cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ሰበር ዜና ET🇪🇹

መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇 @Akiyas21bot የyoutube ቻናላችን ይቀላቀሉ👇👇

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
18 653
Suscriptores
+224 horas
-257 días
-10230 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

በሳውዲ አረቢያ በሞት ሊቀጣ የነበረው ኬንያዊ ግለሰብ ሁለት ቀን ሲቀረው ቅጣቱ ተራዘመለት በሳውዲ አረቢያ በሞት ሊቀጣ የነበረው ኬንያዊ መጠነ ሰፊ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ መደረጉን ተከትሎ በመጨረሻው ደቂቃ እረፍት አግኝቷል። የአንጋፋው ጋዜጠኛ ዶሮቲ ክዌዩ ልጅ እስጢፋኖስ ሙንያኮ እ.ኤ.አ በ2011 ከባልደረባው ጋር በባህረ ሰላጤው ሀገር ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ በግድያ ወንጀል በመሳተፍ የሞት ቅጣት ብይን ተሰጥቶበታል። የሙንያኮ ደጋፊዎች በከፈቱት ዘመቻ ሌሎች የሙት ፍረደኞች ሲገደሉ እርሱ ግን በህይወት ለመትረፍ በቅቷል። የሞት ፍርደኛው ሙንያኮ በሳውዲ ህግ መሰረት ቤተሰቡ ለሟች ቤተሰብ በምትኩ ካሳ ለመስጠት ከተስማማ የሞት ፍርድ ሊነሳ ይችላል። በኬንያ የሚኖሩ ቤተሰቦቹ ለሟች ቤተሰብ የሚፈለገውን የደም ገንዘብ ሶስት ሚሊዮን ተኩል የሳዑዲ ሪያል ወይን 940 ሺ የአሜሪካን ዶላርለማሰባሰብ ሲሞክሩ ቆይተዋል። ሰኞ እለት ሙንያኮ ሊገደል ሁለት ቀናት ሲቀረው የኬንያ የውጭ ጉዳይ ዋና ፀሃፊ የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ሞትን ለሌላ ጊዜ ለማስተላለፍ ያቀረበውን ጥያቄ "በሁሉም ወገኖች መካከል ተጨማሪ ድርድር" ለማድረግ "በትህትና ተቀብላለች" ብለዋል።ዋና ፀሀፊ ኮሪር ሲንግ ኦይ በማህበራዊ ሚዲያ መድረክ ኤክስ ላይ መልዕክታቸውን አስፍረዋል።ይህን ጉዳይ ይበልጥ ተቀባይነት ያለው መደምደሚያ ላይ ለመድረስ እየተንቀሳቀስን ነው ብለዋል። በዚህም ለሁለቱም ቤተሰቦች ለሟችም ሆና ለገዳይ በጣም የሚያስፈልገውን ምላሽ ለመስጠት የምናደርገውን ጥረት እንቀጥላለን። ከሳዑዲ አጋሮቻችን ጋር ያለን ወዳጅነት፣ እንዲሁም በሁሉም የኬንያውያን መልካም ፈቃድ ላይ የተመሰረተ ነው ሲሉ አክለዋል።(ስምኦን ደረጄ) ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት     👉 @Akiyas21bot    @ET_SEBER_ZENA @ET_SEBER_ZENA
Mostrar todo...
👍 2
ደመወዝ‼️ 👉 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትናንት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ላይ የፌደራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010ን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ መክሯል። 👉የመንግስት ሰራተኞች የሰው ሀይል ምልመላና መረጣ ግልጽነት ባለው ውድድርና ብቃት ላይ የተመሰረተ ሆኖ ሁሉንም ባካተተና ብዝሀነትን በጠበቀ መልኩ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ስርአት መዘርጋት በማስፈለጉ ረቂቅ አዋጁ መዘጋጀቱ ተነግሯል። በረቂቅ አዋጁ ማሻሻያ ከተደረገባቸው ጉዳዮች ውስጥ ፦ ✔የደሞዝ ጭማሪ ✔የደሞዝ እርከን ✔ክፍያና ጥቅማጥቅሞች ማትጊያና ማበረታቻ ስርአት ✔ የሰራተኞች ብቃት  ምዘናና ማረጋገጫ ስልጠና አሰጣጥ ስራ ስምሪት እና ነጻ ገለልተኛ ስርአት መገንባት፣ ✔ የመንግስት ሰራተኛነት ውል ማቋረጥና ማራዘም የሚሉና ሌሎች እንደሚገኙበት ገልጸዋል፡፡ ✔ረቂቅ አዋጁ አዋጅ ቁጥር 13/2016 ሆኖ በሙሉ ደምጽ ለሰው ሀብት ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል፡፡ =ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት     👉 @Akiyas21bot    @ET_SEBER_ZENA @ET_SEBER_ZENA
Mostrar todo...
👍 9 3
ፖሊስ ጣቢያው ተዘረፈ‼️ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወልቂጤ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ዝርፊያ እንደተፈጸመበት ተነግሯል፡፡ ሸገር ኤፍ ኤም እንደዘገበው በፖሊስ ጣቢያው ዝረፊያ የተፈፀመው ከትናንት በስተያ ሰኞ ግንቦት 5/2016 ዓ.ም  ከምሽቱ 7፡40 ገደማ ነው ብሏል፡፡ በዝርፊያው ለጊዜው ተለይተው ያልታወቁ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ከፖሊስ ጣቢያው እንደተወሰዱ የወልቂጤ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ትዕግስቱ ፉጅየ ነግረውናል ያለው ዘገባው በተጨማሪም ከጣቢያው ተዘርፎ የነበረ ፓትሮል መኪና መንገድ ላይ መገኘቱን ኃላፊዋ ነግረውናል ብሏል፡፡ በአሁን ሰዓት ፖሊስ ጣቢያው ታሽጎ የማጣራት ሂደት እየተከናወነ እንደሆነም ነው የተሰማው፡፡ =================== ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት     👉 @Akiyas21bot    @ET_SEBER_ZENA @ET_SEBER_ZENA
Mostrar todo...
በወላይታ ዞን የሶስት ወር ደመዝ ያልተከፋላቸው የመንግስት ሰራተኞች ሰልፍ መውጣታቸውን የአዩዘሀበሻ ምንጮች ገለፁ‼️ በወላይታ ዞን ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ 3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የዞኑ ገቢዎች መምሪያ ባለፈው ሳምንት ገልፆ ነበር። በትናንትናው ዕለት የሶስት ወር ደሞዝ ባለመከፈሉ አደጋ ላይ ወድቀናል የሚሉ የዎላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ መንግስት ሰራተኞች በሰላማዊ ሰልፍ እስከ ክልሉ ርዕሰ መስተደድር ቢሮ ድረስ መሄዳቸውን የአዩዘሀበሻ ምንጮች ገልጸዋል። የመንግስት ሰራተኞችን የወከሉ ሰልፈኞቹ ጥያቄያቸውን ይዘው ወደ አደባባይ እንዲወጡ ያስገደዳቸው የወረዳውን ሆነ የዞኑን መንግስት በተደጋጋሚ ቢጠይቁም በቂ ምላሽ ባለመሰጠቱ እንደሆነ አንድ የሰልፉ አስተባባሪ ገልፆልናል። በተቃራኒው ዞኑ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ ከ 3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ የተገለፀ ቢሆንም በአከባቢው ልማት ስራዎች ቆሞ በአብዛኛው መዋቅር ደመወዝ መክፈል አለመቻሉ ለበርካቶች ጥያቄ ፈጥሯል)። =================== ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት     👉 @Akiyas21bot    @ET_SEBER_ZENA @ET_SEBER_ZENA
Mostrar todo...
ባለቤቱን ቤት ውስጥ ለ6 ዓመታት ቀብሮ ቤተሰቦቿን አረብ ሀገር ሄዳለች ብሎ ያታለለው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ በሸገር ከተማ አስተዳደር ገላን ክፍለ ከተማ አንዶዴ ወረዳ ውስጥ አቶ ደበበ ተሰማ እና ወ/ሮ ዝናሽ ባይሳ የተባሉ ጥንዶች ከ2004 ጀምሮ እስከ 2010 ዓ.ም ድረስ አንድ ልጅ አፍርተው በትዳር አብረው ይኖሩ እንደነበር የሸገር ከተማ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ በእነዚህ ዓመታት ውስጥ  ከ2004 ዓ.ም እስከ 2007 ዓ.ም ሚስት ወ/ሮ ዥናሽ ወደ አረብ ሀገር ሄዳ ነበር፡፡ ከአረብ ሀገር ስትመለስ አንድ ልጅ ወልደው በመኖር ላይ ሳሉ ከቆይታ በኃላ ሚያዝያ 25 ቀን 2010 ዓ.ም ነው ምሽት ላይ  ሚስት በድጋሚ ኮንትራት ስላላት ወደ አረብ ሀገር ለመሄድ ሀሳብ ታቀርባለች ባል ግን በዚህ ፍቃደኛ አልሆነም፡፡ ከሀገር መውጣት  እንደማትችል እና እዚው አብረን መኖር አለብን በማለት በሀሳቧ እንደማይስማማ ያሳውቃታል፤ በሁኔታው ወደ ከፍተኛ ጭቅጭቅ ውስጥ ይገባሉ  ጭቅጭቁ እና አለመግባባቱም ከሮ ባል አካፋ አንስቶ የሚስቱን ጭንቅላቷን ከመታት በሓላ በህይወት ትኑር አትኑር የሚለውን ሳያረጋግጥ ቤት ውስጥ ጭቃ ለመመረግ የተቆፈረ የአፈር ጉድጓድ ውስጥ ይቀብራታል፡፡ ባል ከሶስት ቀን በሓላም ወደ ቤተሰቦቿ በመሄድ ልጃቸው  ወደ አረብ ሀገር እንደሄደች ይነግራቸዋል፤ ቤተሰቦቿም እንዴት ሳትነግራቸው እንደሄደች ላቀረቡለት ጥያቄ እንዳትሄድ እናንተ ስለከለከላቿት ነው ብሎ ያሳምናቸዋል እነሱም ይቅናት በማለት ጉዳዩን እንደተውት የሸገር ከተማ አስተዳደር የህፃናት እና ሴቶች ጉዳይ ፅ/ቤት ኃላፊ ኮማንደር ረቢሱ ደቻሳ ተናግረዋል  ፡፡ በዚህ ሁኔታ ግን ለ6 ዓመት ያህል ቤተሰቦቿ ስለሷ ምንም አይነት መረጃ ባለማግኘታቸው ተጠራጥረው ባልን ይጠይቁታል ባልም እሱ ጋር እንደምትደውል እና የቤት እና የመኪና መግዣ እስኪሞላላት ወደ ሀገር አልመለስ እንዳለችው ለቤተሰብ ይናገራል፡፡ ቤተሰቦቿም በሁኔታው በድጋሚ ጥርጣሬ ውስጥ ስለገቡ ለፖሊስ ያመለክታሉ። ፖሊስም ጉዳዩን ለማጣራት  ኢምግሬሽን እና ዜግነት ምዝገባ አገልግሎት ያመለከትታል በዚህም ወ/ሮ ዝናሽ ወደ ሀገር ውስጥ መመለሷን እንጂ ከሀገር መውጣቷን የሚያመላክት መረጃ እንደሌለ ለፖሊስ መረጃው ይደርሰዋል፡፡ ፖሊስ በቀጥታ ባለቤቷን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ ማጥራት ሲጀምር አቶ ደበበ ሚስቱን ለስድስት ዓመታት  ቆፍሮ መቅበሩን እና ቤተሰቧን ሲያታልል እንደነበር  ቃል ይሰጣል በዚህ መሰረትም የግለሰቧ አስክሬንም ተቆፍሮ እንዲወጣ የኦሮሚያ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍል ክትትል በማድረግ ለጳውሎስ ሆስፒታል ፓቶሎጂስቶች አስክሬኑን እንዲመረምሩ በመደረጉ የአስክሬም ምርመራው ለፖሊስ ይደርሰዋል፡፡ የሸገር ከተማ ፖሊስ እና የገላን ከተማ ፖሊስ ባደረጉት ምርመራ ባል ጥፋተኛ መሆኑ በመረጃ በመረጋገጡ የምርመራ መዝገቡን ለሸገር ከተማ ዓቃቢ ህግ ተልኳል፡፡ ዓቃቢ ህግም በአቶ ደበበ ላይ  ከባድ የግድያ ወንጀል ክስ መስርቶበት ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ተከሳሽ ደበበ ተሰማ በእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን የሸገር ከተማ አስተዳዳር ከፍተኛ ፍርድ ቤት መወሰኑን የሸገር ከተማ አስተዳደር የህፃናት እና ሴቶች ጉዳይ ፅ/ቤት ሀላፊ ኮማንደር ረቢሱ ደቻሳ ጨምረው ተናግረዋል፡፡ ዘገባው የብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን ነው። ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት     👉 @Akiyas21bot    @ET_SEBER_ZENA @ET_SEBER_ZENA
Mostrar todo...
👍 15 4
ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የደረሰችበት የባሕር በር መግባቢያ ስምምነት አተገባበር ወደ ኹለተኛ ምዕራፍ መሸጋገሩን አስታውቃለች። የመግባቢያ ስምምነቱ አተገባበር ግብረ ኃይል ሰብሳቢ ባሺ ሐጂ ኦማር፣ በመጀመሪያው ዙር የትግበራ ምዕራፍ፣ ስብሰባዎችን የማካሄድ፣ አማራጭ የባሕር ኃይል ጣቢያ ቦታዎችን የመለየት ሥራዎችና የሕዝብ አስተያየቶችን የማካተት ሥራዎች ሲሠሩ እንደቆዩ መግለጣቸውን የራስ ገዟ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ሶማሊላንድ የመጨረሻውን የመግባቢያ ስምምነት ለመፈራረም በምትሄድበት ሂደት ዙሪያ የሚያማክራትን አንድ የእንግሊዝ አማካሪ ኩባንያ መቅጠሯንም ሰብሳቢው መናገራቸውን ዘገባዎቹ አመልክተዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የመግባቢያ ስምምነቱ አተገባበር ምን ደረጃ ላይ እንዳለ በቅርብ ጊዜያት ውስጥ መረጃ ሰጥቶ አያውቅም። ሱማሊያ በበኩሏ፣ ኢትዮጵያ የመግባቢያ ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ ካልሰረዘች በባሕር በር ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር አልነጋገርም በሚለው አቋሟ እንደጸናች ናት።(ዋዜማ) ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት     👉 @Akiyas21bot    @ET_SEBER_ZENA @ET_SEBER_ZENA
Mostrar todo...
👍 3 1
በምዕራብ ሀረርጌ ትናንት አራት ሰዓት አካባቢ ከፍተኛ ተኩስ እንደነበር የደረሰኝ መረጃ ያመላክታል። በተኩሱ ቦንብ ጭምር ጥቅም ላይ ሳይውል እንዳልቀረ ምንጮቼ ገልፀው ጥቃቱን ያደረሱት የሸኔ ታጣቂዎች ሳይሆኑ አይቀሩም ብለዋል። ጥቃቱን ለፈፀም ምክንያት የሆናቸው ደግሞ ወደ መከላከያ ሰራዊት ሊሄዱ የነበሩ ወጣቶችን ለማስለቀቅ ነበር ተብሏል። በዚህ ጥቃት ሶስት የፀጥታ አካላት የቆሰሉ ሲሆን አንዱ ሳይሞት እንዳልቀረ ጠቁመዋል። ወደ ስልጠና ሊሄዱ የነበሩ ወጣቶችም አብዛኞቹ አምልጠዋል ብለዋል። ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት     👉 @Akiyas21bot    @ET_SEBER_ZENA @ET_SEBER_ZENA
Mostrar todo...
👍 3🤔 2
ዋቻሞ ዩኒቨርስቲ🙆‼️ በሀድያ ዞን ዋቻሞ ዩኒቨርስቲ ለአንድ የዩኒቨርስቲው የፋይናንስ ቡድን መሪ የ790 ቀን አበል እንዲሁም ለሌላኛው የፋይናንስ የቡድን መሪ ደግሞ በስድስት ወራት ውስጥ ብቻ የ1,469 ቀን (1,056,854 ብር) አበል እንደተከፈላቸው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የሰነድ ማስረጃዎችን፣ጥቆማዎችን እና መመሪያዎችን በማጣቀስ ምርመራ አድርጎ ውጤቱን ይፋ አድርጓል። ሌላም የዩኒቨርስቲው ፋይናንስ ሳያውቅ 1.4 ቢሊዮን ብር ለኦክስጅን ማምረቻ በሚል በህገወጥ መንገድ መንቀሳቀሱን እና ፍቃድ የሌለው የኮንስትራክሽን ድርጅት ግንባታውን እንዲሰራ ያለ ጨረታ እንደተሰጠው በምርመራ ውጤቱ ተገልጿል። በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም ተመሳሳይ ምርመራ ቢደረግ ከዚህም በላይ የሙስና ወንጀል እንደሚገኝ እሙን ነው። ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት     👉 @Akiyas21bot    @ET_SEBER_ZENA @ET_SEBER_ZENA
Mostrar todo...
👍 3 1
በትምህርት ተቋማት በሚቀጠለው 2017 ዓ.ም ምንም አይነት አዳዲስ ፕሮጀክቶች እንደማይኖሩ ተገለጸ‼️ በሚቀጠለው ዓመት 2017 ዓ.ም ምንም አይነት አዳዲስ ፕሮጀክቶች እንደማይኖሩ የገንዘብ ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ አስታወቁ። ሚኒስትር ዴኤታው ይህንን ያስታወቁት የትምህርት ሚኒስቴርና የ22 ዩኒቨርሲቲዎች የ2017 በጀት ዕቅዳቸው በተገመገመበት ወቅት ነው። የትምህርት ሚኒስቴር፣ የሚኒስቴሩ ሁለት ተጠሪ ተቀማት፣ የ8 የምርምርና የ14 የአፕላይድ ዩኒቨርስቲዎች የ2017 በጀት እቅድ በገንዘብ ሚኒስቴር በተካሄደ የበጀት ስሚ መርሀ ግብር ተገምግሟል። የበጀት ስሚ መርሀ ግብሩን የመሩት የገንዘብ ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ እንደገለጹት የበጀት ዝግጅቱ ዋና ትኩረት የሀገሪቱን ሀብትና የመንግስትን በጀት በእቅድ ለተያዘለት አላማ ብቻ በአግባቡና በቁጠባ መጠቀም መሁኑን ጠቁመው አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶችና የስራ ሀላፊዎችም በጀትን በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ ሚኒስቴር መሰሪያ ቤቱ እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ የበጀት እቅዳቸውን በተቀመጠላቸው የበጀት ጣሪያ መሰረት አስተካክለው በጠቂት ቀናት ውስጥ ለገንዘብ ሚኒስቴር እንዲያቀርቡ መጠየቃቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል። አዲስ ሰታንዳርድ =================== ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት     👉 @Akiyas21bot    @ET_SEBER_ZENA @ET_SEBER_ZENA
Mostrar todo...
👍 1👨‍💻 1
በትምህርት ተቋማት በሚቀጠለው 2017 ዓ.ም ምንም አይነት አዳዲስ ፕሮጀክቶች እንደማይኖሩ ተገለጸ‼️ በሚቀጠለው ዓመት 2017 ዓ.ም ምንም አይነት አዳዲስ ፕሮጀክቶች እንደማይኖሩ የገንዘብ ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ አስታወቁ። ሚኒስትር ዴኤታው ይህንን ያስታወቁት የትምህርት ሚኒስቴርና የ22 ዩኒቨርሲቲዎች የ2017 በጀት ዕቅዳቸው በተገመገመበት ወቅት ነው። የትምህርት ሚኒስቴር፣ የሚኒስቴሩ ሁለት ተጠሪ ተቀማት፣ የ8 የምርምርና የ14 የአፕላይድ ዩኒቨርስቲዎች የ2017 በጀት እቅድ በገንዘብ ሚኒስቴር በተካሄደ የበጀት ስሚ መርሀ ግብር ተገምግሟል። የበጀት ስሚ መርሀ ግብሩን የመሩት የገንዘብ ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ እንደገለጹት የበጀት ዝግጅቱ ዋና ትኩረት የሀገሪቱን ሀብትና የመንግስትን በጀት በእቅድ ለተያዘለት አላማ ብቻ በአግባቡና በቁጠባ መጠቀም መሁኑን ጠቁመው አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶችና የስራ ሀላፊዎችም በጀትን በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ ሚኒስቴር መሰሪያ ቤቱ እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ የበጀት እቅዳቸውን በተቀመጠላቸው የበጀት ጣሪያ መሰረት አስተካክለው በጠቂት ቀናት ውስጥ ለገንዘብ ሚኒስቴር እንዲያቀርቡ መጠየቃቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል። አዲስ ሰታንዳርድ =================== ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት     👉 @Akiyas21bot    @ET_SEBER_ZENA @ET_SEBER_ZENA
Mostrar todo...