cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Ethiopia Public health Institutes(EPHI) 🇪🇹

🎗እትዬጵያ የህብረተሰብ ጤና ክብካቤ( Ethiopia Public health institute)EPHI 🎗የህብረተሰብ #ጤና #መረጃዎችን ለሁሉም ማዳረስ ነው።የዜጎች ጤና ለሀገር ብልፅግና!! 🎗በዚህ አድራሻ ሀሳብዎንና ጥያቄዎን ማቅረብ ይችላሉ. ✅ #Timely updates public health information &news

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
3 595
Suscriptores
+224 horas
+167 días
+4730 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

የከፍተኛ አመራር እና የባለድርሻ አካላት ወቅታዊ የወባ ስርጭት ጫናን በዘላቂነት የመግታት አድቮኬሲ መድረክ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሚዛን አማን ከተማ ተካሂዷል። https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid037CZjFY6kTR39kW2Mwvk16ZqjVbZQB6gTUT6R3vjnMQdM72ucNkVxRxcaR9mg7vKtl&id=100064567187444&sfnsn=mo&mibextid=RUbZ1f
Mostrar todo...
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የስርዓተ ጤና ምርምር ዳይሬክቶሬት ከብሔራዊ ስልጠና ማዕከል፣ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ እና ከLondon School of Hygiene and Tropical Medicine ጋር በመተባበር በምርምር ስራዎች እና  መረጃ አቀራረብ ላይ ያተኮረ  የሶስት ቀናት ስልጠና ለኢንስቲትዩቱ መካከለኛ ደረጃ ተመራማሪዎችና የሦስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች   ሰጥቷል። ስልጠናው ተመራማሪዎች በምርምር የሚያገኙዋቸውን  ውጤቶች በብቃት እንዲያስተላልፉ በእውቀት እና በክህሎት ለማስታጠቅ፣ መረጃን በግልፅ እና በተጠያቂነት በእይታ አስደግፎ ማቅረብን ለማስቻል ያለመ ነው። ይህ ስልጠና በተጨማሪም ውጤታማ መልዕክት ማዘጋጀት እና የዝግጅት አቀራረቦችን፣  እንዲሁም በራስ መተማመንን ማዳበርን ያካትታል። በዚህ ወርክሾፕ ማጠቃለያ ላይ የስርዓተ ጤና ምርምር ዳይሬክቶሬት  ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ ጌታቸው የአዘጋጅ ቡድኑን ጥረት በማመስገን በቀጣይም አንስቲትዩቱ የምርምር ስራዎችን ለማገዝ ተቋማዊ አቅም ግንባታ ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ገልፀዋል።
Mostrar todo...
ኢንስቲትዩቱ ከአፍሪካ የላብራቶሪ ሕክምና ማህበር (African Society for Laboratory Medicine [ASLM]) ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የአደገኛ ኬሚካል ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ላይ ያተኮረ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ፡፡ ------------------------ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከአፍሪካ የላቦራቶሪ ሕክምና ማህበር (ASLM) ጋር በመተባበር ከሞሎኪውላር ላቦራቶሪዎች የሚመነጨው አደገኛ የኬሚካል ቆሻሻ (Guanidinium Thiocyanate [GTC]) አያያዝና አወጋገድ ላይ ያተኮረ ስልጠና ከኢትዮጵያና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ባለሙያዎች ለአራት ቀናት (ከግንቦት 20 እስከ 23/2016 ዓ/ም) የሚቆይ ስልጠና በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ስልጠና ማእከል መሰጠት ተጀመሯል፡፡ በዚህ ስልጠና መክፈቻ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሳሮ አብደላህ ስልጠናው እጅግ በጣም አሰፈላጊና ወቅታዊ መሆኑን ሲገልጹ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትም ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ገልጸዋል፡፡ እንዲሁም የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቱዩት በአሁኑ ወቅት የጤናው ዘርፍ ብቁ በሆነ የሰው ሀይል ማደራጀት አስፈላጊ በመሆኑ የኢንስቲቱዩቱ የስልጠና ማእከል በማደራጀት ከሀገር ባሻገር በምሰራቅ አፍሪካ ተመራጭ የስልጠና ማእከል ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻ ይህንን ስልጠና ከኢንስቲትዩታችን ጋር በመተባበር ያዘጋጁትን US-CDCን እና ASLMን ያመሰገኑ ሲሆን, እዲሁም በዚህ የስልጠና ተሳታፊ ለሆኑት የላቦራቶሪ ባለሞያዎች በዚህ ስልጠና የምታገኙትን እውቀትና ክህሎት ተጠቅማቹህ ጠንካራ የሆነ የአደገኛ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስርዓት ወደ መጣችሁበት ስትመለሱ ተግባራዊ እንድታደርጉ በማለት አሳስበዋል፡፡
Mostrar todo...
በኢንስቲትዩቱ NIPN-ኢትዮጵያና በሲዳማ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መካከል የተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ፣ የስርዓተ ምግብ ተግባራትን የማከናወን ስራን ያጠናክራል ------------------------------ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (ኢሕጤኢ) ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ ህብረተሰቡ በአገር አቀፍ ደረጃ ተገቢውን የተመጣጠነ ምግብ ተጠቃሚ ለማድረግ የሁሉም የሚመለከታቸው ሴክተሮች በትብብር መስራታቸው አስፈላጊ መሆኑን አስገነዘቡ። ዶ/ር መሳይ ይህንን የገለፁት ዛሬ በኢሕጤኢ ብሔራዊ መረጃ ፕላትፎርም ለሥነ-ምግብ ((National Information Platform for Nutrition) (NIPN-Ethiopia)) እና በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (ሲሕጤኢ) መካከል ትስስር ለመፍጠር እንዲሁም ስራዎችን ወደ ክልሉ ለማውረድ (ካስኬድ) የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ በተፈራረሙበት የምክክር አውደ ጥናት ላይ ነው። ዋና ዳይሬክተሩ የመግባቢያ ሰነዱን ከተፈራረሙ በኋላ እንደተናገሩት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚደርሱ የጤና ችግሮችን ለመቅረፍ ብዙ እንደሚጠበቅብን እና ፖሊሲ ለመቅረፅ የሚቅርቡ መረጃዎችን ምንጮችን አስተማማኝነት ለማረጋገጥ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መሰብሰብና መተንተን እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። "NIPN-ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ስር ከሥነ-ምግብ ጋር የተገናኙ የፖሊሲ ጥያቄዎችን በማጠናከርና በመተንተን ጉልህ ሚና እየተጫወተ ሲሆን እንዲሀገር የተቀየሱ የስነ-ምግብ ስትራቴጂዎችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት ለማጠናከር ይረዳል። ስለዚህ የመግባቢያ ሰነዱ በሥነ-ምግብ ላይ ፖሊሲውን እና ስትራቴጂውን የመተግበር አስፈላጊነትን ያጠናክርዋል፣” ብለዋል ዶ/ር መሳይ። ዋና ዳይሬክተሩ የጤና እና የስነ-ምግብ ፕሮጀክቶችን ወደ ህብረተሰቡ ለማድረስ የክልል ጤና ቢሮዎች እና የህዝብ ጤና ተቋማት ወሳኝ ሚናን አጽንኦት ሰጥተውታል። ለማንኛውም ተመሳሳይ ፕሮጀክት ስኬት የእነዚህ ዘርፎች ተሳትፎ ወሳኝ ነው፣” ሲሉም ጨምረው ተናግረዋል። "የጤና ፕሮጀክቶችን ስኬት ለማጎልበት NIPN/EPHI ከክልል ጤና ቢሮዎች እና የህዝብ ጤና ተቋማት ጋር በትብብር መስራት አስፈላጊ ነው። ከእነዚህ አካላት ጋር በቅርበት መስራት የአመጋገብ እና የጤና ውጥኖች የታለመላቸው ተጠቃሚዎችን በብቃት እንዲደርሱ ለማድረግ ወሳኝ ነው። በየክልሉ ያሉ የህዝብ ጤና ተቋማትን አቅም በማጎልበት ስራቸውን በጥራትና በብቃት እንዲወጡ ማስቻል የሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ ኃላፊነት ነው ብለዋል ዶ/ር መሳይ። የ EPHI ዋና ዳይሬክተር ከሲህጤኢ ጋር የተፈረመው ሁለተኛው የካሳዲንግ ስምምነት ፍሬያማ እንደሚሆን ያላቸውን እምነትና በክልሎች ደረጃ እየተከናወኑ ያሉትን ተግባራት የኢትዮዽያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መደገፉን ይቀጥላል፣" ብለዋል. የሲሕጤኢ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ በበኩላቸዉ እንደተናገሩት ኢንስቲትዩታቸው በካስኬዲንጉ የተቀመጡትን ዓላማዎች ለማሳካት በትጋት እንደሚሰራ ነው። "በክልላችን ውስጥ የ NIPNን ተግባራት ለማከናወን ሲሕጤኢ ከብዙ ተወዳዳሪዎች መካከል መመረጡ ለኛ ትልቅ ዕድል ነው። ሲሕጤኢ የሚጠበቀውን ያህል ለመስራት ዝግጁ መሆኑን በድጋሚ ማረጋገጥ እፈልጋለሁ፣” ብለዋል፣ ዶ/ር ዳመነ። የምክክር አውደ ጥናቱን የከፈቱት ኢሕጤኢ የምግብ ሳይንስና ስነ-ምግብ ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ማስረሻ ተሰማ የNIPN/EPHI ውጥኖችን በመላ ክልሎች ማስፋፋትና ያለውን መተግበር ያለውን ጠቀሜታ ያብራሩ ሲሆን ዶ/ር አረጋሽ ሳሙኤል የ NIPN-ኢትዮጵያ አስተባባሪ ደግሞ የNIPN-ኢትዮጵያን ሚና እና አላማ ገልፀው ፕሮጀክቱ ከሚንቀሳቀሰባቸው ዘጠኝ ሀገሪት ውስጥ በአፈፃፀም ኢትዮዽያ ከመጀመሪያዎች ሦስቱ ውስጥ መሆኗን አስረድተዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘም ዶ/ር ታደሰ ዘርፉ ስለ ፕሮጀክቱ ካስኬዲንጉ ለምን እንዳስፈለገ ጠቅልል ያለ ፅሑፍ አቅርበዋል። NIPN/EPHI ከዚህ ቀደም ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር ተመሳሳይ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ስራውን በሚጠበቀው መልክ እንዲተገበር ማድረጉ የሚታወስ ነው።
Mostrar todo...
ኢንስቲትዩቱ ከአፍሪካ የላብራቶሪ ሕክምና ማህበር (African Society for Laboratory Medicine [ASLM]) ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የአደገኛ ኬሚካል ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ላይ ያተኮረ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ፡፡ ------------------------ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከአፍሪካ የላቦራቶሪ ሕክምና ማህበር (ASLM) ጋር በመተባበር ከሞሎኪውላር ላቦራቶሪዎች የሚመነጨው አደገኛ የኬሚካል ቆሻሻ (Guanidinium Thiocyanate [GTC]) አያያዝና አወጋገድ ላይ ያተኮረ ስልጠና ከኢትዮጵያና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ባለሙያዎች ለአራት ቀናት (ከግንቦት 20 እስከ 23/2016 ዓ/ም) የሚቆይ ስልጠና በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ስልጠና ማእከል መሰጠት ተጀመሯል፡፡ በዚህ ስልጠና መክፈቻ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሳሮ አብደላህ ስልጠናው እጅግ በጣም አሰፈላጊና ወቅታዊ መሆኑን ሲገልጹ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትም ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ገልጸዋል፡፡ እንዲሁም የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቱዩት በአሁኑ ወቅት የጤናው ዘርፍ ብቁ በሆነ የሰው ሀይል ማደራጀት አስፈላጊ በመሆኑ የኢንስቲቱዩቱ የስልጠና ማእከል በማደራጀት ከሀገር ባሻገር በምሰራቅ አፍሪካ ተመራጭ የስልጠና ማእከል ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻ ይህንን ስልጠና ከኢንስቲትዩታችን ጋር በመተባበር ያዘጋጁትን US-CDCን እና ASLMን ያመሰገኑ ሲሆን, እዲሁም በዚህ የስልጠና ተሳታፊ ለሆኑት የላቦራቶሪ ባለሞያዎች በዚህ ስልጠና የምታገኙትን እውቀትና ክህሎት ተጠቅማቹህ ጠንካራ የሆነ የአደገኛ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስርዓት ወደ መጣችሁበት ስትመለሱ ተግባራዊ እንድታደርጉ በማለት አሳስበዋል፡፡
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.