cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

The Home of all የሁሉም ቤት

Well come to the home of all in this channel all things about human being life post every day * Motivate for free * learn for free * earn more for free Buy ads: https://telega.io/c/+LiBy-b_3bjIyMjk0 ══════❁✿❁═════════

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
15 997
Suscriptores
-11124 horas
+247 días
+47830 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

😂😂😂 @funny_coment
Mostrar todo...
😁 12🤣 9👍 2
#Morning_Motivation! ▸ ''ማንኛዉም አሰልቺ የሚያደርግህ ነገር ካለ እሱ ነገር ትእግስት እንዲኖርህ እያስተማረህ ነዉ፡፡ ▸ ማንኛዉም የሚያናድድህ ነገር ይቅርታንና ደግነትን እያስተማረህ ነዉ፡፡ ▸ ማንኛዉም ባንተ ላይ ሃይል ያለዉ ነገር የራስህን ጉልበትና ሃይል እንድትቆጣጠር እያስተማረህ ነዉ፡፡ ▸ ማንኛዉም የምትጠላዉ ነገር ያለቅድመ ሁኔታ እንድትወድ እያስተማረህ ነዉ፡፡ ▸ ማንኛዉም የምትፈራዉ ነገር ፍርሃትህን አሸንፈህ እንድትራመድ እያስተማረህ ነዉ፡፡'' በመልካም ሀሳብ የምንሞላበት ብሩህ ቀን ይሁንልን!
Mostrar todo...
👍 15🥰 4 2
ሲቲ አሸነፈ አላሸነፈ አይመለከተንም😍 ሁሌም እንቅልፍ ያሸንፋል👌 መልካም አዳር🙏
Mostrar todo...
🤣 13🤨 2👍 1😁 1
አይዞን አርሴ 😂😂😂
Mostrar todo...
🤣 8👍 4😢 2
ሰላም ሰላም ቤተሰብ አሁን online ላላችሁ ብቻ የ ካርድ ቀጥር እየለቀቀ ቀድመው ለሞሉ የሚሸልም algiti crypto channel ልጠቁማችሁ ተሎ ግቡ 3 ስዓት ነው የሚጀምረው
Mostrar todo...
👍 1 1
‍ ═ •⊰❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦             
🌹የፍቅር ንቅሣት♥
                  ክፍል 6⃣ ✅በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✅      📝 በቃ ቀኑንም ለሊቱንም ነበር ምናወራው።ት/ት ሲከፈት እሡም እኛ ት/ቤት ለወደ ቤት ሠአት እየመጣ መገናኘት ጀመርን።ከሠኞ እስከ ሀሙስ እሡ ት/ቤት እየመጣ እንገናኛለን አርብ ደሞ እኔ እናቴ ጋ ከት/ቤት ስወጣ ስለምሄድ ቅዳሜ እና እሁድ አብረን እየዋልን ሠኞ ደሞ አብረን ወደ ት/ቤት እንሄዳለን።የፍቅር ምሣሌዎች እስክንባል ፍቅራችን ገዘፈ።አንዳንዴ ወደ ውጪ ወጣ ስንል ከአባቴ ጋ ምኖርበት ሠፈር እየመጣም እንገናኝ ነበር።ፍቅራችን እንኳን ለሚያቀን መንገድ ላይ ላየን እንኳን የሚያስቀና ነበር።እንዲህ እየተባለ አንድ ወራችን ደረሠ ግን አልተገናኘንም ነበር ምክንያቱም በማግስቱ በጣም የሚወደው አባቱ ሙት አመት ነበር።ስለዚህ ት/ቤት አልሄደም።እኔም ቀኑ ረቡዕ ስለነበር እናቴ ጋ አልሄድኩም አርብ ቀንን ምመርጠው ሁለቷን የእረፍት ቀኔን እሧ ጋ ለማሣለፍ እንጂ ሌላ ምክንያት ኖሮኝ አይደለም።ረቡዕ ወደ ቤት ስገባ አስት ደወለችልኝና ነገ እንዳትቀሪ ብላ በአደራ እና በማስጠንቀቂያ ነገረችኝ።እኔም እንቢ ማለት ስለከበደኝና ለሮቢ እንደማስፈልገው ስለማውቅ እሺ አልኳት።የሧን ስልክ እንደዘጋሁት ወዲያው እናቴ ደወለችና እሧም እንዳትቀሪ ነይ አለችኝ።ለአባቴ ሀሙስ እንደምሄድና ሠኞ እንደምመጣ ነገርኩት።መጋቢት 6/2010አ.ም ሀሙስ ቀን ከት/ቤት ስወጣ እነ ሮቢ ቤት መሄድ ጀመርኩኝ።ድንገት ሄጄ ደስ ላሠኘው ፈልጌ ለሮቢ እንደምመጣ አልነገርኩትም ነበር።ልክ የውጪው በር ጋ ስደርስ ሮቢ እየወጣ ነበር ልክ ሲያየኝ በጣም ደስ አለው።አልመጣም ብዬው ስለነበር ሲያየኝ አላመነም መጥቶ አቀፈኝና ሠላም አለኝ።አብረን ወደ ውስጥ ገባን ግቢ ውስጥ ብዙ ሠው ነበር ሠላም አልኳቸውና አስት እና እናቴን ስሜያቸው ወደ ውስጥ ገባው።ልብሴን ቀያይሬ የሠው ብዛት እስኪቀንስ ትንሽ ጋደም አልኩኝ።ማታ ላይ አስት ጠራችኝና እነሡ ቤት ሄድኩኝ።እናቴ ነበረች ሌሎች ማላውቃቸው ሠዎች ነበሩ።ሮቢ ከሁሉም ጋ አስተዋወቀኝ ዘመዶቹ ነበሩ።ከዛ እራት እየበላን ድንገት ሮቢ ተነስቶ መናገር ጀመረ። 🫶🌹 ክፍል ሰባት (7) ይቀጥላል........
Mostrar todo...
👍 14 1
ዛሬ ምን ይለቀቅ ዉዶች ሁላችሁም ምረጡ
Mostrar todo...
👍 5
😜meme 😜
😂ቀልድ😂
🌟አጫጭር ድርሰት🌠
🍭ሁሉም በአንድ🍭
እሷ:ፍቅር ❤️ እሱ:ወዬ ❤️‍🩹 እሷ:እኔ ላንተ ምንህ ነኝ? እሱ:አንቺ ለኔ የሕይወቴ ፋኖስ❤️‍🔥 የሕይወቴ መብራት❣ ነሽ♡♡😘 እሷ: እሺ 😒ግን ማታ ቤትህ ያደረችውስ ምንህ ናት😠? እሱ: see more
Mostrar todo...
ሙሉዉን ለማንበብ
‍ ​        
     🌹የፍቅር ንቅሣት♥
                  ክፍል 4⃣ ✅በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✅       የካቲት 4/2010አ.ም እሁድ ቀን እነ ሮቢ ቤት ቁጭ ብዬ ስልኬን ወሠደብኝ።እኔም የሡን ስልክ ወስጄ ፎቶ እያየው ድንገት የኔ ስልክ ላየሸ text ገባ።ማነው ስለው በአንዴ ፊቱ ተቀያይሮ ስልኬን ወርውሮልኝ ወደ ውጪ ወጣ።እኔ በጣም ደንግጬ ስልኬን ሣየው እኛ ት/ቤት የሚማር የጓደኛዬ ፍቅረኛ ነበር text የላከልኝ<እምወድሽ>ነበር ሚለው።እሡ ሁሉንም ሠዉ እንዲ እያለ ነው ሚጠራው የሡ text ምንም አልገረመኝም።ይልቅስ የገረመኝና ጥያቄ የሆነብኝ የሮቢ እንዲህ መሆን ነው ለምን እንዲህ ተናደደ።እንደውም ስልኬን ወርውሮብኝ ጥሎኝ ስለወጣ ተናድጄ እኔም ወደ ቤቴ ሄድኩኝ።ማታ ላይ ፍቅር መጥታ አስት እየጠራችሽ ነው ብላኝ እነሡ ቤት ሄድኩኝ።ከዛ እቤት ስገባ ሮቢ ሶፋ ላይ ተኝቶ በearphone ሙዚቃ እያዳመጠ ስልኩን እየነካካ ነበር ድምፁን በጣም ከፍ ስላደረገው ሚሠማው ዘፈን ይሠማ ነበር<ያለ ተቀናቃኝ ያለ ፉክክር          ቦታ አለሽ በልቤ በፍቅሬ መንደር> የሚለው ነበር።እቤት ገብቼ እሡ ከተኛበት ሶፋ አጠገብ ከተቀመጥኩ ብዙ ቆየው ግን እሡ እስካሁን አላዋራኝም ከአስት ጋ ብቻ ነበር ሣወራ የነበረው።አስት ተነስታ ወደ kitchen ስትገባ<ምን ሆነህ ነው ሮቢ>ብዬ text አረኩለት።አይቶት ዝም ሲለኝ በጣም ከፍቶኝ እንደ ሌላው ጊዜ አብሬያቸው እራት ሣልበላ ደና ደሩ ብዬ ወጣው።ልክ እቤት ስገባ text ገባልኝ፤ሮቢ ነበር<የውሸት ነበር ለካ>ይላል።<ምኑ>ብዬ ወዲያው መለስኩለት።<በቃ ተይው>አለኝ።እኔም ነገሩን ከሡ መስማት ፈልጌ እንጂ መጀመሪያም ገብቶኝ ስለነበር ልጁ ምኔም እንዳልሀቀነ እንዲያውም የጓደኛዬ ፍቅረኛ እንደሆነ ላስረዳው ሞከርኩኝ።እሡ ግን ወይ ፍንክች እኔ እኮ የምር ወድጄሽ ነበር አንቺም እንደዛ ይመስለኝ ነበር ሲለኝ አልተሣሣትክም እኮ ታድያ ብዬ ስልክለት balance ጨርሼ ነበር። እሡ ግን ወይ ፍንክች እኔ እኮ የምር ወድጄሽ ነበር አንቺም እንደዛው ይመስለኝ ነበር ሲለኝ አልተሣሣትክም እኮ ታድያ ብዬ ስልክለት balance ጨርሼ ነበር።ደግሞ ሌላ text ላከልኝ<እሺ ቅድም ላስረዳህ ስትዪ አልነበር አሁን እሠማሻለዉ ስለ ልጁ በደንብ ንገሪኝ>አለኝ።balance እንደጨረስኩኝ አውቆ ነው እንዴ አልኩኝ ለራሴ ከ5 ደቂቃ በኀላ<አየሽ ልታስረጂኝ አትችይም ምንም ማለት አትችይም>አለኝ።ጠዋት ደርሶ ምን ብዬ እንደማስረዳው ሣስብ ለሊቱ ሲጋመስ ነበር እንቅልፍ የወሠደኝ።አይደርስ የለ ያቺ ጠዋት ደረሣ ተገናኘን።እንደ ሌላዉ ቀን እንኳን አቅፎ ሠላም ሊለኝ ይቅርና ለአይኑ ራሡ ያስጠላሁት መሠለኝ ዛሬም አብሬያቸዉ ሣልበላ ስትጨርስ ጥራኝ ብዬው ወጣው።ብዙም ሣይቆይ ፍቅር መጥታ ውጪ እየጠበቀሽ ነው አለችኝ።እኔም ወድያው ወጣውና መሄድ ጀመርን።ማታ እንቅልፍ አሣጥቶኝ ያደረውን ስብሰለሰልበት የነበረውን ልነግረው <ይኸውልህ ሮቢ ልጁ እኮ...>አላስጨረሠኝም።<እኔ እኮ አያገባኝም ለኔ መናገር አይጠበቅብሽም>ሲለኝ ሊፈስ የደረሠውን እንባዬን ዋጥ አድርጌው በዝምታ መጓዝ ጀመርን።ለሁለታችንም እኩል በሚሆነወሸ መንገድ ስንሄድ ይበልጥ ዝምታ ነፈሠ እያንዳንዷ ምንራመዳት እርምጃ የ10 ሠዎችን ያህል ጩኸት ገዘፈብኝ።ጩሂ ጩሂ ሁላ አለኝ።ምንም ትንፍሽ ሣንል መለያያችን ጋ ስንደርስ ተቃቀፍንና ሁለታችንም ጀርባችንን ተሠጣጥተን በየ መንገዳችን ሄድን።ክፍል ውስጥ ያለመደብኝን ጥግ ላይ ሄጄ ተቀመጥኩ።እረፍት ሠአት ላይ ጓደኞቼ በግድ ይዘውኝ ወጡ።ግን ድንገተኛ ረብሻ በአከባቢው ላይ ስለተነሣ ሁሉም ወላጅ እየመጣ ልጆቹን መውሠድ ጀመረ።ሁሉም ጓደኞቼ ከሄዱ በኀላ አባቴ በድንጋጤ እየበረረ መጣ።ልክ ሣየው ሄጄ ተጠመጠምኩበት።በጣም ፈርቼ ነበር።አባቴም አቅፎኝ ድንጋጤው ሲለቀው ወደ ቤታችን ሄድን።አይገርምም ሮቢ ነበር ለእናቴ ደውሎ ብጥብጥ እንደተነሣ ነግሯት ለአባቴ ደውላ የነገረችው።ሮቢ ለኔ እንደዚ ማሠቡ አስደስቶኝ ወደ ቤት እንደገባው በሠላም ገባህ የሚል text ላኩለት።እሡም ወድያው በሠላም እንደገባ ነግሮኝ የኔን ደህንነት ጠየቀኝ።እናም በዚ ተነስቶ እኔ በጣም እንደምወደው ነገርኩት እሡም ለኔ ተመሣሣይ ስሜት እንዳለው ነግሮኝ የፍቅራችንን የመጀመሪያ ቀን ሀ ብለን ጀመርን።በተነሣው ረብሻ ምክንያት ለ3ቀን ት/ት ተዘግቶ ነበር።በቃ ቀኑንም ለሊቱንም ነበር ምናወራው።     ገና ትምሀርት ከመከፈቱ ....... ይቀጥላል 🫶🫶🫶🫶 👍❤😍😜😇😂🌻 ::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::: Share➨  @yehulum_bet Share➨  @yehulum_bet ::::::::::::::::::::::::::::::::::::: 🍂🍀🍂🍂🍀🍂🍀🍂   ✽┉┉‌»‌🌹✿🌹»‌✽‌┉┉
Mostrar todo...
👍 11 2
መልካም ቃላት መልካም ቀን! መልካም ቃላት እንደማር ናቸው፤ ለነብስም ምግብ ለአካልም መዳን ይሆናሉ። በመልካም ንግግሮችህ ላይ ስታተኩር፣ ግንኙነቶችህን ታጠነክራለህ። ዶክተር ጆን ጎትማን (ከአርባ አመታት በላይ ባለትዳሮች ላይ ምርምር የሰሩ ሳይኮሎጂስት) እንዲህ ይመክራሉ፡- “አንድ ትዳር ዘላቂ እና ደስተኛ እንዲሆን በመጥፎ ንግግሮች መሃል ቢያንስ አምስት መልካም ንግግሮች ያስፈልጋሉ” የጎትማንን ምክር ለሌላም ግንኙነታችን ልንጠቀመው እንችላለን። የግጭቶች መብዛት እና መጥፎ ንግግሮች ሰዎችን ከእኛ ያርቃሉ። ማስተዋል የለውጥ የመጀመሪያ እርምጃ ነው። በጭውውቶችህ መሃል ያሉትን ምልልሶች እና ጥቃቅን ሁኔታዎችን በማስተዋል ተመልከታቸው፤ በተለይ የፍቅር ግንኙነትህ ላይ። በቃላቶችህ እና በአእምሮህ የምታስባቸው ሃሳቦች መሃል ማጣሪያ አስገባ። ቃላት ኃይል አላቸው፣ ሰዎችንም እንደሚያቆስሉ ወይም እንደሚፈውሱ አትርሳ። ለአናዳጅ ድርጊት ወይም ቃል ወዲያውኑ ምላሽ ላለመስጠት ሞክር። ቃላትን ለማውጣት አፍታ ውሰድ፤ ቃላቶችህን ምረጥ። አፍቃሪ፣ አዛኝ፣ የሚረዳ እና ክብርን የተሞላ ሆነህ አረጋጋቸው - ሌላኛው ሰው ምንም ያክል ቢያናደድህ ወይም ቢሳደብ፣ ፈጽሞ የማስፈራራት ወይም የቁጣ ድምጸት አትጠቀም። በማስተዋል መናገር ስትጀምር፣ በአካባቢህ ያሉ ሰዎች መልካም ሆነው ያናግሩሃል። መልካም ባይሆኑም እንኳ ራስህን ተቆጣጠር እናም ውስጣዊ ሰላምህን ታገኛለህ። (ጭንቅላትህን አጽዳ መጽሐፍ) @melkam_enaseb
Mostrar todo...
👍 6💯 5 2