Civil Engineering
Ir al canal en Telegram
*ለሲቪል ; ለአርክቴክቶች÷ለኮንስትራክሽን ÷ ለሀይድሮሊክ መሀንዲሶች እና ተማሪዎች የተዘጋጀ ትምህርታዊ ቻናል ፡፡ @engineer03 http://www.Indiabix.com በዚህ ደግሞ ማንኛውንም ጥያቄና መልስ ታገኛላችሁ! ╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯╯☼ ▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲╭ ╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲ ▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔ ▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕
Mostrar más1 363
Suscriptores
Sin datos24 horas
+27 días
+230 días
Archivo de publicaciones
1 363
🏗️ ከበዓል መልስ የኮንስትራክሽን ሳይት ማኔጅመንት፦ የሰኞ ማለዳ ስንቅ
በዓላትን አክብሮ ወደ ሥራ የሚመለስ ሠራተኛ ላይ ድካም፣ ትኩረት ማጣትና መዘናጋት ሊታይ ይችላል። ይህ ደግሞ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለአደጋና ለሥራ መጓተት ዋነኛ መንስኤ ነው። ሰኞ ማለዳ ሥራ ከመጀመሩ በፊት የሚከተሉትን ነጥቦች መተግበር ውጤታማ ያደርጋል፦
1. የደህንነት ንቃተ-ተሃድሶ (Safety Toolbox Talk)በመጀመሪያው ቀን ጠዋት ሁሉንም ሠራተኞች በማሳተፍ አጭርና ግልጽ የሆነ የደህንነት ገለፃ ማድረግ። የትኩረት ነጥብ፦ ስለ ግል ደህንነት መጠበቂያ (PPE) አጠቃቀም፣ ስለ ሳይቱ አደገኛ ቦታዎች እና ስለ ተገቢ የሥራ ሂደቶች ማስታወስ። አላማ፦ የሠራተኛውን አእምሮ ከበዓል ድባብ አውጥቶ ወደ ሥራው ደህንነት እንዲመለስ ማድረግ።
2. የማሽነሪዎችና የሳይቱ ፍተሻ (Site Inspection)ሥራ ከመጀመሩ በፊት ለተወሰነ ጊዜ ተዘግቶ የነበረው ሳይትና ማሽነሪዎች በጥንቃቄ መፈተሽ አለባቸው። ማሽነሪዎች፦ ኤክስካቫተሮች፣ ዶዘሮችና ሌሎች ከባድ ማሽኖች ለብልሽት ወይም ለስርቆት አለመጋለጣቸውን ማረጋገጥ። መሠረተ ልማት፦ የኤሌክትሪክ መስመሮች፣ ስካፎልዲንግ (Scaffolding) እና ጉድጓዶች ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን መፈተሽ።
3. ድካምንና ሞራልን ማመጣጠንሠራተኞች በበዓል ምክንያት ሊደክሙ ስለሚችሉ ሥራውን ቀስ በቀስ ማስጀመር። ቀላል ጅምር፦ በመጀመሪያው ቀን ከባድና እጅግ ውስብስብ የሆኑ ሥራዎችን ከመጀመር ይልቅ ቀለል ያሉና የዝግጅት ሥራዎችን መስራት። ንቃት፦ የሠራተኞችን ንቃት መከታተል፤ በድካም ምክንያት የሚመጡ ስህተቶችን ለመቀነስ የአጭር ጊዜ እረፍቶችን መስጠት።
4. የሰው ኃይል ብቃትና ዝግጁነትእያንዳንዱ ሠራተኛ ለሥራው ብቁና በአካልም ሆነ በአእምሮ ዝግጁ መሆኑን ማረጋገጥ። ከበዓል መልስ የሚታዩ የጤና መጓደሎችን ወይም ከፍተኛ የትኩረት ማጣትን መለየት።
5. የሥራ ዕቅድ ክለሳ (Resource Planning)በበዓል ምክንያት የተቋረጡ ሥራዎችንና የቀሩ የጊዜ ገደቦችን (Deadlines) መገምገም። ሠራተኛውን ሳያስጨንቁ ፕሮጀክቱ በታቀደለት መሠረት እንዲቀጥል የጊዜ ሰሌዳውን ማስተካከል። ለማስታወስ፦ "ደህንነቱ የተጠበቀ ጅምር፣ የተሳካ ፕሮጀክት መሠረት ነው።"
1 363
⭐️የ mat foundation አይነቶች
1. Flat plate -
እንደ ፓድ ፋውንዴሽን ሆኖ ሙሉ ህንፃው ሚያርፍበትን ቦታ ይሸፍናል።
⏺ብረት ደግሞ ኮለን እና ሺር ዎል ያለበት ጋር spacing ማጥበብ (ብረት ጨመር ማረግ)
2. Plate thickened under the column
⏺የ ኮለኖቹ ሚመጣው ክብደት በ ሶሌታው ውፍረት ብቻ ልንቋቋመው ካልቻልን የኮለኖቹን ረድፍ ከ ሶሌታው ስር ጥልቀቱን እንጨምራለን
3. Piled raft foundation
⏺ማታችን በ pile ቢደገፍ ልክ እንደ pile cap ሆኖ ግን ጥልቀት የሌለው shallow
4. Beam and slab two way raft foundation
⏺ሶሌታችን ላይ ግሬድ ቢም ሲረበረብ አይነት ነገር
5. Ridged /cellular raft foundation
⏺ፋውንዴሽኑን እንደ ቤዝመንት ስንጠቀመው
6. Plate with pedestal
- ኮለኖቹ ላይ ከ ሶሌታው በላይ ኮርቻ ሲኖረው
1 363
እንዴት በደላሎች ይዘወራል?
👉የመንግስትና የግል ሽርክና ውጤቱ "ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ" በደላሎች ሴራ እየታመሰ ነው ተባለ‼
የመንግስትና የግል ባለሀብቶች በጋራ ሽርክና (Joint Venture) የመሰረቱትና የሀገሪቱ ትልቁ የኢንዱስትሪ ተስፋ የሆነው ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ምርት፣ በደሴ ከተማም ሆነ ኮምቦልቻ በደላሎችና ስግብግብ ነጋዴዎች "የዋጋ ቁማር" ሰለባ መሆኑን የምርቱ ተጠቃሚዎች ገልፀዋል።
ይህ በሰሜን ሸዋ ለሚ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘው ግዙፍ ፋብሪካ፣ አንድ ኩንታል ሲሚንቶን በ1,140 ብር እያከፋፈለ ቢሆንም፤ በደሴና ኮምቦልቻ ከተማ ግን ምንም ዓይነት ይፋዊ የዋጋ ጭማሪ ሳይደረግ በ2,400 ብር እንዲሸጥ እየተደረገ ይገኛል በማለት ነው ጥቆማ አቅራቢዎቹ ያስረዱት።
የመንግስትና የግል ሽርክና የሆነው ኩባንያ ለምን በደላላ ቁጥጥር ስር ወደቀ?
ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት የመንግስት ድርሻ ያለበትና የህዝብን የግንባታ ፍላጎት ለማርካት የተቋቋመ መሆኑ ይታወቃል። ሆኖም ግን፣ ቀደም ሲል ምርቱ ደሴና ኮምቦልቻ ሲደርስ የትራንስፖርት ወጪ ተጨምሮበት በ1,500 ብር ሲሸጥ የቆየው ሲሚንቶ፣ አሁን ላይ በኩንታል የ900 ብር ልዩነት ታይቶበታል። ይህ ድንገተኛ "ዝርፊያ" የመንግስትና የግል አጋርነቱን ዓላማ የሚጻረርና የዜጎችን የመኖሪያ ቤት የመስራት ህልም የሚያጨልም ሆኖ ታይቷል።
በከተማዋ የሚገኙ ግንባታ አቅራቢዎችና ተጠቃሚዎች እንደገለጹት፤ በደላሎችና በወኪል አከፋፋዮች መካከል በተፈጠረ "ያልተገባ የጥቅም ትስስር" ሳቢያ ዋጋው ከአቅም በላይ ሆኗል።በዚህም "የግንባታ ዘርፉ ክፉኛ ፈተና ላይ ወድቋል"ብለዋል። በከተማዋ የተጀመሩ የግልና የመንግስት ግንባታዎች "ቀጥ" ብለው መቆማቸውን ጠቁመዋል።
"የመንግስት እጅ ያለበት ፋብሪካ ምርት እንዴት በደላሎች ይዘወራል?" የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎች፣ መንግስት አስቸኳይ ጣልቃ በመግባት ይህን የገበያ ምስቅልቅል እንዲያስተካክልና ወንጀለኞችን ተጠያቂ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
1 363
+4
🛣️ የባቱ - አርሲ ነገሌ የፍጥነት መንገድ ግንባታ ዋና ዋና ሥራዎች ተጠናቀቁ!
የአዲስ አበባ - ሞያሌ - ናይሮቢ - ሞምባሳ ዓለም አቀፍ የመንገድ ኮሪደር አካል የሆነው የሞጆ - ሐዋሳ ክፍል 3 (ባቱ - አርሲ ነገሌ) የ57 ኪሎ ሜትር የፍጥነት መንገድ ግንባታ በስኬት መጠናቀቁ ተበሰረ።
📍 የፕሮጀክቱ ዋና ዋና መረጃዎች፦ርዝመት፦ 57 ኪሎ ሜትር የመንገዱ ስፋት፦ 31.6 ሜትር (ከመካከለኛ አካፋይ ጋር) ወጪ፦ 5.3 ቢሊዮን ብር (በዓለም ባንክ ድጋፍ የተሸፈነ) ተቋራጭ፦ ቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ (CCCC) 🌟
ይህ የፍጥነት መንገድ ምን ፋይዳ አለው?የጉዞ ጊዜን ይቀንሳል፦ ከሞጆ - ሐዋሳ የነበረውን የ4 ሰዓት ጉዞ ወደ 2 ሰዓት ዝቅ ያደርገዋል። የንግድና ግብርና ትስስር፦ እንደ ስንዴ፣ ቲማቲም፣ ሽንኩርት እና ድንች ያሉ የግብርና ውጤቶች በፍጥነትና ሳይበላሹ ለገበያ እንዲቀርቡ ይረዳል። ቱሪዝምን ያነቃቃል፦ ወደ ሐይቅ ዳርቻዎች (ደምበል፣ ላንጋኖ፣ አብያታ፣ ሻላ) እና ወደ ሐዋሳ ለሚሄዱ ጎብኚዎች ምቹና ፈጣን ጉዞን ያረጋግጣል። ዓለም አቀፍ ትስስር፦ ይህ መንገድ 10,000 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የታላቁ የምስራቅ አፍሪካ ኮሪደር (ኬፕታውን ትራንስ አፍሪካን ሐይዌይ) ወሳኝ አካል ነው።
መንገዱ ዘመናዊ የትራንስፖርት ሥርዓት (ITS - Intelligent Transport System) የተገጠመለት በመሆኑ፣ ደህንነቱ የተጠበቀና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ ሆኗል።የአካባቢው ማህበረሰብም ሆነ የሀገሪቱ የንግድ እንቅስቃሴ ከዚህ ታላቅ ፕሮጀክት ከፍተኛ ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል። እንኳን ደስ አለን! 🇪🇹
1 363
+4
በጅግጅጋ የተገነባው ተለዋጭ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ
በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ሲገነባ የቆየው የ6.93 ኪሎሜትር ተለዋጭ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ፕሮጀክት መጠናቀቁን ተከትሎ፣ ደረጃውን የጠበቀ የትራፊክ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተበሰረ።
መነሻውን የጅግጅጋ ከተማ መግቢያ አድርጎ ቶጎ-ጫሌ አደባባይ ላይ የሚያበቃው ይህ ግዙፍ የመንገድ ፕሮጀክት፣ 30 ሜትር የጎን ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ የተገነባ ነው። ግንባታው የእግረኛ እና የብስክሌተኞች መተላለፊያን ጨምሮ ዘመናዊ የከተማ መንገድ ሊያሟላቸው የሚገቡ መመዘኛዎችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።የመንገዱን ግንባታ ሀገር-በቀሉ ይርጋለም ኮንስትራክሽን ያከናወነው ሲሆን፣ የማማከርና የቁጥጥር ሥራው ደግሞ በኤልዳ አማካሪ ድርጅት እና በዳምራ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ ጥምረት ተከውኗል።
ለዚህ ታላቅ የመሠረተ ልማት ግንባታ ማስፈጸሚያ የዋለው 672 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ሙሉ በሙሉ በፌደራል መንግሥት በጀት የተሸፈነ መሆኑ ተረጋግጧል።የመንገዱ መጠናቀቅ በተለይ በጅግጅጋ ከተማ መግቢያና መውጫ ላይ ይታይ የነበረውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ በከፍተኛ ሁኔታ ያቃልላል ተብሎ ይታመናል። ለጭነት ተሽከርካሪዎች፦ ከቶጎ-ጫሌ እና ከደገሀቡር የሚመጡ ከባድና ቀላል የጭነት ተሽከርካሪዎች የከተማዋን መሃል ሳያቋርጡ እንዲያልፉ አማራጭ ሆኖ ያገለግላል። ለከተማዋ ገጽታ፦ ፕሮጀክቱ የጅግጅጋን ሁለንተናዊ ዕድገትና ውበት ከማሳለጥ ባለፈ፣ የንግድ እንቅስቃሴውን ቀልጣፋ እንደሚያደርገው ተመልክቷል። በአሁኑ ወቅት የመንገዱ ዋና ዋና ስራዎች ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን፣ የትራፊክ ምልክቶች ተከላና ሌሎች ጥቃቅን የማጠናቀቂያ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ከወጣው መረጃ ለመረዳት ተችሏል።
1 363
73. የግንባታ ዘርፉ ስራ ግዥ ክፌያ አፆጻጸም - - - - - -
የመንግስት መ/ቤት የግንባታ ዘርፌ ስራ ግዥ ክፌያ የሚፆፀመው የግንባታውን የክንውን ዯረጃ መሰረት አዴርጎ እና የሚከተለውን አፆፃፀም ተከትል መሆን ይኖርበታሌ፡-
እንዯ ስራው ውስብስብነት ሇዚህ ዓላማ ከተቀጠረ አማካሪ ወይም ከመ/ቤቱ መሃንዲስ በሚሰጥ የክፌያ የምስክር ወረቀት መነሻነት ብቻ ይሆናሌ፡፡ የክፌያ የምስክር ወረቀት እንዱሰጠው ከሥራ ተቋራጩ ጥያቄ በቀረበበት በ7 (ሰባት) የሥራ ቀናት ውስጥ የቁጥጥር ስራውን የሚያከናውነው አማካሪ ወይም የመ/ቤቱ መሃንዲስ የምርመራውን ሥራ ማጠናቀቅ ይኖርበታል፡፡
የክፌያ የምስክር ወረቀት በአማካሪው ወይም በመ/ቤቱ መሃንዲስ ተረጋግጦ ሲቀርብ መ/ቤቱ በ30 (ሰሊሳ) ቀናት ተገቢውን ክፉያውን ለሥራ ተቋራጩ መፈፀም አለበት፡፡
በክፌያ የምስክር ወረቀት መሰረት ከሚፈጸመው ከእያንዲንደ ክፌያ ላይ ለግንባታ ሥራው ጥራት ዋስትና እንዱሆን 7% (ሰባት በመቶ) በማያዣ መልክ ተቀንሶ ይያዘሌ፡፡ የግንባታ ስራው ሲጠናቀቅ እና ጊዜያዊ ርክክብ ሲደረግ በዚህ ንዐስ አንቀጽ ፉዯሌ ተራ /ሠ/ መሰረት ከሚያዘው ገንዘብ ሊይ 50% (ሃምሳ በመቶ) ለሥራ ተቋራጩ ይለቀቃል፡፡ ቀሪው 50% (ሃምሳ በመቶ) ጊዜያዊ ርክክብ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ በአንድ ዓመት የጥገና ጊዜ ተይዞ የሚቆይ ሲሆን፣ የስራ ተቋራጩ በ12 ወራት የሚቆይ በሁኔታ ሊይ ያልተመሰረተ ዋስትና ካቀረበ የተያዘው ገንዘብ ይለቀቅለታል፡፡
(the text is due to font problem , read page 133 for more.)
1 363
የ2018 ዓ/ም 2ኛ ሩብ ዓመት የኮንስትራክሽን ስራዎች ቀጥተኛ ዋጋ ጥናት
2018E.C 2nd Quarter Construction Works (Only Direct Cost)t
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ
1 363
ስራ ላይ ያለው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የህንጻ መመሪያና ስታንዳርድ ቁጥር 127/2014.
Addis Ababa City Administration Building Permit and Control Authority Building Guidelines and Standards (Directive No. 127/2014).
1 363
የ2018 ዓ/ም 2ኛ ሩብ ዓመት የኮንስትራክሽን ስራዎች ቀጥተኛ ዋጋ ጥናት
2018E.C 2nd Quarter Construction Works (Only Direct Cost)t
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ
1 363
የ ኮንስትራክሽን ብቃት ማረጋገጫና ምዝገባ መመሪያ
- ኮንትራክተር ከ ደረጃ 1 እስከ 10
- የአማካሪ መሃንዲስ ፈቃድ
- ባለሙያ ሁሉም አይነት
1 363
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአደጋ ስጋት ደህንነት ደንብ
ማንኛውም ህንፃ እና ግንባታ በግንባታ ሂደት የሚከተሉትን ማሟላት ይኖርበታል ፡-
ሀ) ለማንኛውም ህንጻ ወይም ግንባታ ወይንም መሰረተ ልማት የግንባታ ፍቃድ ከመሰጠቱ በፊት በስትራክቸራል ዲዛይን ውስጥ መሟላት ያለባቸው የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎችን የእሣት፣ የጎርፍ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ፣ አውሎንፋስ፣ የመስመጥ፣ መደርመስ እና የሌሎች አደጋ መከላከያና መቋቋሚያ መስፈርቶች መካተታቸውን በማረጋገጥ እንዲሁም የአገሪቱን የህንጻ ስታንዳርድን ከግምት ያስገባ የግንባታ ፈቃድ መሰጠት አለበት፤
ለ) ለእያንዳንዱ አዲስ ግንባታና ጥገና ለሚያካሂድ ሠራተኛ የአደጋ ጉዳት መከላከለያ እና የአደጋ ጥንቃቄ የግል መሳሪያዎች ሊሟላለት ይገባል፤
ሐ) በህንጻ ውስጥ ነዋሪዎች ወይም ተጠቃሚዎች እያሉ የጥገና ሥራ የሚከናወን ከሆነ ለጥገና ሥራ የሚውል ማንኛውም ቁሳ ቁስና መሳሪያ ስራ ላይ ሲውል አሠሪው አካል እና ተጠቃሚዎቹ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ግዴታ አለበት፡፡
1 363
🤔🤔🤔
አፈርን ከሲሚንቶ ጋር በመቀላቀል ደረጃውን የጠበቀ ቤት ለመገንባት የሚያስችል ጥናት ተጠናቀቀ
ከትንሽ ሲሚንቶ ጋር በመቀላቀል ደረጃውን የጠበቀ ቤት ለመገንባት የሚያስችል ጥናት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ታምራት ሙሉ (ኢ/ር) ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ ከሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የተጠናው ይህ ጥናት ትኩረት ያደረገው በሐረሪ፣ በድሬዳዋ እና በጅግጅጋ አካባቢዎች የሚገኘውን አፈር ለቤት ግንባታ በሚውል መልኩ ማዘጋጀት ላይ ነው።
ቴክኖሎጂው የተለመደውን ብሎኬት ከመጠቀም ይልቅ፣ በአካባቢው የሚገኘውን አፈር ከትንሽ ሲሚንቶ ጋር በመቀላቀል ደረጃውን የጠበቀ ቤት ለመገንባት የሚያስችል ነው ብለዋል።
በእነዚህ አካባቢዎች ለሚኖሩ ከ6 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች የቤት ግንባታ ችግርን የሚቀርፍ መፍትሔ ይዞ መቅረቡን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
ግንባታዎች ሙሉ በሙሉ በሲሚንቶ ላይ ብቻ የተንጠለጠሉ እንዳይሆኑ በማድረግ የግንባታ ወጪን በእጅጉ እንደሚቀንስም ተገልጿል።
ጥናቱ ሁሉንም የኢንጂነሪንግ መስፈርቶች አሟልቶ በቤተ-ሙከራ የተረጋገጠ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት "ለአካባቢያዊ ችግር አካባቢያዊ መፍትሔ" በሚል ስትራቴጂ ለመጨረሻ ማረጋገጫ ለውይይት ቀርቧል።
በታደሠ ብናልፈው
https://t.me/ethioengineers1
1 363
የባንክ ሒሳብን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር አላጣመሩም? ጊዜው እየሄደ ስለሆነ በቀጥታ ካሉበት ሆነው ኦንላይን ያጣምሩ።
ልብ ይበሉ፦ ሲስተም ላይ በነበረ መጨናነቅ ለቀናት ቆይቶ የነበረውም የመዘግየት ችግር በመፈታቱ ፣ ደንበኛ የሆኑበትን ባንክ ከታች በተዘረዘሩት ዝርዝር በመምረጥ ባለ 16 አኃዝ የፋይዳ ቁጥርዎን (FAN/FCN) በመጠቀም ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር ለማጣመር (Harmonization) በነዚህ ሊንኮች ይጠቀሙ።
💸 አቢሲኒያ ባንክ: https://cs.bankofabyssinia.com/fayda_connect
💸 አዋሽ ባንክ : https://fayda.awashbank.com
💸 የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ: https://my.coopbankoromiasc.com/harmonization
💸 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፡ https://cbefayda.cbe.com.et/
💸 ኦሮሚያ ባንክ ፡ https://obfayda.oromiabank.com/
💸 ወጋገን ባንክ : https://fayda.wegagenbanksc.com.et/harmonization
💸 ንብ ባንክ፡ https://fayda.nibbank.com.et/
💸 ፀሀይ ባንክ፡https://fayda.tsehaybank.com.et/FAYDA/home
💸 ስንቄ ባንክ : https://fayda.siinqeebank.com:7443
💸 ዘምዘም ባንክ : https://fayda.zamzambank.com.et
💸 አማራ ባንክ : https://fayda.amharabank.com.et
1 363
🏗️ Heavy Construction Machinery Line-Up 🚧 A complete showcase of essential machines used in modern construction projects, each playing a vital role in building, lifting, mixing, and transporting materials efficiently ⚙️🚜
1 363
የአዲስ አበባ ሁሉንም FM ጣቢያዎች online ማዳመጥ ከፈለጋችሁ ደግሞ
https://qedamawi.vercel.app/
በጣም በቀላል ኔትዎርክ በጥራት ይሰማል።
1 363
Oromia Construction Authority (OCA) የ2018 ዓ.ም 2ኛ ሩብ ዓመት የግንባታ ሥራዎች የቀጥተኛ ዋጋ (Direct Cost) ጥናት ሰነድ
@ConstructionIE
