es
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

Ir al canal en Telegram

EEP Communication

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram EEP Communication

El canal EEP Communication (@eepcommuication) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 15 559 suscriptores, ocupando la posición 8 384 en la categoría Tecnologías y Aplicaciones y el puesto 2 165 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 15 559 suscriptores.

Según los últimos datos del 23 junio, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de 0, y en las últimas 24 horas de -2, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 25.89%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 15.48% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 4 026 visualizaciones. En el primer día suele acumular 2 408 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 9.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
EEP Communication

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 24 junio, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Tecnologías y Aplicaciones.

15 559
Suscriptores
-224 horas
-37 días
Sin datos30 días
Archivo de publicaciones
photo content
+9

ሪጅኑ የኮንዳክተር ገመድ የመቀየር ሥራ እያከናወነ ነው .......///……... በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር ሳቢያ ጉዳት የደረሰበትን የአላማጣ - አሸጎዳ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር በአዲስ ኮንዳክተር የመቀየር ሥራ እያከናወነ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰሜን ሪጅን የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን መምሪያ አስታወቀ። በመምሪያው የማስተላለፊያ መስመሮች ጥገና ሥራ አስኪያጅ አቶ ህንፃ አረጋዊ እንዳስታወቁት የኮንዳክር ገመድ የመቀየር ሥራው ከ40 በመቶ በላይ ተከናውኗል። የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ በአካባቢው በነበረው የፀጥታ ችግር በመጎዳቱ ምክንያት የኃይል መቆራረጥ በተደጋጋሚ ይከሰት እንደነበር የጠቀሱት ሥራ አስኪያጁ በግሪድ ኔትወርኩ ላይም አሉታዊ ጫና ሲያሳድር መቆየቱን ጠቅሰዋል። ከአላማጣ - አሸጎዳ የተዘረጋው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር 126 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ቢሆንም ከዚህ ውስጥ በአዲስ የኮንዳክተር ገመድ ለመቀየር የታሰበው 30 በመቶውን ብቻ መሆኑን ነው የተናገሩት። መስመሩን ለመቀየር የሚያስፈልጉ 38 ድራም የኮንዳክተር ሽቦ ገመድ እና የሚዘረጋውን የኮንዳክተር ገመድ የሚያገናኙ 100 የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ማገናኛዎች (Mid Span Joint) መረከባቸውን አቶ ህንፃ ገልፀዋል። በአሁኑ ወቅት በአዲስ መልክ የኮንዳክተር ዝርጋታ መከናወን ካለበት 37 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር ውስጥ 15 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር መጠናቀቁንም ነው ሥራ አስኪያጁ የጠቆሙት። እንደ አቶ ህንፃ ገለፃ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሶሶዎቹ የተዘረጉበት አካባቢ በረሃማና የመልክዓ ምድሩ አቀማመጥ አስቸጋሪ መሆን፣ ስርቆት እና የነዳጅ አቅርቦት ችግሮች የኮንዳክተር ገመድ ቆየራ ሥራውን ፈታኝ አድርገውታል። የኮንዳክተር ሽቦ እና የኦ.ፒ.ጂ. ደብሊው ፋይበር መስመር ዝርጋታው ሲጠናቀቅ ከኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች መረጃዎችን ማግኘት ስለሚቻል በፍጥነት የጥገና ሥራዎችን ለማከናወን ሚናው የጓላ እንደሆነም ነው የተናገሩት። የኮንዳክተር ሽቦ ገመድ ቅየራ ሥራው በሪጅኑ አቅም እንዲከናወን በመወሰኑ ከፍተኛ ወጪ ማዳን ተችሏል ያሉት አቶ ህንፃ የዝርጋታ ሥራው እንዲሰራ ዕድሉን ላመቻቹ በየደረጃው ለሚገኙ የተቋሙ የሥራ አመራሮች ምስጋናቸውንም አቅርበዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠https://twitter.com/EEPethiopia ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power ዩትዩብቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ሚያዝያ 14 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+6

#የፈተናጥሪ የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሾፌር-4ኛ የስራ መደብ ሰራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ.ም የውጪ ማስታወቂያ ማውጣታችን ይታወሳል፡፡ በዚሁ
+2
#የፈተናጥሪ የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሾፌር-4ኛ የስራ መደብ ሰራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ.ም የውጪ ማስታወቂያ ማውጣታችን ይታወሳል፡፡ በዚሁ መሰረት ከላይ ስማችሁ የተገለጸው አመልካቾች በሙሉ ሚያዚያ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ማንነታችሁን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ኮተቤ ብረታ ብረት ፊት ለፊት በሚገኘው በዋናው መ/ቤት የመሰብሰብያ አዳራሽ የጽሁፍ ፈተና የሚሰጥ በመሆኑ ለፈተና እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠https://twitter.com/EEPethiopia ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power ዩትዩብቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ሚያዝያ 14 ቀን 2017 ዓ.ም

የጂ አይ ኤስ ብሬከሮች ቅየራ ከኃይል አቅርቦት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ቅሬታዎችን ይፈታል ………///………. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እያከናወነ ያለው የማከፋፈያ ጣቢያዎችን የማዘመን ሥራ የጣቢያዎቹን አሰራር በማዘመን በደንበኞች የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት እንደሚያግዝ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡ በአገልግሎቱ የሻሸመኔ ሪጅን የቴክኒክ ክፍል ኃላፊ አቶ ጅብሪል ሩቤ እንደገለፁት የጂ አይ ኤስ መቆጣጠሪያ ቅየራ መከናወኑ የጣቢያቹን አቅም በማሳደግ ለህብረተሰቡ አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ ያስችላል፡፡ በሻሸመኔ ማከፋፈያ ጣቢያ የ33 ኪሎ ቮልት መቆጣጠሪያ ከዚህ በፊት ተቀይሮ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ያስታወሱት አቶ ጅብሪል በአሁኑ ወቅት ደግሞ የ15 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመር መቆጣጠሪያዎችን ወደ ጂ አይ ኤስ መቆጣጠሪያ የመቀየር ሥራ እየተከናወን ይገኛል ብለዋል፡፡ በአገልግሎቱ የሲዳማ ሪጅን ዳይሬክተር አቶ አበበ እድሉ በበኩላቸው የማከፋፈያ ጣቢያ መቆጣጠሪያዎች የአገልግሎት ጊዜ እና የሚሰሩበት ዘዴ በማከፋፈያ ጣቢያዎች ለሚፈጠሩ የኃይል መቆራረጦች አንድ ምክንያት እንደሚጠቀሱ ገልፀዋል፡፡ በሪጅኑ ከሚገኙ አራት ማከፋፈያ ጣቢያዎች መካከል በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በይርጋለም አንድ ማከፋፈያ ጣቢያ መቆጣጠሪያዎችን በዘመናዊ ዕቃዎች የመቀየር ሥራ ስለመጀመሩ ተናግረዋል፡፡ ቀደም ሲል በአንድ ወጪ መስመር ተደርበው ኃይል ሲያገኙ የነበሩ ከተሞችና አካባቢዎች አሁን በተጀመረው የመቆጣጠሪያ መሳሪያ ቅየራ ሥራ ለየብቻቸው የሚወጡበትን ዕድል እንደሚፈጥርም አቶ አበበ ተናግረዋል፡፡ እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ የብሬከር ቅየራው ከኃይል አቅርቦት ጋር በተያያዘ ከደንበኞች ሲነሱ የነበሩ ቅሬታዎችን ለመፍታት እና በኃይል መቆራረጥ ምክንያት ሁለቱ ተቋማት ሲያጡት የነበረውን ገቢ በማስተካከል በኩል ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡ የሥራ ኃላፊዎቹ እንደገለፁት ሁለቱ ተቋማት ለህብረተሰቡ ያልተቆራረጠ ኃይል ለማቅረብ በቅንጅት እየሰሩ ናቸው፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠https://twitter.com/EEPethiopia ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power ዩትዩብቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ሚያዝያ 14 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+2

የትንሳዔ በዓል ያለምንም የኃይል እጥረት ተከብሯል ……....///…….... ትላንት በተከበረው የትንሳዔ በዓል እና በዋዜማው ምንም ዓይነት የኃይል እጥረት አለማጋጠሙን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል አስታወቀ፡፡ በማዕከሉ የሪል ታይም ኦፕሬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ጉልላት እንግዳ እንደገለፁት ከበዓሉ ዋዜማ አንስቶ በበዓሉ ዕለት የኃይል እጥረት እና መቋረጥ እንዳያጋጥም ከኃይል ማመንጫ እስከ ማከፋፈያ ጣቢያ ድረስ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ የተለያዩ ሥራዎች ሲከናወኑ ነበር። ለበዓሉ ለመጠባበቂያ ከተያዘው ኃይል ውጪ ከ4 ሺህ ስምንት መቶ ሜጋ ዋት በላይ ኃይል ለማቅረብ ዝግጅት ቢደረግም በዋዜማው 4 ሺ 624 ሜጋ ዋት እንዲሁም በበዓሉ ዕለት 3 ሺ 856 ሜጋ ዋት ኃይል ከፍተኛ የኃይል ጭነት መመዝገቡን ገልፀዋል፡፡ የከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚ ለሆኑት የዳታ ማይኒንግ ኩባንያዎች፣ ትላልቅ ኢንዱስትሪዎች እና ለኤክስፖርት የሚቀርበው ኃይል ሳይቋረጥ ዝግጁ ከተደረገው ኃይል ውስጥ በዋዜማው176 ሜጋ ዋት እንዲሁም በበዓሉ ዕለት 944 ሜጋ ዋት ትርፍ ኃይል እንደነበር አቶ ጉልላት አስረድተዋል። ተቋሙ ያለምንም ችግር የሚፈለገውን ኃይል ማቅረብ መቻሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ አስተማማኝ ኃይል የማቅረብ አቅሙን በከፍተኛ ደረጃ እያሳደገ መምጣቱን የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠https://twitter.com/EEPethiopia ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power ዩትዩብቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ሚያዝያ 13 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+1

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ ልባዊ ምኞቴን እገልፃለሁ። በዓሉ የሠላም፣ የፍቅርና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ። ኢንጂነር አሸ
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ ልባዊ ምኞቴን እገልፃለሁ። በዓሉ የሠላም፣ የፍቅርና የመተሳሰብ  እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ። ኢንጂነር አሸብር ባልቻ፣ ዋና ሥራ አስፈፃሚ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠https://twitter.com/EEPethiopia ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power ዩትዩብቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ሚያዝያ 11 ቀን 2017 ዓ.ም

ለትንሳዔ በዓል በቂ ያኃይል አቅርቦት እንዲኖር ዝግጅት ተደርጓል ..........///............ ለትንሳኤ በዓል የኃይል አቅርቦት ችግር እንዳያጋጥም በቂ ዝግጅት መደረጉን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የግሪድ ሲስተም ኦፕሬሽን መምሪያ አስታወቀ። የመምሪያው ዳይሬክተር አቶ ሚኪያስ ወንድሙ እንዳስታወቁት በዋዜማውና በበዓሉ ዕለት በመላው ሀገሪቱ የሚኖረው የኃይል ፍላጎት 4 ሺህ 800 ሜጋ ዋት ሊደርስ እንደሚችል  ተተንብይዋል፡፡ በመሆነም ይህን ታሳቢ ያደረግ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መሰራታቸውን እና ሊመጣ የሚችል ተጨማሪ የኃይል ፍላጎትን ለማስተናገድ 400 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ለመጠባበቂያነት ዝግጁ መደረጉን ገልፀዋል፡፡ የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ለኃይል መቋረጥ ምክንያት እንዳይሆኑ የቅድመ መከላከልና የፍተሻ ሥራዎች መከናወኑንም ጠቁመዋል፡፡ ከፍተኛ ጭነት በሚበዛባቸው ሰዓታት በመካከለኛና ዝቅተኛ መስመሮች ላይ ጫና እንዳይፈጠር የኃይል አጠቃቀምን ማስተካከል እንደሚገባ አቶ ሚኪያስ አሳስበዋል። እንደ ሥራ አስኪያጁ ገለጻ ለበዓሉ በቂ ኃይል ዝግጁ በመደረጉ ከተቋሙ በቀጥታ ኃይል የሚያገኙ የዳታ ማይኒንግ ኩባንያዎች፣ ከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚዎች እና ኤክስፖርት ላይ ከወትሮ የተለየ አጠቃቀም አይኖርም። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠https://twitter.com/EEPethiopia ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power ዩትዩብቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ሚያዝያ 11 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content

የቀጣይ መቶ ቀናት ዕቅዶቻችንን በሙሉ ልብና ፍላጎት ተረባርበን እናሳካለን ---///--- የቀጣይ መቶ ቀናት ዕቅዳችንን በሙሉ ልብ ተረባርበን በመሥራት ለስኬት እናበቃለን ሲሉ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የምሥራቅ አንድ ሪጅን አመራሮችና ሠራተኞች ተናገሩ። ሪጅኑ በስሩ የሚገኙ የኃይል ማስተላለፊያና ማከፋፈያ ጣቢያ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞችን ያሳተፈ የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የመጨረሻ ሩብ ዓመት የመቶ ቀናት ዕቅድ ላይ በድሬድዋ ከተማ ውይይት አካሂዷል፡፡ የምሥራቅ ሪጅን አንድ ዳይሬክተር አቶ ወርዲ መሐመድ በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት ለውይይት የቀረበውን የመቶ ቀናት ዕቅድ ተፈፃሚ በማድረግ በየደረጃው ያሉ ሁሉም  የሪጅኑ ሠራተኞችና ኃላፊዎች በንቃትና በመሉ የኃላፊነት ስሜት እንዲሁም ቁርጠኝነት በርብርብ እንዲፈፀም አሳስበዋል። በሪጅኑ የትራንስሚሽንና ሰብስቴሽን የሰው ኃይል አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ኃላፊ ወ/ሮ ኤልሳቤት ዳባ በበኩላቸው ለተሰብሳቢዎች ባስተላለፉት መልዕክት  ሁሉም የሰብስቴሽን እና የትራንስሚሽን ኃላፊዎች ዕቅዱን ለማሳካት የሚያስችላቸውን የድርጊት መርኃ ግብር አዘጋጅተው በንቃት እንዲተገብሩ ጠቁመዋል። ዕቅዱ ተዘጋጅቶ መቅረቡ ይበል የሚያሰኝ መሆኑን የገለፁት የመድረኩ ተሳታፊዎች በቀረበው ሰነድ ላይ በቂ ውይይት መደረጉ የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ አስችሏል። ይህም በዘርፉ የተናበበ ዕቅድና የጋራ አፈፃፀም እንዲኖር የሚግዝ መሆኑን አብራርተዋል።  ተሳታፊዎቹ አክለውም የቀረበለቸውን ዕቅድ ለመፈፀምና ከግብ ለማድረስ መሟላት ያለበትን የመስሪያ ቁስና ሠው ኃይል ግብዓቶችን በዝርዝር በመወያየት ለቀጣይ አፈፃፀም ተግተው እንደሚሠሩ የጋራ አቋማቸውን አስታውቀዋል። የምሥራቅ ሪጅን  አንድ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በድሬደዋ በተዘጋጀው የጋራ መድረክ የ2017 ዓ.ም የመጨረሻ ሩብ አመት የመቶ ቀናት ዕቅድ ፀድቋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ሚያዝያ 10 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+5

#Vacancy የውጪ ሥራ ቅጥር ማስታወቂያ 🌟 ……///…. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (ኢኤኃ) በጁኒየር ኤሌክትሪካል መሐንዲስ እና በጁኒየር ሜካኒካል መሐንዲስ የስራ መደቦች ብቁ ሠራተኞችን አወዳ
#Vacancy የውጪ ሥራ ቅጥር ማስታወቂያ 🌟 ……///…. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (ኢኤኃ) በጁኒየር ኤሌክትሪካል መሐንዲስ እና በጁኒየር ሜካኒካል መሐንዲስ የስራ መደቦች ብቁ ሠራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች በሚከተሉት ሊንኮች መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡ 🔗 Link 1      🔗 Link 2 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ሚያዝያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም

ሪጅኑ ሲያካሂድ የቆየውን የዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ አጠናቀቀ ...///... በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የምስራቅ ሪጅን አንድ ለሁለት ቀናት በድሬደዋ ሲያካሂድ የቆየውን የ2017 ዓ.ም የዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ በዛሬው እለት አጠናቋል። በመዝጊያ መረኃ ግብሩ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር ሥራ አስፈፃሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌትነት መኮንን ማህበሩ ከተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ያደረጋቸው የሁለትዮሽ ህብረት ስምምነት አስመልክቶ ገለፃ አድርገዋል። አቶ ጌትነት እንደተናገሩት ማህበሩ የሠራተኛውን ሁለንተናዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚያስችሉ በርካታ ጉዳዮች ላይ በመደራደር አመርቂ ስራዎች መሠራታቸውን አመላክተዋል። የሠራተኞች ዝውውር፣ የደረጃ ዕድገት፣ የደሞዝ ማሻሻያ፣ የትራንስፖርትና የቤት አበል፣ የበረሃ አበል፣ የህክምና ወጪን የመሳሰሉ በርካታ ጉዳዮችን በህብረት ስምምነቱ በመደራደር የሰራተኛውን ጥቅም በማረጋጋጥ የተሄደበትን ርቀት ገልፀው የስምምነቱ አጠቃላይ ይዘትና ትግበራ በሚቀጥለው ግንቦት አንድ 2017 ዓ.ም ይፋ እንደሚሆንም አስታውቀዋል። በመድረኩ ሲሳተፉ የቆዩ የሪጂኑ ሠራተኞች እንዲሁም የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ እና ማስተላለፊያ መስመር ኃለፊዎች፣ የጥገና ቡድን ባለሙያዎች፣ የኦፐሬሽን ባለሙያዎች፣ የቡድን መሪዎች፣ አሽከርካሪዎች እና የጥበቃ ሰራተኞች ላነሷቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ተሰጥቷል። በመርኃግብሩ ማጠቃለያ ሪጅኑ በስሩ ከሚገኙ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ባለፉት ዘጠኝ ወራት የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ሦስት ጣቢያዎችን ጨምሮ የማስተላለፊያ መስመር ሰራተኞች፣ የጥገናና የኦፕሬሽን ሰራተኞች፣ አሽከርካሪዎች እንዲሁም የሪጅኑ የአስተዳደር ሰራተኞችን የዕዉቅና የምስክር ወረቀት አበረክቷል። የምስክር ወረቀት የተበረከተላቸው ጣቢያዎች።፣ የቡድን መሪዎች እና ሰራተኞች በተዘጋጀላቸዉ ሽልማት መደሰታቸውን ገልፀዉ ለቀጣይ የተጠናከረ ስራ መሰረት እንደሚሆናቸው ገልፀዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ሚያዝያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+6

የተቋሙ ሠራተኞችና የሥራ መሪዎች በመንግስት የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት አፈፃፀም ላይ ተወያይተዋል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች በመንግስት የ2017 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ በዛሬው ዕለት ተወያይተዋል። በውይይቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተወካይ እና የኢንጅነሪንግና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዘርፍ ም/ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጅነር ውድነህ የማነ እንደገለፁት ውይይቱ ሠራተኞችና የሥራ መሪዎች ሃገራዊና ዓለም አቀፋዊ አውዱን እንዲገነዘቡ ለማድረግ ያለመ ነው። ውይይቱ በዘጠኝ ወሩ ውስጥ እንደ ሃገር በተመዘገቡ ስኬቶች፣ ባጋጠሙ ችግሮች፣ ለችግሮቹ በተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎች እና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር እንዲሁም ተቋሙ ለሀገሪቱ እድገት እያበረከተ ያለውን አስተዋፅኦ በማሳወቅ የቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ እንደሚረዳ ተናግረዋል። በዕለቱም ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ አዝማሚያዎችና በኢትዮጵያ የሚኖረው አንደምታ፣ የማክሮ ኢኮኖሚ እና የሪፎርሙ አፈፃፀም ውጤቶችና አዝማሚያዎች፣ የዋና ዋና መሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች አፈፃፀም፣ ቀጣይነት ባላቸው የዘላቂ ልማቶች፣ በአስቻይ ሁኔታዎች እና በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን የተመለከተ የመወያያ ሰነድ በተቋሙ የትራንስሚሽን ቢዝነስ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ በኢንጅነር አንዷለም ሲዓ ቀርቧል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው የኢኮኖሚ አዝማሚያ በኢትዮጵያ ላይ የሚያሳድረውን አዎንታዊና አሉታዊ አዝማሚያዎቸ በመለየት የተለያዩ ክንውኖች ሲደረጉ እንደነበር ገልፀዋል። በሀገሪቱ የተደረገው ሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ኢኮኖሚያዊ መረጋጋትትን ማረጋጋጥ፣ ኢንቨስትመንትን ማሻሻል፣ የመንግስት የመፈፀም አቅም ማጎልበት እና ምርታማነትንና ተወዳዳሪነትን ማሳደግ ላይ ትኩረት ያደረገ እንደሆነም  አስረድተዋል። ማሻሻያውን ጨምሮ በተቋማት ላይ እየተከናወኑ ያሉ የለውጥ ሥራዎች ተቋሙን በዕዳ ሽግሽግና በሌሎች የተለያዩ ጉዳዮች ተጠቃሚ ማድረጉን ም/ዋና ሥራ አስፈፃሚው አስታውቀዋል። የኤሌክትሪክ ዘርፉ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት በኩል የድርሻውን እየተወጣ መሆኑን የተናገሩት ኢንጂነር አንዷለም  በዚህም ተቋሙ በሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ከሚያስገኙ ተቋማት በአምስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጡን አስታውቀዋል፡፡ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከኤሌክትሪክ ዘርፉ 230 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ መገኘቱንም ጠቁመዋል፡፡ በዘጠኝ ወራት ውስጥ በሃገሪቱ እየተካሄዱ የሚገኙ የዋና ዋና ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ውጤታማ እንደነበር የተናገሩት ኢንጅነር አንዷለም በኃይል ማመንጫ ዘርፍም የታላቁ ህዳሴ ግድብ 98 ነጥብ 66፣ ኮይሻ 71 ነጥብ 37፣ አይሻ 84 ነጥብ 8 እንዲሁም አሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት 82 ነጥ 31 በመቶ መድረሳቸውን አብራርተዋል። ሃገሪቱ እያመነጨችው ያለው ኤሌክትሪክ ኃይል ለቤት ውስጥ መብራት ብቻ ሳይሆን ኢንዱስትሪንና ኢንቨስትመንት ለማስፋፋት እንዲሁም በቀጣናው ላይ ተፅዕኖ ለመፍጠር እንደሚረዳ ተናግረዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ከዋጋ ግሽበትና የኑሮ ውድነት፣ በሀገሪቱ በሚስተዋለው የፀጥታ ችግር፣ ከኮሪደር ልማት አተገባበር፣ ሠራተኛውን ተጠቃሚ ለማድረግ እየከናወኑ ባሉ ሥራዎች ላይ ትኩረት ያደረጉ ጥያቄዎችና አስተያየቶችን አንስተዋል። ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ማብራሪያ የሰጡት የኮርፖሬት ፋይናንስ እና ሃብት አስተዳደር ዘርፍ ም/ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ደመረ አሰፋ እንደተናገሩት በሀገሪቱ እየተከናወኑ ያሉ የኮሪደር ልማቶች ለቀጣይ ትውልድና ለኢኮኖሚው የሚኖረውን ሚና በመገንዘብ ነው እየተከናወነ የሚገኘው። የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ  ተወካይ እና የኢንጅነሪንግና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዘርፍ ም/ዋና አስፈፃሚ ኢንጅነር ውድነህ የማነ በበኩላቸው የኮሪደር ልማቱ ኢንቨስትመንትን፣ ቱሪዝምን እና ታላላቅ አህጉርና ዓለም አቀፍ መድረኮች በሀገሪቱ እንዲካሄዱ እየሳበ ይገኛል ብለዋል። የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት በመንግስት እየተደረገ ካለው ድጎማ ባለፈ ችግሮቹን በዘላቂነት ለመፍታትም የማምረት አቅም ማሳደግ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ሚያዝያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+1

photo content
+9

የሪጅኑን የበጀት ዓመት ዕቅድ ለማሳካት ሁሉም መረባረብ አለበት …..///….. በሪጅኑ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የነበሩ ክፍተቶችን በማረም በቀሪ ወራት የበጀት ዓመቱን ዕቅድ ለማሳካት ሁሉም ሊረባረብ እንደሚገባ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የምስራቅ ሪጅን አንድ ዳይሬክተር አሳሰቡ፡፡ ሪጅኑ በስሩ የሚገኙ የማከፋፈያ ጣቢያ የሥራ ኃላፊዎች፣ የኦፕሬሽንና የጥገና ባለሙያዎች በተገኙበት የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ በድሬድዋ ከተማ እያካሄደ ነው፡፡ የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ ወርዲ ሙሐመድ እንደገለፁት ለሁለት ቀናት የሚካሄደው ግምገማ የሪጅኑን የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀም፣ ያጋጠሙ ችግሮች እና የተወሰዱ የመፍትሄ ርምጃዎች ላይ ውይይት በማድረግ የኦፕሬሽንና የጥገና ሥራዎች ያሉበትን ደረጃ ለማወቅ እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ያለመ ነው፡፡ ሁሉም የሪጅኑ አመራርና ሠራተኛ በተቋሙ እየተከናወነ ያለውን የሪፎርም ሥራ በሚደግፍ መልኩ የኦፕሬሽን ሥራዎችን በአግባቡ ማከናወን እንዳለበትም ጠቁመዋል፡፡ በግምገማው በተለያየ ጊዜ በችግር መልክ ሲነሱ የቆዩና መፍትሄ ያላገኙ ጉዳዮችን በመለየት በቀጣይ በሚፈቱበት አግባብ ዙሪያም አቅጣጫ እንደሚቀመጥ አመልክተዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ ሪጅኑ ያቀዳቸውን ተግባራት በሙሉ ለማከናወን ባለፉት ዘጠኝ ወራት ያልተከናወኑ ተግባራትንና በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ለማከናወን የታቀዱ ሥራዎችን በማካተት የመቶ ቀን ዕቅድ መዘጋጀቱን የጠቆሙት አቶ ወርዲ አመራሩና ሠራተኛው በዕቅዱ ላይ የጋራ መግባባት ኖሯቸው ወደ ሥራ እንዲገቡ ውይይት እንደሚደረግበትም አብራርተዋል። የሪጅኑ የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም በድሬደዋ ቁጥር ሁለት ማከፋፈያ ጣቢያ የኦፕሬተር ባለሙያ አቶ በሱፍቃድ ባዩ ቀርቧል፡፡ አስተማማኝና ያልተቆራረጠ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር በሪጅኑ ሥር ባሉ የማከፋፍያ ጣቢያዎችና ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ጊዜውን የጠበቀ የቅድመ መከላከል፣ የትንበያ፣ የፍተሻ ጥገና ሥራዎች እንዲሁም የማዘመን ሥራዎች በራስ አቅም ጭምር መከናወናቸው በሪፖርቱ በጥንካሬ ተነስቷል፡፡ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ስርቆት እና የማስተላለፊያ መስመሮች በቀለበት አለመያያዛቸው በክፍተት የተጠቀሰ ሲሆን በቀረበው ሪፖርት ላይ በተሳታፊዎቹ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል፡፡ የምስራቅ ሪጅን አንድ በስሩ ዘጠኝ የማከፋፈያ ጣቢያዎችን እና 1950 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ማስተላለፊያ መስመሮችን ያስተዳድራል፡፡ ግምገማው በነገው ዕለትም የሚቀጥል ይሆናል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠https://twitter.com/EEPethiopia ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power ዩትዩብቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ሚያዝያ 8 ቀን 2017 ዓ.ም