cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

⚖Ethiopian law by Daniel Fikadu Law office⚖

ዳንኤል ፍቃዱ ተስፋዬ በሁሉም የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጠበቃና የህግ አማካሪ ስልክ - 0913158507 ወይም 0978554559 Daniel Fikadu Tesfaye Certified Attorney of law at all Federal Courts of Ethiopia. Email- nurotekore@gmail. Com ⚖️⚖️Ethiopian Law by Daniel Fikadu channel ⚖️⚖️⚖️

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
8 465
Suscriptores
+1624 horas
+1577 días
+71630 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ከህግ ውጪ የተቋረጠ የስራ ውል ለሰራተኛው የሚያስገኛቸው ጥቅማጥቅሞች 1 የስራ ስንብት ክፍያ የስራ ውሉ አላግባብ የተቋረጠበት ሰራተኛ በአዋጅ 1156/11 አንቀፅ 39(1) እና 40(1) መሰረት እንደ ነገሩ ሁኔታ የአንድ አመት ደሞዙን የሚደርስ የስራ ስንብት ክፍያ ያገኛል፡፡ 2. የካሳ ክፍያ የስራ ውሉ አላግባብ የተቋረጠበት ከስራ ስንብት ክፍያ በተጨማሪ በአዋጅ 1156/11 አንቀፅ 43(4)(ለ) መሰረት የካሳ ክፍያ ያገኛል፡፡ሆኖም ካሳው የሰራተኛውን ማዕከላዊ የቀን ደሞዝ ደመወዙ በ180 ተባዝቶ ከሚያገኘው ውጤት መብለጥ የለበትም፡፡ 3. ያልተጠቀሙበት የአመት እረፍት ወደ ገንዘብ ተቀይሮ የሚከፈል ክፍያ የስራ ውሉ አለአግባብ የተቋረጠበት ሰራተኛ ከስራ ስንብት ክፍያ እና ከካሳ ክፍያ በተጨማሪ ያልተጠቀመበት የአመት እረፍት ወደ ገንዘብ ተቀይሮ በአዋጅ 1156/11 አንቀፅ 77(4) መሰረት ይከፈለዋል፡፡ 4. ክፍያ ለዘገየበት ክፍያ ሰራተኛው የሚለግበትን የአሰሪ ንብረት መልሶ ክሊራንስ ከጨረሰ በኋላ ሊከፈሉት የሚገቡ ክፍያዎች በ7 ቀን ውስጥ ካልተከፈሉት በአዋጁ አንቀፅ 38 መሰረት እስከ 3 ወር ደመወዝ ሊከፈለው ይችላል፡፡ 5.ያልተከፈለው የወር ደመወዝ ካለ ይከፈለዋል፡፡ 6. ለተጨማሪ ስራ ክፍያ ከመደበኛ የስራ ሰአት ውጪ በበአል ቀናት የተሰራ ስራ፤በእረፍት ቀናት የተሰራ ስራ ካለ ለእነኝህ ስራዎች በአዋጅ አንቀፅ 66 እና 68 መሰረት ሰራተኛው ክፍያ ያገኛል፡፡ 7. የስራ የምስክር ወረቀት በአዋጁ አንቀፅ 12(8) መሰረት ሰራተኛው የስራ ልምድ ማስረጃ ያገኛል አንድ የግል ድርጅት ሰራተኛ የስራ ውሉ የህግ ውጪ ሲቋረጥ የሚያገኛቸው ህጋዊ ጥቅማ ጥቅሞች እነዚህ ናቸው፡፡   Join us 1. https://t.me/joinchat/TDlwVN4QoPeK894b 2. https://t.me/joinchat/VHW6uiw5vqk6mgeZ 3.https://m.facebook.com/groups/1928323943874057/?ref=bookmarks 4.https://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
Mostrar todo...
የኢትዮጵያ ህግ /Ethiopian Law/

ዳንኤል ፍቃዱ ተስፋዬ በሁሉም የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጠበቃና የህግ አማካሪ ስልክ - 0913158507 ወይም 0978554559 Daniel Fikadu Tesfaye Certified Attorney of law at all Federal Courts of Ethiopia. Email- nurotekore@gmail. Com ⚖️⚖️Ethiopian Law by Daniel Fikadu channel ⚖️⚖️⚖️

👍 8 1
እነ ቀሲስ በላይ መኮንን በተጠረጠሩበት በሀሰተኛ ሰነድ የዶላር ዝውውር ወንጀል  ክስ መመስረቻ ተፈቀደ #Ethiopia  | እነ ቀሲስ በላይ መኮንን በተጠረጠሩበት በሀሰተኛ ሰነድ የዶላር ዝውውር ወንጀል  ክስ መመስረቻ ለዐቃቤ ህግ ተፈቅዷል። የክስ መመስረቻውን የፈቀደው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት  ነው። የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መርማሪ ፖሊስ በቀሲስ በላይ መኮንን ፣ያሬድ ፍስሃ እና ዳባ ገናና በተባሉ 3 ተጠርጣሪዎች ላይ ሲያከናውን የቆየውን የምርመራ ማጣሪያ ስራን ማጠናቁን ጠቅሶ የምርመራ መዝገቡን ለዐቃቤ ህግ ማስረከቡን አስታውቋል። የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ህግ በመዝገቡ ላይ ተሰይሞ የምርመራ መዝገቡ ዛሬ መረከቡን ጠቅሶ ፥ ተመልክቶ ለመወሰን እንዲያስችለው በወ/መስ/ህ/ቁጥር 109 /1 መሰረት የ15 ቀን ክስ መመስረቻ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል። በተጨማሪም ዐቃቤ ህግ የተጠረጠሩበት ወንጀል ድርጊት ሀሰተኛ ሰነድ መገልገልና ንግድ ባንክን ማታለል መሆኑን ጠቅሶ ፥ በሙስና አዋጁ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 23 እና አንቀጽ 32 ስር ሊያስከስሳቸው እንደሚችል ገልጿል። ተጠርጣሪዎቹ ከ6 ሚሊየን ዶላር በላይ ጥቅም ሊገኝበት እንደነበር ከ10 ዓመት በላይ በሚያስቀጣ ድንጋጌ ሊያስከስሳቸው እንደሚችል ተናግሮ የጠየቀው ዐቃቤ ህግ ፥ የ15 ቀን የክስ መመስረቻ እንዲፈቀድለት ጠይቋል። የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው ፥ በፖሊስ ሲከናወን የቆየው ምርመራን የሚመራው ዐቃቤ ህግ መሆኑን ጠቅሰው እንደ አዲስ መዝገቡን ተመልክቼ ለመወሰን 15 ቀን ክስ መመስረቻ ይሰጠኝ ማለቱ ተገቢ አይደለም በማለት የዐቃቤ ህግ ክስ መመስረቻ ጊዜ ጥያቄውን በመቃወም ተከራክረዋል። ጠበቆቻቸው ክስ ባልተመሰረተበት ሁኔታ ላይ ከ10 ዓመት በላይ ሊያስቀጣ ይችላል ተብሎ በግምት ሊገለጽ አይገባም በማለት ተከራክረዋል። ሰነዱ የቀረበው ለውጭ ሀገር ድርጅት ሂሳብ በመሆኑ በፀረሙስና አዋጅ ሊታይ እንደማይችል በመግለጽ  በሙስና ሊከሰሱ ይችላሉ ተብሎ በዐቃቤ ህግ መገለጹ አግባብ አይደለም በማለት ተከራክረዋል። በተጨማሪም ጠበቆቹ በ2 ኛ እና 3ኛ ተጠርጣሪዎች ላይ ምንም ተሳትፎ ባልተገለጸበት ሁኔታ ላይ አብረው በእስር መቆየታቸው እና ክስ መመስረቻ ጥያቄ መቅረቡን ተቃውመዋል። ጠበቆቹ "ሰነዱ የቀሲስ በላይ ስም ሆነ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን ስም ባልጠቀሰበት ሁኔታ ላይ ቅንነት በጎደለው መልኩ ወንጀል ተብሎ መቅረቡ አግባብ አይደለም" በማለት ጠበቆቹ መከራከሪያ ነጥብ አንስተዋል። ቀሲስ በላይ የልማት ሰብሳቢ፣ በምዕመናኖቻቸው ዘንድ የሚታመኑና በተፈለጉ ሰዓት የሚቀርቡ መሆናቸውን ጠበቆቻቸው ገልጸው ፥ የዋስ መብታቸው እንዲከበርም ጠይቀዋል። ዐቃቤ ህግ በበኩሉ ከጠበቃ ለተነሳ መከራከሪያ ነጥብ መልስ የሰጠ ሲሆን ÷ በዚህም  ምርመራውን ሲመራ ቆይቶ  አሁን መዝገቡን ተመልክቼ ክስ መመስረቻ ተብሎ የቀረበው ነጥብን በሚመለከት  የወንጀል ምርመራ ስልጣን ያለው ፖሊስ መሆኑን በመጥቀስ  ምርመራ መምራት ማለት የህግ ድጋፍ መስጠት ማለት መሆኑን ገልጾ መልስ ሰጥቷል። በተጨማሪም በጠበቆች በኩል ቅንነት የጎደለው ተግባር ነው ተብሎ በተገለጸው ክርክርን በሚመለከት ስነ ስርዓታዊ አለመሆኑን በመጥቀስ ዐቃቤ ህግም ሆነ ተቋሙ  ማንንም ለመጉዳት እንደማይሰራና ህግን ተከትሎ የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ስራ ብቻ እንደሚሰራ አብራርቷል። የውጭ ሀገር ሂሳብና ሰነድ በኢትዮጲያ ፀረሙስና አዋጁ ሊታይ የማይችል መሆኑን ጠበቆች የጠቀሱበትን ነጥብ በሚመለከት መልስ የሰጠው ዐቃቤ ህግ የማታለል ተግባር ሊፈጸም የነበረው ህጋዊ ሰውነት ባለው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሆኑን ጠቅሶ ፥ ክፍያው ተፈጽሞ ቢሆንና ጉዳት ቢደርስ ተጎጂው የኢትዮጵያ  ንግድ ባንክ መሆኑን ጠቅሶ፤ መታየት ያለበት በሙስና አዋጁ 881 /2007 ስር ነው በማለት በመከራከር መልስ ሰጥቷል። ሰነዱን በሚመለከት ደግሞ ሰነዱ ንግድ ባንክ ቀርቦ የነበረ መሆኑን በመጥቀስ በህዝባዊ ድርጅት ወይም በመንግስታዊ ድርጅት ስር የሚታይ ሰነድ በመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 23/3 ስር ይካተታል በማለት ተከራክሯል። ወንጀል በሌለበት ወንጀል ተብሎ ሊቀርብ አይገባም በማለት ለቀረበ የጠበቆች መከራከሪያን በሚመለከት ደግሞ ዐቃቤ ህግ በወንጀል ህጉ ሞራላዊ፣ ህጋዊና ግዙፋዊ ጉዳዮችን ያሟላ የወንጀል ድርጊት መሆኑን ገልጾ ፥ በሙስና አዋጁ እንደሚካተትና ከ10 ዓመት በላይ ሊያስቀጣ በሚችል ድንጋጌ ስር ሊያስከስስ እንደሚችል ጠቅሶ መልስ ሰጥቷል። 2ኛ እና 3ኛ ተጠርጣሪዎች ምንም ተሳትፎ የላቸውም በተባለው ጉዳይ ላይ ዐቃቤ ህግ ግብረዓበር ናቸው በማለት በአዋጁ ከአንቀፅ 32 እስከ አንቀጽ 37 ድረስ ባለ ድንጋጌ ስር በግብረአበርነት ክስ ሊቀርብባቸው እንደሚችል ገልጾ ማብራሪያ ሰጥቷል። የግራ ቀኙን ክርክር የመረመረው ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ግለሰቦቹ የተጠረጠሩበት ወንጀል በሙስና አዋጁ ስር የሚታይና ዋስትና የሚያስከለክል መሆኑን ጠቅሶ ፥ ተጠርጣሪዎቹ ክስ እስኪመሰረትባቸው ባሉበት ማረፊያ ቤት እንዲቆዩ በማለት ዐቃቤ ህግ የጠየቀውን የ15 ቀን ክስ መመስረቻ ጊዜ ፈቅዷል። ቀሲስ በላይ መኮንን ከአንድ ሣምንት በፊት በአፍሪካ ህብረት ቅጥር ጊቢ ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ  ንግድ ባንክ ውስጥ በአካል ቀርበው ሀሰተኛ የክፍያ ሰነዶችን በመያዝ ለ3 ግለሰቦች እና ለአንድ የግል ድርጅት ሂሳብ 6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር ለማዘዋወር ለባንኩ ጥያቄ በመቅረቡና የያዙት የክፍያ ሰነድ ሀሰተኛ መሆኑ መረጋገጡን ተከትሎ  በአፍሪካ ህብረት ጥበቃ ተይዘው ለፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ተላልፈው መሰጠታቸውን ተከትሎ  በጊዜ ቀጠሮ መዝገብ በፖሊስ የምርመራ ማጣሪያ ሲከናወንባቸው እንደነበር ይታወሳል። በታሪክ አዱኛ
Mostrar todo...
👍 8 2🎉 1
የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ *** በሰዎች የመነገድ ድርጊት ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመነገድና ለብዝበዛ አላማ በማከናወን በአለም አቀፍ ደረጃ በሰው ልጆች የመኖር ህልውና ላይ ከፍተኛ አደጋን የጋረጠ ተግባር ነው፡፡ በሰዎች መነገድ በሀገር ውስጥ ወይም ከሀገር ውጪ ሰዎችን በማዘዋወር ሊፈፀም ይችላል፡፡ ይህ ተግባር በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ በተለያየ መንገድ እና ምክንያት ሊፈፀም የሚችል ሲሆን ለድርጊቱ በብዛት ተጋላጭ ከሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ውስጥ ሴቶች እና ህፃናት ይገኙበታል፡፡ የተባበሩት መንግስታት የህፃናት መብቶች ስምምነት አንቀፅ 1 ህፃን ማለት ማንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በታች የሆነ ሰው ማለት ነው ይላል። የሀገራችንን ህጎች ስንመለከትም በተሻሻለው የፌደራል የቤተሰብ ቤተሰብ ህግ አንቀፅ 215 መሰረት ህፃን በማለት ትርጉም ባይሰጥም ለአካለ መጠን ያልደረሰ ሰው ፆታ ሳይለይ ማንኛውም እድሜው 18 ዓመት ያልሞላው ልጅ ማለት እንደሆነ ያመለክታል። በተጨማሪም በሰው የመነገድና ሰውን በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ቁጥር 1178/12 አንቀፅ 2(10) መሰረት ህፃን ማለት ዕድሜው ከ18 ዓመት በታች የሆነ ማንኛውም ሰው ነው፡፡ ህፃናት በሀገር ውስጥ እንዲሁም ከሀገር ውጪ በሰዎች የመነገድ ድርጊት በመጋለጥ ለከፍተኛ ጉዳት ሲዳረጉ ይስተዋላል፡፡ ህፃናትን በሰዎች የመነገድ ድርጊት ተጋላጭ የሚያደርጓቸው የተለያዩ ምክንያች ያሉ ሲሆን እድሜያቸው ውሳኔ የመወሰን አቅማቸው ላይ ከሚፈጥረው ተፅዕኖ በተጓዳኝ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች እንደ ዋና መንስኤ ሊወሰዱ ይችላሉ፡፡ በሰዎች የመነገድ ድርጊት የተዳረጉ ህፃናት ከሚደርሱባቸው ጉዳቶች መካከል የጉልበት ብዝበዛ ዋንኛው ነው፡፡ ይህም ህፃናትን ለከፋ የአካል እና የስነ-ልቦና ጉዳት ይዳርጋቸዋል፡፡ በአለም አቀፍ ስምምነቶች፣ አህጉራዊ ስምምነቶች እንዲሁም በአገራችን የህግ ማዕቀፍ የህፃናት መብቶች መከበር እንዳለባቸው የተደነገገ ቢሆንም የህግ ድንጋጌዎችን በሚጥስ መልኩ ህፃናት ተጎጂ ሆነው እናገኛለን፡፡ በመሆኑም በህፃናት የመነገድ ድርጊትና የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ ምክንያት በህጻናት ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እንዲሁም ጉዳት አድራሾችን ለመቅጣት የተለያዩ አለም አቀፍ ስምምነቶች እና ህጎች በስራ ላይ ውለዋል፡፡ ይህ የንቃተ ህግ ትምህርታዊ ፅሑፍ በሁለት ክፍል የቀረበ ሲሆን የመጀመሪያው ክፍል ምንነት በአጠቃላይ፣ ህፃናትን ለሰዎች የመነገድ ድርጊትና ጉልበት ብዝበዛ ተጋላጭ የሚያደርጓቸው መንስኤዎች እና የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ አይነቶችና የሚያስከትሉት ጉዳት እንመለከታለን፡፡ በክፍል ሁለት በህፃናት የመነገድ ድርጊትና የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ በኢትዮጵያ ህጎች ያለው ሽፋን ይዳሰሳል፡፡ • በሰዎች የመነገድ ድርጊት ምንነት በአጠቃላይ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰዎች የመነገድ ድርጊት በተለይም በሴቶችና ሕጻናት የመነገድ ድርጊት ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና ወንጀል ፈጻሚዎችን ለመቅጣት በወጣው እና ሀገራችን ባፀደቀችው ፕሮቶኮል አንቀፅ 3 መሰረት በሰዎች የመነገድ ድርጊት የሚከተለውን ትርጉም ይዞ እናገኘዋለን፡፡ "በሰዎች የመነገድ ድርጊት ማለት ብዝበዛን አላማ በማድረግ ዛቻን፣ ሀይልን ወይም ሌላ የማስገደጃ ዘዴ በመጠቀም፣ በማገት፣ በመጥለፍ፣ በተንኮል፣ በማታለል ወይም የተስፋ ቃል በመስጠት፣ ሥልጣንን አላግባብ በመጠቀም፣ የሰዎችን ለጥቃት ተጋላጭነት በመጠቀም ወይም ስለሌላው ኃላፊነት ያለበትን ሰው ፈቃድ ለማግኘት መደለያ ወይም ጥቅም በመስጠት ወይም በመቀበል ሰዎችን መመልመል፣ ማጓጓዝ፣ ማዘዋወር፣ ማስጠለል ወይም መቀበል ሲሆን የብዝበዛ ተግባር ቢያንስ በሌሎች ሰዎች ዝሙት አዳሪነት መጠቀም ወይም ሌላ ማንኛውም አይነት ወሲባዊ ብዝበዛን፤ የጉልበት ብዝበዛ፣ የግዳጅ ሥራ ወይም አገልጋይነት፤ ባርነት ወይም ባርነት መሰል ተግባር፤ የሰው ልጅን አካል ማውጣት ወይም መውሰድን ያካትታል፡፡" ስለሆነም እነዚህ ድርጊቶች እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች በሆኑ ህፃናት ላይ የተፈፀሙ እንደሆነ በህፃናት የመነገድ ድርጊት ይሆናል ማለት ነው፡፡ በዚህ መግለጫ ውስጥ ሶስት መሰረታዊ ፍሬ ነገሮች ማለትም ተግባር (The Act, What is done)፣ አደራረግ/ዘዴ (The Means, How it is done) እና አላማ (The Purpose, Why it is done) መሟላት ያለባቸው መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። በተጨማሪም ከብዝበዛ ተግባራት ውስጥ የጉልበት ብዝበዛ በፕሮቶኮሉ የተካተተ በመሆኑ የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ በዚሁ የሚሸፈን መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ በመሆኑም በሰዎች የመነገድ ድርጊት እና የጉልበት ብዝበዛ የማይነጣጠሉ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ እርግጥ የብዝበዛው አይነት እንደ ተጎጂው አይነት የሚለያይ ቢሆንም ማለትም በሴቶች ላይ የሚደረገው ብዝበዛ እና በወንዶች ወይም በህፃናት ላይ የሚደረገው ብዝበዛ ሊለያይ ቢችልም ድርጊቱ ግን በሰው ልጆች ሰብዓዊ መብት ላይ ጉዳትን ማስከተሉ አጠያያቂ አይደለም፡፡ በፕሮቶኮሉ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ፍሬ ነገሮች መቀመጣቸው አንድ ድርጊት በሰዎች የመነገድ ድርጊት ውስጥ ይወድቃል ወይስ አይወድቅም የሚለውን ለመወሰን የአለም ሀገራት ወጥነት ያለው እና ስምምነት የተደረሰበት (consistency and consensus) መለኪያ እንዲጠቀሙ የሚያደርጋቸው ሲሆን ይህንም በህጎቻቸው ውስጥ እንዲያካትቱ ይረዳቸዋል፡፡ የፕሮቶኮሉ አንቀፅ 5 በፕሮቶኮሉ አንቀፅ 3 ስር የተቀመጡትን ድርጊቶች ሀገራት በህጎቻቸው ውስጥ በወንጀል የሚያስቀጡ ተግባራት እንደሆኑ (criminalized in domestic legislation) መደንገግ እንዳለባቸው ያስቀምጣል፡፡ ይህንንም ሲያደርጉ ከሀገራቸው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በሚስማማ መልኩ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም ለተግባራዊነቱ ጠቀሜታ ስለሚኖረው ነው፡፡ በሌላ በኩል ከሰዎች የመነገድ ድርጊት ጋር የሚነሳው ጉዳይ የፍቃድ ወይም የስምምነት (consent) ጉዳይ ነው፡፡ በፕሮቶኮሉ አንቀፅ 3/ለ/ ስር እንደተደነገገው ለመነገድ ድርጊት ስምምነቱ የተገኘው በዛቻ፣ በሀይል፣ በተንኮል፣ በማታለል ወይም የተስፋ ቃል በመስጠት፣ ሥልጣንን አላግባብ በመጠቀም፣ የሰዎችን ለጥቃት ተጋላጭነት በመጠቀም ወይም ሌሎች የተከለከሉ መንገዶችን በመጠቀም ከሆነ ተገጂው ተስማምቷል ወይም ፍቃዱን ሰጥቷል ለማለት አይቻልም፡፡ ስለሆነም የበሰዎች የመነገድ ድርጊት ፈፃሚዎች የተጎጂውን ፍቃደኝነት ከህግ ተጠያቂነት ለማምለጥ እንደመከላከያ ሊያነሱት አይችሉም፡፡ ህፃናትን በተመለከተ ደግሞ ከላይ የተጠቀሱት መንገዶች (The Means) ተግባራዊ ባይደረጉም በህፃናት የመነገድ ድርጊት ከተከናወነ የወንጀል ድርጊቱ ተፈፀመ ማለት ይቻላል፡፡ በሁለቱም ጊዜ ማለትም አዋቂዎች ፍቃዳቸውን በተለያዩ ተፅዕኖ ውስጥ ሲሰጡ እንዲሁም ህፃናት በተፅዕኖም ይሁን ያለተዕፅኖ በሰዎች የመነገድ ድርጊት ሲጋለጡ ስምምነታቸውን ሰጥተዋል ማለት አይቻልም፡፡ ምክንያቱም የሰው ልጅ በምንም አይነት ሁኔታ ለብዝበዛ ነፃ ፍቃዱን ይሰጣል ተብሎ አይታሰብም፡፡ በዚህ ጊዜ የአዋቂዎች ፍቃድ ተገቢ ባልሆነ መንገድ እንደተገኘ፣ ህፃናት ደግሞ ተጋላጭ (vulnerable) በመሆናቸው ፍቃድ መስጠት እንደማይችሉ መገንዘብ ይቻላል፡፡
Mostrar todo...
👍 5🔥 1
• ህፃናትን በሰዎች የመነገድ ድርጊትና ጉልበት ብዝበዛ ተጋላጭ የሚያደርጓቸው መንስኤዎች የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ ህፃናት ለእድሜያቸው የማይመጥን፣ የህፃናቱን የጤና፣ የእድገት፣ የማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ ደህንነታቸውን የሚጎዳና ለህይወታቸው አስጊ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ እንዲሰሩ የሚያስገድድ ተግባር ነው። ይኸውም የህፃናትን ጉልበት በክፍያም ሆነ በነፃ፣ በቤት ውስጥም ሆነ ከቤት ውጭ ያላግባብ በመጠቀም ህፃናትን ለጥቃትና ብዝበዛ ማጋለጥን ያመለክታል። ህፃናትን ለጉልበት ብዝበዛ ከሚያጋልጡ ተግባራት ውስጥ በሰዎች የመነገድ ድርጊት አንዱ ነው፡፡ የህጻናት ጉልበት ብዝበዛን በሚያስከትሉ ስራ ላይ የተሰማሩ ህጻናት አብዛኛውን ጊዜ በሰዎች የመነገድ ድርጊት ደላሎች አማካኝነት ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው ከገጠር ወደ ከተማ እንዲኮበልሉ የተደረጉ ናቸው። እንዲሁም በማሳደግ ሰበብ ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው ለብዝበዛ የሚጋለጡ ህፃናት ቁጥር ጥቂት የሚባል አይደለም፡፡ በሰዎች የመነገድ ድርጊት አላማው በብዝበዛ ትርፍ ወይም ጥቅም ማግኘት በመሆኑ ህፃናቱ ከሚሰሩት የስራ አይነት በተጨማሪ የጉልበት ብዝበዛን የሚያሳዩ አመላካቾችንም መረዳት የሚያስፈልግ ሲሆን የህጻናትን ጤናማ ስራ ማለትም ቤተሰቦቻቸውን ለማገዝ ከሚሰሩት ስራ እና በህግ በተፈቀደው የእድሜ ክልል የሚሰራ የስራ አይነት ከጉልበት ብዝበዛ ለይቶ መገንዘብ ይጠቅማል። አመላካቾች ተብለው ከሚጠቀሱት የሚከተሉት ይገኙበታል፦ የህጻናቱ እድሜ፣ በስራው ላይ የሚያሳልፉት ጊዜ፣ የስራው ጸባይ፣ የስራው አካባቢ፣ የህጻናቱን የመማር መብት የሚነፍግ መሆን አለመሆኑ፣ ሲሰሩ የቤተሰብ ወይም አሳዳጊ ጥበቃና ክትትል መኖሩና አለመኖሩ የመሳሰሉት ሁኔታዎች ናቸው። ብዙ ጊዜ ህጻናትን ለጉልበት ብዝበዛ ተጋላጭ ከሚያደርጓቸው ምክንያቶች ድህነት በቀዳሚነት ይጠቀሳል። ብዙ ደሃ ቤተሰቦች ኑሯቸውን ለመደጎም ሲሉ ለስራ ያልደረሱ ህጻናትን የተለያዩ ስራዎችን በማከናወን ለቤተሰቡ ተጨማሪ ገቢ እንዲያስገኙላቸው ይጥራሉ። በዚህም ምክንያት ቤተሰቦቻቸው በተለያየ ተፅዕኖ ስር በመሆን ህፃናቱ በሰዎች የመነገድ ድርጊት ፈፃሚዎች እጅ እንዲወድቁ ያደርጋሉ፡፡ ህጻናትን ለጉልበት ብዝበዛ የሚያጋልጣቸው ሌላው ምክንያት ከባህላችንና ከልምዳችን ጋር የተያያዘ ነው። አብዛኛዎቹ ህዝቦች ህጻናት በለጋ እድሜያቸው የተለያዩ እውቀቶችና ክህሎቶች እንዲኖራቸው በማሰብ በስራ ላይ እንዲሰማሩ ይደግፋሉ ይገፋፋሉም። ይህም ወደ ፊት ህጻናት ከራሳቸው በተጨማሪ ለወላጆቻቸው የሚሰጡትን ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ ግምት ውስጥ በማስገባት ነው። ሌሎች መንስኤዎች በግለሰብ፣ በቤተሰብ፣ በማህበረሰብና በተቋማት ደረጃ ሊገለጹ የሚችሉ ምክንያቶች ናቸው። በግለሰብ ደረጃ አጋላጭ መንስኤ ሊሆን የሚችል ለምሳሌ አንድ ህጻን አካል ጉዳተኛነቱ ለጉልበት ብዝበዛ ተጋላጭ መሆኑን ይበልጥ ያጠናክረዋል። ይኸውም ህፃኑ በልመና ስራ ላይ ተሰማርቶ ገቢ እንዲያስገኝ ሊደረግ ይችላል፡፡ ሌላው የትምህርት እድል ያላገኙ ህጻናትም እንደዚሁ ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ ይሆናል። በቤተሰብ ደረጃ ሲታይ ደግሞ የወላጆች ሞት፣ በቂ የገቢ ምንጭ አለመኖር፣ የወላጆች የትምህርት ደረጃ ማነስ፣ የቤተሰብ መፍረስ፣ ግጭትና የቤት ውስጥ ጥቃቶች የመሳሰሉት ሊጠቀሱ ይችላሉ። በማህበረሰብ ደረጃ ደግሞ የጾታ ልዩነት፣ መድሎ፣ የማህበረሰቡ ባህልና የአኗኗር ሁኔታ የህጻናቱን ተጋላጭነት ከሚያጠናክሩ መንስኤዎች ይጠቀሳሉ። በተቋም ደረጃ የትምህርት፣ የጤናና ሌሎች መሰረታዊና ማህበራዊ ተቋማት ያለመስፋፋታቸው፣ ምቹ የትምህርት አካባቢ ያለመመቻቸት፣ የህግ ማእቀፍና የፖሊሲ ክፍተቶች፣ የልደት ምዝገባ አለመስፋፋት ወ.ዘ.ተ የሚጠቀሱ መንስኤዎች ናቸው። ከላይ የተጠቀሱት ድህነትና ሌሎች ቀስቃሽ መንስኤዎች ህፃናቱን በሰዎች የመነገድ ድርጊት በማጋለጥ አልያም ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሆነው የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ እንዲጠናከር ምቹ ሁኔታን ይፈጥራሉ። የህጻናትን ጉልበት ተጠቃሚዎች ከአዋቂዎች ይልቅ ህጻናትን ለመመልመል/መቅጠር የሚፈልጉበት የሚጠቀሱ በርካታ ምክንያቶች አሉ። ለምሳሌ፡- ህፃናት እንደ አዋቂዎች ለጉልበታቸው ዋጋ የመከራከር አቅም ስለሌላቸው፣ ህፃናት ለአዋቂዎች ታዛዦች ሆነው ማገልገል ይችላሉ ተብሎ ስለሚገመት፣ በርካሽ ሊገኝ የሚችል ጉልበት ተደርጎ ስለሚገመት፣ ለረጅም ጊዜ በታማኝነት ሊያገለግሏቸው እንደሚችሉ በማሰብ፣ ወ.ዘ.ተ የሚሉት ሊጠቀሱ ይችላሉ። በአጠቃላይ ከላይ የተጠቀሱት ምክንያቶች የህፃናትን በተለየ ሁኔታ በሰዎች የመነገድ ድርጊት ተጋላጭነት (a position of vulnerability) ያመላክታሉ፡፡ • የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ አይነቶችና የሚያስከትሉት ጉዳት በህፃናት የመነገድ ድርጊት (child trafficking) ህፃናትን የመሸጥ፣ የመግዛት እንዲሁም የማዘዋወር ተግባርን የሚያካትት ሲሆን ይህም የህፃናት ጉልበት ለመበዝበዝ አላማ የሚከናወን ተግባር ነው፡፡ ህፃናት ለተለያየ አላማ መጠቀሚያነት ከቦታ ወደ ቦታ ሊዘዋወሩ ይችላሉ፡፡ ከዚህም ውስጥ፡- ለፆታዊ ብዛበዛ (sexual exploitation)፣ ለጉልበት ብዛበዛ፣ ለወታደርነት፣ በልመና እና በወንጀል ድርጊቶች ላይ እንዲሳተፉ ለማድረግ እና ለመሳሰሉ ድርጊቶች መጠቀሚያነት ሊመለመሉ ይችላሉ፡፡ በአጠቃላይ በህፃናት ላይ ከሚደረጉ የጉልበት ብዛበዛ አይነቶች ውስጥ የቤት ውስጥ ስራ፣ ባርነት ወይም የግዴታ ስራ፣ ዝሙት አዳሪነት፣ በወንጀል ድርጊቶች እንዲሳተፉ ማድረግ፣ በልመና ተግባር ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ እና የደመወዝ ስራ( በአነስተኛ ክፍያ) ማሰራት ይገኙበታል፡፡ በተጨማሪም ከብዝበዛ አይነቶች አንዱ የሆነው የሰውነት ክፍልን ማውጣት በህፃናት ላይ ሊፈፀም ይችላል፡፡ በሌላ በኩል በህፃናት የመነገድ ድርጊት እና የጉልበት ብዛበዛ በህፃናቱ ጤናና እድገት ላይ ከሚያደርሰው ተፅእኖ በተጨማሪ በማህበረሰቡም ላይ የሚኖረው ጉዳት ቀላል አይደለም። ከሁሉም በላይ ለህፃናት ጉልበት ብዝበዛ የሚዳርግ በህፃናት የመነገድ ድርጊት መስፋፋት በሁለት መልኩ ማህበራዊ ቀውስን ሊያስከትል እንደሚችል ጥናቶች ይጠቁማሉ። ይኸውም በአንድ በኩል በሰው የመነገድ ድርጊት መስፋፋት በማህበረሰቡ ውስጥ ህገ-ወጥነትንና ወንጀል እንዲበራከት አይነተኛ ምክንያት ይሆናል። በሰው የመነገድ ድርጊት ፈፃሚዎች በተለይም በድንበር ዘለል የመነገድ ድርጊት ላይ የሚሳተፉት በአብዛኛው ከሌሎች ወንጀሎች ጋር ግንኙነት ያላቸው እንደሆነ ይጠቀሳል። በሌላ በኩል ደግሞ የብዝበዛ ሰለባ የሆኑት ህፃናት ራሳቸው ለአደንዛዥ እፆችና ለተለያዩ ሱሶች ስለሚጋለጡ ይኸውም ሁኔታ ወደ ወንጀል ነክ ተግባራት እንዲገቡ በመገፋፋት ማህበራዊ ጠንቅን ሊፈጥር ይችላል። ከዚህም በተጨማሪ ለችግሩ ሰለባ የሆኑት ህፃናት ወደ ትውልድ ቀያቸው ሲመለሱ ወይም ከተሰማሩበት ቦታ ሆነው ቤተሰቦቻቸውን በገንዘብም ሆነ በቁሳቁስ ለመርዳት ሲሞክሩ የአካባቢውን ማህበረሰብ የመነገድ ድርጊትን ይበልጥ በማነሳሳት ማህበረሰቡ ከችግሩ ይልቅ በሚገኘው ገንዘብ ላይ እንዲያተኩርና ለብዝበዛው የተሳሳተ አመለካከት እንዲኖረው በማድረግ ማህበራዊ ችግርን ሊፈጥር ይችላል።
Mostrar todo...
👍 4
የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ በአንድ ሀገር ኢኮኖሚ ላይም አሉታዊ ተፅእኖን ያስከትላል። ከድህነት ጋር በተያያዙ ልዩ ልዩ ምክንያቶች በሀገር ውስጥም ሆነ ወደ ውጭ በሚደረገው በሰው የመነገድ ድርጊት የወደ ፊት ሀገር ተረካቢ ሊሆን የሚችለውን በርካታ አምራች የሰው ሀይል ማጣት ሊያስከትል ይችላል። በአጠቃላይ የህጻናት ጉልበት ብዝበዛ ለወደፊት ትልቅ አምራች የሚሆንን ትውልድ በአጭር የሚቀጭ ድርጊት ነው፡፡ በአጠቃላይ በድርጊቱ ህፃናት ከቀላል የአካል ጉዳት እስከ ሞት ለሚደርስ ጉዳት ሊጋለጡ ወይም እድሜ ልክ ለማይሽር አካላዊም ሆነ አእምሯዊ ጉዳት ሊዳረጉ ይችላሉ። በመሆኑም በህፃናት የመነገድ ድርጊትና የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ የህፃናቱን የመኖር፣ የመማር፣ የጨዋታ፣ እንክብካቤና ጥበቃ የማግኘት መብታቸውን የሚያሳጣ ተግባር መሆኑን በመገንዘብ ድርጊቱ እንዳይፈፀም መከላከል፣ ተፈፅሞም ሲገኝ ፈፃሚዎች የሚቀጡበትን ስርዓት መዘርጋትና ማጠናከር ያስፈልጋል፡፡
Mostrar todo...
👍 5
Repost from TIKVAH-MAGAZINE
#Update በፎፌክስ ትሬዲንግ ስም የሚያታልሉ ግለሰቦችንና ቡድኖችን በህግ ተጠያቂ ማድረግ እንደሚቻል ተገለፀ። በፎሬክስ ትሬዲንግ የኦንላይን ስራ ትርፋማ እናደርጋችኋለን" የሚል የፌስቡክና የቴሌግራም ማስታወቂያ በሚያስነግሩ የተደራጁ ቡድኖች የተጭበረበሩ ሰዎችን አስመልክቶ ቲክቫህ ተከታታይ ዘገባ መስራቱ ይታወሳል። ጉዳዩን አስመልክቶ የሚመለከተውን አካል ያነጋገርን ሲሆን ፥ በዚህ ጉዳይ ወንጀል ተፈፅሞብኛል የሚሉ ግለሰቦች የሚያቀርቡትን ጥቆማና መረጃ ተከትሎ ከህግ አካላት እና ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በመተባበር ጉዳዩን እንደሚያጣሩ የኢትዮጵያ ፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት የህዝብ ግንኙነትና የኮሚኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ እንዳለ አሰፋ ለቲክቫህ ገልፀዋል።  አቶ እንዳለ በፎሬክስ ትሬዲንግ የማጭበርበር ድርጊት ጉዳይ እስካሁን ጥቆማ ለመስሪያ ቤቱ እንዳልደረሰ የገለፁ ሲሆን "ወንጀል ተፈፅሞብኛል" የሚሉ ሰዎች በአቅራቢያቸው ለሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወንጀል ምርመራ ክፍል ሪፖርት ማድረግ እንዳለባቸው በማሳሰብ ፥ በፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት መስሪያ ቤት በኩል የሚፈለገው እገዛ ለፖሊስ እንደሚሰጥ አስረድተዋል። ይህን መሰል የማታለል ድርጊት በህግ እንዴት ይታያል? ይህን ጉዳይ አስመልክቶ ያናገርናቸው ጠበቃ እና የህግ አማካሪ እንዲሁም በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት አቶ እሱባለው አማረ የወንጀል ድርጊቱ ፈርጀ ብዙ የህግ ተጠያቂነት እንደሚያስከትል ገልፀዋል። ጠበቃ እና የህግ አማካሪው አቶ እሱባለው ድርጊቱ በንብረት መብት (property right) ላይ ከሚፈፀም ወንጀል ጋር እንደሚያዝ ያስረዱ ሲሆን በዋናነት በንብረት ላይ ሊፈፀም ከሚችሉ ወንጀሎች ተብለው በወንጀል ህጋችን  ከተጠቀሱት መሃከል በ"አታላይነት" ወንጀል እንደሚያስጠይቅ ለቲክቫህ ገልፀዋል። "አታላይነት" በወንጀል ህጉ ከአንቀፅ 692 ጀምሮ ሽፋን እንደተሰጠው የገለፁት የህግ መምህሩ ፥ "ማታለልን ያካተቱ ወንጀሎች" በሚል ንዑስ ስር ያለ የዚህ ድንጋጌ ንዑስ አንቀፅ 1 "ማንም ሰው የማይገባ ብልፅግና ለራሱ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ አሳሳች የሆኑ ነገሮችን በመናገር፣ የራሱን ማንነት ወይም ሁኔታ በመሰወር ወይም መግለጽ የሚገባውን ነገር በመደበቅ ወይም የሌላውን ሰው የተሳሳተ እምነት ወይም ግምት በመጠቀም፣ በማድረግም ሆነ ባለማድረግ ሌላውን ሰው አታልሎ የራሱን ወይም የሶስተኛ ወገንን የንብረት ጥቅም የሚጎዳ አድራጎት እንዲፈፀም ያደረገ እንደሆነ የአታላይነት ወንጀል እንደተፈፀመ ያስቀምጣል" ሲሉ አስረድተዋል። ይህ የወንጀል ድርጊት በቀላል እስራት ወይም እንደነገሩ ከባድነት ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እስራትና በገንዘብ መቀጮ እንደሚያስቀጣም ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ ፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት የህዝብ ግንኙነት እና የኮሚኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ እንዳለ አሰፋ በፎሬክስ ስም የማታለል ወንጀል ተፈፅሞብኛል የሚሉ ሰዎች ወይም በጉዳዩ ላይ አጠራጣሪ ነገሮችን የተመለከቱ ግለሰቦች ፖሊስ ጋር ከመሄድ ባሻገር ለተቋሙ በስልክ ቁጥር +251-11-812-8261 ጥቆማ መስጠት እንደሚችሉ በማስረዳት ፥ ከሚመለከተው አካል ጋር በመተባበር ክትትል እንደሚደረግ ገልፀዋል። በኦላይን የሚፈጸሙ የማጭበርበር ድርጊቶችን ለመጠቆም @tikvahmagbot ይጠቀሙ። በጉዳዩ ላይ ለመወያየት https://t.me/tikvahforum/22079 ላይ ሀሳቦትን ያካፍሉን። 👋  @TikvahethMagazine
Mostrar todo...
👍 7
የካሣ ክፍያ ኮንትራቱን ሊያቋርጥ ይችላል፡፡ ሠራተኛውምያለምንም ማስጠንቀቂያ ኮንትራቱን ሊያቋርጥ ይችላል፡፡በሚል ተመዛዛኝ ደረጃ ደንግጎ ይገኛል፡፡ የሥራ ቅጥር መቋረጥ ስምምነት ቁጥር 158 አንድ ሰራተኛ ከስራው በሚሰናበትበት ጊዜ ካለው የአገልግሎት ጊዜ ርዝመት ጋር የሚጣጣም የማስታወቂያ ጊዜ ሊሰጠው እንደሚገባ ያስቀመጠ ሲሆን ፡፡የተሻሻለው የሀገራችን አሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀፅ 24-35፤ የፍታብሄር ህግ አንቀፅ 2571 በህጉ ወይም ህብረት ስምምነት ወይም በሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች ስምምነት መሰረት ማንኛውም ወገን ማስታወቂያ በመስጠት ወይም አስፈላጊውን ክፍያ በመፈፀም ውሉን ሊያቋርጥ ይችላል፡፡ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ መሰረት ለተወሰነ ጊዜ ወይም ስራ የተገባው የስራ ውል ሲያበቃ ወይም ሲጠናቀቅ፣ ሰራተኛው ሲሞት ወይም ሰራተኛው በህጋዊ መንገድ ጡረታ ሲወጣ ድርጅቱ በኪሳራ ወይም በሌላ ማንኛውም ምክንያት ሙሉ በሙሉ ስራ ሲያቆም ወይም በአካል ጉዳት ምክንያት መስራት የማይችል ሲሆን የስራ ቅጥር ውሉ ሊቋረጥ ይችላል፡፡ እንዲሁም የስራ ቅጥር ውሉ ከሰራተኛው ጠባይ ወይም የሠራተኛውን የመስራት ችሎታ ወይም ከድርጅቱ ድርጅታዊ አቋም ወይም የስራ እንቅስቃሴ ጋር ባላቸው ምክንያቶች ሊቋረጥ ይችላል፡፡ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ በተጨማም የስራ ውል ያለማስጠንቀቂያ ሊቋረጥ የሚችልባቸውን ሁኔታዎች ይጠቅሳል፡፡ ውሉን ማቋረጥ የፈለገ ሰራተኛ ለአሰሪው የ30 ቀናት ቅድመ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ማቋረጥ ይችላል፡፡ በሌላ በኩል አሰሪው ከሰራተኛው ጋር ያለውን የስራ ውል ማቋረጥ ከፈለገ ማስታወቂያ የሚሰጠው በሚከተለው መሰረት ይሆናል፡፡ • የሙከራ ጊዜያቸውን ላጠናቀቁ እና የአገልግሎት ጊዜያቸው ከአንድ አመት ላልበለጠ         አንድ ወር • ከአንድ እስከ 9ዓመት የአገልግሎት ጊዜ ላላቸው ሰራተኞች ሁለት ወር • ከ9ዓመት በላይ አገልግሎት ላላቸው 3 ወር • የሙከራ ጊዜያቸውን ላጠናቀቁ እና ነገር ግን የሰራተኛ ኃይል በመቀነሱ ምክንያት የስራ ውላቸው ለተቋረጠ ሰራተኞች 2 ወር ለተወሰነ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ሥራ የተደረገ የሥራ ውልን በሚመለከት የማስጠንቀቂያ ጊዜው ተዋዋይ ወገኖች በውሉ ላይ በተስማሙት መሠረት ይሆናል፡፡ የሥራ ቅጥር መቋረጥ ስምምነት ቁጥር 158 ስለ ስንብት ክፍያ አሰሪዎች ሰራተኞች ከስራ በተለያዩ ምክንያቶች ለምሳሌ እንደ ቅነሳ ባሉ ምክንያቶች ሲሰናበቱ የስራ ስንብት ክፍያ እንዲከፈላቸው የመጠየቅ መብት እንዳላቸው ፡፡ ነገር ግን የችሎታ ማነስ (የሥራ አፈጻጸም ብቃት ማነስ)ና የባህርይ ችግርን አስመልክቶ ከሰራተኛው ለሥራው ባህሪ ያለመስማማት (ያለመመጠን) ጋራ የሚያያዝ በመሆኑ ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች የሥራ ውላቸው የሚቋርጥ ሰራተኞች ክፍያ የመጠየቅ መብታቸው የሚገደብ መሆኑን ይደነግጋል፡፡ በተቀራራቢ ሁኔታ የተሻሻለው የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀፅ 32፣39-40 የሙከራ ጊዜውን ላጠናቀቀ አንድ ሰራተኛ የስራ ስንብት ክፍያ እንደሚከፈለው ይደነግጋል፡፡ የስራ ቅጥር ውሉ የአሰሪው ድርጅት በቋሚነት ስራዎቹን በኪሳራ ወይም በሌላ ምክንያት በማቆሙ በአሰሪው የተቋረጠ እንደሆነ ወይም የሰራተኛው የስራ ቅጥር ውል ከህግ ድንጋጌ ውጪ ከተቋረጠ ወይም ሰራተኛው የተቀነሱ ሰራተኞች ውስጥ ከተካተተ ወይም አሰሪው የሰራተኛውን መብት የሚነካ ህገ-ወጥ ድርጊት ከፈጸመ ወይም አሰሪው በስራ ቦታ ስላለ አደጋ ካወቀ በኋላ የሰራተኛውን ጤንነት እና ደህንነት ለማስጠበቅ እርምጃ ያልወሰደ እንደሆነ እና የስራ ቅጥር ውል ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የአካል ጉዳት ስለደረሰበት የሥራ ውሉ የተቋረጠ ሰራተኛ የስራ ስንብት ክፍያ የማግኘት መብት ይኖረዋል፡፡ የስራ ስንብት ክፍያው መጠን በአገልግሎት ዘመን ላይም የተመሰረተ ነው፡፡ በዚህም መሰረት በሚከተለው ተመን መሰረት የሚከፈል ይሆናል፡፡ • ለአንድ አመት አገልግሎት የ30 ቀናት ደመወዝ /ከአንድ አመት በታች ላገለገሉ ሠራተኞች የስራ ስንብት ክፍያው ባገለገሉበት ጊዜ መጠን ተሰልቶ ይከፈላቸዋል/ • ከአንድ ዓመት እስከ ዘጠን ዓመት አገልግሎት የ30 ቀናት ደመወዝና ለእያንዳንዱ ተጨማሪ አመት የ10 ቀናት ክፍያ / የስራ ስንብት ክፍያ ከሁለት ወራት ደመወዝ መብለጥ የለበትም፡፡ • የስራ ውላቸው በቅነሳ ምክንያት ለሚቋረጥ ሰራተኞች ከላይ ከተዘረዘሩት በተጨማሪ የ60 ቀናት ደመወዝ ይከፈላቸዋል፡፡ • ከላይ ከተመለከተው የሥራ ስንብት ክፍያ በተጨማሪ ሠራተኞች ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውላቸውን ሲያቋርጡ ተጨማሪ የ30 ቀናት ክፍያ በካሣ መልክ ያገኛሉ፡፡ የሥራ ውልን ያለ ማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ በቂ ምክንያቶች ዝርዝር የሚከተሉትን ሁኔታዎች ያካትታል፡- . አሠሪው የሠራተኛውን ሰብአዊ ክብርና ሞራል የሚነካ ወይም በወንጀል ሕጉ መሠረት የሚያስቀጣ ሌላ አድራጎት የፈጸመበት እንደሆነ፤ . ለሠራተኛው ደኅንነት ወይም ጤንነት የሚያሰጋና ሊደርስ የተቃረበ አደጋ የኖረ እንደሆነ፤ አሠሪው አደጋን እንዲቀርፍ እና ለመከላከል በሰጠው ማስጠንቀቂያ መሠረት በተወሰነው የጊዜ ገደብ ውስጥ እርምጃዎችን ያልወሰደ እንደሆነ እና በዚህ አዋጅ በኅብረት ስምምነት ወይም በሥራ ደንብ ወይም አግባብ ባላቸው ሌሎች ሕጎች በተወሰነው መሠረት አሠሪው ለሠራተኛው መፈጸም ያለበትን ግዴታዎች በመደጋገም ያልፈጸመ እንደሆነ፡፡ • አንድ ሰራተኛ በአሠሪ ወይም በሥራ መሪ በሚፈፀምበት ወሲባዊ ጥቃት ወይም ትንኮሳ ምክንያት የሥራ ውሉን ያለማስጠንቀቂያ ያቋረጠ እንደሆነ ሰራተኛው ከሥራ ስንብት ክፍያው በተጨማሪ የቀን ደመወዙ በ90 ተባዝቶ ይከፈለዋል፡፡ በማለት ከዓለም አቀፉ የሰራ ድርጅት ድንጋጌዎች ጋራ በተመዛዘነ መልኩ አስቀምጧል፡፡   Join us 1. https://t.me/joinchat/TDlwVN4QoPeK894b 2. https://t.me/joinchat/VHW6uiw5vqk6mgeZ 3.https://m.facebook.com/groups/1928323943874057/?ref=bookmarks 4.https://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
Mostrar todo...
የኢትዮጵያ ህግ /Ethiopian Law/

ዳንኤል ፍቃዱ ተስፋዬ በሁሉም የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጠበቃና የህግ አማካሪ ስልክ - 0913158507 ወይም 0978554559 Daniel Fikadu Tesfaye Certified Attorney of law at all Federal Courts of Ethiopia. Email- nurotekore@gmail. Com ⚖️⚖️Ethiopian Law by Daniel Fikadu channel ⚖️⚖️⚖️

👍 5
⚖Ethiopian law by Daniel Fikadu Law office⚖: የሥራ ዋስትና የዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት ለአሰሪና ሰራተኞች ህግጋት ፤የሠራተኛ ማሕበራት አሠራር ሥርዐት፤እንዲሁም የአሰሪ ድርጅቶች (ሰዎች) ከውጤታማ የሥራ  እና ምቹ ከባቢያዊ የሥራ ሁኔታ ከመፍጠር እና የሠራተኛ መብት እና ግዴታዎችን ከማስጠበቅ አንጻር ለስምምነት አባል ሃገራት በመነሻነት እንዲያገለግሉ በማዝጋጀት እና አባል በማበርከት ከፍተኛ ሚና እንዳለው ይታወቃል፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያም በድርጅቱ የሚዘጋጁ የተለያዩ ስምምነቶችን በመቀበል የምትታወቅ ሲሆን  እ.ኤ.አ 1982 በድርጅቱ የተዘጃጋጀውንና ለስምምነቱ አባል ሃገራት የቀረበውን የሥራ ቅጥር መቋረጥ ስምምነት ቁጥር 158 ተቀብላ ያፀደቀች መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በመሆኑም ከዚህ በመቀጠል የዚህን ስምምነት ጥቅል ይዘት እንደሚከተለው መመልከት ይቻላል፡፡ በዚህ ክፍል ስር ያሉት ጥያቄዎች የሚመዝኑት በስራ ግንኙነት ውስጥ ያለውን የሥራ ዋስትና ግትር ያለመሆን /flexibility/ እንዲሁም የዘፈቀደ ያለመሆን /Precariousness/ ባማከለ መልኩ ነው፡፡ በቅጥር ማቋረጥ ስምምነት ቁ.158 ውስጥ የስራ ስንብት ክፍያና የማስታወቂያ አስፈላጊነት የተደነገገ ሲሆን በጠጨማሪ ሌሎች በመስኩ ያሉ ምርጥ አሰራሮች ተካተውበት ይገኛሉ እነዚህም ሰራተኞች ቅጥራቸው ወይም የቅጥር ውላቸው በፅሁፍ እንዲበጣቸው፣ የቋሚነት ባህርይ ላላቸው ስራዎች የውስን ጊዜ ሰራተኞች እንዳይቀጠሩ፣ በቂ የሙከራ ጊዜ / ለ6 ወራት ወይም ላነሰ ጊዜ/ በመስጠት የሠራተኛን ተስማሚነት መገምገም እንዳለበት፣የስራ ግንኙነትን ከማቋረጥ በፊት በማስታወቂያ ጊዜ መስጠት እንዳለበት እና የስራ ግንኙነት በሚቋረጥበት ጊዜ ሰራተኞች የስንብት አበል እንዲከፈላቸው ይጠይቃሉ፡፡ ስምምነቱ ከዚሁ ጋር የሚያያዙ በርካታ ቁም ነገሮችን በውስጡ አቅፎ የያዘ ሲሆን ከነዚህም መካከል የቅጥር ውል በቃል ወይም በፅሁፍ ሊደረግ የሚቻል ስለመሆኑ እና ነገር ግን ሰራተኞች ስራ ሲጀምሩ የቅጥር ሁኔታው ዝርዝር በፅሁፍ ሊሰጣቸው እንደሚገባ ሲያስገነዝብ፡፡ በዚሁ ልክ የሀገራችን የአሰሪ እና ሰራተኛ አዋጅ 1158/2011 አንቀጽ 4-8 የሚከተሉትን ጥቅል ሐሳቦች አካቷል፡- የግለሰብ የቅጥር ስምምነት በቃል ወይም በፅሁፍ ሊፈጸም የሚችል ሲሆን ለተወሰነ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ስራ የተደረገ ውል ካልሆነ በስተቀር የስራ ቅጥር ውል ላልተወሰነ (የጊዜ ገደብ ያልተደረገበት) ጊዜ እንደተደረገ የሥራ ውል ይቆጠራል፡፡ በሌላ በኩል የስራ ቅጥር ውል በግልጽ መቀመጥ ያለበት ሲሆን በህገ-ወጥ ስራ ወይም ሞራልን የሚነኩ ተግባራትን ለመፈጸም ሊደረግ አይገባም፡፡ ውሉም በህጉ፣ በህብረት ስምምነቱ እና በስራ ደንብ ውስጥ ከተቀመጡት በተሻለ ለሰራተኛው አመቺ የሆኑ ድንጋጌዎችን ማካተት የሚደነግግ ሲሆን፡፡ በጽሑፍ የተደረገ የስራ ቅጥር ውል (የስራ ውል ከሌለ ዝርዝር ሁኔታዎችን የሚገልጽ መግለጫ) የሚከተሉትን መግለጽ ይጠበቅበታል፡ የቀጣሪው ስምና አድራሻ፣ የሠራተኛው ስም፣ አድራሻ እና የሥራ ካርድ ቁጥር፣ የቅጥሩ ዓይነት፣ የሥራ ቦታ፣ የደሞዝ መጠንና ስሌት፣ የክፍያው ጊዜ እና የኮንትራት ጊዜ፡፡ በሁለቱ ወገኖች መፈረም ይኖርበታል፡፡ አሰሪው የነዚህን ድንጋጌዎች መስፈርቶች የሚያሟላ ከሆነ ሰራተኛው በዚህ አዋጅ መሰረት የተሰጡትን መብቶችን ሊገፈፍ አይገባም፡፡ በሚል ዝርዝር ሁኔታ የስምምነቱን መሰረታዊ ሐሳብ በማካተት ድንጋጌው እንዲዘጋጅ ተደርጓል፡፡   በተጨማሪ የሥራ ቅጥር መቋረጥ ስምምነት ቁጥር 158 የቅጥር ውል ወደ የዘፈቀደ ቅጥር እንዳያመራ የቋሚነት ባህርይ ላላቸው ስራዎች የኮንትራት ሰራተኞች መቀጠር የሌለባቸው መሆኑን የደነገገ ሲሆን፡፡ ከላይ ከተቀሰው ድንጋጌ ጋር በሚጣጣም መልኩ የሃገራችን ሠራተኛ እና አሰሪ አዋጅ ቁጥር 1158/2011 አንቀጽ 9-10 እና አንቀጽ 46 እንዲሁም የፍትሐብሄር ህግ አንቀጽ 2568 የቋሚነት ባህርይ ላላቸው ስራዎች የውስን ጊዜ ሰራተኞች መቅጠርን ይከለክላል፡፡ ለተወሰነ ወይም ለተቆረጠ ጊዜ የሚሰራ የቅጥር ውል በሚከተሉት ሁኔታዎች ወቅት ሊፈፀም ይችላል፡፡ ተቀጣሪው ይሰራው ዘንድ ለተቀጠረበት የተወሰነ ስራ ፣ በእረፍት ወይም በሕመም ወይም በሌላ ምክንያት ለጊዜው በስራው ላይ ያልተገኘን ሰው ለመተካት፣ ከተለመደው የተለየ የስራ ጫና በሚኖርበት ወቅት፣ በሕይወት ወይም በንብረት ላይ አደጋ ወይም ጉዳት እንዳይደርስ ለመከላከል የሚሰራ አስቸኳይ ስራ ሲኖር፣ በስራ ቦታ የሚገኙ የካምፓኒው ስራዎች፣ ማቴሪያሎች፣ ህንፃዎችንና ማሽኖችን እንከኖችንና ብልሽቶችን ለመጠገን፣ የዋናው ስራ አካል የሆነ ነገር ግን መደበኛ ባልሆነ ጊዜያት የሚሰራ መደበኛ ያልሆነ ስራ፣የቀጣሪው ዋና ስራ አካል የሆነና በዓመት ለተወሰነ ጊዜ የሚሰራ ነገር ግን በየተወሰነ ዓመት የሚደጋገሚ ወቅታዊ ስራ፣ የቀጣሪው ዋና ተግባር ወይም ስራ አካል ያልሆነ ነገር ግን አልፎ አልፎ የሚሰራ ስራ፣ የረዥም ጊዜ የስራ ውል እያለው በድንገትና ጠቅላላውን ከስራ የለቀቀን ሰራተኛ በጊዜያዊነት ለመተካት፣በአደረጃጀት መዋቅር ጥናትና በትግበራ መካከል ባለው ጊዜ በክፍት ቦታ በጊዜያዊነት ሰው ለመመደብ፡፡ የሰራተኛ አዋጁ ውሉ ከ45 ተከታታይ ቀናት መብለጥ የለበትም እንደዚሁም መከናወን ያለበት አንድ ጊዜ ነው ብሎ ለመጨረሻዎቹ ሁለት አይነቶች ካስቀመጠው በስተቀር የውስን ጊዜ ውል የጊዜ መጠንን (እድሳቶችን ጨምሮ) አይወስንም፡፡ ለተወሰነ ጊዜ/ሥራ የተደረገ የሥራ ውል ከፍተኛው የቆይታ ጊዜ 5 ዓመት መሆኑ በፍትሐ ብሔር ህጉ ተደንግጓል፡፡ ሆኖም ሠራተኛው ከ5 ዓመት በኋላ ሥራውን ከቀጠለ ወይም ውሉ ከታደሰ ነባሩ ውል ላልተወሰነ ጊዜ/ሥራ ውል እንደተደረገ ይሆናል፡፡(ጠተፖሰተ) አዲሱ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ አንድ ሰራተኛ በራሱ ቤት ሆኖ አሠሪው በቀጥታ ሳይቆጣጠረው ወይም ሳይመራው ለተሰራው ሥራ ደመወዝ የሚከፈልበትን በቤት የሚሰራን ስራ አካቷል፡፡ በራሱ ቤት በሚሠራ ሠራተኛና በአንድ አሠሪ መካከል የሚደረግ ውል ለተወሰነ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ሥራ እንደተደረገ የሥራ ውል ይቆጠራል፡፡በመሆኑም የሃገራችን አሰሪ እና ሰራተኛ ህግ ልክ ከላይ የሥራ ውል ሊያሟላቸው ስለሚገቡ ጉዳዮች በዝርዝር እንደገለጸው በዚህ ክፍልም ስለውስን ጊዜ የስራ ውል ወይም ስለውስን የሥራ ዓይነት ውል ከላይ እንደተመለከተው በዝርዝር አካቶ ይዟል፡፡  በድጋሚ የሥራ ቅጥር መቋረጥ ስምምነት ቁጥር 158 አንድ ሰራተኛ አዳዲስ ክህሎቶችን ማዳበር እንዲችል በቂ የሙከራ ጊዜ ሊሰጠው እንደሚገባ የሚደነግግ ሲሆን የሃገራችን ሠራተኛ እና አሰሪ አዋጅ ቁጥር 1158/2011 አንቀጽ 11 መሠረት የሙከራ ጊዜ አንድ ሰው በስራ ውሉ መሠረት ሊመደብበት ለታቀደው ቦታ ተስማሚ መሆኑን ለመመዘን የሚደረግ ነው፡፡ የሙከራ ጊዜው ስምምነት በፅሁፍ መደረግ ሲኖርበት ከ60 ተከታታይ ቀናት ሊበልጥ አይችልም፡፡ በተመሳሳይ ቀጣሪ ለተመሳሳይ ሥራ የተቀጠረ ሠራተኛ ከአመክሮ (የሙከራ ጊዜ) ነፃ ነው፡፡ የአመክሮ ተቀጣሪዎች ከሌሎች ተቀጣሪዎች ጋር ተመሳሳይ መብቶች እና ግዴታዎች አሏቸው፡፡  በተጨማሪ የሥራ ቅጥር መቋረጥ ስምምነት ቁጥር 158 አዲስ የተቀጠረ ሰራተኛ ያለምንም መጥፎ ተከታይ ሁኔታዎች በሙከራ ጊዜ ውስጥ ሊባረር እንደሚችል ሲያስቀምጥ የሃገራችን ሠራተኛ እና አሰሪ አዋጅ ቁጥር 1158/2011 ከላ በተጠቀሰው አንቀጽ አንድ ሠራተኛ በአመክሮው ወቅት ለሥራው ተስማሚ ሳይሆን ከቀረ አሠሪው ያለምንም ማስጠንቀቂያና ምንም ዓይነት የጥቅማ ጥቅም ወይም
Mostrar todo...
የኢትዮጵያ ህግ /Ethiopian Law/

ዳንኤል ፍቃዱ ተስፋዬ በሁሉም የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጠበቃና የህግ አማካሪ ስልክ - 0913158507 ወይም 0978554559 Daniel Fikadu Tesfaye Certified Attorney of law at all Federal Courts of Ethiopia. Email- nurotekore@gmail. Com ⚖️⚖️Ethiopian Law by Daniel Fikadu channel ⚖️⚖️⚖️

👍 3