Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
Ir al canal en Telegram
Mostrar más
2 406
Suscriptores
+924 horas
+527 días
+35430 días
Archivo de publicaciones
በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በተለያየ የትምህርትና ስልጠና መስክ ያሰለጠናቸውን ሰልጣኝ ተማሪዎችን አስመረቀ። በምረቃ ስነስርዓቱም ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና ንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀርቢ ቡህ እና የድሬዳዋ አስተዳደር የስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው እንዲሁም የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ተገኝተው ለተመራቂ ሰልጣኝ ተማሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልክት አስተላልፈዋል።
ኮሌጁ ከተቋቋመ ከ2001 እስከ 2015 ዓ.ም በ9 ዲፓርትመንቶች ማለትም በአውቶቲቭ፣ በአሌክትሪክ፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በአይ.ሲ.ቲ፣ በኮንስትራክሽን፣ በሆቴል፣ በሰርቬይ፣ በፈርኒቸር እና በቢዝነስ ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 5 አጠቃላይ በመደበኛ ስልጠና 16,461 አንዲሁም በአጫጭር ስልጠና ሙያ መስኮች ከ20,000 በላይ ሰልጣኞች አሰልጥኗል፤ በተጨማሪም በሳተላይት ዲግሪ መርሃ-ግብር ከ300 በላይ ሰልጣኞች በመደበኛና በኤክስቴንሽን መርሃ ግብር ተቀብሎ እንያሰለጠ ይገኛል፡፡
በዛሬው ዕለት የተመረቁ ሰልጣኝ ተማሪዎች ብዛት ወንድ-246 እና ሴት-297 በድምሩ 543 ሲሆኑ የዘንድሮ ምረቃ ስነስርዓት ልዩ የሚያደርገው ጉዳይ በዘርፍ አዲሱ ፖሊሲ መሰረት ከፍተኛ አካዳሚክ ውጤት ያላቸው ሰልጣኝ ተማሪዎች ተሸላሚ መሆናቸው ነው፡፡
የኢንደስትሪ ቴክኒካል አዲቫይዘሪ ቦርድ
በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከኢንዱስትሪው ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር በማሰብ የኢንደስትሪ አዲቫይዘሪ ቦርድ አቋቁሞ የተለያዩ ስራዎችን በጋራ ሲሰራ ቆይቷል፤
በ2015 ዓ.ም ይህንን ቦርድ በአደረጃጀት ለማጠናከር በተያዘው ዕቅድ መሰረት በዛሬው ዕለት ከተለያዩ ኢንደስትሪዎች የተወጣጡ ቴክኒካል አባላትን በመያዝ የቦርዱ ቻርተር ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል በዚህም ሰብሳቢ፣ ም/ሰብሳቢ እና ጸኃፊ በመምረጥ ወደ ሰራ የሚገቡበትን አቅጣጫ አስቀምጠዋል፤
በመጨረሻም የቦርዱ አባላት በኮሌጁ የሚገኙ የተለያዩ ዲፓርትመንት ወርክሾፖችን ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በቀጣይም ኮሌጁን በቴክኒኩ አቅጣጫ አስፈላጊ በሆኑ ነገሮች ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
መስከረም 14/2015 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2014 የስራ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2015 ዓ.ም ዕቅድ ለኮሌጁ ቦርድ ቀርቦ ተገመገመ።
በዚህም የኮሌጁ ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ የተሰሩትን ስራዎች አድንቀው በቀጣይ በተለይም አዳዲስ ሰልጣኞችን ለመቀበል የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እንዲሁም ከኢንዱስትሪዎች ጋር የሚኖረውን ትስስር ማሻሻል ላይ ትኩረት ሊደረግ ይገባል ብለዋል።
አያይዘውም በካይዘን ትግበራ ጥሩ አፈጻጸም እያሳዩ የሚገኙ የዉድ ቴክኖሎጂ እና ኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ ዲፓርትመንቶችን በመዘዋወር የጎበኙ ሲሆን የዚህ ለውጥ ባለቤት የሆኑትን አሰልጣኝ መምህራንንም አበረታተዋል።
በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የማኔጅመንት ኮሚቴ በኮሌጁ የትምህርትና ስልጠና እና የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፍ አሰጣጥ ያለበትን አሁናዊ ሁኔታ የመስክ ምልከታ አደረገ።
በምልከታውም ከሰልጣኝ ተማሪዎች በትምህርትና ስልጠና አሰጣጥ ሂደቱ ላይ ያላቸውን ሀሳብና አስተያየት እንዲሁም የሚያነሷቸውን ጥያቄዎችና ቅሬታዎች መመልከት የተቻለ ሲሆን በተጨማሪም ከውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ሂደቱ ጋር በመወያየት የተነሱትን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት በቀጣይ ዕቅድ አውጥቶ ክትትልና ምላሽ ለመስጠት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ አቅጣጫ ተቀምጧል።
በተመሳሳይ በተቋም ደረጃ እየተሰሩ ያሉ ቴክኒዎሎጂዎች በተቻለ አቅምና ፍጥነት ማጠናቅ እንዲቻልና ለውጤት እንዲበቃ አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን፤ ለኢንተርፕራይዞች የሚደረገው የድጋፍ አገልግሎት በተለይም በቀጥተኛ ሞያዊ ተዛምዶ ባላቸው አሰልጣኝ መምህራን የሚሰጠው ድጋፍ ውጤት ያስገኘ መሆኑን ተመልክቷል።
በቀጣይም ትምህርትና ስልጠናውን በዚህ አመት በጥናት ላይ ተመስርቶ ወደ ተግባር የተገባውን የአተገባበር ስርአት በማጠናከር ለዚህም የስልጠና አስተባባሪዎችን ሚና የማጎልበት ስራ እንደሚሰራ እና ከቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ጋር ተያይዞ የተጠኑ ጥናቶችን ተግባራዊ በማድረግ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የመለየትና የመፍታት ስራዎች ትኩረት ተሰጥቶ የሚተገበሩ ይሆናል።
ድሬዳዋ
ሰኔ 08/2014 ዓ.ም
የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የማኔጅመንት ኮሚቴ በኮሌጁ የትምህርትና ስልጠና እና የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፍ አሰጣጥ ያለበትን አሁናዊ ሁኔታ የመስክ ምልከታ አደረገ።
በምልከታውም ከሰልጣኝ ተማሪዎች በትምህርትና ስልጠና አሰጣጥ ሂደቱ ላይ ያላቸውን ሀሳብና አስተያየት እንዲሁም የሚያነሷቸውን ጥያቄዎችና ቅሬታዎች መመልከት የተቻለ ሲሆን በተጨማሪም ከውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ሂደቱ ጋር በመወያየት የተነሱትን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት በቀጣይ ዕቅድ አውጥቶ ክትትልና ምላሽ ለመስጠት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ አቅጣጫ ተቀምጧል።
በተመሳሳይ በተቋም ደረጃ እየተሰሩ ያሉ ቴክኒዎሎጂዎች በተቻለ አቅምና ፍጥነት ማጠናቅ እንዲቻልና ለውጤት እንዲበቃ አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን፤ ለኢንተርፕራይዞች የሚደረገው የድጋፍ አገልግሎት በተለይም በቀጥተኛ ሞያዊ ተዛምዶ ባላቸው አሰልጣኝ መምህራን የሚሰጠው ድጋፍ ውጤት ያስገኘ መሆኑን ተመልክቷል።
በቀጣይም ትምህርትና ስልጠናውን በዚህ አመት በጥናት ላይ ተመስርቶ ወደ ተግባር የተገባውን የአተገባበር ስርአት በማጠናከር ለዚህም የስልጠና አስተባባሪዎችን ሚና የማጎልበት ስራ እንደሚሰራ እና ከቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ጋር ተያይዩየተጠኑ ተግባራዊ ጥናቶችን ተግባራዊ በማድረግ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የመለየትና የመፍታት ስራዎች ትኩረት ተሰጥቶ የሚተገበሩ ይሆናል።
ድሬዳዋ
ሰኔ 08/2014 ዓ.ም
የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የማኔጅመንት ኮሚቴ በድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን መምሪያ በመገኘት በኮሚሽኑ የተሠሩና እምርታ ያሳዩ የሪፎርም ስራዎች አፈጻጸምን ጉብኝትና ምልከታ ማድረግ ችሏል።
በጉብኝቱም በኮሚሽኑ የተወሰደው ተቋሙን የማሻሻል አልፎም የመለወጥ እንቅስቃሴ ሁሉን ያሳተፈ እና የሁሉንም የተቋሙን ሰራተኞች እና ባለድርሻ አካላት እርብርቦሽ እና ትብብር ቀምሮ ውጤታማነቱም በተግባር ያረጋገጠ መሆኑ ታይቷል።
ድሬዳዋ
ግንቦት 10/2014 ዓ.ም
የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
የጥናት ግኝቶች ላይ ተመስርተው የተዘጋጁ የአተገባበር ረቂቅ ሰነዶች ላይ ውይይት ተደረገ።
🗯በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ስር ከዚህ በፊት የተጀመሩ የፕሮጀክት ማዕቀፎች ማለትም የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት አተገባበር ተግባራዊ ጥናትና ምርምር የጥናት ግኝቶች ላይ ተመስርቶ የተዘጋጁ የአተገባበር ረቂቅ ሰነዶች ላይ ለአመራር ፑል እና ለአጠቃላይ የኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራን ጥናቱን ባካሄዱት የኮሌጁ A ደረጃ አሰልጣኝ መምህራን፤ የቴክኖሎጂ ሽግግር አተገባበር ተግባራዊ ጥናትና ምርምር የጥናት ግኝቶች በአሰልጣኝ መምህር ጌታቸው ወንድሙ እና አሰልጣኝ መምህር ደረጀ ተሾመ አንዲሁም የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት አተገባበር ተግባራዊ ጥናትና ምርምር የጥናት ግኝቶች በአሰልጣኝ መምህር አቤል ዘገየ ቀርበው ገለጻና ውይይት ማድረግ ተችሏል፡፡
🗯 በዚህም ተግባራዊ ጥናትና ምርምር አጥኚ አሰልጣኝ መምህራኖቹ ከተመለከቷቸው የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት አተገባበር ተግባራዊ ጥናትና ምርምር የጥናት ግኝቶች በመነሳት የሚከተሉትን ምክረ ሃሳቦች አስቀምጠዋል፤
🗯የቴክኖሎጂ ሽግግር አተገባበርን ለማሻሻል
• ሊያሰራ የሚችል ማዕቀፍ እና መመሪያ ማዘጋጀት፤
• በኮሌጁ የቴ/ሽ ትግበራ፣ ክትትል እና ግምገማ የሚያደርግ የቴ/ሽ ክፍልን ማቋቋም፤
• ለዕውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት አቅም ቅድሚያ መስጠት እና ለአሰልጣኞች ቴክኖሎጂን በማሸጋገር ላይ ስልጠና መስጠት፤
• ተቋማዊ የቴክኖሎጂ ማእከላትን (ማሳያ እና መረጃ ማደራጃን ጨምሮ) ማልማት እና ማስተዋወቅ፤
• በኮሌጁ ውስጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እና በማሳተፍ ያለውን የቴ/ሽ አቅም ማሳደግ፤
• የተቋማዊ ሀብቶችን (ቁሳቁስ እና ፋይናንሺያል) የማስፈፀም አቅምን ማሻሻል፤
🗯 የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት አተገባበርን ለማሻሻል
• መዋቅር እና አስተዳደርን ማሻሻል፤
• በማህበረሰብ አገልግሎት ውስጥ ንቁ ተሳትፎን ማረጋገጥ፤
• በፍላጎት ላይ የተመሰረተ ወይም በፍላጎት የሚመራ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፍን ማጠናከር፤
🗯 በቀረበውም ምክረ ሃሳብ ላይ የኮሌጁ አመራር ፑል እና አሰልጣኝ መምህራን ሃሳብና አስተያየት የሰጡበት ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥም የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት አተገባበር ላይ የሚስተዋለውን ችግር በሚፈታ አግባብ ተግባራዊ መደረግ እንዳለበት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አሳስበዋል፡፡
ድሬዳዋ
ሚያዚያ 28/2014 ዓ.ም
የኢትዮ ጣሊያን ኮምኒኬሽን
