cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

طــــريــقــة الــنــجــاح

من أحب أن لا ينقطع عمله بعد موته فلينشر العلم {ابن الجوذي رحمه الله /التذكرة(٥٥)

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
654
Suscriptores
-124 horas
-17 días
-730 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

#አዲስ_ደርስ ↩️ شرح الأصول الثلاثة ↪️ የሶስቱ መሰረቶች ማብራሪያ ╭┈─────── ╰┈➤ ክፍል 01 📝 بقلم الشيخ الدكتور حسين بن محمد بن عبد الله السلطي الإثيوبي حفظه الله 📝 አዘጋጅ:- ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ ቢን ዐብደላህ አስ-ሲልጢይ (አላህ ይጠብቃቸው!) 🎙 لأخ أَبِي عِمرَان مُحَمَد مَكُونْنْ حَفِظَهُ اللّٰه 🎙 በወንድም አቡ ዒምራን [መሐመድ መኮንን] 📮 የኪታቡ pdf ➴➴➴ https://t.me/AbuImranAselefy/8866 🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥 🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️ https://t.me/AbuImranAselefy https://t.me/AbuImranAselefy https://t.me/AbuImranAselefy
Mostrar todo...
01 شَرْحُ الأُصُولُ الثَلَاثَة .mp325.75 MB
የሰለፎችን ጎዳና የተቃረነ ሰው... 📝 በታላቁ ሊቅ ሸይኽ ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸው ⁉️ በሰለፍ መንሐጅ ላይ የተቃረነ አካል ከአህለል ቢድዓ ይቆጠራል ወይም ከአህለሱና መጠሪያነት ይወጣል ወይስ አይወጣም?  ✅ የሰለፎችን መዝሀብ የተቃረነ ከአህለሱና ወልጀማዓህ አይደለም፡፡ ይልቁንም ከኸለፎች (ወደኋላ መጠው በዲኑ ላይ ከዘባረቁት) ነው፡፡ የሰለፎችን መዝሐብ ከተቃረነ በሰለፍ መንሐጅ ሊሆን አይችልም፡፡ በእርግጥ ጥመቱ በተቃርኖው መጠን ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም ሰዎች በተቃርኖ ይበላለጣሉ፡፡ በመሆኑም እንደተቃርኗቸው የሚሰጣቸውም ብይን በዚያው መጠን ይለያያል፡፡ 💼 ከሸይኽ ዩሱፍ አላህ ይጠብቃቸው ▵▮▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▯▴ ⚙ 📝 أَبُـــو عِـمْــرَان ❨𝕒𝕓𝕦 𝕚𝕞𝕣𝕒𝕟❩ 🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣  ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞 🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥 🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️ https://t.me/AbuImranAselefy/8875 https://t.me/AbuImranAselefy https://t.me/AbuImranAselefy ሀሳብ  ካለዎ  ⤵️⤵️⤵️⤵️ https://t.me/AbuImranAselefybot
Mostrar todo...
Abu Imran Muhammed Mekonn

ዝም አንልም እኛ በህይወት እስካለን፤ ባለችው አቅማችን እንፋለማለን፤ ያበጠው ይፈንዳ ሲፈልግ ይተርተር፤ እውነት ይነገራል ቢጣፍጥም ቢመር። ያለወትን ሀሳብ 💡 ➢ @AbuImranAselefybot በሚለው ያድርሱኝ ⤵ ↪ እቀበላለሁ ↩ ⤴ ➻ በተለይ ስህተት ካዩ በፍጥነት ይጠቁሙኝ

ከዘረፋ ወደ ታላቅ ኢማምነት ❴በአንዲት የቁርአን አንቀፅ በመስራት የተገኘ ታላቅ ክብር❵ ከታቢዒዮች መካከል ታላቅ መሪ የሆኑት ፉዶይል -አላህ ይዘንላቸውና- ጸጸት ከማድረጋቸው በፊት ግማሽ የሆነውን ህይዎታቸውን ያሳለፉት በዘረፋ ተግባር ወይም በሽፍትነት ነው፡፡ አርባ አመት እስኪሞላቸው ድረስ የአካባቢው ህብረተሰብ በጣም ይሰጋቸው ነበር፡፡ “ሲየር አዕላም አን’ኑበላእ” በተባለው ኪታብ ዘህብይ -ረሂመሁሏህ- የእርሳቸውን የጸጸት ታሪክ እንደሚከተለው ይገልጹታል፡፡ ለጸጸት ምክንያት የሆነቻቸው አንዲትን ሴት በማፍቀራቸው ምክንያት እንደሆነ ይወሳል፡፡ ወደሴትዮዋ ቤት ለመድረስ አጥር ላይ ሲወጡ በአጋጣሚ የሚከተለውን የቁርኣን አንቀጽ የሚቀራ ሰው አደመጡ፡፡ ۞ أَلَمْ يَأْنِ لِلَّذِينَ آمَنُوا أَن تَخْشَعَ قُلُوبُهُمْ لِذِكْرِ اللَّهِ “ለነዚያ ለአመኑት ለአላህ ተግሳጽና ከቁርኣንም ለወረደው ልቦቻቸው ሊፈሩ…. አልቀረበምን?” 📚 [ ሱረቱ አል-ሐዲድ - 16 ] “ጌታየ ሆይ አዎ ቀርቧል” የሚል መልስ ሰጡ፡፡ ከዚያም ካሰቡት አላማ ተጸጽተው ተመለሱ፡፡ ያኔ እርሳቸው በተጸጸቱበት ወቅት መንገደኞች “እንለፍ አንለፍ? ፉዶይል ቢዘርፈንስ?” በማለት ጭንቀት ውስጥ እንደነበሩ በታሪክ ተዘግቧል፡፡ ፉዶይል የሚከተለውን ተናገሩ፡- ((አስተነተንኩ፣ ሙስሊሞች እኔን ይሰጋሉ፣ እኔ ግን በሌሊት ወንጀል ለመፈጸም እንቀሳቀሳለሁ፣ እኔን ወደዚህ አላህ አላመጣኝም ጸጸትን ለእኔ ሽቶልኝ እንጅ፤ አላህ ሆይ! እኔ ወደአንተ ተጸጽቻለሁ፤ በህይዎት እስካለሁ ድረስ ካዕባን መጎራበት ለእኔ ከጸጸቴ መካከል አንዱ ነው፡፡)) 📖 ሲየር አዕላም አን ኑበላእ፡ 8/423 ፉዶይል ከዚህ ዓለም በሞት እስኪሰናበቱ ድረስ መካ ውስጥ አላህን ይገዙ ነበር፡፡ ከመካ ዑለሞች የሐዲስ የተለያዩ የፊቅህ እውቀቶችን ቀስመዋል፤ ሐዲስ ሀፍዘዋል፡፡ ለዚህ ነው ሙስሊሞች የተፍሲር፣ የሐዲስና የፊቅህ መጽሐፎችን ገልጠው ሲያነቡ የዚህን ታላቅ ኢማም ስም ዘወትር የሚያስተውሉት፡፡ አንዲት አንቀጽ የፉዶይልን ህይዎት ከከባድ አመጸኝነት ወደ ደጋግ የአላህ ባሪያነት ቀየረች ፤ የኢማሞች ሁሉ ኢማም አደረገች፡፡ 💼 ከሸይኽ ዩሱፍ አላህ ይጠብቃቸው ▵▮▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▯▴ ⚙ 📝 أَبُـــو عِـمْــرَان ❨𝕒𝕓𝕦 𝕚𝕞𝕣𝕒𝕟❩ 🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣  ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞 🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥 🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️ https://t.me/AbuImranAselefy https://t.me/AbuImranAselefy https://t.me/AbuImranAselefy ሀሳብ  ካለዎ  ⤵️⤵️⤵️⤵️ https://t.me/AbuImranAselefybot
Mostrar todo...
Abu Imran Muhammed Mekonn

ዝም አንልም እኛ በህይወት እስካለን፤ ባለችው አቅማችን እንፋለማለን፤ ያበጠው ይፈንዳ ሲፈልግ ይተርተር፤ እውነት ይነገራል ቢጣፍጥም ቢመር። ያለወትን ሀሳብ 💡 ➢ @AbuImranAselefybot በሚለው ያድርሱኝ ⤵ ↪ እቀበላለሁ ↩ ⤴ ➻ በተለይ ስህተት ካዩ በፍጥነት ይጠቁሙኝ

🔶አዲስ የአቂዳ ኪታብ ቂርአት 📚 اسـم الكتـاب፡- ➘➷➴ ⬅️ مـن أصـول عقيـدة أهـل السنـة والجمـاعة ➡️ ሚንኡሱሊ አቂደቲ አህሊሱነቲ ወልጀማአህ! 📝تأليف፡- الشيـخ صالـح بـن فـوزان بـن عبـد اللَّـه الفـوزان ▶"ደርስ ቁጥር 1⃣1⃣ 🎙أبو عبد الرحمن المرسي(حفظه الله) 📜የኪታብ 𝐏𝐝𝐟  ለማግኘት⇩⇩ https://t.me/Abu_Abdirehman_Almersi/2834 ⤵ክፍል 1⃣0⃣ ለማግኘት↘↘ https://t.me/Abu_Abdirehman_Almersi/3036 ሌሎች ትምህርቶችን ለማግኘት ⤵ 📲⇘»https://t.me/Abu_Abdirehman_Almersi 📲⇘»https://t.me/Abu_Abdirehman_Almersi
Mostrar todo...
من أصول 11.m4a7.03 MB
🔷 የነብዩላሂ ኢብራሂም ታሪክ ክፍል ሰባትና የመጨረሻው ነብዩላሂ ኢስማኢል ከአደን ሲመለሱ የመጣ ሰው ነበር ወይ ብለው ጠየቅዋት ። አው ብላ የሆነውን ነገረቻቸው ። ምን አለሽ አሉዋት ባለቤትሽ ሲመጣ የቤትህን መቃን አጥብቀው ጥሩ መቃን ነው በይው ብሎኛል አለችው ። እሳቸውም እሱ አባቴ ነው መቃኗ አንቺ ነሽ በደንብ ያዛት ማለቱ ነው አሉዋት ።    ነብዩላሂ ኢብራሂም ለሶስተኛ ጊዜ ቤተሰባቸውን ለማየት ወደ መካ መጡ ። ነብዩላሂ ኢስማኢል ቀስት እየሰሩ አገኟቸው ። ሁለቱም ተያዩ አባት በልጁ ላይ ልጅም በአባቱ ላይ እንደሚያደርገው ተቃቅፈው ተሳሳሙ ። ነብዩላሂ ኢብራሂም ካዕባን ከልጃቸው እስማኢል ጋር ሆነው መሰረቱን ከፍ አድርገው እንዲገነቡ አላህ ያዘዛቸው መሆኑን ነገሯቸው ። ነብዩላሂ ኢስማኢልም በጣም ተደሰቱ ። ካዕባንም መገንባት ጀመሩ ። ይህን ክስተትና ከግንባታው ጋር የተገናኙ ሁለቱም ያደረጓቸው ዱዓኦችን አላህ በላሚቷ ምእራፍ ከ25 – 30ኛው አንቀፅ ላይ እንዲህ ብሎ ይነግረናል : – وَإِذْ جَعَلْنَا الْبَيْتَ مَثَابَةً لِّلنَّاسِ وَأَمْنًا وَاتَّخِذُوا مِن مَّقَامِ إِبْرَاهِيمَ مُصَلًّى ۖ وَعَهِدْنَا إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ أَن طَهِّرَا بَيْتِيَ لِلطَّائِفِينَ وَالْعَاكِفِينَ وَالرُّكَّعِ السُّجُودِ ቤቱንም ለሰዎች መመለሻና ጸጥተኛ ባደረግን ጊዜ (አስታውስ) ፡፡ ከኢብራሂምም መቆሚያ መስገጃን አድርጉ ፡፡ ወደ ኢብራሂምና ወደ ኢስማዒልም ቤቴን ለዘዋሪዎቹና ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ ስንል ቃል ኪዳን ያዝን ፡፡ وَإِذْ قَالَ إِبْرَاهِيمُ رَبِّ اجْعَلْ هَٰذَا بَلَدًا آمِنًا وَارْزُقْ أَهْلَهُ مِنَ الثَّمَرَاتِ مَنْ آمَنَ مِنْهُم بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ ۖ قَالَ وَمَن كَفَرَ فَأُمَتِّعُهُ قَلِيلًا ثُمَّ أَضْطَرُّهُ إِلَىٰ عَذَابِ النَّارِ ۖ وَبِئْسَ الْمَصِيرُ ኢብራሂም ባለ ጊዜ (አስታውስ) ፡፡ ጌታዬ ሆይ! ይህንን ጸጥተኛ አገር አድርግ፡፡ ቤተሰቦቹንም ከነሱ በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነውን ሰው ከፍሬዎች ስጠው ፡፡ (አላህም) የካደውንም ሰው፤ (እሰጠዋለሁ) ፡፡ ጥቂትም እጠቅመዋለሁ፤ ከዚያም ወደ እሳት ቅጣት አስጠጋዋለሁ፤ ምን ትከፋም መመለሻ! (አለ) ፡፡ وَإِذْ يَرْفَعُ إِبْرَاهِيمُ الْقَوَاعِدَ مِنَ الْبَيْتِ وَإِسْمَاعِيلُ رَبَّنَا تَقَبَّلْ مِنَّا ۖ إِنَّكَ أَنتَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ ኢብራሂምና ኢስማኢልም «ጌታችን ሆይ! ከእኛ ተቀበል፡፡ አንተ ሰሚውና ዐዋቂው አንተ ነህና» የሚሉ ሲኾኑ ከቤቱ መሠረቶቹን ከፍ ባደረጉ ጊዜ (አስታውስ) ፡፡ رَبَّنَا وَاجْعَلْنَا مُسْلِمَيْنِ لَكَ وَمِن ذُرِّيَّتِنَا أُمَّةً مُّسْلِمَةً لَّكَ وَأَرِنَا مَنَاسِكَنَا وَتُبْ عَلَيْنَا ۖ إِنَّكَ أَنتَ التَّوَّابُ الرَّحِيمُ «ጌታችን ሆይ! ላነተ ታዛዦችም አድርገን ፡፡ ከዘሮቻችንም ላንተ ታዛዦች ሕዝቦችን (አድርግ) ፡፡ ሕግጋታችንንም አሳየን፤ (አሳውቀን) ፡፡ በኛም ላይ ተመለስን፤ አንተ ጸጸትን ተቀባዩ ሩኅሩኅ አንተ ብቻ ነህና ፡፡» رَبَّنَا وَابْعَثْ فِيهِمْ رَسُولًا مِّنْهُمْ يَتْلُو عَلَيْهِمْ آيَاتِكَ وَيُعَلِّمُهُمُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَيُزَكِّيهِمْ ۚ إِنَّكَ أَنتَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ «ጌታችን ሆይ! በውስጣቸውም ከነሱው የኾነን መልክተኛ በነርሱ ላይ አንቀጾችህን የሚያነብላቸውን መጽሐፍንና ጥበብንም የሚያስተምራቸውን (ከክህደት) የሚያጠራቸውንም ላክ፤ አንተ አሸናፊው ጥበበኛው አንተ ብቻ ነህና» (የሚሉም ሲኾኑ) ፡፡ وَمَن يَرْغَبُ عَن مِّلَّةِ إِبْرَاهِيمَ إِلَّا مَن سَفِهَ نَفْسَهُ ۚ وَلَقَدِ اصْطَفَيْنَاهُ فِي الدُّنْيَا ۖ وَإِنَّهُ فِي الْآخِرَةِ لَمِنَ الصَّالِحِينَ ከኢብራሂምም ሕግጋት ነፍሱን ያቄለ ሰው ካልኾነ በስተቀር የሚያፈገፍግ ማነው? (የለም)፤ በቅርቢቱም ዓለም በእርግጥ መረጥነው ፡፡ በመጨረሻይቱም ዓለም እርሱ ከመልካሞቹ ነው ፡፡ አላህ ለነብዩላሂ ኢብራሂም የካዕባን ቦታ አመላክቷቸው ከገቡ በኋላ ካዕባን ገንብተው ጨረሱ ። አላህም ለሐጅ ጥሪ እንዲያደርጉ አዘዛቸው ። እሳቸውም ጌታዬ ሆይ እንዴት አሰማለሁ አሉ ። አላህ አንተ ተጣራ እኔ አሰማለሁ አላቸው ። ተጣሩም ። አላህ ጥሪው እንዲሰሙ ካደረጋቸው ነፍሶች ውስጥ በዛን ጊዜ የነበሩና የቻሉ እንዲመጡ አደረጋቸው ። ነብዩላሂ ኢብራሂምም የመጡትን የሐጅን ስርኣት አስተማሯቸው ። እነዚያ ስርኣቶች ናቸው ሐጅ ላይ የሚከናወኑት ። ይህ ክስተት በሐጅ ምእራፍ ላይ በሰፊው ተብራርቷል ። ከዛውስጥ 26ኛውና 27ኛውን አንቀፅ ቀጥሎ እንመልከት : – وَإِذْ بَوَّأْنَا لِإِبْرَاهِيمَ مَكَانَ الْبَيْتِ أَن لَّا تُشْرِكْ بِي شَيْئًا وَطَهِّرْ بَيْتِيَ لِلطَّائِفِينَ وَالْقَائِمِينَ وَالرُّكَّعِ السُّجُودِ ለኢብራሂምም የቤቱን (የካዕባን) ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ «በእኔ ምንንም አታጋራ፣ ቤቴንም ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው» (ባልነው ጊዜ አስታውስ) ፡፡ وَأَذِّن فِي النَّاسِ بِالْحَجِّ يَأْتُوكَ رِجَالًا وَعَلَىٰ كُلِّ ضَامِرٍ يَأْتِينَ مِن كُلِّ فَجٍّ عَمِيقٍ (አልነውም) ፡- በሰዎችም ውስጥ በሐጅ ትዕዛዝ ጥራ ፡፡ እግረኞች ከየሩቅ መንገድ በሚመጡ ከሲታ ግመሎችም ሁሉ ላይ ሆነው ይመጡሃልና ፡፡ ከዚህ በኋላ ነብዩላሂ ኢብራሂም መካ ላይ ተረጋግተው መኖር ጀመሩ ። የኢስሐቅን ልጅ ነብዩላሂ የዕቆብን ካዩ በኋላ ወደ አኼራ ሄዱ ። የነብዩላሂ ኢብራሂም አጭር የህይወት ታሪክ በዚህ ተፈፀመ ። ክፍል አንድን ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/bahruteka/5019 ክፍል ሁለት 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/bahruteka/5022 ክፍል ሶስት 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/bahruteka/5026 ክፍል አራት 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/bahruteka/5033 ክፍል አምስት 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/bahruteka/5034 ክፍል ስድስትን 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/bahruteka/5037 http://t.me/bahruteka
Mostrar todo...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

👉 የነብዩላሂ ኢብራሂም ታሪክ ክፍል አንድ የነብዩላሂ ኢብራሂም ታሪክ ቁርኣን ላይ ቱክረት ከተሰጣቸው የነብያት ታሪክ ውስጥ በግንባር ቀደምትነት ይመደባል ። ታሪካቸው ቁርኣን ውስጥ በ17 ምእራፍ ወደ 69 ጊዜ ተጠቅሷል ። ይህ የሚያሳየው ታሪካቸው ምን ያክል አስፈላጊና ቁም ነገር አዘል መሆኑ ነው ። ነብዩላሂ ኢብራሂም ዒራቅ ውስጥ ባቢል በሚባል ቦታ በጣኦት አምላኪ ማህበረሰብ ውስጥ ተወለዱ ። ከህብረተሰቡ ውስጥ ኮከብ የሚያመልክ ፣ ጨረቃ የሚያመልክና ፀሀይ የሚያመልክ እንዲሁም ከእንጨት የተሰራ ጣኦት የሚያመልክ ነበር ። አባታቸው ኣዘር ከእንጨት ጣኦት እየሰራ ይሸጥ ነበር ። እሳቸው በልጅነታቸው እርሻ ይሰሩ ነበር ። አባታቸው ጣኦት እያዞሩ እንዲሸጡላቸው ሲያዙዋቸው ተቀብለው መሬት ለመሬት እየጎተቱ የማይጠቅምና የማይጎዳ የሚገዛ እያሉ ያዞሩ ነበር ። በዚህም ምክንያት ማንም የሚገዛ ስለማያገኙ ይዘውት ይመለሳሉ ። እድሜያቸው 13 አመት ሲሞላቸው ፈጣሪዬ ማን ነው ብለው ማሰብ ጀመሩ ። ቤተሰቦቻቸውና ማህበረሰቡ በሚያመልኩት ነገር ደስተኛ አልነበሩም ። ለብቻቸው ሲሆኑ ማን ነው የፈጠረኝ እያሉ ይብሰለሰላሉ ። በዚህ ስሜት ውስጥ ሆነው ከቤት ወጥተው ወደ ሰማይ በሚያዩበት ጊዜ የተከሰተውን አላህ ሲነግረን በአል አንዓም ምእራፍ ከ75 – 79 ድረስ እንዲህ ይለናል : – وَكَذَٰلِكَ نُرِي إِبْرَاهِيمَ مَلَكُوتَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَلِيَكُونَ مِنَ الْمُوقِنِينَ እንደዚሁም ኢብራሂምን (እንዲያውቅና) ከአረጋጋጮቹም ይኾን ዘንድ የሰማያትንና የምድርን መለኮት አሳየነው ፡፡ فَلَمَّا جَنَّ عَلَيْهِ اللَّيْلُ رَأَىٰ كَوْكَبًا ۖ قَالَ هَٰذَا رَبِّي…

👉 የነብዩላሂ ኢብራሂም ታሪክ ክፍል ስድስት ነብዩላሂ ኢብራሂም የጌታቸውን ትእዛዝ ብቸኛ ልጃቸውን በማረድ ለመፈፀም ባሳዩት ቁርጠኛና አስገራሚ አቋም አላህ ሌላ ልጅም እንደሚሰጣቸው ብስራት ላከላቸው ። ይህም በተከበረው ቃሉ ከመጀመሪያ ሚስታቸው ሳራ ኢስሓቅና የልጅ ልጃቸው የዕቆብም የሚሰጣቸው መሆኑን በሚቀጥለው የሁድ ምእራፍ 71ኛው ላይ አንቀፅ እንዲህ ብሎ ይነግረናል : – وَامْرَأَتُهُ قَائِمَةٌ فَضَحِكَتْ فَبَشَّرْنَاهَا بِإِسْحَاقَ وَمِن وَرَاءِ إِسْحَاقَ يَعْقُوبَ ሚስቱም የቆመች ስትኾን (አትፍራ አሉት) ሳቀችም፡፡ በኢስሐቅም አበሰርናት፡፡ ከኢስሐቅም በኋላ (በልጁ) በያዕቁብ (አበሰርናት)፡፡ ሳራ እኔ አሮጊት ሆኜ ባለቤቴም ሽማግሌ ሆኖ ሳለ እወልዳለሁኝ እንዴ አለች በመገረም ። መላኢካዎችም በአላህ ጉዳይ ትገረሚያለሽን አሉ ። አላህ ሁሉን ቻይ ነውና ያሻውን ይሰራል ። እሱ ካሻ ከአሮጊት ማህፀን ነብይ ይፈጥራል ። ይህንንም በዛው ምእራፍ ቀጥሎ ባለው አንቀፅ ይነግረናል : – قَالَتْ يَا وَيْلَتَىٰ أَأَلِدُ وَأَنَا عَجُوزٌ وَهَٰذَا بَعْلِي شَيْخًا ۖ إِنَّ هَٰذَا لَشَيْءٌ عَجِيبٌ (እርሷም) ዋልኝ! እኔ አሮጊት ይህም ባሌ ሽማግሌ ሆኖ ሳለ እወልዳለሁን ይህ በእርግጥ አስደናቂ ነገር ነው አለች ፡፡ قَالُوا أَتَعْجَبِينَ مِنْ أَمْرِ اللَّهِ ۖ رَحْمَتُ اللَّهِ وَبَرَكَاتُهُ عَلَيْكُمْ أَهْلَ الْبَيْتِ ۚ إِنَّهُ حَمِيدٌ مَّجِيدٌ «ከአላህ ትዕዛዝ ትደነቂያለሽን የአላህ ችሮታና በረከቶቹ በእናንተ በኢብራሂም ቤተሰቦች ላይ ይሁን እርሱ ምስጉን ለጋስ ነውና» አሉ ፡፡ ነብዩላሂ ኢብራሂም ኢስማኢልን ለማረድ ወስነው አላህ በሙክት ቀይሮላቸው ካበሰራቸው በኋላ ወደ ሻም ተመልስው ወደ አላህ አምልኮ ይጣሩ ጀመር ። ኢስማኢልም አደጉ እድሜያቸውም ለነብይነት ደረሰ አላህ ነብይ አደረጋቸው ። ዳዕዋ ማድረግ ጀመሩ ከጁርሁም ጎሳዎችም የሆነች ሴት አገቡ ። ነብዩላሂ ኢብራሂም ቤተሰባቸውን ለማየት ወደ መካ መጡ ። ነብዩላሂ ኢስማኢል ለአደን ወጥተዋል ። ሚስትየውን አገኙ ስለኑሯቸው ጠየቁዋት በጣም በችግር ነው ያለነው ። አዝመራም የለም ። ምግብም ውሀም የለም ረሀብና ጥም ነው አለቻቸው ። አላህ በወሰነው ነገር ባለመውደድዋ ደስ አላላቸውም ። ባለቤትሽ ሲመጣ የቤትህን መቃን ቀይረው ብለኋል ብለሽ ንገሪው ብለው ወደ ሻም ተመለሱ ። ነብዩላሂ ኢስማኢል ከአደን ተመለሱ ። የመጣ ሰው ነበር ወይ ብለው ጠየቁ አው አንድ ሽማግሌ እንግዳ መጥቶ ነበር አለችው ። ምን ጠየቀሽ አሉ ስለኑሯችን ጠየቀኝ ከዛም ያለንበትን ችግር ነገርኩት አለች ። ያለሽ ነገር አለን አሉዋት አው የቤትህን መቃን ቀይር በይው ብሎኛል አለች ። እሱ አባቴ ነው የቤቴ መቃን አንቺ ነሽ ፍታት ብሎኛል ወደ ቤተሰቦችሽ ሂጂ አሏት ( ፈቱዋት) ። ነብዩላሂ ኢስማኢል ሌላ የአንድ ምስኪን ልጅ አገቡ በጣም አላህን የምትፈራ ባለው የምትብቃቃ ለባልዋ ታዛዥ ነበረች ። ነብዩላሂ ኢስማኢል በደስታ ወደ አላህ መገዛት እየተጣሩ መኖር ጀመሩ ። አንድ ቀን እንደ ልማዳቸው ወደ አደን ሄዱ ። ነብዩላሂ ኢብራሂም ቤተሰባቸውን ለማየት መጡ ። ልጃቸው የለም ። ሁለተኛዋን ሚስት አገኙዋት ። እንግዳ ትወዳላችሁ ወይ ? ለእንግዳስ የምታቀርቡት ነገር አለ ወይ ብለው ሰላምታ አቅርበው ገቡ ። ሚስትየውም አልሐምዱ ሊላህ ምን ጠፍቶ ሁሉ ነገር አለ ግቡ አለች ። ነብዩላሂ ኢብራሂምም በሁኔታዋና መልሷ በጣም ተደሰቱ ። ምግባችሁ ምንድነው አሏት ስጋ አለቻቸው ። መጠጣችሁስ ምንድነው አሏት ውሀ ( የዘምዘም ውሀ ) አለች ። ዱዓእ አደረጉላቸው ። ባለቤትሽ ሲመጣ የቤትህን መቃን አጥብቀው ጥሩ መቃን ነው በይው ብለዋት ወደ ሻም ተመለሱ ። አላህ ካለ ይቀጥላል ። http://t.me/bahruteka
Mostrar todo...
ዳዕዋ ዳዕዋ ዳዕዋ 📢 ‼️ አስላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካትሁ ውድና የተከበራችሁ የሱና እአህቶችና ወንድሞች በያላችሁበት ቦታ ሁናችሁ ያአላህ እዝነቱና በረከቱ አይለየን አይለያችሁ በሱናም ላይ አላህ ያፅናን ያፅናችሁ እንኳን ለ (1445) ኢደል አድሃ በአል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ እነሆ አስደሳች ዜና ይዘን ዘልቀናል የፊታችን እሁድ ማለትም ሰኔ ቀን /16/2016/ታላቅ የዳዕዋ ዝግጅት ስላለን በተባለው ቦታ በጧት በመገኝት የዳዕዋው ተቋዳሽ ትሆኑ ዘንድ ታድማችኋል 🔄ብርቅየ ተጋባዥ እንግዶቻችነን ስናሳውቃችሁ በታላቅ ደስታ ነው ↘️1 ሸይኽ ሙሐመድ ሃያት ከሃራ ↘️2 ሸይኽ ሁሴን ከረም     ከሃራ ↘️3 ሸይኽ ሙሃመድ ሲራጅ ከሃሮ ↘️4 ሸይኽ ሁሴን አባስ  ከጉራ    ወርቄ ↘️5 ኡስታዝ ኑራድስ           ከሃራ ↘️6 ኡስታዝ ኑረድን            ከመርሳ ↘️7 ኡስታዝ አብዱረህማን  ከመርሳ የሚጠቀሱትና የሚዳሰሱት እርዕሶች በሰአቱ በቦታው ላይ የሚነገሩ ሲሆን ጥሪውን አስታውሱ እንዳትረሱ 👁‍🗨የዳዕዋው ባታ አጆሜዳ ሲሆን ከጃራ ከፍ ያለች ከድሌሮቃ ዝቅ ብላ የምትገኝ የገጠር አድስ ከተማ ናት  ወረዳ ሃብሩ ቀበሌ ( 024) በድጋሜ አጆ ሜዳ 🕑 የሚጀመርበት ሰአት ከጧቱ ሁለት 2:00 ሰአት ጀምሮ እስከ 10:00 ሰአት ድረስ የዘልቃል የኦናይን ስርጭትም ስለሚኖረን ሳትርቁ ጠብቁን 🕌 መስጅደ ፉርቃን አጆ ሜዳ ሰኔ/ቀን/16/2016/1445/ዓ/ሂ https://t.me/hussenhas
Mostrar todo...
አቡ አዒሻ العلم نور

የዚህ ቻናል ዋና አላማ ሱናን ማንገስ ሽርክን ማርከስ ነው!! የሱና መሻይኮችና የሱና ዳዒዎች የሚላክበት የዳዕዋ የደርስ ሴንተር ቻናል ነው ሐሳብ አስተያትን ያለምንም ጥበት እንቀበላለን ቅድሚያ ለተውሂድ በተግባር

🔶አዲስ የአቂዳ ኪታብ ቂርአት 📚 اسـم الكتـاب፡- ➘➷➴ ⬅️ مـن أصـول عقيـدة أهـل السنـة والجمـاعة ➡️ ሚንኡሱሊ አቂደቲ አህሊሱነቲ ወልጀማአህ! 📝تأليف፡- الشيـخ صالـح بـن فـوزان بـن عبـد اللَّـه الفـوزان ▶"ደርስ ቁጥር 9⃣ 🎙أبو عبد الرحمن المرسي(حفظه الله) 📜የኪታብ 𝐏𝐝𝐟  ለማግኘት⇩⇩ https://t.me/Abu_Abdirehman_Almersi/2834 ⤵ክፍል ዘጠኝን ለማግኘት↘↘ https://t.me/Abu_Abdirehman_Almersi/3021 ሌሎች ትምህርቶችን ለማግኘት ⤵ 📲⇘»https://t.me/Abu_Abdirehman_Almersi 📲⇘»https://t.me/Abu_Abdirehman_Almersi
Mostrar todo...
من أصول 10.m4a8.39 MB
🔷  ውድ የሱና ቤተሰቦቻችን አላህ እንኳን ለዒደል አድሓ በሰላም አደረሳችሁ تقبل الله منا ومنكم አላህ ዒዱ የሰላም የፍቅርና የአላህን ውዴታና እዝንት የሚያስገኝ ያድርግልን ።    የዘንድሮ ዒድ ከሌላ ጌዜ ለየት ባለ መልኩ የሚዘረፍበት ነውና እንጠቀምበት ። ብዙ ወንድምና እህቶች በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ያሉበት ነው ። ከሞቀ ቤታቸው ከተረጋጋ ህይወታቸው አላህ ለሒክማው በፈለገው ነገር ሜዳ ላይ ወድቀው ህፃናቶቻቸውን ይዘው የሰው እጅ እያዩ ነው ። የዚህ አይነት ፈተና ይገጥመናል ብለው አስበውት በማያውቁት ፈተና ውስጥ ናቸው ። በርግጥ ሶብር ካደረጉ መጨረሻው ያመረ መሆኑ ጥርጥር የለውም ።     እናስታውሳቸው አብሽር እንበላቸው ሐዘናቸውን እናስረሳቸው ። ዒዱ የደስታ እንዲሆንላቸው እንድረስላቸው እንዘይራቸው ። የዱንያ ህይወት ፈተና አያጣውምና የኛም ሁኔታ አይታወቅም ስለዚህ የዛሬ መልካም ስራችን ለነገ ስንቃችን ነውና እንሰንቅ ። https://t.me/bahruteka
Mostrar todo...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

🔷 የነብዩላሂ ኢብራሂም ታሪክ ክፍል አምስት ሃጀር የህፃኗ ረሀብና ለቅሶ ረፍት ነሳት ረሀቡ በህፃኑ ላይ እየበረታ ሄደ ለቅሶዉም እየጨመረ ሄደ ። እናት የልጇን ስቃይ ማየት አቃታት ተነስታ ቆማ ታማትር ጀመር ። የሶፋ ኮረብታ ቅርብ ሆኖ አየችው ወደዛ ሄደች ኮረብታው ላይ ወጥታ ግራና ቀኝ ማማተር ጀመረች ። ምናልባት ከሩቅ የሚታይ ነገር ቢኖር ብላ ምንም የለም ። ከሶፋ 30 መቶ ሜትር አካባቢ ርቆ የመርዋ ኮረብታ ታያት ። ወርዳ ወደዛ አመራች የተወሰነ ቦታ በሶምሶማ ሄደች መቀጠል ግን አልቻለችም ቀስ ብላ ደረሰች። ወደ ኮረብታው ወጥታ ማማተር ጀመረች ። ምንም ነገር የለም ጭንቀቷ ጨመረ ወደ ህፃኑ ዞር ብላ ስታይ ጩኸቱ በድካም ቀንሶ በጣረ ሞት በእግሩ መሬት እየመታ አየችው ። ምድሩ ጠበባት እየሆነ ያለው ነገር እውነት አልመስልሽ አላት ። ወደ ሶፋ ሄዳ እንደመጀመሪያ አደረገች ። ወረደች ወደ መርዋ ሄደች እዛም እንደተለመደው አደረገች ። በዚህ መልኩ በሶፋና በመርዋ 7 ጊዜ ተዘዋወረች ። መርዋ ላይ ሆኗ ስታማትር የሆነ ድምፅ ሰማች ለራሷ እስኪ ዝም በይ አለች ። አሁንም ድምፅ ሰማች ሲሞት ላለማየት ወደ ህፃኗ ማየት አትፈልግም ነበረ ። ድምፁ በልጇ አቅጣጫ ነበር ማሰማቱስ አሰማህ የምትረዳው ነገር ካለህ አለች ። ዞር ስትል ጅብሪል በክንፉ ከልጇ እግር ስር ሲመታ አየች ወዲያ ምንጭ ፈለቀ ። የሞት ሞቷ ደረሰች ምንጩን ሁለት እጆቿን ዘርግታ ዘም ዘም ( እትሂድ አትሂድ ) እያለች ትከበው ጀመር ስሙም ዘምዘም ተባለ ። ጠጣች ልጇንም አጠባች ። እሷም ልጇም በሚገርም ሁኔታ ሀይል አገኙ ። አላህ በዚህ መልኩ የሀጀርን አላህ ከሆነ ያዘዘህ አይጥለንም ያለችበትን ተወኩል እውን አደረገው ። ከየመን ወደ ሻም የሚሄዱ ነጋዴዎች አሞራ ሲያንዣብብ ተመለከቱ ። እስከዛሬ ድረስ በዚህ ስናልፍ አሞራ ሲያንዣብብ አይተን አናውቅም አንድ የተከሰተ ነገር ቢኖር ነው አሞራ የሚያንዣብበው ውሀ ባለበት አካባቢ ነውና እስኪ ሄዳችሁ እዩ ተብሎ ሁለት ሰዎች ተላኩ ። ሰዎቹም ሃጀርና ህፃኗ ውሀ አጠገብ ሆነው አዩ ተመልሰው ያዩትን ተናገሩ ። ሃጀርን ከሷ ጋር ለመኖር ትፈቅድላቸው እንደሆነ ጠየቋት እሷም ከውሀው መብት የላችሁም እኔ ነኝ ባለቤቱ መቀመጥ ትችላላችሁ አለቻቸው ። ጁርሁም የሚባሉት የየመን ሰዎች ቤተሰቦቻቸውን ይዘው መጥተው ከሃጀር ጋር መኖር ጀመሩ ። እነርሱ የምትፈልገውን ነገር እያቀረቡ እሷ ከዘምዘም ውሀ ትሰጣቸዋለች ። በዚህ መልኩ መካ ተቆረቆረች ። ነብዩላሂ ኢብራሂም ዘንድ 3 እንግዶች መጡ መልካቸው በጣም አስገራሚ ነበር ። ነብዩላሂ ኢብራሂም ከኔ በስተቀር ማንም አያስተናግዳቸውም አሉ ። ራሳቸው ምግብ ሰሩላቸው አቀረቡ ነገር ግን አይበሉም ። ይህን ታሪክ አላህ በዛሪያት ምእራፍ ከ24 – 28 አንቀፅ እንዲ ብሎ ይነግረናል : – هَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ ضَيْفِ إِبْرَاهِيمَ الْمُكْرَمِينَ የተከበሩት የኢብራሂም እንግዶች ወሬ መጥቶሃልን? إِذْ دَخَلُوا عَلَيْهِ فَقَالُوا سَلَامًا ۖ قَالَ سَلَامٌ قَوْمٌ مُّنكَرُونَ በእርሱ ላይ በገቡና «ሰለም» ባሉ ጊዜ (አስታውስ) ፡፡ «ሰላም ያልታወቃችሁ ሕዝቦች ናችሁ፤» አላቸው ፡፡ فَرَاغَ إِلَىٰ أَهْلِهِ فَجَاءَ بِعِجْلٍ سَمِينٍ ወደ ቤተሰቡም ተዘነበለ፤» ወዲያውም የሰባ ወይፈንን አመጣ ፡፡ فَقَرَّبَهُ إِلَيْهِمْ قَالَ أَلَا تَأْكُلُونَ ወደእነርሱም (አርዶና ጠብሶ) አቀረበው፡፡ «አትበሉም ወይ?» አላቸው ፡፡ فَأَوْجَسَ مِنْهُمْ خِيفَةً ۖ قَالُوا لَا تَخَفْ ۖ وَبَشَّرُوهُ بِغُلَامٍ عَلِيمٍ ከእነርሱ መፍራትንም በልቡ አሳደረ ፡፡ «አትፍራ» አሉት ፡፡ በዐዋቂ ወጣት ልጅም አበሰሩት ፡፡ ነብዩላሂ ኢብራሂም ቤተሰባቸውን ለማየት ከሻም ወደ መካ መጡ ። ልጃቸውን ኢስማኢልን ሲያዩ ከሚጠብቁት በላይ ተደሰቱ ። ኢስማኢል ወደ 14 አመታቸው አካባቢ ሆኗል ። ለአላህ የሰጡት አደራ በሚገርም ሁኔታ ተጠብቋል ። የልጃቸው እድገትና ሁኔታ ትልቅ ደስታ ፈጥሮባቸዋል ። ፍቅሩ በውስጣቸው ገባ አላህ ነብዩላሂ ኢብራሂም ከአላህ ውጪ የሌላ ነገር ፍቅር ውስጣቸው እንዲገባ አይፈቅድም ። ነብዩላሂ ኢብራሂም በመናማቸው ኢስማኢልን ሲያርዱት አዩ የነብያት መናም እውነት ነውና ለኢስማኢል ነገሩት ኢስማኢልም አባቴ ሆይ የታዘዝከውን ፈፅም ከታጋሾች ሆኜ ታገኘኛለህ አላቸው ። ነብዩላሂ ኢብራሂምም ኢስማኢልን ይዘው ወደ ማረጃው ቦታ ማምራት ጀመሩ ። መንገድ ላይ ሸይጣን ኢስማኢልን አባትህ መናም ማየቱን እንዴት አመንክ እያለ ይወሰውስ ጀመር ። ኢስማኢልም ጠጠር አንስተው በሸይጣን ላይ ይወረውሩ ጀመር ። እናቱ ጋር ሄዶ መወትወት ጀመረ ። ተመሳሳይ ነገር ገጠመው ። ቦታው ላይ ሲደርሱ ነብዩላሂ ኢብራሂም ኢስማኢልን ሊያርዱዋቸው አስተኙዋቸው ። የነብዩላሂ ኢብራሂም ሁኔታ ያየው ኢስማኢል በፊት ለፊቴ አስተኛኝና በማጅራቴ በኩል እረደኝ አላቸው ይላሉ አንዳንድ ዘገባዎች ። አስተኝተው ሊያርዱት ሲሉ ጅብሪል ሙክት ይዞ መጥቶ በኢብራሂም ፈንታ ይህን እረድ አላቸው ። አላህ የፈለገው የኢስማኢል መታረድ ሳይሆን አባትና ልጅ ለአላህ ትእዛዝ ያላቸውን ቦታ ማሳየት ነበርና ታይቷል ። ይህን ክስተት ቁርኣን በሷፋት ምእራፍ ከ102 – 107 ድረስ ይነግረናል : – فَلَمَّا بَلَغَ مَعَهُ السَّعْيَ قَالَ يَا بُنَيَّ إِنِّي أَرَىٰ فِي الْمَنَامِ أَنِّي أَذْبَحُكَ فَانظُرْ مَاذَا تَرَىٰ ۚ قَالَ يَا أَبَتِ افْعَلْ مَا تُؤْمَرُ ۖ سَتَجِدُنِي إِن شَاءَ اللَّهُ مِنَ الصَّابِرِينَ ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ ፡፡ فَلَمَّا أَسْلَمَا وَتَلَّهُ لِلْجَبِينِ ሁለቱም ትዕዛዙን በተቀበሉና በግንባሩም ጎን ላይ በጣለው ጊዜ (የሆነው ሆነ) ። وَنَادَيْنَاهُ أَن يَا إِبْرَاهِيمُ ጠራነውም፤ (አልነው) «ኢብራሂም ሆይ! قَدْ صَدَّقْتَ الرُّؤْيَا ۚ إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ ራእይቱን በእውነት አረጋገጥክ፡፡» እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡ إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ الْبَلَاءُ الْمُبِينُ ይህ እርሱ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው ፡፡ وَفَدَيْنَاهُ بِذِبْحٍ عَظِيمٍ በታላቅ ዕርድም (መስዋዕት) ተቤዠነው ፡፡ የነብዩላሂ ኢብራሂም የሃጀርና ኢስማኢል ታሪክ በአብዛኛው ከሀጅ ስራ ጋር ይገናኛል ። በየአመቱ ዒደል አድሓ ቀን የሚታረደው እርድም ይህን ታላቅ ክስተት ለማስታወስ ነው ። አላህ ካለ ይቀጥላል ። http://t.me/bahruteka
Mostrar todo...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.