es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቅዱሳት መጻሕፍት

Ir al canal en Telegram

በዚህ ቻናል 👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ:: 👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ:: 👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ። ⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️ @Holy_scriptures

Mostrar más
7 959
Suscriptores
+824 horas
+247 días
+4630 días
Archivo de publicaciones
በክፉ ቀን..! '' ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን እቃ ጦር ሁሉ አንሱ፡፡'' ኤፌ. 6፤10-19    "የክፉው ቀን" የቱ ነው?  የክፉው ቀን መቼስ ነው? ልክ እንደ አሁኑ ጊዜ ማለት ነው ፡፡ ብዙ ፈተና የበዛበት፣ የጸለዩት የማይሰማበት የሚመስልበት ቀን፤ ለጠላት የተፈቀደለት ቀን ይመስላል፡፡ ምናልባትም የዓለም ፍጻሜ ቀን የመጨረሻዎቹ ደቂቃ ላይ እንገኛለን፡፡ በፍጹም ያልጠበቅነው ነገር ገጥሞናል፡፡ በዚህ ክፉ ቀን የብዙዎች አቅም የሚፈተሽበት ፣ ጉልበታቸው የሚላላበት፣ እምነታቸውን የሚፈትን ነገር የሚገጥምበት ... ጊዜ ነው፡፡  በሕይወት ያልታሰበ  ነገር ሲገጥም ያስደነግጣል፤ ቢሆንም የመጨረሻው ዘመን ባህሪ በመሆኑ ልንታገስ ደግሞ ይገባል፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ለልጁ ለጢሞቴዎስ እንደጻፈለት '' ነገር ግን በመጨረሻ ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና ፣ገንዘብን የሚወዱ፣ ትምክህተኞች፣ ትዕቢተኞች፣ ተሳዳቢዎች፣ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፣ የማያመሰግኑ፣ ቅድስና የሌላቸው፣ ፍቅር የሌላቸው፣ ዕርቅን የማይሰሙ፣ ሐሜተኞች፣ ራሳቸውን የማይገዙ፣ ጨካኞች፣ መልካም የሆነውን የማይወዱ፣ ከዳተኞች፤ ችኩሎች፣ በትዕቢት የተነፉ፣ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ፣ ይሆናሉ፤ የአምልኮት መልክ አላቸው ኀይሉን ግን ክደዋል ከእነዚህ ደግሞ ራቅ፡፡" 2ኛ ጢሞ.3፤1-5  አንዳንዱ ነገር ለምን እንደሆነብን እና እንደሚሆን ላይገባን ይችላል፡፡ አንገታቸውን በሰይፍ የሚቀሉ ሰዎች ብዛት፣ በህክምና ስህተት ያሳደጉዋቸውን ወላጆች የሚያጡ ሰዎች ብዛት፣ ጽኑ ወዳጅነት ወደ ጠላትነት መቀየር፣ ልጆችን በተለያየ አደጋ ማጣት፣ ክፉ ዘዴኛነት ፣ ብልጠት፣ ራስ ወዳድነት፣ ማታለል አስገራሚ ጭካኔዎች ሲሆኑ፤ ለምን ? እንዴት ማለታችን አልቀረም፡፡ ጌታ  የት ሄዶ ነው ይህ  ሁሉ የሚሆንብን ትሉ ይሆናል፡፡    የብሉይ ኪዳን የመጨረሻው ነብይ መጥምቁ ዮሐንስ እንዲህ ዓይነት ጥያቄ ተፈጥሮበት ነበረ '' የምትመጣው መሲህ አንተ ነህ  ወይስ ሌላ እንጠብቅ ?'' ብሎ ወደ ኢየሱስ መልዕክተኞችን ላከ፡፡ወንጀል ሳይሰራ እስር ቤት መግባቱ ፣ በዚህም ላይ ብዙ የመሰከረለት ብርቱው ኢየሱስ በርሱ ጉዳይ ጣልቃ ገብቶ ፣ አልያም አንዳች ተአምራት ሰርቶ እርሱን ከእስር አለማስፈታቱ አደናግሮት ይሆናል፤ ነገር ግን ከዚህም የከፋ ሆነ፡፡ በእስራቱ ጊዜ ዝም ማለቱ ሲገርመን ጭራሽ በሔሮደስ ልደት ላይ ለዘፈነች አንዲት ወጣት ብላቴና ጥያቄ መሰረት አንገቱ ተቆርጦ በወጪት ቀረበ፡፡ ጌታስ? ዝም! በቃ ዝም! አንዳንዱ ጉዳይ ከእኛ አዕምሮ በላይ ነው፡፡ ምናልባት ከጌታ ጋር መግባባት ስለማንችል ይሆን ዝም የሚለን? እስጢፋኖስን በድንጋይ ወግረው ሲገድሉት ሁሉን የሚችለው ጌታ በዙፋኑ ላይ ቆሞ እያየው ነበር፤ ለምን እንዳላስጣለው አይታወቅም፣ የታመነው ምስክሩ አንቲጳስ ሲገደል ጌታ ጣልቃ አልገባም ፣ ሐዋርያቱ በዘይት ተጠብሰው ሲሞቱ፣ ህዝብ በተሰበሰበበት አናብስት ቦጫጭቀው ሲገድሉዋቸው የጠራቸው ጌታ በዙፋኑ ላይ ነበር፡፡ ለአንዳንዱ ጥያቄ መልስ በእጃችን የለም፡፡ አንድ የእግዚአብሔር ሰው እንዳሉት በፊሊፒንስ የጭቃ ጎርፍ 250 ህጻናትን ለምን ከድኖ እንደገደለ አናውቅም፡፡ በቅርብ ጊዜ አንድ የምታሳሳ ወጣት ከሲያትል ለሚሽን ጉዞ ወደ ህንድ ሄዳ በተመሳሳይ ለአገልግሎት ወደ ኢትዮጵያ የሄደው መጋቢ አባት ከጥቂት ቀናት በሁዋላ ተጠርቶ የመጣው ፡ ልጅህ ድንገት ሞታለች ተብሎ ተረድቶ ነበር፡፡ በጣም አሳዛኝ ነበረ፡፡ በሌላ ጊዜ አንድ  ዘማሪት እህት እናቱዋን በሞት ያጣችው ኦፕራሲዎን ልታስደርጋቸው ወስዳ በወቅቱ ሐኪሞቹ መቀስና ሌሎች ነገሮች ሆዳቸው ውስጥ ረስተው ስለ ሰፉአቸው ነበር፡ ነገሩ ኢንፌክሽን ፈጥሮባቸው ዳግመኛ ሲደረጉ  እንደሞቱ ነው ለቅሶ ስደርስ የነገረችኝ፤ ወገኖች ለእኛ የሚበጀን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ነው ፤ ጥያቄያችን ባይመለስም እናመልከዋለን ፣እንወደዋለን፡፡ እንደዚህ የመሰሉ ቀናትን ልናሸንፍ  / ልንቋቋም / እንችላለን ፤የምንችለው ግን የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር በመልበስ  / በማንሳት/ ነው፡፡ መሳሪያው ሰው ሰራሽ መሳሪያ ሳይሆን የእግዚአብሔር ዕቃ ጦር ይለዋል፡፡ እግዚአብሔር ለዚህ ክፉ ጊዜ እንዲሆነን ያዘጋጀልን መከላከያ እና ማሸነፊያ ዕቃ ጦር ነው፡፡ ቢያንስ ስድስት ነገሮች ናቸው ፤ቀጥለን እናያቸዋለን፡-   1-  የእምነት መታጠቂያ- ወገባችን ላይ 2-  የጽድቅ ጥሩር- ደረታችን አካባቢ 3-  የሰላም ወንጌል- እግሮቻችን ላይ 4-  የእምነት ጋሻ- በአንደኛው እጃችና ላይ 5-  የመዳን ራስ ቁር- በጭንቅላታችን ላይ የሚደረግ 6-  የመንፈስ ሰይፍ /የእግዚአብሔር ቃል ነው/- በቀኝ እጃችን ይዘን የምናጠቃበት ነው፡፡   ከራስ እስከ እግራችን ድረስ መሸፈን ያስፈለገን ምክንያት ጠላት እኛን ለመጉዳት ወይም ለመግደል ከጭንቅላታችን ጀምሮ ወርውሮ ስለሚሞክረን ነው፡፡ መዳኑ አስተማማኝ የሆነን ክርስቲያን ጭንቅላቱን መትቶ ሊጎዳው አይችልም፡፡ ነገር ግን ደረቱን በጥሩር ካልታጠቀ ማለትም ጽድቅ ላይ ገና የሚያመቻምች ሆኖ ካገኘው ይጎዳዋል፡፡ ነገር ግን እርሱም ከተሸፈነበት ቢያንስ እግሩን ስበሩት ብሎ መልዕክተኛ ይልካል:: ይህን ጊዜ ጠንካራ የወንጌል ከስክስ ያላደረገ  ሆኖ ከተገኘ ባይሞትም እንኩዋ ዘመኑን ሁሉ በመንፈስ እያነከሰ ይኖራል ስለዚህ ሙሉውን ትጥቅ መታጠቅና መመላለስ አለብን፡፡ እንደሚታወቀው ሰይጣን ትንሽ ቀዳዳ ፈልጎ  ነው የሚያጠቃን ፤ያልተሸፈነ አካላችንን ፈትሸን እንልበስ  /እንታጠቅ/፡፡ የእስራኤል ንጉስ አክአብ የሞተው በጥሩርና በጥሩር መጋጠሚያ በኩል ከጠላት ወገን በተወረወረ ቀስት ተወግቶ ነው፡፡ ምናልባት ሁሉን ታጥቆ ነበር፤ ይሁንና  መቀነት ግን አላደረገም እንደማለት ነው፡፡ ምንም እንኩዋ በእርሱ ሞት ላይ ፍርድ ከእግዚአብሔር ዘንድ የወጣም ቢሆን፡፡ጥቃት የደረሰበትና ለሞት የበቃው ግን በተገኘው ክፍተት በኩል ነበር፡፡  ወገኖች ሙሉ የእግዚአብሔርን ትጥቅ ታጥቀን በዚህ ዘመን እንድንኖር አሳስባችሁዋለሁ! እስቲ የላሉትን ጠበቅ እናድርጋቸው፤ ከትናንሽ ጥያቄዎቻችን እንውጣና ኩርፊያውን ትተን በእግዚአብሔር ፊት በጽድቅ ፣ በእውነት እንመላለስ!! የሚመጣልን መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ወደ ልዩ እረፍት ቦታ ይወስደናል፡፡ ብንጸና እንወርሳለን፡፡ በነገር ሁሉ ጌታ ከሁላችን ጋር ይሁን ፡፡ አሜን!!! ምንጭ:- lemekeru.com ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

. ──•◈•─────•◈•─ የዕለቱ ጥቅስ ──•◈•─────•◈•─ “የአምላኬም እጅ በእኔ ላይ መልካም እንደሆነች፥ ንጉሡም የነገረኝን ቃል ነገርኋቸው። እነርሱም፦ እንነሣና እንሥራ አሉ። እጃቸውንም ለ
.       ──•◈•─────•◈•─                  የዕለቱ ጥቅስ          ──•◈•─────•◈•─ “የአምላኬም እጅ በእኔ ላይ መልካም እንደሆነች፥ ንጉሡም የነገረኝን ቃል ነገርኋቸው። እነርሱም፦ እንነሣና እንሥራ አሉ። እጃቸውንም ለበጎ ሥራ አበረቱ።” ነህምያ 2፥18 ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

. ──•◈•─────•◈•─ የዕለቱ ጥቅስ ──•◈•─────•◈•─ “ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደ
.       ──•◈•─────•◈•─                  የዕለቱ ጥቅስ          ──•◈•─────•◈•─ “ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።” ይሁዳ 1፥3 ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በቤቴልና በዳን የወርቅ ጥጃዎችን ያሠራው የእስራኤል ንጉሥ ማን ነው?
Anonymous voting

. ──•◈•─────•◈•─ የዕለቱ ጥቅስ ──•◈•─────•◈•─ “እኔም መልሼ፦። የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን፤ እናንተ ግን በኢየሩሳሌም እድል ፈንታና መብት
.       ──•◈•─────•◈•─                  የዕለቱ ጥቅስ          ──•◈•─────•◈•─ “እኔም መልሼ፦። የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን፤ እናንተ ግን በኢየሩሳሌም እድል ፈንታና መብት መታሰቢያም የላችሁም አልኋቸው።” ነህምያ 2፥20 ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

ርዕስ:- የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን መሠረተ እምነት የገጽ ብዛት፦ 12 መጠን፦ 3.6MB ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

. ──•◈•─────•◈•─ የዕለቱ ጥቅስ ──•◈•─────•◈•─ “እናንተ ደግሞ ታገሡ፥ ልባችሁንም አጽኑ፤ የጌታ መምጣት ቀርቦአልና።” ያዕቆብ 5፥8 ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scrip
.       ──•◈•─────•◈•─                  የዕለቱ ጥቅስ          ──•◈•─────•◈•─ “እናንተ ደግሞ ታገሡ፥ ልባችሁንም አጽኑ፤ የጌታ መምጣት ቀርቦአልና።” ያዕቆብ 5፥8 ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

#እራሳችንን_እንመርምር “እንግዲህ በአንተ ያለው ብርሃን ጨለማ እንዳይሆን ተመልከት።” ሉቃስ 11፥35 “ስለዚህ በውስጥህ ያለው ብርሃን ጨለማ እንዳይሆን ተጠንቀቅ።” ሉቃስ 11፥35 (አዲሱ መ.ት) ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

. ──•◈•─────•◈•─ የዕለቱ ጥቅስ ──•◈•─────•◈•─ “ለእግዚአብሔርም ክብር እየሰጠ፥ የሰጠውንም ተስፋ ደግሞ ሊፈጽም እንዲችል አጥብቆ እየተረዳ፥ በእምነት በረታ እንጂ በአለማመን ምክንያ
.       ──•◈•─────•◈•─                  የዕለቱ ጥቅስ          ──•◈•─────•◈•─ “ለእግዚአብሔርም ክብር እየሰጠ፥ የሰጠውንም ተስፋ ደግሞ ሊፈጽም እንዲችል አጥብቆ እየተረዳ፥ በእምነት በረታ እንጂ በአለማመን ምክንያት በእግዚአብሔር ተስፋ ቃል አልተጠራጠረም።” ሮሜ 4፥20-21 ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

Bridgeway Bible Commentary A running explanation of the biblical textfor the people of today's world Don Fleming ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

EASTONS BIBLE DICTIONARY by M. G. Easton ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

. ──•◈•─────•◈•─ የዕለቱ ጥቅስ ──•◈•─────•◈•─ “የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ይህ ሸክላ ሠሪ እንደሚሠራ በውኑ እኔ በእናንተ ዘንድ መሥራት አይቻለኝምን? እነሆ፥ ጭቃው በሸክላ ሠሪ እጅ እ
.       ──•◈•─────•◈•─                  የዕለቱ ጥቅስ          ──•◈•─────•◈•─ “የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ይህ ሸክላ ሠሪ እንደሚሠራ በውኑ እኔ በእናንተ ዘንድ መሥራት አይቻለኝምን? እነሆ፥ ጭቃው በሸክላ ሠሪ እጅ እንዳለ፥ እንዲሁ እናንተ በእኔ እጅ አላችሁ።” ኤርምያስ 18፥6 ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

📔Title፦ Zondervan Illustrated Bible Dictionary 👤Author፦ J.D Douglas and Merrill C.Tenney 🖋Revised By:- Moises Silva 📃Page፦ 3,263 💾Size፦45.8MB ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

በተናገረው መልእክት ምክንያት በጭቃማ ጉድጓድ ውስጥ የተጣለው ነቢይ ማን ነበር?
Anonymous voting

. ──•◈•─────•◈•─ የዕለቱ ጥቅስ ──•◈•─────•◈•─ “አክሊልን እንደ ለበሰ ሙሽራ፥ በጌጥ ሽልማትዋም እንዳጌጠች ሙሽራ፥ የማዳንን ልብስ አልብሶኛልና፥ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛልና
.       ──•◈•─────•◈•─                  የዕለቱ ጥቅስ          ──•◈•─────•◈•─ “አክሊልን እንደ ለበሰ ሙሽራ፥ በጌጥ ሽልማትዋም እንዳጌጠች ሙሽራ፥ የማዳንን ልብስ አልብሶኛልና፥ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛልና በእግዚአብሔር እጅግ ደስ ይለኛል፥ ነፍሴም በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች።” ኢሳይያስ 61፥10 ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

የእንግሊዝኛ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ 👉Bible Knowledge Commentary, NEW TESTAMENT ➡️An Exposition of the Scriptures by Dallas Seminary Faculty Based on the New International Version ✍John F. Walvoord and Roy B. Zuck GENERAL EDITORS ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የእግዚአብሔር ቤት ፈርሶ ሳለ፣ ሕዝቡ በራሳቸው በተሸለሙ ቤቶች ውስጥ በመኖራቸው ምክንያት የገሠጻቸው ነቢይ ማን ነው?
Anonymous voting

. ──•◈•─────•◈•─ የዕለቱ ጥቅስ ──•◈•─────•◈•─ “እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚ
.       ──•◈•─────•◈•─                  የዕለቱ ጥቅስ          ──•◈•─────•◈•─ “እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።” 1ኛ ዮሐንስ 4፥16 ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

በተለያየ ቋንቋ የተጻፉ የመጽሐፍ ቅዱስ ታዋቂ ቅጂዎች ከእነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፦ 1. የአሌክሳንደሪያ ጽሑፍ (Codex alexandrinus) የተጻፈው በ5ኛው ክፍለ ዘመን ከእስልምና መጀመር አንድ መቶ አመት በፊት ነው፡፡ አሁን በለንደን ብሪቲሽ ሙዝየም ውስጥ ይገኛል። 2. የሲናይቲክስ ጹሑፍ (Codex sinaiticus) ይህ ደግሞ በ4ኛው ክፍለ ዘመን የተጻፈ ሲሆን አሁን በብሪቲሽ ሙዝየም ይገኛል፡፡ 3. የቫቲካነስ ጹሑፍ ( Codex vaticanus) ከሁለቱ ይልቅ ረጅም እድሜ ያለው ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በሮም የባቲካን ላይብረሪ ይገኛል። 4. የእብራይስጡ ማዘሬቲክ መጽሐፍ (The Hebrew massoretic text) በእብራይስጥ ቋንቋ የተጻፈ ሲሆን በክርስቲያኖችም በአይሁዶችም እጅ አለ፡፡ ከክርስቶስ ልደት በፊት የተጻፈ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ነው፡፡ 5. የሙት ባሕር ጥቅልል (Dead sea scroll) በሙት ባሕር አካባቢ በተደረገው የአርኪኦሎጂ ቁፋሮ የተገኘ መጽሐፍ ነው፡፡ ይህም መጽሐፍ ቅዱስ ከክርስቶስ ልደት በፊት ሁለት መቶ ዓመታት እድሜ አለው፡፡ 6. ሰፕቱጀንት ከእብራይስጥ ወደ ግሪክ የተተረጎመ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ነው፡፡ ይህም መጽሐፍ የተጻፈው ከክርስቶስ ልደት ሁለት መቶ ዓመታት አስቀድሞ ነው፡፡ 7. የላቲን ቩልጌት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በ4ኛው ክፍለ ዘመን ከሰፕቱጀንትና ከጥንታዊ የግሪክ መጽሐፍት የተረጎመችው ነው፡፡ ምንጭ፦ "መጽሐፍ ቅዱስ ይጣረሳልን?"፤ አንዋር መሐመድ፤ ገጽ 11-12 ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በ3ኛ ዮሐንስ ላይ ዋናቸው ሊሆን እንደሚወድና ወንድሞችን እንደማይቀበል በመናገር ሐዋርያው ዮሐንስ የወቀሰው ሰው ማን ነው?
Anonymous voting