cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ፍራሽ አዳሽ

የተለያዩ የጥበብ ስራዎች ✔ፊልሞች ✔ግጥሞች ✔ትረካዎች ✔ሙዚቃዎች ✔መረጃዎች ✔ትምህርቶች ✔ጥርስ እማያስከድኑ ቀልዶች በነዚህ ቀልድ እና ቁም ነገሮች ሂወቶን እናድሳለን ከርሶ አልፎ የወዳጅ ዘመዶ ጓደኛ ሂወት እንዲታደስ ይኋዉ መጋበዣ linku 👉 @frash_adash @frash_adash 4 any comment and promotion @expesive12

Mostrar más
Etiopía6 542Amárico5 831La categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
788
Suscriptores
Sin datos24 horas
+17 días
-230 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

"የጥሩ ጊዜ መጥፎነቱ ማለፉ ነው የመጥፎ ጊዜም ጥሩነቱ እሱም ማለፉ ነው🥰 " https://t.me/frash_adash
Mostrar todo...

በሥተመጨረሻ ሁላችንም ታሪክ ነን!!!!! https://t.me/frash_adash
Mostrar todo...
ፍራሽ አዳሽ

የተለያዩ የጥበብ ስራዎች ✔ፊልሞች ✔ግጥሞች ✔ትረካዎች ✔ሙዚቃዎች ✔መረጃዎች ✔ትምህርቶች ✔ጥርስ እማያስከድኑ ቀልዶች በነዚህ ቀልድ እና ቁም ነገሮች ሂወቶን እናድሳለን ከርሶ አልፎ የወዳጅ ዘመዶ ጓደኛ ሂወት እንዲታደስ ይኋዉ መጋበዣ linku 👉 @frash_adash @frash_adash 4 any comment and promotion @expesive12

And good night 🙌
Mostrar todo...
"አያስፈራም?" አለቺኝ በሚጣፍጥ የልጅ ለዛ ባለው ንግግሯ... ምን እንዳስፈራት አልገባኝም ፊቴን በአሉታ ነቅንቄ ሐሳቧን እንድትቀጥል በጉጉት ተመለከትኳት። ትኩር ብላ አይታኝ ንግግሯን ቀጠለች... " በቀን መሸነፉን ፤ በቀን መረታቱን ፤ መናቁን መገፋቱን ዋጥ አድርጎ ይዞ አብሮህ በቀልዶችህ የሚስቅ፣አብሮ እየበላ አብሮ እየጠጣ የእርሱን ቀን የሚጠብቅ ሰው እንዳለ ስታስብ አያስፈራም? አለች በጥያቄ እየተመለከተቺኝ። አብረውኝ የሚስቁትን በእዝነ ልቦናዬ ማየት ዠመርኹ... ተመልክታኝ ፈገግ አለችና..."ፈራህ እንዴ?" አለቺኝ። (መች እንዳስብ ፋታ ሰጠሺኝ 😁) መልሴን ሳትጠብቅ " አትፍራ ! በቀልን ሳይሆን ፈጣሪን ፈርተህ መልካም አድርግ። መልካም ስራ አርነት ያወጣሃል አለችና ትከሻዬን ተንተርሳ በሐሳብ ነጎደች...እኔም ፀጉሯን እየዳበስኹ ተከተልኋት። ከ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ ©ሶፊ
Mostrar todo...
የፌስቡክ ትዊተር እና ኢንስታግራም አልጎሪዝም ወደ አፍሪካ የሚተላለፈው ሆን ተብሎ በፆታዊ እንቅስቃሴ እና በብልግና ላይ ያተኮረ ነው። እኔ ሁለት የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮችን አስተናግዳለሁ፣ አንደኛው እንግሊዝኛ ተናጋሪ የአፍሪካ አገሮች ላይ ያተኮረ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በአሜሪካ እና በካናዳ ላይ ያተኮረ ነው።  የአልጎሪዝም ፍሰቶች በጣም የተለያዩ መሆናቸውን አስተውያለሁ። የእርስዎ ስኪት ወይም ይዘት በወሲብ ላይ ያተኮረ ከሆነ ብዙ ሰዎችን እንደሚደርስ እና በአፍሪካ ውስጥ ብዙ ምላሽ እንደሚያገኙ ያስተውላሉ።  ይህ በምዕራባውያን አገሮች ውስጥ አይከሰትም. የማህበራዊ ሚዲያ አልጎሪዝም ሆን ብሎ ወሲባዊ ይዘትን ወደ አፍሪካ ያስተዋውቃል እና አስተማሪ ይዘቶችን ይቀንሳል። የእርስዎ ስኪት ስለ ወሲብ ወይም እርቃንነት ከሆነ ከአስተማሪ ይዘት ጋር ሲወዳደር እየጨመረ ይሄዳል።  በሞኝ ወሲባዊ ወይም ሙሙ ይዘት በየቀኑ ሁለት ሺህ ተከታዮችን በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ። ነገር ግን የእርስዎ ይዘት ጥራት ያላቸውን ሀሳቦች ወይም አስተማሪ ስራዎችን ለማስተዋወቅ ከሆነ የማህበራዊ ሚዲያ ስልተ ቀመሮች አያስተዋውቁትም ወይም በቫይራል እንዲሰራጭ አያደርገውም። ኢሞራላዊ ይዘትን ማስተዋወቅ ሆን ተብሎ በአፍሪካ ላይ  እየተደረገ ነው። በዩኬ፣ አሜሪካ ወይም ቻይና ያሉ የወጣትነት ይዘቶችን ተመልከት፣ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያሉ ወጣቶች አዳዲስ የቴክኖሎጂ ሀሳቦችን ወይም መሰረታዊ ማህበራዊ ግንኙነቶችን እንደሚያስተዋውቁ ታውቃለህ፣ ነገር ግን በአፍሪካ ውስጥ ያለውን ስኪት ወይም ይዘት ተመልከት፣ በተለይም ናይጄሪያ፣ ኬንያ፣ ሁሉም ነገር ስለ ወሲብ፣ ራቁት ገላ  እና ብልግና ነው። ቻይናውያን፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና አሜሪካውያን ልጆች በሳይንስ እና ምህንድስና አዳዲስ ፈጠራዎችን ለመፈተሽ ማህበራዊ ሚዲያ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እየተጠቀሙ ነው፣ በአፍሪካ ውስጥ ማህበራዊ ሚዲያዎችን ጾታን፣ ብልግናን እና ገንዘብን መናፍስታዊ ድርጊቶችን ለማስተዋወቅ እንጠቀማለን። አዲስ የአይምሮ ቅኝ ግዛት ወደ ወሲብ፣ እርቃን ሰውነት እና ብልግናን በአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያችን እያየን ነው። የምዕራባውያን ሀገራት አፍሪካን ለማጥፋት እና ህዝቦቻችንን እንደገና ለመገዛት ማህበራዊ ሚዲያን እንደ መሳሪያ ይጠቀማሉ። ወጣቶቻችን በየቀኑ በማህበራዊ ድህረ ገጽ ላይ ይህን አሉታዊ ወሲባዊ ይዘት እየበሉ ሲሄዱ ውጤታማ እና ደደብ ያደርጋቸዋል። በእኛ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያለው እርቃንነት መጠን ሊስተካከል ይገባል። ይህን እወቅ፣ ሰውን የሚያጠፋው የሚገባው እርሱ ነው። እንደ ህዝብ ወደፊት መሻሻል ማየት ካለብን ይዘታችን ለውጥ ያስፈልገዋል።  ማህበራዊ ሚዲያ ቀስ በቀስ ባህላችንንና ሥልጣኔያችንን እያጠፋ ነው። @books_worldd #ሼር
Mostrar todo...
🐪ሶሪያዊዉ ጋዜጠኛ በአገሩ ፍርስራሽ ለይ ቆሞ አገራቸውን ከማፍረሳቸው በፊት  የነበረውን ሁኔታ መለስ ብሎ በምሬት እያስታወሰ  እንዲህ በእንባው ጻፈ :-" " ተከፋፍለን ነበር። እንጨቃጨቅ ፤ እንከራከር ፤ እንጣላ  ነበር።  መንፈሳዊ እሴቶች ወድቀው ነበር። ማናችንም ለማናችንም ግድ አልነበረነም። "ሌሎች ደግሞ  ራሳቸውን ገለልተኛ አድርገው በሩቅ ቆመው ያዩን   ነበር።  ሌሎችም በእለት ሕይወታቸው ለይ ተጠምደው ነበር። ማንም እያስተዋለ አልነበረም። " ይኸ ሂደት እያደረ ጠነከረና ቀዳዳ ሲያገኝ ድንገት ፈነዳና አገራችንን በሁላችንም ለይ አፈረሳት። አገራችን አይናችን እያየ ሳናስበው ድንገት  ፊታችን  ለይ  ነደደች። "ያኔ ታዲያ ማናችንም በሰአቱ አገራችንን በማፍረስ ሂደት ለይ  እንደነበርን አላስተዋልንም ነበር። አገራችን መፍረሷን ያወቅነው አገራችን በሁላችንም ለይ ፈርሳ ሲጨልምብን ነበር.........። "በወቅቱ አለን አለን ሲሉ የነበሩ የየቡድኑን መሪዎችን ጨምሮ ሕጻናትና እናቶችን ሳይምር በወቅቱ  ገለልተኞች የነበሩትን ሳይለይ አገራችን ሁላችንንም በፍረስራሿ ለይ ቀበረችን። ። " እያለ ይቀጥላል። ዛሬ ሶሪያውያኑ አገራቸውን ዳግም ማግኘት ይፈልጋሉ። አላገኟትም ። የለችምና !! ልብ ያለው ልብ ይበል‼️‼️‼️ via-Wondwosen seifu kidus @books_worldd #ሼር
Mostrar todo...
📃ደብዳቤ📄 መስከረም 2 ይድረስ ለአንተ እንገናኛለን መስከረም 2..ትዝ ይልኻል ድሮ ዘምረነው ነበር-አዎ ያኔ  ልጆች ሳለን።ዜማውን ተከትለን  ግጥሙን ብለነዋል። ከየት እንደሆነ ባናውቀውም እኛም ልጅነታችንን አስደስተንበታል። መቼ እለት ነው እንደለመድኩት የሀሳብ ጥጤን ልፈትል እንዝርቴን ይዤ ደጅ  ተቀምጫለሁ።በርከት ያሉ ልጆች ከኔ ትንሽ ፈቀቅ ብለው ልጅነታቸውን ይጫወታሉ።መንጫጫታቸው በዝቶ ከሀሳቤ ሲያናጥቡኝ'እነዚህ ውሪዎች ካልጠፋ ቦታ እዚህ ምን ያንጫጫቸዋል?' እያልኩ እበሰጫጭ ነበር።በዃላ ግን ጨዋታቸው ሀሳቤን አሽቀንጥሮ ሙሉ ቀልቤን ተረከበ።እንደ መቅናትም እንደ መፍዘዝም ሸነጥ አርጓኝ እንደ መነሳትም እያረገኝ አያቸው ነበር።እናልህ'እንገናኛለን መስከረም 2'የሚለው የልጆች መዝሙር የመጨረሻ ስንኝ ወደገፋሁት ሀሳቤ መለሰኝ።.....እኔ ምልህ የኔ እና የአንተ መገናኛ መሰከረም 2 ግን የትኛው ዘመን ላይ ይሆን የወደቀው?ወይስ አንተ በብስክሌት እኔ በፉጨት(መዝሙሩ ላይ ያለ ቃል)ስንመጣ ተላልፈን መገናኛችን መስከረምን ያለፈው ዘመን ጥለነው ይሆን?አይ እንደዛማ አይሆንም ደጅ ላይ ተቀምጨ ጥጥ የምፈትልለት ጋቢ ለማን ሆነና! እንደው ግን ምን አለበት ያኔ'እንገናኛለን በዚህ አመት መስከረም 2'ብለን ዘምረን በነበርና እንደ መውጣትም እንደ መግባትም ያረገኝን የመገናኘት እንቆቅልሻችንን ብንፈታው።ያንተም ዝምታ እኮ ልክ አጣ።ደጅ ተቀምጨ የምፈትለው የሀሳብ ጥጤም አሁንም አሁንም ከእንዝርቱ እየተቆረጠ የጋቢውን መቋጯ እድሜ አረዘመው።ነው ወይስ እንቆቅልሽ የሆነብኝን የመዝሙሩን የመጨረሻ ስንኝ በራሱ መዝሙር የመጀመሪያ ስንኝ ልፍታው? ...."ሐና ሐና ይለኛል የት አባቱ ያውቀኛል...." እኔም የማያውቀኝን ሰው ከማላውቀው መስከረም ላይ ለምን ብየ እስከ መቼስ ልጠብቀው? ያንተው 📝 ራሔል
Mostrar todo...
አዲስ ዓመት ለሱ ማልቀስ ለታከተው ካምና ከካቻምናው ህመሙ ለጠናው እንደ ጤዛ ረግፎ ፥ ዝሎ ሁለመናው ማርቆስም ዮሐንስ ፥ሉቃስ ስለሆነ አዲስ ዓመት ለሱ ፥ አዲስ መቼ ሆነ ትንሽ እፍኝ ስንዴ ፥ ላጣ ከማጀቱ በርሃብ በጥማት ፥ ለታጠፈ አንጀቱ ዮሐንስ ቢገባ ፥ ሉቃስም ቢወጣ ልዩነት የለውም ፥ የለት ጉርሱን ላጣ ✍አቤል ታደለ 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱 @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19
Mostrar todo...