cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ሰውና ~ ፍልስፍናው

☞የዕውቀት መጀመሪያ አለማወቅን ማወቅ ነው፠ ~ማወቅ ደግሞ ከማሰብ ይጀምራል✔️ #የፍልስፍና_ስራ_ሰውን ለተፈጠረበትየሰውነትአላማ ማብቃትነው ❖ ጥንታዊ ፍልስፍናዎች< ❖ አስገራሚ አውነታዎች< ❖ ሳይኮሎጂ< ❖ አስደማሚ ታሪኮች< ❖ መፅሀፍ ቅዱሳዊ አስተንትኖት< ☞ጠቅልሎ የያዘ ለነፍስና ለስጋ የሚበጁ ለሰላማዊ ህይወትም ሆነ ለምድራዊ ቆይታ መሠረት የሚሆኑ አጅግ በረካታ ሀሳቦችን ለናንተ ያደርሳል

Mostrar más
Advertising posts
18 123Suscriptores
-924 hours
+27 days
+3130 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ህይወት ቀጥላለች እዚህ ሰአት ላይ ደርሳለች በእያንዳንዱ ሰከንድ መንቀሳቀስ ደሞ ወደ ሞታችን እየቀረብን ነው ። እናም በሞታችን ስራችንን እንድናስቀጥል በእያንዳንዱ ሰከንድ ልክ መንቀሳቀስ አለብን ተማሪ ከሆንክ ጥናት ሰራተኛ ከሆንክ ስራህን ምክንያቱም ያንተ እረፍት ስራህ እንዲሆን ሁሌ መሞከር አለብህና ያለፈውን ስህተትህን መልሰህ ማስተካከል ትችላለህ ግን ያለፈህን ጊዜ መመለስ አትችል መልካም ቀን ይሁንላችሁ። share and join https://t.me/RasenMagyet3679
Mostrar todo...
ራስን ማግኘት!!!

ወዳጄ፥ ሕይወት አጭር ናት።ዛሬን እንጂ ነገን ስለመኖርህ እርግጠኛ መሆን አትችልም። ስለዚህ ዛሬን መልካም አስብ፤ለሌሎች መልካም አድርግ።በሙሉ ልብህ እመን።ስላለህ ነገር አመስግን።ሰው አትበድል ነገር ግን ብትበድል ይቅርታን ጠይቅ፤ቢበድሉህም ይቅርታ እስኪጠይቁህ ሳትጠብቅ ይቅርታን አድርግ። የዋህ ሁን ነገር ግን ይቅርታ ያደረክለት ሰው ዳግም ይበድልህ ዘንድ ሞኝ አትሁን። መልካም ዛሬ(ከዛሬም አሁን)!?

⚜መልካም ዝልፈተ ሰንበት!🌿
Mostrar todo...
ኃዘንተኛ ለመሆን ከፈለጋችሁ . . .  ሃዘንተኛ ሰው ሆናችሁ መኖር ከፈለጋችሁ ቀላሉ መንገድ ሁልጊዜ፣ በሁሉም ቦታና በሁሉም ሁኔታ፣ ሁሉንም ሰው ለማስደሰት ሲጦዙ መኖር ነው፡፡ ማንም ሰው እንዳያዝንባችሁ፣ ቅር እንዳይሰኝባችሁን ሁል ጊዜ ሁሉም ሰው በእናንተ ሃሳብም ሆነ ተግባር ደስተኛ እንዲሆን የምትፈልጉ ከሆነ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ አደገኛ የስሜት ቀውስ ውስጥ መግባታችሁ አይቀርም፡፡ ጉዳዩ ግን ከዚያም ትንሽ ሰፋ ያለ ነው፡፡ ቀላላል እውነቶች . . . • ሁሉንም ሰው ለማስደሰት የሚጦዝ ሰው ሰዎችን ለማስደሰት ሌላ ሌላውን ሲኖር ራሱን ሆኖ መኖር አይችልም፤ ራሱን ሆነ የማይኖር ሰው ደግሞ በፍጹም ደስተኛ መሆን አይችልም፡፡  • ሁሉንም ሰው ለማስደሰት የሚጦዝ ሰው ለማስደሰት በሚፈልገው ሰው ቁጥጥር ስር ይውላል፤ ሰው ተቆጣጥሮ እንደፈለገ የሚያደርገው ሰው ደግሞ በፍጹም ደስተኛ መሆን አይችልም፡፡  • ሁሉንም ሰው ለማስደሰት የሚሯሯጥ ሰው በየሰዓቱና በየቀኑ የሚለዋወጥ የስሜት ውጣውረድ (ሙድ) ውስጥ ራሱን ያገኘዋል፤ ስሜቱ (ሙዱ) በየጊዜው የሚለዋወጥ ሰው ደግሞ በፍጹም ደስተኛ መሆን አይችልም፡፡ • ሁሉንም ሰው ለማስደሰት የሚጦዝ ሰው “ሰዎችን ያስደስትልኛል” ከሚለው ሃሳብ አንጻር እንጂ ከዓላማ አንጻር መኖር አይችልም፤ ከዓላማ ውጪ የሚኖር ሰው ደግሞ ደስተኛ  መሆን አይችልም፡፡ በሕይወታችሁ ሰዎችን ማስደሰት እጅግ ደስታን የሚሰጥ ልምምድ መሆኑን ማስመራችንን ሳንዘነጋ፣ የሕይወታችሁ ዋና ዓላማ ግን ማንም ሰው ቅር እንዳይሰኝባችሁ፣ በክፉ እንዳያስባችሁ፣ እንዳያወራባችሁ፣ እንዳይገፋችሁ . . . ከሆነ የዚህች ምድር አጭር እድሜያችሁን በኃዘን የምታሳልፉ ሰዎች ናቸው፡፡ በመጨረሻም፣ ሁሉንም ሰው ማስደሰት እንደማይቻል ትደርሱበትና ያን ጊዜ ደግሞ ያንን የማይቻል ነገር ለመቻል ስትጦዙ ዓመታቶቻችሁን ስላባከናችሁ በመቆጨት ታዝናላችሁ፡፡ በሉ እንግዲህ፣ ማድረግ ወደምትችሉትና ወደሚገባችሁ እውነታ ተመለሱ! ማድረግ የምትችሉት፣ በገባችሁና በአቅማችሁ መጠን ለራሳችሁ ጨዋ ኑሮን መኖር፣ ለሰዎች ደግሞ መልካም ሰው መሆንና ሁልጊዜ ከስህተት ለመታረም የተዘጋጀ ልቦና ማዳበር መሆኑን አትዘንጉ፡፡ /Dreyob
Mostrar todo...
Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

አብዘርዲዝም - ካምዩ ምንጭ ፦ ፍልስፍና ከዘርዓያዕቆብ እስከ ሶቅራጠስ ምንጭ ፦ ፍሉይ አለም መጠለያ ባጣህበት ሁኔታ በዝናብ እየተደበደብክ እየተጓዝክ ሳለ፣ መሳቅ ጀምረህ አታውቅም? የሆነ ጉዳይ በእጅጉ ተበላሽቶብህ ከዚህ በላይ ምን ሊመጣ አይነት ስሜት ፈገግ ብለህ አታውቅም? በችግሮችህ ውስጥ ሳለህ እያንዳንዷን ደቂቃ ወደህ አታውቅም? ይህን አልበርት ካምዩ አብሰርዲቲ ይለዋል፡፡ ካምዩ ፈረንሳያዊ የኤግዚስታንሻሊዝም (ህላዌነት) ፈላስፋ ነው፡፡ በቀላል ታሪክም ፍልስፍናውን ይጀምራል፡፡ ሲሲፈስ የተባለ የጥንታዊቷ ግሪክ ንጉስ አማልክቱን የሚያስቆጣ ተግባር ፈጸመ። ሲሲፈስ ሞትን በሰንሰለት አሰረው፡፡ ይህንንም በማድረጉ የሰው ልጅ ዘላለም ኗሪ ሆነ። በመጨረሻም አማልክቱ ሲሲፈስ ያደረገውን አወቁ፤ በርሱ ላይም ዘላለማዊ ቅጣት ፈረዱበት፤ የሞትንም ሰንሰለት በጠሱ፡፡ እናም ሲሲፈስ ለመቀጣጫ እንዲሆነው ዘላለም ድንጋይ ሲያንከባልል እንዲኖር ተፈረደበት። ግዙፍ ቋጥኝ እየገፋ ወደ ተራራ አናት ያደርስዋል፤ ወዲያውም ቋጥኙ ወደ ተራራው ስር ተንከባሎ ይወርዳል፤ ሲሲፈስም እንደገና ከታች ጀምሮ ወደ ላይ ቋጥኙን ይገፋዋል፡፡ ቋጥኙም ተመልሶ ወደ ተራራው ግርጌ ይወርዳል... ይህ የሲሲፈስ ዘላለማዊ ቅጣቱ ነው። ያንተስ ሕይወት ከርሱ ይለያልን? የሲሲፈስ እልፍ ጊዜ እየተመላለሰ ቋጥኝ ማንከባለሉ ትርጉም አልባ እንደሆነ ይሰማሃል? ሆኖም ያንተ ሕይወት ትርጓሜው ምንድን ነው? ሕይወትህን ልክ እንደ ሲሲፈስ ትርጉም አልባ ቋጥኞችን ስትገፋ ነው የምታሳልፈው፡፡ የማይሞላ ሆድ አለህ... ሚልዮን ጊዜ መግበኸው ሚልዮን ጊዜ ጎድሎብሃል፤ የማይሞላ ፍላጎት አለ... ሚልዮን ጊዜ ተደስተህ ሚልዮን ጊዜም ተከፍተሃል። በጠዋት ከእንቅልፍህ ትነሳለህ፤ ገንዘብን ፍለጋም ወደ ስራ ትሄዳለህ... ቀኑ ይመሻል ዳግም ይነጋል... በጥዋት ወደ ስራ ትሄዳለህ. ከእለታት በአንዱ ቀንም ራስህን በሞት አልጋ ላይ ታገኘዋለህ፡፡ እናም በሕይወት ዘመንህ የምታደርገው ነገር ሁሉ ልክ እንደ ሲሲፈስ ቋጥኝ መግፋት- ዘበት ነው! የሰው ልጅ ህልቆ መሳፍርት በሌለው ሁለንተና ላይ ራሱን ሲያገኘው፤ “ለምን?” የሚል ጥያቄን ይጠይቃል። ለምን ተፈጠርኩ? ለምን እኖራለሁ? የሕይወቴ ትርጉምስ ምንድን ነው? ሆኖም እውነታው ይህ ነው... ያንተም የኔም የመኖር ሁኔታ በአጋጣሚዎች የተፈጠረ እንጂ ትርጓሜ ያለው ነገር አይደለም በጸጥታ ውስጥ ባለው በግዙፉ ሁለንተና ውስጥ አንተ ማን ነህና ሕይወትህ ትርጉም ይኖረዋል? ሁለንተናም ስላንተ ግድ የለውም... ለጥያቄህም መልስ የለውም፡፡ ሆኖም ይህ መሆኑን ብናውቅም፤ ሰው ነንና የሕይወታችንን ትርጉም መፈለጋችንን አናቆምም የሞትን ቀን ያበቃለታል። ሞት በሕይወታችን የኖርንላቸውን ተግባራቶች በሙሉ ዋጋ ያሳጣቸዋል፡፡ ይህንን ነው አብሰርዲዝም ወይም የሕይወት ዘበትነት ሲል የሚጠራው፡፡ እና ዘበት በሆነ ዓለም ላይ እንዴት እንኑር? ታይታኒክ በተባለው ፊልም መጨረሻ ላይ መርከቧ እየሰመጠች ሳለ ሙዚቀኞች ቫዮሊን ሲጫወቱ ይታያል፡፡ እንደሚሞቱ ቢያውቁም፣ ቅጽበታቸውን ብቻ መኖር ጀመሩ፤ የሚወዱትንም ሙዚቃ ከልባቸው ተጫወቱ፡፡ እንደ ካምዩ እሳቤ የሰው ልጅ የሚኖርበት ምክንያት ከሌለው philosophical suicide ይፈጽማል፡፡ ይህም ማለት ሕይወት ትርጉም ባይኖራትም ትርጉም እንዳላት አድርጎ ማሰብ ይጀምራል። ለዚህ ዋነኛ ተጠቃሽ የሚሆኑት ጭፍን አማኞች ናቸው፡፡ በእምነት ውስጥ መመርመር የለም... የምትኖርበት አላማ እንዳለህ እና የምታምንበት ሀይል ለዚህ አላማ እንደፈጠረህ ያለምንም መጠራጠር በጭፍን ትቀበላለህ፡፡ ስለሆነም መኖርህ ዋጋ አልባ ወይም ዘበት እንደሆነ አይሰማህም፡፡ ሌላኛው ደግሞ የምናገኘው ካምዩ absurd hero ይለዋል። ይህ ሰው ሕይወቱ ትርጉም እንደሌላት ያውቃል፤ ለሌሎች ሰዎች ትርጉም የማይሰጥ ነገር ግን ለእርሱ ብቻ ዋጋ ያለው ... ለእርሱ ብቻ የሚሰራ የሕይወት ትርጉምንም ይፈጥራል። ይህ የትርጉም ፈጠራ ሂደትም በራሱ ደስተኛ ያደርገዋል። ለሲሲፈስም ድንጋዩን ወደ ተራራ ማንከባለሉ ለእርሱ ትርጓሜ አለው፡፡ ይህ ለስው ልጆች የከፈለው መስዋእትነት ምልክት ነው. ይህ አማልክቱ ለእርሱ የሰጡት ቅጣት ምንም እንዳልሆነ ማሳያ መንገዱ ነው... ፈገግ ብሎም ድንጋዩን ይገፋል... የእርሱ ፈገግታም አማልክቱን እንደሚያስቆጣቸው ያስባል። እናም ድንጋይ ማንከባለሉ ብቻ ልቡን በደስታ ይሞላዋል። ካምዩም ሕይወት ትርጉም አልባ እንደሆነች ቢያውቅም እንኳ እንደ ሲሲፈስ ሁን ይልሃል። በዝናብ ውስጥ ደንስ... ትርጉም አልባ በሆነች ዓለም ላይ ለራስህ ብቻ እውነት የሆነ የመኖር ትርጉም ፍጠር፡፡
Mostrar todo...
አብዘርዲዝም - ካምዩ መጠለያ ባጣህበት ሁኔታ በዝናብ እየተደበደብክ እየተጓዝክ ሳለ፣ መሳቅ ጀምረህ አታውቅም? የሆነ ጉዳይ በእጅጉ ተበላሽቶብህ ከዚህ በላይ ምን ሊመጣ አይነት ስሜት ፈገግ ብለህ አታውቅም? በችግሮችህ ውስጥ ሳለህ እያንዳንዷን ደቂቃ ወደህ አታውቅም? ይህን አልበርት ካምዩ አብሰርዲቲ ይለዋል፡፡ ካምዩ ፈረንሳያዊ የኤግዚስታንሻሊዝም (ህላዌነት) ፈላስፋ ነው፡፡ በቀላል ታሪክም ፍልስፍናውን ይጀምራል፡፡ ሲሲፈስ የተባለ የጥንታዊቷ ግሪክ ንጉስ አማልክቱን የሚያስቆጣ ተግባር ፈጸመ። ሲሲፈስ ሞትን በሰንሰለት አሰረው፡፡ ይህንንም በማድረጉ የሰው ልጅ ዘላለም ኗሪ ሆነ። በመጨረሻም አማልክቱ ሲሲፈስ ያደረገውን አወቁ፤ በርሱ ላይም ዘላለማዊ ቅጣት ፈረዱበት፤ የሞትንም ሰንሰለት በጠሱ፡፡ እናም ሲሲፈስ ለመቀጣጫ እንዲሆነው ዘላለም ድንጋይ ሲያንከባልል እንዲኖር ተፈረደበት። ግዙፍ ቋጥኝ እየገፋ ወደ ተራራ አናት ያደርስዋል፤ ወዲያውም ቋጥኙ ወደ ተራራው ስር ተንከባሎ ይወርዳል፤ ሲሲፈስም እንደገና ከታች ጀምሮ ወደ ላይ ቋጥኙን ይገፋዋል፡፡ ቋጥኙም ተመልሶ ወደ ተራራው ግርጌ ይወርዳል... ይህ የሲሲፈስ ዘላለማዊ ቅጣቱ ነው። ያንተስ ሕይወት ከርሱ ይለያልን? የሲሲፈስ እልፍ ጊዜ እየተመላለሰ ቋጥኝ ማንከባለሉ ትርጉም አልባ እንደሆነ ይሰማሃል? ሆኖም ያንተ ሕይወት ትርጓሜው ምንድን ነው? ሕይወትህን ልክ እንደ ሲሲፈስ ትርጉም አልባ ቋጥኞችን ስትገፋ ነው የምታሳልፈው፡፡ የማይሞላ ሆድ አለህ... ሚልዮን ጊዜ መግበኸው ሚልዮን ጊዜ ጎድሎብሃል፤ የማይሞላ ፍላጎት አለ... ሚልዮን ጊዜ ተደስተህ ሚልዮን ጊዜም ተከፍተሃል። በጠዋት ከእንቅልፍህ ትነሳለህ፤ ገንዘብን ፍለጋም ወደ ስራ ትሄዳለህ... ቀኑ ይመሻል ዳግም ይነጋል... በጥዋት ወደ ስራ ትሄዳለህ. ከእለታት በአንዱ ቀንም ራስህን በሞት አልጋ ላይ ታገኘዋለህ፡፡ እናም በሕይወት ዘመንህ የምታደርገው ነገር ሁሉ ልክ እንደ ሲሲፈስ ቋጥኝ መግፋት- ዘበት ነው! የሰው ልጅ ህልቆ መሳፍርት በሌለው ሁለንተና ላይ ራሱን ሲያገኘው፤ “ለምን?” የሚል ጥያቄን ይጠይቃል። ለምን ተፈጠርኩ? ለምን እኖራለሁ? የሕይወቴ ትርጉምስ ምንድን ነው? ሆኖም እውነታው ይህ ነው... ያንተም የኔም የመኖር ሁኔታ በአጋጣሚዎች የተፈጠረ እንጂ ትርጓሜ ያለው ነገር አይደለም በጸጥታ ውስጥ ባለው በግዙፉ ሁለንተና ውስጥ አንተ ማን ነህና ሕይወትህ ትርጉም ይኖረዋል? ሁለንተናም ስላንተ ግድ የለውም... ለጥያቄህም መልስ የለውም፡፡ ሆኖም ይህ መሆኑን ብናውቅም፤ ሰው ነንና የሕይወታችንን ትርጉም መፈለጋችንን አናቆምም የሞትን ቀን ያበቃለታል። ሞት በሕይወታችን የኖርንላቸውን ተግባራቶች በሙሉ ዋጋ ያሳጣቸዋል፡፡ ይህንን ነው አብሰርዲዝም ወይም የሕይወት ዘበትነት ሲል የሚጠራው፡፡ እና ዘበት በሆነ ዓለም ላይ እንዴት እንኑር? ታይታኒክ በተባለው ፊልም መጨረሻ ላይ መርከቧ እየሰመጠች ሳለ ሙዚቀኞች ቫዮሊን ሲጫወቱ ይታያል፡፡ እንደሚሞቱ ቢያውቁም፣ ቅጽበታቸውን ብቻ መኖር ጀመሩ፤ የሚወዱትንም ሙዚቃ ከልባቸው ተጫወቱ፡፡ እንደ ካምዩ እሳቤ የሰው ልጅ የሚኖርበት ምክንያት ከሌለው philosophical suicide ይፈጽማል፡፡ ይህም ማለት ሕይወት ትርጉም ባይኖራትም ትርጉም እንዳላት አድርጎ ማሰብ ይጀምራል። ለዚህ ዋነኛ ተጠቃሽ የሚሆኑት ጭፍን አማኞች ናቸው፡፡ በእምነት ውስጥ መመርመር የለም... የምትኖርበት አላማ እንዳለህ እና የምታምንበት ሀይል ለዚህ አላማ እንደፈጠረህ ያለምንም መጠራጠር በጭፍን ትቀበላለህ፡፡ ስለሆነም መኖርህ ዋጋ አልባ ወይም ዘበት እንደሆነ አይሰማህም፡፡ ሌላኛው ደግሞ የምናገኘው ካምዩ absurd hero ይለዋል። ይህ ሰው ሕይወቱ ትርጉም እንደሌላት ያውቃል፤ ለሌሎች ሰዎች ትርጉም የማይሰጥ ነገር ግን ለእርሱ ብቻ ዋጋ ያለው ... ለእርሱ ብቻ የሚሰራ የሕይወት ትርጉምንም ይፈጥራል። ይህ የትርጉም ፈጠራ ሂደትም በራሱ ደስተኛ ያደርገዋል። ለሲሲፈስም ድንጋዩን ወደ ተራራ ማንከባለሉ ለእርሱ ትርጓሜ አለው፡፡ ይህ ለስው ልጆች የከፈለው መስዋእትነት ምልክት ነው. ይህ አማልክቱ ለእርሱ የሰጡት ቅጣት ምንም እንዳልሆነ ማሳያ መንገዱ ነው... ፈገግ ብሎም ድንጋዩን ይገፋል... የእርሱ ፈገግታም አማልክቱን እንደሚያስቆጣቸው ያስባል። እናም ድንጋይ ማንከባለሉ ብቻ ልቡን በደስታ ይሞላዋል። ካምዩም ሕይወት ትርጉም አልባ እንደሆነች ቢያውቅም እንኳ እንደ ሲሲፈስ ሁን ይልሃል። በዝናብ ውስጥ ደንስ... ትርጉም አልባ በሆነች ዓለም ላይ ለራስህ ብቻ እውነት የሆነ የመኖር ትርጉም ፍጠር፡፡ ምንጭ ፦ ፍልስፍና ከዘርዓያዕቆብ እስከ ሶቅራጠስ ምንጭ ፦ ፍሉይ አለም
Mostrar todo...
ጣፋጩ ገዳይ መርዝ! በሰሜን አንታርቲካ ላይ የሚኖሩ እስኪሞ የተባሉ ጎሳዎች ተኩላ ለመግደል ሲፈልጉ የሚዘይዱት ዘዴ አለ፡፡ በበረዶ ውስጥ ጫፉ በጥቂቱ የወጣ ቢላ ይደብቃሉ፤ በላዩ ላይ ጥቂት የበግ ደምን ያደርጉበታል:: ተኩላው ደሙን አሽትቶ ይመጣል፡፡ በረዶው ላይ ያለውን ደም መላስ ይጀምራል። ደሙ ይጣፍጠዋልና ፍጥነቱን እየጨመረ መላስ ይጀምራል፡፡ በዚህ ፍጥነት ውስጥም እያለ ሳያስበው ደም የተቀባው ቢላዋ ምላሱን ይቆርጠዋል፡፡ ነገር ግን ደም መላሱን አያቆምም፡፡ አሁን ላይ ይህ ተኩላ ባለማወቅ ከራሱ ምላስ የሚፈሰውን ደም እየላሰ ነው፣ ሆኖም ጣፍጦታል እና በፍጥነት መላሱን ይቀጥላል። ከመጠን በላይ ደምም ይፈሰዋልና በነጋታው ተኩላው ሞቶ ይገኛል። የራሱን ደም እየጠጣ እንደነበረም አልታወቀውም። ይህ ተኩላ ከእኛ ታሪክ ጋር ይቆራኛል፡፡ ብዙዎቻችን ጊዜያችንን የምናሳልፈው በስልካችን ላይ አልያም በቴሌቪዥን ላይ ነው... ጊዜያችንን ሳንጠቀምበት እንዲሁ ያልቃል... ይጣፍጣልና፤ ጥቂት ብቻ አይበቃንም፤ በፍጥነት እና በኃይልም ህይወታችንን፣ ጊዜያችንን ልሰን እየጨረስነው ነው:: በተቻለህ መጠንም ከስራህ እና ከማሰብ ከሚያስተጓጉሉህ ነገሮች ሁሉ ለማራቅ ሞክር። ድብቁ አእምሮ ድብቁ ኃይል
Mostrar todo...
“ፓፒዮ- Papillon” ✍ሔነሪ ሽርየ ትርጉም ጌታቸው ገብሬ ጸሐፊው ሔንሪ ሽሪዬ ይባላል፡፡ (Papillon) የሽሪዬ ቅጽል ሥም ነው፤ ይህ ሰው ያለ ሀጥያቱ በግድያ ወንጀል ተከሶ ገና በ25 አመቱ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት። ከአስፈሪ ወሕኒ ቤት የማምለጥ ትግል የራሱ ዕውነተኛ ታሪክ ነው፡፡ ከ26 ጥቅምት 1931 እስከ 18 ጥቅምት 1945 “ሰይጣን ደሴት” በተባለው ቦታ ያሳለፈውን መከራ ይተርካል።
Mostrar todo...