cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ጤናዎ በእጅዎ

Publicaciones publicitarias
5 334
Suscriptores
-224 horas
-197 días
-7630 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ነገር ግን ይህ ክስተት በ12ኛ፣ በ13ኛ ወይም በ14ኛው ቀናት አካባቢ ሊሆንም ይችላል። ይሄኔ የወንድ የዘር ፍሬ በማህፀን ውስጥ የሚገኝ ከሆነ ጽንስ ሊፈጠር ይችላል፡፡ በነገራችን ላይ ይህ እንቁላል ማምረት እንደየሴቶቹም ሊለያይ ይችላል፡፡ አንዳንድ ሴቶች በወር አበባ መካከል ወደ 35 ቀናት አካባቢ ረዘም ያለ ዑደት አላቸው። እንቁላል ማምረት በ21ኛው ቀን አካባቢ ሊከሰት ይችላል፡፡ አጭር የ21 ቀን ዑደት ያላቸው ሴቶች በ7ኛው ቀን አካባቢ እንቁላል ያመርታሉ፡፡ ☑️ አንዲት ሴት በወር አበባዋ ጊዜ እንዴት ማርገዝ ትችላለች? ጉዳዩን ቀለል አድርጎ ለማስረዳት ያክል፣ የብልት መድማትን ልክ እንደወር አበባ የመጀመሪያ ቀን በመቁጠር ልንሳሳትበት የምንችልበት እድል ሰፊ ነው፡፡ ለምን መሰለሽ እንቁላል በሚመረትበት ወቅት አልያም ጽንስ ለመጸነስ ምቹው ጊዜ ላይ መድማት ሊከሰት ይችላል፡፡ ይህን ደግሞ በቀላሉ የወር አበባ ነው በማለት ልንሳሳት እንችላለን፡፡ ታዲያ በዚህ ጊዜ ጥንቃቄ የጎደለው የግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸም የመፀነስ እድልን በእጅጉ ይጨምራል። ሌላው ሊታሰብበት የሚገባው ነገር የወንዱ የዘር ፈሳሽ ከወጣ በኋላ በሴቷ ውስጥ እስከ 72 ሰአታት ውስጥ ሊኖር ይችላል፡፡ ምናልባትም እስከ የወር አበባ መጨረሻ አካባቢ፣ ይህም የመፀነስ እድልን ይጨምራል። ውድ የሰዋስው ቤተሰብ የሆነው ሆኖ ለመፀነስ እየሞከሩ ካልሆነ በስተቀር ወሲብ በሚፈጽሙበት ጊዜ ኮንዶምና በሀኪምዎ የተመረጠልዎትን የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴ መጠቀም አለብዎት። ምንጭ: healthline #በቅንነት #ሸር #አድርገው #ለሌሎችም #ያድርሱ፡፡ ጤና ነክ  እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል፡ ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100076171566897 ቴሌግራም https://t.me/ba051219
Mostrar todo...
ጤናዎ በእጅዎ

ጤናዎ በእጅዎ. 10,947 likes · 280 talking about this. የዚህ ፔጅ ዓላማ የህብረተሰቡን የጤና ግንዛቤ ማሳደግ ነው!!!!

👍 4 2
Photo unavailableShow in Telegram
#በወር #አበባ #ወቅት #ግንኙነት #ብፈጽም #እርግዝና #ይፈጠራል? ====== እንደ ህክምና ባለሙያዎች ምክር ከሆነ፤ ለማርገዝ አየሞከርሽ አልያም እርግዝና እንዳይፈጠር እየተጠነቀቅሽ ከሆነ የወር አበባ ዑደትሽን ትኩረት ሰጥተሸ መከታተል አለብሽ፡፡ ምክንያቱም ይህን ዑደት በትክክል መረዳትሽ ለማርገዝ አልያም ላለማርገዝ ምቹው ወቅት መቼ እንደሆነ ለመረዳት ያስችልሻል፡፡ ታዲያ ከወር አበባ ዑደት ጋር ተያይዞ ያለው ልምድ አንዲት ሴት የወር አበባ እያየች ባለበት ወቅት አታረግዝም የሚል ነው፡፡ በርግጥም የማርገዝ እድሏ እጅግ በጣም ጠባብ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ዜሮ (0) ነው ማለት አይደለም፡፡ ይህን ለመረዳት እስኪ ስለእርግዝና አፈጣጠርና በወር አበባ ወቅት ወሲብ ማድረግ ያላቸውን ግንኙነት እንመልከት፡፡ ☑️ ጽንስ እንዴት ይፈጠራል? በእውነቱ የመፀነስ ችሎታ ተአምራዊ ነው፡፡ የወንድ የዘር ፍሬ ከሴት እንቁላል ጋር መገናኘትን ይጠይቃል፡፡ አንዴ የዳበረው እንቁላል ከተለቀቀ በኋላ ከ12 እስከ 24 ሰዓታት ድረስ መኖር ሲችል የወንድ ዘር በበኩሉ ከብልት ከወጣ በኋላ እስከ 3 ቀናት መኖር ይችላል፡፡ ታዲያ የተለመደው የሴቶች የወር አበባ ዑደት 28 ቀናት ነው፡፡ 1ኛው ቀን የወር አበባዋን ስትጀምር ነው። በ14ኛው ቀን ደግሞ እንቁላል ታመርታለች።
Mostrar todo...
👍 2 2
በፕሮግራሙ ላይ መልክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሌንሳ ቢየና በሴት የቤት ሰራተኞች ላይ እየደረሱ ያሉ የመብት ጥሰቶች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መሆናቸውን አፅንዖት በመስጠት  ይህንን ጉዳይ የሚመለከት የህግ ማዕቀፍ እስከሚዘጋጅ ድረስ ቀጣይ የውትወታ ስራዎች እንደሚያስፈልግ ማሕበራቸውም ቀጣይ ስራዎችን እንደሚገፋበት ገልፀዋል። ሌላኛዋ መልዕክት አስተላላፊ የፓካርድ ፋውንዴሽን አማካሪ ወ/ሮ የምስራች በላይነህ በበኩላቸው የሴት የቤት ሰራተኞች ላይ የሚደርሰው የመብት ጥሰት በአንድ ፊልም ብቻ ተወስቶ የሚያልቅ አለመሆኑን ገልፀው ይልቁንም ይህንን ፊልም ፊልም እንደመነሻ እና እንደ አይን መክፈቻ በመውሰድ ቀጣይ የውትወታ ስራዎች መሰራት እንደለባቸው አሳስበዋል። የኢ,ፌ,ዴ,ሪ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር የሶስትዮሽ ግንኙነት ማስተባበሪያ ዴስክ ኃላፊ አቶ እንዳልክ ተ/ኃዋሪያት በበኩላች መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት የህግ ማዕቀፍ ለማዘጋጀት እየሰራ መሆኑን ገልፀው ለጉዳዩም ተገቢው ትኩረት እንደሚሰጠው ቃል ገብተዋል። የመጨረሻዋ ተናጋሪ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሴቶች፣ ሕጻናት፣ የአካል ጉዳተኞችና አረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ወ/ሮ ርግበ ገ/ሐዋርያት በበኩላቸው  ኪነጥበብ የአንድን ማህበረሰብ አመለካከት ለመቀየር  ትልቅ መሳሪያ መሆኑን አስታውሰው የተለያዩ ባለሙያዎች ከሰብዓዊ መብቶች ጋር ተቀናጅተው የሚሰሩት ስራ ውጤታማ እንደሚሆን በመግለጽ ኢ.ሰ.መ.ኮ የተለያዩ የህግ ማዕቀፎች እንዲወጡ በማድረግ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሚገኝና በቀጣይም ከኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር ጎን በመቆም የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ አረጋግጠዋል፡፡ ደራሲ አዜብ ወርቁ እና ፕሮዲውሰር ቅድስት ይልማ  እንደገለፁት የፊልሙ ዋና ዓላማም የኢትዮጵያም መንግስት ሆነ ሕግ አውጪ አካላት እነዚህን ድንጋጌዎች በፖሊሲም ሆነ ሌሎች የሕግ ማእቀፎች ቀርጸው ውደተግባር እንዲገባ ጫና የሚያሳድር እና ለውጥ እንዲመጣ የሚጎተጉት እንዲሆን ነው። ስለሆነም፣ ብቻውን የቤት ውስጥ ጥቃት እና ሌሎች መሰል ሀሳቦች የሚንሸራሸሩበት ሳይሆን ይህን ለውጥ እንዲያመጣ የህግ ማዕቀፍ እንዲያገኝ  ታስቦ ነው የተዘጋጀው። የህግ ማዕቀፉ ለቤት ሠራተኞቹ ብቻ ሳይሆን ለቀጣሪው፣ ለአስቀጣሪው፣ ለሰሪ እና አሰሪ አገናኝ፡ ለመንግስት፣ ለማሕበረሰቡ. ጥቅሙ ለሁሉም እንደሚሆን ገልፀዋል። በቀጣይም ፊልሙ ከሀምሌ 5 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በአለም ሲኒማ መታየት ይጀምራል።
Mostrar todo...
👍 2
ጀስቲሽያ - (“የፍትህ ሴት”) #Ethiopia | በታዋቂዋ የፊልም ደራሲ አዜብ ወርቁ እና ቅድስት ይልማ ተደርሶ በታዋቂዋ የፊልም አዘጋጅ ቅድስት ይልማ የተዘጋጀ እና በመመክያዬ ለማ ፕሮዲዉሰር የተደረገው ፊልም በሸራተን አዲስ በድምቀት ተመረቀ። ይህ “ጀስቲሽያ” ወይም “የፍትህ ሴት” የተሰኘ ፊልም ለሴት የቤት ውስጥ ሰራተኞች ምቹ የስራ ሁኔታ ለመፍጠር የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ እንዲወጣ ጫና ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ፊልም ሲሆን የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር ከዴቪድ እና ሉሲል ፓካርድ ፋውንዴሽን ጋር አጋርነት በመፍጠር እና ከይሁን ኢንተርቴይንመንት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው። በቤት ውስጥ ሰራተኛ ሴቶች መብት ላይ ያተኮረና የቤት ዉስጥ ጥቃትን መከላከል እና በማህበራዊ ፍትህ ላይ የሚያጠነጥነው ይህ ፊልም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ተወካዮች፣ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶችና የኤምባሲ ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተመርቋል። በፊልሙ ላይ በበርካታ ፊልሞች ላይ አድናቆትን ያተረፈቸው እድለወርቅ ጣሰው፥ አንጋፋዎቹ ድርብ ወርቅ ሰይፉ እና ህሊና ሲሳይ ፥ እና ታዳጊዋ ቢታኒያ መስፍን እንዲሁም ሌሎች በርካታ ታዋቂ ተዋንያን በድንቅ ብቃት የተወኑበት በተወዳጅዋ ሙዚቀኛ ራሄል ጌቱ የሙዚቃ ማጀቢያ የተሰራለት ድንቅ ፊልም ሲሆን በምርቃት ስነስርዓቱ ላይም በርካታ እውቅ ተዋንያን እና የጥበብ ሰዎች እንዲሁም ከሶስት መቶ በላይ ታዳሚዎች ተገኝተዋል።
Mostrar todo...
👍 1 1
https://t.me/hamster_komBat_bot/start?startapp=kentId740173939 Play with me, become cryptoexchange CEO and get a token airdrop! 💸 2k Coins as a first-time gift 🔥 25k Coins if you have Telegram Premium
Mostrar todo...
Hamster Kombat

Just for you, we have developed an unrealistically cool application in the clicker genre, and no hamster was harmed! Perform simple tasks that take very little time and get the opportunity to earn money!

ሃምስተር ኮምባት ህጋዊ ወይስ ማጭበርበሪያ ዘዴ(ፌክ) ነው? ===== “ሃምስተር ኮምባት” (Hamster Kombat) በክሪፕቶ ገንዘብ ተፈጥሮ ምክንያት ህጋዊ ወይም ማጭበርበሪያ ዘዴ ነው ብሎ ለመደምደም የሚያስችል ምንም መንገድ የለም። ነገር ግን ሃምስተር ኮምባት ጠቃሚ ነገር ሊሆን እንደሚችል የሚጠቁሙ ምልክቶች አሉ የተባለ ሲሆን፤ ከእነዚህም አንዱ ማሳያዎ እንደ “BingX” ካሉ ልውውጦች ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነት መፍጠሩ ነው። ይህ ማለት ወደፊት በ”BingX” ልውውጥ ላይ የሃምተርን ተመዝግቦ ልናይ እንችላል፤ ነገርግን አሁን ማድረግ ያለብን ማመን እና ጨዋታውን መጫወት ብቻ ነው። ተለዋዋጭ በሆነው እና ተገማች ባልሆነው በክሪፕቶ ዓለም ውስጥ ማድረግ የምንችለው እንድ ነገር ወይ አምኖ መጫወት አሊያም መተው ብቻ ነው። ሃምስተር ኮምባት እንዴት መጀመር እንችላለን? ====== መጀመሪያ የሃምስተር ኮምባት ቦት ማስጀመር ያስፈልጋል፤ ይህን ለማድረግም ከታች ሊንኩን እናስቀምጥላችኋለን ''lunch''የሚለውን ተጭናችሁ በመግባት የሚጠይቃችሁን ነገር በጥንቃቄ መከተል ያስፈልጋል። “ሃምስተር ኮምባት” (Hamster Kombat) ተጫዋቾች ያለመታከት በተከታታይ የስልካቸውን ስክሪን በጣጣቸው መታ መታ (ታፕ ታፕ) ባደረጉ ቁጥር እስከ 2000 እና ከዚያ በላይ ኮይን ያገኛሉ። ከታፕ የምናገኘውን የሳንቲም ቁጥር ለመጨመር ወደ ቡስት ገጹ በመግባት አስፈላጊ የሆኑ ሂደቶችን በመከተል ማሳደግየምንችል ሲሆን፤ ይህ ግን የተወሰኑ ሳንቲችን (ኮይን) ሊያስወጣን ይችላል።
Mostrar todo...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ስለ #ሀምስተር #ኮምባት (Hamster Combat) #የምታውቁት #ነገር #ካለ #ንገሩን! #እውነት #ነው #ወይስ #ፌክ #ነው? ====== ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ሀገራት ላይ “ሃምስተር ኮምባት” በበርካቶች እየተዘወተረ መጥቷል። “ሃምስተር ኮምባት” ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በበርካቶች ዘንድ እየተዘወተረ የመጣ በቴሌግም ላይ የተመሰረተ ጨዋታ ሲሆን፤ ተጫዋቾቹ በየቀኑ ስክሪናቸውን በጣታቸው መታ መታ (ታፕ ታፕ) ሲያደርጉ ክሪፕቶ ሳንቲሞችን የሚያገኙበት ነው። “ሃምስተር ኮምባት” ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ሀገራት ላይ በበርካቶች እየተዘወተረ የመጣ ጨዋታም ሆኗል። በቴሌግራም ላይ የተመሰረተው ሃምስተር ኮምባት በአለም አቀፍ ደረጃ 200 ሚሊዮን ተጫዋቾችን በማፍራት ከፍተኛ ተወዳጅነትን አግኝቷል።
ሃምስተር ኮምባት ምንድን ነው?
==== ሃመስትር ኮምባት በቴልግራም ላይ የተመሰረተ ጨዋታ ሲሆን፤ ኤር ድሮፕ ሊሆኑ የሚችሉ ሳንቲሞችን (ኮይን) ተጫዋቾችን የሚሸልም የቴሌግራም ጨዋታ ነው። እንዲሁም ሰዎች በቴሌግራም ለይ ጓኞቻውን እየጋበዙ በርከት ያለ የክሪፕቶ ሳንቲሞችን ለመሰብሰብ በጋራ የሚጫወቱት ጨዋታ እንደሆነም ይነገራል። ምናልባት ጨዋታ ብቻ ስለሆነ ዋናው ጥቅሙ ምንድነው? የሚል ጥያቄ ሊያስከትል ይችላል፤ ምንም እንኳን በአሁኑ ጊዜ ጨዋታ ቢሆንም፣ በሃመስተር ኮምባት የሰበሰብናቸው ሳንቲች (ኮይኖች) ኤርድሮፕ የመሆን ዝግጅት እንዳለ ነው የሚነገረው። ይህ ማለትም በዚህ ጨዋታ ሳንቲሞችን (ኮይን) የሰበሰቡ ተጫዋቾች በቲ.ጂ.ኢ (ቶከን ጄኔሬሽን ኢቨንት) ወቅት ለኤር ድሮፕ ብቁ የመሆን እንደል አላቸው። ሳንቲሞቹ አስተዳዳሪዎች ያዋጣል ብለው ያመኑትን ማንኛውንም ተመን በመጠቀም ወደ ቶከን ይቀየራሉ፤ ስለዚህ “ሃምስተር ኮምባት” መጫወት ከጉዳቱ ጥቅሙ ያመዝናል ነው የተባለው።
Mostrar todo...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
የጽንስ ማስወረድ (Miscarriage) የፅንስ ማስወረድ ምንነት የጽንስ ማስወረድ አንዲት እርጉዝ ሴት የእርግዝናው እድሜ 20 ሳምንታት(በሃገራችን 28 ሳምንት) ከመሆኑ በፊት እርግዝናው ሲቋረጥ ነው። አንድ መደበኛ እርግዝና ለ 40 ሳምንታት ይቆያል ተብሎ ይታሰባል ። የፅንስ ማስወረድ ምክንያቱ ምን ሊሆን ይችላል? የተለያዩ ችግሮች የጽንስ ማስወረድ ሊያስከትሉ ይችላሉ - ፅንሱ ማደግ ይጀምራል ነገር ግን በዘረመል (chromosomes) ችግሮች ምክንያት እድገቱ ሲቋረጥ ። - የእናትየው የውስጥ ደዌ በሽታዎች መኖር። ለምሳሌ እምብዛም ቁጥጥር የማይደረግበት የስኳር በሽታ ። - በ አንዳንድ ችግሮች ምክኒያት ማህጸን ጽንሱን መሸከም ሲያቅተው ። ምልክቶች በጣም የተለመዱ ምልክቶች ከሴቷ ብልት ደም መፍሰስና የሆድ ህመም ወይም ቁርጠት ናቸዉ ። እርጉዝ ከሆኑ እና እነዚህን የበሽታ ምልክቶች ካዩ ወዲያውኑ ሐኪምዎን ወይም ነርስዎን ያማክሩ። እርጉዝ መሆንዎ እርግጠኛ ካልሆኑ እርግጠኛ ለመሆን የሽንት ምርመራ ያድርጉ። በተጨማሪም እነዚህ ምልክቶች ካዩ ሐኪምዎን ወይም ነርስዎን ማየት አለብዎ - 100 ºF (37.8 ° C) ወይም ከዚያ በላይ ትኩሳት ካለ - የረጋ ወይም የተጠቀለለ ነገር ከማህጸን ከወጣ - መጥፎ ሽታ ያለው የማህጸን ፈሳሽ ካለ - ሐኪምዎ ወይም ነርስዎ ማግኘት ካልቻሉ ወይም ከባድ ደም መፍሰስ ካለብዎት (ከ 1 እስከ 2 ሰዓታት ውስጥ ሞዴስ ከቀየሩ) ወደ አቅራቢያዎ የሚገኝ ሃኪም ቤት ይሂዱ። እነዚህ ምልክቶች ሁልጊዜም የፅንስ ማስወረድ ያሳያሉ ማለት አይደለም ነገር ግን የችግሩ ምክኒያት በሐኪምዎ የሚታወቅ ይሆናል።
Mostrar todo...
👍 1
የፅንስ ማስወረድ  እንዴት ነው የሚታከመው?  ===== የፅንስ ማስወረድ ካጋጠመና በማህፀን ውስጥ የቀረ ነገር ካለ መውጣት ይኖርበታል። ሐኪምዎ የቀረው ነገር በራሱ እስኪወጣ ድረስ እንዲጠብቁ ሊነግርዎት ይችላሉ ። ,ይህ አማራጭ ካልሆነ ሐኪምዎ የሚከተሉት መንገዶች በመጠቀም የቀረውን ማውጣት ይችላሉ።   - ማህጸንዎ በውስጡ ያለውን ነገር ለማውጣት  እንዲረዳዎ መድሃኒት  ወይም   - የማህጸን መጠረግ በመጠቀም  ቀሪውን ማውጣት ይቻላል የፅንስ ማስወረድን እንዴት መከላከል እችላለሁ?  የፅንስ ማስወረድ  በእርግጠኝነት እንዳይኖር ለማድረግ የሚያስችል መንገድ የለም። ይሁን እንጂ - ሲጋራ ፣የአልኮል መጠጥ፣ ኮኬይንና የመሳሰሉትን ነገሮችን በማቆም የጽንስ ማስወረድ  እድሎዎን ሊቀንሱ ይችላሉ። - ትኩሳት ወይም አንዳንድ የኢንፌክሽን ዓይነቶች የፅንስ መጨንገፍ ሊያስከትሉ ይችላሉ  ስለዚህ ትኩሳት ወይም  ኢንፌክሽን ሲይዞት ሐኪምዎን ያማክሩ።  - በተጨማሪም አንዳንድ መድሃኒቶች ወይም ሌሎች ህክምናዎች ለፅንሱ ጎጂ ሊሆኑ ይችላሉ። ማንኛውንም መድሃኒት ከመውሰድዎ በፊት ወይም የሕክምና ወይም ራጂ ከመነሳትዎ በፊት ጽንሱ ሊጎዳው ይችል እንደሆነ ዶክተርዎን ይጠይቁ። #amharahealthbereau
Mostrar todo...
👍 1
ለምን ብራቸውን አትከፍሏቸውም ? ስንል ለጠየቅነው ጥያቄ ፤  “ለጉዳዩ ምላሽ መስጠት ያለበት ወረዳ ነው። በወረዳው በጀት ዞን ጤና መምሪያው የሚመለከተው ስላልሆነ ” ብሏል። ተመሳሳይ ጥያቄ የቀረበላቸው የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መላኩ ገ/ህይወት በሰጡት ቃል፣ “ የበጀት እጥረት ገጥሞን ነው ” ብለዋል። ታዲያ ችግሩን ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተነጋግራችሁ ነበር ? ለሚለው ጥያቄ፣ “ በሚቀጥው በአዲሱ በጀት ተይዞ ይከፈላቸዋል ” ነው ያሉት። “ ለዚህም ደግሞ አስተዳደሩ ደብዳቤ ጽፏል። ‘በቀጣይ እከፍላለሁ’ የሚል ” ሲሉ አክለዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ባለሙያዎቹ ' የጸጥታ ችግር ባለበት ለክትባት ውጡ ተብለናል ' የሚል ቅሬታ አላቸው፤ ለመሆኑ ይህን ስታደርጉ ለደህንነታቸው ከለላ ታደርጉላቸዋላችሁ ? ሲል ጥያቄ አቅርቧል። ኃላፊው በምላሻቸው፣ “ የጸጥታ ችግር የሌለበት የለም። ዞሮ ዞሮ ግን በሚቻለው አግባብ የአገር ሽማግሌዎችን ይዘን እንሰራለን ” ነው ያሉት። #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
Mostrar todo...
👍 3
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.