💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
Ir al canal en Telegram
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው። 👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው። 💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Mostrar más8 855
Suscriptores
+224 horas
+357 días
-330 días
Archivo de publicaciones
Repost from SadatKemal Abu Meryem
💐በነዚህ ውድ አስረቱ ቀናቶች የሚወዱዱ ስራዎች❗
🕋🕋🕋🕋🕋⚠️🕋🕋🕋🕋🕋🕋🕋
ረሱል صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል፦
﴿ما أَهَلَّ مُهِلٌّ قطُّ إلّا بُشِّرَ، ولا كَبَّرَ مُكَبِّرٌ قطُّ إلّا بُشِّرَ، قيل: بالجنةِ؟ قال: نَعَمْ﴾
ድምፁን ከፈ አድረጎ ላኢላሀ ኢለላህ የሚል አንድም አይኖርም ብስራት የሚበስረ ቢሆን እንጂ። እንዲሁም አላሁ አክበረ የሚል የለም አንድም አይኖርም ብስራት የሚበሰረ ቢሆን እንጂ። እንዲህ ተባሉ፦ ብስራቱ ጀነት ነውን? አዎን! አሉ።”
📚 ሲልሲለቱ አሶሂሃ፡ 1621
الله اكبر الله اكبر لا اله الا الله 🔺لا إله إلا الله🔺
🎀ሚስት ሆይ.... !
የማትረሳ የማትቀየር እና የማትሰለች መርጊያ ሁኚ !ካንቺ የሚጠበቀው ሙሉነት አይደለም ሙሉነት ለአላህ ብቻ ነውና !
ግን የሚረዳ ልብ፣ ድካምን አብሶ የሚያራግፍ ደጋፊ ክንድ፣ ዱንያ ምንም ያክል ብትከፋ በእጅሽ ግን ታላቅ ሰላምን የያዝሽ እና የምትሰጪ ሁኚ ።
የቤቱ ግድግዳ እና እቃ ሳይሆን መርጊያ፣ መስከኛ እና መኖሪያ ሁኚ !
بارك الله لكما وبارك عليكما وجمع بينكما فى الخير
አልሃምዱሊላህ እንኳን ደስ አለሸ የፈይሰል ማሚ የፍቅር የደስታ ያማረ የሰመረ ትዳር ያድርግላችሁ 🎉🎀💎🌹
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የማር ምርቱ እንዲጨምር አስበው የሱፊያ ሸይኽ አመጡ። ንቡ ግን "ወሃቢ" ሆነባቸው። እየነደፈ አባረራቸው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
💧ይህን ድንቅ የተከበረ ቦታ ማን አለ ያልናፈቀዉ አ?!
አላህ የልባችሁን ፍላጓት ካሰባችሁት በላይ አሟልቶ ያዘይራችሁ ።
እኛም ደጋግመን ......ከዉድ መህረሞቻችን ጋ የምንዘይረዉ ያድርገን ።
لَسـتُ نِعـمَ العَبْـد ؛ لَكنِّي أَرجُوا أنْ أَكُـونَ أوَّابٌ ۦٰ
اللَّهُمّ أصَلَحَني 🌱
🎀ከሰዎች ጥበበኛዉ !
▪ዱኒያን የተወ እሱን ከመተዋ በፊት ፤
▪ቀብሩን ያበራ በሱ ዉስጥ ከመኖሩ በፊት ▪ጌታዉን ከመገናኘቱ በፊት ጌታዉን ያስደሰተ፤
▪ሰላተል ጀመኣን የሰገደ በሱ ላይ ከመሠገዱ በፊት እራሱን የተሳሰበ ሂሳብ ከመደረጉ በፊት።
📘ኢሚሙ ሻፍኢ አላህ ይዘንላቸዉና!
Repost from 📱[ انتبه أنت مراقب ] 📲
ዛሬ መፈጠርህን እንኳ ለማያውቅ አንድ የእግር ኳስ ክለብ አሸነፈ ብለህ ያፈሰስከውን እንባ፤ ወንጀልህን አስታውሰህ አላህ ፊት ብታነባዉ ኖሮ፣ ምናልባት ከእሳት አድኖ ወደ ጀነት መግቢያ ሰበብ ሊሆን ይችል ነበር።
©
حدد شخصيتك
የአንተን ነፍስ አይነት ለይ
ኢብኑል ቀይይም (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦
“ነፍሳት (የሰዎች ስብዕናዎች) ሶስት ናቸው፦
1:- ሰማያዊና የላቀች ነፍስ (النفس الملكية العلوية)፦
ፍቅሯና ዝንባሌዋ ወደ እውቀት፣ ወደ በጎ ምግባር እና ለሰው ልጅ ወደሚቻለው የላቀ ፍጹምነት መድረስ ነው። መጥፎ ጠባዮችንም ትርቃለች። ወደ አላህ የሚያቀርባትን ነገር በጣም ትወዳለች፤ ይህም ኃይሏ፣ ምግቧና መድኃኒቷ ነው። ከዚህ ውጭ በሆነ ነገር መጠመድ ግን ለእሷ በሽታዋ ነው።
2:- አውሬያዊና ቁጣ የተሞላች ነፍስ (النفس السبعية الغضبية)፦
ፍቅሯ ወደ ግፍ፣ ወደ በደል፣ በምድር ላይ ራስን ከፍ ከፍ ለማድረግ (ለትዕቢት) እና በሰዎች ላይ በኃይልና በበላይነት ለመግዛት ይመራል። ደስታዋና ምኞቷ ያለው በዚህ ውስጥ ነው።
3:- እንስሳዊና ስሜታዊ ነፍስ (النفس الحيوانية الشهوانية)፦
ፍቅሯ ወደ መብላት፣ ወደ መጠጣትና ወደ ስጋዊ (ወሲባዊ) ፍላጎት ይመራል። አንዳንዴም ይህች ነፍስ ከቁጣዊቷ ነፍስ ጋር በመጣመር ሁለቱን ባህሪያት በአንድ ላይ ታሰባስባለች፤ በምድር ላይ ራሷን ከፍ ለማድረግና ለማጥፋት ትጥራለች። አላህም ስለ ፊርዓውን እንዲህ ብሏል፦
﴿إِنَّ فِرْعَوْنَ عَلَا فِي الْأَرْضِ وَجَعَلَ أَهْلَهَا شِيَعًا يَسْتَضْعِفُ طَائِفَةً مِّنْهُمْ يُذَبِّحُ أَبْنَاءَهُمْ وَيَسْتَحْيِي نِسَاءَهُمْ ۚ إِنَّهُ كَانَ مِنَ الْمُفْسِدِينَ﴾
«ፊርዓውን በምድር ላይ ኮራ (ራሱን ከፍ አደረገ)፤ ሕዝቦቿንም የተከፋፈሉ ቡድኖች አደረጋቸው፤ ከእነርሱም አንዱን ወገን ያዋርድ ነበር፤ ወንድ ልጆቻቸውን ያርድ ነበር፣ ሴቶቻቸውንም በሕይወት ይተው ነበር፤ እርሱ በእርግጥ ከአጥፊዎች ነበር።»
(አል-ቀሰስ፡ 4)
📌በዚህ ዓለም ያለው ፍቅር ሁሉ በእነዚህ ሶስት ነፍሳት ባህሪ ዙሪያ ይሽከረከራል። ከእነርሱም ማንኛዋም ነፍስ ከተፈጥሮዋ ጋር የሚስማማውን ነገር ባገኘች ጊዜ ትወደዋለች፣ ወደ እርሱም ትዘነብላለች፤ ተግሣጽንም አትሰማም፣ በእርሱ ላይም የሚወቅሳትን ወቃሽ ግድ አትለውም።”
=
አቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ
https://telegram.me/abutoiba
https://telegram.me/abutoiba
ከአምስት ነገሮችን የተጠበቀ የዱንያም የአኺራንም ሸር ተጠብቋል :
1.በራስ መደነቅ
2.እዩልኝ
3.ኩራት ،
4.ሌላውን አሳንሶ ማየት
5.ስሜት
«ሰውነቱን ለዓይን ግብር ያላቀረበ፣ ነፍሱን ግን ለፈጣሪው የገበረ» ማንነት ምንኛ የታደለ ነው! በዘመናዊነት ስም «መገለጥ» የሥልጣኔ መለኪያ በሆነበት በዚህ ዘመን፣ እነርሱ ተንጠፍጥፎ የቀረውን የሐያእ ካባ እንደ ብርቅዬ ቅርስ ጠባቂዎች ሆነው ቆመዋል። ያ ካባ ጨርቅ ብቻ አይደለም፤ የክብር ምሽግ እንጂ። ያ ኒቃብ መጋረጃ አይደለም፤ የነጻነት አዋጅ እንጂ።
منقول
...
«اللهُ أكْبَرُ اللهُ أكْبَرُ ، لَا إلَهَ إلَّا اللهُ ، اللهُ أكْبَرُ اللهُ أكْبَرُ ، وَلِلهِ الحَمْدُ».
.
የዙል ሂጃ አስር ቀናቶች እዉነተኛ የአላህ ባሪያዎች የሚለዩበት ቀናቶች ናቸዉ።
በነዚህ 10 ቀናቶች የሚሰራ ኢባዳ
የታወቀው የጅሀድ አይነት ብቻሲቀር ከጅሀድ ይበልጣል።"እናም እንበርታ!
እራስሽን ለማስተካከል ሁሌ የምትጥሪ እና የምትታገይ ከሆነ ሳሊህ መሆንሽን እርግጠኛ ሁኚ…
ይህ አይነቱ ትግል ከተበላሹ ልቦች አይፀናምና!
ኢብራሂማዊ ሰው ለመቅረጽ ከሚረዱት ዋና መንገዶች አንዱ የአሏህን ኒዕማዎች ማመስገን ነው። ሁልጊዜም ኒዕማን በሚደነቅ አይን እንጂ በተለምዶ አለማየት ነው… ከዚህ ኒዕማዎች መገለጫ አንዱ፡-
አሏህ ከእርሱ ጋር የመታረቅን ዘመን እንድትገኝ ሕይወትህን ማስቀጠሉ ታላቅ እድል ነው። ልክ እሱ (ልዕልና ይግባው) እንዲህ እንደሚልህ ነው፡- "አሁንም እፈልግሃለሁ፣ አሁንም የመመለሻ በሮችን እከፍትልሃለሁ፤ ታዲያ አትቀርብምን?!"
شاكرا لأنعمه🌿
🔖ከአቢ ሁረይራ አላህ መልካም ስራዉን ይዉደድለትና ተይዞ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል አሉ። አላህ አሸናፊና የላቀዉ የሆነዉ ጌታ ብሏል፦
~የአደም ልጅ ያስቸግረኛል' ዘመንን (ጊዜን)ይሳደባል እኔ ጊዜ ነኝ ሌሊትንና ቀንን አገላብጣለሁ አተካካለሁ።
👉 አላህ ሱብሀነሁ ተአላ የተናገረበት የአላህ መልእክተኛ አላህ እንዲህ ብሏል ብለዉ የሚያስተላልፉበት ሀዲሰል ቁርሲይ (ሀዲሰ ኢላሂ)ተብሎ ይጠራል።
🔖ከአላህ ጋ የተያያዘ አደብ ሊኖረን ይገባል።
ዘመንን የሚሳደብ ሠዉ ምንን ነዉ የሚፈልግበት ፦ዘመኑ (ጊዜዉ)ያደርጋል ከሆነ ቀጥታ ጊዜዉ ፈፃሚ አድርገዉ እሚገልፁ አነጋገሮች እሚናገሩ ከሆነ ከእስልምና የሚያስወጣ ትልቁ ሽርክ ይሆናል።ጊዜዉ በራሱ አድራጊነዉ ፈፃሚ ነዉ ብለዉ ካሰቡ ማለት ነዉ።
👉 በጊዜ ዉስጥ ክስተቶች የሚፈፀሙ በመሆኑ በዛ ሰበብ ቢሳደቡስ ይህ ነገር የተከለከለ ሀራም ነዉ። ስለዚህ ጊዜ ነገሮች የሚፈፀሙበት ክስተት ነዉ አላህ ሱብሀነሁ ተአላ በዚህ መልኩ ፈጥሮታል።ኸይሩም ሸሩም ይፈፀማል። ከዛ ባለፈ ራሱ አድራጊ ፈፃሚ ፤ፈጣሪአደለም።
👉የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል።
ይህ የከፋ ዘመን የክፋት ዘመን አትበሉ። ምክንየቱም አላህ ራሱ ዘመኑ ነዉና ብለዋል።
🔍አይ ክስተቱ ስለተከሰቱበት ያንን ምክንያት በማድረግ ነዉ እንጅ ዘመኑ ያደርጋል ብየ አደለም የምሰድበዉ ቢል አንድ ሰዉ ሀራም የተከለከለ ነገር ነዉ እየፈፀመ ያለዉ ማለት ነዉ።
📍በሌላ ነገር ደግሞ የተከሰቱ ክስተቶችን ለመግለፅ ብንጠቅስ ለምሳሌ ፦ከባድ ጊዜ ነዉ፤ነገሮች በጣም ፈታኝ የሆኑበት ጊዜ ነዉ፤የመሳሰሉት ቢገለፅ የተፈለገዉ በዛ ዉስጥ የተከሰተዉ ክስተቶች እንጅ ዘመንን መሳደብ መዉቀስ ስላልሆነ ችግር የለዉም።
👉አላህ የሉጥ ህዝቦችን አዉስቶ ፦
هَٰذَا يَوْمٌ عَصِيبٌ
ይህ ከባድ ቀን ፈታኝ ቀን ነዉ ብሏልና።
