cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegaciĂłn. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

🎭 Årt Før Jèsûs 🎭®

💎 ነገር ግን እግዚአብሔር አስቀድሞ ከዘመናት በፊት ለክብራችን የወሰነውን፥ ተሰውሮም የነበረውን የእግዚአብሔርን #ጥበብ በምሥጢር እንናገራለን።" 1ቆሮ 2:7 📌ራዕያችን ፦ የስነ-ፅሁፍ (የአርት) አገልግሎት በቤ/ክ ውስጥ ተገቢውን ስፍራ አግኝቶና በሚገባው ልክ አድጎ ማየት ነው። Our Group @art4Jesus ለአስተያየትና ፅሁፎችን ለማድረስ 📩 @everlastingGrace

Mostrar mĂĄs
El paĂ­s no estĂĄ especificadoEl idioma no estĂĄ especificadoLa categorĂ­a no estĂĄ especificada
Publicaciones publicitarias
292
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 dĂ­as
Sin datos30 dĂ­as

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Mostrar todo...
መንፈስ ቅዱስ | HOLY SPIRIT ASTU University Students | ASTUECSF Choir new Gospel music video | Adama

This is Adama Science and Technology University Evangelical Christian Students fellowship Official YOUTUBE channel "" የመንግሥቱን አደራ በመንፈስቅዱስ መጠበቅ "" መልካሙን አደራ በእኛ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ ጠብቅ። —2ኛ ጢሞቴዎስ 1: 14 Find us on Telegram -

https://t.me/astuecsf

Instagram -

https://www.instagram.com/astuecsf2k19/

Facebook -

https://www.facebook.com/astu.ecsf.92

ግጥም ሰው አለን በሰማይ ከሌዊ ነገድ ከነ አሮን ወገን ሌዋዊ ተብሎ ካህን ይመረጣል ሚቆም ሸክም አዝሎ ከካህናት ደግሞ አለ ሊቀ ካህን ህዝቡን የሚወክል ምትክ የሚሆን ቅድስተ ቅዱሳን በአመት አንዴ ገብቶ ደሙን ይረጨዋል መስዋዕቱን ሰቶ ይሄ ሊቀ ካህን በአመት ሲገባ ታስሮ ነው ከሞተ በገመድ ከጀርባ እንደው ከዘገየ ሳይወጣ እንኳ ቢቀር ገመዱ ይሳባል በድኑ እንዳይቀር ህዝቡ በአደባባይ ካህን ቅድስት ላይ ቅድስተ ቅዱሳን ደግሞ ሊቀ ካህን ነው የሚቆመው ሊያቀርብ መስዋዕትን አብን ያላረካው ይሄ አገልግሎት መቋጫ አግኝቷል በወልድ ሰውነት አሁን አንኖርም በዘሌዋውያን እውነቱ ተነግሯል አለ በዕብራውያን የዕብራዊያን ፀሀፊ የእ/ር አገልጋይ ጥርት አርጎ ፅፏል ያገኘውን ከላይ የእኛ ሰው በሰማይ በአብ ቀኝ ተቀምጧል ዛሬም ትኩሱ ደም ስለ እኛ ይታያል ጉዳያችን ሲሄድ በአብ ቢሮ እላይ ምንም አንሰጋም ሰው አለን በሰማይ ፍፁም አምላክ እና ፍፁም ሰው የሆነ አለን ሊቀ ካህን ሞቶ እኛን ያዳነ በፍፁም አንወርድም ከዚህ እውነት እታች መስዋዕቱ ቀርቧል የቀረ የለም አንዳች ቅድስተ ቅዱሳን ደሙን ይዞ ገብቷል ራሱን ሲያቀርብ አንዴ ፈፅሞታል ቅዱስ እና ያለ ተንኮል ነውር የሌለበት ከሀጢያተኞች የተለየ ከፍ ከፍ ያለ ከሰማያት እንዲህ ያለ ሊቀ ካህን ይገባናልና እውነቱን አንከድንም እንገልጣለን ገና ✍🏾 K.T
Mostrar todo...
#ትረካ (የቀጠለ) በዚህ ነገሮች በጨላለሙበት፣ የእግዚአብሔርን ስርዓት መጠበቅ ፍሬ አልባ ድካም እንደሆነ በሚታሰብበት ጊዜ ነበር በገሊላ አውራጃ ወደምትገኘው መልካም ነገር ወደማይወጣባት ወደ ታናሿ ናዝሬት ከተማ ወደ አንዲት ሴት እንግዳ  መልእክት የመጣው። እግዚአብሔር ዝምታውን ሰበረ። ያኔ በታሪካቸው ጅማሮ 400 ዓመት በግብፅ ሲሰቃዩ አይቷቸው በነብዩ በሙሴ ህግንና የነብያትን አገልግሎት አስተዋውቆ ወደ አዲስ ስርዓትና ወደ መልካም ምድር ያፈለሳቸው ያህዌ አሁን ደግሞ ከሌላ የሽግግር 400 ዓመታት በኋላ ከቀድሞው ወደ ተሻለ በድንጋይ ላይ ሳይሆን በልብ ላይ ወደሚፃፍ ህግ ለማምጣት የሚሆን መንገድ ቀየሰ። እንደ ከዚህ ቀደሙ ነብይ አልላከም። ነገር ግን 400ውን ዓመት ሙሉ ነብያት ቢኖሩ እንኳን ሊስተካከሉት በማይችሉት መልኩ እግዚአብሔር ተናገረ። ልሹ እግዚአብሔር ሰው ሆነ። ከእግዚአብሔርነቱ ሳይቀንስ ሰውነትን ልሹ ላይ ደመረ። ለዓመታት የጠበቁት መሲሕ ተገለጠ። እንደጠበቁት ንጉስና የዳዊት ዘር ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር ሆኖ መጣ። ከሮም ባርነት ሳይሆን ከኃጥያት ባርነት ሊያወጣቸው አምላክ ሰው ሆነ። ኪዳን ተለወጠ! በነብያት በኩል የሚደመጠው እግዚአብሔር፣ መልእክቱን በሰዎች የሚያስተላልፈው አምላክ ልሹ መልእክት ሆኖ በኃጢያተኛ ሥጋ ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ። ዝም ያለው መለኮት ሁሌም ከእናንተ ጋር ነኝ ብሎ አማኑኤል ሆነ፣ ከእኛ እንደ አንዱ ተቆጠረ። ለአህዛብ መዳን እንድትሆን የተለየችው እስራኤል፣ ሌሎችን በመናቅና ግድግዳን በመስራት ስትከልል፣ በግብሯ ደግሞ አህዛብን መስላ ጠሪዋን ስታሳዝን… አንዱ የእግዚአብሔር ልጅ በዚሁ ባልታዘዘ ህዝብ መሀል ለእውነተኛ እስራኤልነት በሰው መካከል ደኮነ። በዚህም…   በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃን አየ፤ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው። ሕዝብን አብዝተሃል፥ ደስታንም ጨምረህላቸዋል፤ በመከር ደስ እንደሚላቸው፥ ሰዎችም ምርኮን ሲካፈሉ ደስ እንደሚላቸው በፊትህ ደስ ይላቸዋል። በምድያም ጊዜ እንደ ሆነ የሸክሙን ቀንበር የጫንቃውንም በትር የአስጨናቂውንም ዘንግ ሰብረሃል። የሚረግጡ የሰልፈኞች ጫማ ሁሉ፥ በደምም የተለወሰ ልብስ ለቃጠሎ ይሆናል፥ እንደ እሳት ማቃጠያም ሆኖ ይቃጠላል። ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፥ ለሰላሙም ፍፃሜ የለውም። የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል። ✍🏾 Y.H Share if u like it 🎭 @artforJesus 🎭 🎭 @artforJesus 🎭
Mostrar todo...
ከሞላ ጎደል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መላእክት በሚገለጡባቸው ቦታዎች ሁሉ የሚናገሩት የመጀመሪያ ቃል “አትፍራ” (አትፍሪ/አትፍሩ) የሚል ነው፡፡ ይህ መናገራቸው እምብዛም አያስደንቅም፡፡ ልዕለ ተፈጥሮአዊው አካል መሬት ከተሰኘችው ፕላኔት ጋር ሲነካካ ተመልካቾቹ ላይ አስበርጋጊ ፍርሀት ወድቆባቸው ከመሬት መደፋታቸው አይቀርምና፡፡ ወንጌላዊው ሉቃስ ግን እግዚአብሔር በማያስፈራና በማያስደነግጥ ቅርጽ (መልክ) መሬት ላይ መከሰቱን ይነግረናል፡፡ በከብቶች በረት ውስጥ በተወለደውና ከብቶቹ ምግባቸውን በሚበሉበት ስፍራ በተኛው በኢየሱስ በኩል እግዚአብሔር እኛን ሳያስፈራ የሚገለጥበትን መንገድ አገኘ፡፡ ከአራስ ልጅ በላይ ማንንም የማያስፈራ ምን ነገር አለ? እንደገና ሕፃን መሆንን - መናገር፣ ጡንቻን ማቀናጀት፣ ጠንካራ ምግብ መመገብ፣ ፊኛን መቆጣጠር አለመቻልን - አስቡት እስቲ፡፡ ይህም እግዚአብሔርን ስላለፈበት “ራስን ባዶ የማድረግ” ሂደት ትንሽ ፍንጭ ይሰጣችኋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረን ኢየሱስ በምድር ላይ ሰውም፣ አምላክም ነበር፡፡ በአምላክነቱ ተአምር ማድረግ፣ ኀጢአትን ይቅር ማለት፣ ሞትን ማሸነፍ እና ነገን መተንበይ ይችላል፡፡ ኢየሱስ ይህን ሁሉ ሲያደርግ በዙሪያው በነበሩ ሰዎች ላይ ፍርሀትና ድንጋጤ ያድርባቸው ነበር፡፡ እግዚአብሔርን በብሩህ ዳመና እና በእሳት ዓምድ በምናባቸው መሣል በለመዱት አይሁዳውያን ዘንድ ግን ይህ ብዙ ግራ መጋባትና ውዝግብ አስከትሏል፡፡ በቤተ ልሔም የተወለደ ሕፃን፣ የአናጢ ልጅ፣ ከናዝሬት የመጣ ሰው እንዴት ከእግዚአብሔር የተላከ መሲሕ ሊሆን ይችላል? የኢየሱስ ሰው-ነት እንቅፋት ሆነባቸው፡፡ ነገሩ እንቆቅልሽ የሆነባቸው ሰዎች ኢየሱስ ለአገልግሎት በሄደበት ሁሉ ከዙሪያው አይጠፉም ነበር፡፡ ሉቃስ 2 እንደሚያሳየን ግን እግዚአብሔር የኢየሱስን ማንነት ቀደም ብሎ አስታውቋል፡፡ መስክ ላይ የነበሩት እረኞች የመላእከት መዘምራን ያስተላለፉላቸው መልእክት ጥሩ ዜና እንደሆነ ጥርጥር አልነበራቸውም፡፡ አንድ ሽማግሌ ነቢይ እና አንዲት አረጋዊት ነቢይም ማንነቱን ተረድተውታል፡፡ በቤተ መቅደስ የነበሩ ተጠራጣሪ መምህራን እንኳ ተደንቀውበታል፡፡ እግዚአብሔር ለምን ራሱን ባዶ አድርጎ ሰው ሆነ? መጽሐፍ ቅዱስ የተለያዩ ምላሾችን ያቀርብልናል፤ አንዳንዶቹ ነገረ መለኮታዊ ሲሆኑ ሌሎቹ ተግባራዊ ናቸው፡፡ ጌታ ኢየሱስ በወጣትነቱ መቅደስ ውስጥ የአይሁድ ራባዮችን ሲያስተምር ማየቱ አንዳች ፍንጭ ይሰጠናል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ተራ ሰዎች ከሚታይ አምላክ ጋር መነጋገር፣ መወያየት፣ መከራከር ቻሉ፡፡ ኢየሱስ ወላጆቹን፣ አንድን የአይሁድ መምህር፣ አንዲት ድኸ መበለትን - በአጠቃላይ ማንንም ሰው ማናገር ይችላል፤ “አትፍሩ” የሚል ማስጠንቀቂያ መስጠት ሳያስፈልገው፡፡ በኢየሱስ፣ እግዚአብሔር ቅርባችን ሆነ፡፡ ፊሊፕ ያንሲ (Meet the Bible)
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
Let's share it
Mostrar todo...
#ትረካ “እነሆ፥ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ። መጥቼም ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፥ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል።” የሚለውን የትንቢት ቃል በሚሰሙበት ጊዜ ማንም የመጨረሻው ይሆናል ብሎ አልጠበቀም ነበር። ጊዜው 430 ከክርስቶስ ልደት በፊት አካባቢ ነበር። የሰባው ዓመት የባቢሎን የምርኮ ዘመን አብቅቶ በነቢዩ በኤርሚያስ እንደተነገረው ዳግም ቤተ መቅደሱና ቅጥሩ የተሰሩበት ወቅት። በጊዜው እስራኤል እንደገና እየተገነባች በመሆኗ ህዝቡ ስለ መጪው ብሩህ ዘመን ያልም ጀምሯል። ይህ ብቻ አልነበረም… በወቅቱ የነበሩት ነቢያትም ከ300 ዓመት በፊት ጀምሮ በነቢዩ ኢሳይያስ ሲነገር የነበረውን ትንቢት ዳግም ለህዝቡ ማወጅ ጀመሩ…መሲህ ይመጣል፣ ከዳዊት ዘር የሆነ ገዢና ንጉሥ ከመካከላችሁ ይነሳል። ለዚህ ከባርነት በቅርቡ ለተገላገለ ህዝብ ይህ ምን ያህል ታላቅ ብስራት ነው?! ህዝቡም ይህ የተባለው መሲሕ ከዛሬ ነገ መጣልኝ እያለ መጠባበቁን ተያያዘው። …ጊዜያት ሄዱ… እነዚህ ተደጋግመው የሚያስተጋቡ ድምፆች ቀስ በቀስ መደብዘዝ ጀመሩ። ነብይ እንደልቧ የበዛላት እስራኤል በዘመኑ የነበረው ሚልክያስ የመጨረሻዋ መሆኑን አልተረዳችም ነበር። ከሚልክያስ በኋላ ‘የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ…’ የሚል ሰው ጠፋ። ስለ መሲሑ ከዚህ በፊት የተነገሩ ትንቢቶችንን መደጋገምና ህዝቡን ማስታወስ የራባዮች የሰንበት ሃላፊነት ሆነ። ነገሩ በዚህ አላበቃም፣ በእግዚአብሔር ዝም ማለት ግር የተሰኙት እስራኤላውያን ጭራሽ ሌላ ዱብ እዳ ወረደባቸው… ከሚልክያስ ትንቢት መቶ ዓመታት በኋላ ወደ ገናናነት የመጣችው ግሪክ በመሪዋ በታላቁ እስክንድር እስራኤልን ወረረች። ቀጥላም ደግሞ ሮም የግሪክን ቦታ ያዘች። ይህ ሁሉ ሲሆን ድፍን 400 ዓመታት። ታላቅ ንጉስ ይወጣልኛል ብሎ ሲጠብቅ የነበረ ህዝብ ጭራሽ ወደ ከፋ ባርነትና ከባድ የግብር ሸክም ውስጥ ተዋጠ። ወደ አባቶቻቸው አምላክ ደጋግመው ቢጮሁም ተስፋ የሚሰጥ ነብይ እንኳን አጡ… እግዚአብሔር ዝም አለ… መኖሩና ታላቅነቱም ታሪክ ሆነ። . . . ይቀጥላል ✍🏾Y.H 🎭 @artforJesus 🎭 🎭 @artforJesus 🎭
Mostrar todo...
በመካተቻው ግን እስከዛሬ ከተጠየቁት ‹‹ ለምን)›› ኦች ሁሉ የላቀውን ‹‹ለምን›› የመልሶች ሁሉ ዐውራ የሆነውንም መልሱን መናገር አለብኝ፡፡ ጠያቂው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነበረ፡፡ ‹‹ አምላኬ ፣ አምላኬ ለምን ተውኸኝ;›› ሰበቡም (መልሱም) የእኔ እና የእናንተ ኀጢአት ነበረ፡፡ መትረፊያውም መስቀሉ ነበረ፤ ነውም፡፡ ለዓለሙ ሁሉ ‹‹ለምን››ታ የእግዚአብሔር ቁርጥ መልስ የክርስቶስ ኢየሱስ መስቀል ነው፡፡ ወዳጆቼ ሆይ በመስቀሉ አምባ ውስጥ ተገን እናገኛለን፡፡ ሙጥኝታችን፣ ትምክህታችንም ራቁቱን የተሰቀለው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ እኛን ያድነን ፤ አገራችንን ይፈውስልን፤ ቤተክስቲያንንም ያድስልን፡፡ ንጉሤ ቡልቻ
Mostrar todo...
‹‹--------- ይህ ነገር ሁሉ ለምን ደረሰብን;›› ‹‹ አጥብቆ ጠያቂ የእናቱን ሞት ቢረዳም›› እውነቱን አውቆ እርሙን ማውጣት፣ ማድረግ ያለበትንም አስተውሎ ማድረግ ይሻለዋል፡፡ የእኛ አገር ነገር አደናጋሪ፣ አሳሳቢ፣ አስጨናቂ፣ አጠያያቂ ከሆነ ሰነበተ፡፡ በአንድ ወገን ሲቃና በሌላ ወገን ይደረመሳል፣ ዛሬ በሰለ ሲባል አድሮ ቃሪያ ይሆናል፡፡ እፎይታ የሩቅ ህልም እየመሰለ ሄደ፡፡ ውጥረትና ሁካታ የወትሮ ልብስ ሆኑ፤ ጣርና ሲቃ አየሩን ሞሉት፡፡ ለምንድነው ይህ የሚሆነው; ምን ቢሆን ነው የሚስተካከለው; መቼ ነው ይህ አገር አደብ የሚገዛው; ብርቱ ጥያቄ ልቦናችንን ይገዘግዛል፡፡ እንደ አገር ሁሉ ቤተክርስቲያንም እንደታመመች እንዳቃሰተች አለች፡፡ የብርሃን ማማ እንድትሆን የተጠራች፣ የተስፋ ቋት እንድትሆን የምንጠብቃት ይህች የክርስቶስ አካል ኩራዟ እየተስለመለመ፣ ጎተራዋ እየተመናመነ የሚሄድ ይመስላል፡፡ ለምን ይህ ሁሉ ሆነ; የዚህ መጣጥፍ ርዕስ ከመጽሐፈ መሳፍንት ምዕራፍ 6 የተቀዳ ነው፡፡ ጌዴዎን ብርቱ ገበሬ እንደነበር ከትጋቱ እናስተውላለን፤ በጠላት በተዋከበ አገር ውስጥ ተደብቆም ቢሆን፣ ጉድጓድ ገብቶም ቢሆን ስንዴውን ይወቃል፣ አላረፈም፣ እጅ አልሰጠም፡፡ በሥራ ቦታው የተገለጠለት መልአክ ከጌዴዎን አስተሳሰብ ጋር የማይገጥም ከፍ ያለ ነገር ይናገራል፡፡ ‹‹ አንተ ጽኑዕ፣ ኃያል ሰው ፣ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፡፡›› የመልአኩ ዐዋጅ እና የመሬቱ እውነታ አልገጣጠም ያለው ጌዴዎን ብርቱ ጥያቄ ጠየቀ፡፡‹‹ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ይህ ነገር ሁሉ ለምን ደረሰብን; ለምን የምድያም መጫወቻ ሆንን; ለምን ዘወትር በፍርሀት እና በሰቀቀን እንኖራለን; ለምን መቅኖ ቢስ ተንከራታቾች፣ የዋሻ እና የጉድጓድ ነዋሪዎች ሆንን; ስንት ታሪክ እየተተረከልን፣ ስንት ታምራት እየተነገረን አሁን ያለንበት ሰቆቃ ውስጥ ለምን ወደቅን; የጌዴዎንን ታሪክ ዙሪያ ገባ ስናጤን መልሱ አጅግም ውስብስብ አይደለም፡፡ ሕዝበ እስራኤል ከባርነት ያወጣቸውን አምላክ በሌሎች አማልክት ተክተውታል፡፡ ‹‹ባዕዳን አማልክትን አታምልኩ›› ያላቸውን የታዳጊያቸውን ቃል አልሰሙም፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ በመከራም ውስጥ ሆነው ትዕቢታቸው እና ‹‹ ከእኛ በላይ ላሣር›› የሚለው መፈክራቸው አልተለወጠም፡፡ ‹‹ እስራኤል እጄ አዳነኝ ብሎ እንዳይታበይብኝ የሰራዊቱን ቁጥር ቀንስ›› ብሎ እግዚአብሔር ጌዴዎንን ያዘዘው የልባቸውን ዐውቆ ነው፡፡ ከድል በኋላ እንኳ አንዳንዶቹ የታሪክ ሽሚያ ውስጥ ገብተው ‹‹ እኛን ሳትጠሩን ለምን ዘመታችሁ;›› እስኪሉ ድረስ ጉረኞች ነበሩ፡፡ በኢሳይያስ መጽሐፍ ውስጥ ደግሞ ሌሎች ጥያቄዎች አሉ፡፡ ‹‹ ፀሎት የማትመልስ ከሆነ ለምን ጾምን; ለምንስ ጸለይን; የሚሉ፡፡ ‹‹ አንተን ፈልገን እራሳችንን ያዋረድነው ፋይዳው ምንድነው; የሚሉ፡፡ ለእነዚህም መልሱ ሩቅ አይደለም፡፡ አስመሳይ ሀይማኖተኞች፣ ጸሎት አሳማሪ፣ ክፉ ሥራ ሠሪ ሆነው የተገኙ ናቸው፡፡ ግብዝ ሃይማኖተኝነት ከባዕድ አምልኮ አይተናነስም፡፡ ይጾማሉ፣ እንደ እንግጫ እራሳቸውን መሬት ላይ ያነጥፋሉ፤ ግን ከጸሎት ሲነሡ ያው የራሳቸውን ፍቃድ ይፈጽማሉ፡፡ ምንም ለውጥ የለም፡፡ ከጾምና ከጸሎት ሲመለሱ በግፍ ጡጫ ይማታሉ፣ ፍትህ ማጓደል፣ እብሪት ና ንፉግነት ያጠመቀው የኑሮ ዘይቤያቸው በሀይማኖተኝነት ካባ ተጀቡኖ ይጎማለላል፡፡ አምላክ እንዴት ይስማ; የዕዝራ-ነህምያ ዘመን ሰዎች ደግሞ የገቡበት አስጨናቂ በደል ድብልቅነት ነበር፡፡ የተመረጠው ሕዝብ ከአሕዛብ ጋር ተደባለቀ፣ከርኩሰታቸው እና ከጸያፍ ሥራቸው ጋር ተባበረ፡፡ ልዩ ማንነቱን አሽቀንጥሮ ጥሎ ያው እንደጀማው፣ ያው እንደሰፈሩ፣ ያው እንደጎረቤቱ ሆነ፡፡ ‹‹ ፊቴን ወዳንተ ለማንሣት አፍራለሁ፣ እፈራማለሁ›› እስኪል ድረስ የካህኑ የዕዝራ ለቅሶ ከባድ ነበር፡፡ ለአገራዊ ችግሮቻችን ብዙ ፖለቲካዊ፣ ታሪካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ምናልባትም ሥነልቦናዊ ትንታኔ ሊሰጥ እንደሚችል አይጠፋኝም፡፡ሁሉም በአግባቡ ቦታ ይኖረዋል፡፡ ይሁን እንጂ እንደ እግዚአብሔር ሰዎች መሰረታዊ ምክንያቱን ቆፍረን ማግኘት ይገባናል እላለሁ፡፡ እንደ ሕዝበ እስራኤል ሆነንስ ቢሆን; • በነባር ባህል ስም፣ በአባቶቻችን ቅርስ ስም ባዕድ አምልኮን አንግሠንስ ቢሆን; ዐደባባዮቻችን ለሌሎች አማልዕክት መሠዊያ መሥሪያ ሜዳ ሆነውስ ቢሆን; በየልባችን ጓዳ የፍቅረ ነዋይ፣ የአውስቦ፣ የዝና ጣዖታት እያባበለን ቢሆንስ; • በዘር፣በታሪክ ትምክህት ልባችን ተደፍኖ ዕብሪት እና ትዕቢት አፍኖን ከሆነስ; • በዝሙት፣ በርኩሰት፣ በከንቱ ፈንጠዝያ፣ በዓለማዊ ልማድ ተጠፍረን፣ እየፀለይንም፣ እየጾምንም እዚያው ረግረግ ውስጥ ተዘፍቀን እንደሆነስ; • በየቤታችን ፣በየመሥሪያ ቤታችን ግፍ እየፈፀምን፣ፍትህ እያዛባን ማስነን እንደሆነስ; ይህን ሁሉ በክርስትና ካባ፣ በጮሌ ቋንቋ ሸፋፍነን እየተሳሳቅን ቢሆንስ; • የጥላቻ መርዝ በሠራ አካላችን ተሰራጭቶ በቁም የሞትን ሬሳ አድርጎንስ ቢሆን;---- ይህን ሁሉ የምጠይቀው በትህትና ነው፤ተጨንቄ ነው፤ ራሴንም እዚያው ውስጥ እየተመለከትኩ ነው፡፡ ወገኖች‹‹ ይህ ነገር ሁሉ ለምን ደረሰብን;›› ብሎ መጠየቅ ነውር ነው እንዴ; አምላክ ጥያቄ አይፈራም፤ ለመልስም አይቸገርም፤ ስለዚህ በቅንነት እንጠይቅ፡፡ ‹‹ አሁን የእኛ ኀጢአት ከሌሎች አገሮች እና ሕዝቦች በደል በልጦ ነው እንዴ;›› ቢባልስ;‹‹ እግዚአብሔርን ሽምጥጥ አድርገው የካዱት፣የሰደቡት ሕዝቦች ተመችቷቸው ይኖሩ የለ; እኛ ከእነርሱ ብሰን ነው;›› ወዳጆቼ መጽሐፍ ምን ይላል---- ‹‹ ለእያንዳንዱ እንደሥራው እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ›› የሚል የምድር ሁሉ ዳኛ እንዳለ ይነግረናል፡፡ ለማን፣ መቼ ምን እንዳቆየለት አናውቅም፤ ብያኔው በእጁ ነው፡፡ ታሪክም በአንድ ትውልድ ዕድሜ አይቋጭም፡፡ እስራኤል የወጓቸው የአሞራውያን ኀጢአት ጽዋ እስኪሞላ አራት መቶ ዓመት ተጠብቋል፡፡ የዘመንን እና የፍርድ ነገር በጻድቁ አምላክ አጅ ነው፡፡ የእነርሱን ለእነርሱና ለእውነተኛው ዳኛ ትተን በራሳችን ጉዳይ ላይ ማትኮር ይሻለናል፡፡ ይህስ ይሁን----- መዳኛ፣ መቃኛ መንገድ የለም ወይ; ካልን ግን ለሁሉም አጥጋቢ መልስ ተሰጥቷል፡፡ ጌዴዎን ከመዝመቱ በፊት አባቱ የሠራውን የበዓልን መሠዊያ እንዲያፈርስ ተጠየቀ፡፡ በኢሳይያስ ትንቢት የተጠቀሱት ሰዎች የግፍ ሥራን ትተው በርኅራኄ እና በጽድቅ እንዲኖሩ ተነገራቸው፡፡ የዕዝራ-ነህምያ ዘመን የምርኮ ተመላሾች እራሳቸውን ከድብልቅ ሕዝብ እንዲያጠሩ ታዘዙ፡፡ ለእኛም ይኸው ነው፡፡ ቁርጠኛ የመመለስ እርምጃ መውሰድ፡፡ ‹‹ በዚያን ጊዜ ብርሃንህ እንደንጋት ይበራል፣ ፈውስህም ፈጥኖ ይበቅላል፣ ጽድቅህም በፊትህ ይሄዳል፣ የእግዚአብሔርም ክብር በኋላህ ሆኖ ይጠብቅሃል፡፡ የዚያን ጊዜ ትጣራለህ እግዚአብሔርም ይሰማሀል፣ትጮኻለህ እርሱም እነሆኝ ይላል------; (እባካችሁ ኢሳይያሰ 58 ን አንብቡ እና የእግዚአብሔርን ደግነት አስተውሉ፡፡)
Mostrar todo...
የእናቴ ሚኒስትሪ አዝናኝ ወግ _ በአሳየኸኝ ለገሰ 🎭@artforJesus🎭 🎭@artforJesus🎭
Mostrar todo...