cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Skyline media

Mostrar más
Advertising posts
49 978Suscriptores
-4924 hours
-1877 days
-85530 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ዜና፡ ትጥቅ አንግበው የሚታገሉ አካላት ወደ ሀገራዊ ምክክር መድረክ እንዲመጡ ተጠየቀ፤ ጥበቃ ይደርግላቸዋል ተብሏል ትጥቅ አንግበው የሚታገሉ አካላት ወደ ሀገራዊ ምክክሩ መድረኮች እንዲመጡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ፡፡ ኮሚሽኑ ለሚሳተፉ ታጣቂዎች ጥበቃ እንደሚደረግላቸውም ገልጿል። የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገ/ሥላሴ፤ ግጭት ሕይወትና ንብረትን ያጠፋል እንጂ ችግርን አይፈታም ሲሉ ገልጸው፤ “ታሪካዊ አጋጣሚ” በሆነው ሀገራዊ ምክክር በመሳተፍ ሐሳብን በማቅረብ መግባባት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ ኮሚሽነሯ አሁንም ታጣቂዎቹ ወደ ምክክሩ እንዲመጡ በመጠየቅ ሲመጡም ጥበቃ እንደሚደረግላቸው አረጋግጠዋል ተብሏል፡፡ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስን ጨምሮ ሌሎች የሲቪክ ድርጅቶች በሀገራዊ ምክክሩ ከመሳተፍ እራሳቸውን አግልለዋል።
Mostrar todo...
ትጥቅ አንግበው የሚታገሉ አካላት ወደ ሀገራዊ ምክክር መድረክ እንዲመጡ ጥሪ ቀረበ - Addis standard

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 14/2016 ዓ/ም፦ ትጥቅ አንግበው የሚታገሉ አካላት ወደ ሀገራዊ ምክክሩ መድረኮች እንዲመጡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ፡፡ የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገ/ሥላሴ፤ ግጭት ሕይወትና ንብረትን ያጠፋል እንጂ ችግርን አይፈታም ሲሉ ገልጸው፤ “ታሪካዊ አጋጣሚ” በሆነው ሀገራዊ ምክክር በመሳተፍ ሐሳብን በማቅረብ መግባባት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ በዚህም ትጥቅ አንግበው እየታገሉ ያሉ አካላት ወደ ምክክሩ እንዲመጡ …

👍 8 1
ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር በተፈራረመችው የወደብ ስምምነት ዙሪያ የአቋም ለውጥ አድርጋለች?? የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ነብዩ ተድላ በወቅታዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ካነሷቸው ጉዳዮች መካከል የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር ጉዳይ፣ ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ስለተደረገው የወደብ መግባቢያ ስምምነት እና ሌሎቹም ተጠቃሽ ናቸው። አቶ ነብዩ እንዳሉት የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር ጉዳይ በድንበር አካባቢ ያሉ ማህበረሰብ ክፍሎችን ባሳተፈ መንገድ በሁለቱ ሀገራት በሚዋቀር ኮሚቴ ይፈታል ብለዋል። የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስቴር የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስቴር ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ በኤርትራ እና ኢትዮጵያ መካከል ያለው ድንበር ሊቀየር በማይችል ኹኔታ ለመጨረሻ ጊዜ ተሠምሯል ማለቱ አይዘነጋም። የኤርትራ ጦር በርካታ የኢትዮጵያ አካባቢዎችን እንደተቆጣጠር እና አካባቢዎቹን ወደ ኤርትራ ማካለሉን እንዴት ኢትዮጵያ እንዴት ታየዋለች? በሚል ለቃል አቀባዩ ለቀረበላቸው ጥያቄም "ጥያቄው ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ ከትግራይ ክልል ከተውጣጡ የማህበረሰብ ጋር በተወያዩበት ወቅት እንደተነሳ እና ጉዳዩ በውይይት ይፈታል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፣ አሁንም ማለት የምችለው ይህንን ነው" ብለዋል። ከአራት ወር በፊት በአዲስ አበባ የተካሄደው የኢትዮጵያ እና ራስ ገዟ ሶማሊላንድ መካከል የተካሄደው የወደብ መግባቢያ ስምምነት ጉዳይ ሌላኛው በዛሬው መግለጫ የተነሳ ጉዳይ ሲሆን ኢትዮጵያ ከሶማሊያ እና ሌሎች ሀገራት ባደረሱት ጫና ምክንያት የአቋም ለውጥ ወይም ሌላ አዲስ ነገር ይኖር ይሆን? በሚል ጥያቄ ተነስቷል። ቃል አቀባዩ በሰጡት ምላሽም " ከሶማሊላንድ ጋር በተደረገው የወደብ መግባቢያ ስምምነት ዙሪያ የተቀየረ አቋም የለም" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
Mostrar todo...
👍 13 2
የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶች አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የስኳር ህመም በደም ውስጥ የስኳር መጠን ከሚገባው በላይ ሆኖ በሚገኝበት ሰዓት የሚከሰት ተላላፊ ያልሆነ የህመም አይነት ነው። በዋናነት አራት የስኳር ህመም አይነቶች አሉ፤ እነርሱም አይነት አንድ፣ አይነት ሁለት፣ በእርግዝና ወቅት የሚከሰትና በሌሎች ተዛማች ህመሞች የሚመጣ የስኳር ህመም ናቸው። ከነዚህ ውስጥ ሁለቱ (አይነት አንድ፣ አይነት ሁለት)… https://www.fanabc.com/archives/242856
Mostrar todo...
1
በፅንፈኛው የፋኖ አመራርና አባላት ላይ እርምጃ ተወሰደ፡፡ የፅንፈኛው አመራርና አንድ የቡድኑ አባል ሲገደሉ አንደኛው በቁጥጥር ስር ውሏል ፡፡ *** የፅንፈኛው ቡድን አባላት የሆኑት ናሁሰናይ አንድአርጌ ታረቀኝ ፣ አቤኔዜር ጋሻው አባተ እና ሀብታሙ አንድአርጌ ተሰማ የተባሉት የፅንፈኛው ፋኖ ቡድን አባላት በከተማችን አዲስ አበባ የሽበር ጥቃት ለመፈፀም ተልዕኮ ይዘው እየተንቃሰቀሱ መሆኑን የፀጥታ አካላት ባደረጉ ክትትል ይድረሱበታል፡፡ አሸባሪዎቹ የሽብር ተግባራቸውን ሳይፈፅሙ በቁጥጥር ስር ለማዋል የፖሊስ አባላት እንቅስቃሴ እያደረጉ ባለበት ሁኔታ ሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ/ም ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ሚሊኒዬም አዳራሽ አካባቢ ፅንፈኞቸ እጃቸውን እንዲሰጡ ቢጠየቁም ፍቃደኛ ባለመሆን በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2C 14373 አ/አ አይነቷ አይሱዙ ዲዛዬር መኪናን በመጠቀም ከፖሊስ አባላት ጋር ቶክስ በመክፈታቸው የፅንፈኛው ፋኖ መሪ ናሁሰናይ አንዳርጌ ታረቀኝ ቆስሎ ወደ ህክምና ከተላከ በኋላ ሲሞት ፅንፈኛው ሀብታሙ አንዳርጌ ተሰማ በተኩስ ልውውጡ መሃል ተገድሏል፡፡ አቤኔዘር ጋሻው አባት የተባለው የቡድኑ አባል ሳይቆስል በቁጥጥር ስር መዋሉን አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ ፅንፈኞቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገ እንቅስቃሴ ሳጅን አራርሳ ተሾመ እና ኮንስታብል ማቲያስ ጴጥሮስ ሲቆስሉ አቶ እንዳሻው ጌትነት የተባሉ ግለሰብ ፅንፈኞቹ በመኪናቸው እንዲጭኗቸው ቢያስገድዷቸውም ግለሰቡ አልተባበር በማለታቸው በፅንፈኛው አባላት ተገድለዋል፡፡ አቶ እንደሻው ሲያሽከርክሯት የነበረቸው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2 አ/አ 80457 በጥይት ጉዳት እንደረሰባት አዲስ አበባ ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል ፡፡ በቀጣይ ፖሊስ የደረሰበትን ዝርዝር መረጃ እንደሚገልፅ አስታውቋል፡፡
Mostrar todo...
👍 24👎 2
በኢትዮጵያ እርግጥ ሁለት ዜግነት ተፈጥሯል? ከህግ በላይ የሆነስ አለን?
Mostrar todo...
👎 11👍 2 2
Repost from Natnael Mekonnen
ለህግ ይቅረብ‼️ ከጀርባው ልክ እንደሱ የባለገና ጭፍን ጥላቻ ያለው ባለስልጣን ሳይኖር እንዲህ ሊናገር አይችልም:: ይህ ያልኩበት ምክንያት ቲክቶኩን በጥቆማ ገብቼ አብዛኛው ፎቶና ቪዲዮዎቹን ስመለከት ከተለያዩ አመራዎች ጋር ፎቶ አለው:: በኦሮሚያ ክልል ድሬድዋ ይመስለኛል ወይም ሃረር የብልጽግና ቢሮ ውስጥ ስብሰባ እንደሚመራ ሰው ተቀምጦ የተነሳቸው ምስሎች አሉ:: ልጁ ነዋሪነቱ በአሜሪካን ሃገር ሜኖሶታ ሲሆን አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ያለው:: በዚህ ቪዲዮ ላይ የሚናገረው መረን የለቀቀና እጅግ አጸያፊ አንድ ማህበረሰብን የሚያንቋሽሽ አብሮ የመኖርን እሴት የሚሸረሽር አጸያፊ ስድቦችን የሚሳደብበትን ቪዲዮን ደግሜ እዚህ ላይ መለጠፍ ይቅርና ሰምቶ ለመጨረስም ያማል!!! እጅግ ይሰቀጥጣል:: ኢትዮጵያ ውስጥ ተቀምጦ በቀጥታ (Live) ይህን ሲናገር መስማት እጅጉን ያማል‼️ የኦሮሚያ ክልል መንግስት የፌደራል ፖሊስ አዲስ አበባ ፖሊስ የብሔራዊ መረጃ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ከወዴየት ነው ያላችሁት? ምንስ እየተከናወነ ነው???????!!!
Mostrar todo...
👍 8 1
Mostrar todo...
anteneh123(antenehabrahamb) is LIVE | TikTok

ከልብ እንነጋገር. Check out anteneh123(antenehabrahamb) LIVE videos on TikTok! Watch, follow, and discover the latest content from anteneh123(antenehabrahamb).

8👍 5