es
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

Ir al canal en Telegram

EEP Communication

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram EEP Communication

El canal EEP Communication (@eepcommuication) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 15 548 suscriptores, ocupando la posición 8 340 en la categoría Tecnologías y Aplicaciones y el puesto 2 158 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 15 548 suscriptores.

Según los últimos datos del 26 junio, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de 27, y en las últimas 24 horas de -7, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 26.05%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 16.01% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 4 053 visualizaciones. En el primer día suele acumular 2 491 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 8.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
EEP Communication

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 27 junio, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Tecnologías y Aplicaciones.

15 548
Suscriptores
-724 horas
+147 días
+2730 días
Archivo de publicaciones
በትግራይ በአንዳንድ አካባቢዎች የኃይል መቋረጥ ይኖራል .........///........ ወደተከዜ የኃይል ማመንጫ ግድብ የሚገባውን ውሃ በማስተንፈስ ሂደት የጣቢያው ዩኒቶች  ሥራ በማቆማቸው በትግራይ አንዳንድ አካባቢዎች የኃይል መቋረጥ ሊኖር ይችላል። ከግድቡ ውሃ ሲለቀቅ  የሚፈጠረው የእንፋሎት ጭጋግ በትራንስፎርመሮችና የኃይል ማመንጫ ቤቱ ላይ ጉዳት እንዳያስከትል ሁለቱ ዪኒቶች እንዲቆሙ ተደርጓል። በዚህ የተነሳ  የቮልቴጅ መዋዠቅ በማጋጠሙ በትግራይ ክልል አንዳንድ ከተሞች የኃይል መቋረጥ  ያጋጥማል። የክረምቱ ዝናብና ወደ ግድቡ የሚገባው የውሃ መጠን እስከሚቀንስ ድረስ ችግሩ ለቀናት የሚቀጥል በመሆኑ የኃይል ተጠቃሚ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠብቁና ሌሎች አማራጮችን እንዲጠቀሙ እናሳስባለን። በዚህ አጋጣሚ ከግድቡ በላይኛውና በታችኛው ተፋሰስ በሚገኙት በጣንቋ፣ አበርገለ፣ በቆላ ተንቤን፣ በላዕላይ እና ታህታይ ማይጨው፣ በመረብለኸ፣ በአስገደ ጽንበለ፣ በላዕላይና ታህታይ አዲያቦ፣ በመደባይ ዛና፣ በታህታይ ቆራሮ፣ በአጠቃላይ የተከዜ ወንዝ ተዋሳኝ በሆኑ ወረዳዎች ነዋሪዎችና የመስተዳድር አካላት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እነወዲያደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን። "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ነሐሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content
+1

የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሎየር 1ኛ የስራ መደብ መጋቢት 11 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣው ማስታወቂያ መሰረት ከላይ ስማችሁ የተገለጸው አመልካቾች በሙሉ
+2
የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሎየር 1ኛ የስራ መደብ መጋቢት 11 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣው ማስታወቂያ መሰረት ከላይ ስማችሁ የተገለጸው አመልካቾች በሙሉ ነሐሴ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ማንነታችሁን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ኮተቤ ብረታብረት በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ የጽሁፍ ፈተና የሚሰጥ በመሆኑ ለፈተና እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡ "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ነሐሴ 14 ቀን 2016 ዓ.ም

ለወርቅ ማዕድን ማምረቻ ፕሮጀክት ኃይል ለማቅረብ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ ........///.......... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከኩርሙክ የወርቅ ማምረቻ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ጋር የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ ስምምነቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ እና የኩርሙክ ወርቅ ማምረቻ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ብሮክስ ወርቁ ተፈራርመዋል፡፡ በኢትዮጵያ ኤሌክትክ ኃይል የገበያና ቢዝነስ ልማት መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ሕይወት እሸቱ ስምምነቱን አስመልክተው እንደተናገሩት ከኩባንያው ጋር የተካሄደው ስምምነት ለ12 ዓመታት የሚቆይና 35 ሜጋ ዋት ኃይል ለማቅረብ የሚያስችል ነው፡፡ የኃይል አቅርቦት ስምምነት ክፍያው በዶላር እንደሚፈፀም ገልፀው ይህም የተቋሙን የውጭ ምንዛሬ በማሳደግ በኩል ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው አስታውቀዋል፡፡ እንደ አቶ ሕይወት ገለፃ ስምምነቱ ከኃይል አቅርቦት ባለፈ ለወርቅ ማምረቻ ፕሮጀክቱ ኃይል ለማቅረብ የሚያግዘውን የኃይል ማስተላለፊያ መስመር የዲዛይን እና የግንባታ ሥራዎችን በማከናወን ለተቋሙ ተጨማሪ ገቢ የሚያገኝበትን ዕድል ይፈጥራል፡፡ ይህም ተቋሙ በኃይል መሰረተ ልማቶች ግንባታ ሥራ ላይ ያለውን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተናግረዋል፡፡ ተቋሙ በሀገሪቱ እየተከናወኑ ለሚገኙ የተለያዩ ዘርፎች አስተማማኝ ኃይል በማቅረብ የኢንቨስትመንት ሥራዎችን በመደገፍ ሃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝም ተመላክቷል፡፡ የኩርሙክ ወርቅ ማምረቻ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ብሮክስ ወርቁ በበኩላቸው ከተቋሙ ጋር የተደረገው ስምምነት ፕሮጀክቱን እውን ለማድረግ ለኩባንያው እንደ ትልቅ ስኬት የሚቆጠር ነው ብለዋል፡፡ ስምምነቱ ፕሮጀክቱ ወደ ሥራ ሲገባ አስተማማኝ ኃይል ለማግኘት እንደሚያስችለው ጠቅሰው ተቋሙ በስምምነቱ መሰረት ኃይል ማቅረብ እንደሚኖርበትም አስገንዝበዋል፡፡ የወርቅ ማምረቻ ፋብሪካውን በ2018 ዓ.ም ወደ ሥራ ለማስገባት ዕቅድ እንደተያዘለት የተናገሩት ዋና ሥራ አስኪያጁ በአሁኑ ወቅትም ለፕሮጀክቱ ግንባታ የሚያስፈልጉ ነገሮችን ወደ ቦታው የማጓጓዝ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ ዘጠኝ ቶን የሚጠጋ ወርቅ የማማረት አቅም ይኖረዋል የተባለው እና የ500 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት እንደሆነ የተነገረለት ይህ የወርቅ ማምረቻ ፋብሪካ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ኩርሙክ ወረዳ የሚገነባ መሆኑንም አቶ ብሮክስ ተናግረዋል፡፡ የወርቅ ማምረቻ ፋብሪካው ተጨማሪ የኃይል ፍላጎት ሲኖረው በአቅርቦቱ እና በዋጋው ላይ ማሻሻያ እንደሚደረግበት በውሉ ላይ መካተቱንም የሥራ ኃላፊዎቹ አስታውቀዋል፡፡ "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ነሐሴ 13 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content
+6

photo content
+6

የማከፋፊያ ጣቢያው የኢንቨስትመንት ፍሰቱን ጨምሯል .....//...... የቡኢ ማከፋፊያ ጣቢያ የከተማዋንና የአካባቢውን ኢኮኖሚያዊ እድገት እያፋጠነ መሆኑን የቡኢ ከተማ አስተዳደር ገለጸ። የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ በለጠ ጫካ እንደገለጹት የቡኢ ማከፋፊያ ጣቢያ ከመገንባቱ በፊት ከተማዋ የኃይል አቅርቦት ከቡታጅራ ማከፋፊያ ጣቢያ ስታገኝ የነበረ ሲሆን ይህም በከተማዋና አካባቢው የሚመጡ የኢንቨስትመንት ጥያቄዎችን ተቀብሎ ለማስተናገድ እንቅፋት ፈጥሮ ቆይቷል። የቡኢ ባለ 132 ማከፋፊያ ጣቢያ ከተገነባ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ ግን የአካባቢው የኢንቨስትመንት ፍሰት እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል። በዚህም ከፍተኛ ኃይል የሚጠይቁ ከ40 በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ ወስደው 6ቱ ወደ ማምረት ሲገቡ ቀሪዎቹ ደግሞ በግንባታ ሂደት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል። አሁንም በከተማውና አካባቢው ያለውን አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት ከግምት ውስጥ በማስገባት በርካታ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ጥያቄ እያቀረቡ መሆኑንም አቶ በለጠ አብራርተዋል። የአካባቢውን የመልማት አቅምና ፍላጎት ታሳቢ በማድረግ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር በማድረጉ አመስግነዋል። የቡኢ ማከፋፍያ ጣቢያው የኦፕሬሽን ባለሙያ አቶ አይሸሹም አበረ በበኩላቸው የማከፋፍያ ጣቢያው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 4 ከተሞችና 3 ወረዳዎች እንዲሁም አጎራባች የኦሮሚያ ክልል ወረዳዎችን የኃይል ተጠቃሚ ማድረጉን ገልጸዋል። ጣቢያው 45 ሜጋ ዋት የመጫን አቅም ያለው ሲሆን አሁን በጥቅም ላይ የዋለው ዘጠኝ ከመቶው ብቻ መሆኑን ጠቁመዋል። ይህም ቡኢ ከተማን ጨምሮ በአካባቢው በመገንባት ላይ ለሚገኙ ፋብሪካዎችም ሆነ በቀጣይ ለሚመጡ ኢንቨስትመንቶች የኃይል አቅርቦት ጥያቄዎችን በአግባቡ ለመመለስ የሚያስችል አቅም ያለው መሆኑን ተናግረዋል። "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ነሐሴ 13 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content
+9

ሥምምነቱ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ንፁህና ታዳሽ የኃይል ማዕከል ለመሆን ካላት ራዕይ ጋር የሚጣጣም ነው ........///.......... የአይሻ አንድ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በቀጣይ ለሚተገበሩ የታዳሽ ኃይል ፕሮጀክቶች ማሳያ መሆን እንደሚችል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አስታወቁ። ተቋሙ አሜአ ፖወር ከተሰኘው የተባበሩት አረብ ኢመሬቶች ኩባንያ ጋር የኤሌክትሪክ ኃይል ግዥ ሥምምነት ሲፈራረም ዋና ሥራ አስፈፃሚው ኢንጂነር አሸብር ባልቻ እንደተናገሩት ሥምምነቱ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ንፁህና ታዳሽ የኃይል ማዕከል ለመሆን ካላት ራዕይ ጋር የሚጣጣም ነው። መንግሥት ለቱሪዝም ዘርፉ፣ ለኮሪደር ልማቱ እና ለጤናማ የኑሮ አካባቢዎች መስፋፋት ትኩረት በመስጠቱ ምክንያት የኃይል ፍላጎት እያደገ መምጣቱን ኢንጂነር አሸብር ተናግረዋል። የኢነርጂ ዘርፉ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት መፋጠን፣ የኑሮ ደረጃ መሻሻልና ለዘላቂ የልማት ግቦች መሳካት ከፍተኛውን ድርሻ እየተወጣ እንደሚገኝም ነው የጠቆሙት። ተቋሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ለመጣው የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት በርካታ የልማት ሥራዎችን በማከናወን ላይ መሆኑን ተናግረዋል። እንደ ኢንጂነር አሸብር ገለፃ ኢትዮጵያ ለታዳሽ ኃይል ባላት ቁርጠኝነት መሠረት በንፋስ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ላይ በንቃት እየተሳተፈች ነው። የአይሻ 1 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የዚሁ ዕቅድ አካል መሆኑንም ነው የገለፁት። ሥምምነቱ ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ላይ መሰረት ላደረገ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ስትራቴጂዋ ተጨማሪ ግብዓት ይሆናል ብለዋል። የንፋስ ኃይል ማመንጫ ግንባታው ሲጠናቀቅ በዓመት በአማካኝ 1 ሺህ 261 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል እንደሚያመነጭም ነው የጠቀሱት። በታዳሽ ኃይል ልማት፣ ግንባታና አስተዳደር ዘርፍ የተሰማራው አሚአ ፓወር በአይሻ አንድ የንፋስ ኃይል ማመንጫ 300 ሜጋ ዋት በማመንጨት ለ25 ዓመታት ለኢትዮጵያ ለመሸጭ ነው ሥምምነቱን የፈረመው። ሥምምነቱ ከዳር እንዲደርስ ላደረጉት አካላት ምስጋናቸውን ያቀረቡት ዋና ሥራ አስፈፃሚው ጥረቱ በትብብርና በጋራ የማደግን አስፈላጊነት ያሳየ ነው ብለዋል። "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ነሐሴ 12 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content
+4

photo content
+7

የፕሮጀክቱ ሠራተኞች ከ3 ሺህ በላይ ችግኞችን ተከሉ ........///...... የበቆጂ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክት ቋሚና ጊዜያዊ ሠራተኞች በፕሮጀክቱ ሳይት የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል። ሠራተኞቹ የተለያየ ዝርያ ያላቸው ከ3 ሺህ በላይ ችግኞችን በመትከል አሻራቸውን አኑረዋል። የፕሮጀክቱ የሳይት ኃላፊ እንዳልካቸው ጃምቦ እንደገለፁት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሠራተኞች የአረንጓዴ አሻራ ተሳታፊ በመሆን ለታዳሽ ኃይል ልማት አስተዋጽኦ ማበርከት ይጠበቅባቸዋል። ዛሬ የሚተከሉት ችግኞች ነገ ሀገራዊ የደን ሽፋንን በማሳደግ የአየር ንብረትን ለማስተካከልና ምቹ የሥራ ቦታ ለመፍጠር ያግዛሉ ብለዋል። የፕሮጀክቱ ሰራተኞች ችግኞቹን ለግማሽ ቀን ሲተክሉ እንደዋሉ ኃላፊው ገልፀዋል። "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ነሐሴ 11 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content
+7

photo content
+9

የኃይል ግዥና የፕሮጀክት ትግበራ ሥምምነት ተፈረመ .........///........ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሜአ ፓወር ከተሰኘ የተባበሩት አረብ ኢሜሬቶች ኩባንያ ጋር የኃይል ግዥ ሥምምነት ተፈራረመ። የአይሻ 1 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ትግበራ ይፋ ለማድረግ በተዘጋጀው የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ላይ አልሚው አሜአ ፓወር ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር የፕሮጀክት ትግበራ አጋርነት እንዲሁም ከሶማሌ ክልል መንግስት ጋር የመሬት ሊዝ ሥምምነት ተፈራርሟል። የኃይል ግዢ ሥምምነቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ እና በአሜአ ፓወር ኩባንያ የአይሻ 1 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ራጂሽ ራሚሽ ተፈራርመዋል። በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት ንግግር ያደረጉት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ኢትዮጵያ በኢኮኖሚው ዘርፍ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ዕድገት በማስመዝገብ ላይ ትገኛለች ብለዋል። በአሁኑ ወቅት ወደ ተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፓሊሲ ትግበራ መገባቱን የገለፁት ሚኒስትሩ በዘርፉ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል። እንደ አቶ አህመድ ገለፃ የአይሻ 1 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኢሜሬቶች ከዚህ ቀደም በተለያዩ መስኮች ያላቸውን ሁሉን አቀፍ ትብብርና ግንኙነት የሚያጠናክር ነው። ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የታዳሽ ኃይል ማዕከል ለመሆን እያከናወነቻቸው ላሉ ተግባራት ማሳያ እንደሆነም ነው አቶ አህመድ የገለፁት። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጅነር አሸብር ባልቻ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ አቅሟን ለማጠናከር በነደፈቻቸው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ የኢንዱስትሪ እና የከተሞች መስፋፋት ዕቅዶች ፈጣን ለውጥ እያስመዘገበች ትገኛለች። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሦስት ዓመት ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ቀርፆ ተግባራዊ በማድረግ ላይ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈፃሚው ገልፀዋል። የአይሻ 1 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የዚሁ ዕቅድ አካል መሆኑንም ተናግረዋል። እንደ ኢንጂነር አሸብር ገለፃ ሥምምነቱ ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ላይ መሰረት ላደረገ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ስትራቴጂዋ ተጨማሪ ግብዓት ይሆናል። የንፋስ ኃይል ማመንጫ ግንባታው ሲጠናቀቅ በዓመት በአማካኝ 1 ሺህ 261 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል እንደሚያመነጭም ነው የጠቀሱት። በአሜአ ፓወር የአይሻ 1 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ራጂሽ ራሚሽ በበኩላቸው የተባበሩት አረብ ኢሜሬቶች ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ዕድገት የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ ተናግረዋል። ፕሮጀክቱ ለ1 ሺህ 500 ዜጎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል ያሉት ሥራ አስኪያጁ ኃይል ማመንጨት በሚጀምርበት ወቅትም ከ4 ሺህ በላይ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት ተደራሽ ለማድረግ ያስችላል ብለዋል። በገንዘብ ሚኒስቴር የመንግሥትና የግል አጋርነት ቦርድ ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አበበ ገ/ህይወት በበኩላቸው ፕሮጀክቱ በዓመት 690 ቶን የካርበን ልቀትን የማመጣጠን አቅም አለው። ከኩባንያው ጋር የተደረገው ሥምምነት ከፕሮጀክት ሥምምነት በላይ አድርገን የምናስበውና ለቀጣይ ኢንቨስትመንት መሰረት የሚጥል ነውም ብለዋል። ፕሮጀክቱ በመንግሥት እና የግል አጋርነት ማዕቀፍ በ620 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚገነባ ትልቅ ኢንቨስትመንት እንደሆነም ነው ዋና ዳይሬክተሩ የጠቆሙት። በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሸዴን ጨምሮ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታዎች፣ የመንግሥትና የግል አጋርነት ቦርድ አባላትና የጽ/ቤት ሠራተኞች፣ የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ተወካዮች፣ የመንግሥት የልማት ድርጅቶ ይዞታና አስተዳደር ዋና ዳይሬክተርና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች፣ የተባበሩት አረብ ኢሜሬቶች ከፍተኛ የመንግሥትና የአሜአ ፓወር የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ነሐሴ 11 ቀን 2016 ዓ.ም

በመላ ሀገሪቱ የሲስተም ማሻሻያ ሥራ እየተከናወነ ነው ......///...... በመላው ኢትዮጵያ የሲስተም ማሻሻያ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የብሔራዊ ኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል አስታወቀ። ማዕከሉ እንደገለፀው በሚከናወነው የሲስተም ማሻሻያ ሥራ በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች ከፍተኛ የኃይል ጭነት በሚበዛባቸው ሰዓታት ዛሬና ነገ የኃይል መቋረጥ ሊያጋጥም ይችላል። በመሆኑም የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ደንበኞች በሙሉ ችግሩን ተረድተው በትግዕስት እንዲጠብቁና ሌሎች ጊዜያዊ አማራጮችን እንዲጠቀሙ ማዕከሉ ጥሪ አቅርቧል። "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ነሐሴ 11 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content
+1

የአይሻ አንድ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታ ስምምነት ሊፈረም ነው ......///...... በኢትዮጵያ ከንፋስ ኃይል በማመንጨት አቅሙ ትልቁ የሆነውን የአይሻ አንድ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታ ለማስጀመር የሚያስችል ሥምምነት ሊፈረም ነው፡፡ ዛሬ እንደሚፈረም የሚጠበቀው የሦስትዮሽ የፊርማ ሥነ-ሥርዓት በገንዘብ ሚኒስቴር እና በአልሚው አሜአ ፓወር እንዲሁም በአልሚው እና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መካከል የሚካሄድ ነው፡፡ 300 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቱ በሶማሌ ክልል አይሻ ወረዳ ላይ ይገኛል። ፕሮጀክቱ በመንግሥት እና በግል አጋርነት ማዕቀፍ የሚገነባ ትልቁና የመጀመሪያው ኢንቨስትመንት ይሆናል። "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ነሐሴ 11 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content
+1

photo content