HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ
Ir al canal en Telegram
❤️ ቅዱሳን አባቶች እንዲህ ይላሉ **ጸጋ ያለምስጋና አያድግም ይላሉ** እግዚአብሔር ሆይ ስለሆነልኝ፣ ክፉውንም ከእኔና ከቤተሰቦቼ ስላራክልኝ 👏 አመሰግንሃለሁ ❤️ 👇👇👇 http://www.youtube.com/@haileG2239
Mostrar más2 280
Suscriptores
Sin datos24 horas
+117 días
+3830 días
Archivo de publicaciones
ጥያቄ 1: እሷ የዳዊት ታላቅ አያት ናት፡ የቦኤዝ ምስት፡ ለኑኃሚን ምራት። ይህቺ ሴት ማን ትባላለች?
=> እግዚአብሔር ሆይ እናመሰግንሃለን፡፡ ዓለም ለዲዮጋን እንዳለፈች፤ ለእስክንድርም አልፋለችና አሳላፊው ጌታዬ እናመሰግንሃለን፡፡ ያኖረን እጅህ እንጂ መልፋታችን መፍጨርጨራችን አይደለም፡፡ ሁሉ ባንተ ዘንድ ከተወሰነ መጨነቃችን ከንቱ ነውና አርቅልን፡፡ ስለጎደለን ነገር አንተን ከሰይጣን ጋር ከምናማህ፣ ስላለን ነገር ከመላእክት ጋር እንዳመሰግንህ እርዳን፡፡ እንዳትረሳን በእጆችህ መዳፍ ስለቀረጽከን እናመሰግንሃለን፡፡ ያመኑህን በመንገድ ጥለህ አትገባምና ለዘላለሙ አሜን!!
=> አገልግሎታችን እንደቀጠለ ነው የፊታችን እሁድ ጥቅምት /3/ 2017 ዓ.ም በሰሚት ዋሻ መካነ ሕይወት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ከቅዳሴ በኋላ አገልግሎቱ ይቀጥላል!
=> የቤተክርስቲያኑ አድራሻ፤ ሳሚት ኮንዶሚኒየም 2ተኛ በር ወረድ ብሎ ከኢትዮ ቻይና ት/ቤት እንደ ሁለተኛ መንገድ አማራጭ ሰሚት ጤና ጣቢያ መግቢያ መሆኑን እየገለጽን #Share, Like, Comment እያደረጋችሁ ላልሰሙት አሰሙ ላልነቁ አንቁ! መንፈሳዊነት ይብለጥ! የማዳመጥ ጊዜ ላይ ነን!!!
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@Estifanos2239
ከቤተሰቦቼ ጋር ወሲብ ያስፈጽመኛል! | ትዳርን የሚዘጋ፣ የሚያስጠላ የዓይነጥላ መንፈስ | የጠቋር መንፈስ ከባዱ ሴራው | ህልሜ ለሊትና የአጋንንት ፈተና 😭😱💥 https://youtu.be/BdZCYtTBPl8
ዘገምተኛና የአዕምሮ በሽተኛ ያደረኩት እኔ ነኝ! | በጸሎት ውስጥ ልካተቱ የሚገቡ ነገሮች | ከቡዳ መንፈስ ልጆቻችንን ለመጠበቅ ይሄን እናድርግ! #ebs 😱😭🚩 https://youtu.be/U4m9sKrRIQY
"ክፉ ክፉን ከቶ አያወጣም ማንም ክፉ ቢያደርግብህ መልካም ብታደርግለት መልካም ሥራህ ክፉዎቹን ያጠፋል።" (ቅዱስ ጲሜን)
"ትንሽም ቢሆን ለተቸገረው ሰው ስጡ። ምንም ለሌለው ሰው ትንሽ አይደለምና። የምንችለውን ከሰጠን ለእግዚአብሔርም ትንሽ አይደለም።" (ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ)
"ትልቁ የበጎ አድራጎት ተግባር ሌሎችን ከልብ ይቅር ማለት ነው።" (አባ ዞሲማስ)
"እግዚአብሔር በክርስቲያኖች ላይ የሚፈርደው ኃጢአት ስለሠሩ ሳይሆን ንስሐ ስላልገቡ እንጂ።" (ቅዱስ ኒፎን ዘቁስጥንጥንያ)
"ከእግዚአብሔር ጋር መዋደድ ከሁሉ የላቀ ፍቅር ነው። እርሱን መፈለግ ታላቅ ጀብድ ነው፤ እሱን ማግኘት ትልቁ የሰው ልጅ ስኬት ነው።" (ቅዱስ አውገስጢኖስ)
"ይህ ሕይወት ለንስሐ ተስጥቷችኋል በከንቱ ማሳደድ አታባክኑት።" (ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ)
"ክንፍ እምደሌላት ወፍ ክንዶች እንደሌሉት ወታደር የማይጸልይ ክርስቲያንም እንዲሁ ነው።" ስለዚህ ሁላችንም ባለንበት ሆነን በተቻለን አቅም ለጸሎት እራሳችንን ዝግጁ ማድረግ ያስፈልጋል።
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@Estifanos2239
"ክንፍ እምደሌላት ወፍ ክንዶች እንደሌሉት ወታደር የማይጸልይ ክርስቲያንም እንዲሁ ነው።" ስለዚህ ሁላችንም ባለንበት ሆነን በተቻለን አቅም ለጸሎት እራሳችንን ዝግጁ ማድረግ ያስፈልጋል።
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@Estifanos2239
ይሄንን ነበር ተጠንቀቁ ያልነው!! || የባልና ምስት የጸሎት ሰዓታት || ለጸሎት ማድረግ ያለብን ዝግጅቶች || መምህር ተስፋዬን የምትቃወሙ አዳምጡ! 🔥😱🚩💥😱 https://youtu.be/G712Ve9bnCs
"የሰይጣን ወጥመድ"
=> አባ ኔቅጣስ ስለ ኹለት ወንድሞች የሚከተለውን ተናግረዋል። አንድ ጊዜ ኹለት መነኮሳት በአንድነት ለመኖር ወሰኑ። አንደኛው በልቡ "ወንድሜ የሚፈልገውን ኹሉ አደርግለታለሁኝ" ሲል ቃል ገባ። ሌላኛውም "የወንድሜን ፈቃድ እፈጽምለታለሁ" ሲል በልቡ ወሰነ። በዚህ ውሳኔያቸው ለብዙ ዘመናት በለጋሥነት ኖሩ። በዚህ ፍቅራቸው የቀና ሰይጣን ሊለያያቸው ተነሣ። በበአታቸው በር ላይ ቆመና ለአንደኛው ርግብ ለሌላኛው ቍራ መስሎ ታያቸው። በዚህ ጊዜ አንደኛው መነኩሴ "ርግቧን አየሃት?" ሲለው ሌላኛው ደግሞ "ርግብ አይደለችም ቍራ ናት" ሲል መለሰ። "ርግብ ናት" ፣ "ቍራ ነው" ክርክር ጀመሩ። ክርክሩ ወደ ጭቅጭቅ፣ ጭቅጭቁ ወደ ድብድብ አመራና ደም በደም እስኪ ኾኑ ድረስ ተደባደቡ። በመጨረሻም ተለያዩ። ከሦስት ቀናት በኋላ ወደ ልባቸው ተመልሰው ኹለቱም ተፀፀቱ። ይቅርታም ተጠያየቁ። ኹለቱም በተለያየ መልክ አንድ ዓይነት ነገር ማየታቸውንና ልዩነታቸው የመጣው ከነገሩ ሳይኾን ከዲያብሎስ መኾኑን ተረዱ። እስከ ዕለተ ሞታቸውም ድረስ አብረው ያለ ፀብ ኖሩ። (ዳንኤል ክብረት (ዲ/ን፣ አርተር)፣ በበረሓው ጉያ ውስጥ፣ ሦስተኛ ዕትም 2004 ዓ.ም፣ ገጽ 57-58)።
=> አስተውሉ! ብዙ ጊዜ መንፈሳዊ ሕይወታችን ምስቅልቅል የሚልብን በእንዲህ ዓይነት ስውር የሰይጣን ወጥመድ ነው። አንድን ነገር በእርጋታ ከመመርመር ይልቅ ያየነውን ብቻ መሠረት አድርገን ወደ ተሳሳተ ውሳኔ የምንገባም እና የእግዚአብሔርን መግቦት የምንጠራጠር ብዙ ሰዎች አለን። ከሌሎች ጋር በፍቅር ለመኖር የወሰነውን ውሳኔ ድንገት በአንዲት ተራ ምክንያት የምናፈርስ መኾኑን እናስተውል። የገመጠንን ነገር በልቡናችን ከገባነው ቃል ኪዳን ጋር እያስተያየን በትዕግሥት ልንጸናና ረጋ ልንል ሲገባን በጥድፊና ተቃራኒ መልስ እየመለስን ወደ ጥልና ፀብ የምንገባ ልንጠነቀቅ ይገባናል። የልቡናችንን ዐይን ስሜታዊነታችንን አንጫነው፤ እኔ የማየው ብቻም ነው ትክክል ብለንም የሌሎችን ሐሳብ አንግፋ። ለሕይወታችን ሊጠቅም የሚችለውን ወዳጅ እኔ እንደ ማየው አላየም ብለን አንግፋው። በጎ አንድነት እንዳይኖር የሚሻ ጠላት ልዩነትን ኾነ ብሎ እየፈጠረብንም እንደ ኾነ ልብ እንበል። የሚሻለን ኹሌም ቢኾን ራስን ዝቅ አድርጎ ለሕይወት ከሚጠቅመን ወዳጃችን ጋር በአንድነት መኖር ነው። እግዚአብሔር ዓይነ ልቡናችንን ያብራልን።
=> በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ነገር በተለያየ መንገድ ለተለያዩ ሰዎች በማሳየት ሰይጣን ምን ያህል ፀብና ጥልን የሚፈጥር ክፉ ጠላት መኾኑን ልብ ማለት እንችላለን። ክፉው ጠላት ሰይጣን እኛን ለመጣል ያን ያህል የሚዋጋ ከኾን እኛስ እርሱን ለመግጠም ምን ያህል ሠልጥነን ይኾን? ይህን ኹላችንም ለየራሳችን እንጠይቅ። በክርስትና ሕይወት በጣም የዛልን፣ በእምነታችን ላይ ጥርጣሬ የመጣብን፣ በሃይማኖታዊ ጉዳይ ለዘብተኛ ወደ መኾን እየሄድን ያለን በሙሉ ለአንድ አፍታ ቆም ብለን እናስብ። ጠላት ምን ያህል የጥፋት ጉድጉድ እየቆፈረልን እንደ ኾነም ልብ በማለት ንቁ ተዋጋጊ እንኹን። ሊዋጋው እና ሊያጠፋው በብዙ ኃይል ታጥቆ የሚመጣን ጠላት እያየ ባዶ እጁን ቍጭ ብሎ የሚጠብቅ ተዋጋ ይኖራልን? ቢኖሩ እንኳን ለማሸነፍ ያሰበ ሳይኾን አስቀድሞ በስንፍናው ምክንያት የተሸነፈ ጠላትም ሲመጣ እጁን ሰጥቶ ባርያ ሊኾንለት ያቀደ ብቻ ነው ሊኾን የሚችለው። ወይም ሕይወቱን የጠላና ለበለጠ ሥቃይና መከራ ራሱን በፈቃዱ አሳልፎ ለመስጠት የፈቀደ ሞኝና ሰነፍ ነው ሊኾን የሚችለው። ይህ ደግሞ በራስ ላይ ራስን ጠላት እንደ ማድረግ ነው። ስለዚህ በጥንቃቄ እንኑር።
=> ሰይጣን በተለያየ መልክ እየተገለጠ ወደ ልዩነትና ፀብ የሚወስድ መኾኑን ልብ ከማለት ጋር እኔ የማየው ብቻ ነው ትክክል ከማለት በፊት ጸሎት ማድረግ ወደ እግዚአብሔር መጮህ ያስፈልጋል። ብዙ ጊዜ ልዩነት እየመሰሉን የምንጣላባቸው ነገሮች ልክ እንዲሁ ናቸው። ወደ ልዩነት፣ ፀብና ክርክር፣ አለፍ ሲልም ወደ ጭቅጭቅ እና ድብድብ ድረስ የሚያደርሰን ለነገሮች ያለን የተቃረነ አረዳድ ነው። ኹላችንም ማንኛውንም ነገር በጸሎትና እግዚአብሔርን በመጠየቅ ብናደርገው እጅጉን ጠቃሚ ነው። ተቃራኒ የሚመስለን ወደ ፀብ ሊያመራን የሚችል ነገር ኹሉ የጠላታችን የዲያብሎስ ወጥመድ መኾኑን ኹሌም ልብ እንበል። የእኔ ብቻ ትክክል ነው፣ ያንተ ትክክል አይደለም እያሉ የሌሎችን ሐሳብም ኾነ ንግግር ለማድመጥ ፈቃደኛ አለመኾን ወደ ጭቅጭቅና ከዚያም አልፎ ደም እስከ ማፋሰስ ድብድብ የሚያደርስ መኾኑን ልብ ይሏል። እንዲህ ዓይነት የልዩነትና የፀብ ፈተና በገዳም እንኳን የማይቀር መኾኑን ኹል ልብ እንበል። ስለዚህ አንዱ እሳት ሲኾን ሌላው ውኃ፣ አንዱ ቍጡ ሲኾን ሌላው በራድ፣ አንዱ ቸኳይ ሲኾን ሌላኛው ረጋ ያለ ትዕግሥተኛ መኾን አለበት። ዕለት ቀንና ሌሊት እንደሚኖረው ሕይወትም ብርሃንና ጨለማ ይኖረዋል። ጨለማ ብቻ ቢኾን ወይም ብርሃን ብቻ ቢኾን አኹን ባለን አኗኗር ጥሩ አይኾንም ነበር። እንቅልፍም ንቃትም ያስፈልጋሉና። አንዱ ሲተኛ አንዱ ካላነቃ፣ አንዱ ሲስት ሌላኛው ካላቀና እንዴትስ ሕይወት ሥምረት ሊኖራት ይችላል?
=> ኹለቱ መነኮሳት ለጊዜው ባይረዱትም ዃላ ወደየልቡናቸው ሲመለሱ ያጣላቸው ሰይጣን እንደ ኾነ ተረድተው፡ ይቅር ተባብለው፡ አንዴ አለያይቷቸው ደም ያፋሰሳቸውን ጠላት እስከ ሞታቸው ድረስ ተዋግተው ድል አድርገውት እነርሱ በፍቅር በአንድነት ምድራዊ ሕይወታቸውን አጠናቀዋል። እንግዲያውስ እኛም እንደነርሱ ወደየ ልቡናችን ተመልሰን የተጣላን ይቅር ብንባባልና ወደ ልዩነት እና ፀብ የመራን ሰይጣን መኾኑን ተረድተን በፍቅርና ክርስቲያናዊ በኾነ አንድነት ብንኖር አሸናፊ መኾናችን በዚያ ይታወቃል። እግዚአብሔር ለኹላችንም ንጹሕ ልቡና አድሎ በፍቅር በአንድነት የምንኖርበትን ኃይል ይስጠን፤ አሸነፍኩ ተሸነፍኩ ከሚያስብል ክፉ እልህና ግራ መጋባት ይሰውረን፤ በእርሱ ቃል ልቡናችን ተሸንፎ ራሳችንን ከኹሉ የምናንስ አድርገን ለመቍጠርም ያብቃን አሜን።
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@Estifanos2239
ጥያቄ 5: የአብርሃም ስም አብራም፤ የሣራ ስም ሦራ፤ የቅዱስ ጳውሎስ ስም ሳውል ተብሎ እንደሚታወቀው ሁሉ የቅዱስ ጴጥሮስ ስም ማን በመባል ይታወቅ ነበር?
ጥያቄ 4: “እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል።” በማለት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረው ሐዋሪያ ማነው?
ጥያቄ 3: ለአብርሃም ትዕግስትን፣ ለኢዮብ ጽናትን፣ ለሰሎሞን ጥበብን፤ ለኤርሚያስ ___________??
ጥያቄ 2: የእስራኤላውያንን ከግብፅ የመውጣት የመጀመርያ ታሪክ የሚዘገበው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የትኛው ነው?
ጥያቄ 1: ጌታችን አምላካችን ዓርብ በዘጠኝ ሰዓት ነፍሱ ከሥጋው በተለየች ጊዜ በሰማይና በምድር የታዩት 7 ተአምራት የትኞቹ ነበሩ? ወይም የትኛው ነው?
ሰይጣን የሚያቀርብልን የንስሐ ፈተና | የሰው ልጅ እንዴት ሞትን መረጠ? ጬንገር የደም መንፈስ ትውልድ ገዳይ | የመምህር ተስፋዬ የጥላወጊ መንፈስ ፈተና 😭😱🔥
https://youtu.be/Xhx9qBvYrtA
