cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

የጥበብ ና የፍልስፍና መንደር

የምናብ አለም

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
334
Suscriptores
Sin datos24 horas
-27 días
-630 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

🌿#እኔ_የምፈራው. . . እኔ የምፈራው. . . "ምን አለኝ?" ከሚል ጥያቄ ይልቅ "ሰው ምን ይላል?!" በሚል ስጋት ተውርሮ ሕልምን ማጨናገፍ! አድገው ጽጌረዳ ሳይሆኑ በለጋነት መርገፍ! ዓለም በፈጠረችው ሕግጋት ታስሮ የራስን ዓለም ሳይፈጥሩ ማለፍ! #እኔ_የምፈራው. . . ደስታዬን በሰዎች ላይ መገንባት! ከሰው ሲስማሙ ጮቤ መርገጥ፣ሰው አለኝ ብሎ ደረትን መንፋት! ሰው የጠፋ ቀን ማንነትን ፈልጎ ማጣት፣እውነትን መካድ፣መንገድ አልባ ሆኖ ከንፋስ ጋ መጥፋት! . #እኔ_የምፈራው. . . በሚተኩኝ ሰዎች ዙሪያ ማንዣበብ! "አይተኬ ነኝ" ብለው ሲደነቁ ከርመው፣ ከታች ተወርውሮ አፈር ድሜ መብላት፣እንደ ዘበት. .. እንደ ዋዛ ተዘንግተው መና ሆኖ መቅረት! . #እኔ_የምፈራው. . . ባልተፈጠሩበት መስክ ዕድሜን ማሟጠጥ! የሚወዱትን ሰውተው፣የኔ በማይሉት መስክ ላይ ያለ ሰበብ መረገጥ! በሕሊና ጩኸት፣በፀፀት ረመጥ እየታቀጠሉ በሞት ሽረት ህመም ዕድሜ-ዘመን መራወጥ! . #እኔ_የምፈራው. . . በሰው እጅ መውደቅ! እኔ የምፈራው. . ፍርሃቴን ብቻ እየቆጠርኩ፣ፍርሃቴን ብቻ እየፈራሁ፣!ፍርሃቴን ብቻ እየተመንኩ መኖር!          ••●◉Join us share◉●••           ═════❥━━━❥═════      🌾ነገ መልካም ይሆናል !  🌾 💫 https://t.me/philoso_phy 💫              🎖  @cekuaa 🎖
Mostrar todo...
ት     ሆ          ነ             ዋ                  ለ                     ህ!🌿 🐚 እውነተኛ ለውጥ። የፀባይ ወይም የውጤት አሊያም የአካሄድ ለውጥ አይደለም። እውነተኛ ለውጥ የማንነት ለውጥ ነው። ለአንድ ቀን መጽሐፍ ማንበብ ግብ አይደለም። መጽሐፍ ለመጻፍ አንድ አንቀጽ መጻፍ ግብ አይደለም። 🐚 የሆነ ነገር ለማግኘት፣ የሆነን ሰው ለመሆን በማያቋርጥ ፍልሚያ አንድ ነገር መስራት ነው። ማሻሻል፣ ማሳደግ የማንነት ለውጥ ናቸው። ሁሌም የሆነ ልምድን ማዳበር መለማመድ በራሱ ፈተና አይደለም። ለፈተናው ዝግጅት ጥናት እንደማድረግ ነው ። ሁሌ የምትጽፍ ስትሆን ጸሐፊ፤ ሁሌ 'ስፖርት' ስትሰራ የአካል ብቃት ያለው ትሆናለህ። 🐚 ሁሌም መሳል፣ መዝፈን፣ ሚስማርን በትክክል በመዶሻ መምታት ምንም ይሁን ምትፈልገውን ለመሆን የሚያስፈልገውን ልምምድ ስታደርግ .... .... .... ት     ሆ          ነ             ዋ                  ለ                     ህ። ጠቃሚና ትናንሽ ልምዶች ሁሌም ስነ-ዘዴዎች አይደሉም። የስኬታማ ሰው መመዘኛዎችም ናቸው። 🐚  ሰውነት ለመጨመር፣ ለመቀነስ፣ ገንዘብ ለማግኘት፣ ጭንቀትን ለመቀነስ  የሚደረጉ ልምምዶች ማንነትን በመቀየር የሚሳኩ ናቸው። ☑️ የሚፈለገውን ሰው ለመሆን የሚያስፈልገውን ልምድ ማካበት ያስፈልጋል። #ATOMIC_HABITS_
Mostrar todo...
🌿ባለም ስንክሳር ላይ እንዳየነው ኖረን የሕይወት ከፍ ዝቅ ቀርጾ እንዳስተማረን ድልን የሚወልደው ሌላ ድል ነውና፣ በ እችላለሁ” አስኳል አእምሮህ ካልጸና፣ የመውደቅን ሃሳብ ልብህ ካገዘፈ፣ #ውድቀትህ_እርግጥ_ነው_ደምቆ_የተጻፈ፡፡ 'እበለጣለሁ' ካልክ ውስጥህ እንዲያ ካለ፡ ብትበልጥም አትበልጥም፣ መብለጥ ለእምነት እንጂ ለሚዛን አትከፍልም፡ የሕይወት ጦር ሜዳ የስኬት እንጎቻ ለፈጠነ አትቀናም ወይ ለባለ ጡንቻ ታሽራለችእንጂ ጊዜ ቀኗን ቆጥራ #እችላለሁን_ብሎ_ድልን_ለሚጣራ!" 🌿 ሰውና_ፍልስፍናው 🌿        🎖 @cekuaa🎖 🕊 ነገ መልካም ይሆናል ! 🕊 💫 https://t.me/philoso_phy 💫              
Mostrar todo...
🌿ፈጣሪ ሆይ፣ ወደ እኔነቴ መልሰኝ ራስን የመሆን ቁልፍ! የጥንት አፈ-ታሪክ እንዲህ ይነገረናል፡፡ አንድ ጊዜ አንዲት አይጥ በሰላም ስትኖር ሳላች በድንገት ድመት አይታ እጅግ ደነገጠች፡፡ ከዚህ ድንጋጤ ለመዳን ምርጫዋ ብዙ ነው - ለምሳሌ ምናልባት ድመቷ ፈሪ ልትሆን ስለምትችል መጋፈጥና ሁኔታውን ማየት፣ አላዛልቅ ካለ ወደቀዳዳዋ ገብታ ቀን እስኪያልፍ መሸሸግ፡፡ አይጧ ግን የመረጠችው ያልተጠበቀ መንገድ ነው፡፡ “ፈጣሪ ሆይ፣ ሁለተኛ ድመትን እንዳልፈራ፣ ድመት አድርገኝ” በማለት ጸሎት አደረሰች፡፡ የተመኘችው ሆነላትና ወዲያው ወደ ድመትነት ተቀየረች፡፡ ብዙም ሳትቆይ ግን ውሻ በፊቷ ተደንቅሮ አገኘችው፡፡ የለመደችውን ጸሎት ማነብነብ ቀጠለች፣ “ፈጣሪ ሆይ፣ ሁለተኛ ውሻን እንዳልፈራ፣ ውሻ አድርገኝ”፡፡ አሁንም የተመኘችው ሆነላትና ወዲያው ወደ ውሻነት ተቀየረች፡፡ ሆኖም ይህኛውም ማንነት ብዙም አላዛለቃትም፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ መንገድ ስታቋርጥ አንበሳን አየችና የተለመደውን ጸለቷን አደረገች፡፡ “ፈጣሪ ሆይ፣ ሁለተኛ አንበሳን እንዳልፈራ፣ አንበሳ አድርገኝ”፡፡ እንደገና የተመኘችው ሆነላትና ወዲያው ወደ አንበሳነት ተቀየረች፡፡ አንበሳነቱም አላዛለቃትም፡፡  ከጥቂት  እርምጃ  በኋላ  አንድ  ለአደን  የወጣ  ሰው  መሳሪያ  ታጥቆ  አየችና እጅግ ደከማት፡፡ “ፈጣሪ ሆይ፣ አንዴ ብቻ ታገሰኝ፡፡ ሁለተኛ ሰውን እንዳልፈራ፣ እባክህን ሰው አድርገኝ” ብላ የተለመደ ጸሎቷን ጸለየች፡፡ አሁንም ምኞትዋ ደረሰና ወደ ሰው ተቀየረች፡፡ በመለዋወጥ የደከመ ማንነቷን ለማሳረፍ እቤቷ ገብታ ቁጭ ባለ ቴሌቭዥን ስታይ አንድን የኮሽታ ድምጽ ሰማች፡፡ ዘወር ስትል፣ አይጥ ወዲህ ወዲያ ስትል አየችና እጅግ ፈራች፡፡ የመጨረሻው ምኞትዋ በጸሎት መልክ በድንገት ከአንደበቷ ወጣ፣ “ፈጣሪ ሆይ፣ ሁለተኛ አይጥን እንዳልፈራ፣ ወደ እኔነቴ መልሰኝ”፡፡ ወዲያውኑ ይህ የመጨረሻ ምኞቷ ሆነላትና ችግሯን ለማሸነፍ ራስን የመቀየር ጉዞዋን ወደ ጀመረችበት ወደ አይጥነቷ ተመለሰች - ብዙ ቀናትን ካባከነች በኋላ፡፡ ራስን ከመሆን፣ ማንነታችንን ከማሳደግ እና ባደገው ማንነታችን ፍርሃታችንን ከመጋፈጥ ውጪ ድል የማግኛው መንገድ ምንድን ነው? በፊታችን እንደተደነቀረው ገጠመኝና እንደ እለቱ ሁኔታ ራስን እንደመለወጥ ምን አድካሚ ሕይወት አለ? ማንነቴን አውቄና ተቀብዬ፣ ድካሜን በማሸነፍና ብርታቴ ላይ በመገንባት ራሴን ሆኜ መኖር የድሎች ሁሉ ድል ነው! ራስንና ማንነትን ለቅቆ የሚጀመር ጉዞ የማያልቅ፣ አድካሚና፣ ወደተነሳንበት ስፍራና ሁኔታ እንደገና “በዜሮ” የሚያስጀምር ሁኔታ ነው፡፡ ሌሎች የራሳቸው ማንነት በማሳደግና በመበርታት ያሸነፉትን ችግር አንተ እነሱን ለመሆን በመሞከር አታሸንፈውም፡፡ አንተነትህ አንተነትህን ይፈልገዋልና ራስህን ሆነህና ከራስህ ጋር ተስማምተህ ኑር፡፡
Mostrar todo...