es
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

Ir al canal en Telegram

EEP Communication

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram EEP Communication

El canal EEP Communication (@eepcommuication) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 15 572 suscriptores, ocupando la posición 8 384 en la categoría Tecnologías y Aplicaciones y el puesto 2 165 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 15 572 suscriptores.

Según los últimos datos del 23 junio, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de 0, y en las últimas 24 horas de -2, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 25.89%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 15.48% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 4 026 visualizaciones. En el primer día suele acumular 2 408 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 9.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
EEP Communication

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 24 junio, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Tecnologías y Aplicaciones.

15 572
Suscriptores
-224 horas
-37 días
Sin datos30 días
Archivo de publicaciones
በከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ በተፈፀመ ስርቆት አራት ታወሮች ወድቀዋል ………///……… ከባህርዳር - ወልዲያ - ኮምቦልቻ በተዘረጋው ባለ 400 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ በተፈፀመ ስርቆት አራት የኃይል ተሸካሚ ምሶሶዎች መውደቃቸውን ፕሮጀክቱ አስታወቀ፡፡ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የባህርዳር - ወልዲያ - ኮምቦልቻ ፕሮጀክ የሳይት ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮሐንስ ኪሮስ እንዳስታወቁት ስርቆቱ የተፈፀመው መጋቢት 2 ቀን 2017 ዓ.ም በደቡብ ጎንደር ደብረታቦር ከተማ አቅራቢያ ጉና ወረዳ ነው። በተፈፀመው ስርቆት አራት የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎች በሙሉ መውደቃቸውን ያረጋገጡት ሥራ አስኪያጁ በስርቆቱ 129 ሚሊዮን ብር የሚገመት ኪሳራ በተቋሙ ላይ ደርሷል ብለዋል። በስርቆትና በፀጥታ መደፍረስ ሲፈተን የቆየውን ፕሮጀክት በማጠናቀቅ ከግሪድ ጋር ለማገናኘት ተቋሙ ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ በሚገኝበት ወቅት ችግሩ መፈጠሩ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ የፕሮጀክቱ አፈጻጸም 87 በመቶ ቢደርስም በፕሮጀክቱ ላይ የሚፈፀሙ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ስርቆቶች ለሥራው እንቅፋት መሆናቸውን ሥራ አስኪያጁ አመልክተዋል። ስለሆነም ቀሪ የፕሮጀክቱን ሥራዎች በአጭር ጊዜ አጠናቆ አገልግሎት ለማስጀመር ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለችግሩ ልዩ ትኩረት ሊሰጡት እንደሚገባ አሳስበዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+6

ከፕሮጀክቱ የዕውቀትና ቴክኖሎጅ ሽግግር እየተገኘ ነው ………///……… ከደቡባዊ የኤሌክትሪክ ግሪድ ማስፋፊያ ፕሮጀክት የዕውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር እየተገኘበት መሆኑን በፕሮጀክቱ የሳይት ሁለት ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ፡፡ ሥራ አስኪያጁ አቶ አርጋዉ ታዲ እንዳስታወቁት በደቡባዊ የኤሌክትሪክ ግሪድ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ሳይት ሁለት በሚከናወኑ የማከፋፈያ ጣቢያና ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት ላይ 80 የውጭ ሀገር ዜጎች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡ ከግንባታ ሥራዎቹ የዕውቀት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖር ለማድረግ በሥራው ላይ እየተሳተፉ ያሉ ኢትዮጵያዊያንን ከውጭ ሀገር ዜጎች ጋር በማቀናጀት እንዲሰሩ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡ ይህም ወደፊት የሚከናወኑ ሥራዎችን በራስ ኃይል ለማከናወን የሚያስችል አቅም ለመፍጠርና የሥራ ባህልን ለማሳደግ እንደሚያግዝ ነው አቶ አርጋው ያስታወቁት፡፡ በባዮክሰን ኢንጂነሪንግ አማካሪ ሲቪል መሃንዲስ አቶ አብርሃም ደሳለኝ በበኩላቸው የውጭ ሀገራት ዜጎች በፕሮጀክቱ የግንባታ ሥራዎች መሳተፋቸው ብቁ ሠራተኞችን ለማፍራት ያግዛል ብለዋል፡፡ በሽግዳን ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ የሲቪል መሐንዲስ የሆኑት አቶ መኮንን ጥላሁን በበኩላቸው እንደተናገሩት ከውጭ ሀገር ዜጎች ጋር መስራቱ ክህሎትን ለማዳበር፣ ቴክኖሎጂና ልምድ ለመቅሰም ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡ በሽግዳን ማከፋፈያ ጣቢያ በረዳት ፎርማንነት እየሰራ የሚገኘው አሳየኸኝ አሻግሬ እንደገለፀው ወደ ፕሮጀክቱ ከመቀላቀሉ በፊት ከሹፍርና ውጭ ከግንባታ ሥራዎች ጋር በተያያዘ ምንም አይነት ዕውቀትና  ልምድ አልነበረውም፡፡ ይሁንና ፕሮጀክቱን በተቀላቀለ በአንድ አመት ከስድስት ወር ውስጥ የተለያዩ ሙያዎች ባለቤት እንደሆነና ለዚህ ደግሞ ከውጭ ዜጎች ጋር አብሮ መስራቱ ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚወስድ ተናግሯል፡፡ በሳይት ሁለት በሚከናወኑ የሽግዳንና ቲርጋ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች እንዲሁም ከሳውላ ቲርጋ በሚዘረጋው የማስተላለፊያ መስመር ላይ ከአንድ ሺህ በላይ ሠራተኞች እየተሳተፉ መሆናቸውን ከዚህ በፊት መዘገባችን ይታወሳል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et መጋቢት 3 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+6

በማስፋፊያ ሥራ ተጨማሪ 310 ሜጋ ዋት ኃይል ማግኘት ተችሏል ……….///…… በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለፉት አምስት ዓመታት በማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ በተከናወኑ የአቅም ማሳደግና የማዘመን ሥራዎች ተጨማሪ 310 ሜጋ ዋት ኃይል ማግኘት መቻሉን በተቋሙ የሪጅኖች ማስተባበሪያ መምሪያ  አስታወቀ፡፡ የመምሪያው ዳይሬክተር አቶ ጋሻው እንድሪያስ እንዳስታወቁት ከከተሞችና ከኢንዱስትሪ መስፋፋት ጋር ተያይዞ በየጊዜው እያደገ የመጣውን የኃይል ፍላጎት ለማሟላት ከአዳዲስ የኃይል መሰረተ ልማት ግንባታዎች በተጨማሪ በነባር ማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ የአቅም ማሳደግ፣ የማስፋፊያ እና ማዘመን ሥራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡ የማከፋፈያ ጣቢያዎች ዕድሜ፣ የኃይል ጭነት ከመጠን በላይ መሆን እና በጣቢያዎች ላይ በሚከሰቱ ድንገተኛ ችግሮች በዕቃዎች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች ለአቅም ማሳደግ እና ማሻሻያ ሥራዎች መከናወን ምክንያት እንደሆኑ አስረድተዋል፡፡ ሥራው በስዊች ጊሮች፣ ትራንስርመሮች፣ ቮልቴጁን በሚያመጣጥኑ ሸንት ሪያክተሮች እና በሌሎች ዋና ዋና የማከፋፈያ ጣቢያ አካላት ላይ እንደሚከናወንም ዳይሬክተሩ ጠቅሰዋል፡፡ እንደ አቶ ጋሻው ገለፃ ባለፉት አምስት ዓመታት በነባር ማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ 22 የሚሆኑ ፓወር ትራንስፎርመሮችን በመትከል 310 ሜጋ ዋት ተጨማሪ ኃይል ማግኘት ተችሏል፡፡ የጣቢያዎቹን የመቆጣጠሪያ ብሬከሮች (swichgear) አቅም የማሳደግና የማዘመን ሥራዎች በመሰራታቸው ትራንስፎርመሮቹ በተሻለ አቅም እንዲሰሩ ማድረግ መቻሉን አስታውቀዋል፡፡ በ75 ማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ ለማከናወን ከታቀደው የመቆጣጠሪያ ብሬከር ቅየራ ሥራዎች እስከ አሁን የ25ቱ መጠናቀቁን የጠቆሙት ዳይሬክተሩ በተያዘው ዓመት የአስር ጣቢያዎችን ለማጠናቀቅ ታቅዶ እየተሰራ ነውም ብለዋል፡፡ ቦሌ ለሚ፣ ሻሸመኔ፣ ጂግጂጋ፣ በደሌ፣ ሐረር II እና III፣ ወልቂጤ፣ ደብረ ታቦር፣ ጊንጭ፣  ደብረ ብርሃን፣ ድሬዳዋ II እና III፣ አሸጎዳ፣ ገላን፣ ሆሳዕና፣ ባህርዳር II፣ ጌዶ እና ጋሸና ማከፋፈያ ጣቢያዎች የአቅም ማሳደግ፣ ማስፋፊያ እና የማዘመን ሥራዎች ከተከናወኑባቸው  መካከል ተጠቃሾች ናቸው፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et መጋቢት 2 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+6

ለሠራተኞች የሥራ ላይ ደህንነት ቅድሚያ ተሰጥቶ እየተሠራ ነው ……..///……… በግንባታ ሥራ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ ሠራተኞችን ጤንነትና ደህንነት ለመጠበቅ ለሥራ ላይ ደህንነት ቅድሚያ ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የደቡባዊ የኤሌክትሪክ ግሪድ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ሳይት ሁለት አስታወቀ፡፡ የፕሮጀክቱ ሥራ ተቋራጭ ሃይሰን ሄቪ ኢንደስትሪ ኮርፖሬሽን የሳይት ሁለት የሥራ ቦታ ደህንነትና የሠራተኛ ጤንነት ቁጥጥር ሥራ አስኪያጅ አቶ ባህሩ በቀለ እንዳስታወቁት የቲርጋና ሽግዳን ማከፋፈያ ጣቢያዎች እና የማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት ከከተማ ርቆ የሚገኝ በመሆኑ የሚያጋጥሙ አደጋዎችን ቀድሞ ለመከላከል እና የሠራተኞችን ጤንነት ለማረጋገጥ በሳይቱ የሥራ ላይ ደህንነት የሥራ ክፍል በማቋቋም ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡ በግንባታ ሥራ ላይ የሚሳተፉ ሠራተኞች ለተለያዩ አደጋዎች ተጋላጭ በመሆናቸው በሥራ ላይ የሚደርሱ የተለያዩ አደጋዎችን ለመከላከል የሚያስችሉ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ ሠራተኛው ሥራ ከመጀመሩ በፊት ስለ አደጋ አጋላጭ ሁኔታዎች፣ ስለአደጋ መከላከያ መንገዶች፣ ሠራተኞች በስራ ቦታቸው ላይ ስለሚኖራቸው እንቅስቃሴ እንዲሁም ከደህንነት መሳሪያዎች አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የግንዛቤ ማስጨበጫ በየጊዜው እንደሚሰጥ አመልክተዋል፡፡ በሥራው ላይ አደጋ ቢያጋጥም ለተጎጂዎቹ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት በሥራ ቦታዎች ላይ የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ ክፍል  መዘጋጀቱንና ከአቅም በላይ ከሆነ ደግሞ ወደ ህክምና ተቋማት የሚላኩበት አሰራር መዘርጋቱን ሥራ አስኪያጁ አንስተዋል፡፡ የሥራ ላይ ደህንነት መጠበቂያ መንገዶችን በማያከብር ሠራተኛ ላይ እስከ ሥራ ማሰናበት የሚደርስ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድም አስታውቀዋል፡፡ እንደ አቶ ባህሩ ገለፃ ሠራተኛው የሥራ ላይ ደህንነት ጉዳይን ባህል በማድረጉ እና አስፈላጊው ክትትልና ቁጥጥር በመደረጉ እስከ አሁን ምንም አይነት አደጋ አላጋጠመም፡ በሽግዳን ማከፋፈያ ጣቢያ የግንባታ ሥራ ላይ በአናፂነትና በረዳት ፎርማን እየሰሩ የሚገኙት  ጃኪ አይቾሚ እና አሳየኸኝ አሻግሬ በበኩላቸው በፕሮጀክቱ የሥራ ቦታ ለአደጋ እንዳይጋለጡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከመስጠት ጀምሮ የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች እንደሚቀርብላቸው ተናግረዋል፡፡  የሚሰጣቸውን የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎችን በአግባቡ በመተግበር ደህንነታቸውን ጠብቀው እየሠሩ እንደሆነም አረጋግጠዋል፡፡ በደቡባዊ የኤሌክትሪክ ግሪድ ማስፋፊያ ፕሮጀክት በሳይት ሁለት በሚከናወኑ የግንባታ ሥራዎች ላይ ከአንድ ሺ በላይ ሠራተኞች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+7

በጣቢያው የፍተሻና የሙከራ ሥራ ለማከናወን የሚያስችል የዝግጅት ሥራ እየተሰራ ነው ……..///…….. የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ የባለ 230 ኪሎ ቮልት የማከፋፈያ ጣቢያ የፍተሻና የሙከራ ሥራ ለማከናወን የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሰራ መሆኑን የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ተናገሩ፡፡ ሥራ አስኪያጁ አቶ ጌቱ ያደታ እንደተናገሩት የተጠናቀቁ የንፋስ ማማዎችን ከቆቃ- መልካዋከና ከሚያልፈው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጋር በማገናኘት ኤሌክትሪክ ወደ ብሔራዊ የኃይል ቋት ለማስገባት ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ ፕሮጀክቱ በተለያዩ ምክንያቶች በዕቅዱ ከተቀመጠው ጊዜ በላይ ቢወስድም በአሁኑ ወቅት በንዑስ ሥራ ተቋራጮቹ አማካኝነት የ20ዎቹ ተርባይኖች የቅድመ ፍተሻ ሥራ መከናወኑን ተናግረዋል። እንደ ሥራ አስኪያጁ ገለፃ በኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው ላይ የሙከራና የፍተሻ ሥራው ከተጠናቀቀ በኋላ የቅድመ ፍተሻ የተከናወነላቸውን ተርባይኖች በሂደት ወደ ግሪድ የማስገባት ሥራ ይሰራል። በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ በየሳምንቱ 10 ሜጋ ዋት በድምሩ 80 ሜጋ ዋት ወደ ብሔራዊ የኃይል ቋት ለማስገባት ታቅዶ እየተሰራ ነው ብለዋል። በፕሮጀክቱ የተቋሙ የራስ ኃይል መምሪያ ተወካይ አስተባባሪ አቶ ቴዎድሮስ ጋሻው በበኩላቸው የራስ ኃይል መምሪያ በፕሮጀክቱ የሁለት የኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎችና የሽቦ ዝርጋታ ሥራን በ3 ክሬኖች እያከናወነ ነው ብለዋል። ሥራውን በሁለት ቀናት ውስጥ በማጠናቀቅ ከቆቃ-መልካዋከና ከተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የማስተላለፊያ መስመር ላይ በመቀጠል የማከፋፈያ ጣቢያውን ለሙከራና የፍተሻ ሥራ ዝግጁ ለማድረግ እየተሰራ ነው። በተመሳሳይ የበቆጂ ባለ230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ የፍተሻና የሙከራ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል። የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ እንደ አገር ከንፋስ የሚመነጨውን ኃይል ከ404 ሜጋ ዋት ወደ 504 ሜጋ ዋት ከፍ በማድረግ የኃይል ስብጥሩን ለማሳደግና አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ ያስችላል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+7

ክልሉ በአዋሽ-ወልዲያ- ሃራ ገቢያ የባቡር የኃይል አቅርቦት ፕሮጀክት ላይ የተፈፀመውን የስርቆት ወንጀል አወገዘ .......///........ የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በአዋሽ-ወልዲያ-ሃራ ገቢያ የባቡር የኃይል አቅርቦት ፕሮጀክት ላይ የተፈፀመውን የስርቆት ወንጀል በፅኑ እንደሚያወግዝ አስታውቋል። በአስር ቀናት ውስጥ ብቻ ከ80 ኪሎ ሜትር በላይ የኮንዳክተር ሽቦ ገመድ እና 25 ነጥብ 7 ኪሎ ሜትር የኦ.ፒ.ጂ ደብሊው ፋይበር መስመር ለስርቆት መዳረጉን ተከትሎ የክልሉ መንግሥት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም ያላቸውን የወረዳ የሥራ ኃላፊዎች ከሥልጣን ማንሳቱንም ገልጿል። በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሃጂ አወል አርባ የተዋቀረ ኮማንድ ፖስት የስርቆት ወንጀሉ በተፈፀመባቸው የገቢረሱ ዞን ሁለት ወረዳዎች ላይ ትናንት የመስክ ምልከታ አድርጓል። የክልሉ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት፣ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የሰላምና ፀጥታ ዘርፍ፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ጠቅላይ አቃቤ ህግ ኃላፊዎችን ያካተተው ኮማንድ ፖስት ከሁሉም የዞንና ወረዳ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ተወካዮች ጋር ውይይት አድርጓል። ውይይቱ በክልሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ የመጣውን የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ስርቆት በጋራ ለማውገዝና በወንጀሉ ዙሪያ አፋጣኝ እርምጃ ለመውሰድ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ለመምከር ያለመ ነው። በውይይቱ ላይ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአዋሽ-ወልዲያ-ሃራ ገቢያ የኃይል አቅርቦት ፕሮጀክት ሳይት ሥራ አስኪያጅ አቶ ተክለወይን ብርሃነአሰፋ በ2016 እና 2017 በጀት ዓመት በገቢረሱ ዞን ስር በሚገኙ ወረዳዎች ስለተፈፀሙ የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች፣ የኮንዳክተር ሽቦ እና የኦፕቲካል ፋይበር መስመር ስርቆት መጠንና ስርቆቱ በተቋሙ ላይ ስላደረሰው ኪሳራ ለተወያዮቹ ገለፃ አድርገዋል። በክልሉ በሁለቱ በጀት ዓመት ብቻ በኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ በተፈፀመ ስርቆት ሳቢያ ከ717 ሺህ ዶላር በላይ እና ከ25 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ መድረሱን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰሜን ምስራቅ ሁለት ሪጅን የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ሀሰን መሐመድ እንደገለፁት ሪጅኑ ሦስት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎችን እና ከ436 ኪሎ ሜትር በላይ የሚሸፍኑ የማስተላለፊያ መስመሮችን ያስተዳድራል። ተቋሙ ለህብረተሰቡ ኤሌክትሪክ ለማዳረስ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ በኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎችና የኮንዳክተር ሽቦ ላይ የሚፈፀመው የስርቆት ወንጀል ማነቆ እንደሆነ አስረድተዋል። በውይይቱ ላይ የዞንና የወረዳ እንዲሁም  የፀጥታ ዘርፍ አካላት በኃላፊነት ስሜት መንቀሳቀስ አለመቻላቸው በኃይል መሰረተ ልማቶቹ ላይ ከፍተኛ የዝርፊያ ወንጀል እንዲፈፀም በር ከፍቷል ተብሏል። የስርቆት ወንጀሉን ከምንጩ ለማድረቅ በየደረጃው ያሉ ሁሉም የክልሉ አመራሮች በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባም ነው ኮማንድ ፖስቱ አቅጣጫ ያስቀመጠው። ኮማንድ ፖስቱ በክልሉ የሚገኙ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን ደህንነት ለመጠበቅ ያስችላል ያለውን የመግባቢያ ሥምምነት ከሁሉም የዞንና የወረዳ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተፈራርሟል። ሥምምነቱ በኃይል መሰረተ ልማት ስርቆት ላይ የሚሳተፉ ወንጀለኞችን ተከታትሎ ለፍርድ ለማቅረብና በየደረጃው በሚገኙ አመራሮች ላይ ተጠያቂነትን ለማስፈን እንዲያስችል እንዲሁም ወንጀሉ ዳግም እንዳይከሰት ለማድረግ ያስችላል ተብሏል። ህብረተሰቡ መሰረተ ልማቶቹን በእኔነት ስሜት እንዲጠብቅ ለማድረግ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ እስከታችኛው የክልሉ የአስተዳደር መዋቅር ድረስ በአስቸኳይ እንዲሰራም ውሳኔ ላይ ተደርሷል። በውይይቱ ላይ የአፋር ክልል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጎልቤ ሲሌን ጨምሮ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሙሳ አብዶ፣ የክልሉ የሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ሁሴን መሐመድ፣ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢስማኤል መሐመድ እና የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ቢልኤ አህመድ እንዲሁም የዞንና የወረዳ የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+7

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ለዘመናት በሴቶች ላይ ተንሰራፍቶ የቆየው ጭቆናና በደል ያንገሸገሻቸው ሴቶች ዝቅተኛ የሥራ ሰዓት፤ የተሻለ ክፍያ እና የመምረጥ መብታቸው እንዲከበርላቸው ባካሔዱት ትግል የሴቶች ቀን እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ1909 በአሜሪካ ሶሻሊስት ፓርቲ ውሳኔ መሰረት ለመጀመሪያ ጊዜ በብሔራዊ ደረጃ በአሜሪካ ተከበረ፡፡ በቀጣዩ ዓመትም በዴንማርክ ኮፐንሃገን በተካሄደው ሁለተኛው ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ በዓለም ላይ የሚገኙ ሴቶች ፍላጎታቸውን በሚገባ ማንፀባረቅ እንዲችሉ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን እንዲከበር ሃሳብ ቀረበ፡፡ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በተሳታፊዎች ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት በማግኘቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በኦስትሪያ፤ ጀርመንና ሲውዘርላንድ እ.ኤ.አ በ1911 ማርች 19 ተብሎ ተከበረ፡፡ በዚህ ሥነ-ሥርዓት ላይም ሴቶች መብቶቻቸው እንዲከበሩ እና በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጭቆናዎች እንዲቆሙ የተለያዩ ንቅናቄዎች ተካሂደዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ1913 በተካሄዱ ውይይቶች ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በየዓመቱ ማርች 8 እንዲከበር ውሳኔ ላይ የተደረሰ ሲሆን ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ቀኑ በተለያዩ ፕሮግራሞችና መሪ ቃሎች እየተከበረ ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያም በዓሉ መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማትና ድርጅቶች በተለያዩ መርሃ ግብሮች የሚከበር ሲሆን የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንም /ማርች 8/ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ114ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ49ኛ ጊዜ "ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል’’ በሚል መሪ ቃል መካሄድ ጀምሯል፡፡ ቀኑ የሴቶችን የልማት ህብረቶችን በማቋቋምና ማጠናከር፤ የቁጠባ ባህል እንዲዳብር በማድረግ፤ ምርትና አገልግሎታቸውን በኢግዚቢሽንና ባዛር እንዲያስተዋውቁና እንዲሸጡ ሁኔታዎችን በማመቻቸት የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ፤ የማህፀንና የጡት ጫፍ ካንሰር ምርመራ እንዲያደርጉ ንቅናቄ በመፍጠርና አገልግሎቱን በማመቻቸት እንዲመረመሩ ማድረግ እንዲሁም የህዳሴ ግድብ የቦንድ ንቅናቄ መፍጠርና ሽያጭ ማካሄድ ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልም በዓሉ በተቋሙ የተለያዩ የሥራ ቦታዎች ላይ የሴቶችን መብቶች ለማስከበር በሚያግዙ ጉዳዮች የግንዛቤ ማስጨበጫዎችን በመስጠት ያከበራል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content

ፋብሪካው ያቀረበውን ተጨማሪ የኃይል አቅርቦት ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል ዝግጅት ተጀምሯል ……..///……. የናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ለሚገነባው አዲስ የኢንዱስትሪ ኮምፕሌክስ ያቀረበውን ተጨማሪ የኃይል አቅርቦት ጥያቄ ለመመለስ ከፋብሪካው ጋር ውይይት መጀመሩን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የምሥራቅ አንድ ሪጅን አስታወቀ፡፡ የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ ወርዲ መሀመድ እንደገለፁት  ፋብሪካው ለተቋሙ ላቀረበው የኃይል አቅርቦት ጥያቄ  ምላሽ ለመስጠት ከፋብሪካው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይቶች ተጀምረዋል። በናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ የመልካ ጀብዱ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ አቶ መላኩ ገብሬ በበኩላቸው ፋብሪካው በድሬዳዋ መዳረሻ መልካ ጀብዱ ላይ ሊገነባ ላሰበው የኢንዱስትሪ ኮምፕሌክስ እስከ 600 ሜጋ ዋት ተጨማሪ ኃይል ይፈልጋል ብለዋል። የኢንዱስትሪ ኮምፕሌክሱ የሲሚንቶ ማቀነባበሪያና ማሸጊያ ከረጢቶችን ጨምሮ ለተገጣጣሚ ቤቶች፣ ለኮንክሪት እና ኖራ ማምረቻ እንዲሁም ለኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ግንባታ እና ለተለያዩ ድርጅቶች በግብዓትነት የሚያገለግሉ ምርቶችን የሚያመርቱ ፋብሪካዎችን እንደሚያካትት ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል። እንደ ሥራ አስኪያጁ ገለጻ ፕሮጀክቱን በቅርቡ ለመጀመር የሚያስችሉ የአዋጭነት፣የአካባቢ ደህንነት፣ የመልክዓ ምድር ጥናቶች እና ሌሎች ቅድመ ዝግጅቶች ተጠናቀዋል። የኢንዱስትሪ ኮምፕሌክሱ ለሚፈልገው እስከ 600 ሜጋ ዋት ኃይል ሪጅኑ  የተለያዩ አማራጮችን እያየ መሆኑን  ዳይሬክተሩ አቶ ወርዲ መሀመድ ጠቁመዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+2

ፕሮጀክቱ በአማካይ ከ400 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል  ........///….… የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በአማካኝ ከ400 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ጊዜያዊና ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠሩን የፕሮጀክቱ የሳይት ሥራ አስኪያጅ ገለጹ። ሥራ አስኪያጁ አቶ ፈቃዱ አብርሃም እንደገለፁት ፕሮጀክቱ 29 የንፋስ ማማዎች ተከላን፣ 230 ኪሎ ቮልት ማከፋፍያ ጣቢያን እና 38 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የባለ 33 ኪሎ ቮልት የማስተላለፊያ መስመር ግንባታ ሥራዎችን ያጠቃልላል። ከሥራ ተቋራጩ ጋር በተደረገው ስምምነት መሰረት ከፕሮጀክቱ እስከ 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ያሉ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ቅድሚያ በመስጠት የአካባቢውን ነዋሪዎች የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡ እስካሁን ባለው የፕሮጀክቱ ሂደት በአማካይ ከ400 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የሥራ ዕድል መፍጠሩንና አብዛኛው ተጠቃሚ የአካባቢው ወጣቶች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል ወጣት ቶሎሳ ሮባ እንደገለፀው በፕሮጀክቱ ሥራ ከመጀመሩ በፊት ቋሚ ሥራ ስላልነበረው በሚያገኘው ገቢ ከራሱ አልፎ ቤተሰብን ለማስተዳደር ትልቅ ፈተና ሆኖበት ነበር። በፕሮጀክቱ በተፈጠረለት የሥራ ዕድል ላለፉት 2 ዓመታት መስራቱንና በዚህም እሱን ጨምሮ ሦስት ቤተሰቦቹን ለማስተዳደር የሚያስችል የተሻለ ገቢ ለማግኘት እንዳስቻለው ተናግሯል፡፡ ሌላኛዋ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ወጣት ሙሉ ተካ በበኩሏ በፕሮጀክቱ ሥራ ከመጀመሯ በፊት እሷንና ቤተሰቧን ለማስተዳደር አረብ ሀገር ሄዳ ለመስራት ተገዳ እንደነበረ አንስታለች፡፡ ፕሮጀክቱ በትውልድ ቀየዋ ሥራ ከጀመረ ካለፉት 3 ዓመታት ወዲህ ግን በፕሮጀክቱ ተቀጥራ ቤተሰቧን እያስተዳደረችና ልጆቿን እያስተማረች መሆኑን ገልጻለች፡፡ ፕሮጀክቱ ለአካባቢው ማህበረሰብ የሥራ ዕድል ከመፍጠሩም ባለፈ ሲጠናቀቅ አስተማማኝ ኃይል እንዲኖር በማድረግ ኢኮኖሚያዊ እድገትን የሚያፋጥኑ ፕሮጀክቶች እንዲከፈቱ ያግዛል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et የካቲት 26 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+5

ተቋማቱ በጋራ ለመስራት በሚያስችሏቸው የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄዱ .......///.......... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በጋራ መስራት በሚችሉባቸው የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡ ምክክሩ ሁለቱ ተቋማት ከዚህ ቀደም በጋራ ያከናወኗቸውን ሥራዎች ለመገምገምና ቀጣይ የሥራ ግንኙነቶች በሚጠናከሩበት ሁኔታ ላይ ያለመ ነው። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ በውይይቱ ወቅት እንደተናገሩት ተቋሙ የኃይል ልማት ዘርፉን ለማሳደግ የሚያስችሉ የተለያዩ ሜጋ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ላይ ይገኛል። ተቋሙ በሚያከናውናቸው የኃይል መሠረተ ልማት ግንባታዎች ላይ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት አሻራ የጎላ መሆኑንም አንስተዋል። እንደ ዋና ሥራ አስፈፃሚው ገለፃ ተቋማቱ የዘረጉትን የኢ.አር.ፒ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የመረጃ ልውውጥ ሥርዓታቸውን ማሳለጥ ይገባቸዋል። ከዚህ ቀደም ከአሰራር ሥርዓትና አገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዘው ይነሱ የነበሩ ችግሮች ዳግም እንዳይከሰቱ ለማድረግ ከሁለቱ ተቋማት የተውጣጣ ቡድን በማዋቀር መስራት እንደሚገባም አመልክተዋል። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የጀነሬሽን ቢዝነስ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ኤፍሬም ወ/ኪዳን በበኩላቸው የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት አሁን ለደረሰበት የግንባታ ምዕራፍ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት አስተዋፅዖ ከፍተኛ ነው ብለዋል። በኃይል ልማት ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ ሜጋ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት ተቋሙ ቅድሚያ ሰጥቶ እገዛ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል። ተቋማቱ በፋይናንስ የመረጃ ልውውጥ ላይ ያላቸውን የአሰራር ቅልጥፍና ማዘመን እንደሚጠበቅባቸው የጠቀሱት ደግሞ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት ፋይናንስና ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ደመረ አሰፋ ናቸው። በኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የሺፒንግ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ካፒቴን ወንድወሰን ካሳ የተቋማቸውን አሁናዊ ገፅታ አስመልክተው ገለፃ አድርገዋል። ተቋማቸው በሀገራዊ የኃይል መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ በመሆኑ ኩራት እንደሚሰማቸውም ነው የተናገሩት። ከኮንቴነር ኪራይ፣ ከደረቅ ወደብ አጠቃቀም እና ከፋይናንስ እንዲሁም ከአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ጋር ተያይዘው ለሚነሱ ችግሮች መፍትሔ ለመስጠት ተቋማቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተቀራርበው መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል። በኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ የጭነትና አስተላላፊነት ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሻረው ከበደ በበኩላቸው ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት የግንባታ ዕቃዎች በወቅቱ የሚቀርቡ ከሆነ የማጓጓዝ ሥራዎችን በፍጥነት ለማከናወን ተቋማቸው ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል። በውይይቱ ላይ የሁለቱ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et የካቲት 26 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+8