es
Feedback
Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Ir al canal en Telegram
1 756
Suscriptores
+124 horas
+37 días
+1830 días
Archivo de publicaciones
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ  በዘንድሮ አመት አዲስ ገቢ ለሆኑ ሰልጣኝ ተማሪዎቹ በ TVET Policy & Strategy ላይ ያተከሮ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል።    በቀጣይ ቀናትም አዲስ ሰልጣኝ ተማሪዎች ትምህርትና ስልጠናቸውን ከመጀመራቸው አስቀድሞ የLife Skill ስልጠና የሚወስዱም ይሆናል። የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን መጋቢት 4/2015 ዓ.ም

የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2015 ዓ.ም የአዲስ ገቢ ሰልጣኝ ተማሪዎችን ከ የካቲት 27 ጀምሮ ለ 1 ሳምንት እየመዘገ እንደሆነ ይታወቃል።   ሆኖም በተለያየ ምክንያት ያልተመዘገቡና  ከአጎራባች ክልሎች ጭምር የሚመጡትን ተመዝጋቢዎች ታሳቢ በማድረግ ኮሌጁ ምዝገባውን እስከ ሚቀጥለው ሳምንት  ያራዘመ መሆኑን እየገለፀ  እስካሁን በተለያዩ ምክንያቶች መታችሁ መመዝገብ ያልቻላችሁ ትምህርትና ስልጠና ፈላጊዎች በአካል በመገኘት መመዝገብ እንደምትችሉ ኮሌጁ ለመግለፅ ይወዳል።

የ2015 ዓ.ም የአዲስ ገቢ ተማሪዎች ምዝገባ።

አዲስ ተመዝጋቢዎች ለምዝገባ ስትመጡ ማሟላት የሚጠበቅባችሁ ማስረጃዎች።

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ      በስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የውስጥ ማስተግበሪያ መመሪያ አዲሱ የሰልጣኝ ተማሪዎች ውጤት አያያዝ እና አገባብ ዙሪያ ለኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራን የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ።

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2015 ዓ.ም የአዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ከ የካቲት 27/ 2015 ዓ.ም ጀምሮ የሚያካሂድ መሆኑን እየገለፀ እርሶም ባሉት ጥቂት የምዝገባ ቀናት በአካል ተገኝተው እንዲመዘገቡ ይጋብዛል።

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሰራተኞች የ2015 ዓ.ም የመጀመሪያ 6ወር የስራ አፈፃፀምና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ተወያዩ።      በዕለቱ በተዘጋጀው መድረክ የኮሌጁን የመጀመርያ 6ወር የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ጠቅለል ባለ መልኩ  በኮሌጁ ዲ/ን የቀረበ ሲሆን ከሰራተኛውም በግማሽ አመቱ ተግዳሮት የነበሩና በቀጣይ ሊሻሻሉ ይገባል ባሏቸውን ጉዳዮች ላይ ሀሳባቸውን ለመድረኩ አካፍለዋል።    በተጨማሪም በተቋሙ በቀጣይ ትኩረት ሊደረግባቸውን የታቀዱ ተግባራትን ለኮሌጁ ማህበረሰብ የቀረቡ ሲሆን ባጠቃላይ በመድረኩ የተነሱ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ላይ በ ኮሌጁ ዲኖች ሰፋ ያለ ማብራሪያ ተሰቶባቸው ውይይቱ ፍፃሜውን አጊዥቷል። የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን የካቲት 10/2015 ዓ.ም ድሬዳዋ

የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአስተዳደራችን ለሚገኘው የድል ጮራ ሪፈራል ሆስፒታል የማቴሪያል ድጋፍ አደረገ።     ተቋማችን በኮሚኒቲ ሰርቪሲንግ ለሆስፒታሉ ያደረገው ድጋፍ 10 የታካሚዎች መቀመጫ ወንበሮች እና 30 የግሉኮስ መስቀያ(IV Stands) ሲሆኑ ድጋፉንም የኮሌጃችን ም/ዲን አቶ ኤልያስ አህመድ ለሆስፒታሉ ተውካዮች አስረክበውልናል።      እነዚህ የማቴሪያል ድጋፎችም በኮሌጃችን በሚገኙት የውድ ዎርክ ዲፓርትመንት፣ የማኑፋክቸሪንግ ዲፓርትመንትና ከኢ/ኤ/አ ቴክኖሎጂ ስራ ሂደት ጋር በትብብር የተመረቱ ናቸው። የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን ጥር 30/2015 ዓ.ም