cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegaciĂłn. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

ሶፊ 👉 @umsofi27 enjoy ✌ "I don't write words; i write sentiments." -®Sofi Do what it worth to live..." . . . በካፊያ አልደነግጥም የተዘጋጀውት ለዶፍ ነው። . . #💚💛❤ @sofimemo

Mostrar mĂĄs
EtiopĂ­a4 651AmĂĄrico3 492La categorĂ­a no estĂĄ especificada
Publicaciones publicitarias
3 693
Suscriptores
-424 horas
-97 dĂ­as
-1330 dĂ­as

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Photo unavailableShow in Telegram
...ተስፋ መቁረጥ አያውቀኝም !…ያው እንደ ሰው ይከፋኝ አዝን እና እተክዝ ይሆናል…ነገር ግን በጭረሽ ተስፋ አልቆርጥም…እራሴን ከፍታው ላይ ብቻ ነው ማየት እምፈልገው…🤍   ✍🏽 ፊሊሞን 🍷
Mostrar todo...
❤ 24👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
"ናፍቀሺኛል... ቲሽ ! ናፍቀሺኛል ብቻ ናፍቆቴን አይገልፀውም። ቃለ አጋኖ ልጨምርበት ይሆን ? እርሱም በቂ አይደለም ። በጣም ናፍቀሺኛል ብላትስ? ግን በጣም ብቻ አይደለም። ታዲያ ምን ይሻላል ? የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ ©ሶፊ
Mostrar todo...
❤ 9😍 4🤷‍♀ 2🤩 2
English book pdf የምታገኙበት App ነው። Share ማንበብን እናበረታታ ! ©ሶፊ
Mostrar todo...
👍 3❤ 2👏 1
ቅንድም አንዱ በውስጥ መስመር መጥቶ " ቻናሉን ይዘህ ከምትተኛበት ለምን ህብረተሰቡን የሚያነቃ ነገር አትፅፍበትም " አለኝ ። "ቆይ አሁን ልተኛ ነው ስነቃ እፅፍላቸዋለሁ " ብዬው ነበር ሳልፅፍላችኹ ረሳሁት። አሁንም እንቅልፌ መጣ የሚያነቃ ነገር ሳልፅፎላችሁ ልተኛ ነው። እንደውም ለመንቃት መጀመሪያ በርትተን እንተኛ። ©ሶፊ
Mostrar todo...
🤣 23👍 10😁 7❤ 1😍 1
"ሰበቡ ብዙ ነው እንዳፈር ለሳሱለትማ ነገር ባላየሁ ባልወደድኩህ ምን ነበር... ኡኡኡ ምቀኛው ብዙ ነው እንዳፈር ለሳሱለትማ ነገር ባላየሁ ባልወደድኩህ ምን ነበር... ኡኡኡ" "ሰማሀት?" አለቺኝ አንዳች የምስራች እንደተበሰረ ሰው በደስታ እየተፍነከነከች። "ማንን?" አልኳት ካቀረቀርኩበት አሳዛኝ የፌስ ቡክ ወሬ ቀና እያልኩኝ። "ሚካያን ነዋ!" አለች እንዳኮረፈ ሰው ከንፈሯን ጣል አድርጋ። "እእ..." ብዬ መከፈቱን እንኳን ያላስተዋልኩትን ሙዚቃ ለማዳመጥ ጆሮዬን ጣል አደረኩ። በሚማርክ ድምፅ የተዜመ፤ በስሱ የተከፈተ ሙዚቃ ወደ ጆሮዬ ፈሰሰ... ላንተ ስል ሲያቀብጠኝ ወድጄ ሰስቼህ እንደ ስለት ልጄ ላንተ ስል ለሊትና ቀን ቀን ክፉውን አያለኹ ሰቀቀን... ሰማዋት በማለት አይነት ወደ እሷ አቅጣጫ ዞሬ ፈገግ አልኩኝ። "ሰማሀት አይደል ?" ብላ እሷም ፈገገች። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሙዚቃ መስማት እርግፍ አድርጌ እንደተውኩ ታውቃለች።እሷ ስትጋብዘኝ ግን በድሮ ሙዚቃ አልጨክንም በተለይ...በእዮብ፣በጂጂ እና በሚካያ። "አዎ ሰምቻታለሁ" አልኳት። ፈገግታዋ ሳይቀዘቅዝ (ማግኘትና ማጣት የማያደበዝዘው ፈገግታ፤መውጣትና መውረድ ሳቋን አያሸንፉትም፤ ሁሌ ስትስቅ ነው የማውቃት...ሞልቶላት ግን አይደለም።) "ታውቃለህ ስላንተ እንደዚህ ነው የማስበው..." አለቺኝ። "እንዴት?"አልኳት ለመስማት ጓጉቼ አቀማመጤን እያመቻቸው። "በስስት..." አለችና ትንሽ አሰብ አድርጋ ቀጠለች። "እኔ ወንፊት ነበርኩ ሁሉንም ለሰው የማወራ እኔ ጋር የማስቀረው ምንም ነገር የሌለኝ።ወንፊት እንኳን ከቀዳዳው የገዘፈውን ነገር ለራሱ ያስቀራል።እውነት ነው የምልህ ሰው የማያውቀው፤ያላወራኹት ደስ የሚል ነገር እንዲኖረኝ ስመኝ ነው የኖርኩት...ያ አንተ ነህ።ለሰው ያላወራሁ በስስት የያዝኩህ፣የምጠነቀቅልህ...ያ የተመኘውት ሰው አንተ ነህ።" አለቺኝ በፈገግታ እየተመለከተቺኝ። ፈገግታዋ ከጥርሴ አልፎ ወደ ውስጤ ሰርፆ በሐሴት ሞላኝ። ሶሻል ሚዲያው የነጠቀኝን ትኩረት አስመልሼ ዙሪያ ገባውን ቃኘውት...ምሳ ልንበላ የተቀመጥንበት ቤት ደጋግሜ የመጣሁበት ቢሆንም ዛሬ እንደ አዲስ አምሮ ታየኝ። ይሄን አንብቦ... "Oh Sofi is in love." የሚል አይጠፋም። እኔ ግን እላለኹ እነሆ ይሄ ድርሰት ምሳ ሊበሉ ከፊቴ የተቀመጡ ጥንዶችን ንግግር በምናብ ተስሎ ተፃፈ። ከተቀደደው ማስታወሻ 18/02/2015 ©ሶፊ
Mostrar todo...
😍 16😁 8👍 5👏 2❤ 1
Photo unavailableShow in Telegram
ለሚንቃት ወንድ ነፍሷን መበደል... ለኩራተኛው እራሷን መግደል... የዘመናችን ሴትነት አይደል... የሚወዳትን መች ትወድና... ትሳለቃለች ፍቅርን በትና... ከፍቅር ሸሽታ ፍቅርን ፍለጋ... ትባክናለች ከማይሆን ሰው ጋ... -Mahiru 🫡
Mostrar todo...
❤ 18👍 8🔥 1🤬 1
Photo unavailableShow in Telegram
"እወድሻለሁ" እንኳን ብሎኝ አያውቅም ብለሽ ማማረርሽን ሰማሁ... እውነት እንደዛ ነው የምታስቢው? ባልወድሽ ነው ከስርሽ የማልጠፋው? ባልወድሽ ነው አስሬ ስምሽን የምጠራው? ባልድሽማ...እስክትረሽኝ ነበር ከእይታሽ የምጠፋው...እኔ እንደዛ ነኝ የማልፈለግበት ስፍራ የምቆይ አይነት ሰው አይደለውም። አየሽ ስስቴ ቃላት ሲደጋገም አቅሙን ያጣል...እንደቀላል ነገር "እወድሻለሁ" ይባላል? በእኔ ቤት ይሄ ውድ የሆነ ቃል መለኮታዊ ሀይሉን አጥቶ ተርታ ቃል እንዳይሆንብኝ...መጠንቀቄ ነበር። እንጂ... እ ወ ድ ሻ ለ ሁ። ከዚህ ህይወት ፤ ከዚህ አለም ይዤሽ ልጥፋ ? ከ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ ©ሶፊ
Mostrar todo...
🥰 31👏 10👍 3❤ 1
Photo unavailableShow in Telegram
"What Kind of Person Are You?" Me??? I am different. I am imaginative. I am far more than I have ever revealed People know me as someone strong But I'm fragile inside. I'm someone who doesn't show my vulnerable side Not because I don't have anyone It's because I don't want them to stop relying on me I am someone who smiles at small things But I am also someone who gets hurt very often I'm a shoulder to cry on for many people But I'm also the one who has no shoulder to cry and to rely on. I'm someone who forgives very fast But I'm also someone who can't forget everything that's said. I'm someone who adores sunlight Yet, I'm also someone who discovers solace in the darkness of night. I'm someone who has never been asked, "Are you okay?" Yet, I'm also someone who will respond with, "I'm okay, I'm fine, nothing changed" ~Unknown source
Mostrar todo...
❤ 7👍 2💔 2🔥 1