስካሁን ይፋ ያልተደረገ እና ይፋ የሚደረግበት ትክክለኛ ቀን ያልታወቀ ሲሆን ትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ በፊት በሰጠው ቃል ፤ አጠቃላይ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ውጤት #ከሁለተኛ_ዙር ፈተና በኋላ የሚገለጽ መሆኑን አሳውቆ ነበር ስለሆነም 2ኛ ዙር ተፈታኞች ከተፈተኑ እና እርማት በቶሎ ከተጠናቀቀ በቅርብ ቀናት ይለቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
➳አዲስ ነገር ሲኖር በቻናላችን እናሳውቃለን 🙏
🎖📖🎖
@aplusacademyy
@aplusacademyy
▬▬▬▬▬▬▬▬
2 787
#Update #AddisAbaba
የ2ኛውን ዙር የሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና ለመፈተን #በአዲስ_አበባ ከተማ አስተዳደር የተመዘገቡ ተማሪዎች በክፍለ ከተማቸው በኩል በ16 / 4 /2015 ዓ/ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሳይንስና ቴክኖሎጂ 5 ኪሎ ካምፓስ እንዲገቡ የከተማው ትምህርት ቢሮ ዛሬ አሳስቧል።
የ2ኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከታህሳስ 18 እስከ ታህሳስ 21 ቀን 2015 ዓ/ም ድረስ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ መግለፁ ይታወሳል።
🎖📖🎖
@aplusacademyy
@aplusacademyy
▬▬▬▬▬▬▬▬
2 787
#NationalExam
2ኛው ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከታህሳስ 18 እስከ 21/2015 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።
በሁለተኛው ዙር ለፈተና የሚቀመጡ የሁሉም ክልል ተማሪዎች መለየታቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
በሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚወስዱ ፦
• የመጀመሪያውን ዙር ፈተና በወሊድ ወይም በእርግዝና ምክንያት መፈተን ያልቻሉ፣
• በሕግ ጥላ ስር ወይም በማረሚያ ቤት ሆነው ለመፈተን ያልቻሉ፣
• የሀገር መከላከያ ሠራዊት ወይም የፌዴራል ፖሊስ ወይም የክልል ልዩ ኃይል አባል ሆነው በወቅቱ በግዳጅ ላይ በመሆናቸው ያልተፈተኑ፣
• በህመም ወይም ተቀባይነት ባገኘ ችግር ምክንያት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ፈተና ያልወሰዱ፣
• ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በደረሰው የድልድይ መደርመስ አደጋ ምክንያት ያልተፈተኑ፣
• በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ችግር ምክንያት አንድ ፈተና እንዲፈተኑ የተወሰነላቸው፣
• ተቀባይነት ባገኙ ችግሮች ምክንያት ፈተና እንዲወስዱ የተወሰነላቸው።
2 787
" የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና (የ2ኛ ዙር) ከታህሳስ 18 - ታህሳስ 21 ይሰጣል " - የሲዳማ ክልል ትምህርት ቢሮ
ከዚህ ቀደም በነበረው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ወቅት ፈተናቸውን መውሰድ ላልቻሉ ተማሪዎች ፈተና ለመስጠት እየተሰራ ይገኛል።
ዛሬ ከሲደማ ክልል የትምህርት ቢሮ ባገኘነው መረጃ በተለያዩ ምክንያቶች ፈተና ሳይፈተኑ የቀሩ ተማሪዎችን በ2ኛ ዙር ፈተና ከታህሳስ 18 እስከ ታህሳስ 21 ድረስ ለማስፈተን ዝግጅት ተደርጓል።
@tikvahethiopia
2 787
የሁለኛው ዙር መፈተኛ ቀን ታወቀ!!!
በምዕራብ ሸዋ ዞን ባሉ 7 ወረዳዎች የመጀመሪያ ዙር ፈተና ያልተፈተኑ ሲሆን የሁለተኛው ዙር ፈተና ቀን ታህሳስ 11 2015 እንደሆነ ዛሬ የሸዋ ዞን ትምህርት መመሪያ አረጋግጧል።
ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ዩንቨርስቲዎች ከ ታህሳስ 7-9 ይጓጓዛሉ
የተማሪዎች ዉጤት ከታህሳስ 20 እስከ 25 ውስጥ ባሉት ቀናት ያሳውቃል ተቦሏል።
ሌላ የሰላም እና ፀጥታ ችግር ካላጋጠመን በስተቀር ተማሪዎች ከ ጥር መጀመሪያ ጀምሮ ወደ ዩኒቨርስቲ እንዲገቡ ይደረጋል።
@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
2 787
ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን በዲጂታል ለመስጠት ታብሌቶችን አገር ውስጥ ለማስመረት እንቅስቃሴ ጀምሬያለሁ ብሏል።
ሚኒስቴሩ ይህን ያለው ትላንት የ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸሙን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሲያቀርብ ነው።
የመልቀቂያ ፈተናውን በኢንተርኔት ለመስጠት በውጭ አገር የቴክኖሎጂ ባለሙያ ኢትዮጵያዊያን የሶፍትዌር ሥራዎችን እንዲሠሩ እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገልጸዋል።
ታብሌቶቹን አገር ውስጥ ለማሰራት የተወሰነው በውጭ አገር ለመግዛት ዋጋቸው በመወደዱ ምክንያት እንደሆነ ጠቁመዋል።
የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን በግንቦት 2015 ዓ.ም ለመስጠት መታቀዱን ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም መግለጻቸው ይታወሳል።
🎖📖🎖
@aplusacademyy
@aplusacademyy
▬▬▬▬▬▬▬▬
2 787
📚 ዘንድሮ ጳውሎስ መወዳደር ለምትፈልጉ ተማሪዎች።
📚 ጠቃሚ መረጃዎችን የያዘ ፋይል ነው።(2 years back). refere ብታደርጉት አሪፍ ነው👍።
🎖📖🎖
@aplusacademyy
@aplusacademyy
▬▬▬▬▬▬▬▬
2 787
" ተማሪዎች ፈተናውን ለመፈተን ዝግጅት አድርጉ " - የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ
በተለያየ ምክንያት የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል ላልተፈተኑ ተማሪዎች ፈተናውን በታህሳስ ወር መጀመሪያ ሳምንት ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርይ መምሪያ አሳውቋል።
ትምህርት መምሪያው ፦
- በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በመሸጋገሪያ ድልድይ ተሰብሮ በደረሰው አደጋ ምክንያት የመጀመሪያውን ቀን ፈተና ያልተፈተኑ፤
- በወሊድ ምክንያት ፈተናውን ያልወሰዱ፤
- የተለያየ ማህበራዊ ችግር አጋጥሟቸው ጉዳዩ ለሚመለከተው አካል አሳውቀው ለፈተና ያልተቀመመጡ ፤
- በሀዋሳ ከተማ ማዕከላዊ ማረሚያ ትምህርት ቤት የሚገኙ ተማሪዎች ፈተናውን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው ብሏል።
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ፤ " ትምህርት ሚኒስቴር ፈተናውን ላልወሰዱ ተማሪዎች በታህሳስ ወር 2015 ዓ.ም በመጀሪያ ሳምንት አከባቢ ፈተናው ለመስጠት ቅድመ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ነው " ያለ ሲሆን ተማሪዎች ይህንን አውቀው ፈተናውን ለመፈተን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።
ምንጭ፦ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ
@tikvahethiopia
2 787
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት መቼ ይገለጻል?
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ውጤትን በተመለከተ የትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቀናል።
ሚኒስቴሩ በተለያዩ ምክንያቶች ፈተናውን ላልወሰዱ ተማሪዎች ሁለተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ሰምተናል።
አጠቃላይ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ውጤት ከሁለተኛ ዙር ፈተና በኋላ የሚገለጽ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
©tikvah university
🎖📖🎖
@aplusacademyy
@aplusacademyy
▬▬▬▬▬▬▬▬
2 787
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት መቼ ይገለጻል?
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ውጤትን በተመለከተ የትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቀናል።
ሚኒስቴሩ በተለያዩ ምክንያቶች ፈተናውን ላልወሰዱ ተማሪዎች ሁለተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ሰምተናል።
አጠቃላይ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ውጤት ከሁለተኛ ዙር ፈተና በኋላ የሚገለጽ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
©tikvah university
🎖📖🎖
@aplusacademyy
@aplusacademyy
▬▬▬▬▬▬▬▬
2 787
#update
በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ዩኒቨርሲቲ መሙላት ስለተጀመረ ተማሪዎቻችን የምትፈልጉትን ዩኒቨርሲቲ ከላይ ባለው ኮድ መሠረት መሙላት ትችላላችሁ: :
#FYI
አሞላላችሁን ውጤት ከመጣ በሁአላ ማስተካከል ይቻላል: :
🎖📖🎖
@aplusacademy9_12
@aplusacademy9_12
▬▬▬▬▬▬▬▬
