cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ስንክሳር

ሁሌ ዝቅ ማለትን አብዝቶ መስማትን ገንዘብ እናድርግ። @Synaxarium "ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን" ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
756
Suscriptores
-224 horas
-67 días
-1530 días
Distribuciones de tiempo de publicación

Carga de datos en curso...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Análisis de publicación
MensajesVistas
Acciones
Ver dinámicas
01
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን። ሰኔ 4 የታዘዘ መልአክ መጥቶ ሰማዕት እንደሚሆን የነገረው በኋላም ሊገድለው ብሎ መርዝ ያጠጣውን ጠንቋይ ጨምሮ በተአምራቱ ብዙዎችን ያሳመናቸው ሰማዕቱ ቅዱስ ሳኑሲ ዕረፍቱ ነው፡፡ ➛ ሐራቅሊ ከምትባል አገር የተገኘው ሰማዕቱ አቡነ ዮሐንስ ዕረፍቱ ነው፡፡ ➛ ምስክርነቷን በብዙ ድካምና በአስጨናቂ መከራዎች የፈጸመች የከበረች ቅድስት ሶፍያ በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን በሰማዕትነት ዐረፈች፡፡ ➛ የአርቃድዎስና የእኅቱ የዲሙናስያ፣ የግብጻውያኑ የአሞንና የሚናስ፣ የዲዮቅልጥያኖስ ጭፍሮችም የሰማዕትነታቸው ፍጻሜ ሆነ፡፡ እነዚህንም ቅዱሳን ከአባ ቢሾይ ጋር በእሳት ምድጃ ውስጥ በጨመሯቸው ጊዜ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ከነበልባሉ መካከል አወጣቸው፡፡ እነርሱም ዳግመኛ ወደ ንጉሡ ቀርበው ‹‹አንተ ከሃዲ ሰማዕትነታችንን በቶሎ ፈጽምልን›› ብለው ረገሙት፡፡ ንጉሡም በቁጣ ራስ ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡና ሥጋቸውን በእሳት እንዲያቃጥሉ አዘዘ፡፡ በትእዛዙም መሠረት ቅዱሳኑ አንገታቸውን ተሰይፈው ሥጋቸውም በእሳት ተቃጥሎ ሰማዕትነታቸውን በድል ፈጽመው የክብር አክሊልን ተቀዳጁ፡፡ የሰማዕታቱ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡ 🔥 አቡነ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ እናቱ ኤልሳቤጥ ስትባል አባቱ ዘካርያስ ደግሞ የጳንጦስና የአብልያ አገሮች ገዥ ነበር፡፡ ልጃቸውን ዮሐንስ ብለው ጠሩትና ስሙ ከመጥምቀ አምላከ ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር አንድ ሆነ፡፡ ሐራቅሊ በምትባል ሀገር የሚኖሩት ወላጆቹ ደጋጎች ስለነበሩ ፈሪሃ እግዚአብሔርንና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እያስተማሩ በሃይማኖት በምግባር አሳደጉት፡፡ አባቱ ከሞተ በኋላ ቅዱስ ዮሐንስ የ20 ዓመት ወጣት ሲሆን መስፍን ሆነ፡፡ የጳንጦስና የጰራቅሊ ሌሎቹም አገሮች ሁሉ ተገዙለት፡፡ እንዲሁም ሆኖ ሲኖር ሰይጣን በመልአክ ተመስሎ ተገለጠለትና ‹‹አንተ ትነግሥ ዘንድ ወደ አንጾኪያ ሄደህ የንጉሥ ኑማርዮስን ልጅ አግባ›› ብሎ መከረው፡፡ ወደ አንጾኪያም ሄደና ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስን አገኘው፡፡ እርሱም ባገኘው ጊዜ አከበረው፣ እጅግ ወደደው፡፡ በማግሥቱም ምሳ ላይ ከእርሱ ጋር እያለ ዲዮቅልጥያኖስ አጵሎንን ያመጡት ዘንድ አዘዘ፡፡ ባመጡትም ጊዜ ዮሐንስ ንጉሡን አይቶ አቃለለው፡፡ ስለ ጣኦት አምልኮውም ስለገሠጸው ንጉሡ በጣም ተቆጥቶ አሰረው፡፡ በእሥር ቤት ሳለም ጌታችን በብርሃን ሰረገላ ሆኖ ታየው፡፡ በማግሥቱም ነጉሡ ከእሥር ቤት አስወጥቶ ከእርሱ ጋር ይስማማ ዘንድ ብዙ ሸነገለው፡፡ በሀሳቡም ፈጽሞ እንዳልተስማማ ሲያውቅ ግብር ያስገብርለት ዘንድ ከሹመት ጋር ወደ ግብፅ አገር ላከው፡፡ ለግብፁ ገዥም ‹‹እነሆ የሐረቅሊውን ዮሐንስን ግብር በማስገበር የአማልክትንም ቤት በአዲስ እንዲሠራ ከግብፅና ከኢየሩሳሌም እስከ ኢትዮጵያም ድረስ ሥልጣን ሰጥቼዋለሁ›› ብሎ ጻፈለት፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም የጣኦታት ቤቶቹን አፍርሶ ተዋቸው፡፡ የግብፁ ንጉሥም ክርስቲያኖችን እያሠቃየ ሲገድላቸው ዮሐንስ አየውና የሹመቱን ሥራ ትቶ እርሱም ከክርስቲያኖች ጋር መከራንና ሥቃይን ይቀበል ዘንድ ወደደ፡፡ በንጉሡም ፊት ቀርቦ አማኝ ክርስቲያንን መሆኑን ከተናገረ በኋላ ንጉሡ ይዞ እጅግ አሠቃየው፡፡ መኰንኑም ተቆጥቶ አሳስሮ ወደሌላ ሀገር በግዞት ላከው፡፡ በዚያም ያለው መኰንን ተቀብሎ አሠቃየው፡፡ በዕንጨት ላይ ሰቅለው ሥጋውን በመንኰራኩር ፈጩት፡፡ ደሙንም እንደ ውኃ አፈሰሱት፡፡ ከሰቀሉበት ዕንጨት ላይ አውርደው ከደበደቡት በኋላ እሥር ቤት አስገቡት፡፡ ከጥቂት ቀንም በኋላ በማረጃ ቢላዋ ቆዳውን ገፈው ቁስሉን በማቅ አሹት፡፡ ዳግመኛም አመድ ጎዝጉዘው በላዩ የእሳት ፍም አድርገው በዚያ ላይ አስተኝተው አሠቃዩት፡፡ በእሳት የጋሉ የብረት ችንካሮችንም አምጥተው በፊቱና በጆሮዎቹ ላይ ቸነከሯቸው፡፡ የታዘዘ መልአክም መጥቶ በሌሊት ፈወሰው፡፡ በማግሥቱም ግንባሩን ወደ ምድር ደፍተው እጆቹንና እግሮቹን ከፈረስ ጋር በገመድ አስረው መሬት ላይ እየጎተቱ አሠቃዩት፡፡ በመጨረሻም ባለ ሰይፍ መጥቶ እጆቹንና እግሮቹን አንገቱንም በየተራ ቆረጣቸውና ሰኔ 4 የሰማዕትነቱ ፍጻሜ ከሆነ በኋላ የክብር አክሊልን ተቀዳጀ፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡ 🔥 ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት ሶፍያ ("ያ" የሚለው ላልቶ ይነበብ) በቀደመው ዘመን በነበሩ ክርስቲያኖች ዘንድ ተወዳጅ ስም ነበር:: ዛሬ ብዙ አሕዛብ ሲጠሩበት ብንሰማም ትርጉሙ "ጥበበ ክርስቶስ" የሚል ነው:: በዚህም ስም ከሚጠሩ ከብዙ ቅዱሳን ዛሬ ታስባ የምትውል ቅድስት ሶፍያ አንዷ ናት። ቅድስት ሶፍያ በከሃዲው ዲዮቅልጥያኖ ዘመን የነበረች ታላቅ ሰማዕት ናት፡፡ ወላጆቿ ደጋግ ክርስቲያኖች ስለነበሩ እግዚአብሔርን መፍራትና ቅዱሳት መጻሕፍትን እያስተማሩ አሳደጓት፡፡ ባደገችም ጊዜ ለመስፍን ልጅ ሊያጋቧት ፈለጉ፡፡ እርሷ ግን ሳይነግሯት የወላጆቿን ሀሳብ ዐውቃ ወደ ፈጣሪዋ እንዲህ ብላ ጸለየች፡- ‹‹የክብር ባለቤት የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ወደ አንተ የምደርስባት የከበረችና የቀናች መንገድህን ለእኔ ለባሪያህ ለሶፍያ ምራኝ፤ ወደ ጥፋት በሚወስድ በጠማማ መንገድ እንድንከራተት አትተወኝ፤ የሚጠፋውን ዓለም ያስብ ዘንድ ልቤን አትተወው፤ የከበደ የዓለማዊ ፍላጎት ሸክምን ተሸካሚ አታድርገኝ፤ ቀላልና ልዝብ የሆነ ቀንበርህን ይሸከም ዘንድ ትከሻዬን ዘንበል አድርገው እንጂ…›› እያለች ከጸለየች በኋላ ወዲያው አንድ ሀሳብ መጣላት፡፡ ተነሥታ ጠፍታ ከሩቅ ሀገር በመሄድ በአንዱ በረሃ ውስጥ ገብታ እግዚአብሔርን ለማገልገል ወሰነች፡፡ ወዲያውም እንድታገለግላት ወላጆቿ የሰጧትን ገረዷን ጠርታ የሚትጠጣው ወይን እንድታመጣላት አዘዘቻት፡፡ ሶፍያም ጥቂት ከቀመሰች በኋላ ለገረዷ ሰጠቻትና በብዛት አጠጣቻት፡፡ ገረዷም ከስካር የተነሣ ልቧ በተሰለበ ጊዜ ቅድስት ሶፍያ የገረዷን ልብስ ለብሳ የእርሷን ልብስ ሰጠቻትና አስተኝታት በስውር ወጥታ ሄደች፡፡ ርቃ በሄደች ጊዜ በተራራዎችና በዋሻዎች ውስጥ ሊሰወሩ ፈልገው በሃይማኖት ምክንያት ከከሃዲው ዲዮቅልጥያኖስ ፊት የሸሹ ክርስቲያኖችን አገኘች፡፡ ከየት እንደመጡ ስትጠይቃቸው ሀገራቸውን ከነገሯት በኋላ ስለ ዲዮቅልጥያኖስና ስለ ክፉ ሥራው ክርስቲያኖችንም እያሠቃየ እንደሚገድል በደንብ ነገሯት፡፡ ቅድስት ሶፍያም ወደ ዲዮቅልጥያኖስ የሚወስደውን መንገድ ጠየቀቻቸውና በቀጥታ ወደ ከሃዲው ንጉሥ ገሰገሰች፡፡ በፊቱም ቆማ ስለ ክርስቶስ መሰከረች፡፡ እርሱም እጅግ ተቆጥቶ ለጣዖቱ ለአጵሎስ ስገጂ አላት፡፡ ቅድስት ሶፍያ ግን በድፍረት ‹‹የሰው እጅ ለሠራው ለረከሰውና የአጋንንት ማደሪያ ለሆነው ጣዖት አልሰግድም›› አለችው፡፡ ከዚህም በኋላ የተለያዩ እጅግ ብዙ ሥቃዮችን አደረሰባ፡፡ በብረት ጅራፍ ደሟ እስኪወርድ ድረስ አስገረፋት፡፡ ዳግመኛም በአንገቷ ከባድ ድንጋይ አስሮ ሥጋዋ ተቆራርጦ መሬት ላይ እስኪወድቅ ድረስ በከተማው አስጎተታትና መልሶ እሥር ቤት ጨመራት፡፡ በማግስቱም አስወጥቶ ‹‹በክፉ አሟሟት እንዳትሞቺ ለአጵሎን ስገጂ›› ሲላት እርሷ ግን ‹‹ክፉ ሞትስ ለአንተ ነው፤ የእኔስ ከአንተ የሚገኘው ሞት በፈጣሪዬ ዘንድ ሕይወት ነው›› አለችው፡፡ እርሱም ‹‹ከገደልኩሽ በኋላ ከሞት ትነሻለሽን›› አላት፡፡ ቅድስት ሶፍያም ‹‹አንተ ሰነፍ የእኔንስ ተወውና ለአንተም የደይን ትንሣኤ አለህ›› አለችው፡፡ ይህን ጊዜም አጥንቶቿ እስኪሰበሩ ድረስ አስደበደባት፡፡ በብረት አልጋ አስተኝተው ከበታቹ እሳት አነደዱባትና ሲመሽ መልሰው አሠሯት፡፡ በሌሊትም ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ገላዋን በመዳሰስ
20Loading...
02
ከቁስሏና ከሕመሟ ሁሉ ፈወሳት፡፡ በማግሥቱም ንጉሡ ቅድስት ሶፍያን ባያት ጊዜ ከመታጠቢያ ቤት የወጣች እንጂ ያን ሁሉ መከራ ያደረሰባት አትመስልም ነበር፡፡ ንጉሡም ሲያያት ‹‹የሥራይዋን ጽናት እዩ ትናንት በእሳት አሠቃይተናት ነበር ዛሬ እንዲህ ድናለች›› እያለ ተናገረ፡፡ ቅድስት ሶፍያም ‹‹እኔስ ሥራይ አላውቅም ነገር ግን ፈጣሪዬ ሥራይን የሚሽር ነው›› አለችው፡፡ ከዚህም በኋላ እሺ ትለው ዘንድ ሊያባብላት ሲሞክር በእምነቷ ጸንታ እምቢ ብትለው ሰኔ 4 ቀን አንገቷን በሰይፍ አስቆርጦታል፡፡ ጌታችንም ተገልጦላት ብዙ ቃልኪዳን ሰጥቷታል፡፡ የቅድስት ሶፍያ ረድኤት በረከቷ ይደርብን፣ በጸሎቷ ይማረን፡፡ 🔥 ሰማዕቱ ቅዱስ ሳኑሲ ይኽም ቅዱስ በልጅነቱ የአባቱን በጎች ሲጠብቅ ምሳውን ለጦም አዳሪዎች እየሰጠ እርሱ ግን እስከ ማታ ድረስ ይጾም ነበር፡፡ በአንዲት ሌሊት የታዘዘ መልአክ ተገልጦለት ‹‹የክብርን አክሊል ትቀበል ዘንድ ወደ መኮንኑ ሄደህ ስለ ፈጣሪህ ስለ ክርስቶስ መስክር›› አለው፡፡ ቅዱስ ሳኑሲም ትእዛዙን በመቀበል እናቱን ተሰናብቶ ማሪያ ከምትባል ደገኛ ሴት ጋር በሰማዕትነት ይሞቱ ዘንድ ወደ ከሃዲው ገዥ ወደ አርሳኖስ ዘንድ ሄዱ፡፡ ከዚህም በኋላ በከሃዲው ገዥ ፊት ቀርበው ክርስቲያን መሆናቸውን ተናገሩ፡፡ ገዥውም ብዙ አሠቃቂ መከራዎችን አደረሰባቸው፡፡ ቅድስት ማርያ በስቃይ ውስጥ ሳለች ዐርፋ ሰማዕትነቷን ስትፈጽም ቅዱስ ሳኑሲ ግን በጌታችን ኃይል ታደሰ፡፡ መኮንኑም ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ ወደ እንዴናው ገዥ በግዞት ላከው፡፡ በዚያም እጅግ አድርገው አሠቃዩት፡፡ ተረከዙን ሰንጥቀው ገመድ አግብተው በከተማው ውስጥ ሲጎትቱት ዋሉ፡፡ ሥራየኛ ሰው አምጥተው ሥራየኛው ሰው በጽዋ የተመላ መርዝ እንዲጠጣ ቢሰጠው ቅዱስ ሳኑሲ በመስቀል ምልክት አማትቦ ቢጠጣው ምንም አልሆነም፡፡ እንዲያውም ምግብ ሆነው፡፡ ይህንን ታላቅ ተአምር ያየው ሥራየኛም ‹‹በቅዱስ ሳኑሲ አምላክ አምኛለሁ›› ብሎ በመመስከር እርሱም ሰማዕት ሆነ፡፡ መኮንኑም ቅዱስ ሳኑሲን ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ አንገቱን እንዲቆርጡት አዘዘና በዚህች ዕለት የከበረች ራሱን በሰይፍ ቆርጠውት ሰማዕትነቱን በክብር ፈጽሞ የክብር አክሊልን ተቀዳጀ፡፡ የቅዱስ ሳኑሲ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡ ምንጭ፦ የሰኔ ❹ ስንክሳር ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎትና ምልጃ ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። 🍃🍃🍃 🍃🍃🍃 🍃🍃🍃 ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ እም እለ አብዑ ብዑላን ዘተርፈ። ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን ሰማዕታት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን ደናግል ዓዲ ወመነኮሳት ኄራን ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን እስከ አረጋዊ ልሒቅ እምንዑስ ሕፃን። ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ ወለዘሰምዐ ቃሎ በእዝነ መንፈስ በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኲሉ እምባእስ ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ ወይፈኑ ለነ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እምይዜ ወእስከ ለዓለም አሜን። ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀይቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል። እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ። ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውንና ያጻፈውንም የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን። አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖ . ⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼ ሰኔ ❸ ቀን 2011 ዓ.ም
20Loading...
03
Media files
20Loading...
04
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን። ሰኔ 2 የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ሥጋ የነቢዩ የቅዱስ ኤልያስ ደቀ መዝሙር ከሆነው ከነቢዩ ቅዱስ ኤልሳዕ ሥጋ ጋር በአንድነት ተገኘ፡፡ ➛ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት አርሲ ፈንታሌ ተራራ ላይ ሠሪቲ ለምትባል ጠንቋይ እየተላላኩ ሕዝቡን የሚያስቱና የሚያሰቃዩ አራት መቶ ሰባ ሺህ ሦስት መቶ አጋንንትን በጸሎታቸው እሳት ከሰማይ አውርደው ያቃጠሏቸው የመሐግሉ አቡነ ቀውስጦስ መታሰቢያ በዓላቸው ነው፡፡ 🔥 አቡነ ቀውስጦስ ዘመሐግሉ ይኸውም ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከሾሙአቸው ከ12ቱ ንብረ ዕድ ወስጥ አንዱ ሲሆኑ ደብረ ሊባኖስንም የሚያጥኑበትም ወር በመጋቢት ወር ነበር። ሕዝቡ አጥብቆ የሚወዳቸውና የሚያከበራቸው አባት ናቸው፡፡ ግብፃዊው አቡነ ያዕቆብ ከግብፅ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የደብረ ሊባኖሱን እጨጌ አቡነ ፊልጶስን አስጠርተው፤ ለስብከተ ወንጌል መስፋፋት “ኢትዮጵያ በአንድ ጳጳስ መወሰን የለባትም፡፡ ስለዚህ ዐሥራ ሁለት አበው መርጠን ክርስትና ይስፋፋ” ብለው ባቀረቡት ሐሳብ መሠረት፤ አቡነ ፊልጶስ ዘደብረ ሊባኖስ /ኤጲስ ቆጶስ/፣ አቡነ አኖሬዎስ ዘሞረት፣ አቡነ ማትያስ ዘፈጠጋር፣ አቡነ ሳሙኤል ዘወገግ፣ አቡነ አኖሬዎስ ዘወረብ፣ አቡነ ታዴዎስ ዘጽላልሽ፣ አቡነ ገብረ ክርስቶስ ዘግድም፣ አቡነ መርቆሬዎስ ዘመርሐ ቤቴ፣ አቡነ አድኃኒ ዘዳሞት፣ አቡነ ቀውስጦስ ዘመሐግል፣ አቡነ ኢዮስያስ ዘወጅ፣ አቡነ ዮሴፍ ዘእናርያን መርጠው ሀገረ ስብከት ተሰጥቷቸው ለሐዋርያዊ ተልእኮ ተሠማሩ፡፡ ዐሥራ ሁለቱን ንቡራነ ዕድ ለስብከተ ወንጌል በመላዋ አገሪቱ ሲሠማሩ፡፡ ጻድቁ አቡነ ቀውስጦስ አርሲ ፈንታሌ ተራራ ላይ ሠሪቲ ለምትባል ጠንቋይ እየተላላኩ ሕዝቡን የሚያስቱና የሚያሰቃዩ 470300 (አራት መቶ ሰባ ሺህ ሦስት መቶ) አጋንንትን በጸሎታቸው እሳት ከሰማይ አውርደው ተራውንን ደምስሰው አጋንንቱን ያቃጠሉ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ የታናሽ ወንድማቸው የዐፄ ይኩኖ አምላክ ልጅ ዐፄ አምደ ጽዮን በክፉዎች ምክር የአባቱን እቁባት በማግባቱ አቡነ ቀውስጦስ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ ሄደው ንጉሡን ስለገሠፁት በግዞት ወስዶ ጎናቸው በጦር ወግቶ ገድሏቸዋል፡፡ ጻድቁ ልደታቸውም ሆነ ዕረፍታቸው ከእመቤታችን ልደትና ዕረፍት ጋር የተባበረላቸው ናቸው፡፡ በዛሬዋ ዕለት ደግሞ መታሰቢያ በዓላቸው ነው፡፡ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን። 🔥 መጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ሥጋ የነቢዩ የቅዱስ ኤልያስ ደቀ መዝሙር ከሆነው ከነቢዩ ቅዱስ ኤልሳዕ ሥጋ ጋር በአንድነት እንደተገኘ፡- የመጥምቁ ዮሐንስ ቅድስት ነፍሱ ከተቆረጠች ራሱ ጋራ በአየር ውስጥ እየበረረች 15 ዓመት ስታስተምር ከኖረች በኋላ ጥቅምት 30 ቀን በዐረቢያ ምድር በግልጽ ታይታለች፡፡ ይኸውም የሆነው እንዲህ ነው፡- ሄሮድያዳ ልጅ ርጉም የሆነ ንጉሥ ሄሮድስን በዘፈኗ በጣም አድርጋ ስላስደሰተችው እርሱም በተራው ሊያስደስታት ፈለገና እስከ መንግሥቱ እኩሌታ ድረስም ቢሆን የለመነችውን ይሰጣት ዘንድ በሕዝቦቹና በመኳንንቱ ሁሉ ፊት እንዳይከዳት በፅኑ ቃልኪዳን ማለላት፡፡ እርሱም አስቀድሞ ‹‹የፈለግሽውን ጠይቂኝ፣ የመንግሥቴንም እኩሌታ ቢሆን እሰጥሻለሁ ምን ላድርግልሽ?›› እያለ በመሐላ ባላት ጊዜ በእናቷ ምክር የዮሐንስን አንገት ቆርጦ ይሰጣት ዘንድ ለመነችው፡፡ እርሱም ስለማሐላው የዮሐንስን አንገት እንድትቆረጥ አደረገ፡፡ በመጀመሪያም የሄሮድስ ወታደሮች ሠይፍ ይዘው የዮሐንስን አንገት ይቆርጡ ዘንድ ወደ መኅኒ ቤት ሲሄዱ ቅዱስ ዮሐንስም የሄሮድስ ጭፍሮች ሊገድሉት እንደመጡ በመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ስላወቀ ከጨለማው ቤት ውስጥ አንገቱን በመስኮት አውጥቶ እንደሚመቻቸው አድርጎ ጠበቃቸው፡፡ የንጉሡም ጭፍሮች የመጥምቁን ራስ በወጪት አድርገው ለንጉሣቸው ሄሮድስ ሰጡት፡፡ ሄሮድስም ለሄሮድያዳ ልጅ ሰጣት፡፡ የመጥምቁ ዮሐንስ ግን በወጪት ላይ ሆና ሕዝቦቹና የመንግሥቱ ታላላቅ ሰዎች እየሰሟት በየመኳንንቱ ፊት ንጉሥ ሄሮድስን ‹‹የወንድምህን የፊሊጶስን ሚስት ማግባት አይገባህም›› እያለች መጀመሪያ ትዘልፈው እንደነበረው ሁሉ አሁንም ዘለፈችው፡፡ መዓዛዋም እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነበር፣ ዐይኖቹም እንደፀሐይ ያበሩ ነበር፡፡ የሄሮድያዳም ልጅ የመጥምቁን ራስ ወስዳ ለእናቷ ልትሰጣት ስትል ዐይኖቹ እንደፀሐይ ሲያበሩ ብታየው ‹‹ንጉሡን አትፈራውምን?›› በማለት ተቆጣች፡፡ በመቀጠልም ‹‹እነዚህን ዐይኖቹን በወስፌ እያወጣሁ እጥላቸዋለሁ፣ ምላሱንም ደግመኛ እንዳይገሥጽ ቆርጨ እጥላቸዋለሁ›› በማለት ፊቱን በጥፊ ለመምታት እጇን ስታነሣ ያንጊዜ የዮሐንስ ራስ ክንፍ አውጥታ በረረች፡፡ በአየር ላይ ሳለችም ዳግመኛ ‹‹የተረገምሽ ሄሮድያዳ የባልሽን ወንድም ሄሮድስን ማግባት አይገባሽም፣ ቀድሞ የምዘልፍሽ አሁንም የምዘልፍሽ እኔ ነኝ›› እያለች የዮሐንስ ራስ የቤቱን ጣሪያ ሰንጥቃ እንደንሥር በአየር በራ ሄደች፡፡ ከዚህም በኋላ ለጥፊ የዘረጋቻቸው የሄሮድያዳ እጆቿ ከትከሻዋ እየተቆረጡ መሬት ላይ ወደቁ፤ እውነቷንም መሬት አፏን ከፍታ ዋጠቻት፡፡ ዘፋኟ ልጇም አብዳ የቤተ መንግሥቱን ዕቃ ሁሉ መሰባበር ጀመረች፡፡ የንጉሡ አንዱ ጭፍራም የሄሮድያዳን በእሳት እንደተለበለበ የግንድ እሳት የመሰለና የተቆረጠ እጇን አምጥቶ ለሄድሮስ ሰጠውና የሆነውን ነገረው፡፡ ንጉሡም ነገሩ እውነት መሆኑን ሄዶ ባየ ጊዜ በሀፍረት እጅግ ተሸማቀቀ፡፡ ዘፍና በማስደሰት የዮሐንስን ራስ እንዲያስቆርጠው ያደረገችው የሄሮድያዳ ሴት ልጅም አብዳ በቤተ መንግሥቱ ስትለፈልፍ አገኛት፡፡ ሄሮድስም መኳንንቶቹን ‹‹በቤተ መንግሥቴ የተደረገውን ይህን ነገር ለማንም አትንገሩ›› ብሎ አማላቸው ነገር ግን ያበደችው የሄሮድያዳ ሴት ልጅ ራሷ ሄዳ ሄሮድስን ‹‹የወንድምህን የፊሊጶስን ሚስት ማግባት ፈጽሞ አይገባህም›› እያለች በመኳንንቶቹ ፊት ገሠጸችው፡፡ ንጉሥ ሄሮድስም ይህን ቃል ከእርሷ በሰማ ጊዜ እጅግ ተናደደና ‹‹ቀደሞ ያልሆነ ሥራ ታሠራ በኋላ ደግሞ ምሥጢር ታወጣ ንሣ በሰይፍ ቁረጣት›› ብሎ አንገቷን በሰይፍ አስቆረጣት፡፡ ሥጋዋንም ዓሣ አንበሪ ተቀብሎ ዋጣት፡፡ ሄሮድም የወንደሙን ሚስት ሲያገባ አስቀድሞ አግብቷት የነበረችውን ሚስቱን በግፍ አባሯት ነበር፡፡ እርሷም ይህንን ሄሮድስ ያደረሰባትን ግፍ ለአባቷ አርጣ ብትነግረው አባቷ ብዙ ጦር ሰብስቦ መጥቶ ምድረ ገሊላን በኃይል አፈራረሳት፡፡ የበላዩ ንጉሥ ቄሳርም የገሊላን መፍረስና መውድም ሲሰማ ምክንያቱን ቢጠይቅ ሄሮደስ ባደረገው ግፍ ምክንያት መሆኑን ነገሩት፡፡ ቄሳርም ሄሮድስን ከሥልጣኑ ሽሮ አጋዘውና በወህኒ ጣለው፡፡ ሄሮድስም በወህኒ ቤት ሳለ አብዶ ራሱን ስቶ የገዛ አካሉን እየነጨ እየበላ ቷ ብሎ ፈንድቶ ተልቶ ሸቶ እጅግ ክፉ አሟሟት ሞተ፡፡ የኃጢአት መጨረሻው ይህ ነው፡፡ የቅዱስ ዮሐንስን ራስ ካስቆረጡ በኋላ ሦስቱም የደረሰባቸውን ተመልከቱ፡፡ በሥጋም በነፍስም ጽኑ ቅጣት አገኛቸው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ግን በምድርም በመንግሥተ ሰማያትም ለዘለዓለም ከብሮ ይኖራል፡፡ የተቀደሰች ራሱም በሰማይ ላይ እየበረረች ወደ ደብረ ዘይት ሄደች፡፡ ጌታችንም በደብረ ዘይት እያስተማረ ሳለ ወደ እርሱ ሄደችና ከእግሩ በታች ወድቃ ሰገደች፡፡ ጌታችንም የዮሐንስን ራሱ በእጆቹ አቅፎ ይዙ በመለኮት አፉ አክብሮ ሰማት፡፡ እመቤታችንም የዮሐንስን ራስ በጌታን እጅ ላይ ሆና ባየቻት ጊዜ በሀዘን እጅግ አምርራ አለቀሰች፡፡ ጌታችንም ቅድስት እናቱን ካረጋጋት በኋላ ‹‹ክብርት እናቴ ሆይ! አታልቅሺ እነሆ ዮሐንስ ሙቶ እንዳየሽው እኔም
380Loading...
05
ዮሐንስን ዐፅም ከሌሎቹ ቅዱሳን ዐፅም ጋር አብረው በግሸን እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ክብር አስቀምጠውታል፡፡ ይህንንም መጽሐፈ ጤፉት በዝርዝር ይገልጸዋል፡፡ የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን፡፡ ምንጭ፦ የሰኔ 2️⃣ ስንክሳር፤ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ሁሉ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም በሁላችንም ይደርብን አሜን። 🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃 🍃🍃🍃🍃 ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ እም እለ አብዑ ብዑላን ዘተርፈ። ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን ሰማዕታት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን ደናግል ዓዲ ወመነኮሳት ኄራን ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን እስከ አረጋዊ ልሒቅ እምንዑስ ሕፃን። ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ ወለዘሰምዐ ቃሎ በእዝነ መንፈስ በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኲሉ እምባእስ ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ ወይፈኑ ለነ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እምይዜ ወእስከ ለዓለም አሜን። ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀይቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል። እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ። ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውንና ያጻፈውንም የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን። አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር . ⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼ ሰኔ 1️⃣ ቀን 2011 ዓ.ም
550Loading...
06
ደግሞ እሞታለሁኝ እገደላለሁኝ፡፡ ነገር ግን የእኔ ሞት እንደ ዮሐንስ አንገቴን በሰይፍ ተቆርጨ አይደለም እጅና እግሬን በብረት ተቸንክሬ በመስቀል ላይ ተሰቅዬ ነው፣ ቀኝ ጎኔንም በጦር እወጋለሁ ደምና ውኃም ከጎኔ ይፈሳል›› አላት፡፡ ሌላም ብዙ ምሥጢርን ነገራትና አጽናንቶ አረጋጋት፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ ራስ መለስ ብሎ እንዲህ በማለት ሥልጣን ሰጣት፡- ‹‹እነሆ መንፈስሽን በራስሽ ውስጥ አድርጌልሻለሁ በሰማይም የምትበሪበት እንደ ንሥር ክንፍ ሰጥቼሻለሁና እንደንስር በሰማይ እየበረርሽ በዓለም ሁሉ እየዞርሽ የሄሮድስንና የሄሮድያዳን ኃጢአት ግለጭባቸው፤ እስከ 15 ዓመት ድረስ ገቢረ ተአምራት የምታደርጊበት ኃይሌን መንፈሴን በእራስሽ ውስጥ አድርጌልሻለሁ›› አላት፡፡ ዳግመኛም ጌታችን ዮሐንስን ‹‹እኔም ከ3 ዓመት በኋላ ለአዳም የሰጠሁትን ተስፋ ፈጽሜ በሞቴ ወደ ሲኦል ወርጄ ነፍሳትን ከዲያብሎስ እጅ ማርኬ በ3ኛው ቀን ከሙታን ተለይቼ ተነሥቼ ወደ ባሕርይ ክብሬ ተመልሼ ወደ ሰማይ አርጌ ባባቴ ቀኝ በተቀመጥኩኝ ጊዜ ከ15 ዓመት በኋላ ርጉም ሄሮድስ ካስፈጃቸው ከትንንሾቹ ሕፃናት ጋራ ትሆን ዘንድ በአባቴ ፈቃድ እራስህን ተሸክመው ወደ አባትህ ወደ ዘካርያስ ያመጧት ዘንድ እኔ መላእክትን አዛቸዋለሁ፡፡ ዛሬ ግን ነፍስህን በእኔ ቀኝ ባባትህ በዘካርያስ አጠገብ አኑሬያታለሁ መንፈስህንም እስከ 15 ዓመት በእራስህ ውስጥ እንድትኖር አዝዣታለሁ፣ ሥጋህም ከነቢዩ ከኤልሳዕ ጋር እንዲቀመጥ አድርጌያለሁ›› አለው፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን እንዳዘዛት የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ እራስ እንደንስር በአየር ላይ እየበረረች የምታስተምር ሆነች፡፡ በምሥራቅ በኩል ሄዳ በዐረብ አገር ውስጥ በሰማይ ላይ ስታስተምር በዚህች ዕለት ጥቅምት 30 ቀን በግልጽ ታየች፡፡ ነጋዴዎች ድምጹዋን ሰምተውና አይተዋት እጅግ ተደስተው ገንዘባቸው ሁሉ ጥለው የቅዱስ ዮሐንስን እራስ ለመያዝ ሰውነታቸውን ብዙ አደከሙ፡፡ ነገር ግን ለመያዝ አልተቻላቸውም፡፡ ከዚህም በኋላ ከሰማይ ‹‹የምትያዝበት ጊዜ ስላልደረሰ ሰውነታችሁን አታድክሙ›› የሚል ድምጽ ከሰማይ መጣላቸው፡፡ መፈለጋቸውንም ተው፡፡ የቅዱስ ዮሐንስም እራስ 15 ዓመት ስታስተምር ኖራ ሚያዝያ 15 ቀን በዐረብ ሀገር ዐረፈች፡፡ የታዘዙ ቅዱሳን መላእክትም መጥተው ከቅዱስ ዮሐንስ እራስ ከተባረኩ በኋላ በታላቅ ዝማሬ እያመሰገኑ የቅዱስ ዮሐንስን አንገት ወስደው በነቢዩ ኤልሳዕ መቃብር ውስጥ አብረው ቀበሯት፡፡ ቅድስትን ነፍሱንም እያመሰገኑ ወደ ሰማይ አሳረጓት፡፡ በዚያም በሥሉስ ቅዱስ ዙፋን ፊት ወድቃ ከሰገደች በኋላ አባቷ ዘካርያስንና እናቷ ኤልሳቤጥን እጅ ነሳቻቸው፡፡ ከዚህም በኋላ በ3ኛው ሰማይ ውስጥ ተቀመጠች፡፡ ጌታችን ሦስቱን ሰማየ ሰማያት ርስት ጉልት አድርጎ ሰጥቶታልና፡፡ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ መላ ዘመኑ 45 ዓመት ከ8 ወር ነው፡፡ 2 ዓመት በእናት በአባቱ ቤት ተቀመጠ፣ 28 ዓመት በበረሃ ብቻውን ኖረ፣ 8 ወር ርጉም ሄሮድስ አንገቱን ከማስቆረጡ በፊት ሲያስተምር ቆየ፣ 15 ዓመት አንገቱ ከተቆረጠች በኋላ በዓለም ዞሮ ሲያስተምር ኖረ፡፡ ይህች እጅግ የከበረች የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ እራስ እኛው ሀገር ኢትዮጵያውያ ውስጥ ነው የምትገኘው፡፡ ይህንንም መጽሐፈ ጤፉት በደንብ ይገልጸዋል፡፡ ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግውና የቅዱሳን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ቅዱስ መስቀሉን በተአምራት አባቶቻችን ወደ ሀገራችን እንዲያመጡት ሲያደርግ የብዙ ቅዱሳንን ዐፅንም አብሮ ሰጥቶናል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ የከበረች እራሱ አንዷ ናት፡፡ እርሷም በግሸን ደብረ ከርቤ በእግዚአብሔር አብ ቤተ መቅደስ ውስጥ በክብር ተቀምጣ ትገኛለች፡፡ የአመጣጧም ነገር እንዲህ ነው፡- የቅዱስ ዮሐንስ እራስ 15 ዓመት ስታስተምር ኖራ ሚያዝያ 15 ቀን በዐረብ ሀገር ካረፈች በኋላ የታዘዙ ቅዱሳን መላእክት ወስደው በነቢዩ ኤልሳዕ መቃብር ውስጥ አብረው ቀበሯት፡፡ ከብዙ ዘመን በኋላ በገንዘብ ድኆች በሃይማኖት ግን ባለጸጎች የሆኑ ሁለት ደጋግ ክርስቲያኖች ለአርባ ጾም ስግደት ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው ሳለ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ለአንደኛው በራእይ ተገለጠለትና የከበረች ራሱ ያለችበትን ቦታ ነገረው፡፡ እርሱም ወዳመለከተው ቦታ ቢሄድ የቅዱስ ዮሐንስን ራስ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አገኛት፡፡ መዓዛዋም እጅግ የሚመስጥ ነው፡፡ ሰውየውም ከእርሷ ከተባረከ በኋላ ከእርሱ ጋራ ወደቤቱ ወስዶ በፊቷ መብራት እያበራ ዕጣን እያጠነ በታላቅ ክብር አኖራት፡፡ እርሱም በሞት ባረፈ ጊዜ ለእኅቱ ምሥጢሩን ነግሯት እርሷም በክብር ስትብቃት ኖረች፡፡ የቅዱስ ዮሐንስም ራስ በአንድ አርዮሳዊ ሰው እጅ እስከገባች ድረስ ከአንዱ ሰው ወደ አንዱ ሰው የምትፋለስ ሆነች፡፡ አርዮሳዊውም ሰው ከሞተ በኋላ በኢየሩሳሌም፣ አባ አንያኖስ በሀገረ ኀምዳ ኤጲስቆጶስነት ተሹመው ሳለ ቅዱስ ዮሐንስ ለአባ አንያኖስ ተገለጠለትና የከበረች ራሱ ያለችበትን ነገረው፡፡ አባ አንያኖስም ሄዶ እንደዛሬው ባለ ዕለት ግንቦት 30 ቀን ከዚያ አወጣት፡፡ ይህም የካቲት 30 ቀን ከአገኟት በኋላ ዳግመኛ ያገኙበት ነው፡፡ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስንም ራስ በነቢዩ ኤልሳዕ መቃብር ውስጥ አብረው ካኖሯት ከብዙ ዘመን በኋላ የነቢዩ ኤልሳዕና የመጥምቁ ዮሐንስ ዐፅም ሰኔ 2 ቀን ፍልሰተ ዐፅማቸው ሆነና በፈቃደ እግዚአብሔር በተአምር ወደ እስክንድርያ ሄደ፡፡ የቅዱሳኑም ዐፅም እስክንድርያ እንደደረሰ ቅዱስ አትናቴዎስ ሕዝቡን ይዞ ወጥቶ በታላቅ ክብር ተቀበላቸው፡፡ በዓላቸውንም በደስታ አከበረላቸው፡፡ በስማቸውም ቤተ ክርስቲያን አነጸላቸውና ዐፅማቸውን በክብር አስቀመጠው፡፡ የቅዱሳኑም ዐፅም በእስክንድርያ እጅግ ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን እያደረጉ ብዙ ዘመን ኖሩ፡፡ ከዓባይ ወንዝ ውጭ ሕይወት የሌላቸው ግብጾች አምጸው በሀገሪቱ ያሉትን ክርስቲያኖች ያሠቃዩአቸው ጀመር፡፡ ሊቀ ጳጳሳቱን አባ ሚካኤልንም አሠሯቸው፡፡ ይህንንም ሲሰሙ ዐፄ ዳዊት ሱዳን ድረስ ዘምተው የዓባይን ወንዝ አቅጣጫውን በማስቀየር ግብጻውያንን በረሀብ ሊፈጇቸው ሲሉ እስላሞቹ የግብጽ መሪዎች ሊቀ ጰጳሳቱን ከእስር ፈቷቸውና አከበሯቸው፡፡ ዐፄ ዳዊትም የግብጹን ሊቀ ጳጳሳት ከእስላሞች የግዞት እስራት ካስፈቷቸው በኋላ ሊቀ ጳጳሳቱና ክርስያኖቹ ተመካክረው ብዙ ወርቅ እጅ መንሻ አድርገው ቢሰጧቸው ንጉሣችን ግን ‹‹የዳነው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ነው እንጂ በሰው ነውን? እኔስ ወርቅና ብር አልሻም የጌታዬን ቅዱስ መስቀሉን ስጡኝ እንጂ›› ብለው መልእክት ጽፈው እጅ መንሻቸውን መልሰው ላኩላቸው፡፡ ዐፄ ዳዊትም የዓባይን ወንዝ አለቀቀላቸውም ነበርና ገዥዎቹ እስላሞች እጅግ ተጨንቀው ሊቀ ጳጳሳቱንና ኤጲስቆጶሳቱን ካህናቱንም ሁሉ ሰብስበው የኢትዮጵያዊውን ንጉሥ ፈቃዱን እንዲፈጽሙለት ነገሯቸው፡፡ የግብጹ ሊቀ ጳጳሳትና ክርስያኖቹም በጉዳዩ ከተመካከሩ በኋላ ‹‹እርሱስ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን የሚወድ ሃይማኖቱ የቀና ደገኛ ንጉሥ ነውና ቅዱስ መስቀሉን ከሌሎች ቅዱሳን ዐፅም ጋር እንስደድለትና ደስ እናሰኘው›› ብለው ተማሩ፡፡ በመጨረሻም በፈቃደ እግዚአብሔር በግብጽ ያሉ የከበሩ ቅዱሳት ንዋያትንና የብዙ ቅዱሳንን ዐፅም ከቅዱስ መስቀሉ ጋር ለዐፄ ዳዊት ላኩለት፡፡ ከእነዚህም ቅዱሳን ዐፅም ውስጥ እጅግ የከበረች የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ እራስ አንዷ ናት፡፡ ጥንቁቅ የሆኑ አባቶቻችን የጌታችንን ቅዱስ መስቀል በዕንጨት፣ በብረት፣ በነሐስና በወርቅ ሣጥን ደራርበው በክብር ሲያስቀምጡ የመጥምቁ
390Loading...
07
Media files
440Loading...
08
የከበረ ቅዱስ ቢፋሞንን ግን አርያኖስ ወደ ንጉሡ መክስምያኖስ ሰደደው፡፡ ንጉሡም ‹‹የነገሥታቱን ትእዛዝ የምትተላፍ ለአማልክት የማትሠግድ ሥራየኛው ቢፋሞን አንተ ነህን?›› አለው፡፡ ቅዱሱም ‹‹እኔ ሥራይን አላውቅም፣ ለረከሱ አማልክትህ ግን አልሰግድም፣ አንተም እነርሱም በአንድነት ወደ ገሃነመ እሳት ትወርዳላችሁ›› አለው፡፡ ንጉሡም ይዞ በእጅጉ አሠቃው፡፡ ማሠቃየትም በሰለቸው ጊዜ ወደ መኮንኑ ኄሬኔዎስ ላከው፡፡ እርሱም ካሠቃው በኋላ መልሶ ለአርያኖስ ላከው፡፡ በእነዚህም ጊዜ ቅዱስ ቢፋሞን ምንም አልበላም ነበር፡፡ አርያኖስም በብረት ችንካሮች ቸነከረውና ‹‹ለአማልክት ካልሰገድክ አጠፋሃለሁ› አለው፡፡ ቅዱሱም ንጉሡንና አማልክቱን ረገማቸው፡፡ መኮንኑም በዚህ ጊዜ አሥሮ እየጎተተ በከተማው ሁሉ አዞረው፡፡ ከእንዴና ከተማ ውጭ አውጥቶ በእሳት አቃጠለው፤ ነገር ግን ጌታችን ቅዱስ ቢፋሞንን ከእሳቱ ውስጥ ያለምንም ጉዳት በደህና አወጣው፡፡ ቅዱሱም በእሳት ቆሞ ሳለ ከእግሮቹ ብዙ ደም ፈሰሰ፡፡ በዚያም ቦታ አንድ ዐይነ ሥውርና ለምጻም ሰው ነበረ፡፡ እርሱም ከቅዱስ ቢፋሞን ደም ወስዶ ዐይኑን ቢቀባው ወዲያው ማየት ቻለ፣ ከለምጹም ነጻ፡፡ ከዚህም በኋላ ‹‹እኔም በቅዱስ ቢፋሞን አምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኛለሁ›› ብሎ ጮኸ፡፡ ወዲያውም መኮንኑ ተናዶ ራሱን በሰይፍ አስቆረጠውና የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ፡፡ ከዚህም በኋላ መኮንኑ አርያኖስ የቅዱስ ቢፋሞንንም አንገት በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ፡፡ ቅዱስ ቢፋሞንም አገልጋዩን ዲዮጋኖስን ወደ እርሱ አቅርቦ ሥጋውን በስውር እንዲጠብቅ ደሙንም በበፍታ ልብስ እንዲቀበል ይኸውም ከመከራው ዘመን በኋላ ለበረከት እንዲሆን ነገረው፡፡ ገድሉንም ለምእመናን እንዲነገር ከነገረው በኋላ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ብሎ በመስቀል ምልክት አማተበና ወደ ጭፍሮቹ ሄዶ ‹‹የታዘዛችሁትን ፈጽሙ›› በማለት እንዲሰይፉት ራሱን አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ እነርሱም ወደ ላይኛው ግብጽ አጥማ አውራጃ ወስደው ራሱን በሰይፍ ቆረጡትና የሰማዕትነት ፍጻሜው ሆነ፡፡ የተዘጋጀለትንና አስቀድሞ ያየውን የክብር አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ፡፡ ከአንገቱም ብዙ ደም በፈሰሰ ጊዜ አገልጋዩ ዲዮጋኖስ በፍታውን ዘርግቶ ደሙን ተቀበለ፡፡ በቦታው መዓዛው እጅግ ጣፋጭ የሆነ ሽታ በሸተተ ጊዜ ችፍሮቹ ደንግጣና ፈርተው ከቦታው ሸሹ፡፡ ምእመናንም መጥተው ሥጋውን ወስደው በክብር ገንዘው ቀበሩት፡፡ ከመቃብሩም ብዙ ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራት ተገለጡ፡፡ አገልጋዩም ያችን በፍታ ወደ አገሩ ወስዶ ምን እንደሚያደርግ እያሰበ ሳለ ቅዱስ ቢፋሞን ተገለጠለትና ለወዳጁ ለቴዎድሮስና ለአገሩ ሰዎችም ሁሉ ገድሉን እንዲነግር አዘዘው፡፡ እርሱም በመርከብ ተሳፍሮ ሲሄድ በመርከብ ሳለ ጌታችን በዚያች በቅዱስ ቢፋሞን ደም በታለለች በፍታ ብዙ ተአምር አደረገ፡፡ ዲዮጋኖስም የቅዱሱን ገድል ነገራቸው፡፡ እነርሱም እያደነቁ ወደ አገሩ አውሲም አደረሱት፡፡ ዲዮጋኖስም አውሲም እንደደረሰ ለቅዱስ ቴዎድሮስና ለአገሩ ሰዎች ሁሉ የቅዱስ ቢፋሞንን ገድል ነገራቸው፣ ያችንም በደሙ የታለለች በፍታ ሰጣቸው፡፡ እነርሱም ብዙ ተአምራት እያደረገችላቸው ከእነርሱ ጋር በክብር አኖሯት፡፡ የመከራው ዘመን አልፎ ደገኛው ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ከነገሠ በኋላ እግዚአብሔርም የከበረ የቅዱስ ቢፋሞንን ሥጋ ገለጠላቸው፡፡ የተዋበች ቤተ ክርስቲያንም አንጸውለት ቅዱስ ሥጋውን በዛሬዋ ዕለት ሰኔ አንድ ቀን በውስጧ አኖሩት፡፡ ዕለቷንም እጅግ አከበሯት፡፡ ከቅዱሱም ሥጋ ብዙ አስደናቂ ተአምራት ተፈጽመው ታዩ፡፡ እነርሱም ከቅዱስ ቢፋሞን ሥጋ በረከትን እየተቀበሉ በሰላም ኖሩ፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን፡፡ 🔥 ቅዱስ ዮሴፍ አባቱ ያዕቆብ እናቱ ራሄል ይባላሉ፡፡ ለአባቱ 11ኛ ልጅ ነው፡፡ አባቱ ያዕቆብ የወንድሙን የኤሳውን በረከት ከአባቱ ከወሰደ በኋላ ከኤሳው ሸሽቶ ወደ አጎቱ ላባ ዘንድ ተሰዶ 14 ዓመት ለላባ ተገዝቶ ራሄልንና ርብቃን አግብቶ ብዙ ልጆችን ወለደ፡፡ ሀብት ንብረትም ካፈራ ከ21 ዓመት በኋላ ወደ አባቱ አገር ተመልሶ ከወንድሙ ጋር ታረቀ፡፡ ያዕቆብም በምድረ በዳ አቅራቢያ ባለች አብርሃም ይቀመጥባት ከነበረ አገር ከአባቱ ከይስሐቅ ዘንድ ደረሰ፡፡ ይህችውም በከነዓን ያለችው ኬብሮን ናት፡፡ አባቱ ይስሐቅ አብርሃም ይቀመጥባት በነበረችው የወይራ ዛፍ ሥር ተቀምጦ አገኘው፡፡ ከዚህም በኋላ ይስሐቅ አርጅቶ ዘመኑን ጨርሶ ሞተ፡፡ ያዕቆብም አባቱ ይስሐቅ ይኖርባት በነበረች አገር ኖረ፡፡ ያንጊዜም ልጁ ዮሴፍ 17 ዓመት ሆኖት ነበር፡፡ እርሱም ከአባቱ ከያዕቆብ ሚስቶች ከዘለፋ ልጆችና ከባላ ልጆች ጋር የአባቱን በጎች ይጠብቅ ነበር፡፡ ያዕቆብም በእርጅናው ዘመን ወልዶታልና አብልጦ ይወደው ነበር፡፡ ወንድሞቹም በዚህ ምክንያት ጠሉት፡፡ ዮሴፍም ሕልም አልሞ ሕልሙን ለወንድሞቹ ነገራቸው፡፡ ዮሴፍም ያየው ሕልም 11ዱ ወንድሞቹና አባቱም ጭምር ለዮሴፍ እንደሚገዙለትና እንደሚሰግዱለት የሚያሳይ ነበር፡፡ ይህንንም ሕልሙን ሲሰሙ ወንድሞቹ ይበልጥ ጠሉት፡፡ የዮሴፍም ወንድሞች የአባታቸውን በጎች ይዘው ወደ ሴኬም ጎዳና ሄዱ፡፡ አባቱም ዮሴፍን ‹‹ወንድሞችህን አይተሃቸው ና›› ብሎ ስንቃቸውን ቋጥሮ ወደ ቆላው ላከው፡፡ ሴኬምም እንደደረሰ አንድ ሰው ወንድሞቹ ያሉበትን አሳይቶት ወደ ዶታይን ወረደ፤ በዶታይንም አገኛቸው፡፡ እነርሱም በሩቅ ሳለ አዩትና ወደ እነርሱ ገና ሳይቀርብ ይገድሉት ዘንድ በእርሱ ላይ ተማከሩ፡፡ ‹‹እንግደለውና በአንድ ጕድጓድ ውስጥ እንጣለው፡፡ ክፉ አውሬም በላው እንላለን›› ብለው ሲመካከሩ ከእነርሱ ውስጥ ሮቤል ይህን ሲሰማ ‹‹ሕይወቱን አናጥፋ፣ ደም አታፍስሱ፤ በዚህች ምድረ በዳ ባለችው ጕድጓድ ጣሉት፣ ነገር ግን እጃችሁን አትጣሉበት›› አላቸው፡፡ ሮቤልም እንዲህ ማለቱ ከእጃቸው ሊያድነውና ወደ አባቱ ሊመልሰው ነው፡፡ ዮሴፍንም ቀሚሱን ገፈው ወስደው ወደ ቀበሮ ጕድጓድ ጣሉት፡፡ ጉድጓዱንም በድንጋይ ገጥመው በላይ ተቀምጠው ዮሴፍ ያመጣላቸውን እንጀራ እየተመገቡ ሳለ የእስማኤላውያን ነገዶች ወደ ግብፅ ለመውረድ ከገለዓድ ሲመጡ አይተው በይሁዳ ምክር ወንድማቸውን ከጕድጓድ አውጥተው ለእስማኤላውያን በሀያ ብር ሸጡት፤ እስማኤላውያንም ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወሰዱት፡፡ የፈርዖን ጃንደረባ የዘበኞቹም አለቃ የሚሆን የግብፅ ሰው ጲጥፋራ ዮሴፍን ወደ ግብፅ ካወረዱት ከእስማኤላውያን እጅ ገዛው፡፡ እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ነበረ፣ ሥራውም የተከናወነለት ሰው ሆነ፡፡ ጌታውም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንዳለ፣ እርሱ የሚሠራውንም ሁሉ እግዚአብሔር በእጁ እንዲያከናውንለት አየ፡፡ ዮሴፍም በጌታው ፊት ሞገስን ስላገኘ በቤቱ ላይ ሾመው፣ ያለውንም ሁሉ በእጁ ሰጠው፡፡ በቤቱ ባለውም ሁሉ ላይ ከሾመው በኋላ እግዚአብሔር የግብፃዊውን ቤት ስለ ዮሴፍ ባረከው፤ የእግዚአብሔር በረከት በውጪም በግቢም ባለው ሁሉ ላይ ሆነ፡፡ ጲጥፋራም ያለውን ሁሉ ለዮሴፍ አስረከበ። የዮሴፍም ፊቱ መልከ መልካምና ውብ ነበረ፡፡ ይኸውም ምሳሌ ነው፡፡ ዮሴፍ የጌታችን፣ ወንድሞቹ ደግሞ የአይሁድ ምሳሌ ናቸው፡፡ ዮሴፍ ምግባቸውን ይዞላቸው ቢሄድ ከበው እንደደበደቡት ሁሉ ጌታችንም ‹‹እኔ ግን እላችኋለሁ…›› እያለ የነፍሳቸውን ምግብ ቢያስተምራቸው አይሁድ ጠልተውት ገድለውታል፡፡ ዮሴፍ እንዲሸጥ ሀሳብ ያመጣው ይሁዳም ጌታችንን የሸጠው የይሁዳ ምሳሌ ነው፡፡ ዮሴፍ በግብፅ ሕያው በከነዓን ግን ምውት እንደሆነ ሁሉ ጌታችንም በመለኮቱ ሕያው ሲሆን በትስብእቱ ግን ምውት ሆኗል፡፡
350Loading...
09
ሆነ፡፡ ሁለተኛም በሌላ ጊዜ በቅዱስ ዳዊት መዝሙር ሲያመሰግን ከዚያ አንድ ጋኔን የሚጥለው ሰው ነበረና ‹‹የእግዚአብሔር ቅዱስ ሆይ ተወኝ፣ ከዚህ ቦታ ልጥፋ›› ብሎ ጮኸ፡፡ ቅዱስ ቢፋሞን ወደ ጌታችን ጸልዮ ያንን ጋኔን ያደረበትን ሰው አዳነው፡፡ መምህሩም ይህን አይቶ በዚህ ሕፃን ልጅ ያደረውን ጸጋ አደነቀ አከበረውም፡፡ በመምህሩም ዘንድ 8 ዓመት ኖረ፡፡ ጌታችንም ቅድስት እናቱን ድንግል ማርያምንና ቅዱሳኑን እያስከተለ እየመጣ ይገለጥለት ነበር፡፡ ቅዱስ ቢፋሞን በየሰባት ቀን በመጾም ተጋድሎውን ጨመረ፡፡ ከሰንበት በቀር አይበላም ነበር፡፡ ዕድሜው ከፍ ሲል ወላጆቹ ሚስት ሊያጋቡት አሰቡ፡፡ እርሱ ግን ‹‹በዚህ እንደጤዛ በሚያልፍ ዓለም ከሴት ጋር መኖር ለእኔ ምኔ ነው? ፍላጎቱም ዓለሙም ሁሉም ያልፋል›› አላቸው፡፡ ከዚህም በኋላ በሰባተኛው ወር አባቱ ሲያርፍ ቅዱስ ቢፋሞን ንብረቱን ሁሉ አውጥቶ ለጦም አዳሪዎች ሰጣቸውና በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የተጠመደ ሆነ፡፡ በዚያም ወራት የፋርስ ሰዎች በሮም ሰዎች ላይ ጦርነት አስነሥተው ነበር፡፡ የሮሙ ንጉሥ በጦርነቱ ስለሞተ ሮም ያለንጉሥ ቀረች፡፡ መኳንንቱና የመንግሥት ታላላቅ ሰዎችም ተሰብስበው ከአገሮች ሁሉ ተዋጊዎች የሆኑ አርበኞችን ይሰበስቧቸው ዘንድ በየአገሩ አዘዙ፡፡ ከላይኛው ግብፅ ልበ ደንዳና የሆነ ስሙ አግሪጳዳ የሚባል ሰይጣን በልቡ ያደረበት ፍየል ይጠብቅ የነበረ ኃይለኛ ሰው ተገኘ፡፡ እርሱንም ወደ አንጾኪያ አገር ወስደው የፈረሶች ባልደራስ አድርገው ሾሙት፡፡ በአንዲት ዕለትም ሸንበቆ አንሥቶ ዋሽንት ሠርቶ ሲነፋ በፈረሶቹ ላይ ሰይጣን አደረባቸውና ፈረሶቹም እያሽካኩ ይጨፍሩ ጀመር፡፡ በጦርነት የሞተው ንጉሥ ሴት ልጅም በቤተ መንግሥት አዳራሽ ሆና ሲዘፍንና ዋሽንት ሲነፋ አግሪጳዳን አይታ ወደደችው፡፡ ሰይጣንም በልቧ የዝሙትን ፍላጻ ጨመረባትና ወደ እርሷ አስመጣችውና አገባችው፡፡ ስሙንም ዲዮቅልጥያኖስ ብላ ሰየመችውና አነገሠችው፡፡ ታናሽ እኅቷም በእርሷ ቀንታ መክስምያኖስ የሚባለውን አንዱን መኮንን መልምላ አገባችና ልብሰ መንግሥት አልብሳ አነገሠችው፡፡ መክስምያኖስና ዲዮቅልጥያኖስም በአንጾኪያና በሮም ተስተካከለው ነገሡ፡፡ ከዚህም በኋላ ሰይጣን ተገለጠላቸውና እንዲህ አላቸው፡- ‹‹በንጉሡ ሴቶች ልጆች ላይ የዝሙትን ፍቅር በልባቸው ላይ አሳድሬ እንዲወዷችሁና እንዲያገቧችሁ ያደረኩት እኔ ነኝ፤ አሁንም ትእዛዜን ከሰማችሁ በምድር የሚኖረውን ሕዝብ ሁሉ በእጃችሁ ውስጥ አደርግላችኋለሁ፤ እናንተም ስገዱልኝ የብርና የወርቅ ምስልም ሠርታችሁ አማልክት በሏቸው፡፡ ስማቸውንም አጵሎን አርዳሚስ ብላችሁ ጥሯቸው፡፡ ሰዎችም ሁሉ ዕጣን እንዲያሳርጉላቸውና እንዲሰግዱላቸው እዘዙ፤ ያልሰገዱላቸውንም ራስ ራሶቻቸውን በሰይፍ ቁረጡ፤ ይህን ካደረጋችሁ መንግሥታችሁን አሰፋላችኋለሁ ካለዚያ ግን መንግሥታችሁ ታልፋለች›› አላቸው፡፡ እነዚህም ሁለት ሰነፎች መክስምያኖስና ዲዮቅልጥያኖስም ለሰይጣን ሰገዱለትና ‹‹ያዘዝከንን ሁሉ እናደርጋለን ብቻ መንግሥታችንን አጽናልን›› አሉት፡፡ በዚህም ጊዜ ኄሬኔዎስንና አርያኖስን በግብጽ አገር ላይ መኳንንት አድርገው ሾሟቸው፡፡ ለጣዖት የማይሰግዱትን ሁሉ እንዲገድሉ አዘዟቸው፡፡ የከበረ ቅዱስ ቢፋሞንም ይህንን ትእዛዝ በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ፡፡ ወዳጁን ቴዎድሮስን ጠራውና በክብር ባለቤት በጌታችን ስም ደማቸው አፍስሰው ሰማዕት ይሆኑ ዘንድ በምክር ተስማሙ፡፡ የቅዱስ ቢፋሞን ዜናው በሁሉ ዘንድ የታወቀ ነውና ወሬው ከሃዲው ንጉሥ መክስምያኖስ ዘንድ ተሰማ፡፡ መኳንንቶቹም ‹‹በምስር አውራጃ በአውሲም ከተማ የሚኖር ስሙ ቢፋሞን የሚባል ሰው አለ፣ እርሱም የነገሥታትን ትእዛዝ የሚተላለፍ አማልክትን የሚረግምና የሚያቃልል ነው›› ብለው ለንጉሥ መክስምያኖስ ነገሩት፡፡ በዚህም ጊዜ ንጉሡ ቅዱስ ቢፋሞን ለአማልክት ካልሰገደ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጠው ትእዛዝ ጽፎ ለጨካኙ መኮንን ለአርያኖስ ላከለት፡፡ ደብዳቤውም ከመኮንኑ ዘንድ ሳይደርስ የታዘዘ የእግዚአብሔር መልአክ ለቅዱስ ቢፋሞን ተገልጠለትና በሰማዕትነት እንደሚሞት እናቱና አገልጋዩ ዲዮጋንዮስም አብረውት እንደሚሞቱ ከነገረው በኋላ ሰማዕትነቱን በትዕግስት እንዲፈጽም ነገረው፡፡ የተዘጋጀላቸውንም የክብር አክሊላት አሳየው፡፡ ቅዱስ ቢፋሞን ተነሥቶ ለእናቱ መልአኩ የነገረውን ነገራት፡፡ መልአኩ ለእርሷም ተልጦ ይህንኑ እንደነገራት ለልጇ ነገረችውና ለሰማዕትነት በመመረጣቸው በአንድነት እጅግ አላቸው፡፡ ሲጸልዩ አደሩና በነጋታው ቅዱስ ቢፋሞን ወዳጁን ቴዎድሮስን አስጠራውና ሁሉን ነገረው፡፡ ቀጥሎም ‹‹የመከራው ጊዜ ካለፈ በኋላ አንተ በዚህች አገር ላይ ኤጲስቆጶስነት ትሾማለህ ያንጊዜም በስሜ ቤተ ክርስቲያን ትሠራለህ›› ብሎ ትንቢት ነገረው፡፡ ወዲያም ሰላምታ ተሰጣጡና ተሳስመው ተለያዩ፡፡ ከጥቂት ቀኖች በኋላ በአውሲም ከተማ መኮንኑ አርያኖስ ደረሰ፡፡ የሀገሩን ታላላቅ ሰዎችንም አቅርቦ ስለከበረ ቅዱስ ቢፋሞን ጠየቃቸው፡፡ የአገር ሽማግሎችም ስለእርሱ አዘኑ-እርሱ ተአምራትን የሚያደርግ አማልክትንም የሚረግም መሆኑን ያውቃሉና፡፡ ወዲያውም ቅዱስ ቢፋሞን ቤተሰቦቹን ተሰናብቶ ያማሩ ልብሶቹን ለብሶ ፈረስ ጋልቦ የሀገሩ ሽማግሎችና መኮንኑ ካሉበት ቦታ ደረሰ፡፡ መኮንኑ አርያኖስም ባየው ጊዜ ደስ ብሎት በክብር ሰላምታ ሰጠው፡፡ ቅዱስ ቢፋሞንም ‹‹የሰላም ትርጓሜው ደስታ ነው፣ እኔ በጌታዬና በፈጣሪዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ደስታ አለኝ አንተና ባልንጀሮችህ ግን በሰማያት ደስታ የላችሁም›› አለው፡፡ አርያኖስም ‹‹እኔ ክፉ ነገርን እንድትነግረኝ አልመጣሁም፣ ለአማልክት እንድትሠዋ በንጉሡ ደብዳቤ ታዝዤ መጣሁ እንጂ›› አለው፡፡ ቅዱስ ቢፋሞንም ‹‹አማልክቶቻችሁ አፍ እያላቸው የማይናገሩ፣ እጅ እያላቸው የማይዳስሱ፣ ጆሮ እያላቸው የማይሰሙ፣ ዐይን እያላቸው የማያዩ፣ አፍ እያላቸው የማይተነፍሱ ናቸውና የሠሩአቸውና የሚያመልኳቻም እንደ እነርሱ ይሁኑ፡፡ እኔ ግን ሰማይንና ምድርን በውስጣቸውም ያለውን ሁሉ ለፈጠረ ለጌታዬ ለፈጣሪዬ ለኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ አሰግዳለሁ›› አለው፡፡ መኮንኑ አርያኖስም ይህንን ነገር ከቅዱስ ቢፋሞን አፍ በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ፡፡ ጽኑ በሆኑ ልዩ ልዩ ማሠቃያዎችም አሠቃየው፡፡ ዳግመኛም በፈረሶች ላይ አሥሮ መሬት ለመሬት እየጎተተ ከተማውን ሁሉ አዞረው፡፡ የቅዱስ ቢፋሞን እናቱና አገልጋዩ በመጡ ጊዜ በከበረች የወንጌል ቃል አጽናናቸው፡፡ እነርሱና ሌሎችም የከተው ሰዎች ‹‹እኛም በቅዱስ ቢፋሞን አምላክ የምናምን ነን፣ ሰማዕትም እንሆን ዘንድ እንወዳለን›› ብለው ጮኹና የመኮንኑን ወንበር ገለበጡት፡፡ መኮንኑም ጥልቅ ጉድጓድ አስቆሮ እሳት አስነድዶ ከዚ ውስጥ ጨመራቸውና ሰማዕትነታቸውን በድል ፈጽመው የድል አክልሊን ተቀዳጁ፡፡ ቁጥራቸውም አምስት መቶ ሆነ፡፡ እነዚህም 500 ቅዱሳን ምስክርነታቸውን እስኪፈጽሙ ድረስ ቅዱስ ቢፋሞን ያጽናናቸውና ያበረታቸው ነበር፡፡ የከበረች እናቱም በላይዋ ላይ እንዲጸልይ ለመነችው፣ እርሱም በመስቀል ምልክት በላይዋ አማተበና በሰላም ሂጂ አላት፡፡ እርሷም ወዲያው ማንም ሳይነካት ዘላ ከእሳቱ ገባች፡፡ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለች፡፡
280Loading...
10
አይዟችሁ አትፍሩ›› እያለ እንዳይፈሩ አጽናናቸው፤ ደስም አሰኛቸው፡፡ ዮሴፍም በግብፅ ተቀምጦ 110 ዓመት ኖረ፡፡ የኤፍሬምን ልጆች እስከ ሦስት ትውልድ ካየ በኋላ ወንድሞቹን ጠርቶ ‹‹እኔ እሞታለሁ፤ እግዚአብሔርም መጎብኘትን ይጎበኛችኋል፣ ከዚህችም ምድር ያወጣችኋል፤ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም ወደማለላቸው ምድር ያደርሳችኋል፡፡ እግዚአብሔር ሲያስባችሁ አጥንቴን ከዚህ አንሥታችሁ ከእናንተ ጋር ውሰዱ እንጂ ከዚህ አትተውት›› ብሎ አማላቸው፡፡ ዮሴፍም በ110 ዕድሜው በሰላም ዐረፈ፡፡ በሽቱ አሽተው በግብፅ ምድር በሣጥን ውስጥ አኖሩት፡፡ ዮሴፍም ‹‹እግዚአብሔር ሲያስባችሁ አጥንቴን ከዚህ አንሥታችሁ ከእናንተ ጋር ውሰዱ እንጂ ከዚህ አትተውት›› ማለቱ አንድም ከግብፅ ምድር እንደሚወጡና የአባቶቻቸውን ርስት ከነዓንን እንደሚወርሱ ሲነግራቸው ነው፡፡ ፍጻሜው ግን ግብፅ የመቃብር ከነዓን የትንሣኤ ምሳሌ ናቸው፡፡ አንድም ግብፅ የገሃነም ከነዓን የመንግሥተ ሰማይ ምሳሌ ናቸው፡፡ ያዕቆብም እንዲሁ ብሏልና ዮሴፍም እንዲህ ያለ ስለምን ነው ቢሉ አባቶቻችን እንዲህ ማለታቸው መውጣታችንን ቢያውቁ ነው ብለው እንዲነቁ፣ እንዲተጉ፣ አንድም ለማጸየፍ ነው፣ ‹‹አባቶቻችን አጥንታችን እንኳን ከዚህ አይቅር›› ብለዋል ብለው እንውጣ እንዲሉ ነው፡፡ የቅዱስ ዮሴፍ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን፡፡ ምንጭ፦ የሰኔ ❶ ስንክሳር ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎትና ምልጃ ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 1️⃣ ስንክሳር፤ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ሁሉ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም በሁላችንም ይደርብን አሜን። 🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃 🍃🍃🍃🍃 ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ እም እለ አብዑ ብዑላን ዘተርፈ። ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን ሰማዕታት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን ደናግል ዓዲ ወመነኮሳት ኄራን ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን እስከ አረጋዊ ልሒቅ እምንዑስ ሕፃን። ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ ወለዘሰምዐ ቃሎ በእዝነ መንፈስ በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኲሉ እምባእስ ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ ወይፈኑ ለነ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እምይዜ ወእስከ ለዓለም አሜን። ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀይቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል። እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ። ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውንና ያጻፈውንም የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን። አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር . ⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼ ግንቦት 3️⃣0️⃣ ቀን 2011 ዓ.ም
770Loading...
11
ወንድሞቹም የዮሴፍን ቀሚስ ወስደው የፍየል አውራም አርደው ቀሚሱን በደም ነክረው ወደ አባታቸው ሄደው ‹‹ይህንን አገኘን፣ ይህ የልጅህ ልብስ እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ እስኪ እየው›› አሉት፡፡ ያቆዕብም ‹‹ይህ የልጄ ቀሚስ ነው፤ ክፉ አውሬ በልቶታል›› ካለ በኋላ ልብሱን ቀዶ በወገቡም ማቅ ታጥቆ ለልጁ ብዙ ጊዜ አምርሮ ስላለቀሰ ዐይኑ ጠፋ፡፡ ዮሴፍም ጌታውን በቅንነት እያገለገለ ሲኖር የጌታው ሚስት ባሏ በሌለበት ጠብቃ በዮሴፍ ላይ የዝሙት ዐይኗን ጣለችበትና ‹‹ከእኔ ጋር ተኛ›› አለችው፡፡ ዮሴፍም ‹‹እነሆ ጌታዬ በቤቱ ያለውን ምንም ምን የሚያውቀው የለም፣ ያለውንም ሁሉ ለእኔ አስረክቦኛል፤ ለዚህ ቤት ከእኔ የሚበልጥ ሰው የለም፤ ሚስቱ ስለሆንሽ ከአንቺም በቀር ያልሰጠኝ ነገር የለም፤ እንዴት ይህን ትልቅ ክፉ ነገር አደርጋለሁ? በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ኃጢአትን እሠራለሁ?›› አላት፡፡ እርሷ ግን ስለዚህ ነገር በየጊዜው ትጨቀጭቀው ነበር፡፡ አንድ ቀን ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ በቤት ውስጥ ከቤት ሰዎች ማንም ስላልነበረ ወደ እርሱ ገብታ ከእኔ ጋር ተኛ ስትል ልብሱን ተጠማጥማ ያዘች፤ እርሱም ልብሱን በእጅዋ ትቶላት ሸሽቶ ወደ ውጭ ወጥቶ ሄደ፡፡ የጲጥፋራ ሚስት ግን የቤቷን ሰዎች ጠርታ ‹‹እዩ ዕብራዊው ሰው ከእኔ ጋር ሊተኛ ወደ እኔ ገባ፣ እኔም ድምፄን ከፍ አድርጌ ስጮኽ ቢሰማ ልብሱን በእኔ ዘንድ ጥሎ ሸሸ ወደ ውጭም ወጣ›› ብላ በሐሰት ከሰሰችው፡፡ ባሏም ሲመጣ እንዲሁ ብላ ነገረችው፡፡ ባሏም የእርሷን ቃል በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ፡፡ ዮሴፍን ይዞ እስር ቤት ጣለው፡፡ እግዚአብሔርም ከዮሴፍ ጋር ነበረ፣ ምሕረትንም አበዛለት፥ በግዞት ቤቱም አለቃ ፊት ሞገስን ሰጠው፡፡ የሚያደርገውንም ሁሉ እግዚአብሔር ያቀናለት ነበር፡፡ የጲጥፋራ ሚስት የኃጢአት ምሳሌ ስትሆን ዮሴፍ የንጽሕና ምሳሌ ነው፡፡ ኃጢአት ደርሳ ሥሩኝ ሥሩኝ ስትላችሁ የንጽሕናን የቅድስናን ነገር አስባችሁ ፈጥናችሁ ከእርሷ ተለዩ ሲል ነው፡፡ ንጽሕናችሁን በኃጢአት አታቆሽሹ አለ፡፡ አንድም የጲጥፋራ ሚስት የዚህ ዓለም ዮሴፍ የመናንያን ምሳሌ ነው፡፡ ዮሴፍን የጲጥፋራ ሚስት ሽንገላ ሳያታልለው ጥሏት እንደሸሸ ሁሉ መናንያንም የዚህ ዓለም ሀብት፣ ንብረት፣ ቤት፣ ልጅ፣ ባል፣ ሚስት… ሳያታልላቸው የዓለምን ጣዕም ሸሽተው ገዳም ይገባሉና ነው፡፡ ዮሴፍ ከታሰረ ከሁለት ዓመት በኋላ ንጉሡ ፈርዖን ሕልም አየ፡፡ በነጋም ጊዜ ነፍሱ ታውካ የግብፅን ሕልም ተርጓሚዎችና ጠቢባንን ሁሉ ሰብስቦ እንዲተረጉሙለት ሕልሙን በዝርዝር ነገራቸው፡፡ ነገር ግን ሊተረጉሙለት አልቻሉም ነበር፡፡ የንጉሡም የጠጅ አሳላፊ አስቀድም ከዮሴፍ ጋር ታስሮ ሳለ እርሱ ያየውን ሕልም ዮሴፍ ተርጉሞለት እንደነገረው ሆኖለት ስለነበር በዚህ ጊዜ የጠጅ አሳላፈው ለንጉሡ ስለ የሴፍ ነገረው፡፡ ፈርዖንም ዮሴፍን አስመጥቶ ሕልሙን ነግሮት ተረጎመለት፡፡ በፈርዖንም ሕልም መሠረት ሰባት ዓመታት ጥጋብ እንደሚሆንና ከዚያም በኋላ ሰባት የርኃብ ዓመታት እንደሚመጡ ነገረው፡፡ ፈርዖንም ዮሴፍን ‹‹እኔ በዙፋኔ ብቻ ከአንተ እበልጣለሁ›› ብሎ በቤቱና በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ሾመው፡፡ ቀለበቱንም አውጥቶ አሰረለት፡፡ ይህም የሆነው በ30 ዘመኑ ነው፡፡ ዮሴፍ በእናት በባቱ ቤት 17 ዓመት፣ በጲጥፋራ ቤት 10 ዓመት፣ በእስር ቤት ሁለት ዓመት ተቀምጦ ባጠቃላይ ልክ 30 ዓመት ሲሆነው በፈርዖን ፊት ለሹመት ቆመ፡፡ ይኸውም ምሳሌ ነው፡፡ ዮሴፍ በ30 ዘመኑ ለሹመት በፈርዖን ፊት እንደቆመ ሁሉ ጌታችን መድኃኔዓም ክርስቶስም በጲላጦስ ፊት ለፍርድ የቆመው በ30 ዘመኑ ነው፡፡ ዮሴፍም በግብፅ ምድር ዞሮ የሰባቱን ዓመት እጅግ ብዙ እህል ሰበሰበ፡፡ ሰባቱም የጥጋብ ዘመን ሲያልፍ ሰባቱ የርኃብ ዘመን በጀመረ ጊዜ በሀገሩ ሁሉ ታላቅ ርኃብ ሆነ ነገር ግን በግብፅ ምድር ብቻ እህል ነበር፡፡ ንጉሡም ከየሀገሩ ሁሉ ወደ እርሱ የሚመጡትን ወደ ዮሴፍ እየላካቸው ዮሴፍም እህል ከጎተራ እያወጣ ይሸጥላቸው ነበር፡፡ የዮሴፍ አባት ያዕቆብ በግብፅ እህል እንዳለ በሰማ ጊዜ ልጆቹን እህል እንዲሸምቱ ወደ ግብፅ ላካቸው፡፡ ነገር ግን ክፉ እንዳያገኘው ብሎ የዮሴፍን ወንድም ብንያምን ከእነርሱ ጋር አላከውም ነበር፡፡ ዮሴፍም ዐሥሩ ወንድሞቹ ከሕዝቡ ጋር ገብተው ሲሰግዱለት አይቶ ዐወቃቸው፣ እነርሱ ግን የሰገዱለት የሀገሩ ገዥ ስለነበረ ነው እንጂ ወንድማቸው እንደሆነ ዐላወቁትም ነበር፡፡ ዮሴፍም በልጅነቱ ከእነርሱ ጋር ሳለ ያየውን ሕልም አሰበ፡፡ እነርሱም ስለራሳቸው በነገሩት ጊዜ ‹‹እቤት የቀረውን ወንድማችሁን አምጡ›› ብሎ ለርኃባቸው እህሉን ሰጥቶ አንዱን (ስምዖንን) ለይቶ አስቀርቶ ዘጠኙን ስንቃቸውን ጭኑ ወደ አባታቸው ቤት ወደ ከነዓን ላካቸው፡፡ ሄደውም የሆነውን ለያዕቆብ ነገሩት፡፡ እርሱም ከወንድማቸው ጋር ድጋሚ ወደ ግብፅ ላካቸውና ድጋሚ በዮሴፍ ፊት ሰግደው ሰላምታ አቅርበው እጅ መንሻን አመጡለት፡፡ ዮሴፍም የእናቱን ልጅ ብንያምን ባየው ጊዜ ወደ ውስጥ ገብቶ አለቀሰ፡፡ ዮሴፍ ቆይቶ ራሱን ገለጠላቸው፡፡ ያደረጉበትንም ነገራቸው፡፡ የርኃቡም ዘመን ገና 5 ዓመት ይቀረው ነበርና ዮሴፍ ወንድሞቹን ‹‹ስለሸጣችሁኝ አትዘኑ እነሆ ሕይወታችሁን ለማዳን እግዚአብሔር አስቀድሞ ከእናንተ በፊት ወደ ግብፅ ልኮኛል›› አላቸው፡፡ አባቱንም ወደ እርሱ እንዲያመጡት ላካቸው፡፡ ያዕቆብም ከነቤተሰቡ ንብረቱንም ሁሉ ሰብስቦ ወደ ግብፅ ወረደ፡፡ ልጁን ዮሴፍንም ባየው ጊዜ እያለቀሰ አቅፎ ከሳመው በኋላ ሞቱን ተመኘ፡፡ በግብፅ የያዕቆብ የልጅ ልጆቹ ቁጥር 66 ሆነ፡፡ ከዮሴፍም ልጆች ጋር አንድ ላይ 70 ሆኑ፡፡ ያዕቆብም ፈርዖንን ገብቶ ከባረከው በኋላ በግብፅ ጌሤም ምድር 17 ዓመት ተቀመጠ፡፡ ዘመኑም 140 በሆነ ጊዜ በሞት ማረፉን ዐውቆ ልጁን ዮሴፍን ጠርቶ በአባቶቹ መቃብር ቤት ውስዶ እንዲቀብረው ነገረው፡፡ የዮሴፍንም ሁለቱን ልጆች ምናሴንና ኤፍሬምን ባረካቸው፡፡ ‹‹አባቶቼ አብርሃምና ይስሐቅ በፊቱ የሄዱለት እርሱ እግዚአብሔር፣ ከታናሽነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን የመገበኝ እግዚአብሔር፣ ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ እርሱ እነዚህን ብላቴኖች ይባርክ፤ ስሜም የአባቶቼ የአብርሃምና የይስሐቅ ስም በእነርሱ ይጠራ፤ በምድርም መካከል ይብዙ›› ብሎ ባረካቸው፡፡ ያዕቆብም ልጆቹን ጠርቶ ወደፊት የሚሆነውን ሁሉ ይልቁንም የጌታችንን የመወለዱን ነገር በምሳሌ እያደረገ ነገራቸው፡፡ እያንዳንዳቸውንም እንደ በረከታቸው ባረካቸውና በአብርሃምና በይስሐቅ ሣራም በተቀበረችበት መቃብር ወስደው እንዲቀብሩት ከነገራቸው በኋላ በ137 ዕድሜው እግሮቹን በአልጋው ላይ ሰብስቦ በሰላም ዐረፈ፡፡ የግብፅ ሰዎችም 70 ቀን አለቀሱለት፡፡ ዮሴፍም አባቱን ባዘዘው ቦታ በእነ አብርሃም መቃብር ከቀበረው በኋላ ወደ ግብፅ ተመለሰ፡፡ የዮሴፍም ወንድሞች አባታቸው እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ ‹‹ምናልባት ዮሴፍ ይጠላን ይሆናል፣ ባደረግንበትም ክፋት ሁሉ ብድራት ይመልስብን ይሆናል›› ብለው ፈርተው ወደ ዮሴፍ መልዕክት ልከው ‹‹አባትህ ገና ሳይሞት ‹ዮሴፍን እባክህ የወንድሞችህን በደል ኃጢአታቸውንም ይቅር በል፣ እነርሱ በአንተ ከፍተውብሃልና፤ አሁንም እባክህ የአባትህ አምላክ ባሪያዎች የበደሉህን ይቅር በል› ብሎሃል›› ብለው ላኩለት፡፡ ወንድሞቹም መጥው በፊቱም ሰግደው ‹‹እነሆ እኛ ለአንተ ባሪያዎችህ ነን፣ በአባቶችህ አምላክ ባሮችህን ኃጢአታችንን ይቅር በለን›› አሉት፡፡ ዮሴፍም እንዲህ ሲሉት አለቀሰ፡፡ እርሱም ‹‹ሁሉም ነገር በእግዚአብሔር ፈቃድ የተደረገ ስለሆነ
620Loading...
12
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን። ሰኔ 1 ከዕረፍቱ በኋላ ተገልጦ ብዙ ተአምራትን ያደረገው የታላቁ ሰማዕት የቅዱስ ለውንትዮስ ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበት ዕለት (ቅዳሴ ቤቱ) ነው፡፡ ➛ እስራኤል የተባለ የያዕቆብ ልጅ ጻድቁ ዮሴፍና ሚስቱ አሰኔት ዕረፍታቸው ነው፡፡ ➛ የመስተጋድል ሰማዕት የቅዱስ ቢፋሞን የዕረፍቱ መታሰቢያና በስሙ ከታነጹ አብያተ ክርስቲያናያት የመጀመሪያዋ ቅዳሴ ቤት በዚህች ዕለት ተከናወነ፡፡ ➛ የሰማዕቱ ቆዝሞስና ከላይኛው ግብጽ ከጣሀ አውራጃ የጓደኛሞቹ ሰማዕታት የዕረፍታቸው መታሰቢያ መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሳል፡፡ 🔥 ሰማዕቱ ቅዱስ ለውንትዮስ ሀገሩ ሶርያ ጠራብሎስ ሲሆን ሃይማኖቱ የቀና ደግ ክርስቲያን ነው፡፡ በሥጋዊ ሥራውም የከጋዲው ንጉሥ ሠራዊቶች ጋር ነበር፡፡ ቅዱሳት መጸሕፍትን እያነበበ ሁልጊዜ በጾም በጸሎት ይተጋ ነበር፡፡ ባልንጀሮቹ የሆኑ ወታደሮቹንም ጣዖታን ማምለካቸውን ትተው እውነተኛውን አምላክ እንዲያምኑ ያስተምራቸዋል፡፡ ወደ ቀናች ሃይማኖትም የመለሳቸውና በጌታችን ያመኑ ብዙ አሉ፡፡ ከዚህም በኋላ ክፉዎች ወደ ገዥው መኮንን ሄደው ‹‹ለውንትዮስ አማልክትህን አቃለላቸው፤ ‹ሰማይና ምድርን በውስጣቸውም ያለውን ሁሉ የፈጠረ ክርስቶስ ነው› እያለ ያስተምራል›› ብለው ከሰሱት፡፡ መኮንኑም በሰማ ጊዜ ወደ እርሱ አስቀርቦ ጠየቀው፡፡ ቅዱስ ለውንትዮስም ከልጅነቱ ጀምሮ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደሚያመልከውና ለእርሱም እንደሚሰግድ በከሃዲው መኮንን ፊት መሰከረ፡፡ መኮንኑም አስሮ ካሠቃየው በኋላ በማግሥቱ ‹‹የንጉሡን ትእዛዝ ለምን ትተላለፋለህ? አማልክቶቹን ለምን አታመልክም?›› አለው፡፡ ቅዱስ ለውንትዮስም መኮንኑን ‹‹አንተም የረከሱ ጣዖታትን ማምለክህን ትተህ የክብርን ባለቤት ጌታችንን ብታመልከው የዘለዓለም መንግሥትን ባወረስህ ነበር›› አለው፡፡ መኮንኑም ይህንን በሰማ ጊዜ ቅዱስ ለውንትዮስን ደሙ እንደ ውኃ እስኪፈስ ሥጋውም እስኪቆራረጥ ድረስ ጽኑ ግርፋትን አስገረፈው፡፡ እግሩን እየጎተቱና ውኃ ውስጥም እየዘፈቁት ብዙ ካሠቃዩት በኋላ ሰማዕትነቱን ሐምሌ 22 ቀን በድል ፈጸመና ጌታችን ቅድስት ነፍሱን ተቀበላት፡፡ ከታላላቅ መኳንንት ውስጥ የአንዱ ሚስት የሆነች አንድ አማኝ ደግ ክርስቲያን ሴትም መጥታ ለወታደሮቹ ገንዘብ ከፍላ የቅዱስ ለውንትዮስን ሥጋ ወስዳ በወርቅ ሣጥን ውስጥ አድጋ በቤቷ ውስጥ በክብር አስቀመጠችው፡፡ ሥዕሉንም አሠርታ በወርቅ ሣጥኑ ላይ አስቀምጣ ሁልጊዜ በፊቱም የሚበራ መብራት አኖረች፡፡ ሰማዕቱም የፍቅሯንና የድካምዋን ዋጋ ቆጥሮ ብዙ አስደናቂ ተአምራትን አድጎላታል፡፡ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ በመኮንኑ ባሏ ላይ በሆነ ሥራ ምክንያት ተቆጣና በአንጾኪያ ከተማ በወህኒ ቤት አሠረው፡፡ ቅዱስ ለውንትዮስም ለሥጋው መልካም ለሠራችለት ለመስፍኑ ሚስት መልካም የሆነ ዋጋዋን ሊከፍላት ሽቶ በዚያች ሌሊት በወህኒ ቤት ላለው ባሏ ተገለጠለት፡፡ ከወህኒ ቤቱም ታላቅ ብርሃን ወጣ፡፡ ለመኮንኑ ባሏም የተገለጠለት የራሱ የሆነውን ቤቱ ያስቀመጠውንና የሚያውቀውን የወርቅ ልብስ ለብሶ በጎልማሳ ፈረሰኛ አምሳል ነበር፡፡ ለመስፍኑም እንዲህ አለው፡- ‹‹አትዘን አታልቅስም፣ ዛሬ ከዚህ ወህኒ ቤት ወጥተህ ከንጉሥ ጋር በማዕዱ ትቀመጣለህና ከዚያም ወደቤትህ ወጥተህ በሰላም ትሄዳለህ፡፡›› የታሠረው መስፍንም ይህን ጎልማሳ ፈረሰኛ ስላየው፣ በላዩም ስለወጣው ታላቅ ብርሃን፣ የወህኒ ቤቱም ደጅ እንደተዘጋና እንደተቆለፈ ወደ እርሱ ስለመግባቱ፣ ደግሞም የራሱ የሆነውንና በቤቱ ውስጥ የተወውን የወርቅ ልብስ ለብሶ ስለማየቱ በእጅጉ ተደነቀ፡፡ ቅዱስ ለውንትዮስም በዚያች ሰዓት ወደ ንጉሡ ሄዶ በመኝታው ተኝቶ ሳለ ረገጠው፡፡ ንጉሡም እጅግ ደነገጠ፡፡ ቅዱስ ለውንትዮስም ‹‹ንጋት በሆነ ጊዜ መስፍን እገሌን ከወህኒ ቤት አውጣው አክብረውም፣ በክፉ አሟሟትም ሞተህ እንዳትጠፋ ወደቤቱ ይሄድ ዘንድ በሰላም አሰናብተው›› አለው፡፡ ንጉሡም ከቅዱስ ለውንትዮስ ግርማ የተነሣ እጅግ ፈርቶ እየተንቀጠቀጠ ‹‹እሺ ጌታዬ እንዳዘዝከኝ አደርጋለሁ›› ብሎ መለሰለት፡፡ በነጋም ጊዜ ንጉሡ ወደ ወህኒ ቤት ሄዶ መስፍኑን አወጣውና በክብር ልብሶች አስውቦ ከእርሱ ጋር በማዕዱ አስቀመጠው፡፡ ንጉሡም ግርማው እጅግ የሚያስፈራ ፈረሰኛ ተልጦለት መስፍኑን ይፈታው ዘንድ እንዳዘዘው ሲነግረው መስፍኑ ተደነቀ፡፡ ንጉሡም የሥራይ ሥራ እንደሆነ ሲናገር መስፍኑም ‹‹እኔ የሥራይ ሥራ ፈጽሞ አላውቅም፣ የተገለጠልህም ማን እንደሆነ አላውቅም›› አለው፡፡ ከግርማው የተነሣ ፈርቷልና ከማዕዱ በኋላ ንጉሡ በሰላም አሰናበተውና መስፍኑ ወደ ሀገሩ ጠራብሎስ ሲጓዝ ቅዱስ ለውንትዮስ በመልአክ አምሳል ተገለጠለትና እቤቱ እስኪደርስ ድረስ እንደ ጓደኛ እያወራው ሲደርስ ተሰወረው፡፡ መስፍኑም ወደቤቱ በገባ ጊዜ የሆነውን ሁሉ ለቤተሰቦቹ ነገራቸው፡፡ ሚስቱም ያዳነው ቅዱስ ለውንትዮስ መሆኑን ዐውቃ ‹‹ብታየው ታውቀዋልህን?›› አለችው፡፡ እርሱም ‹‹አዎን ባየው ዐውቃዋለሁ›› ሲላት የቅዱስ ለውንትዮስ ሥዕል ወዳለበት ቤት ይዛው ገባች፡፡ መስፍኑም አይቶ ‹‹በእውነት የተገለጠልኝ ይህ ነው›› አለ፡፡ ሁለተኛም የቅዱስ ለውንትዮስ ሥጋ ያለበትን የወርቅ ሣጥን ከፈተችውና ያንጊዜም የመስፍኑን የወርቅ ልብስ እንደለበሰ አየው፡፡ የፊቱንም መሸፈኛ ገልጦ የተገለጠለትና ያዳነው እርሱ መሆኑን ከተረዳ በኋላ ማን እንደሆነ ሚስቱን ጠየቃት፡፡ እርሷም የቅዱስ ለውንትዮስን ገድል አንድ በአንድ ነገረችው፡፡ መስፍኑም ይህን መልካም ሥራ በመሥራቷ ሚስቱን እጅግ አድርጎ አመሰገናት፡፡ በቅዱሳኑ ላይ አድሮ ድንቅ ድንቅ ነገርን የሚሠራ እግዚአብሔርን ካመሰገነ በኋላ መብራትና ማዕጠንት እንዳይለየው ሚስቱን አዘዛት፡፡ ከሃዲውን ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስን ጌታችን እስካጠፋው ድረስ እንዲሁ እያደረጉ ቆዩ፡፡ ከዚህም በኋላ ያማረች መልካም ቤተ ክርስቲያን አንጸውለት ቅዱስ ሥጋውን በዛሬዋ ዕለት ሰኔ አንድ ቀን በውስጧ አኖሩት፡፡ ዕለቷንም እጅግ አከበሯት፡፡ ከቅዱስ ለውንትዮስም ሥጋ ብዙ አስደናቂ የሆኑ እጅግ የበዙ ተአምራት ተደርገው ታዩ፡፡ የዚኽ ታላቅ ሰማዕት የቅዱስ ለውንትዮስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን፡፡ 🔥 ሰማዕቱ ቅዱስ ቢፋሞን ይኸውም ቅዱስ ገና ሲወለድ 500 ዓመት የሆነውን ሙት አስነሥቷል፡፡ በተወለደ በ3ኛ ቀኑም ‹‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ›› ብሎ አምላኩን አመስግኗል፡፡ አባቱ ከከበሩ ወገኖች የሆነ ስመ አንስጣስዮስ እናቱ ሶስና ይባላሉ፡፡ እነርሱም መመጽወትን የሚወዱ ደገኛ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ በእመቤታችንና በቅዱሳን የበዓላት ቀን ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች ምጽዋትን በመስጠት ያከብራሉ፡፡ የሚኖሩትም በምስር አገር አውሲም በሚባል ቦታ ነው፡፡ እግዚአብሔርም ደግነታቸውን ተመልክቶ መልኩ እጅግ ያማረ ልጅ ቅዱስ ቢፋሞንን ሰጣቸው፡፡ እነርሱም ገና ሲወልድ ጀምሮ ብዙ ተአምራት አድጎላቸዋልና እጅግ አላቸው፡፡ በሃይማኖት በምግባር ኮትኩተው አሳደጉት፡፡ ዘጠኝ ዓመትም በሆነው ጊዜ ሃይማኖትንና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እንዲማር ለአንድ መምህር ሰጡት፡፡ ከመምህሩም ዘንድ ጥበብንና ተግሣጽን የቤተ ክርስቲያንንም መጻሕፍት ሁሉ አጠና፡፡ ከልጅነቱም ጀምሮ በጾም በጸሎት በስግደት ይጋደል ነበር፡፡ እግዚአብሔር ለቅዱስ ቢፋሞን ገና በልጅነቱ በእጆቹ ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን የማድረግ ጸጋ ሰጠው፡፡ በቁስል ደዌ እጆቹንና እግሮቹን የታመመ አንድ ድኃ ቅዱስ ቢፋሞንን ምጽዋት ቢለምነውና ቅዱሱም በእጆቹ ቢነካው ወዲያው ከደዌው ድኖ ጤነኛ
440Loading...
13
Media files
610Loading...
14
በ11ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ቅዱስ ላሊበላ በጌታችን በአምላካችን በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ መሰረት ወደዚሁ ታላቅ ስፍራ በመምጣት የጻድቋ ማረፈያ/መታሰቢያ ዋሻ ቤተ መቅደስ በመፈልፈል የሰራላት ሲሆን በመቀጠል አፄ ይስሐቅ በ14ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ይህን ገዳም በስሟ በመገደም በዚሁ ዋሻ ውስጥም የጻድቋ የቅድስት ዜና ማርያም መቃብሯ እንዲሁም የመታሰቢያዋ ፅላት የሚገኝ ከመሆኑ አንጻር በአካባቢው ያሉት ሕዝበ ክርስትያን ከካህናት ጋር በመሆን ሥርዓተ አምልኮ በመፈፀም እየተገለገሉበት ይገኛሉ፡፡ ይህ ዋሻም አስቀድሞ ሦስቱ ቅዱሳን ማለትም አቡነ እንድርያስ ዘጣራ ገዳም ፣አቡነ ተክለኃይማኖት ዘደብረ ሊባኖስ፣ ጻድቋ ቅድስት ዜናማርያም ዘደሪጣ ውስጥ ለውስጥ በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት በፀጋ እግዚአብሔር ይገናኙበት የነበረ ሲሆን በአሁን ሰዓትም እግዚአብሔር የመረጣቸው ቅዱሳን ይመላለሱበታል፡፡ ለጻድቋ ቅድስት ዜና ማርያም የተሰጠ ቃል ኪዳን እግዚአብሔር አምላክ መርጦና ፈቅዶ በጻድቋ አማላጅነት ካለበት ስፍራ ተነስቶ የጻድቋ ደጃን የረገጠ ለ3 ግመል ጭነት ጤፍ ወይም የሦስት አህያ ጤፍ ያህል ነፍሳትን እምርልሻለሁ፤ ከሲዖልም እሳት ነፍሳትን አወጣልሻለሁ የሚል ቃል ኪዳን ለጻድቋ ቅድስት ዜና ማርያም ተሰቶታል። ከእናታችን ቅድስት ዜና ማርያም ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎቷም ይማረን። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። የግንቦት ወር ስንክሳርም በዚኹ ተፈጸመ፡፡ ወርሃ ሰኔንም በሰላም አስጀምሮ ያስፈጽመን ዘንድ አምላከ ቅዱሳን ይርዳን፡፡ ምንጭ፦ የግንቦት ❸⓪ ስንክሳር፤ የቅዱሳን ታሪክ-169 ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ሁሉ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም በሁላችንም ይደርብን አሜን። 🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃 🍃🍃🍃🍃 ይደርብን ለዘላለሙ አሜን። ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ እም እለ አብዑ ብዑላን ዘተርፈ። ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን ሰማዕታት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን ደናግል ዓዲ ወመነኮሳት ኄራን ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን እስከ አረጋዊ ልሒቅ እምንዑስ ሕፃን። ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ ወለዘሰምዐ ቃሎ በእዝነ መንፈስ በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኲሉ እምባእስ ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ ወይፈኑ ለነ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እምይዜ ወእስከ ለዓለም አሜን። ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀይቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል። እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ። ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውንና ያጻፈውንም የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን። አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር . ⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼ ግንቦት2️⃣9️⃣ ቀን 2011 ዓ.ም
620Loading...
15
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን። ግንቦት 30 በዚህች ቀን የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት አባ ሚካኤል አረፈ። ➛ ከ72ቱ አርድእት አንዱ ሐዋርያ ቆሮስ አረፈ። ➛ የእናታችን ቅድስት ዜና ማርያም መታቢያ ነው። ➛ ተጋዳይ የሆነች ፍትወተ ሥጋን ድል ያደረገች በበጎ ሥራዋም እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘች ቅድስትአርዋ አረፈች። ➛ እናታችን ቅድስት ወለተ ማርያም መታሰቢያዋ ነው፡፡ 🔥 አባ ሚካኤል ሊቀ ዻዻሳት ግንቦት 30 በዚህች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት 38ኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት አባ ሚካኤል አረፈ። ይህም አባት የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍት ስለ ተማረ አዋቂ ነበር። በልቡም አጠናቸው በቃሉም አጠናቸው። ከዚህም በኋላ ንጽሕት ሰውነቱ ከአምላክ በተገኘ የምንኵስና መንገድ በመጋደል ክብር ይግባውና የክርስቶስ ጭፍራ ልትሆን ወደደች። ወደ አስቄጥስ ገዳም ሒዶ በውስጡ ብዙ ዓመታት ኖረ ቅስናም ተሾመ። ከዚህም በኋላ በግብጽ አገር ወደ አለ ወደ ሠንጋር ወጣ በዚያም በዋሻ ውስጥ ራሱን እሥረኛ አድርጎ አርባ ዓመት ኖረ ከዚያም የሚበዛ ኖረ በዚያም ዋሻ ውስጥ ታላቅ ተጋድሎ ተጋደለ። የትሩፋቱ የጽድቁና የዕውቀቱ ወሬ በተሰማ ጊዜ በእስክንድርያ አገር ሊቀ ጵጵስና ይሾሙት ዘንድ ኤጲስቆጶሳት ተስማው ወዲያውኑ ይዘው በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት። በተሾመም ጊዜ በጎ አካሔድን ሔደ የዚህን ዓለም ጥሪት ሁሉ ንቆ ተወ። ከሚገባው ከሚያመጡለት ገጸ በረከት አንድ ዲናር ወይም አላድ ጥሪት አድርጎ አላኖረም። ከእርሱ በየጥቂት እየተመገበ የቀረውን ለድኃና ለጦም አዳሪ ይሰጣል ለአብያተ ክርስቲያናትም ለንዋየ ቅድሳትና ለቅዱሳት መጻሕፍት መግዣ ያደርገዋል። ሕዝቡንም ያስተምራቸውና ይገሥጻቸው ይመክራቸውም ነበር። መልካም አገልገሎቱንም በፈጸመ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችን ከዚህ ዓለም ድካም ሊያሳርፈው የሕይወትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ሊሰጠው ወዶ የአንዲት ቀንና የአንዲት ሌሊት ሕመም በላዩ አመጣ። ከቶ አልተናገረም በሚሞትበትም ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችንን አመሰገነው ፊቱንም በመስቀል ምልክት አማተበ። ነፍሱንም ክብር ይግባውና በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ መላ ዕድሜውም 90 ዓመት ከስምንት ወር ነው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በጸሎቱ ይማረን። 🔥 ቅዱስ ቆሮስ ይኸውም ቅዱስ ሐዋርያ ጌታችን በሚያስተምርበት ወራት ሦስት ዓመት አገልግሎታል፡፡ ከጌታችንም ዕርገት በኋላ ሐዋርያትን አገለገላቸው፡፡ ከእነርሱም ጋራ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ተቀብሎ ለስብከተ ወንጌል ተሰማርቷል፡፡ ቅዱስ ቆሮስ ከሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ጋር በመሆን መልእክቶቹንም ወደ ብዙ አገሮች ተሸክሞ በመውሰድ ብዙ አገለገለው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ቆሮስ ከአይሁድና ከአሕዛብ ብዙዎችን አስተምሮ የክርስትና ጥምቀትን አጥምቋቸዋል፡፡ ከዚህም በኋላ ወደ ምሥራቅ አገሮች ሄዶ ወንጌልን ሰብኮ ብዙዎችን በጌታችን እንዲያምኑ አድርጓቸዋል፡፡ ክፉዎች አረማውያንም በየምኩራቦቻቸው ብዙ መከራ አድርሰውበታል፡፡ መልካም ተጋድሎውንና አገልግሎቱንም ፈጽሞ ብዙ መከራ ደርሶበት በዚህች ዕለት ዐረፈ፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን፡፡ 🔥 ቅድስት ወለተ ማርያም ዘጎንደር ዳግመኛም በዚኽች ዕለት የጎንደሯ ቅድስት ወለተ ማርያም ዕረፍቷ ነው፡፡ ይኽችውም ቅድስት ትውልዷ ጎንደር ሲሆን በዐፄ ወናአግ ሰገድ ዘመን የነበረች ከቤተ መንግሥት ወገን የሆነች ጻድቅ እናት ናት፡፡ ደብረ ሊባኖስ ሄዳ ከመነኮሰች በኋላ ወደ ጣና ገዳም ገብታ በጣና ባሕር ውስጥ ለ11 ዓመት ቆማ የጸለየች ድንቅ እናት ናት፡፡ ታሪኳ ተጽፎ ባለመገኘቱ ጽኑ የሆነው ገድሏ ብዙም አልታወቀም፡፡ ረድኤት በረከቷ ይደርብን በጸሎቷ ይማረን፡፡ 🔥 ቅድስት አርዋ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት ‹‹ተጋዳይ የሆነች ፍትወተ ሥጋን ድል ያደረገች፣ በበጎ ሥራዋም እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘች ቅድስት አርዋ›› ዕረፍቷ መሆኑን ስንክሳሩ በአጭሩ ይጠቅሳታል፡፡ ረድኤት በረከቷ ይደርብን በጸሎቷ ይማረን፡፡ 🔥 ጻድቋ ቅድስት ዜና ማርያም በዚህች ዕለት የእናታችን ቅድስት ዜና ማርያም መታቢያ ነው፡፡ ከአባቷ ከገብረ ክርስቶስ ከእናቷ አመተ ማርያም በ11መቶ ክፍለ ዘመን በቅዱስ ላሊበላ ዘመነ መንግሥት በምድ ነጋሲ በጎጃም ምድር ግንቦት 30ቀን የተወለደች ሲሆን ለአቅመ ሔዋን በደረሰች ጊዜ በንፅህ ድንግልና በምድረ ሂንፍራንስ ጣራ ገዳም አካባቢ በሚገኘው በአቡነ እንድርያስ ዋሻ ለ25 ዓመት በጾም በፀሎት ምንም ዓይነት የላመ የጣፈጠ እህል ሳትቀምስ በቅል ውስጥ የሚገኘውን መራራ ፍሬ ከኮሶ ጋር በአንድነት ደርጣ (አዋህዳ) በመዘፍዘፍ ከ3 ቀን በኃላ በመመገብ እስከ ሕይወቷ ፍጻሜ ድረስ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ አደባባይ ላይ የቀመሰውን መራራ ሐሞትን በማሰብ ሙሉ ሕይወቶን እየተመገበች ታላቅ ተጋድሎዋን ፈፅማለች፡፡ ከዚህ የተነሳ ሸክላ ማርያም ተብላ ትጠራ የነበረችው ቦታ ስያሜ ተቀይሮ ደሪጣ ዜና ማርያም ዋሻ ተብሎ እስከ አሁን ድረስ በስሞ እየተጠራ ይገኛል፡፡ ከአቡነ እድርያስ ዋሻ በመቀጠል ከአዲስ አበባ ተነስተን ስንጓዝ አዲስ ዘመን ከተማ በስተቀኝ በኩል ተገንጥለን 15 ኪሜ ያክል የጥርጊያ መንገድ እንደተጓዝን በስሞ የተሰየመውን ደሪጣ ጻድቋ ቅድስት ዜና ማርያም ገዳም ላይ ቀሪ ሕይወቶን ምንም አይነት ዋሻ ባልነበረበት በከፍተኛ ተራራ ላይ እጅግ አስቸጋሪ ቀዝቃዛ አየር ባለበት ብርዱን፣ ፀሐዩን፣ ቁሩን፣ ረኃቡንና ጥሙን በመቋቋም ራቁቶን በመሆን መራራ ምግቦችን አዋህዳ በመመገብ በጾም በፀሎት በመትጋት አስቸጋሪ የሆነውን ተጋድሎዋን በመፈፀም በዚሁ በተቀደሰ ስፍራ ነሐሴ 30 ቀን በታላቅ ክብር አርፋለች፡፡ በዚህም ወቅት ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከእልፍ አላፋት ቅዱሳ መላዕክት ጋር እንዲሁም ከሐዋርያት ፣ ከሰማዕታት ፣ ከጻድቃን ፣ ከደናግል ጋር በመሆን ከሰማይ በመውረድ በታላቅ ክብር ዕረፍቷን አክብሮላታል ታላቅ ኪዳንም ገብቶላታል፡፡ በዚሁ በተቀደሰ ስፍራ ላይ ወይንም በአሁኑ ሰዓት መቃብሯ በሚገኝበት ዋሻ ቤተመቅደስ አካባቢ በተጋድሎዋ ጊዜ ራቁቷን በሆነች ሰዓት መላ ገላዋን የሸፈነላት ፀጉር በእየ ዛፎቹ ላይ እስከ አሁን ድረስ አለ ፡፡ ይህም የጸጉር አምሳያ ከገዳሙ በመውሰድ ብዙ ሰዎች በቤታቸው በመታጠን ከአስም እንዲሁም ከተለያዩ በሽታዎች እየተፈወሱና እየዳኑ ሲሆን ታላላቅ ታምራትን እያደረገ ይገኛል፡፡ በዚህ ገዳም ከሌሎች ገዳማት ለየት የሚያደርገው ታሪክ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማይ በመውረድ ራሱ የባረከው ልዩ ታሪክ ያለው ጠበል የሚገኝ ሲሆን ይህም ጠበል በቦታው ላይ ሆኖ የተጠመቀ ፣ የጠጣ ፣ አልያም በአለበት ቦታ ሆኖ የተጠቀመ እስከ አሁን ድረስ መካን የሆኑ ሰዎች በፍጥነት ልጅ የሚያገኙ ከመሆናቸው ባሻገር ከማንኛውም ከተለያዩ በሽታዎች በመፈወስ ታላላቅ ታምራትን እየሰራ ይገኛል፡፡
590Loading...
16
Media files
620Loading...
17
ሄደ፡፡ አድዋ አውራጃ የሐ አቡነ አፍጼ ገዳምን ከተሳለመ በኋላ ገዳሙን ከከበቡት ተራሮች መካከል በአንደኛው ማይ ዱር ወደሚባለው ተራራ ወጥቶ አዲስ ገዳም መሠረተ፡፡ ታቦተ ማርያምን አስገብቶ ሲኖር ከየአቅጣጫው መናንያን መነኮሳት ወደ እርሱ መጡ፡፡ አቡነ መዝራዕተ ክርስቶስም እስከ 93 ዓመቱ ገዳሙን በአበምኔትነት እያስተዳደረ በታላቅ ተጋድሎ ከኖረ በኋላ ግንቦት 29 ቀን ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፈ፡፡ ‹‹ማይዱር›› በተባለው ገዳሙ ራሱ በሠራት በእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተቀበረ ሲሆን ገዳሙም እስከዛሬ ድረስ ‹‹እንዳ አቡነ መዝራዕተ ክርስቶስ ገዳም›› እየተባለ ይጠራል፡፡ 🔥 አቡነ አፍጼና አቡነ ጉባ ከተሰዓቱ ቅዱሳን ውስጥ አራቱ በምድር ላይ ሞትን ሳያዩ የተሰወሩ ናቸው፡፡ እነዚህም አቡነ አረጋዊ፣ አቡነ ገሪማ፣ አቡነ ሊቃኖስና አቡነ አፍጼ ሲሆኑ ሁሉም ስውራን ወደፊት በሐሣዌው መሢሕ ዘመን ወደ ምድር ወርደው ከእነ ሄኖክና ኤልያስ ጋር መጥተው ሰማዕት የሚሆኑ ናቸው፡፡ ተሰዓቱ ቅዱሳን ከአብርሃ ወአጽብሐ 6ኛ ንጉሥ በሚሆን በአልሜዳ ዘመነ መንግሥት ከአውሮፓና ከእስያ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው አክሱም ከተማ ካረፉ በኋላ ሀገረ ስብከታቸውን ተከፋፍለው ገዳም እየገደሙ፣ በዓት እያበጁ፣ ከሣቴ ብርሃን አባ ሰላማ የመሠረተውን የክርስትና ሃይማኖት በከፍተኛ ሁኔታ አስፋፍተዋል፡፡ ገዳማትን በከፍተኛ ሁኔታ አስፋፍተዋል፤ የምንኩስና ሕይወትን በሀገራችን በማስፋፋት ሕይወት ዘርተውበታል፤ መጻሕፍትን ወደ ግእዝ ቋንቋ ተርጉመዋል፤ የወንጌልን ብርሃን በሀገራችን ላይ አብርተዋል፤ ድውያንን እየፈወሱ ሙታንን እያስነሡ በተአምራታቸው ቁስለ ሥጋን ፤ በትምህርታቸው ቁስለ ነፍስን ፈውሰዋል፡፡ የሮም ነገሥታት ወገን የሆነው አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል) ከነገሥታት ወገን የምትሆን ሚስት አጋብተው ሊያነግሡት ሲያስቡ እርሱ ግን ዓለምን ፍጹም በመናቅ ወደ ታላቁ አባት አባ ጳኩሚስ ገዳም ገብቶ መነኮሰ፡፡ የንጉሡን ልጅ የአቡነ አረጋዊን በሕፃንነቱ ምንኩስና መቀበሉን የሰሙ 8 ደጋግ ሌሎች የነገሥታት ልጆችም ከያሉበት ተሰባስበው አባ ጳኩሚስ ገዳም ገብተው ከአባ ዘሚካኤል ጋር ተገናኙ፡፡ አባ ጳኩሚስን ‹‹እኛንም እንደዚህ ሕፃን አመንኩሰን›› አሉትና አመንኩሶ ባረካቸው፡፡ የሃይማኖትን ምሥጢር ሁሉ ከአባ ጳኩሚስ ጠንቅቀው እየተማሩ ለብዙ ዓመታት ከእርሱ ጋር ተቀመጡ፡፡ ▪️ እነዚህም ቅዱሳን ➛ የቁስጥንጥንያው አባ ሊቃኖስ ➛ የሀገረ ቁስያው (ኢጣሊያ) አባ ይምአታ ➛ የአንጾኪያው (ሶሪያ) አባ ጽሕማ ➛ የቂልቅያው (ግሪክ) አባ ጉባ ➛ የእስያው አባ አፍጼ ➛ የሮምያው አባ ጰንጠሌዎን ➛ የቂሣርያው አባ አሌፍ ሲሆኑ ሁሉም የነገሥታት ልጆች ናቸው፡፡ ከዚህም በኋላ እነዚህ ቅዱሳን ወደ ትውልድ ሀገራቸው ሮም ተመልሰው ሮምን ወደ ቀናች ሃይማኖት መለሷት፡፡ በዚያም ሳሉ በምድረ አዜብ ብሔረ ኢትዮጵያ ስለሚኖሩ ሰዎች ዝና ስለ ነገሥታቶቻቸውም ቅድስናና ሀገሪቱም የእመቤታችን ዓሥራት መሆኗን ከመጻሕፍት ተረዱ፡፡ አባ ዘሚካኤልም ከሁለቱ ደቀ መዛሙርቶቹ ጋር በሌሊት ወጥቶ ወደ ኢትዮጵያ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል እየመራው መጥቶ አክሱም ደረሰ፡፡ በዚያም ጥቂት ጊዜ በመቀመጥ ተመልሶ ወደ ሮምያ ሄዶ ስለ ኢትዮጵያ ያየውንና የሰማውን በሙሉ ሁሉ ለሌሎቹ ቅዱሳን ሲነግራቸው እነርሱም ‹‹ይህችን የተቀደሰች ምድርማ ሄደን ማየት አለብን›› ተባበብለው ያላቸውን ሁሉ ይዘው ታቦቶቻቸውን፣ ካህናቶቻቸውን፣ ንዋየ ቅድሳቶቻቸውን፣ መጻሕፍቶቻቸውን ሁሉ ይዘው በዘሚካኤል መሪነት በመምጣት በ460 ዓ.ም ጳጳሱና ንጉሡ ካሉበት አክሱም ከተማ ገቡ፡፡ እነዚህ ቅዱሳን የነገሥታት ወገን ስለሆኑ በሮም ነግሦ የሚገኘውን ወንድማቸውን ይስሐቅን ላኩበት፡፡ ንጉሡ ይስሐቅ ለአባ ዘሚካኤል የእኅት ልጅ ነው፡፡ እርሱም መልእክቱ እንደደረሰው 7 ዓመት በሮም ከነገሠ በኋላ መንግሥቱን ትቶ በሌሊት ተነሥቶ በመውጣት ወደ ሀገራችን በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል መሪነት መጣና ከወንድሞቹ ጋር ተቀላቀለ፡፡ እነርሱም አመነኮሱትና ስሙን ገሪማ አሉት፡፡ ተሰዓቱ ቅዱሳን በአንዲት የጸሎት ቤት በምንም ሳይለያዩ በአንድነት እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ፣ እንደ አንድ ልብ መካሪ ሆነው ለጸሎት ቆመው ውለው ያድሩ ነበር፡፡ የአባ ዘሚካኤልም እናት ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ መጥታ ከሴት መነኮሳት ጋር እነርሱ ባሉበት አካባቢ ትኖር ነበር፡፡ አባ ዘሚካኤልን የበላይ አድርገው ሾሙትና ስሙንም አረጋዊ አሉት፡፡ እነዚህ ቅዱሳን ድውያንን እየፈወሱና ሙታንን እያስነሱ እጅግ በጣም አስገራሚ የሆኑ ድንቅ ድንቅ ብዙ ተአምራትን ያደርጉ ነበር፡፡ ከሰንበት በቀር እህል የሚባል ነገር የማይቀምሱት እነዚህ ቅዱሳን ኢትዮጵያን በኪደተ እግራቸው ባርከዋታል፣ ጌጦቿ ሆነውላታል፣ በትምህርታቸው የእምነቷን መሠረት አጽንተውታል፣ የልዕልናዋንም ታሪክ ለዓለም መስክረውላታል፡፡ ቅዱሳኑ ለ12 ዓመታት በፍጹም አንድነት አብረው ከተቀመጡ በኋላ ‹‹እርስ በራሳችን እየተያየን ብንኖር ተድላ ደስታ ይሆንብናልና ተለያይተን እንቀመጥ›› ብለው ተማከረው በተለያየ በዓት በተጋድሎ መኖር ጀመሩ፡፡ አባ ሊቃኖስ በደብረ ቁናጽል፣ አባ ጰንጠሌዎንም በእርሱ ትይዩ በሆነ ቦታ፣ አባ ገሪማ በደብረ መደራ፣ አባ ጽሕማ በደብረ ጸድያ፣ አባ ይምአታ በደብረ ገረዓልታ፣ አባ አፍጼ በደብረ ይሐ፣ አባ አሌፍ በደብረ አኅድአ መኖር ጀመሩ፡፡ አባ አረጋዊ ደግሞ በጣም ርቀው በመሄድ በደብረ ዳሞ በዋሻና በፍርኩታ ውስጥ በተራራም ላይ መኖር ጀመሩ፡፡ ከእነዚህም ቅዱሳን ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለአንዳች ሐዋርያ ስብከት አስቀድማ በክርስቶስ እንዳመነችና በዚህም ምክንያት የልዕልናዋን ታሪክ ለዓለም ለማሳወቅ ፈጥነው የሄዱ አሉ፡፡ የኢትዮጵያ ምድር በእነዚህ የቅዱሳን ኪደተ እግር ተቀደሰች፣ በውስጧም በመመላለሳቸው አውራጃዎቿና አደባባዮቿ ሁሉ ታደሱ፡፡ መዓዛ ትምህርታቸውና ተአምራቶቻቸው በሁሉም አውራጃዎች ተሠራጨ፣ የእምነቷንም መሠረት አጸኑ፡፡ አቡነ አፍጼ የተወለዱት እስያ ውስጥ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን ወላጆቻቸው አቡሊዲስና አቅሌስያ ይባላሉ፡፡ ገና በሕጻንነታቸው ብሉይ ከሐዲስ ጠንቅቀው በመማር መንኩሰዋል፡፡ አባ አፍጼ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በአልዐሜዳ ዘመን ከ8ቱ ባልንጀሮቻቸው ጋር ነው፡፡ ጻድቁ ጸበል እያፈለቁ ብዙ ድውያንን ፈውሰዋል፡፡ ትግራይ ውስጥ የሓ የተባለው ቦታም ማረፊያቸው ነበር፡፡ ዛሬም ትልቁ ገዳማው በዚያው ይገኛል፡፡ ጻድቁ ከሠሯቸው በርካታ ሥራዎች ውስጥ ከብዙ በጥቂቱ፡- ከ100 ዓመት በላይ አበ ምኔት ሆነው በኖሩበት ገዳማቸው በፍጹም ትጋት በጾምና በጸሎት አገልግለዋል፡፡ ሁለተኛ በመጀመሪያ ያስከተሏቸውን 366 ደቀ መዛሙርት ጨምሮ ብዙ መናንያንን አፍርተው በሃገራችን ገዳማዊ ሕይወትን አስፋፍተዋል፡፡ ሦስተኛ ቅዱሳት መጻሕፍትን ከሱርስትና ከጽርዕ ቋንቋ ወደ ግእዝ ቋንቋ ተርጉመዋል፡፡ ሌላው ጻድቁ በስብከተ ወንጌል ለሀገራችን ብርሃን አብርተዋል፡፡ ሕዝቡ በጣዕመ ስብከታቸው ይገረም ስለ ነበር ‹‹አፍፄ-አፈ ዐፄ›› ብሏቸዋል፡፡ ይኽም የዐፄ/የንጉሥ አንደበት ያለው›› ወይም ‹‹ንግግር አዋቂ›› ማለት ነው፡፡ አቡነ አፍጼ ከ200 ዓመታት በላይ ቤተ ክርስቲያንን አገልግለው ግንቦት 29 ቀን በ684 ዓ.ም በሞት ፈንታ ተሰውረዋል፡፡ እግዚአብሔርም በስማቸው ለተማጸነ፣ ገዳማቸውን ለተሳለመ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል፡፡
510Loading...
18
➛ ሌላኛው በዚህች ዕለት ዕረፍታቸው የሆኑት አቡነ ጉባ ናቸው፡፡ እርሳቸውም የተወለዱት ታህሣሥ 29 ቀን 336 ዓ.ም በመንፈቀ ሌሊት ነው፡፡ አባታቸው ጌርሎስ እናታቸው ቴዎዶክስያ የተባሉ ደጋግ ቅዱሳን ናቸው፡፡ አቡነ ጉባ በተወለዱ ቀን ጌታችን ከመላእክቱ ጋር በመውረዱ ቤታቸው ለ7 ቀናት በብርሃን ተሞልቶ ነበር፡፡ ሕጻኑ ጉባም ፈጣሪያቸውን ሃሌ ሉያ ብለው አመስግነዋል፡፡ ጻድቁ በልጅነታቸው መጻሕፍትን አጥንተው ወደ ገዳመ አስቄጥስ ገብተው መንነዋል፡፡ ለበርካታ ዓመታት ከተጋደሉ በኋላ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ‹‹ወደ ቅድስት ሃገር ኢትዮጵያ ሂድ" ብሏቸው ከ8ቱ ቅዱሳን ጋር ወደ ሀገራችን መጥተዋል፡፡ አባ ጉባ በስብከተ ወንጌል፣ መጻሕፍትን በመተርጎም፣ ገዳማትን በማስፋፋትና አብያተ ክርስቲያናትን በማነጽ ብዙ ደክመዋል፡፡ በተለይም ራማ ኪዳነ ምሕረት እርሳቸው ከመሠረቷት ገዳማት ውስጥ በይበልጥ የምትታወቀው ናት፡፡ ጻድቁ ቅዳሴ ሲቀድሱ ከመሬት ከፍ ብለው ይታዩ ነበር፡፡ ብዙ ጸበሎችን አፍልቀው ድውያንን ፈውሰዋል፡፡ ሙታንንም አንሥተዋል፡፡ እመቤታችን ተገልጣላቸው የብርሃን መስቀል ሰጥታቸዋለች፡፡ ጻድቁ ከብዙ ተጋድሎ በኋላ በሰላም ዐርፈው ማይጨው በሚገኘው ትልቁ ገዳማቸው ተቀብረዋል፡፡ መቃብራቸው ካለበት ዓለት ሥር እጅግ ፈዋሽ ጠበል ፈልቋል፡፡ በተለይም ለዐይን እና ለአእምሮ ሕመም ፍቱን መድኃኒት ነው፡፡ የተሰዓቱ ቅዱሳን በተለይም በዛሬው ዕለት በዓመታዊ የዕረፍት በዓላቸው ታስበው የሚውሉት የአቡነ አፍጼና የአቡነ ጉባ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡ ምንጭ፦ የግንቦት 2️⃣9️⃣ ስንክሳር ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ሁሉ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም በሁላችንም ይደርብን አሜን። 🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃 🍃🍃🍃🍃 ይደርብን ለዘላለሙ አሜን። ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ እም እለ አብዑ ብዑላን ዘተርፈ። ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን ሰማዕታት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን ደናግል ዓዲ ወመነኮሳት ኄራን ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን እስከ አረጋዊ ልሒቅ እምንዑስ ሕፃን። ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ ወለዘሰምዐ ቃሎ በእዝነ መንፈስ በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኲሉ እምባእስ ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ ወይፈኑ ለነ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እምይዜ ወእስከ ለዓለም አሜን። ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀይቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል። እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ። ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውንና ያጻፈውንም የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን። አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር . ⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼ ግንቦት2️⃣8️⃣ ቀን 2011 ዓ.ም
660Loading...
19
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን። ግንቦት 29 ከተሰዓቱ ቅዱሳን አንዱ የሆኑት አቡነ አፍጼ በሞት ፈንታ እንደ ሄኖክና ኤልያስ የተሰወሩበት ዕለት ነው፡፡ ሌላኛው ከተሰዓቱ ቅዱሳን አንዱ የሆኑት አቡነ ጉባ ዕረፍታቸው ነው፡፡ ➛ አቡነ መዝራዕተ ክርስቶስ ዕረፍቱ ነው፡፡ ይኸውም ሃይማኖት ምግባር ትሩፋቱን ተመልክተው ዐፄ ፋሲል ልጃቸውን ድረውለት በቤተ መንግሥት በክብር በድሎት ሊያኖሩት ሲሉ እርሱ ግን ንጉሡን ጥሎ በመጥፋት መንኖ ገዳም በመግባት ብዙ የተጋደለ ታላቅ ጻድቅ ነው፡፡ ➛ የአንጾኪያው አቡነ ስምዖን ዘዓምድ ዕረፍቱ ነው፡፡ እርሱም ከብዙ ተጋድሎው የተነሣ ከድንጋይ ምሰሶ ላይ ወጥቶ በላዩም 7 ዓመት ቆሞ የጸለየ ታላቅ አባት ነው። አባቱ ዮሐንስ እናቱ ማርታ ይባላሉ፡፡ እናቱ ገና ሳትፀንስ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ተገልጦላት ልጅ እንደምትወልድና ከእርሱም የሚሆነውን ሁሉ ገለጠላት፡፡ ስምዖንም ተወልዶ 7 ዓመት በሆነው ጊዜ በአንጾኪያ ወዳለ አንድ ገዳም ገብቶ የምንኩስናን ቀንበር ተሸከመ፡፡ መላእክትም እየተገለጡለት መንፈሳዊ ምግብ እያመጡለት ያስተምሩት ነበር፡፡ ከብዙ ተጋድሎውም የተነሣ ከድንጋይ ምሰሶ ላይ ወጥቶ በላዩም 7 ዓመት ቆሞ ጸለየ፡፡ ወደ ሌላም ተራራ ሄዶ በሠራው የድንጋይ በዓት ውስጥ ገብቶ ከእርሱ ሳይወጣ 20 ዓመት ኖረ፡፡ ከዚህም በኋላ ሌላ አንድ ትልቅ ተራራ ራስ ላይ ወጥቶ በላዩ 45 ዓመት በታላቅ ተጋድሎ ኖረ፡፡ መላ ዘመኑም 88 ዓመት ሲሆን በአባቱ ቤትና በአንጾኪያ ገዳም 7 እና 9 ዓመት ከማሳላፉ በቀር ሌላውን 72ቱን ዘመኑን በምሰሶ፣ በድንጋይ ውስጥና በተራራ ላይ ቆሞ በመጸለይ ነው ያሳለፈው፡፡ አቡነ ስምዖን ዘዓምድ ያደረጋቸውንም ተአምራት ብዛታቸው ተጽፈው አያልቁም፡፡ ብዙ ድርሳናትንና ተግሣጻትንም ደርሷል፡፡ ተጋድሎውንም ፈጽሞ ግንቦት 29 ቀን በሰላም ዐርፏል፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡ 🔥 አቡነ መዝራዕተ ክርስቶስ አባቱ ለባሴ ክርስቶስ የዐፄ ፋሲል የቅርብ ወዳጅ የነበረ የጦር አዛዥ ደጃዝማች ሲሆን እናቱ ሚላንያ ትባላለች፡፡ ጻድቁ ታኅሣሥ 29 ቀን በጎንደር ተወለዱ፡፡ ወቅቱ ዐፄ ሱስንዮስ የረከሰች የሮም ካቶሊክ እምነትን ተቀብሎ የሀገራችንን ክርስቲያኖች በሰማዕትነት የሚገድልበት ዘመን ስለነበር እናቱ ይዛው ፎገራ ወረዳ ቆራጣ ወለተ ጴጥሮስ ገዳም ገባች፡፡ በዚያም ሕፃን ልጇን ክርትስትና የሚያነሳላት ካህን አጥታ ስታለቅስ ደገኛው አባት አባ ስነ ክርስቶስ በስውር መጥተው አጠመቁትና ስሙን መዝራዕተ ክርስቶስ አሉት፡፡ የመዝራዕተ ክርስቶስ እናት ብዙም ሳትቆይ ስለሞተች በዚያው የምትኖር መነኩሲት የሆነች አያቱ አሳደገችው፡፡ እንደ አገሩም ባሕል ፈረስ ግልቢያና ጦር ውርወራ እየተማረ ከፎገራ ልጆች ጋር አደገ፡፡ አያቱም ወላጅ እናቱ ትመስለው ነበር፡፡ አንድ ቀን አብሮት የሚጫወተው ልጅ ወላጆቹ ሲያወሩ የሰማውን ወስዶ ለመዝራዕተ ክርስቶስ እናቱ እንዳልሆነች ነገረው፡፡ እርሱም በሰማው ነገር ደንግጦ አያቱን ስለእውነቱ ጠየቆ ተረዳ፡፡ ከዚህም በኋላ ደጃዝማች አባቱ ወደ ዐፄ ፋሲል ቤተ መንግሥት ወሰደው፡፡ መዝራዕተ ክርስቶስ መልከ መልካም ስለነበር ንጉሡ ዐፄ ፋሲል በወጣቱ ደም ግባት ደስ ተሰኝቶ ድምጹን አሰምቶ ‹‹ለዚህ ልጅ ሴት ልጄን እድርለታለሁ›› ሲል ለመኳንንቱ ሁሉ ተናገረ፡፡ መዝራዕተ ክርስቶስ ግን በልቡ መንኩሶ ስለመኖር የወሰነው በቤተ መንግሥት ይህንን የሰማ ዕለት ነበር፡፡ ከዚኽም በኋላ መዝራዕተ ክርስቶስ ምን ማድረግ እንዳለበት ሲያስብ ቆይቶ ወደ አንዱ ገዳም ጠፍቶ በመሄድ በምንኩስና ለመኖር ወሰነ፡፡ አንድ ቀን አባቱን ተከትሎ ግምጃ ቤት ማርያም ወደምትባለው ቤተ ክርስቲያን ሄዶ ሳለ አጣኙን አባት ባሕታዊ አባ ቴዎድሮስን ‹‹አባቴ ከዛሬ ጀምሮ በምንኩስና ለመኖር ወስኛለሁና መርቀህ ላከኝ›› አለው፡፡ ባሕታዊውም ‹‹አንተ ገና ልጅ ነህ›› ቢለው የሚቀበለው አልሆንም፡፡ በመጨረሻም መርቆ አሰናበተው፡፡ ወዲያም ጻድቁ በሌሊት ከጎንደር ከተማ ጠፍቶ ወደ ሰሜን አርማጭሆ ቆላ ሄደ፡፡ በዚያም በያዕቆብ ግሙድ ስም በተገደመው ገዳም ገብቶ ከአባ ስነ ክርስቶስ ጋር ተገናኘ፡፡ ያመነኩሰውም ዘንድ ለመነው፡፡ አባ ስነ ክርስቶስ ማንነቱን ከጠየቀው በኋላ ‹‹አንተ ገና ልጅ ስለሆንክ የምንኩስናን ቀንበር መሸከም አይቻልህም›› በማለት ወደ አባቱ እንዲመለስ መከረው፡፡ በሌላም በኩል ከንጉሡና ከመሳፍንቱ ጋር ላለመጣላት ፈርቶ ነበር፡፡ መዝራዕተ ክርስቶስ ግን እያለቀሰ ‹‹የአንተ አምላክ ጽናት ይሆነኛልና አመንኩሰኝ›› በማለት ለመነው፡፡ እርሱም ተግባር ቤት በአርድዕትነት እያገለገለ እንዲቆይ የአመክሮ ጊዜ ሰጠው፡፡ መዝራዕተ ክርስቶስም አባቱ ጭፍሮቹን ልኮ እንደገና ወደ ዓለም እንዳይወስደው ፈርቶ ቶሎ እንዲያመነኩሱት ‹ታመምኩ›› ብሎ ተኛ፡፡ መነኮሳቱም ‹‹ሳይመነኩስ ቢሞት ኩነኔ ይሆንብናል›› ብለው አበምኔቱን ለምነው አመነኮሱት፡፡ ከመነኮሰ በኋላ በሳምንቱ አባቱ ልጁ ያለበትን ገዳም ዐውቆ ታናሽ ወንድሙን ከጭፍሮቹ ጋር በመላክ ለአባ ስነ ክርስቶስ ‹‹ልጄ መዝራዕተ ክርስቶስ አንተ ጋር እንዳለ ሰምቻለሁና ከመመንኮሱ በፊት በአስቸኳይ እንድትልክልኝ›› ብሎ መልእክት ላከበት፡፡ አባ ስነ ክርስቶስም ለመጡት ጭፍሮች መዝራዕተ ክርስቶስ እንደመነኮሰ ነገራቸው፡፡ ጭፍሮቹም ከአባ ጋር ብዙ ስለተጨቃጨቁ መዝራዕተ ክርስቶስ ከእነርሱ ጋር ለመሄድ ተስማማ፡፡ ከእነርሱም ጋር ሳለ ከጭፍሮቹ አንዱና መሪያቸው የሆነውን ሰውም ‹‹ተሳልሜ ልምጣ፣ ጋቢህን ስጠኝ›› ብሎ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ በምሥራቅ ባለው በር ወጥቶ ጠፍቶ አርማጭሆ ጫካ ውስጥ ገብቶ ጠፋ፡፡ አጎቱና ጭፍሮቹም ፈልገው ቢያጡት ተስፋ ቆርጠው ተመለሱ፡፡ ከዚህም በኋላ አቡነ መዝራዕተ ክርስቶስ ወደ አንገረብ ወንዝ ሄዶ በዚያ ከርኩሳን መናፍት ጋር እየተዋጋ በተጋድሎ በጾም ጸሎት ተወስኖ ኖረ፡፡ ተመልሶ ወደገዳም ቢመጣ አባቱና ዘመዶቹ እንደማያስቀምጡት ስላወቀ አባ ስነ ክርስቶስን አስፈቅዶ ወደላይ አርማጭሆ ደብረ ሙጅና አባ አብሳዲ ገባሬ ተአምር ገዳም ሄደ፡፡ በዚያም 7 ዓመት በተጋድሎ ከኖረ በኋላ ወደ ዋልድባ ገዳም ሄደ፡፡ በዚያም ሥዕለ ማርያምን በጎኑ ታቅፎ ሲያዝን ለብዙ መናንያን የተሰወረችው ደብረሲና የተባለች በዋልድባ የምትገኝ ቅድስት ቦታ ተገለጠችለት፡፡ በደብረ ሲና ተራራ ላይ ወጥቶ 40 ቀንና 40 ሌሊት ሱባኤ ያዘ፡፡ በዋልድባ 11 ዓመት እንደተቀመጠ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ‹‹በዚህ ገዳም የምትኖርበት ጊዜ አልቋልና ውጣ›› ብሎ አዘዘው፡፡ ከዚያም ከዋልድባ ወጥቶ ወደ ሰሜን ተራራ ሄዶ ከቅዱስ ያሬድ ገዳም ተባርኮ ወደ ትግራይ ገርዓልታ ሄደ፡፡ ቀጥሎም ወደ ጉንዳጉንዲ ማርያም ገዳም ገብቶ በተጋድሎ መኖር እንደጀመረ አንድ የበቃ ባሕታዊ መጥቶ ‹‹ክፍልህ በዚህ ገዳም አይደልምና ወደ ሌላ ገዳም ሂድ›› አለው፡፡ ወደ መጠራ መቃብረ ጻድቃን ዘንድ ሄዶ ዐጽመ ቅዱሳንን ሲያጥን ‹‹ይህ ገዳም ክፍልህ አይደለም›› የሚል ድምጽ ከሰማይ መጣለት፡፡ ተነሥቶም ወደ ደብረ ቢዘን ሲጓዝ ሌሎች መነኮሳትን አገኘና በመረብ ወንዝ ሸለቆ ውስጥ ብዙ መናንያን እንዳሉ ሲነግሩት በሌላ አቅጣጫ ወደ መረብ ወንዝ አቀና፡፡ በዚያም ሸንፋ በተባለ ቦታ ገዳም መሥርቶ ሲቀመጥ መንፈሰ እግዚአብሔር የጠራቸው 12 መነኮሳት መጥተው አርድእት ሆኑለት፡፡ እነርሱም በወባ በሽታ ታመው ስላረፉ አቡነ መዝራዕተ ክርስቶስ ‹‹ወንድሞቼን አጥቼ በዚህ መኖር ለእኔ አይገባኝም፣ ክፍሌ አይደለም›› ብሎ ወጥቶ ወደ ትግራይ
570Loading...
20
Media files
650Loading...
21
የሚተነትን) በዋነኛነት ይጠቀሳሉ፡፡ በተለይም አክሲማሮስ በተሰኘው ድርሰቱ ላይ ስነ ፍጥረትን እንዴት አድርጎ እጅግ ጥልቅ በሆነ መንገድ እንዳብራራው በቃላት ለመግለጽም አስቸጋሪ ነው፡፡ ሊቁ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በመልካም እረኝነትና በሚደነቅ ቅድስና ሲያገለግል ኖሮ በ406 ዓ.ም ዐርፏል፡፡ የዕረፍቱን ሁኔታ በተመለከተ ከዮሐንስ አፈወርቅ ጋር የተገናኘ ታሪክ አለው፡፡ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ዘመን የነበረችው ጨካኟና አረመኔዋ ንግሥት አውዶክሲያ የድሃ ንብረት እየቀማች ተወስድ ስለነበር ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ዘወትር ይመክራትና ይገሥጻት ነበር፡፡ አንድ ቀን አንዱ ድሃ ሄዶ ለዮሐንስ አፈወርቅ ነግሮት ሄዶ ‹‹የድሃውን ንብረት መልሺለት›› ቢላት እምቢ ስትለው ከቤተ ክርስቲያን እንዳትገባና ከክርስቲያኖችም ኅብረት እንዳትቀላቀል አወገዛት፡፡ እርሷም ‹‹ከግዝትህ ፍታኝ›› ብትለውም ‹‹የድሃውን ገንዘብ ካልመለሽ አልፈታሽም›› ስላላት ‹‹በከንቱ አወገዘኝ አባት ያስተምራል እንጂ እንዲህ አያደርግም›› እያለች ታስወራበት ጀመር፡፡ ለቅዱስ ኤጲፋንዮስም ‹‹ዮሐንስ ያለ አግባብ አውግዞኛልና መጥተህ አስፈታኝ አለዚያ ሃይማኖቴን እቀይራለሁ፣ ቤተ ክርስቲያንንም አቃጥላለሁ›› ብላ ላከችበት፡፡ ቅዱስ ኤጲፋንዮስም ሄዶ ዮሐንስ አፈወርቅን ‹‹ሰይጣን በልቧ አድሮባታል ያሰበችውንም ያስፈጽማታልና ለአገልግሎታችንም እንቅፋት እንዳትሆን ፍታት›› ቢለው ቅዱስ ዮሐንስም እምቢ አለው፡፡ እርሷም በየከተማው እየዞረች ‹‹ተመልከቱ ዮሐንስ ኤጲፋንዮስንም አወገዘው›› እያለች በውሸት ታስወራ ጀመር፡፡ ቅዱስ ኤጲፋንዮስም እንዲህ ማለቷን አልሰማም ነበርና ከዮሐንስ ጋር በኋላ ተሰነባብተው ሊለያዩ ሲሉ ቅዱስ ዮሐንስ ‹‹ለምን በነገሬ ገባህብኝ?›› አለው፡፡ ቅዱስ ኤጲፋንዮስም ‹‹አልገባሁም›› ቢለው በንግግር ሳይግባቡ ቀርተው ተጣሉ፡፡ በዚህም ጊዜ ሁለቱም የሚሞቱበት ጊዜና የሚሞቱበት በምን ዓይነት ሁኔታ እንደሆነ ተገልጦላቸው አንዳቸው ለአንዳቸው ትንቢት ተነጋግረዋል፡፡ ዮሐንስ ኤጲፋንዮስን ‹‹ሄደህ ከቤትህ አትገባም ከመንገድ ላይ አንበሳ ሰብሮ ይገድልሃል›› አለው፡፡ ኤጲፋንዮስም ዮሐንስን ‹‹የእኔን ትላለህ አንተም እንጂ ደግሞ ተግዘህ በከሃዲዮች ተወግዘህ በአንጾኪያ ደሴት ታስረህ ተሠቃይተህ ትሞታለህ›› አለው፡፡ በተነጋገሩትም ትንቢት መሠረት ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ወደ በዓቱ ሲሄድ አንበሳ ገደለውና የአንበሳ ሆድ መቃብሩ ሆነለት፡፡ ስንክሳሩ ግን በመርከብ ሲሄድ እንዳረፈ ይገልጻል፡፡ ዮሐንስም በግዞት ታስሮ ብዙ ከተሠቃየ በኋላ ግንቦት 12 ቀን ዐረፈ፡፡ ጨካኟና አረመኔዋ ንግሥት አውዶክሲያም ‹‹ዮሐንስ ኤጲፋንዮስን አውግዞት ወደ ሀገሩ አባሮት በመንገድ ላይ እንዲሞት አደረገው›› እያለች በሀሰት አስወርታ የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች የሆኑትን ሰዎች ሰብስባ ዮሐንስን እንዲያወግዙት ካደረገች በኋላ በግዞት ታስሮ እንዲኖርና ተሠቃይቶ እንዲሞት አድርጋዋለች፡፡ በዛሬዋ ዕለት ግንቦት 28 ቀን የቅዱስ ኤጲፋንዮስ ፍልሰተ ሥጋው ስለተከናወነ በዓመታዊ በዓሉ ታስቦ ይውላል፡፡ የአባ ኤጲፋንዮስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን ፤ የአምላካችን የቅዱስ አማኑኤል ቸርነቱ ለኹላችን ይደረግልን። ምንጭ፦ የግንቦት 2️⃣8️⃣ ስንክሳር ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ሁሉ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም በሁላችንም ይደርብን አሜን። 🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃 🍃🍃🍃🍃 ይደርብን ለዘላለሙ አሜን። ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ እም እለ አብዑ ብዑላን ዘተርፈ። ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን ሰማዕታት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን ደናግል ዓዲ ወመነኮሳት ኄራን ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን እስከ አረጋዊ ልሒቅ እምንዑስ ሕፃን። ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ ወለዘሰምዐ ቃሎ በእዝነ መንፈስ በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኲሉ እምባእስ ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ ወይፈኑ ለነ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እምይዜ ወእስከ ለዓለም አሜን። ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀይቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል። እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ። ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውንና ያጻፈውንም የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን። አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር . ⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼ ግንቦት2️⃣7️⃣ ቀን 2011 ዓ.ም
740Loading...
22
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን። ግንቦት 28 በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ ገብታ በዚያ ለ38 ዓመታት ቆማ የጸለየችው እናታችን ቅድስት አመተ ክርስቶስ ዕረፍቷ ነው፡፡ ➛ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት ከአባ ጳኩሚስ ገዳም አባ መርቆሬዎስ ዐረፈ፡፡ ➛ የቆጵሮሱ ቅዱስ አቡነ ኤጲፋንዮስ ፍልሰተ ሥጋው ነው፡፡ 🔥 ቅድስት አመተ ክርስቶስ ሀገሯ ልዩ ስሙ ተጉለት ሲሆን በተጋድሎዋ በእጅጉ ትታወቃለች፡፡ መጽሐፍ ተሐራሚት ገዳማዊት ይላታል፡፡ በበረሃ ውስጥ በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ 38 ዓመት ብቻዋን ማንም ሳያያት የኖረች ታላቅ እናት ናት፡፡ ይኽችም ቅድስት አንድ ቀን አባ ዳንኤል በሌሊት በበረሃ ውስጥ በጨረቃ ብርሃን ሲጓዙ በተራራ ላይ ተቀምጣ ጠጉሯ መላ ሰውነቷን የሸፈናት በዚያም በረሃ ስትኖር በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ 38 ዓመት ብቻዋን ማንም ሳያያት እንደኖረች ምሥጢሯን በዝርዝር ነግራቸዋለች፡፡ ይኸውም አቡነ ዳንኤል በመቃርስ ገዳም 40 ዓመት በአስቄጥስ ገዳም ሲኖሩ ከቅጠል በቀር ተመግበው የማያውቁ እጅግ ገድለኛ አባት ናቸው፡፡ አንድ ቀን አባ ዳንኤል በበረሃው ብቻቸውን በሌሊት ሲጓዙ በተራራው ላይ ለጸሎት እንደቆመች አዩአት፡፡ ወንድ መስላቸውም ‹‹ከዚህስ ታላቅ አባት በረከትን ተቀብዬ ልምጣ›› ብለው ወደ ተራራው ሲወጡ አምልጣቸው ወደተሰነጠቀው ዓለት ዘላ ገባች፡፡ አባ ዳንኤልም ‹‹የእግዚአብሔር ሰው ሆይ በረከትህን እንድቀበል እማልድሃለሁ›› እያሉ እጅግ አብዝተው ሲማጸኑ ‹‹አባቴ ይቅርታ አድርግልኝ እኔ አልወጣም›› የሚል መልስ ተሰጣቸው፡፡ ለምን እንደሆነ ሲጠይቁም ‹‹እኔ ሴት ነኝ እራቁቴንም ስለሆንኩ›› ነው አለቻቸው፡፡ አባ ዳንኤልም ዐጽፋቸውን ከጣሉላት በኋላ ወጣችና በጋራ ጸሎት አደረጉ፡፡ አባ ዳንኤልም ይህ የተሰነጠቀ ዓለት እንዴት እንዳገኘችውና በዚህም ውስጥ ምን ያህል ጊዜ እንደኖረች ጠየቋት፡፡ ቅድስት አመተ ክርስቶስም እንዲህ ብላ ታሪኳን ነገረቻቸው፡- ‹‹ድንግልናዬን ጠብቄ በቅድስና በኢየሩሳሌም እኖር ነበር፡፡ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መቃብርም ላይ ከጸለይኩ በኋላ ወደ በረሃ ሄድኩ፡፡ እስከ ኤርትራም ባሕር ድረስ ደረስኩ፡፡ ከዚያም ወደዚህ በረሃ መጥቼ ይህን የተሰነጠቀ ዓለት አገኘሁና ይህ እግዚአብሔር ያዘጋጀልኝ መኖሪያዬ እንደሆነ ዐውቄ በዚህ መኖር ጀመርኩ፡፡ እነሆ በዚህ በረሃ ውስጥ ስኖር 38 ዓመት ሆነኝ፣ ያለ አንተም ሰው አይቼ አላውቅም፡፡ ልብሴም ከላዬ ላይ አለቀ ነገር ግን ይህ ቦታ ልብስ መከለያ ሆነኝ…›› እያለች ታሪኳን ለአባ ዳንኤል በዝርዝር ነገረቻቸው፡፡ አባ ዳንኤልም ወደ ገዳማቸው ተመልሰው ለአበ ምኔቱና ለመነኮሳቱ ሁሉ ታሪኳን በመንገር ልብስ ይዘውላት ተመልሰው ቢመጡ አጧት፡፡ ከጥቂት ቀናትም በኋላ አረጋውያንን አገኟቸውና አንዲት ሴት ከበረሀው ዐርፋ እንዳገኙ ነገሯቸው፡፡ ጸጉሯም ሥጋዋን እንደሸፈነውና አንሥተው እንደቀበሯት ነገሯቸው፡፡ የዚህችም ታላቅ ጻድቅ እናት ዕረፍቷ ግንቦት 28 ነው፡፡ በሀገራችን በስሟ የተጠራ አንድ ገዳም አላት፡፡ ረድኤት በረከቷ ይደርብን በጸሎቷ ይማረን፡፡ 🔥 አባ መርቆሬዎስ ይኸውም ቅዱስ በታላቅ ተጋደሎ ሥጋቸው እንጨት እስኪመስል ድረስ ሥጋቸውን እጅግ ያሠቃዩ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ ርዕሰ መነኮሳት አባ እንጦንስ ስለ አባ መርቆሬዎስ እንዲህ ብለው መስክረውላቸዋል፡- ‹‹የወንድማችን የመርቆሬዎስ ዕረፍቱ ቀረበ እያሉ ወደእኔ መነኮሳት መጡ፣ እኔም በረከቱን ልቀበል ወደ እርሱ በሄድኩበት ጊዜ ነፍሱ ከሥጋው ሳትለይ በተመስጦ ላይ አገኘሁት፡፡ ከመነኮሳቱ ጋር በእርሱ ዘንድ ሦስት ሌሊቶችን ኖርን›› በማለት አባ እንጦንስ ታላቅ ምስክርነት የሰጡላቸው አባት ናቸው፡፡ አባ መርቆሬዎስም መልካም ተጋድሏቸውን ፈጽመው ግንቦት 28 ቀን በሰላም ዐረፈዋል፡፡ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን፡፡ 🔥 ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ‹‹ኤዺፋንያ›› ማለት የመለኮት መገለጥ ማለት ሲሆን ‹‹ኤጲፋንዮስ›› ማለት ደግሞ ምሥጢረ መለኮት የተገለጠለት ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ የተወለደው ክርስቶስን ከሚጠሉ አይሁዳውያን ቤተሰቦች ሲሆን ቤተሰቦቹ አንድ አህያ በቀር ምንም የሌላቸው ድኆች ነበሩ፡፡ በዚያ ላይ በልጅነቱ አባቱ በመሞቱ ከእናቱና ከአንዲት እህቱ ጋር በረኃብ ሊያልቁ ሆነ፡፡ ሕጻኑ ኤጲፋንዮስ በአህያው እንዳይሠራ አህያው ክፉ ነበርና በእናቱ ምክር ሊሸጠው ገበያ አወጣው፡፡ ሊሸጠውም ከአህያው ጋራ ሲጓዝ ፊላታዎስ ከሚባል ጻድቅ ክርስቲያን ጋር ተገናኘ፡፡ ፊላታዎስም ሊገዛው ፈልጎ ለግዢ ሲደራደሩ አህያው የኤጲፋንዮስን ኩላሊቱን ረግጦት ለሞት አደረሰው፡፡ በዚህ ጊዜ አብሮት ያለው ጻድቁ ክርስቲያን ፊላታዎስ ‹‹በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ›› ብሎ በትእምርተ መስቀል አማትቦ በቅፅበት ኤጲፋንዮስን አዳነው፡፡ አህያውንም ‹‹ስለ እኛ በተሰቀለው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ትሞት ዘንድ ይገባሃል›› ብሎ በቃሉ እንዲሞት ቢያዘው አህያው ወዲያው ሞተ፡፡ ኤጲፋንዮስም እነዚህን አስገራሚ ሁለት ተአምራት ካየ በኋላ ጻድቁን ክርስቲያን ‹‹በስሙ ተአምራት የምታደርግበት የተሰቀለው ኢየሱስ ክርስቶስ ማነው?›› አለው፡፡ ፊላታዎስም ክርስቶስን ሰበከለትና ኤጲፋንዮስ እያደነቀ ሄደ፡፡ ከወራት በኋላ ሀብታም አይሁዳዊ አጎቱ ኤጲፋንዮስን ወሰደውና ገንዘቡን ሁሉ አውርሶት ሞተ፡፡ ኤጲፋንዮስም ገና በ16 ዓመቱ ባለጠጋ ሆነ፡፡ የኦሪትን ሕግ ሁሉ እየተማረ ቢያድግም ያቺ ገበያ ላይ ያያት ተአምር ግን በልቡ ውስጥ ትመላለስ ነበር፡፡ በአንዲት ዕለትም ስሙ ሉክያኖስ ከሚባል ጻድቅ መነኩሴ ጋር ተገናኘ፡፡ አብረው ሲሔዱም አንድ ነዳይ አገኙና ምጽዋትን ጠየቃቸው፡፡ ጻድቁ ሉክያኖስም ገንዘብ ስለሌው የሚለብሰውን የጸጉር ዐፅፉን አውልቆ ለድኃው መጸወተው፡፡ በዚያን ጊዜ የብርሃን ልብስ ከሰማይ ሲወርድለት መላእክት ሲያለብሱት ኤጲፋንዮስ ተመለከተ፡፡ ይህንንም ድንቅ ነገር ከተመለከተ በኋላ ኤጲፋንዮስ ከመነኩሴው እግር ሥር ሰግዶ ክርስቲያን እንዲያደርገው ለመነው፡፡ መነኩሴውም ወስዶ ለኤጲስቆጶሱ ሰጠውና አስተምሮ አጠመቀው፡፡ መመንኮስም እንደሚፈልግ ቢነግረው ‹‹ሀብት ንብረት እያለህ መነኩሴ መሆን አይገባህም›› አሉት፡፡ ከዚህ በኋላ ኤጲፋንዮስ እኅቱን አምጥቶ አስጠመቃትና ገንዘቡን ሁሉ ሸጦ ለድኆችና ጦም አዳሪዎች መጸወተው፡፡ በተረፈው ደግሞ ቅዱሳት መጻሕፍትን ገዛ፡፡ ከዚህም በኋላ መነኮሰና ለእርሱም ለእኅቱም ለጥምቀት ምክንያት ወደሆነው ስሙ ሉክያኖስ ወደተባለው መነኮስ ገዳም ገባ፡፡ በዚህም ጊዜ ዕድሜው 16 ብቻ ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ሽማግሌውን አባ ኢላርዮስን አገኘውና ሕግጋትን ሁሉ አስተማረው፡፡ ከዚያም መናንያኑ እስኪያደንቁት ድረስ በፍጹም ትጋትና ቅድስና በተጋድሎ ኖረ፡፡ ብዙ አስገራሚ ተአምራትን አደረገ፡፡ ድውያንን ፈወሰ፣ በጸሎቱ ሙታንን አስነሣ፣ ከደረቅ መሬት ላይ ውኃን አፈለቀ፡፡ ያለጊዜውም ዝናም አዘነመ፡፡ ብዙ አይሁዶችንም ተከራክሮና በተአምሩ እያሳመነ አጠመቃቸው፡፡ ከዚህም በኋላ መምህሩ ኢላርዮስ በነገረው ትንቢት መሠረት በቆጵሮስ ደሴት ላይ ጳጳስ ሆኖ ተሾመ፡፡ ብሉይን ከሐዲስ የወሰነ እጅግ ምጡቅ ሊቅ ነውና ብዙ መጻሕፍትን ተረጎመ፡፡ በሺሕ የሚቆጠሩ እጅግ ጠቃሚ ድርሳናትን ደረሰ፡፡ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በአፍም በመጽሐፍም እየጠቀሰ መናፍቃንንና አይሁድን ምላሽ በማሳጣቱ ሊቃውንት ‹‹የቤተ ክርስቲያን ጠበቃ›› ይሉታል፡፡ ከደረሳቸው በርካታ መጻሕፍት መካከል ‹‹ሃይማኖተ አበው ዘኤጲፋንዮስ፣ መጽሐፈ ቅዳሴውና አክሲማሮስ (ስነ ፍጥረት በዝርዝር
720Loading...
23
Media files
730Loading...
24
. ♨️ ቶማስ ሐዋርያ ♨️ ግንቦት 26 ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ዕረፍቱ ነው፡፡ ቶማስ ማለት "ፀሐይ" ማለት ነው፡፡ ይኸውም ሐዋርያ በቀድሞ ስሙ ዲዲሞስ እየተባለ ይጠራል፡፡ ዲዲሞስ ማለት ጨለማ ማለት ነው፡፡ በኋላ ግን ስሙ ተውጦ ቶማስ - ፀሐይ ተባለ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ሲሆን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላ ያየው በ8ኛው ቀን እሑድ ነው፡፡ በመጀመሪያ ስለተጠራጠረ ጌታችን በጦር የተወጋ ጐኑን እንዲሳስ አድርጎ ነው ትንሣኤውን ያሳመነው፡፡ ቅዱስ ቶማስ ‹‹ትንሣኤ ሙታን የለም›› ከሚሉት ከሰዱቃውያን ወገን ነበር፡፡ የጌታችንን የተወጋ ጎኑን ከዳሰሰ በኋላ አለማመኑ ርቆለት ‹‹ጌታዬ አምላኬ›› ብሎ የክርስቶስን አምላክነት መስክሯል፡፡ ሐዋርያው ቶማስ የእመቤታችንን ዕርገቷን አስቀድሞ በብቸኝነት ያየው እርሱ ነው፡፡ በአፍሪካና አካባቢዋ እስከ ቻይና ድረስ ሄዶ ወንጌልን ሰብኳል፡፡ ሀገረ ስብከቱ ሕንድ ሲሆን ወደ ሀገሪቱ ገብቶ ወንጌልን ለመስበክ ምክንያት ቢያጣ በ30 ብር ተሽጦ ከመስፍነ ብሔሩ ከሉክዮስ ቤት እያገለገለ መኖር ጀመረ፡፡ መስፍኑም ‹‹ምን መሥራት ትችላለህ?›› ቢለው ቶማስም ‹‹ሕንፃ ማነጽ ሐውልት መቅረጽ እችላለሁ›› አለው፡፡ እንግዲያውስ ‹‹ሠርተህ ቆየኝ›› በማለት ብዙ ወርቅና ብር ሰጠው፡፡ ቶማስም ‹‹ሕንፃ ማነጽ ሐውልት መቅረጽ ከዚህ የበለጠ የለም›› ብሎ ወርቁንና ብሩን በሙሉ ለነዳያን መጸወተው፡፡ ከዚያም የሀገሩን ሕዝብ ወንጌልን አስተምሮ አሳምኗቸው አጥምቋቸዋል፡፡ የመስፍኑንም ሚስት ከነልጆቿና ከነአገልጋዮቿ አሳምኗት አጠመቃት፡፡ መስፍኑ ሉክዮስም ከሄደበት ሲመለስ ‹‹ያነጽከው ሕንፃ የቀረጽከው ሐውልት ወዴት ነው?›› ቢለው ‹‹በወርቅና በብርህ ያነጽኳቸው ሕንፃዎች እነኚህ ናቸው›› ብሎ ያመኑትን አገልጋዮች አሳየው፡፡ እርሱም ‹‹ይህ ክፉ ባሪያ ተጫወተብኝ›› ብሎ እጅና እግሩን አሥሮ ቆዳውን አስገፍፎ ስልቻ አስፍቶ በአሸዋ ሞልቶ አሸክሞት ገበያ ለገበያ ሲያዞረው ዋለ፡፡ ሚስቱም ይህን ክፉና እጅግ አሠቃቂ የባሏን ድርጊት አይታ በድንጋጤ ወድቃ ሞተች፡፡ መስፍኑ ሉክዮስም ‹‹ሚስቴ የሞተችው ባንተ ምክንያት አይደለምን ያዳንካት እንደሆነ እኔም በአምላክህ አምናለሁ›› ቢለው ጌታችን የቶማስን ቁስሉን እንደ ውኃ አቀዝቅዞለት ካለችበት ሄዶ ከአካሉ የተገፈፈውን ስልቻውን ቢያስነካት ከሞት ተነሥታለች፡፡ በዚህም ሉክዮስ አምኖ ተጠመቀ፡፡ ከዚህም በኋላ ቶማስ ስልቻውን ተሸክሞ ከቦታ ወደ ቦታ እየተዘዋወረ ሙት እያስነሣ ድውይ እየፈወሰ አሕዛብን አሳምኖ አጠመቀ፡፡ ቀንጦፍያ የምትባል አንዲት ሀገር ሲደርስ አንድ ሽማግሌ ሰባት ልጆቹን ገድለውበት ሲያዝን አግኝቶ ስልቻውን እያስነካ ሰባቱንም ልጆቹን ከሞት አስነሥቶለታል፡፡ ኢናስ በምትባልም አገር ያሉ የቃሉን ትምህርት የእጁን ተአምራት አይተው ከንጉሡ ሚስት ከንግሥቲቱ ጀምሮ ሁሉም አምነው ተጠምቀዋል፡፡ በዚህ የቀኑት ካህናተ ጣዖት ግን ጥቅም የሚቀርባቸው ቢሆን በተንኮል ከንጉሥና መኳንንቱ አጣልተው በ72 ዓ.ም ግንቦት 26 ቀን አንገቱን በሰይፍ አስቆርጠውታል፡፡ ዛሬም ሕንድ ውስጥ በመንበሩ ላይ የቅዱስ ቶማስ ቀኝ እጁ በሕይወት እንዳለች ሆና ትታያለች፡፡ መለኮትን (የጌታችንን የተወጋ ጎኑን) የዳሰሰች ቅድስት እጅ ናትና ዛሬም ድረስ ሕያው ናት፡፡ በሕንድ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ፓትርያርክ ሲሾሙም የቅዱስ ቶማስን ቀኝ እጅ በሚሾመው ፓትርያርክ ላይ ጭነው ነው፡፡ አንድ ወቅት አንድ ሰው ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ገብቶ የቅዱስ ቶማስ ቀኝ እጅ እጨብጣለሁ ብሎ እጁን ቢዘረጋ የቶማስ እጅ ተሰወረችባቸው፡፡ እንደገና ብዙ እግዚኦታና ኪሪያላይሶን ካደረሱ በኋላ የቅዱስ ቶማስ እጅ በቦታዋ ተመልሳላቸዋለች፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁንም እኛንም በቅዱስ ቶማስ ጸሎት ይማረን አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት 2️⃣6️⃣ ስንክሳር
970Loading...
25
Media files
740Loading...
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን። ሰኔ 4 የታዘዘ መልአክ መጥቶ ሰማዕት እንደሚሆን የነገረው በኋላም ሊገድለው ብሎ መርዝ ያጠጣውን ጠንቋይ ጨምሮ በተአምራቱ ብዙዎችን ያሳመናቸው ሰማዕቱ ቅዱስ ሳኑሲ ዕረፍቱ ነው፡፡ ➛ ሐራቅሊ ከምትባል አገር የተገኘው ሰማዕቱ አቡነ ዮሐንስ ዕረፍቱ ነው፡፡ ➛ ምስክርነቷን በብዙ ድካምና በአስጨናቂ መከራዎች የፈጸመች የከበረች ቅድስት ሶፍያ በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን በሰማዕትነት ዐረፈች፡፡ ➛ የአርቃድዎስና የእኅቱ የዲሙናስያ፣ የግብጻውያኑ የአሞንና የሚናስ፣ የዲዮቅልጥያኖስ ጭፍሮችም የሰማዕትነታቸው ፍጻሜ ሆነ፡፡ እነዚህንም ቅዱሳን ከአባ ቢሾይ ጋር በእሳት ምድጃ ውስጥ በጨመሯቸው ጊዜ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ከነበልባሉ መካከል አወጣቸው፡፡ እነርሱም ዳግመኛ ወደ ንጉሡ ቀርበው ‹‹አንተ ከሃዲ ሰማዕትነታችንን በቶሎ ፈጽምልን›› ብለው ረገሙት፡፡ ንጉሡም በቁጣ ራስ ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡና ሥጋቸውን በእሳት እንዲያቃጥሉ አዘዘ፡፡ በትእዛዙም መሠረት ቅዱሳኑ አንገታቸውን ተሰይፈው ሥጋቸውም በእሳት ተቃጥሎ ሰማዕትነታቸውን በድል ፈጽመው የክብር አክሊልን ተቀዳጁ፡፡ የሰማዕታቱ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡ 🔥 አቡነ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ እናቱ ኤልሳቤጥ ስትባል አባቱ ዘካርያስ ደግሞ የጳንጦስና የአብልያ አገሮች ገዥ ነበር፡፡ ልጃቸውን ዮሐንስ ብለው ጠሩትና ስሙ ከመጥምቀ አምላከ ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር አንድ ሆነ፡፡ ሐራቅሊ በምትባል ሀገር የሚኖሩት ወላጆቹ ደጋጎች ስለነበሩ ፈሪሃ እግዚአብሔርንና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እያስተማሩ በሃይማኖት በምግባር አሳደጉት፡፡ አባቱ ከሞተ በኋላ ቅዱስ ዮሐንስ የ20 ዓመት ወጣት ሲሆን መስፍን ሆነ፡፡ የጳንጦስና የጰራቅሊ ሌሎቹም አገሮች ሁሉ ተገዙለት፡፡ እንዲሁም ሆኖ ሲኖር ሰይጣን በመልአክ ተመስሎ ተገለጠለትና ‹‹አንተ ትነግሥ ዘንድ ወደ አንጾኪያ ሄደህ የንጉሥ ኑማርዮስን ልጅ አግባ›› ብሎ መከረው፡፡ ወደ አንጾኪያም ሄደና ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስን አገኘው፡፡ እርሱም ባገኘው ጊዜ አከበረው፣ እጅግ ወደደው፡፡ በማግሥቱም ምሳ ላይ ከእርሱ ጋር እያለ ዲዮቅልጥያኖስ አጵሎንን ያመጡት ዘንድ አዘዘ፡፡ ባመጡትም ጊዜ ዮሐንስ ንጉሡን አይቶ አቃለለው፡፡ ስለ ጣኦት አምልኮውም ስለገሠጸው ንጉሡ በጣም ተቆጥቶ አሰረው፡፡ በእሥር ቤት ሳለም ጌታችን በብርሃን ሰረገላ ሆኖ ታየው፡፡ በማግሥቱም ነጉሡ ከእሥር ቤት አስወጥቶ ከእርሱ ጋር ይስማማ ዘንድ ብዙ ሸነገለው፡፡ በሀሳቡም ፈጽሞ እንዳልተስማማ ሲያውቅ ግብር ያስገብርለት ዘንድ ከሹመት ጋር ወደ ግብፅ አገር ላከው፡፡ ለግብፁ ገዥም ‹‹እነሆ የሐረቅሊውን ዮሐንስን ግብር በማስገበር የአማልክትንም ቤት በአዲስ እንዲሠራ ከግብፅና ከኢየሩሳሌም እስከ ኢትዮጵያም ድረስ ሥልጣን ሰጥቼዋለሁ›› ብሎ ጻፈለት፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም የጣኦታት ቤቶቹን አፍርሶ ተዋቸው፡፡ የግብፁ ንጉሥም ክርስቲያኖችን እያሠቃየ ሲገድላቸው ዮሐንስ አየውና የሹመቱን ሥራ ትቶ እርሱም ከክርስቲያኖች ጋር መከራንና ሥቃይን ይቀበል ዘንድ ወደደ፡፡ በንጉሡም ፊት ቀርቦ አማኝ ክርስቲያንን መሆኑን ከተናገረ በኋላ ንጉሡ ይዞ እጅግ አሠቃየው፡፡ መኰንኑም ተቆጥቶ አሳስሮ ወደሌላ ሀገር በግዞት ላከው፡፡ በዚያም ያለው መኰንን ተቀብሎ አሠቃየው፡፡ በዕንጨት ላይ ሰቅለው ሥጋውን በመንኰራኩር ፈጩት፡፡ ደሙንም እንደ ውኃ አፈሰሱት፡፡ ከሰቀሉበት ዕንጨት ላይ አውርደው ከደበደቡት በኋላ እሥር ቤት አስገቡት፡፡ ከጥቂት ቀንም በኋላ በማረጃ ቢላዋ ቆዳውን ገፈው ቁስሉን በማቅ አሹት፡፡ ዳግመኛም አመድ ጎዝጉዘው በላዩ የእሳት ፍም አድርገው በዚያ ላይ አስተኝተው አሠቃዩት፡፡ በእሳት የጋሉ የብረት ችንካሮችንም አምጥተው በፊቱና በጆሮዎቹ ላይ ቸነከሯቸው፡፡ የታዘዘ መልአክም መጥቶ በሌሊት ፈወሰው፡፡ በማግሥቱም ግንባሩን ወደ ምድር ደፍተው እጆቹንና እግሮቹን ከፈረስ ጋር በገመድ አስረው መሬት ላይ እየጎተቱ አሠቃዩት፡፡ በመጨረሻም ባለ ሰይፍ መጥቶ እጆቹንና እግሮቹን አንገቱንም በየተራ ቆረጣቸውና ሰኔ 4 የሰማዕትነቱ ፍጻሜ ከሆነ በኋላ የክብር አክሊልን ተቀዳጀ፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡ 🔥 ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት ሶፍያ ("ያ" የሚለው ላልቶ ይነበብ) በቀደመው ዘመን በነበሩ ክርስቲያኖች ዘንድ ተወዳጅ ስም ነበር:: ዛሬ ብዙ አሕዛብ ሲጠሩበት ብንሰማም ትርጉሙ "ጥበበ ክርስቶስ" የሚል ነው:: በዚህም ስም ከሚጠሩ ከብዙ ቅዱሳን ዛሬ ታስባ የምትውል ቅድስት ሶፍያ አንዷ ናት። ቅድስት ሶፍያ በከሃዲው ዲዮቅልጥያኖ ዘመን የነበረች ታላቅ ሰማዕት ናት፡፡ ወላጆቿ ደጋግ ክርስቲያኖች ስለነበሩ እግዚአብሔርን መፍራትና ቅዱሳት መጻሕፍትን እያስተማሩ አሳደጓት፡፡ ባደገችም ጊዜ ለመስፍን ልጅ ሊያጋቧት ፈለጉ፡፡ እርሷ ግን ሳይነግሯት የወላጆቿን ሀሳብ ዐውቃ ወደ ፈጣሪዋ እንዲህ ብላ ጸለየች፡- ‹‹የክብር ባለቤት የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ወደ አንተ የምደርስባት የከበረችና የቀናች መንገድህን ለእኔ ለባሪያህ ለሶፍያ ምራኝ፤ ወደ ጥፋት በሚወስድ በጠማማ መንገድ እንድንከራተት አትተወኝ፤ የሚጠፋውን ዓለም ያስብ ዘንድ ልቤን አትተወው፤ የከበደ የዓለማዊ ፍላጎት ሸክምን ተሸካሚ አታድርገኝ፤ ቀላልና ልዝብ የሆነ ቀንበርህን ይሸከም ዘንድ ትከሻዬን ዘንበል አድርገው እንጂ…›› እያለች ከጸለየች በኋላ ወዲያው አንድ ሀሳብ መጣላት፡፡ ተነሥታ ጠፍታ ከሩቅ ሀገር በመሄድ በአንዱ በረሃ ውስጥ ገብታ እግዚአብሔርን ለማገልገል ወሰነች፡፡ ወዲያውም እንድታገለግላት ወላጆቿ የሰጧትን ገረዷን ጠርታ የሚትጠጣው ወይን እንድታመጣላት አዘዘቻት፡፡ ሶፍያም ጥቂት ከቀመሰች በኋላ ለገረዷ ሰጠቻትና በብዛት አጠጣቻት፡፡ ገረዷም ከስካር የተነሣ ልቧ በተሰለበ ጊዜ ቅድስት ሶፍያ የገረዷን ልብስ ለብሳ የእርሷን ልብስ ሰጠቻትና አስተኝታት በስውር ወጥታ ሄደች፡፡ ርቃ በሄደች ጊዜ በተራራዎችና በዋሻዎች ውስጥ ሊሰወሩ ፈልገው በሃይማኖት ምክንያት ከከሃዲው ዲዮቅልጥያኖስ ፊት የሸሹ ክርስቲያኖችን አገኘች፡፡ ከየት እንደመጡ ስትጠይቃቸው ሀገራቸውን ከነገሯት በኋላ ስለ ዲዮቅልጥያኖስና ስለ ክፉ ሥራው ክርስቲያኖችንም እያሠቃየ እንደሚገድል በደንብ ነገሯት፡፡ ቅድስት ሶፍያም ወደ ዲዮቅልጥያኖስ የሚወስደውን መንገድ ጠየቀቻቸውና በቀጥታ ወደ ከሃዲው ንጉሥ ገሰገሰች፡፡ በፊቱም ቆማ ስለ ክርስቶስ መሰከረች፡፡ እርሱም እጅግ ተቆጥቶ ለጣዖቱ ለአጵሎስ ስገጂ አላት፡፡ ቅድስት ሶፍያ ግን በድፍረት ‹‹የሰው እጅ ለሠራው ለረከሰውና የአጋንንት ማደሪያ ለሆነው ጣዖት አልሰግድም›› አለችው፡፡ ከዚህም በኋላ የተለያዩ እጅግ ብዙ ሥቃዮችን አደረሰባ፡፡ በብረት ጅራፍ ደሟ እስኪወርድ ድረስ አስገረፋት፡፡ ዳግመኛም በአንገቷ ከባድ ድንጋይ አስሮ ሥጋዋ ተቆራርጦ መሬት ላይ እስኪወድቅ ድረስ በከተማው አስጎተታትና መልሶ እሥር ቤት ጨመራት፡፡ በማግስቱም አስወጥቶ ‹‹በክፉ አሟሟት እንዳትሞቺ ለአጵሎን ስገጂ›› ሲላት እርሷ ግን ‹‹ክፉ ሞትስ ለአንተ ነው፤ የእኔስ ከአንተ የሚገኘው ሞት በፈጣሪዬ ዘንድ ሕይወት ነው›› አለችው፡፡ እርሱም ‹‹ከገደልኩሽ በኋላ ከሞት ትነሻለሽን›› አላት፡፡ ቅድስት ሶፍያም ‹‹አንተ ሰነፍ የእኔንስ ተወውና ለአንተም የደይን ትንሣኤ አለህ›› አለችው፡፡ ይህን ጊዜም አጥንቶቿ እስኪሰበሩ ድረስ አስደበደባት፡፡ በብረት አልጋ አስተኝተው ከበታቹ እሳት አነደዱባትና ሲመሽ መልሰው አሠሯት፡፡ በሌሊትም ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ገላዋን በመዳሰስ
Mostrar todo...
Mesele Nigatu