es
Feedback
ጤናዎ በእጅዎ /Your Health on your Hands❤/

ጤናዎ በእጅዎ /Your Health on your Hands❤/

Ir al canal en Telegram
7 531
Suscriptores
-424 horas
-427 días
-18930 días
Archivo de publicaciones
#የህፃናት_የእምብርቱ_ጉቶ_እብጠት (umbilical Hernia) ========= 👉 ወላጆች በጉጉት ከሚጠብቋቸው የመጀመሪያ ምእራፎች ውስጥ አንዱ የልጃቸውን እምብርት መዳን ነው። 👉 ከሳምንት ወይም ከሁለት ሳምንት እንክብካቤ በኋላ የእምብርቱ ጉቶ (umbilical Cord) በትክክል መድረቁን ፣ ኢንፌክሽኑ አለመኖሩን ፣ እምብርቱ ጉቶ (Cord) መውደቁን መከታተል ይኖርባቸዋል። 👉 በየጊዜው ያ የሆድ ዕቃ ክፍል ወይም እምብርት ሲሰፋ ወይም ሲወጠር አንዱ የወላጆች የጭንቀት መንስኤ ሊሆን ይችላል። 👉 አንድ ሕፃን በማህፀን ውስጥ በሚኖርበት ጊዜ ከሚከሰተው መደበኛ እድገት አንዱ የሆድ ጡንቻዎች ከእምብርት በታች መዘጋት ሲሆን ይህም የእምብርት ቀለበት በመባል ይታወቃል። 👉 አንዳንድ ጊዜ ጡንቻዎቹ ሙሉ በሙሉ አይሰበሰቡም ወይም አይዘጋም እናም ትንሽ ቀዳዳ ይቀራል። 👉 ከተወለደ በኋላ አንጀቶቹ በክፍተቱ በኩል አበጥ ብለው ሊታዩ ይችላሉ። ☑️ይህም የእምብርት እብጠት Umbilical Hernia ይባላል። 👉 የእምብርት እብጠት አዲስ በተወለዱ ሕፃናት እና ከስድስት ወር በታች ለሆኑ ሕፃናት የተለመዱ ናቸው። #የእምብርት_እብጠት (umbilical hernia) #ምልክቶች ☑️ህፃኑ ሲያለቅስ ፣ ሲያስል ወይም ሲወጠር ፣ በሆዱ ላይ ባለው ግፊት መጨመር ምክንያት ቦታው እየሰፋ እና እየጠነከረ መሔድ። ☑️ በተለመደው ሁኔታ ወይም ተያያዥ ችግር ከሌለው ሲነካካ ምንም የህመም ስሜት የለውም። #ህክምናው: 👉 ብዙ ጊዜ (80% የሚሆነው) በራሱ ይዘጋል። 👉 ብዙውን ጊዜ በሶስት ወይም በአራት አመት እድሜ ይዘጋል። 👉 ያ ካልሆነ ፣ ወይም እብጠቱ ከታሰረ (በእጅ ወደ ኋላ መመለስ ካልቻለ) ወይም ታንቆ ከሆነ(የአንጀት የደም አቅርቦትን ሲያቋርጥ) ለመጠገን ቀዶ ጥገና ይደረጋል። 👉 ቀዶ ጥገናው በጣም ከተለመዱት እና ቀላል የሕፃናት ቀዶ ጥገና ዓይነቶች አንዱ ነው። ለማጠቃለል: ☑️ በከፍተኛ እብጠቱ ከጨመረ፣ ☑️ ቀለም ከቀየረ ☑️ ሲነካ በጣም የህመም ስሜት ካሳየ ☑️ ማስታወክ ካለ ወይም ☑️ ሆድ ቁርጠት ካጋጠመው ወዲያውኑ ወደ ድንገተኛ ክፍል ይሂዱ። ‼️ አለበለዚያ የእብጠቱን መቀነስ ፣ መጥፈት ለማረጋገጥ ለመደበኛ ክትትል የሕፃናት ቀዶ ህክምና ሐኪም ጋር መከታተል ይችላሉ። ዶ/ር ሳለአምላክ ጥጋቤ: Pediatric Surgeon ለብዙዎች እንድደርስ በቀናነት #ሸር ያድርጉት!!! ለተጨማሪ መረጃ ጤናዎ በእጅዎን Like ያድርጉ፡ ከዚህ በተጨማሪ በቴሌግራም ቻናላችን በዚህ ሊንካችን ገብተው https://t.me/ba051219 ያገኙናል፡፡

#የህጻናት_አጥንት_መለስለስ - Rickets👶🦴 [#ወላጆች #ሊያነቡት #የሚገባ] ======= ሪኬትስ በቫይታሚን ዲ እጥረት ምክንያት የህጻናት አጥንትን ጥንካሬ የሚቀንስ በሽታ ነው። ቫይታሚን ዲ ከጸሃይ ብርሃን እና ከምግብ የሚገኝ ሲሆን ለህጻናት የአጥንት ጥንካሬ እና እድገት ትልቅ ድርሻ አለው። #ሪኬትስ #በምን #ምክንያት #ይመጣል❓ 1. በቂ የጸሃይ ብርሃን አለማግኘት እና ልጆችን በተገቢው ሁኔታ እና በትክክል ጸሃይ አለማሞቅ 🔆 2. ቫይታሚን ዲ እና ካልሺየም ያላቸውን ምግቦች በበቂ ሁኔታ አለመመገብ🍲 3. የአንጀት ፣ የጉበት እና የኩላሊት ህመሞች ምልክቶቹ ምንድን ናቸው? 🔹የጉልበት መጣመም(ብራኬት ፣ የጉልበት መነካካት) 🔹የእድገት መቀንጨር 🔹የአጥንት ህመም 🔹የግንባር አጥንት መተለቅ 🔹ጥርስ ለመውጣት መዘግየት🦷 🔹ለመዳህ እና ቆሞ ለመሄድ መዘግየት 🔹ድካም 🔹የአጥንት መሰበር እንዲሁም የጀርባ አጥንት መጣመም ሊከሰት ይችላል። ህጻናት ሪኬትስ (የህጻናት አጥንት መለስለስ) እንዳላቸው እንዴት ማወቅ ይቻላል?🔎 🔸ሃኪሙ የህጻኑ አጥንት ላይ በሚያድርገው ምርመራ 🔸የደም ምርመራ💉 🔸የአጥንት ራጅ ምርመራ #ህክምናው #እንዴት #ነው?👩‍⚕️ 👉በሃኪም የሚታዘዙ መድሃኒቶች 💊በህጻኑ አጥንት ውስጥ እጥረት ያላቸውን እንደ ካልሺየም እና ቫይታሚን ዲ ያሉ ንጥረ ነገሮች በሂደት እንዲስተካከል ያደርጋል። በዚህም የአጥንቱ ጥንካሬ እየጨመረ ይሄዳል። 👉የከፋ የአጥንት ምጣመም እና መሰበር ከተከሰተ የቀዶ ህክምና ሊያስፈልግ ይችላል። የሪኬትስ በሽታን መከላከል ይቻላል? ✔️ህጻናት ጤናማ አጥንት ኖሯቸው እንዲያድጉ ጸሃይ ማሞቅ ( ምንም ቅባት ሳይቀቡ ፣ ከ 4 እስከ 7 ሰአት ፣ ከ20 – 30 ደቂቃ ያህል እርቃናቸውን መሞቅ አለባቸው)🌞 ✔️ልጆች በክረምት ከሆነ የተወለዱት እና የእናት ጡት ብቻ እሚጠቡ ከሆነ ተጨማሪ ቫይታሚን ዲ ያስፈልጋቸዋል🌧 ✔️በቂ ቫይታሚን ዲ እና ካልሺየም ያላቸውን ምግቦች እንደ ወተት🥛 እና የወተት ተዋፅኦ ፣ አሳ ፣ የአሳ ዘይት ፣እንቁላል🥚 እና የመሳሰሉትን መመገብ ያስፈልጋል ለሁሉም ወላጆች 👨‍👩‍👧‍👦 ይህ 👁️‍🗨️ መረጃ ይደርስ ዘንድ share ያድርጉት አዘጋጅ ፦ዶ/ር ናርዶስ ወርቁ : የህጻናት አጥንት ቀዶ ህክምና ሰብ-ስፔሻሊስት #በቅንነት #ሸር #አድርገው #ለሌሎችም #ያድርሱ፡፡ ጤና ነክ እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል፡ ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100076171566897 ቴሌግራም https://t.me/ba051219

#መካንነት /#Infertility/ #ምንድን_ነው? ====== ✔️መካንነት ማለት ከ12 ወራት (ለ35 ዓመት በታች ለሆኑት) ወይም ከ6 ወራት (ለ35 ዓመት በላይ ለሆኑት) መደበኛ እና ያለመከላከያ ግንኙነት በኋላ እርግዝና መፈጠር አለመቻል ነው። እንዲሁም ተደጋጋሚ ፅንስ መጨንገፍን ሊያካትት ይችላል። በዓለም ላይ ከ6 ጥንዶች ውስጥ አንዳቸው ይህ ያጋጥማቸዋል። እርስዎም እየታገሉ ከሆነ ብቻዎን አይደሉም ። ✅ #ለምን_ይከሰታል? ===== ☑️ #ሴቶች_ላይ_የሚታይ_የመካንነት_ምክንያቶች_ምንድን-ናቸው? ===== ✅ የሆርሞን መዛባት ችግሮች ✅ የኦቩሌሽን ችግሮች ✅ የፋሎፒያን ትቦ ችግሮች (በኢንፌክሽን ወይም በእጢዎች ምክንያት) ✅ ኢንዶመትሮሲስ ወይም ✅ የእንቁላል ጥራት መቀነስ ሴቶች ላይ የመካንነት ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ። ☑️ #ወንዶች_ላይ_የሚታይ_የመካንነት_ምክንያቶች_ምንድን_ናቸው? ===== ✅ የወንድ ዘር መጠን መቀነስ ✅ የሆርሞን መዛባት ችግሮች ✅ የዘር ፍሬ ደምስር እብጠቶች ✅ ያልወረደ የዘር ፍሬ፣የዘር ፍሬ ኢንፌክሽኖች ወይም አደጋዎች የወንድ መካንነትን ሊያመጡ ይችላሉ። ለመካንነት ከሚያጋልጡ ነገሮች መካከል የአኗኗር ዘይቤም ተጽዕኖ አለው—ጭንቀት ፣ ማጨስ፣ ከመጠን በላይ አልኮል ወይም በአከባቢያችን ላይ የሚገኙ መርዛማ ንጥረ-ነገሮች እንደ አጋላጭ ሁኔታዎች ይጠቀሳሉ። ☑️ #መቼ_ወደ_ህክምና_መሄድ_ያስፈልጋል? ✅ ለአመት ለመውለድ ተሞክሮ እርግዝና ካልተፈጠረ (ለ35 አመት በላይ ሴቶች ለ 6 ወር ከተሞከረ) ✅ የወር አበባ መዛባት ወይም የወር አበባ ከሌለ ወይም ✅ ከዚህ በፊት የታወቀ የወሊድ አካላት ችግር ክነበረ ወደ ህክምና መሄድ ያስፈልጋል። ✅ #የህክምና_አማራጮቹ መካንነት ህክምናው እንደ ምክንያቶቹ ይለያያል። ከመድሃኒት ህክምና ጀምሮ እስከ ዘመኑ ያፈራቸው የተራቀቁ እና ውጤታማ ህክምናዎች IVF ፣ IUI ፣ የእንቁላል ወይም የወንድ ዘር ፍሬ ማቆየት የመሳሰሉ ህክምናዎች አሉት።

#የወር አበባ ህመምን ለመቀነስ እና ዑደት እንዲስተካከል የሚረዱ በቤት ውስጥ በቀላሉ የሚዘጋጁ መጠጦች አሉ። እነዚህ መጠጦች የጡንቻ መኮማተርን በመቀነስ እና የደም ዝውውርን በማሻሻል ከፍተኛ እገዛ ያደርጋሉ። 1 #የዝንጅብል ሻይ (Ginger Tea) ዝንጅብል የወር አበባ ህመምን በመቀነስ ረገድ በጣም ውጤታማ ነው። በውስጡ የሚገኙት ንጥረ ነገሮች እንደ ማስታገሻነት ያገለግላሉ። #አዘገጃጀት፡** ትኩስ ዝንጅብል ቀቅለው ጥቂት ማር እና ሎሚ በመጨመር በቀን 2-3 ጊዜ ይጠጡ። 2 #የቀረፋ ሻይ (Cinnamon Tea) ቀረፋ የደም መፍሰስን ለማስተካከል እና የማህፀን መኮማተርን (Cramp) ለመቀነስ ይረዳል። አዘገጃጀት፡** ግማሽ የሻይ ማንኪያ የቀረፋ ዱቄት በአንድ ብርጭቆ የፈላ ውሃ ውስጥ በጥብጥው ለ 10 ደቂቃ አቆይተው ይጠጡ። 3. #የእርድ መጠጥ (Turmeric Milk/Tea) እርድ በሰውነት ውስጥ ያሉ ቁስለቶችን እና ህመሞችን የመቀነስ ከፍተኛ አቅም አለው። በተጨማሪም የሆርሞን መዛባትን ለማስተካከል ይረዳል። #አዘገጃጀት፡** በሙቅ ወተት ወይም በውሃ ውስጥ ግማሽ የሻይ ማንኪያ እርድ እና ጥቂት ጥቁር አዝሙድ (ለመምጠጥ እንዲረዳ) ጨምረው ይጠጡ። 4. #የፔፐርሚንት (የናና) ሻይ ናና በማህፀን አካባቢ ያሉ ጡንቻዎች እንዲዝናኑ በማድረግ የሆድ ቁርጠትን ያስታግሳል። #አዘገጃጀት፡** ትኩስ ወይም የደረቀ ናናን በፈላ ውሃ ዘፍዝፈው መጠጣት። #ተጨማሪ ጠቃሚ ምክሮች፡ ሙቅ ውሃ መጠጣት፡** በቂ ውሃ መጠጣት በሰውነት ውስጥ ፈሳሽ እንዳይከማች እና የሆድ መነፋትን ለመቀነስ ይረዳል። ሙቅ ውሃ መያዣ (Hot Water Bag)፦** በታችኛው የሆድ ክፍል ላይ ሙቅ ውሃ መያዣ ማድረግ ህመምን በፍጥነት ያስታግሳል። #ከፍተኛ ጨውና ስኳር መቀነስ፦** የወር አበባ በሚመጣበት ወቅት ጨውና ስኳር የበዛባቸውን ምግቦች መቀነስ መቆጣትን (Inflammation) ይቀንሳል። #ማሳሰቢያ፦** ህመሙ በጣም ከፍተኛ ከሆነ፣ መደበኛ ያልሆነ የደም መፍሰስ ካጋጠመዎት ወይም ዑደትዎ በጣም የሚዛባ ከሆነ የጤና ባለሙያ ማማከር አስፈላጊ ነው። #ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በኮመንት ሥር ባለው ሊንክ ተጫኑ

#ምልክቶቹ ==== ✍ የእግር ማበጥ ✍ የእግር ህመም ✍ የእግር መቅላት ወይም መጥቆር ✍የእግር መሞቅ ምልክት ላያሳይ ይችላል #የሚያስከትለው_የጤና_ችግር ===== ★የረጋው ደም በደም ሶር ተጉዞ ወደ ሳንባ የመሄድና ቱቦ ዘግቶ በሳምባ ውስጥ አየርና ፈሳሽ እንድጠራቀም ምክናየት ሊሆን ይችላል። ይህ ደግሞ አደገኛ የጤና ችግር ነው። በደቂቃዎች ውስጥ ሞት ሊያስከትል ይችላል፡፡ ምልክቶቹም የሚከተሉት ናቸው። ✔ድንገተኛ የትንፋሽ ማጠር ✔ፈጣን የልብ ምት ✔ ቀለል ያለ የራስ ምታት ✔ ደም የቀላቀለበት አክታና ሳል ናቸው። #ይበልጥ_ተጋላጭ_የሆኑት_እነማን_ናቸው? ====== ❖በቤተሰብ ደም የመርጋት አጋጣሚ ያለበት ❖ ለብዙ ጊዜ የአልጋ ቁራኛ የሆነና ፓራላይዝድ የሆነ ሰው ❖ቀዶ ጥገና የተሰራለት ከቀዶ ጥገና በሗላ ❖ እርጉዝና ከወሊድ በኋላ ❖ በአፍ የሚወሰድ ወሊድ መከላከያ ❖ የሚያጨሱ ❖ የካንሰር ተጠቂዎች ❖ የልብ ችግር ያለባቸው ❖እድሚያቸው ከፍ ያለ ሰዎች ለረጅም ጊዜ የሚቆሙና የሚቀመጡ #መከላከያ_መንገዶች ===== ♦ብዙ ሰአት አለመቀመጥ፡ አለመተኛትና አለመቆም ♦የአኗኗር ዘይቤን መቀየር(ስፖርታዊ እንቅስቄሴ) ♦ ክብደት መቀነስ ♦ ሲጋራ ማጨስ ማስወገድ ♦ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ #ህክምናው ==== ✍ችግሩ እንደተከሰተ በአስቸኳይ ሀኪም ቤት በመሄድ የደም ማቅጠኛ መድሀኒቶችን መውሰድ፡፡ ✍ማሸትም ሆነ ማንኛውንም የባህል መድሀኒት መውሰድ አይመከርም፡፡ ምንጮች 1.Healthline 2.Myoclinic 3.Mediscape #በቅንነት_ሸር_አድርገው_ለሌሎችም_ያድርሱ፡፡ ጤና ነክ  እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል፡ ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100076171566897 ቴሌግራም https://t.me/ba051219

#ደም_መርጋት(Deep vein thrombosis:DVT) ====== ★ አንድ ሰው በሰውነቱ ውስጥ ከ5-7 ሊትር የሚሆን ደም አለው። ደም ፈሳሽ መሳይ የሰውነት ክፍል ሲሆን የለምንም ማቋረጥ በደም ቱቦ
#ደም_መርጋት(Deep vein thrombosis:DVT) ====== ★ አንድ ሰው በሰውነቱ ውስጥ ከ5-7 ሊትር የሚሆን ደም አለው። ደም ፈሳሽ መሳይ የሰውነት ክፍል ሲሆን የለምንም ማቋረጥ በደም ቱቦ ውስጥ በመላ ሰውነት የሚሽከረከር ወይም የሚዘዋወር ነው። ደም ለደቂቃዎች እንቅስቃሴውን ቢያቋም ወደ ጠጣርነት ባህሪው በመቀየር ይረጋል። ምክናየቱም ደም 45%ቱ ጠጣር ሲሆን 55%ቱ ደግሞ ውሀ ነው። #ደም #መርጋት #ስንል ግን በሰውነታችን ውስጥ በሚገኝ በአንድ ወይም ከዚያ በላይ በሆነ ደም መላሽ ውስጥ የደም መጎጎል ወይም መርጋት ሲያጋጥም ወይም የደም መርጋት ችግር(DVT) ይባላል። ብዙ ጊዜ በእግር አካባቢ ይከሰታል። #ምክንያቶቹ ===== ✍የተለያዩ የጤና ችግሮች(ካንሰር ታማሚዎች) ✍ለረጅም ጊዜ አለመቀሳቀስ ✍ለረጅም ጊዜ መቆም መቀመጥ ✍እርግዝና ወይም ከወሊድ በሇላ ከ6ሳምንት እስከ 3ወር ድረስ

✍የሚከተለው መረጃ ከወር አበባ በኋላ እርግዝና የሚፈጠርባቸውን ቀኖች የሚያሳይ ሲሆን መሰረት ያደረገው በየ 28 ቀን የወር አበባዋን ለምታይ ሴት ብቻ ነው፡፡ #ለምሳሌ፡ አንድት እናት ሀምሌ 1 የወር አበባዋ ጀምሮ ሀምሌ 5 ድረስ ቢፈስ እና ሀምሌ 6 ላይ ቢቆም(ብታጥብ) 1,ከሀምሌ 1-5 (የወር አበባ ከፈሰሰበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ እስከ አምስተኛው ቀን)        = የወር አበባ መፍሰሻ ጊዜ ነው፡፡ (Menstrual Bleeding) 2,ከሀምሌ 6-9 = በንጽጽር እርግዝና የማይፈጠርበት ጊዜ ነው፡፡ (Relatively Infertile) 3, ከሀምሌ 10-12 = በንጽጽር በነዚህ ቀኖች እርግዝና ሊፈጠር ይችላል፡፡ (Relatively Fertile) 4, ከሀምሌ 13-15 = በነዚህ ቀኖች  እርግዝና የመፈጠር እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ (Most Fertile) 5 ,ከሀምሌ16-19 = በንጽጽር በነዚህ ቀኖች እርግዝና ሊፈጠር ይችላል፡፡ (Relatively Fertile) 6, ከሀምሌ 20-28 = በነዚህ ቀኖች እርግዝና አይፈጠርም፡፡ (Infertile) #ሲጠቃለል: ይህች እናት የማርገዝ እድል ያላት ከሀምሌ 10 - 19 ባሉት ቀናት ውስጥ ሲሆን ከሀምሌ 13-15(በአማካይ 14)ባሉት ቀናት ግን የማርገዝ እድሏ በጣምም ሰፊ ነው፡፡ ⚡️ማስታወሻ ✍የወንድ የዘር ፍሬ ከግብረ ሥጋ ግንኙነት በኋላ በሴት ሰውነት ውስጥ ከሶስት (3) እስከ አምስት (5) ቀናቶች መቆየት ይችላል። ✍የሴቶች ዕንቁላል ደግሞ ለተጨማሪ ቀናቶች ሊቆዩ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ሊያረግዙባቸው የሚችሉ ከ አምስት(5) እስከ ሰባት (7) የሚደርሱ ቀኖች አሉ ማለት ነው፡፡ #በቅንነት #ሸር #አድርገው #ለሌሎችም #ያድርሱ፡፡ ጤና ነክ  እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል፡ ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100076171566897 ቴሌግራም https://t.me/ba051219 ስለ ጤናዎ ምን ያውቃሉ ጠቅላላ እውቀትGeneral knowledge ethiohaki

#የወር_አበባዬን_ተከታትዬ_እርግዝና_ሊፈጠር_የሚችልባቸውን_ቀኖች_እንዴት_አውቃለሁ???? ========= (#በውስጥ #መስመር #በተደጋጋሚ #የሚጠየቅ #ጥያቄ) ✍በትክክል እርግዝና ሊፈጠርበት የሚችሉት
#የወር_አበባዬን_ተከታትዬ_እርግዝና_ሊፈጠር_የሚችልባቸውን_ቀኖች_እንዴት_አውቃለሁ???? ========= (#በውስጥ #መስመር #በተደጋጋሚ #የሚጠየቅ #ጥያቄ) ✍በትክክል እርግዝና ሊፈጠርበት የሚችሉት ቀናቶች ኦቪውሌሽን በሚከናወንበት ቀናቶች ናቸው፡፡ ✍ኦቪውሌሽን የምንለዉ ያደገ ከእንቁላል ከረጢት ወይም ከእንቁልጢ(Ovary) የሚለቀቅበትን ጊዜ ነዉ፡፡ ✍ኦቪውሌሽን (Ovulation) የሚከሰትበት ቀን አንዲት ሴት ልጅ የወር አበባ ካየችበት #የመጀመሪያ #ቀን ጀምሮ በመቁጠር በ14ኛው ቀን አካባቢ ይከሰታል፡፡

በኬሚካል የታከሙ የፀጉር ማስረዘሚያዎችን ደኅንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ለመጠቀም የተረጋገጠ መንገድ የለም። ተጋላጭነትን ለመቀነስ የሚታሰቡ እርምጃዎች ቢሆኑም አስተማማኝ ላይሆኑ ይችላሉ ሲል ጥናቱ አመልክቷል። ፀጉር ላይ ከመቀጠሉ በፊት ማጠብ ለምሳሌ የቆዳ መቆጣትን ለመቀነስ በኮምጣጤ ማጠብን ጨምሮ ደኅንነት ስለማረጋገጡ ምንም ተጨባጭ መረጃ የለም። በጥናቱ ውስጥ ፍተሻ ከተደረገባቸው 43 ናሙናዎች ውስጥ ሁለቱ ብቻ ሳይንቲስቶች ከለዩዋቸው አደገኛ ኬሚካሎች የፀዱ ሆነው ተገኝተዋል። ሁለቱም "መርዛማ ያልሆኑ" ወይም "ከመርዛማ ነገር ነጻ የሆኑ" ተብለው ተለይተዋል። ነገር ግን ፍራንክሊን እንዲህ ያሉት መግለጫዎች የተሳሳተ ማረጋገጫ ሊሰጡ እንደሚችሉ ተናግረዋል። "እነዚህ መግለጫዎች በማንኛውም አካል ቁጥጥር ስር አይደሉም፤ ስለዚህ ኩባንያዎች ምርቱ ላይ ሊለጥፉት ስለሚችሉ ምንም ዓይነት ተጠያቂነት አይኖርም።" በዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ጎጂ የሆኑ ካንሰር የሚያስከትሉ ንጥረ ነገሮችን በተመለከተ አዳዲስ ጥብቅ ሕጎች በነሐሴ 2026 ተግባራዊ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል። ነገር ግን የፀጉር ባለሙያዎች እንደሚሉት የፀጉር ማስረዘሚያዎችን በመቆጣጠር ረገድ ያለው ክፍተት ሸማቾች ሙሉ በሙሉ ጥበቃ አያገኙም ማለት መሆኑን ያስጠነቅቃሉ። ኮስሞቲክስ ጥብቅ ቁጥጥር የሚደረግባቸው እና የደኅንነት ፍተሻዎች የሚካሄድባቸው ናቸው። ነገር ግን የፀጉር ማስረዘሚያዎች በአብዛኛው በተለየ መንገድ ስለሚመደቡ ፍተሻ አይካሄድባቸውም። ቀደም ባሉት ጥናቶች የፀጉር ማቅለሚያዎች እና ማለስለሻዎች ለጡት ካንሰር እንደሚያጋልጡ ተለይተዋል። ሆኖም ግን ከፀጉር ማስራዘሚያዎች በተለየ መልኩ እነዚህ ምርቶች እንደ መዋቢያ ምርቶች ቁጥጥር የሚደረግባቸው እና የደኅንነት ፍተሻዎች የሚካሄድባቸው ናቸው። የዩኬ ብሔራዊ የፀጉር እና የውበት ፌዴሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ካሮላይን ላሪሴይ "ደንቡ የሚሠራው ምርቶች በትክክል ከተመደቡ እና ወደ አገር በሚገቡበት እና በሚሸጡበት ቦታ ላይ ተግባራዊ ከተደረጉ ብቻ ነው" ይላሉ። "ይህ እውነተኛ ክፍተት ነው፣ እናም ይህ ጥናት መፍትሄ እንደሚያስፈልገው ግልጽ አድርጓል።" በአውሮፓውኑ 2016 ቢቢሲ ባደረገው ምርመራ ብዙ የተሳሳቱ መግለጫዎች የተለጠፈባቸው የሰው ሠራሽ ፀጉሮችን አግኝቷል። አንዳንድ አምራቾች በድረ ገጾቻቸው ላይ ሸማቾች ከመግዛታቸው በፊት የፀጉሩን ጥራት እንዲፈትሹ ያስጠነቅቃሉ። ነገር ግን ሳይንቲስቶች ይህ የእነሱ ኃላፊነት መሆን የለበትም ይላሉ። ፍራንክሊን "ገበያ ላይ ባይቀርቡ ኖሮ፣ መቼም ቢሆን መምረጥ አይጠበቅብንም ነበር" ሲሉ ይሞግታሉ። "ዊግ ወይንም ሂውማን ሄር የሚጠቀም ማንኛውም ሰው ስለ ግኝቶቹ ግድ ሊለው ይገባል።"

ዊግ እና 'ሂውማን ሄር' ከጡት ካንሰር እና ከሌሎች የጤና ችግሮች ጋር የሚገናኙ ኬሚካሎች ተገኙባቸው በመላው ዓለም ሚሊዮኖች የሚጠቀሙበት ፀጉር ላይ የሚቀጠለው ዊግ እና ሂውማን ሄር ከጡት ካንሰር፣ ከሆርሞን መዛባት እንዲሁም በሥነ ተዋልዶ ጤና ጉዳት የሚያደርሱ ኬሚካሎችን መያዛቸውን ጥናቶች አሳዩ። በዓይነቱ ለየት ያለ እና በስፋት የተደረገ ጥናት ነው በተባለው በዚህ ምርምር ሳይንቲስቶች ዊጎቹ ላይ 50 ጎጂ ኬሚካሎችን አግኝተውባቸዋል። እነዚህ ኬሚካሎች ፀጉር ላይ የሚቀጠሉ፣ የሚጠለቁ እንዲሁም የሚሰፉ ዊጎች እና ሂውማን ሄር ላይ በሙሉ መገኘታቸውን ተመራማሪዎቹ ይፋ አድርገዋል። የምርምር ውጤቱ በአሜሪካን ኬሚካል ሶሳይቲ ጆርናል ላይ የታተመ ሲሆን፣ በዚህ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር በሚንቀሳቀስበት ኢንዱስትሪ ላይ ጠንካራ የቁጥጥር ሥርዓት አና ለተጠቃሚዎች የተሻለ ግልጽነት እንዲኖር ጥሪ አቅርቧል። ጥናቱን ያካሄዱት ዶ/ር ኢሊሺያ ፍራንክሊን "ከአንዳንድ አደገኛ ኬሚካሎች የፀዱ ምርቶችን ለመፍጠር እና ለማምረት ምንም ዓይነት መስፈርት የሌላቸውን ኩባንያዎች እንዳሉ እንተማመናለን" ብለዋል። ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ዊጎች ሌሎች የሚጠለቁ ፀጉሮች ለረጅም ጊዜ ስለሚደረጉ እና ከቆዳ ጋር በቅርበት ስለሚገናኙ የተለየ አደጋን ያስከትላሉ። ይህ ሥር የሰደደ ተጋላጭነት የረጅም ጊዜ የጤና አደጋዎችን ሊያስከትል ይችላል። "የፀጉር ማስራዘሚያዎች (ዊጎች) ለቆዳ በጣም በቅርበት ይደረጋሉ" የሚሉት ፍራንክሊን ከዚህም በተጨማሪ "በአንድ ሰው ጭንቅላት እና አንገት ጋር ለብዙ ሳምንታት ወይም ለወራት የሚቆይ ንክኪ ይኖራቸዋል" በማለት ያለውን አደጋ ለማሳየት ያብራራሉ። #አደገኛ_ኬሚካሎች ==== ዓለም አቀፉ የዊግ ገበያ በአውሮፓውያኑ 2028 ከ14 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ እንደሚያንቀሳቅስ ተገምቷል። ብዙ ሴቶች ለመዋቢያ ወይም ለፋሽን በሚል ፀጉር ላይ የሚቀጥሏቸውን ዊጎች እና የሚያጠልቋቸው ፀጉሮችን የሚመርጡ ቢሆንም ከፍተኛ ቁጥር የሚይዙት ግን ጥቁሮች መሆናቸውን ጥናቱ አመልክቷል። ሰው ሠራሽ ፀጉር እስከ 20 ዶላር ብቻ ሊያወጣ ይችላል። ከፍተኛ ጥራት ያለው የሰው ፀጉር (ሂውማን ሄር) ደግሞ በሺዎች የሚቆጠር የአሜሪካ ዶላር ሊያወጣ ይችላል። ሳይንቲስቶች ፍተሻ ባካሄዱባቸው 43 ናሙናዎች ውስጥ 170 ኬሚካሎችን አግኝተዋል። ተመራማሪዎቹ አንድ ነጠላ ንጥረ ነገር ላይ ከማተኮር ይልቅ የተለያዩ ኬሚካሎችን ለመለየት የሚያስችል ዘዴን መጠቀማቸው ተገልጿል። ከእነዚህ ውስጥ 48ቱ በተባበሩት መንግሥታት እና በአውሮፓ የኬሚካል ተቋማት "አደገኛ" በሚል ዝርዝር ውስጥ የገቡ ናቸው። ፍራንክሊን "የእሳት ተቀጣጣይነትን ለመቀነስ ከሚረዱ እስከ ፀረ-ተባይ መድኃኒቶች፣ ሆርሞንን ከሚያዛቡት እና የሥነ ተዋልዶ ጤና ጉዳት እንደሚያደርሱ እስከታወቁት የፕላስቲክን ዕድሜ ለማራዘም ጥቅም ላይ አስከሚውሉ (phthalates) ድረስ ተገኝተዋል" ብለዋል። በ36 የዊግ ናሙናዎች፤ ሰው ሠራሽም ሆነ ሂውማን ሄር ውስጥ ከጡት ካንሰር ጋር የተያያዙ አስራ ሰባት ኬሚካሎች ተገኝተዋል። ከናሙናዎቹ ውስጥ ወደ 10 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ እሳትን የሚቋቋሙ ፕላስቲኮችን ለመሥራት የሚያገለግሉ አደገኛ የኦርጋኖቲን ውህዶችን (organotin compounds) ይዘዋል። ሳይንቲስቶች በተለምዶ በሸማቾች ምርቶች ውስጥ የማይገኙ ኦርጋኖቲን የተባሉ አደገኛ ውህዶችን በማግኘታቸው ተገርመዋል። እነዚህ ኬሚካሎች ከቆዳ መቆጣት ጋር የተያያዙ ሲሆኑ፣ የሆርሞን መዛባትን እንደሚያስከትሉ ይታወቃል። ይህም ማለት በሰውነት ውስጥ ያሉ ብዙ ሂደቶችን የሚቆጣጠሩ ሆርሞኖችን ያውካሉ፤ ይህም ከወሊድ እና ከእድገት ጋር የተያያዙ ሆርሞኖችን ያካትታል። በናሙናዎቹ ውስጥ በብዛት ከተገኙት ኬሚካሎች መካከል ስስ ጣውላ እና ሌሎች የእንጨት ማጣበቂያዎችን ለመሥራት የሚያገለግል ፌኖል (phenol) እና ፕላስቲኮችን የበለጠ ተጣጣፊ ለማድረግ የሚያገለግለው እና ሌሎችም ጉዳትን የሚያስከትሉ ኬሚካሎች ተገኝተውባቸዋል። ተመራማሪዎች እንደሚሉት እነዚህ ኬሚካሎች የጡት ካንሰር አምጪ በመሆን የሚታወቁ ሲሆን፣ በጊዜ ብዛት የጡት ካንሰር የመያዝ ዕድልን ከፍ ያደርጋሉ። 'ሂውማን ሄር' ደኅንነቱ የተጠበቀ ነው? ቀደም ሲል የተደረጉ ጥናቶች በአብዛኛው ትኩረት ያደረጉት በሰው ሠራሽ ፀጉር ላይ ሲሆን፣ አደገኛ ብረቶች መያዛቸውን ደርሰውበታል። ነገር ግን ይህ ጥናት 11 የቨርጂን፣ ሮው እና ከሰው እና ከሰው ሠራሽ ነገሮች ጋር የተደባለቁ ናሙናዎችንም ፈትሿል። ቨርጂን እና ሮው (Virgin and raw) ፀጉሮች ከኬሚካል ነጻ የሆኑ በሚል በጣም በውድ ዋጋ ይሸጣሉ። ሮው የሚባሉት ፀጉሮች በፋብሪካ ውስጥ ያላለፉ እና በቀጥታ ከለጋሽ ላይ የተቆረጡ ወይም የተላጩ ናቸው። ፍተሻ የተደረገባቸው ቨርጂን ወይንም ሮው ተብለው ለገበያ የቀረቡ ሂውማን ሄሮች ከአንዳንድ ሰው ሠራሽ ፀጉሮች የበለጠ አደገኛ ኬሚካሎችን ይዘው ተገኝተዋል። ከእነዚህም ውስጥ ብዙዎቹ የሆርሞን ለውጦችን ወይንም መዛባቶቸን ያስከትላሉ። የጡት ካንሰር መንስኤዎችን የሚያጠኑት የዩኤስ ሳይለንት ስፕሪንግ ኢንስቲትዩት ተመራማሪ ፍራንክሊን "አንድ ምርት ሂውማን ሄር ተብሎ ወይም ከአንድ ግለሰብ የተገኘ 'የተፈጥሮ' መባሉ ብቻ ከሰው ሠራሽ ፀጉር የበለጠ ደኅንነቱ የተጠበቀ አያደርገውም" ይላሉ። "በሰው ሠራሽ ናሙና ውስጥ አደገኛ ተብሎ የተፈረጀ አንድ ኬሚካል ስናገኝ በሂውማን ሄር ውስጥ ግን አደገኛ የተባሉት ኬሚካሎች ብዛት ከአምስት እስከ ሰባት ሊሆኑ ይችላሉ" ሲሉ ገልጸዋል። ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት እነዚህ ኬሚካሎች በፋብሪካ ውስጥ የፀጉሩን ይዘት ለማሳመር፣ ቆይታውን ወይም ነዶውን ለማሻሻል በሚል በሚደረግ የምርት ሂደት ወቅት ሊገቡ ይችላሉ። ጥናቱ የአደገኛ ኬሚካሎችን መጠን ባይገመግምም፣ እንደ ሆርሞን መዛባት ያሉ አንዳንድ ኬሚካሎች በዝቅተኛ መጠን እንኳን ጎጂ ሊሆኑ ይችላሉ ሲሉ ፍራንክሊን ተናግረዋል። ተመራማሪዎቹን ስጋት ካጫሩባቸው ጉዳዮች አንዱ አምራቾች በሚያቀርቧቸው ዊግ ወይንም ሂውማን ሄሮች ውስጥ መኖር ስላለባቸው ኬሚካሎች ግልጽ የሆነ የደኅንነት ገደብ አለመኖሩ ነው። ፍራንክሊን "ለመዋቢያነት በምንጠቀምባቸው ምርቶች ውስጥ አደገኛ ኬሚካሎች ሊኖሩ የማይችሉበት ምንም ምክንያት የለም። በየቀኑ ልናስወግዳቸው ለማንችላቸው ኬሚካሎች ተጋልጠናል" ይላሉ። ብዙ ዊጎች በፈላ ውሃ ውስጥ እንዲሞቁ ወይም እንዲነከሩ ይደረጋሉ፤ ይህም መርዛማ ጭስ እንዲያወጡ ሊያደርግ ይችላል። እነዚህ ኬሚካሎች ወደ ሰውነት ውስጥ በመተንፈሻ አካል በኩል ሊገቡ ይችላሉ። ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት በቆዳ ንክኪ ወደ ሰውነት ውስጥ ሊገቡ ስለሚችሉ ተጠቃሚን ብቻ ሳይሆን አገልግሎቶች የሚሰጡ የፀጉር ባለሙያዎችንም ይጎዳል። አንዳንድ ሰዎች ከሚጠቀሙት ዊግ የተነሳ ማሳከክና መቅላት፣ የራስ ቆዳ፣ አንገትና ፊት ላይ ሽፍታና እብጠት እንዲሁም አልፎ አልፎ የመተንፈሻ አካላት ችግር እንደገጠማቸው ተናግረዋል። ዊግን ወይንም 'ሂውመን ሄር'ን እንዴት መጠቀም የተሻለ ነው?

#ከምጥ_እና_ወሊድ_ጋር_የተያያዘ_ፊስቱላ (Obstetric Fistula) ====== 🔹 #ምንነት (Definition) ===== ፊስቱላ ማለት ሁለት አካላት(ቱቦዎች) ተፈጥሯዊ ባልሆነ መንገድ መገናኘት ማለት ነው ። እንደ ዓለም ጤና ድርጅት(WHO) መረጃ በየዓመቱ ከ50,000_100,000 የሚሆኑ እናቶች ለዚህ ከባድ ችግር ይጋለጣሉ። #ዋና_ዋናዎቹ ===== ☑️ በሽንት ፊኛ(bladder)እና የሴቶች ብልት (vagina) መካከል (Vesicovaginal fistula) ☑️በሽንት ቧንቧ የሴቶች ብልት (vagina) መካከል (Urethrovaginal Fistula) ☑️በታችኛው የአንጀት ክፍል (rectum) እና ሴቶች ብልት (vagina) መካከል (Rectovaginal fistula) 🔹 #መንስኤዎች (Causes) ====== ☑️የተራዘመ እና የተወሳሰበ ምጥ (prolonged/obstructed labor) ☑️በምጥ ወቅት የህክምና እገዛ እጥረት ☑️ ያለ ዕድሜ ጋብቻ እና ወሊድ (early marriage/pregnancy) ☑️ጠባብ የዳሌ እድገት (small pelvis) ☑️ በቂ ልምድ ሳይኖር የምጥ አጋዥ መሳሪያዎችን መጠቀም (instrumental injury) ☑️ስር የሰደደ የማህፀን በር እና የብልት ካንሰር 🔹 (ምልክቶች (Symptoms) ====== 👉ሽንት መቋጠር አለመቻል 👉ሰገራ በብልት ቀዳዳ በኩል መምጣት 👉 ቀጣይት ያለው የብልት እርጥበት (continuous wetness) 👉መጥፎ የብልት ሽታ 👉የብልት ቆዳ መላላጥ እና ቁስለት : 👉 ተደጋጋሚ የሽንት ፊኛ (ቧንቧ)ኢንፌክሽን (recurrent infections) 🔹 #ተፅዕኖዎች (Impacts) ===== 👉የብልት መቁሰል :የቆዳ መላላጥ 👉 ተደጋጋሚ የሽንት ፊኛ (ቧንቧ) ኢንፌክሽን 👉ድባቴ ((ድብርት) (depression)) 👉በቤተሰብ መገለል 👉ስራ ማጣት ወይም ከስራ መቅረት እና መሰናበት 👉ከማህበራዊ ህይወት መገለል 👉የትዳር መፍረስ እና የቤተሰብ መበተን 🔹 #ሕክምና (Treatment) ==== ☑️ቀዶ ሕክምና (Surgical repair) ትልቁ እና ዋነኛው መፍትሄ ነው ☑️ ቀዶ ህክምናው እስከሚከናወን ድረስ በካቴተር (catheterization) ማቆየት የብልት ቆዳ መላላጥ እና ቁስለትን ይከላከላል። #ከቀዶ_ሕክምና_በኋላ: ☑️በባለሙያ የታገዘ የስነ ልቦና ድጋፍ (psychosocial treatment) ማድረግ ☑️ማህበራዊ ህይወትን የመመለስ ግንባታ (rehabilitation) ያስፈልጋል 🔹 #መከላከያ (Prevention) ===== ☑️ ወሊድን ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች ማድረግ (skilled birth attendance) ☑️የቅድመ ወሊድ ክትትል (ANC) ማድረግ ☑️ የተራዘመ ምጥ ሲኖር በጊዜው ሪፈር ማድረግ ☑️ ያለ ዕድሜ ጋብቻ እና ወሊድን መከላከል ☑️ የሴቶችን እና ማህበረሰብን ግንዛቤ በጤና ትምህርት ማዳበር #ምንጮች 1. WHO 2. United Nation population fund 3. Fistula care plus 4.Fistula foundation 5.Hamlin fistula Ethiopia 6.Hamlin fistula UK #በቀናነት #ሸር #አድርገው #ለሌሎችም #ያድርሱ፡፡ ጤና ነክ እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል፡ ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100076171566897 ቴሌግራም https://t.me/ba051219

ጤናዎ በእጅዎ /Your Health on your Hands❤/ - Estadísticas y analítica del canal de Telegram @ba051219